Tuesday, February 2, 2016

በኮንሶ እስሩና ማንገላታቱ ቀጥሎአል

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኮንሶ ህዝብ የተመረጡ 12 ሽማግሌዎችና የደቡብ ክልል ባለስልጣናት ትናንት በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ስቃይ እንዲቆም ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣ ስምምነቱ አንድ ቀን ሳይደፍን የፌደራል ፖሊሶች በድጋሜ አካባቢውን ተቆጣጥረው ሰዎችን እየያዙ በማሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ስምምነቱ ህዝቡ ባቀረበው ጥያቄ ምክንያት ሰዎች እንዳይታሰሩ፣ ከስራ እንዳይፈናቀሉ፣ የታሰሩት እንዲፈቱ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ በዛረው እለት በወረዳው የሚታየው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። በካራት መውጫና መግቢያ ከፍተኛ ፍተሻ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ ወደ ፋሻ መንገድ መሄጃ መጨቀ መገንጠያ ላይ ተጓዞች ከመኪና እየወረዱ መታዋቂያ እየተጠየቁ ፣ ስም ዝርዝራቸው ፖሊሶች ከያዙት የሚታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ጋር እየተመሳከረ እንዲሄዱ ወይም እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ከ250 በላይ ሰዎች እየተፈለጉ ሲሆን፣ 8ቱ በኦነግነት 7 ቱ ደግሞ በግንቦት7 አባልነት ተፈርጀዋል። በካራት ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ 6 ሰዎች ደግሞ ወደ ግዶሌ እስር ቤት እንዲተላለፉ ተደርጓል።በእስር ላይ በሚገኙት ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
የኮንሶ ህዝብ አሁን ከሚገኝበት ሰገል ዞን ወጥቶ የራሱ ዞን እንዲሰጠው በመጠየቅ ላይ ነው።

No comments:

Post a Comment