Monday, February 1, 2016

ከሶማሊያ ባሕር የተረፉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነው

ባለፈው ወር መነሻቸውን ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻዎች አድርገው በጀልባ በባሕር ወደ የመን ሊያቀኑ ሲሞክሩ አብዛሃኞቹ ስደተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
የተወሰኑት ከአደጋ ተራፊዎች ውስጥ በሶማሊ ላንድ ራስገዝ ሃርጌሳ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ድጋፍ አማካኝነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ሊደረግ ነው።
ባለፈው ዓመት ውስጥ ብቻ እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ከ90 ሽህ በላይ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በባሕር በጦርነት ወደምትታመሰው የመን ማቅናታቸውን አይኦኤም ገልጾ ከስደተኞቹ ውስጥ ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አስታውቋል።
...
ባለፈው ወር በጀልባ መገልበጥ አደጋ 34 ኢትዩጵያዊያን መሞታቸውንና በአጠቃላይ ከ96 በላይ ስደተኞች በባሕር አደጋ መሞታቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
አይኦኤም በጎ ፈቃደኛ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያንን ማጓጓዣ እርዳታ ከአሜሪካ የስደተኞች ቢሮ ማግኘቱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አገራቸውን በመተው ሕይወታቸውን ለ አደጋ አጋልጠው መፍለሳቸውን ቀጥለዋል። በስደት አገራት ለሚደርስባቸው ሰቆቃዎች የኢትዮጵያ ኤንባሲና ዲፕሎማት መስሪያቤቶች ለዜጎቻቸው ከለላ በመስጠት ወደ አገራቸው መብታቸው ተጠብቆ ይመለሱ ዘንድ ሲሰሩ አይታይም።

No comments:

Post a Comment