Monday, August 31, 2015

በቡሌሆራ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎቸ ተጎዱ

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነሃሴ 19 ቀን በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ ከተማ፣ በ1949 የተገነባውን የገበያ ማእከል በማፍረስ የመኪና መናሃሪያ ለማድረግ፣ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት ህዝቡ ያሰማውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ከ150 በላይ ሰዎች በድብደባ ሲቆስሉ፣ ወገኖ ወንዳቸው የተባለ ወጣት በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ገብቶ እየታከመ ነው።

የከተማው ባለስልጣናት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ሳይስማሙና ለነጋዴዎቹ አስፈላጊውን ካሳ ሳይከፍሉ የማፍረሻ መኪኖችን በመያዝ ማፍረስ መጀመራቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ ድርጊቱን እንዳየ በባለስልጣኖቹ ላይ ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞውን ገልጿል።
ፖሊሶች ተኩስ በመክፈት ህዝቡን ለመበተን ሙከራ ቢያደርጉም፣ ግጭቱ ለሰአታት ቆይቷል። በፖሊስ ዱላና ጥይት የቆሰሉት በአንቡላንስ እየተጫኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
ይህንን ተከትሎ ፖሊሶች እስከ ሌሊት ድረስ ወደ መኖሪያ ቤቶች እየገቡ ነፍሰጡሮችን ሳይቀር ደብድበዋል። በእለቱ 26 ሰዎች ሲታሰሩ፣ 13 ተለቀው፣ 13 ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
አቶ ታደለ ቢቂላ የተባሉ አባት ልጃቸው ታደለ ቢቂላ ክፉኛ መደብደቡን ተከትሎ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ፣ ልጄን ፖሊስ ደብድቦብኝ ነው ብለው በመናገራቸው የተባሱጩት ፖሊሶች እርሳቸውንም ከ13ቱ ተከሳሾች መካከል በመቀላቀል ፍርድ ቤት አቅርበዋቸዋል።
የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው በቀለ፣ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ አውግዘዋል። ለተጎዱት ቤተሰቦች አስቸኳይ ካሳ እንዲከፈላቸው አቶ ጌታቸው ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከምርጫው በሁዋላ ከ2 ሺ ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆች መታሰራቸውን የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ሊግ ገልጿል።
ሊጉ ባወጣው መግለጫ በቡሌ ሆራ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ምእራብና ሰሜን ሸዋ ዞን አፈሳው ተጧጡፏል።
በዋራ ጃርሶ ወረዳ ከ400 በላይ አርሶአደሮች አመጽያንን አስጠግታችሁዋል በሚል መታሰራቸውን አስታውቓል። ከታሰሩት መካካል የ20 ሰዎችን ስም ይፋ አድርጓል።

የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል ተገደለ

በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያገኘነው መረጃ አመለከተ ሲል የትህዴን ድምጽ ዘግቧል:: በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል የተባለው ለሆዱ ያደረ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬ ነሃሴ 12 /2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቤቱ ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ የትህዴን ድምጽ ዘገበ::

ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ነዋሪው ህዝብ ሊተባበራቸው ባለመቻሉ ምክንያት በግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ተሳስሮ ሰዎች ሊጠረጥሩት ሞክረው ህዝቡ ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ምክንያት ገዳዩ ሳይታወቅ ዝምታን እንደመረጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
በተመሳሳይ- በሳዕስዕ ፃዕዳ እምባ ሳዕስዕ ቀበሌ የሚኖር ህዝብ ደስታ ጎቢጥ የተባለ የቀድሞ ታጋይ ባልታወቁ ሰዎች ነሃሴ 13 2007ዓ/ም በድንጋይና በዱላ እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ተገድለዋል እየተባሉ ያሉት ሰዎች ከአካባቢው ካድሬዎች ጋር ስምምነት ያልነበራቸውና ጥቅም ያጣላቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚል ጥርጣሬ በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አክሎ ገልጿል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙት

1eac1-pg7-logo

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
‪#‎ስምንት‬ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መሬት ላይ ኩላሊታቸውን ለመዝረፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገለፀ፡፡
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ሙሉ እምነት ያላሳደረባቸውን የራሱን ሹሞች በደህንነቶቹ እያሳፈነ ወዳልታወቀ ቦታ እያጋዛቸው ነው፡፡
‪#‎ሱዳን‬ ከኢትዮጵያ ግዛት ተጫሪ መሬቶችን ለመውሰድ ለህወሓት አገዛዝ ጥያቄ ማቅረቧን ሄራልድ ትርቢውን የተባለ የሱዳን ጋዜጣ ዘገበ፡፡

በርካታ የትግራይ ህዝብ ለርሃብ ተጋርጦ ባለበት ሰአት ህወሃት 2 ሺ እንግዶችን በውስኪና በቁርጥ ስጋ አንበሸበሸ

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ባለፈው ቅዳሜ ህወሃት ለኢህአዴግ ጉባኤተኞች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ፣ ከ2 ሺ ያላነሰ ሰው ተገኝቷል። ለእንግዶቹ የተለያዩ ምግቦች፣ ቁርጥ ስጋ እና ውስኪ እንደ ልብ ቀርቦላቸዋል። ግብዣው የተደረገው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የሚላስና የሚቀመስ እንደሌለው ሪፖርት በተደረገበት ወቅት ነው። በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱን ሪፖርቶች ያስረዳሉ። ኢህአዴግ ለተለያዩ በአላት ግብዣዎች በእየአመቱ በቢሊዮን የሚጠጋ ብር ያወጣል። በሌላ በኩል ኢህአዴግ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን በድጋሜ ሊቀመንበር፣ አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ ም/ል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። በሌላ በኩል አቶ ሃይለማርያም በሰቆጣ የአሸንዳን በአል ለማክበር የሚገኙ ሲሆን፣ በአሉ ካለፈ ቀናት ቢቆጠሩም፣ ሴቶች ለበአሉ ሲባል ሹሩባቸውን እንዳይፈቱ ታዘዋል። በአሉ የሚከበረው በከተማው ውስጥ በድርቁ ምክንያት ውሃ በጠፋበት እና በርካታ ህዝብ " በጭንቀት ተውጦ በሚገኝበት ወቅት ነው። የአቶ ሃይለምርያም ጉብኝት በአካባቢው ድርቅ አለመግባቱን ለማሳየት ተብሎ የተዘጋጀ ነው። ይሁን እንጅ ኢሳት በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ችጋር መከሰቱን ከነዋሪዎች አንደበት ለማረጋገጥ ችሏል። ይህንን በተመለከተ ያጣነቀረውን ዘገባ ነገ ያቀርበዋል።

Sunday, August 30, 2015

ከወደ ጎንደር! አስደንጋጭ ተሰምታል


ጎንደር መተማ መስመር 11 የሰሊጥ ከባድ መኪና ሹፌሮች በወያኔ ደህንነት ደላሎች አማካኝነት ሱዳን ዉስጥ የተሻለ ክፍያ ያለዉ ስራ እናገናኛችሁ በማለት ከወሰዱ በሁዋላ 11ዱም በሱዳን ወታደሮች አራጅነት በወያኔ ደህንነት ደላሎች አሳራጅነት ካረዷቸዉ በሁዋላ በእሳት አቃጥለዋቸዋል::
የተገደሉበት ምክንያት ለጊዜዉ ባይታወቅም ወያኔ የነፃነት ታጋዮችን በየቀኑ በየትም የሚቀላቀሉ ወጣቶችን ለመቆጣጠርና በማስፈራራት ”መንገዱ ሰላም አደለም:: ወደሱዳን መስመር አትሂዱ…”
የሚልና ከተቻለም ጉዳዩን ከነፃነት ሀይሎች በተለይም ከአርበኞች ግንቦት ሰባት እና ደምሂት ጋር በማያያዝ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙበትን ስም ለማጠልሸትና ተጠያቂ ሊያደርግ እንዳሰበ ዉስጥ አዋቂወች ጠቁመዋል::

አቶ በረከት ስምኦን በማሌዢያ ፒናንግ ደሴት የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ ቤት እያስገነቡ ነው:: –

Minilik Salsawi – የለውጥ ሃይሉ እርስ በእርሱ በፖለቲካ ጥላቻ ሲጠዛጠዝ በሃገር እና ሕዝብ ላይ ዘረፋው ቀጥሏል:-ከጸረ – ሙስና ኮሚሽን ከመዝገብ ቁጥር /203/2007 ከተገኘው መረጃ መሰረት አቶ በረከት ስምኦን በማሌዥያ ፒናንግ ደሴት ጃላን ባሩው 62 በተባለ ቦታ ላይ በሚሊዮኖች ዶላር በወጣ ወጪ ኢትዮጵያ ውስጥ በብረታብረት ስራዎች ላይ ከሚገንኝ አንድ ማሌዢያዊ ጋር በመቀናጀት እጅግ ዘመናዊ የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ በኢንቨስትመት ስም እያስገነቡ መሆኑን ጥቆማ ለኮሚሽኑ ደርሶ በመመዝገብ እያጣራ መሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::ከሼህ መሃመድ አላሙዲ የሃገሪቱን ሃብት እያሳለፉ እየሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚረከቡት ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምኦን በግልጽ ከሚታወቀው ከአገር ቤቱ በካፒቴኑ ስም ካስመዘገቡት ሆቴል እና ማደያዎች እንዲሁም የሪያል ስቴቶች በተጨማሪ በዱባይ እና አቡዳቢ መኖሪያቤቶች እና አክሲዮኖች ሲኖሯቸው እንዲሁም በሚላን ጣሊያን መኖሪያ ቤት በሕንድ የሚስማር ፋብሪካ ባለድርሻ ናቸው የሚል ከዚህ ቀደም በጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበ ፋይል አላቸው::

ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር – አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር (ኤፍሬም ማዴቦ)


በኤፍሬም ማዴቦ
ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters

Saturday, August 29, 2015

የኦሮሞ ህዝብ እና ኢትዮጵያ (በፍቃዱ ኃይሉ)

ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡትን ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ለአንባቢያን እንዲደርስለት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡ ኦሮምኛውን ቀደም ብለን የለቀቅን ሲሆን አማርኛውን ደግሞ እንሆ!

Guddaa saalpaa fariddi guniddaan dhessa
በፍቃዱ ኃይሉ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)
በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት ተሰብስበው ወሰኑ፡፡ ኃያላኑ መንግስታት የየድርሻቸውን ሲወስዱ የኢትዮጵያን አካባቢዎች ለመውረር የሞከረው የጣሊያን መንግስት ነበር፡፡ አውሮፓውያን ወራሪዎች ‹‹ዓላማችን አፍሪካውያንን ከእንቅልፋቸው ቀስቅሶ ማሰልጠን ነው›› ቢሉም እየዋሹ ነበር፡፡ ዋነኛ ዓላማቸው የአፍሪካን ሀብት ለፋብሪካዎቻቸው ጥሬ ዕቃ ማድረግ ነበር፡፡ ሆኖም እግረ መንገዳቸውን አፍሪካውያንን ሀይማኖታቸውን እያስለወጡ ከራሳቸው ጋር ያመሳስሉታል፡፡ ቋንቋ፣ ወግ እና ልማዶችን በማጥናት ዘመናዊ በሚሉት በራሳቸው ቋንቋ፣ ወግ እና ልማድ ይተኩታል፡፡ አፍሪካውያንን ማሰልጠን የሚሉት ይህንን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከቅኝ ግዛት በኋላ ብዙ አፍሪካውያን የራሳቸውን ቋንቋ፣ ባህል እና ስርዓት ሙሉ ለሙሉ አጥተው በአውሮፓውያን ገዥዎቻቸው ባህል እና ስርዓት እየተዳደሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን በአንጻሩ ይህንን ወረራ በኅብረት መመከት በመቻሏ ምንም እንኳን ከአውሮፓ ተጽዕኖ ባትተርፍም የተለየ (የራሷን) ባህል እና ወጎችን እንደያዘች አለች፡፡

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


የቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገው በደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮች፣ በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። አቶ ጌታቸው ተፈሪ የወ/ስላሴ መታሰር ቅር ሳያሰኛቸው እንዳልቀረና በተጨማሪም የነአዜብ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።

በህወሃት ጉባኤ የአባይ ወልዱና የደብረጺዮን ቡድን አሸናፊ ሆኖ ወጣ

ነባር አመራሮቹ በመመረጥና በመምረጥ መብት በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ የፈቀደው ህወሃት፣ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ በስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩ አብዛኞቹን መሪዎችን በድጋሜ መርጧል። አቶ አባይ ወልዱ የድርጅቱም የግንባሩም ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፣ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ደግሞ ምክትል ሆነው ተመርጠዋል። ቀድም ብሎ ህወሃትን ሊለቁ ነው በሚል ሲወራባቸው የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በስራ አስፈጻሚነት ተመርጠዋል። ዶ/ር አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስዩም መስፍንና አቶ ስብሃት ነጋ በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሳይመረጡ ቀርተዋል። አቶ አባይ ወልዱ በክልሉ የሚኖሩ ታማኝ ደጋፊዎቻቸውን በጉባኤ እንዲሳተፉ በማድረግ፣ እርሳቸው እና በእርሳቸው ዙሪያ ያሉት እንዲመረጡ አድርገዋል በሚል እርሳቸው እንዳይመረጡ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የህወሃት አባላት እየተናገሩ ነው። ምንም እንኳ አቶ አርከበ በጉባኤው ሲሰጡት ከነበረው አስተያየት በመነሳት እና ቀድም ብሎ በመተካካት ስም ከለቀቁት ጉባኤ እንደገና እንዲመለሱ ከመደረጉ አንጻር ፣ ወደ ህወሃት ከፍተኛ የአመራር ቦታ ሊመጡ ይችላሉ የሚል አስተያየት ሲቀርብ ቢቆይም፣ አቶ አርከበ ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሳይጠቆሙ ቀርተዋል። በዚህ ጉባኤ የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ሆኖ ተመርጧል። በሌላ በኩል የህወሃት አመራሮች በአባሎችና ደጋፊዎቹ ቁጣና ተግሳጽ ደርሶባቸዋል። በስብሰባው ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በሙስናና ብልሹ አሰራር መዘፈቃቸውን ፣ህዝብ የሞተለትን አላማ በመርሳት ከደርግ ባልተናነሰ አምባገነነን መሆን ደረጃ መደረሱን ተራ አባላት በግልጽ ተናግረዋል። የመቀሌው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የጉባኤው ተሳታፊዎች እንዳረጋገጡት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች የታገሉለትን አላማ በመርሳት በህዝብ ላይ እየፈነጬ መሆናቸውን ፣እነዚህ ሰዎች ከአድራጎታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋቸዋል። አብዛኛውን ማስጠንቀቂያ ሰጡት ደግሞ የህወሃት የገበሬ አባሎች ናቸው። ይህ የህወሃት ገበሬዎች ቁጣ በመቀሌ ከተማ ከተሰማ በሃላ ነዋሪዎች ድጋፋቸውን በግልጽ ማንጸባረቃቸው የህወሃት ሙሰኛ አመራሮችን ጀምበር እያዘቀዘቀ መሆኑ ምልክት ተደርጎ ተወስዶአል። በተለይ በዚህ መሰል ጉባኤ ላይ ጠንካራና መራር ተቃውሞ በህወሃት አባላትና ካድሬዎች ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያ መሆኑን ያስረዱት ተሳታፊዎች ፣ ይህ ጅምር ራሱን ከህግ በላይ አድርጎ ለሚንቀሳቀሰው ቡድን ጥሩ ምልክት አይደለም በማለት መናገራቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል። ነገ የሚጀመረውን የኢህአዴግ ጉባኤ ተከትሎ መቀሌ በከፍተኛ ጥበቃ ስር ወድቃለች። የጸጥታውን ስራ የክልሉን ፖሊስ በመተካት የታጠቁ የፈዴራል ፖሊሶች በፖትሮል የታገዘ ጥበቃ እያከናወኑ ነው።

Friday, August 28, 2015

ኤርትራ ሄደው ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ነበር ተብለው በተከሰሱት ላይ ምስክርነት ተሰማ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ፡፡
ዛሬ ነሀሴ 22/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ‹‹አቃቤ ህግ በጻፈውና ለተከሳሽ በደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ አቃቤ ህግ የሰው ማስረጃ (ምስክር) አልጠቀሰም፤ እኛም መቃወሚያ ስናስገባም ሆነ እምነት ክህደት ቃል ስንሰጥ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡ ‹‹ባህር ዳር ላይ ለምን ለመመለስ ወሰንህ›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ከ1ኛ ተከሳሽ የቀረበለት ምስክሩ፣ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ የሚያደርጉ የግል ጉዳዮች ስለነበሩብኝ በስሜታዊነት የወሰንኩት ውሳኔ በመሆኑ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡
ምስክሩ ‹‹ለምስክርነት ያስገደደህ አካል የለም ወይ›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹የለም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ግንቦት ሰባት ነጻ አውጭ ድርጅት ነው ወይስ አሸባሪ›› ተብሎ በተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ተነስቶ፣ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን በማሰማት ‹‹ድርጅቱ በተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሏል፡፡ ይህ የህግ ጉዳይ ነው›› በማለት ጥያቄውን ምስክሩ የመመለስ ግዴታ እንደሌለባቸው አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህን ተቃውሞ ተቀብሎ ምስክሩ ጥያቄውን እንዲያልፉት ተደርጓል፡፡ ‹‹ማዕከላዊ ታስረህ ነበር፣ ድብደባም እንደደረሰብህ በሚዲያ ሳይቀር ተዘግቧል፡፡ ልክ ነው?›› ተብሎ በመስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቅ ምስክሩ ‹‹ማዕከላዊ ቃል እንድሰጥ ተደርጌያለሁ፤ ግን አልታሰርኩም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ የምስክሩን ቃል ከሰማ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ የምስክሩ ቃልና የሰነድ ማስረጃውን መርምሮ ፍርድ ቤቱ ብይን እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ለማሰማት ለመስከረም 5/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል

ኢህአደግ ጥራት ያለው አባል ማግኘት አልቻልኩም አለ

ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ሰማእታት አዳራሽ ዛሬ ሲጀምር በጽሁፍ ባሰራጨው ሪፖርቱ የአባላት ጥራት ችግር እንደገጠመው ይፋ አደርጓል።

ሪፖርቱ እንደሚለው አባላት ስለድርጅቱ ታሪክ ፣ፕሮግራም፣እሴቶችና ህገደንብ ዝርዝር ግንዛቤ ሳይዙ የሚመለመሉበት ሁኔታ አለ። “በእኛና በተቃዋሚዎች መካከል ስላለው መሰረታዊ ልዩነት ፣ስለመድረኩ ባህሪና ፈተናዎቹ በቂ መነሻ እውቀት ይዘው የእጩነት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደሙሉ አባልነት እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የሚሰራው ስራም ከጉድለት የተላቀቀ አይደለም። ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ አባላትም ለጥቅም ማግኛ አማትረው ድርጅቱን የሚቀላቀሉ ናቸው” ሲል አማሮአል።
በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ጥራት ያለው አባል መጥፋቱን የሚያወሳው ይህ ሪፖርት፣ በአሰላለፍ ረገድ የጎራ መደበላለቅ ማጋጠሙንም ጠቅሷል። በመንግስት ፖሊሲዎችና ልዩ ልዩ ሰነዶች ስልጠናዎች በተሰጠበት ወቅት፣ በመንግስት መ/ቤቶችና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉ አባላት የሚነሱ የተሳሳቱ አመለካከቶች አባል ካለሆነው ብዙም የተለዩ የማይሆኑበት ሁኔታ በስፋት መታየቱን ለአብነት አንስቷል።

ለምርጫ ተብለው የተቀየሩ ትራንስፎርመሮች ተቃጥለው በርካታ ሰዎች ተጎዶ

ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ የተቀየሩ በርካታ ትራንስፎርመሮች በአንድ ቀንና ሰአት በመቃጠላቸው ሰዎች ተጎድተዋል።

በነ ጸማይ ወረዳ ቃቆ ቀበሌ ትራንስፎርመሩ ሲቃጠል አንድ ነርስ ወዲያውኑ ህይወቱን ሲያጣ፣ 11 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።
በዚሁ ወረዳ ቀይ አፈር ከተማ ላይ ተጨማሪ 3 ትራንስፎርመሮች ሲፈነዱ፣ በሀመር ወረዳ በዲመካ ከተማ አንድ ትራንስፎርም፣ በጂንካ ከተማም እንዲሁ ሌላ ትራንስፎርመር ተቃጥሎአል።ሁሉም ትራንስፎርመሮች በተመሳሳይ ሰአት ነው የተቃጠሉት። ነዋሪዎች ፍንዳታው ከጥራት ችግር ጋር በተያያዘ የተከሰተ መሆኑን ገልጸው፣ እስካሁን ለተጎጂዎች እርዳታ አለመድረሱንም ተናግረዋል።
የተቃጠሉት ትራንስፎርመሮች በቅርቡ ከቻይና የገቡት ይሁኑ ወይም የመከላከያ ኢንጂነሪንግ የገጣጠማቸውና ለመብራት ሃይል ያስረከባቸው በውል አልታወቀም። ይሁን እንጅ ሁሉም ትራንስፎርመሮች ምርጫ ሊካሄድ አንድ ወር ሲቀረው መቀየራቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የዞኑን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ስኳር ኮርፖሬሽን በዚህ አመት 7 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ደረሰበት

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 22 ፣ 2007)

ከአራት አመት በፊት የተቋቋመውና አስር የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ለማካሄድ ሃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የ 2007 አም በጀት አመት የሰባት ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።
የሃገሪቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች እንዲያስተዳድር ሃላፊነት ተሰጥቶት የነበረው ይኸው ኮሮፖሬሽን ለስራው ማስኬጃ ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ለእቃ አቅርቦት መከፈል የነበረበትን ሶስት ቢሊዮን ብር በወቅቱ ሳይከፍል መቅረቱን ታውቋል።
የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ካጋጠመው ከፍተኛ ኪሳራ በተጨማሪ አቶ አባይ ጸሃዬ ኮሮፖሬሽኑን ለሁለት አመታት ያህል በዳይሬክተርነት ባስተዳደሩበት ጊዜ ከ 800 ሚሊዮን ብር በላይ የደረሰበት እንዳልታወቀ የድርጅቱ ምንጮች ለኢሳት በሰጡት መረጃ አመልክተዋል።
የተከሰተውን የገንዘብ ጉድለት ተከትሎም የድርጀቱ የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው ጉዳዩን ለጠቅላላ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ቢሮ በማቅረብ የኦዲት ምርመራ እንዲካሄድ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል።
ይሁንና ጥያቄ የቀረበለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ለጉዳዩ ምላሽ አለመስጠቱን የተናገሩት ምንጮች ለስኳር ኮርፖሬሽኑ ያጋጠመውን የፋይናንስ ቀውስ ተከትሎም በርካታ ሰራተኞች ከድርጅቱ በመልቀቅ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ወረዳ 9 17 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ

ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በድንገት በመምጣት በጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌ 02 የሚገኘውን የንግድ ድርጅታቸውን አሽገውባቸዋል። "በቂ ምክንያት ሳይኖርና በቂ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጠን፣ ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ ስራ ፈተን ቤተሰቦቻችን ለችግር ተጋልጠዋል" በማለት የሚናገሩት ነጋዴዎች፣ ጉዳዩን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መፍትሄ የሚሰጣቸው አላገኙም። የወረዳው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ወኪል የሆኑት አቶ ተክለአብ፣ ነጋዴዎቹ ራሳቸው እንዲሰሩበት የተሰጣቸውን ቦታ ለሶስተኛ ወገን አከራይተዋል በሚል ድርጅታቸው መታሸጉን አምነው፣ ተሰጠ የተባለው የማስጠንቀቂያ ጊዜ አጭር መሆኑን እንደሚያምኑ፣ ነገር ግን እስካሁን ሲሰራበት የነበረ አሰራር በመሆኑ ምንም ማድረግ እንደማይቻል ገልጸዋል። ነጋዴዎቹና ቤተሰቦቻቸው ውሳኔ አጥተው ለአንድ ወር በላይ መጉላላታቸው ተገቢ ነው ወይ ተብለው ለተጠየቁት፣ ሃላፊው ተገቢ አለመሆኑንና ሌሎች አመራሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡዋቸው ግፊት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

Thursday, August 27, 2015

የሕወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ በአባይ ወልዱ ቡድን መሪነት ተጠናቀቀ፣ ሽኩቻው ይቀጥላል ፣ሕወሃት ቀሚስ እንደለበሰ ነው?


አቶ አባይ ወልዱ(የመቀሌው ቡድነን) መሪና ዶ/ር ደብረጽዮን የአዲስ አበባው ቢድን መሪ
አቶ አባይ ወልዱ(የመቀሌው ቡድነን) መሪና ዶ/ር ደብረጽዮን የአዲስ አበባው ቢድን መሪ
ሕወሃት ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ሲያካሂድ የከረመው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር አድርጓል።ሕወሓት በኢትዮጵያ ዋናውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስልጣን የተቆጣጠረው፣በአገሪቱ እየደረሰ ላለው ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ፣ በስም ፌዴራሊዝም የሚቀልደው ሌሎችን ድርጅቶች እንደ አሽከር በማየት የራሱ ታዛዥ በማድረጉ አልፎ አልፎ በኢህአዴግ ውስጥ የጉምጉምታ መነሻ የሆነው ድርጅት ማን ሊቀመንበሩን ይይዛል የሚለው የስልጣን ሽኩቻ በመቀሌና የአዲስ አበባ ቡድን በሚል ውስጥ ውስጡን ከጉባዔው በፊት በይፋ በጉባዔው ሂደት የተስተዋለ ሲሆን የመቀሌው ቡድን አስቀድሞ እንደተዘገበው አባይ ወልዱን የወቅቱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሊቀመንበር ለማድረግ የጀመረው ትግል በበላይነት ተጠናቋል። የክልሉን ፖለቲካ ትኩሳት በቅርበብ የሚከታተለው አምዶም ገ/ስላሴ በተደጋጋሚ ለህብር ሬዲዮ የስልታን ሽኩቻውን አስመልክቶ በሰተው ቃለ ምልልስ ሁለቱም ቡድን በየበኩሉ እስከ ቀበሌ ካድሬ ከጉባዔው በፊት ሲያደራጅ ቆይቷል። አንዱ የአንዱን ቡድን ደጋፊ ለመጣል በልብነትና አልፎ አልፎም በአረና ወገንተኝነት ሲከሱ ቆይተዋል። የአባይ ቡድን ከፌደራለል እነ በረከትን ከብአዴን የያዘ ሲሆን ወ/ሮ አዜብን በሕወሓት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ማስመረጡ ቀድሞም ሲባል እንደነበረው <<የመለስ ራዕይ የመለስ ራዕይ >> የሚለው መዝሙሩን አጠናክሮ የሚወጣ መስሏል።በጉባዔው በአንደኝነት ከአንድ ሺህ ድምጽ በላኢ አግኝተው የተመረጡት ዶ/ር ደብረጽዮን የሳቸው ሳይሆን የአባይ ቡድን ገኖ የሠጣበት ፖሊት ቢሮ ተመርጣል።

የሕወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ በአባይ ወልዱ ቡድን መሪነት ተጠናቀቀ፣ ሽኩቻው ይቀጥላል ፣ሕወሃት ቀሚስ እንደለበሰ ነው?

አቶ አባይ ወልዱ(የመቀሌው ቡድነን) መሪና ዶ/ር ደብረጽዮን የአዲስ አበባው ቢድን መሪ

ሕወሃት ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ሲያካሂድ የከረመው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር አድርጓል።ሕወሓት በኢትዮጵያ ዋናውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስልጣን የተቆጣጠረው፣በአገሪቱ እየደረሰ ላለው ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ፣ በስም ፌዴራሊዝም የሚቀልደው ሌሎችን ድርጅቶች እንደ አሽከር በማየት የራሱ ታዛዥ በማድረጉ አልፎ አልፎ በኢህአዴግ ውስጥ የጉምጉምታ መነሻ የሆነው ድርጅት ማን ሊቀመንበሩን ይይዛል የሚለው የስልጣን ሽኩቻ በመቀሌና የአዲስ አበባ ቡድን በሚል ውስጥ ውስጡን ከጉባዔው በፊት በይፋ በጉባዔው ሂደት የተስተዋለ ሲሆን የመቀሌው ቡድን አስቀድሞ እንደተዘገበው አባይ ወልዱን የወቅቱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሊቀመንበር ለማድረግ የጀመረው ትግል በበላይነት ተጠናቋል። የክልሉን ፖለቲካ ትኩሳት በቅርበብ የሚከታተለው አምዶም ገ/ስላሴ በተደጋጋሚ ለህብር ሬዲዮ የስልታን ሽኩቻውን አስመልክቶ በሰተው ቃለ ምልልስ ሁለቱም ቡድን በየበኩሉ እስከ ቀበሌ ካድሬ ከጉባዔው በፊት ሲያደራጅ ቆይቷል። አንዱ የአንዱን ቡድን ደጋፊ ለመጣል በልብነትና አልፎ አልፎም በአረና ወገንተኝነት ሲከሱ ቆይተዋል። የአባይ ቡድን ከፌደራለል እነ በረከትን ከብአዴን የያዘ ሲሆን ወ/ሮ አዜብን በሕወሓት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ማስመረጡ ቀድሞም ሲባል እንደነበረው <<የመለስ ራዕይ የመለስ ራዕይ >> የሚለው መዝሙሩን አጠናክሮ የሚወጣ መስሏል።በጉባዔው በአንደኝነት ከአንድ ሺህ ድምጽ በላኢ አግኝተው የተመረጡት ዶ/ር ደብረጽዮን የሳቸው ሳይሆን የአባይ ቡድን ገኖ የሠጣበት ፖሊት ቢሮ ተመርጣል።

ህወሃቶች የአቶ መለስን የመተካካት ፖሊሲ ሲቀለብሱ ብአዴኖች ደግሞ አቶ በረከትን በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ይዘው ለመጓዝ መሰኑ

ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያስቀመጡት የመተካካት ፖሊሲ በህወሃት ነባር አመራሮች ሲተች፣ ብአዴኖች ፖሊሲውን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው ግራ ተጋብተዋል። የአቶ መለስ የመተካካት ፖሊሲ በ2007 ዓም ሁሉም የድርጅቱ ነባር አመራሮች በአዳዲስ ወጣት አመራሮች ይተካሉ የሚል ነበር። ይሁን እንጅ ህወሃት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ በአቶ መለስ ወቅት ከአመራር ቦታቸው የተነሱት ነባር ታጋዮች በጉባኤው እንደገና በመምረጥና በመመረጥ መብት እንዲሳተፉ ተደርጓል። ከህወሃት ስልጣን ተገለው የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ እቁባይ፣ ብርሃነ ገብረከርስቶስና ሌሎች 17 የቀድሞ ታጋዮች በጉባኤው በታዛቢነት እንዲገኙ ቢጋበዙም፣ የጉባኤው አባላት ግለሰቦቹ በመተካካት ስም ተገፍተው ወጥተዋል ስለዚህም በሙሉ ስልጣን ይሳተፉ የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው፣ ጉባኤው የመተካካቱን ፖሊሲ በመቀልበስ እንዲሳተፉ ወስኖላቸዋል።

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው


ethiopia millitary in somalia
በሶማሊያ ሀገር  እየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ።በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የሞቱት ልጆቻችን የማይነግረን በመሰረቱ ልጆቻችን ወደ ሶማልያ አገር ሂደው እንዲያልቁ የሚደረገውስ ለምን ዓላማ ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ግልፅ በሆነ መንገድ መነገር አለበት በማለት ጥያቂያቸውን እያቀረቡ መሆናቸው ተገለጸ።
ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ባለስልጣን አልሸባብን ለማጥፋት በሚል ምክንያት ከሃያላን መንግስታት የሚያገኙትን ዶላር ለመሰብሰብ ካልሆነ ከአገሩ ውጭ እየሄደ ህይወቱን እያጣ ላለው ወጣትና ቤተሰቦቹ ግን ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌላቸው የሟቾች ቤተሰብና አንዳንዱ የአገራችን ምሁራኖች አስተያየታቸው እየሰጡ መሆናቸው አስታውቋል።
በተመሳሳይ አንድ በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ተምቤን ዓብይ ዓዲ ውስጥ የሚኖሩ ወላጅ ልጃቸው በሶማልያ ሃገር ሄዶ መሞቱ ለምን አላማ ሲባል ነው ብለው መጠየቃቸው ባለፈው የዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል።

እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ከእስር በነፃ ተፈቱ።

ጀግኖቹ እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ሓሙስ 14 / 12 / 2007 ዓ/ም ከእስር በነፃ ተፈቱ።
ከዓመት በፊት በሽብር ክስት ታስረው የነበሩት ጀግኖቹ የሰለማዊ ትግል ጀግኖች ከተከሰሱበት የፈጠራ ክስ ነፃ ተብለው ተፈትተዋል።
፩) ኣብራሃ ደስታ ከዓረና
፪) ሃብታሙ ኣያሌው ከኣንድነት
፫) የሺዋስ ኣሰፋ ከሰማያዊ
፬) ዳኑኤል ሺበሺ ከኣንድነት
ከተከሰሱበት የሽብር ክስ በነፃ ተሰናበቱ።
ለመላው ኢትዮዽያውያን ስለነዚህ ጀግኖች መታሰር የተጨነቃቹ ወገኖች እንኳን ደስ ኣላቹ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው

በሃማስ የታገተው ኢትዮ እስራኤላዊ ቤተሰቦች የጋዛን መተላለፊያ ዘጉ

ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ በጋዛ ሰርጥ በሃማስ የታገተው ኢቲዮ እስራኤላዊ ወጣት አቭራም መንግስቱ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቹ ልጃችን ይለቀቅ በማለት በጋዛ ኤርዝ መተላለፊያን ዘግተው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን የልጃቸውን መታገት በዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲታወቅላቸውም ተማጽዕኖዋቸውን አሰምተዋል።

የአቭራም ወንድም ”እኛ በነፃነት የመዘዋወር መብትን እናከብራለን፣ ሁላችንም ፍልስጤማዊያንም እስራኤላዊያንም ጭምር እኔ አሁን የምንጠይቀው ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ወንድሜን ሃማስ እንዲለቅልኝ ብቻ ነው።” ብሎአል።
ሃማስ በበኩሉ የታጋቹ ቤተሰቦች ልጃቸው የዐዕምሮ ሕመም ችግር እንዳለበት ያቀረቡትን ተማጽኖ ግድ እንደማይሰጠው አስታውቋል።
ቤተ እስራኤላዊያን እስራኤል ውስጥ መድሎና መገለል እንደሚደርስባቸውና የእስራኤል መንግስት ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ያልተከታተለው በቆዳ ቀለሙ የዘረኝነት ሰለባ በመሆኑ ነው በማለት መናገራቸውን ዘ ጀሩሳሌም ፕሬስ አክሎ ዘግቧል

መልዕክት በድሆች ድህነት ለመክበር መሯሯጥ ላይ ላሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት


def-thumbየግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው። በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።
በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን ግዴታ ነው።

Monday, August 24, 2015

ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው እነ አብርሃ ደስታ እገዳ ተጣለባቸው

ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል፡፡
አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡ ነጻ የተባሉት አመራሮች ባለፈው አርብ ከእስር ይወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ድረስ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
Netsanet Beqalu Mannet's photo.

የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት “የተቃዋሚዎች ሬድዮ ታዳምጣላቹ በሚል እየታሰሩ ነው


11899854_458103757685979_3718763112024142931_n
በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው የስብሰባው መሪዎችና ገምጋሚዎች ሆነው በመቅረብ ለበርካታ የሰራዊቱ አባላት እያባረሩና እያሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በተለይ በሰሜን እዝ እየተካሄደ ባለው የዓመቱ ግምገማ ላይ የሰራዊቱ አባላት ሓቀኛና ገምቢ ግምገማ ነው ብለው ስላላመኑበት ማንኛውም ሃሳብ ከመስጠት እንደተቆጠቡና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሆኑት የበላይ መኮነኖች “እዚህ የተሰበሰብነው ሰራዊቱ አንዣቦበት ካለው የመበታተን አደጋ ለማዳን ስለሆነ የተቃዋሚዎች ሬድዮ ለምን ትሰማላችሁ ብለው ላቀረቡት ሃሳብ በተሰብሳቢዎቹ ማንኛውም ሚድያ መከታተል የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብት ነው” ብለው የተቃወሙትን የናንተ አመለካከት ከተቃዋሚዎች ጎራ ነው በማለት እንድፋሰርዋቸው መረጃው ጨምሮ አስርድቷል።

ለመለስ አካዳሚ ግንባታ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ለኢህአዴግ ፓርቲዎች ተከፋፈለ

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርሶአደሩ ፣ የመንግስት ሰራተኛውና ነጋዴው ለቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አካዳሚ ግንባታ በሚል በግዴታ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍል ቢደርግም፣ ምክንያቱ በውል ባልተገለጸ ሁኔታ ገንዘቡ ለኢህአዴግ አራት ድርጅቶች ማለትም ለህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ተከፋፍሏል። ሁሉም ድርጅቶች 80 ሚሊዮን 566 ሺ 221 ብር ደርሶአቸዋል።

ገንዘቡን ለመንግስት ወይም ለከፈሉት ዜጎች መመለስ ሲገባ ድርጀቶች እንዲከፋፈሉት መደረጉ ፣ ኢህአዴግ በተገኘው አጋጣሚና በሰበብ አስባቡ የህዝብ ገንዘብ እየዘረፈ መሆኑን ያመለክታል ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት በላስ ቬጋስና በለንደን የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ!!

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማጠናከር በላስቬጋስ ከተማ የተጠራው የሀገር አድን ጥሪ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በእለቱ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ከፍተኛ ገንዘብ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል፡

በዚህ ለሰማእታት በተደረገ የህሊና ጸሎት የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሻው ገብሬ የንቅናቄው አመራር አባላት በአዳራሽ ተገኝተው አስፈላጊውን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ የታደመው የላስቬጋስ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በንቅናቄው መሪዎች ወደ ትግሉ ሜዳ መውረድ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ወያኔን አስወግዶ በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት ንቅናቄው የጀመረውን ትግል እስከመጨረሻው ድረስ ከንቅናቄው ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
ንቅናቄውን በገንዘብ ለማጠናከር በጎልድ ኮስት ሆቴል በተጠራው በዚህ ስብሰባ ልይ ከፍተኛ የህዝብ መነቃቃት የታየበት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰቡንም ለማወቅ ተችላል፡፡

በሰቆጣ ከተማ ከፍተኛ የውሃ ችግር መከሰቱን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተያዘው ክረምት በአብዛኛው ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ የሰቆጣ ከተማና የአካባቢው ወንዞች በመድረቃቸው የውኃ እጥረቱ መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ነዋሪዎች ፣ በዝናቡ እጥረት የተነሳ የጉድጓድ ውሃ መጠን በማነሱ የሚጠጣ ውኃ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

“በከተማዋ በአጠቃላይ የውኃ ችግር ተከስቷል፡፡በከተማዋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ ልማት ጽህፈት ቤት ምን እየሰራ እንደሆን አናውቅም የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ የውሃ መስመሩ በየሳምንቱ ተበላሽቷል እንደሚባሉ ይናገራሉ፡፡ በየቤቱ የሚገኘው የቧንቧ መስመር አገልግሎት በመቋረጡ የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በመነሳት ወረፋ በመያዝ የገደል ውሃ ለመቅዳት መገደዳቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በሌሊት ወጥተው እስከ ቀኑ አራት ሰዓት ድረስ አርፍደው ውሃ እንደሚያገኙ በምሬት ገልጸዋል፡፡
በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የውኃ ችግር እንዳለ የሚገልጹት ሌላው የከተማ ነዋሪ ከዝናቡ መጥፋት ጋር ተያይዞ የሚታይ ችግር መሆኑን ይናገራሉ፡፡በከተማው ውስጥ ለውስጥ የሚያቋርጡና በዙሪያው ያሉ ወንዞች መድረቅ ህብረተሰቡ ከወንዝ ቀድቶ መጠቀም እንዳይችል አድርጓል፡፡ዝናብ አንድ አንድ ጊዜ ሲዘንብ እንዲህ ያለ መጨናነቅ እንደማይከሰት የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢ አልፎ አልፎ በሚጥለው ዝናብ ከቆርቆሮ ላይ በመሰብሰብ የየዕለት ችግራቸውን ለመቅረፍ እንደሚሞክሩ ይናገራሉ። ዝናብ በወር አንዴ ብቻ መዝነቡንና ከዚህ ውጭ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሚቆይ ካፊያ ብቻ መሆኑ የውኃውን ችግር እንዳባባሰው ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ አስተድደር ከአሁን በፊት ውኃ በቦቲ በማቅረብ የህዝቡን ጊዜያዊ ችግር ለመቅረፍ ቢሞክርም፣ አሁን አገልግሎቱ በመቋረጡ የከተማው ህዝብ በችግር ላይ ነው፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚናገሩት በነሃሴ ወር ከአሁን በፊት እንደዚህ ዓይነት የውኃ ችግር ተከስቶ እንደማያውቅ ተናግረው፤አልፎ አልፎ በሚጥለው ዝናብ የደረቀውን መሬት ከማራስ አልፎ ወደ ከርሰ ምድር የሚዘልቅ ውኃ ባለመኖሩ ከመስከረም ወር በኋላ ከፍተኛ የውኃ ችግር ሊከሰት ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው አክለዋል።
የገዢው መንግስት አመራሮች ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠታቸው ህብረተሰቡ ለከፍተኛ የውሃ ችግር መጋለጡን የሚገልጹት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ የጉድጓድ ውኃ ለመቅዳት በወረፋ ሰበብ ህዝቡ እርስ በርሱ ሲጣላ እና ቀኑን ሙሉ አንድ ጀሪካን ውኃ ለመቅዳት ተሰልፎ ስራ ሲፈታ በዝምታ ከማየት ሌላ የፈየዱልን የመፍትሄ ነገር የለም በማለት ይናገራሉ፡፡
ከአሁን በፊት ለሃያ አመታት ያገለግላል ተብሎ በከፍተኛ ወጪ የተሰራው የቧንቧ ውኃ ፣ ሶስት ዓመት ብቻ አገልግሎ ደርቋል።

በነባሩና በአዲሱ የድርጅቱ አመራር መካካል ልዩነት መኖሩን ብአዴን ገለጸ

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ እንደገለጸው፣ ለረጅም ጊዜ በአመራርነት ቆይቶ ስልጣኑን በመተካካት ሂደት ባስረከበውና ቁልፍ ስልጣኑን በተረከበው መካካል የመግባባት ችግር መኖሩን ገልጿል።ነባሩ አመራር ሁሉንም ሃላፊነት አስረክቦ ድርጅቱን የመልቀቅና ራሱን ገለል አድርጎ ለመኖር ይፈልጋል ያለው ብአዴን፣ በዚህም ላይ ነባሩ አመራር በአዲሱ አመራር እንደማይረካና ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርብም ገልጿል።

ቁልፍ ስልጣን የተረከበው አዲሱ አመራርም የራሱን አቅም የማያውቅ፣ ስልጣኑን ካስረከበው ነባር አመራር ለመማር ፍላጎት የሌለው ነው ብሎአል።
በአዲሱ እና በነባሩ አመራር በኩል ለታየው አለመግባባት ምንጩ ዲሞክራሲያዊ ትግል አለመጎልበት፣ አድባርይነት ፣ ፊት ለፊት ለመታገል አለመፈለግ፣ ድክመቶችን ለመቀበል ፍላጎት አለመኖር፣ ሂስና ግለሂስን አለመቀበልና የድርጅቱን አሰራሮችን በተግባር ለማዋል ፍለጎት አለማሳየት ናቸው ብሎአል።
በቅርቡ ቁልፍ የሃላፊነት ቦታዎችን በተረከበው አመራርና በቆየው አመራር መካከል መደጋገፍ የሰፈነበት ግንኙነት ካልተፈጠረ መተካካቱ ህይወት አይኖረውም ብሎአል።
በአዲሱ አመራርና እና ሃላፊነቱን ባስረከበው አመራር መካካል የታየው ልዩነት፣ ነባር አመራሩ የመተካካት መርሆ ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እንዲዛመዱ እየጠየቀ ነው። ምንም እንኳ አቶ በረከት ስምኦን በ11ኛው የድርጅቱ ጉባኤ ከስራ አስፈጻሚነት ቦታቸው እንደሚነሱ ቢታወቅም፣ ከዚህ ቀደም በተገለሉት በእነ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ እና ሌሎችም አመራሮችና በአዲሱ አመራር መካካል የተፈጠረው ክፍተት ስጋት ላይ ሳይጥላቸው አይቀርም። አዲሱ አመራር ነባሩን አመራር የሚንቀው ሲሆን፣ ነባሩ አመራር ደግሞ አዲሱ አመራር የትግል ወኔ የለውም ሲል ይተቻል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ብአዴን በተለያዩ ክልሎች እና በውጭ አገር የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ለማደራጀት ያደረገው ሙከራ መክሸፉን አስታውቋል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች የድርጅቱን አስተሳሰብ እንደማይደግፉና ተወላጆቹን ለማደራጀት ቀደም ብሎ ያደረጋቸው ሙከራዎች መክሸፋቸውን አስታውቋል።

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በመዲናዋ አዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ ለቀጣዩ ሦስት ዓመታት ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ አምስት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡ ጉባኤው የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም መርጧል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲን ለቀጣይ ሦስት ዓመታት እንዲመሩ 136 ድምጽ ሲያገኙ ተፎካካሪያቸው አቶ ዮናታን ተስፋዬ 60 ድምጽ አግኝተዋል።
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በሁለቱ ቀናት ጉባኤው ያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ 4 ነብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጋር የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በተያዘው አመት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የተረጅዎች
ከግምት ውጪ ላሻቀበው የተረጅዎች አሀዝ ብቻ 230 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ በጋራ መግለጫው ላይ የተመለከተ ሲሆን፤ከዚህ መካከል መንግስት 33 ሚሊዮን ዶላር ያህሉን መመደቡና ቀሪው 200 ሚሊዮን ዶላር በአስቸክይ ከውጭ ለጋሾች የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል።
2015 ከገባ አንስቶ እስካሁን ድረስ 386 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ እርዳታ ሲሰጥ መቆየቱ በመግለጫው ተጠቅሷል።
የተመድ የስብዊ እርዳታ ሃላፊ ዴቪድ ዴል ኮንቴ ፣ የኢትዮጵያ ሚቲሪዮሎጂ ድርጅት የበልግን ዝናብ አስመልክቶ ከተነበየው በጣም የከፋ የዝናብ እጥረት በበልግ ወቅት ተከሰቷል ብለዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ ፤ ትርፍ አምራች የነበሩት እንደ አርሲና ምእራብ አርሲ የመሳሰሉ አካባቢዎች ሳይቀሩ አሁን እርዳታን ይሻሉ።
እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወረዳዎች ቁጥር ከ49 ወደ 97 ከፍ ማለቱ፤ እንዲሁም አሣሳቢ ሁኔታ ላይ የደረሱና አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት አሀዝም በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡ ተገልጿል።
-በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ሚስ ጁሊያን ሜልሶክ- ለጋሽ ሀገሮች እስካሁን በጥሩ ሁኔታ እርዳታ ሲሰጡ መቆየታቸውን በማውሳት- አሁን ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ በመሆኑ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተማጽነዋል።

Sunday, August 23, 2015

ከ380 በላይ ሰዎች ተይዘው ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ገሚሶቹ ሴቶች ናቸው::


ኢሳት ዜና :-ሁለት ወጣቶች ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ ተጨማሪ አርሶአደሮች እየተያዙ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ከ380 በላይ ሰዎች ተይዘው ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ገሚሶቹ ሴቶች ናቸው። አብዛኞቹ ሴቶቹ የተያዙት በርካታ አርሶአደሮች አፈሳውን ለማምለጥ ጫካ መግባታቸውን ተከትሎ በባሎቻቸው ቦታ ሲሆን፣ የተወሰኑት ደግሞ ለሽፍቶች ምግብና ውሃ አቀብላችሁዋል ተብለው ነው። በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ 8 ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ አርሶደአሮች የተያዙት ሻሾ አንበሳ እና ዘላለም ጊዲሳ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከመንግስት የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ መሸፈታቸው ተከትሎ ነው። አርሶአደሮቹ ኤጀርሳ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው ልብሶቻቸውን እንዲያወልቁ እየተደረገ ሌት ተቀን ተደብድበዋል። ቤተሰቦቻቸው ምግብና ውሃ እንዳያቀበሉም ተከልክለዋል። በህጋዊ መንገድ ያስመዘገቡት የግል የጦር መሳሪያ ከየቤታቸው እየተለቀመ ተወስዶባቸዋል። ኢሳት ትናንት ዘገባውን ካቀረበ በሁዋላ፣ ከእስር ቤት በመጥፋት ጫካ ውስጥ የተደበቀ አንድ አርሶ አደር ባስተላለፈው የስልክ መልእክት፣ በኢሳት የቀረበው አሃዝ አነስተኛና ዛሬም ድረስ በርካታ አርሰዶአሮች እየተያዙ ሲሆን፣ በርካቶቹም ጫካ ውስጥ ተደብቀዋል ብሎሏል። ድብደባው ሌት ተቀን እንደሚካሄድና እስካሁን ጫካ የገቡትን ወጣቶች ያሉበትን አካባቢ አውቃለሁ ያለ ሰው አለመኖሩን ገልጿል። አርሶአደሮቹ ከወር በላይ ለሆነ ጊዜ በመታሰራቸው የእርሻ ስራቸውን ለመስራት አልቻሉም። ቤተሰቦቻቸውም በየደረጃው ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢሉም መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። መረጃውን ያደረሱን አንድ የአካባቢው ሽማግሌ የኢትዮጵያ ህዝብ መረጃውን ሰምቶ አርሶደሮቹ እንዲለቀቁ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ወያኔ እና የሚዘረፈው ሰራዊት (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን (የኢሳት ጋዜጠኛ)
ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ::Ethiopian peacekeeping troops
እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመትቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ::
በዘመቻው በUN ደረጃ ወርሃዊ ደም

Friday, August 21, 2015

ህወሓት መራሹ መንግስት በጭንቀትና በፍርሃት እየተናጠ መሆኑ ተሰማ

በመረጃ መረብ ሰንሰለቱ አማካኝነት ወደ መንግስት መዋቅር ዘልቆ በመግባት ያገኘው የታማኝ ምንጮች መረጃ እንዳረጋገጠው በሙስሊሙ ዑማ ላይ ከፍተኛ በደልና ጭቆና የፈፀመው ህወሓት መራሹ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙ ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ዘፍቆታል ። በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የትግል ስልቱን ቀይሮ ውስጥ ለውስጥ በመደራጀት አንድነቱን እያጠናከረ እና በተናጠልና በቡድን በመሆን ስለ ቀጣይ ትግሉ እየተወያየ ባለበት በዚህ ወቅት ህወሃቶች ” የሙስሊሙ ዝምታና ድምፁን ማጥፋት ” አሳሳቢ ነው በቀጣይ ምን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አይታወቅም በማለት ህወሃቶች በከፍተኛ ስብሰባ መጠመዳቸው ነው የታወቀው እንደ ምንጮቻችን ገለፃ መሰረት ህወሃቶች ባለፉት ቀናቶች በየክፍለ ከተማው ከሚገኙ ታማኝ ካድሬዎቻቸው ጋር ባደረጉት ዝግ እና ጥብቅ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የሙስሊሞችን ዝምታ አሳሳቢ ነው ስለዚህ ትኩረት ሰጥተን መከታተል አለብን ለዚህም ይረዳ ዘንድ ካድሬዎቻችንን ከመቼውም በበለጠ በመስጅዶች እና ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢ ማሰማራት አለብን በማለት ተወያይተዋል :: በሌላ በኩልም በየግዜው በድብቅ የሚያደርጉት ሚስጥራዊ ስብሰባ አፈትልኮ መውጣቱና በተደጋጋሚ በ BBN RADIO በኩል ወደ ህዝብ ጆሮ መድረሱ ከፍተኛ ራስ ምታትና የእርስ በርስ አመኔታ ማጣትን እንዳስከተለባቸው ለማወቅ ተችሏል

በአውሮፕላን ስዊድን የገባው ስደተኛ አየር መንገድ ውስጥ ባለው በዘረኝነት መማረሩን ገለጸ

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 15 ፣ 2007)ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞ አውሮፕላን ውስጥ በእቃ መጫኛ ውስጥ ተደብቆ በስዊድን ጥገኝነትን የጠየቀው ኢትዮጵያ በአየር መንገድ ውስጥ በአንድ ብሄር የበላይነት የሚደርሰው በደልና ግፍ ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ድርጊቱን መፈጸሙን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አስታወቀ።

የ 24 አመቱ ወጣት ይርጋሸዋ ማሽላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር የበላይነት ሰፍኖ እንደሚገኝ እና በአየር መንገዱ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር የበላይነት ሰፍኖ በሚገኝ እስር ቤት ለሁለት ቀን መታሰሩን ገልጿል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ማጓጓዣ ክፍል ውስጥ ሰራተኞች የነበረው ወጣት ይርጋሸዋ በስራው ላይ ያለ እስክሪን ፍተሻ ያለፈ የአንዲት ኢትዮጵያዊ ሻንጣ ተከፍቶ መገመት የሚቸግረው ዶላር መታየቱንና የጸጥታ ሀይሎች ሻንጣውን አውቀህ ነው የከፈትከው በሚል ለእስር እንደዳረጉት አስረድቷል።

Thursday, August 20, 2015

ከ300 በላይ አርሶአደሮች ታስረው እየተደበደቡ ነው

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ በፋጂ ኢጀርሳ፣ ላንቱ ወላርጊ እና ምእራብ ኮርጎጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ300 በላይ አርሶአደሮች ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ኢጀርሳ መንደር ውስጥ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸውና እስራቱን ለማምለጥ የተደበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አርሶ አደሮቹ የታሰሩት ሻሾ አንበሳ እና ዘላለም ጊዲሳ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከመንግስት የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ መሸፈታቸው ከተነገረ በሁዋላ ነው። አርሶአደሮቹ ለሽፍቶቹ ምግብ ታቀብላላችሁ፣ መደበቂያ ቦታም ትሰጣላችሁ በሚል ከ8 ቀበሌዎች ተሰብስበው ኤጀርሳ ትምህርት ቤት ውስጥ ከታሰሩ በሁዋላ፣ ልብሶቻቸውን እንዲያወልቁ ተነግሮአቸው በፌደራል ፖሊስ አባላት ክፉኛ ተደብድበዋል። ቤተሰቦቻቸው ምግብና ውሃ እንዳይወስዱላቸውም ተከልክለዋል። በህጋዊ መንገድ ያስመዘገቡ የግል የጦር መሳሪያቸውም ተወስዶባቸዋል።
ነሃሴ 5 ቀን በተፈጸመው ቢቂ ፣ ድርቤ፣ ትርፉና ኩልኪ ሴቶች ናቸው።
አርሶአደሮቹ ከወር በላይ ለሆነ ጊዜ በመታሰራቸው የእርሻ ስራቸውን ለመስራት አልቻሉም። ቤተሰቦቻቸውም በየደረጃው ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢሉም መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም።
በዚህ ዞን አንድ የወረዳ ባለስልጣን መሳሪያህን ደብቀሃል ያለውን አርሶደአደር በሚስቱ ፊት እርቃኑን አቁሞ ጸያፍ ድርጊት እንደፈጸመ ኢሳት መዘገቡ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብቻ በያመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ይዘረፋል ተባለ

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመንን አስመልክቶ በ51 የአዲስ አበባ አድባራት ባካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት፣ በየወሩ 100 ሚሊዮን ብር፣ በዓመት ደግሞ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በሙስና እንደሚዘረፍ ገልጿል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት ይዞታ ቢኖሯትም የሚገባውን ያኽል ተጠቃሚ እንዳልሆነች ሰሞኑን ለጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ የቀረበው የአዲስ አበባ አድባራት የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመን ጥናታዊ ሪፖርት ማረጋገጡን ፓትርያርኩ ጠቅሰዋል፡፡
ከቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ባሕርይ ጋር የማይስማሙ የሙስና እና የሥነ ምግባር ብልሹነትን ለማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ “ጭላንጭል እየታየበት ነው” ያሉት ፓትርያርኩ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልዕልና እና ሕይወት እስኪመለስ በሰላማዊ መንገድ እና በአቋም መታገላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳስበው በቀጣዩ ዓመት 2008 ዓ. ም. ቤተክርስቲያኗ ከሙስና የፀዳ አስተዳደር ይኖራታል ማለታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

በሰቆጣ ከተማና አካባቢዋ ከወር በሁዋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ዝናብ በመዝነቡ ህዝቡ ደስታውን ገለጸ

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ሰኔ 15 እና 16 የክረምቱ ዝናብ ከዘነበ በሁዋላ፣ ዝናብ ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት አልዘነበም። ሃምሌ 29 ቀን ደግሞ ለአንድ ጊዜ ዘንቦ በመጥፋቱ ፣ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጅ ትናንት ከምሽቱ 11 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ መዝነብ የጀመረው ዝናብ እስከ 12 ሰአት ከ10 ደቂቃ ድረስ በመዝነቡ፣ የከተማው ህዝብ ደስታውን ሲገልጽ አምሽቷል።

በድርቁ ምክንያት በከተማውም ሆነ በዙሪያው ያሉት ወንዞች ድርቀዋል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታየው ድርቅ ህዝቡን እያሳሰበ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝቡ ጸሎት እያደረገ ነው።

የወያኔ ጄነራል አብረሃ ወልደማሪያም መኖሪያ ቤት አዲስ አበባ (ፎቶ)

የሕወሓት መሐይም የጦር ሹማምንት በእንደዚህ አይነት ቪላ ተንደላቀው ሲኖሩ ተራው ወታደር 500 ብር ባልሞላ ደሞዝ እየተሰቃየ አፈር ድሜ እየበላ ይኖራል። በፎቶው የምትመለከቱት ቪላ ጦር ኃይሎች ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ የሚገኝ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ”የሜ/ ጄነራል” አብረሃ ወ/ ማሪያም መኖሪያ ቤት ነው። ቪላው እንዴት ተሰራ!?! ደሞዙ!?! የገንዘብ ምንጩ ከየት ነው!?! የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ በሽብርተኝነት ያስከስሳል፤ በህገ መንግስቱ ያስቀጣል። ይች ናት እንግዲህ የሕወሓቷ ኢትዮጵያ!!

የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡
የህወሓት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ በርካታ ህፃናትን ከየአካባቢው መልምሎ አዲስ አበባ ውስጥ የስለላ ትምህርት በስውር እያስተማረ ይገኛል፡፡
ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ህፃናቱን አገዛዙን ብቻ በታማኝነት እንዲያገለግሉ የሚያመቻች የስለላና ሌሎች ተያያዥ ትምህርቶችን ለረጅም ጊዜ በተከታታይ በመስጠት አስተሳሰባቸውን በመግራት አእምሯቸውን በሚፈለገው መልኩ ለመቅረፅ በከፍተኛ ሁኔታና በትኩረት ሲሰራበት ከርሟል፡፡
በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተመልምለው የስለላ ትምህርት ሲሰጣቸው የቆዩት ጮርቃ ህፃናት ስልጠናቸውን በቅርቡ ጨርሰው አገዛዙ ክትትል ማድረግ ወደሚፈልግባቸው የሲቪል ሰርቪስና ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም ንግድ በሚካሄድባቸው ቦታዎች በሰላይነት እንዲሰማሩ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት የውስጥ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

ሀብታሙ አያሌው፣ዳንኤል ሽበሽ፣አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም አብረሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡

Wednesday, August 19, 2015

አክራሪና አሸባሪዉ ኢህአዴግ ወይስ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት? (ርዕዮት አለሙ)

ልጆች ሆነን “እከሌ (እከሊት) አክራሪ ነዉ (ናት) ” ሲባል ይሰጠን የነበረዉ ትርጉም እና አሁን አክራሪነት እየሰጠ ያለዉ ትርጉም ለየቅል ይመስለኛል፡፡ ያኔ አንድ ሰዉ በአክራሪነት ሲጠራ ከብዙሃኑ በተለይ ሁኔታ ሃይማኖቱን ወይም የሚያምንበትን አንዳች ነገር አጥብቆ መያዙን እና በሚያምንበት ነገር ላይ የማይደራደር መሆኑን ከማሳየት አልፎ የአሁኑን አይነት አሉታዊ ትርጉም አይሰጥም ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀዉ የአማርኛ መዝገበ ቃላትም ያኔ ቃሉን እረዳበት ከነበረዉ ትርጉም ብዙም የራቀ ፍቺ አያቀርብም፡፡ በ1993 ዓ.ም የካቲት ወር የተዘጋጀዉ ይኸዉ መዝገበ ቃላት አክራሪ ለሚለዉ ቃል የሚሰጠዉ ፍቺ “በሚከተለዉ እምነትና አስተሳሰብ ዉስጥ ፍፁምነት ሊኖር ይገባል ብሎ የሚያምንና የቆየዉን እምነትና አስተሳሰብ ከዘመናዊዉ ሁኔታ ጋር ማስተካከል እና ማጣጣም የማይፈልግ አጥባዊ (ሰዉ)” የሚል ነዉ፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የቃሉ ፍቺ እየተቀየረ መጥቶ አሁን ያለዉን እጅግ አሉታዊ የሆነ ገፅታ ይዟል፡፡Journalist Reeyot Alemu on Ethiopian Muslims straggle
የህግ ባለሙያዉ ተማም አባቡልጉ የካቲት3 2007ዓ. ም በወጣዉ ኢትዮምህዳር ጋዜጣ ላይ “አክራሪ ሰዎች እነማን ናቸው?” በሚል ርዕስ ባስነበቡት ፅሁፋቸዉ “የራሱን ዘር፣ ሃይማኖትና ቡድን ጥቅም ሌሎችን በመጉዳት ጭምር ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀስ ወይም ከማስጠበቅ የማይመለስ” ሰዉ እንደሆነ አክራሪ የሚባለዉ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የታየውን ድርቅ ለመቋቋም ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የመኸርና የክረምት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉና በመዘግየቱ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሰለባ ለሆኑ ከ4 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ግምቱ ከ386 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ7 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አፋጣኝ የሆነ የሕይወት አድን የምግብና ሌሎች እርዳታዎች እንደሚያስፈልጉ ጠቅሷል።

በመላ አገሪቱ 49 ወረዳዎች በድርቁ የተጠቁ ሲሆን ይህም አሃዝ በአሁኑ ወቅት ወደ 97 ወረዳዎች ከፍ ብሎአል። በድርቁ ምክንያት በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ላይ በርካታ እንስሳት አልቀዋል። ከተወሰኑ የምዕራብ ትግራይ፣ምዕራብ አማራና ምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች በስተቀር የዝናቡ ስርጭቱ በአብዛሃኛው የአገሪቱ ክልልሎች አናሳ መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
አብዛሃኛው የትግራይ ክልል፣ ምስራቅ አማራ ማለትም ሰሜንና ደቡብ ወሎ ፣ኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ሰሜን ሸዋ፣ አብዛኛው የአፋር ክልል፣ በምስራቅ ኦሮሚያ አርሲ፣ባሌ፣ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ድሬደዋ፣ ሃረሪ፣ መእከላዊና ሰሜን ሶማሊያ ክልል፣ በደቡብ ክልል ጉራጌ፣ሃላባ፣ስልጤና ሃዲያ ዞን በከፊል በድርቁ ተመተዋል።
በተጨማሪም በአፋር፣አማራ፣ደቡብና ሶማሊያ ክልሎች በኤሊኖ የአየር ፀባይ መዛባት ሳቢያ በሚከሰት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚፈጥረው ጎርፍ ሳቢያ ድርቁ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።በመኸር መጠኑ ያነሰ ዝናብ በመጣሉ በውሃ ዕጥረት ሰበብ አርብቶ አደር በሆኑት በሶማልያ ክልል ሲቲና ፋፋን ዞን ከብቶቻቸው በመሞታቸው ሳቢያ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።
ከሕዳርና ታህሳስ በኋላ የምግብ ዋጋ እንደሚንርና የመግዛት አቅሙ የሌላቸው ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ ብሎአል። በደቡብ ክልል ህጻናት ከድርቅ ጋር በተያያዘ ትምህርት ማቋረጣቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል።

Tuesday, August 18, 2015

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገደሉት ሰዎች ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪዎች ተናገሩ

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

በመንጌ ከተማ አካባቢ በነበረ የአርብ ቀን ገበያ ላይ በተወሰደው አሰቃቂ እርምጃ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ወደ ሜዳ ኦዶ ከተማና ዳቡስ አካባቢ ወደ ሚገኙ መልስተናኛ ከተሞች በሸሹት ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወስዷል።
በአካባቢው አሁንም ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአካባቢው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአለፈው ምርጫ እንዳይሰተፉ የተከለከሉ ሲሆን፣ ህዝቡም ይህን ተከትሎ በምርጫው ላለመሳተፍ አቋም ወስዶ ነበር።
ኢሳት ታጠቂዎች በወሰዱት እርምጃ 12 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው መሆኑንና 56 ሰዎች በመንጌ ወረዳ በአሶሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን እንዲሁም 54ቱ ሰዎች መታሰራቸውን፣ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄን በመጥቀስ ዘግቧል።

በደቡብ ወሎ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። ከታሰሩት መካከል 6 ያክሉ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ እቅድ ተይዞ በነበረበት በቱሉ አወሊያ አንድ ፖሊስ ተደብድቦ አቀስታ ሆስፒታል ገብቷል።

በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ወጣቶችን ከቤታቸው እያወጣ መደብደቡን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የጋሞን ህዝብ የሚያንቋሽሽ ጽሁፍ መጻፉን ተከትሎ የተነሳው ውዝግብ እስካሁን አልበረደም። የአካባቢውን የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከሁለት የከፈለውን ውዝግብ ለማብረድ ፣ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የተመራ ቡድን የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ቢያስታውቅም፣ ችግሩ ሊበርድ እንዳልቻለ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተቃውሞው እንዲሰፋ ከጀርባ ሆነው ግፊት ያደርጋሉ የተባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ከትናንት ጀምሮ ተይዘው ታስረዋል።

የደቡብ ሱዳኑ ኢንፎርሜሽን ሚንስትር የስዩም መስፍንን አምባገነናዊ ሽምግልና እንደማይቀበሉት ገለፁ

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዊ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኅብረት ኢጋድ ዋና አደራዳሪ የሆኑትስዩም መስፍን በተደራዳሪዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይሞክራሉ ሲሉ ወቀሳቸውን አሰምተዋል።

ሚካኤል ማኩዊ ” የኢጋድ አደራዳሪዎች ደቡብ ሱዳንን የሙከራ ምድር ለማድረግ ይሞክራሉ።አንዳንዶቹ በጭራሽ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።የግድ መፈረም አለባችሁ ብሎ ለተደራዳሪዎች አስገዳጅ ውል ማቅረብ፣ ካልፈረማችሁ እኛ አንጠቀምም እንደ ማለት ሲሆን ዓለማቀፋዊ የአደራዳሪ ስነ ምግባርና ቋንቋም አይደለም።” ብለዋል።
የሰላም አደራዳሪዎቹ ማስማማት እንጂ የማስገደድና የማዘዝ ስልጣን የላቸውም የሚሉት ሚኒስትሩ፣ የኢጋድ ድርጊት ግን ፍፁም ያልተለመደና ከመደበኛ አደራዳሪዎች ያፈነገጠ ነው ብለዋል። በተለይ ዋናው የአደራዳሪዎች መሪ አምባሳደር ስዩም መስፍን ‘ወደዳችሁም ጠላችሁም ይህን ሳትፈርሙ ወደ ቤታችሁ አትሄዱም!’ ማለታቸው ግለሰቦች መንግስትን በተዘዋዋሪ ለማዘዝ መፈለጋቸውን ሲያመላክት በሌላ መልኩም አዲስ ቅኝ አገዛዝ ነው ሲሉ አክለዋል።
በሁሉም የድርድህ ሃሳቦች ዙሪያ መግባባት ላይ አለመደረሱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የሰላም ስምምነቱን ተቃዋሚዎች ሲፈርሙት ፕ/ት ሳልቫ ኪር የሁለት ሳምንት እድሜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። አሜሪካ ፕሬዚዳንቱ ስምምነቱን በተባለው ጊዜ ካልፈረሙ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ስትል አስጠንቅቃለች።

በእስር ላይ የሚገኙት የመኢአድ አመራሮች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የመኢአድ ፓርቲ የአመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።

ወጣት ተስፋየ ታሪኩ፣ ቀድም ብሎ በእስር ቤት ውስጥ እየተደበደቡ መሆኑን ለፍርድ ቤት ማመልከቱን ተከትሎ ፣ ፖሊሶች ዘቅዝቀው በጠመንጃው ሳንጃ በሽፋኑ ጀርባውን ደብድበውታል፣ እጁና እግሮቹም ተጎድተዋል። ተስፋየን ፍርድ ቤት አካባቢ እንዳገኘውና መደብደቡን እንደነገረው የገለጸው የመኢዴፓ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፣ መላው ሰውነቱ ላይ የሚታየው ነገር ጥሩ አይደለም ብሎአል ። ተስፋየ ተክላይ የሚባል የማረሚያቤቱ ሃላፊ እንዲደበደብ ትእዛዝ መስጠቱንም ተናግሯል።
ሌላው የአመራር አባል አብርሃም ጌጡም እንደሁ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት፣ ለ4 ቀናት ያክል ራሱን ስቶ ነበር። ግራ ጆሮው በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን፣ ለመንቀሰቀስ አለመቻሉንም የቅርብ ዘመዶቹ ገልጸዋል። ቤተሰቦቹ አብርሃምን ለመጎብኘት ላለፉት 2 ወራት ሙከራ ቢያደርጉም ሊሳካላቸው አልቻለም። አብርሃም ፍርድ ቤት ይቅረብ አይቅረብም ለማወቅ አለማቻላቸውን የአለም ህዝብ እንዲያውቅላቸውና ግፊት እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
በእስር ቤት ያሉት አመራሮች ህለውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ዳኞች ግን፣ ይህን እኛን አይመለከተንም ከማለት ውጪ ይህ ነው የሚል መፍትሄ ሊሰጡ አልቻሉም።

የሙያ ብቃት ምዘና በአመለካከትና ክህሎት ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ተጠቆመ፡፡

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ ሃገሪቱ በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የታሰበለትን ሃገራዊ ፋይዳ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ የሽዋስ ተናገሩ፡፡

ዳይሬክተሩ በክልሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተካሄደው ውይይት ለተሳታፊዎች እንደገለጹት በአመለካከትና ክህሎት ዙሪያ ሰፊ ክፍተት አለ ብለዋል።
መዛኝ የኤጀንሲውን ሰራተኞች በየጊዜው ለምዘና ለመላክ የተለያዬ ማባበያ በመቀበልና የጥቅም ትስስር በመፍጠር በተደጋጋሚ የተወሰኑትን በመላክ በተደጋጋሚ ተጠቃሚ ማድረግ በፈጻሚው መስሪያ ቤት በኩል የሚታይ ክፍተት እንደሆነ ዳይሬክተሩ ናግረዋል፡፡ በተመዛኞች በኩልም ታይቷል በማለት የሚገልጹት ሃላፊ፣ ሰልጣኞች በብቃታቸውና ሙያቸው ብቁ በመሆን ተገቢውን ማስረጃ ማግኘት ሲገባቸው ገንዘብ በመስጠት፣በዝምድናና ጾታዊ ግንኙነት በመፈጸም ያልተገባ ማስረጃ ለማግኘት የሚደረገው ጥረት በስፋት ይታይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህም ሆነ ከዚያ የሚታዩ የስነ ምግባር ችግሮች እንዳሉ የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፣ በስርአቱ ላይ የሚታዩ የስነምግባር ችግሮች በየደረጃውና በየፈጻሚው አካል ላይ ከመታየት አልፎ አገልግሎቱን በሚያገኙ ሰልጣኞች ላይም አሻራውን በመጣል ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው ክህሎት የሌላቸው ተመዛኞች መስፈርቱን አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለማግኘት የሚያደርጉት ህገወጥ አካሄድ በአገልግሎት ሰጪና በአምራች ደርጅቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያመጣ ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የገዢው መንግስት አመራሮች ድጋፍ እና የውስጥ ለውስጥ የባለቤትነት ድርሻ እንዳለበት ከሚታሙት የሙያ ኮሌጆች በየጊዜው የሚመረቁ ተማሪዎች እስከ ሶስት ጊዜ ተመዝነው ማለፍ የሚሳናቸው መሆኑ የትምህር ቤቶችን የማስተማር ብቃት ማነስ ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የጅምላ ግድያ በመንግስት ሃይሎች እየፈጸመ ነው ተባለ

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007)
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2007 የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ምሬት በሰላማዊ ሰልፍ የገለጹ ሲሆን፣ በአካባቢው ተሰማርቶ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ በከፈተው ተኩስ 12 ሰዎች ሲገደሉ፣ 56 ሰዎች ቆስለዋል። 5ቱ ደግሞ በእስር ቤት ተመርዘው ሞተዋል።
ከሟቾቹ ውስጥ አባትና ልጅ እንዲሁም ወንድማማቾች እንደሚገኙበት አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ በዝርዝር ገልጸዋል።
ህዝብ ላይ በሚደረገው የሃይል እርምጃ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ወቅትም መታየቱን የገለጹት የቤሕነን ሊቀመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ፣ በወቅቱ 2 ሰዎች መገደላቸውን፣ የራሳቸውን አባት ጨምሮ በርካታ አዛውንቶች የተካተቱበት 54 ሰዎች መታሰራቸውንን ገልጸዋል።
80 አመት ያለፋቸው የእርሳቸው አባት ጨምሮ ለ 54ቱ ሰዎች መታሰርና አሁንም ድረስ በእስር ቤት መቆየት ምክንያት የሆነው በምርጫ ወቅት ህዝብ የክልሉን ገዢ ፓርቲ እንዳይመርጥና በምርጫው እንዳይሳተፍ ተሳትፋችኋል የሚል እንደሆነም ተመልክቷል።
አርብ እለት የተካሄደው ግድያ የዚያ ቀጣይ እንደሆነ የገለጹት የቤሕነን ሊቀመንበር፣ የተጠቀሰው የሟቾች ቁጥር የታወቀውና በስም የተረጋገጠው እንጂ ከዚያ የበለጠ ሰው ሊሞት እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የቆሰሉት 56 ሰዎች በመንጌ ወረዳ በአሶሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።
በቤኒሻንጉል ክልል መንጌ ወረዳ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ያረጋገጡ ሲሆን በመንግስት ወገን የተሰጠ መግለጫ የለም።

የአርበኞች ግንቦት 7 ቃልን ወደ ተግባር የማሸጋገር እንቅስቅሴ ያሸበረው ወያኔን ብቻ አለመሆኑን ከተቃውሞው ጎራ ከሚ ሰማው የተቀዋሚ ተቀዋሚዎች ጩኸት እያየን ነው፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ቃልን ወደ ተግባር የማሸጋገር እንቅስቅሴ ያሸበረው ወያኔን ብቻ አለመሆኑን ከተቃውሞው ጎራ ከሚሰማው የተቀዋሚ ተቀዋሚዎች ጩኸት እያየን ነው፡፡ ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ አንዲሉ ይህ ሰሞነኛ ጩኸት የተረሳ እንዲታወስ የተተወ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኖ የአንዳንዶቹ ጯሂዎች የትናንት ማንነት ድብቅ ዓላማና ፍላጎት ጭምር ጸሀይ እንዲሞቀው እየተደረገ ነው፡፡ የማለባባስ አጉል ባህላችንን ተራምደው የይሉኝታ ገመዳችንን በጥሰው ስም እየጠቀሱ መረጃና ማስረጃ እያጠቀሱ አካፋን አካፋ ለማለት ለደፈሩ ወገኖቼ ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ፡፡ እያለባበስን አርባ አመት አልቅሰናልና በቃ ማለት ይኖርብናል፡፡
አደባባይ ወጥተው የሚጮኹትም ሆኑ ከኋላ ሆነው የሚገፉት የየግል ፍላጎታቸውም ሆነ አንድ የሚያደርጋቸው ምክንያት ምንነትና አንዴትነት በተለያዩ ሰዎች ተጽፋል፡፡ እውነት ናቸውና መስማማቴን እየገለጽሁ ያልተገለጸ የመሰለኝን ልጨምር፡

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር በመካሄድ ላይ ነው

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ድርድር፣ ፕ/ት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ተገኝተዋል። የድርድሩ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ሲሆን፣ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ፊርማቸውን የማያኖሩ ከሆነ ማእቀብ ይጠብቃቸዋል ተብሎአል።

የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድርድሩን በተመለከተ የሚጋጩ መረጃዎችን እየለቀቁ ነው። የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ ድርድሩ ሳይጠናቅ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በአዋሳ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ተሰማ

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን በላከው ሪፖርት በከተማ ውስጥ ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ሆነ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ ፣ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል።

በርካታ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ቀኑን ሙሉ በየማደያዎች ተሰልፈው የታዩ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የታየው የዋጋ ጭማሪ ህዝቡን ለምሬት ዳርጎታል። በባህርዳርም እንዲሁ በቅርቡ ተመሳሳይ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል።

አንድ ሻንጣ ሙሉ ፓውንድ የተሸከመ ወያኔለንደን ላይ በቁጥጥር ስር ዋለ

( ኢሳት ዜና)
ወደ 150 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በሻንጣ ጠርቆ ለንደን የገባ የሀገራችን ዘራፊ የወያኔ ባልደረባ በእንግሊዝ ፖሊሶች ክትትል እጅ ከፈጅ ተያዘ።ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል።
ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ፣ ግለሰቡ ” ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጻል። ይሁን እንጅ ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ? ” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሜ ይቀርባል።

Monday, August 17, 2015

ወያኔ የሚመራዉ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በሁለት የሰራዊቱ ከፍተኛ አባላት ላይ እርምጃ ወሰደ

በተልይም ለአርበኞች ግንቦት 7 መረጃ አቀብላችኍል የተባሉት እነዚህ ሁለት ወታደሮች በሰሜኑ እዝ ዉስጥ የተካተቱና የ 24 ተኛ ክፍ ለ ጦርን በመረጃ ፍሰት ምክንያት በማስጠቃት እና የሜካናይዝዱን እንዲሁም የእግረኛዉን አስተላለፍ የማጥቃትና የአቀማመጥ ወታደራዊ ዲዛኖችን ወይም ጥብቅ የምህንድስና የጦር ስልችን ለጠላት አሳልፋችሁ ሰጥታችኍል.በሚል ሰበብ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ የወሰነዉ የሰሜኑ እዝ የወያኔ ወታደራዊ ጊዜያዊ ፍርድ ቤት መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል. እነዚህ ሁለት በኮረኔልነት የሚያገለግሉ ለጊዜዉ ስማቸዉ ያልደረሰን ነገር ግን አንድ የአማራና አንድ የደቡብ ህዝቦች ተወላጅ የሆኑት ኢትዮጵያዊ ወገኖች የወያኔ ሰራዊት አባላቶች መቀጣጫ ይሆኑ ዘንድ አስቸጋሪና ተጠርጣሪ በተባሉ ሰራዊቱ ፊት ተረሽነዋል.

20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተከሰሱ

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤት በቅርቡ ከፍተኛ ቅጣት የጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ የጠየቁ 20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ቀስቅሰዋል በሚል በ14ኛ ወንከል ችሎት የተከሰሱት ከድር መሃመድ፣ ነዚፍ ተማም፣ ካሊድ መሃመድ፣ ፉአድ አብዱልቃድር፣ ኢብራሂም ካሚል፣ አብዱ ጁባር፣ ሁሴን አህመድ፣ ሃሚድ ሙሃመድ፣ ቶፊቅ ሚስባህ፣ ዑስማን አብዱ፣ ሙሃመድ ኑሪ፣ አብዱልሃፊዝ ሺፋ፣ ዳርሰማ ሶሪ፣ ፍጹም ቸርነት፣ ሃሮን ሃይረዲን፣ ሸሃቡይን ኑረዲን፣ አያትል ኩበራ፣ ሃሺም አብደላ፣ ሙጂብ አሚኖ እና መሃመድ ከማል መሆናቸውን የስርአቱ ዳጋፊ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ግለሰቦቹ ከአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ እና ወራቤ ከተሞች መያዛቸው ተዘግቧል። ግለሰቦቹ በተጠቀሱት ከተሞችም የሌሊቱን ክፍለ ጊዜ ተጠቅመው የአመጽ ወረቀቶች መበተናቸው በክሱ ተመልክቷል።
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የግድግዳ ላይ ጽሁፎች ተጽፈው አድረዋል።
ባቡር ጣቢያን ጨምሮ በእግረኛ መንገዶች እና በስልክ እንጨቶች ላይም መፈክሮች በብዛት ታይተዋል፡፡ ተጽፈው ካደሩት ከመፈክሮች መካካል የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ ነጻነት እንፈልጋለን፣ በአምባገነኖች ላይ ተነሱ፣ ፍትህ ለታሰሩት፣ አሸባሪው ፍርድ ቤት ፍርድ ቤት ይቀረብ፣ ፍትህ ለሙስሊሞች የሚሉት ይገኙበታል።

Sunday, August 16, 2015

የወልቃይትን መሬት በተመለከተ በብአዴን አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል

ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ህዝብ መሬት በግፍ እየተቀማ ለትግራይ ነዋሪዎች ከትግራይ ህዝብም ለህወሀት ደጋፊዎች መከፋፈሉ ይታወሳል ይህንን ተከትሎ ላለፉት በርካታ አመታት የራያ፣ የሁመራ እና የወልቃይት ህዝብ ለስደት እና ለጥፋት የተዳረገ ሲሆን ከሰሞኑም የትግራይ ክልልን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት ተቃውሞ ያሰሙ የክልሉ ነዋሪዎች ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ የአካባቢውን ህዝብ ለማነጋገር ወደስፍራው አቅንተው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ድርሶባቸው ወደባህርዳር መመለሳቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች እና የክልሉ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ ባህር ዳር የክልሉ መስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ስብሰባው ባለመስማማት እስከ 6፡30 ከተካሄደ በኋላ ተሰብሳቢው የተባለው መሬት የአማራ መሬት ነው የሚል አዝማሚያ በማሳየቱ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገቡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከምሳ በኋላ ስብሰባው ሲጀመር ከፌዴራል መንግስት መመሪያ መምጣቱን ተናግረው የሚቀጥለው ቅዳሜ ጥር 2 በአቶ አዲሱ ለገሰ እና በአቶ በረከት ስምኦን ሰብሳቢነት ስብሰባው ከእንደገና እንደሚካሄድ ተናግረው ስብሰባውን በትነውታል።
ይህንን ዜና ከባህር ዳር ያደረሰኝ ግለሰብ እንዳረጋገጠልኝ ከሆነ የወልቃይት መሬት ጉዳይ የክልሉን ካድሬ ቁጭት ውስጥ እንደከተተው የታወቀ ሲሆን ቅዳሜ የሚፈጠረውን ጉዳይ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።