Thursday, February 4, 2016

የጋምቤላ ኒሎትአንድነት ሰራዊት ንቅናቄ የህወሃት ኢሕአዴግ መንግስት በክልሉ የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልበአስቸኳይ እንዲያቆም ጠየቀ።

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው  ለኢሳት በላከው  መግለጫ ሕወሃት  መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ የአኝዋክ ብሔር አባላት ላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን አስታጥቆ የሚፈጽመውን ግድያ
በአጽንዎት በመኮነን ፤ አገዛዙ ድርጊቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም ሲል  ጠይቋል።



የህወሀት -ኢህአዴግ ታጣቂዎች በዶ/ር ሪክ ማቻር ከሚመራው የኑዌር ተወላጆች ከሚበዙበት
የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚፓርቲ ጋር  በማበር በክልሉ በሚኖሩ የአኝዋክ ብሔረሰብ አባላትና በሌሎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ የግድያ፣አካል ማጉደል፣የእስራት፣የማፈናቀልና  የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን
እየተፈጸሙ መሆናቸውን ንቅናቄው  አብራርቷል።

እንደ ንቅናቄው መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት  ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ እየሆኑ መጥተዋል።

ንቅናቄው ኢትዮጵያዊያን አኝዋኮችም ሆኑ የደቡብ ሱዳን አኝዋኮች ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየተፈጸባቸው መሆኑንና  በሁለቱምአገራት ውስጥ የመኖር ዋስትና ማጣታቸውን  የገለጸው  ንቅናቄው፣  <<ይህን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዋናነት የሚመሩትና የሚያቀናብሩት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ከደቡብ ሱዳኑ ዶር ሪክ ማርቻር  ሰራዊት ጋር በማበር ነው" ብሏል።

ንቅናቄው  "ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ነባር አኝዋኮችን ከቀያቸው አፈናቅሎ
 ዝርያቸውን ለማጥፋት በሕወሃትመራሹ  መንግስት  ታጣቂዎችና በደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የሚካሄደውን  ይህን ግፍና ስቃይ መላውኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያወግዝ "ሲል ጥሪ አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment