Monday, February 8, 2016

በጉጂ ዞን ህዝቡ "በቃኝ" በማለት ትግሉን እንደቀጠለ ነው

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ የፌደራል ፖሊስ አባላት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አካባቢውን ተቆጣጥረውታል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችና አዛውንቶች ታስረዋል። ይሁን እንጅ "ህዝቡ የጎበዝ አለቃ መርጦ ትግሉን በጥንቃቄ እና በወኔ እያካሄደ ነው። ትግሉ መቆሚያ የለውም" በማለት በተቃውሞው ላይ የሚሳተፉ አንድ ግለሰብ ለኢሳት ተናግረዋል።
የጉጂ ህዝብ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትና የኢኮኖሚ ነው የሚሉት ግለሰቡ፣ ባለፉት አመታት ችግሮቻቸው እንደሚፈቱ በርካታ ቃሎች ቢገቡላቸውም፣ አንዱም ተፈጻሚ አልሆነም።
የሼክ አላሙዲን ሚድሮክ ወርቅ የተቃውሞው ዋነኛ ኢላማ ሆኗል። የአካባቢው ህዝብ በድህነት እየተሰቃዬ፣ ባለሃብቱ የአካባቢውን ሃብት መዝረፋቸው ፍትሃዊ ባለመሆኑ፣ ከእን...ግዲህ የአላሙዲንን ኩባንያ በሻኪሶ ልናየው አንፈልግም ሲሉም ግለሰቡ ያክላሉ።
የኢህአዴግ መንግስት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን አሰማርቷል። አንዱ ወረዳ ከሌላው ጋር እንዳይገናኝ መንገዶችን ዘግቷል፤ የስልክ መስመሮችን በየጊዜው ያጠፋል፣ መብራት ያቋርጧል፤ ከዚህም አልፎ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ለጥያቄያቸው አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ይሁን እንጅ ህዝቡ የኢህአዴግን ቃል አምኖ የሚቀበል አልሆነም ፣ እንደ ገልሰቡ ገለፃ።
በዛሬው ተቃውሞ የመንግስት ስራተኛው ሰይቀር መውጣቱንም ግልሰቡ ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment