Monday, February 8, 2016

እነ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በጋምቤላ የሚመሩት የሽምግልና ጥረት እስካሁን አልተሳካም

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮች እና የአርብቶአደር አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃንን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ የመከላከያ አዛዡ ጄ/ል ሳሞራ የኑስና ሌሎች ወታደራዊ አዛዦች እንዲሁም የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋምቤላ ገብተው ኑዌሮችና አኝዋኮችን ለማስታረቅ እንቅስቃሴ እያደረጉ ቢሆንም፣ ሽምግልናው ግን እስካሁን ውጤት አላመጣም። የአኝዋክ ሰርቫይቫል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኒካው ኦቻላ፣ መንግስት የሽምግልና ጥረት የጀመረ በመምሰል ፣ ችግሩ እንዲባባስ የሚያደርገው ድርጊት ከግጭቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት የሚያመላክት ነው ይላሉ።
በክልሉ በየየቀኑ ሰዎች እየሞቱ ሲሆን፣ በኢታንግ ቅዳሜ እለት 2 አኝዋኮች ተገድ...ለዋል። ባለፈው አርብ ደግሞ ከፒዩንዶ የስደተኞች ካምፕ የወጡ ኑዌሮች 3 የአኝዋክ ሴቶችን ገድለዋል። ከሟቾች መካከል የ7 አመት ሴት ልጅ ትገኝበታለች። በጋምቤላ ከተማም እንዲሁ አንድ የ45 አመት ሴት ተገድላለች።
ከደቡብ ሱዳን መጥተው በጋምቤላ የሚኖሩ ስደተኞችን በአንድ ላይ ሰብስበው ወደ ድንበር እያጓጓዙዋቸው ነው።
አቶ ኒካው እንደሚሉት፣ አንዋኮች ምንም ችግር እንደሌለባቸውና ችግሩ በንዌሮች እንደተጀመረ በስብሰባ ላይ ቢነገርም እስካሁን ይህ ነው የሚባል ምላሽ አልተሰጠም። የታጠቁ ንዌሮች በማንኛውም ሰአት ጥቃት እየፈጸሙ ነው፡፡ በአኝዋኮች በኩል ደግሞ ይህን የሚያደርጉት ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሪክ ማቻር ወታደሮች ሆነው ሳለ ለምን እርምጃ አይወስድም በማለት እየጠቁ መሆኑን አክለዋል። እርቅ ይደረጋል ቢባልም የመንግስት እጅ እንዳለበት የሚያመላክቱ ጉዳዮች መኖራቸውን አቶ ኒካው ገልጸዋል።
ከ30 በላይ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን የጦር አዛዦች በ መንግስት ቁጥጥር ስር ሆነው የተወሰኑት ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።

No comments:

Post a Comment