Monday, October 22, 2018

የአቶ ጌታቸው አሰፋ ሃብት እንዲታገድና የዝውውር መብታቸው እንዲገደብ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011) የቀድሞ የደህንነት መስሪያ ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሃብታቸው እንዲታገድና የዝውውር መብታቸው እንዲገደብ አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ ማን ጠየቁ።

የኮሎራዶው ኮንግረስ ማን ማይክ ኮፍ ማን የኤች አር 128 የውሳኔ ሀሳብን ጠቅሰው በአቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ለሁለት የአሜሪካ ሚኒስትሮች የጻፉትን ደብዳቤ ዛሬ አስገብተዋል።
ኮንግረስ ማን ኮፍ ማን አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡና በውጭ ያላቸው ሃብት እንዲታገድ መጠየቃቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Thursday, October 18, 2018

ሁለት የሰብዓዊ መብትና የህግ ባለሙያዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011)የአዲስ አበባ ወጣቶችን በማደራጀት ክስ የተመሰረተባቸው ሁለት የሰብዓዊ መብትና የህግ ባለሙያዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና ሚካዔል መላከ አዲስ አበባ ከሌላ አካባቢ በመጣ ሰው አትተዳደርም የሚል ቅስቀሳ በማድረግና የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሲያደራጁ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
የፖሊስ ክስ ላይ ለዚህ እንቅስቃሴ የሚረዳ ግንኙነት ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር መደረጉን የሚያመለክት ነው።
የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማደራጀት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ሌሎች ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ሀሮምሳ በሚል የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የአዲስ አበባ ወጣቶችን የማደራጀት እንቅስቃሴ በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።
የህግ ባለሙያና ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሚካዔል መላከ የተያዙት ትላንት ነበር።
ጠበቃ ሄኖክ ትላንት ቢሮ ውስጥ እንዳለ በፖሊስ መያዙን የሚገልጹት የኢሳት ምንጮች በቢሮው የሚጠቀምባቸው ኮምፒውተሮችና ሌሎች እቃዎች ተበርብረው መወሰዳቸው ታውቋል።
ዛሬ የአራዳ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት ጠበቃ ሄኖክና ሚካዔል ላይ የተከፈተውን ክስ ማዳመጡን ነው ለማወቅ የተቻለው።
በፖሊስ የቀረበው ክስ የአዲስ አበባን ወጣቶች ለማደራጀት ተንቀሳቅሳችኋል የሚል ነው።
ፖሊስ በክስ መዝገቡ ጠበቃ ሄኖክና ሚካዔል መላከ፡ አዲስ አበባን ከሌላ ክልል የመጣ ከንቲባ ሊመራት አይገባም የሚል አቋም ይዘው ሲቀሰቅሱ ነበር ሲል አመልክቷል።
በተጨማሪም የፍልስጤም ወዳጅነት ማህበር ማቋቋም የሚል የፖሊስ ክስ እንደሚገኝበትም ጉዳዩን የተከታተሉ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር በመገናኘት የወዳጅነት ማህበር ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋል ነው የሚለው ፖሊስ።
ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ በተለይ በህወሃት አገዛዝ ዘመን በግፍ ለሚታሰሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች በነጻ ጥብቅና በመቆም የሚታወቅ ነው።
በቅርቡም ከአዲስ አበባ ግጭት ጋር በተያያዘ ለታሰሩት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አቀባበል ኮሚቴ አባላት ጠበቃ በመሆን ቆሞላቸዋል።
ለአሁኑ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለሆኑትና በህወሀት አገዛዝ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርገው ለነበሩት ለአቶ ታዬ ደንደአም ጠበቃ በመሆን ተሟግቶላቸዋል።
በተመሳሳይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሚካዔል መላከም በግፍ ለሚታሰሩ ሰዎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረግ የሚታወቅ ነው።

የስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊየን ተጠጋ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊየን መጠጋቱን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከጥር እስከ ነሐሴ ብቻ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ከ36 ሺ በላይ መሆኑን የገለጸው ይህው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር መከፈቱን ተከትሎም የስደተኞቹ ቁጥር መጨመሩን አመልክቷል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ ነሐሴ 31/2018 በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር 905ሺ 831 መድረሱን የገለጸው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የደቡብ ሱዳን ተወላጆች መሆናቸውን አመልክቷል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች 422ሺ 240 ሲሆኑ በብዛት በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት በቁጥር 257ሺ 283 የሚሆኑት ሶማሊያውያን ናቸው።

ለውጡን ለማደናቀፍ የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተመንግስት ተልከዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) የታጠቁ ወታደሮችን ወደ ቤተመንግስት የላኩት አካላት ለውጡን ለማደናቀፍ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
በወቅቱ ለድርጊቱ የጥንቃቄ ምላሽ ባይሰጥ ኖሮ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ የሚከታት ነበር ሲሉም ገልጸዋል።
ሆኖም ሁሉም ወደ ቤተመንግስት የተንቀሳቀሱት ወታደሮች ይህንን ግንዛቤ ጨብጠው ነበር ለማለት እንደሚያስቸግርም አመልክተዋል።
መስከረም 30 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ቁጥራቸው 250 የሚሆን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነትጥቃቸው ወደ ቤተመንግስት ያደረጉት ጉዞ አብይ መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በወቅቱ ከሰራዊቱ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የሰራዊቱ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ አግባብ እንደነበር በመግለጽ ጥያቄውን ያቀረቡበት መንገድ ግን ሕገ ወጥ ነው ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
የሰራዊቱ አባላት ከጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ሰአረ መኮንንና ከሌሎች የሰራዊቱ አመራሮች ጋር ከተወያዩ በኋላ ድርጊቱን ከበስተጀርባ የመሩና ያቀነባበሩ የሰራዊቱ አዛዦች መታሰራቸውን ጄኔራል ሰአረ መኮንን በሳምንቱ መጨረሻ አስታውቀዋል።
ከታሰሩት የሰራዊቱ አዛዦች ጀርባ ግለሰብም ይሁን ቡድን ካለ ምርመራ መቀጠሉንም አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) ባለፈው ወር መጀመሪያ በጅምላ ታፍሰው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ተወስደው የነበሩ ከ1ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ መለቀቃቸው ተገለጸ።
ለወጣቶቹ ስልጠና ተሰጥቶ መለቀቃቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማጓጓዝ ስራ መጀመሩን አስታውቋል
ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳውና ህገመንግስታዊ መብቶችን የጣሰ ነው የተባለው የአዲስ አበባ ወጣቶች እስርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያለአግባብ የታሰሩ ከነበሩም ለለውጡ የከፈሉት መስዋዕትነት አድርገው እንዲመለከቱት ጠይቀዋል።
ወጣቶቹ ዛሬ ሲለቀቁ ሰላም ለሁላችንም ስለሆነች እንጠብቃት የሚል ጽሁፍ የታተመበት ቲሸርት እንዲለብሱ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ከአንድ ወር በላይ በአደገኛ ሁኔታ በጦላይ የወታደራዊ ካምፕ ታፍሰው የተወሰዱት የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ መፈታታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
በኮሚሽኑ መግለጫ ወጣቶቹ ህገመንግስታዊና የህግ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ መለቀቃቸው ገልጿል።

Wednesday, October 17, 2018

በህገወጥ መንገድ የገባና 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እቃ ተያዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011) የደህንነት ካሜራዎችን ጨምሮ ለዲፕሎማቲክ አገልግሎት በሚል ሰበብ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እቃ መያዙ ተነገረ።

የገቢዎች ሚኒስቴር  እንዳስታወቀው በሁለት ስማቸው ባልተጠቀሰ ኤምባሲዎች እና በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ስም በህገወጥ መንገድ ለዲፕሎማቲክ አገልግሎት በሚል የገቡ እቃዎች ተይዘዋል።

Ethiopia: OLF disarming residents in East and West Wollega

ESAT News (October 17, 2017)
Reports reaching ESAT say combatants of the Oromo Liberation Front (OLF), a separatist ethnic front, has been disarming non-Oromo residents in East and West Wollega.
Resident who spoke to ESAT said the OLF soldiers had confiscated their weapons that they said have owned legally. The residents said the administration in West Wollega has been taken over by the OLF soldiers and the Qeerroo, a vigilante youth network in the Oromo region.
Some residents flee their villages fearing attack by the OLF, according to information obtained by ESAT.
ESAT attempted to reach OLF representative in North America for comment, but to no avail.
Dawud Ibsaa, the leader of the separatist group admits in an interview with the VOA last week that he has armed soldiers in the south and west of the Oromo region although he did not say how many.

ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአርጎባ ብሄር ተወላጆች ከተጠለሉበት ትምህርት ቤት ተባረሩ። ለዜጎች መፈናቀል የወረዳ መስተዳሮች እጅ አለበት ተባለ።

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ቦሌ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በማንነት ላይ ባነጣጠሩ ጥቃቶች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ቁጥራቸው ከ146 በላይ የሚሆኑ የአርጎባ ብሔር ተወላጆች አስታዋሽ አጥተን ለችግር ተዳርገናል አሉ። እስካሁንም በመንግስት በኩል በቂ ዕርዳታ እንዳልተደረገላቸው ጉዳተኞቹ ይናገራሉ። ተፈናቃዮቹ በጊዜያዊ መጠለያነት ተጠግተው ይኖሩበት ከነበረው የመልካ ጅሎ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ እንዲወጡም ተደርገው ቀይ መስቀል በሰጣቸው ጊዜያዊ መጠለያ ድንኳን ውስጥ ተጠልለዋል። ቀይ መስቀል ብርድ ልብስ፣ ውሃ መጠጫ እና አንድ ከረጭት ዱቄት ብቻ የረዳቸው ሲሆን የወረዳው መስተዳድር ለአንድ ቤተሰብ በነፍስ ወከፍ አንድ ሽህ ብር ብቻ ከመርዳት ውጪ ወደ ቀድሞ ይዞታቸው እንዲመለሱም ሆነ መልሶ ለማቋቋም ያደረገላቸው እገዛ የለም። ቤተሰቦቻቸው ከሚያደርጉላቸው እገዛ በተጨማሪ የአርጎባ ህዝቦች ድርጅት የ100 ሺህ ብር እርዳታ የለገሰ ሲሆን፤ የምንጃር ወረዳ ወጣቶች በበኩላቸው ከጎናቸው በመቆም አስፈላጊውን እገዛ አድርገውላቸዋል። መንግስት መጠለያ ቦታ እንደሚሰጣቸው ቃል ቢገባላቸውም ማረፊያ መጠለያን ጨምሮ ከመኖሪያቸው ባዶ እጃቸውን በመውጣታቸው የአልባሳት፣ የቁሳቁስ እና ምግም አላገኙም። በተለይም ሕጻናት ልጆች ያሏቸው ወላጆች ለተጨማሪ ጉዳቶች ተጋላጭ ሆነዋል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ለችግራቸው በአፋጣኝ እልባት እንዲሰጣቸው ተማጽኖ አሰምተዋል። በአርሲ ቦሌ ለጠፈጠረው ችግሮች በአገር ሽማግሌዎች በኩል የማስታረቅ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በምስራቅ ሸዋ በኩል ግን እስካሁን አልተደረገም። ተፈናቃዮቹን ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም ሥጋት

በአፋር ክልል የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ዜጎች በልዩ ሃይል አባላት ጥቃት ደረሰባቸው

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን አንግበው በሰመራ ከተማ ወደ አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ 8 ሰዎች በጥይት ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል መግባታቸውን ነዋሪዎች በስልክ ለኢሳት ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት ገብቶ ግጭቱን ማስቆሙም ታውቋል። የአፋር ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ሊለወጥ ባለመቻሉ በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ችግር እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ አልሄደም። የአፋር ዱከሂና ወጣቶች ክንፍ አባል የሆነው ሙሳ ሂኮ የተንዳሆ እና የቀሰም ቀበና የስኳር ፋብሪካዎች ሲተከሉ ቃል የተገባላቸውን አገልግሎት አለማግኘታቸውን ገልጿል። ወጣት ሙሳ ጥያቄዎቻችን ባለመመለሱ ኢትዮጵያዊነታችንን እየተጠራጠርን ነው ይላሉ። መንግስት የወጣቱን ድምጽ መስማትና ለጥያቄው አፋጣኝ መልስ መስጠት እንዳለበት በጅጅጋ የፖለቲካል ሳይንስና አለማቀፍ ግንኙነት መምህር የሆነው ሙሳ አደም ገልጿል፡፡ ወጣቶች ባቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ዙሪያ የአፋር ክልላዊ መንግስት ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ በሚቀጥለው ዘገባችን ይዘን እንቀርባለን።

Tuesday, October 16, 2018

የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲፈቱ የተከፈተውን ዘመቻ ተከትሎ ሊፈቱ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 6/2011)በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ በስቃይ ላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲፈቱ የተከፈተውን ዘመቻ ተከትሎ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ እንደሚፈቱ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደግፌ በዲ ለቢቢሲ አማርኛው እንደገለጹት ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑት ወጣቶች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይለቀቃሉ።
ኮሚሽነሩ ወጣቶቹ የታሰሩት በጎዳና ላይ ንብረት ሲያወድሙና ሁከት ሲፈጥሩ ነው ብለዋል።
ከአንድ ወር በላይ ሆናቸው። ክስ አልተመሰረተባቸውም። ፍርድ ቤትም አልቀረቡም። በጅምላ ታፈሰው፡ በየክፍለከተማው ፖሊስ ጣቢያ ለቀናት ቆይተው፡ በሰንዳፋ እንዲሰባሰቡ ከተደረጉ በኋላ ወዶ ጦላይ ተወሰዱ።

የካቢኔ አባላት ሹመት ጸደቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 6/2011)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 16 የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ።
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አቅራቢነት ሹመታቸው የጸደቀው ሚኒስትሮች ከኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ሲሆን ከተለመደው አሰራር ብዙም የተለወጠ ነገር እንዳልታየበትም አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
አራት ነባር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከነሚኒስትርነታቸው በቀጠሉበት በአዲሱ ካቢኔ አዲስ የሰላም ሚኒስቴር በሚል ለተቋቋመው ተቋምም ሚኒስትር ተመድቦለታል።
28 የነበሩ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን ወደ 20 በሰበሰበው አዲሱ አወቃቀር የሰላም ሚኒስቴር በሚል ለተሰየመው ተቋም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በሚኒስትርነት ተሹመዋል።

በምዕራብ ወለጋ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ታጣቂዎች ከቄሮና አባገዳዎች ጋር በመሆን በማስተዳደር ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

 ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም ) ኦነግ በሰየ ወረዳ ወየ ቡቡካ በሚባለው ቀበሌ ከጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎችን እንዲሁም በአካባቢው ከ32 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ የሰፈሩትን የአማራ ተወላጆች መንግስት ፈቅዶላቸው የያዙትን የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ የወያኔ ታጣቀዊዎች ናችሁ በማለት ትጥቅ እያስፈታ መውሰዱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኦነግን ጥቃት በመፍራት ጫካ የገቡ ሰዎች መኖራቸውንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። አካባቢውን የኦነግ ታጣቂዎች፣ ቄሮዎችና አባ ገዳዎች በጋራ ተመራርጠው እያስተዳደሩት ሲሆን፣ የመንግስት አካላት በአካባቢው አለመኖራቸውን ተናግረዋል። መንግስት እርምጃ እንዲወስድ ለኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ቢያመለክቱም ጠብቁ የሚል መልስ ከማግኘት የዘለለ ምላሽ እንዳላገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Monday, October 15, 2018

በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ፖሊስ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያጠናቅቅ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 5/2011)የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ባልደረባ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ፖሊስ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያጠናቅቅ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ቀጠሮ ሰጠ ፡፡
ፖሊስ ችሎቱ በፈቀደለት 10 ቀናት የሰው ምስክር መቀበሉን ብሎም ከመስሪያ ቤታቸው የተገኘው ቦምብ ለምርመራ መወሰዱንና ሌሎች ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሷል፡፡
ፖሊስ የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን በተመለከተ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎትን  ለተጨማሪ የምርመራ ስራ 10 ቀናት እንዲፈቀደለት ጠይቋል፡፡
የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በቡኩላቸው በቁጥጥር ስር ከዋሉ 4 ወራት መቆጠሩንና ፖሊስ የሚጠይቃቸው የግዜ ቀጠሮዎች ተገቢነት የላቸውም በማለት ቅሬታችውን አቅርበዋል፡፡

ብርጋዴር ጄኔራል ሃይሉ ጎንፋ ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 5/2011) ብርጋዴር ጄኔራል ሃይሉ ጎንፋ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
በሳምንቱ መጨረሻ ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹና ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች የጸጥታ ከፍተኛ ሃላፊዎች ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
በምርጫ 1997 በኢትዮጵያውያን ላይ የተካሄደውን ጭፍጨፋ በመቃወምና፣የምርጫውን መጭበርበር በማውገዝ ሰራዊት ይዘው ወደ ኤርትራ የገቡት ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ሆነው በሳምንቱ መጨረሻ መሾማቸው ተሰምቷል።
ከእሳቸው ጋር በተመሳሳይ ሰራዊቱን አስከትለው ኤርትራ የገቡት ሌተናል ኮሎኔል አበበ ገረሱ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተመልክቷል።
በነሐሴ ወር 1998 ሰራዊት አስከትለው ኤርትራ የገቡትን ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች በመከተል በተመሳሳይ የመንግስትን የአፈናና የግድያ ድርጊት በማውገዝ በመስከረም 1999 ኤርትራ የገቡት ብርጋዴር ጄኔራል ሃይሉ ጎንፋ የኦሮሚያ ክልል የፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

ሰራዊቱ ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ የማሻሻያ ርምጃዎች በመውሰድ ላይ ናቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 5/2011)የኢትዮጵያ ሰራዊት ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ በየደረጃው የማሻሻያ ርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ጄኔራል ሰአረ መኮንን ገለጹ።
ወደ ቤተመንግስት የተጓዙትን የሰራዊቱን አባላት ድርጊት ጋጠወትና ጸረ ሕገ መንግስት በማለት የጠቀሱት ጄኔራል ሰአረ መኮንን ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አመራሮቹ መታሰራቸውን ገልጸዋል።
አስተማሪ የሆነ ርምጃ እንደሚወስድም ቃል ገብተዋል።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ መስከረም 30/2011 ወደ ቤተመንግስት የተንቀሳቀሱት የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት መሆናቸውን የገለጹት ጄኔራል ሰአረ መኮንን ይህው ሃይል በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ችግር ለማረጋጋት እዚያው መቆየቱን አስታውሰዋል።
አዲስ አበባና አካባቢዋ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋርም በተያያዘ ይህው ሰራዊት ግዳጅ ውስጥ መቆየቱን የገለጹት ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኮንን ያነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወደ ስድስት መቶ የሚሆኑ ሶማሊያውያን የተገደሉበት አንደኛ ዓመት ሢታሰብ ተከሳሹ በአደባባይ እንዲወገድ ተደረገ። በአዲስ አበባና በሶማሊያ ከአርባ ዓመት በኋላ በረራ የተጀመረ ሲሆን፣ በዕለቱ አልሸባብ ጥቃት ፈጽሟል።

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 05 ቀን 2011 ዓ/ም ) በሶማሊያ ታሪክ አሰቃቂውን የቦምብ ፍንዳታ በመፈጸም ስድስት መቶ ለሚጠጉ ሰላማውያን ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነው ሀሰን አዳን ይስሀቅ ትናንት የሟቾቹ አንደኛ ዓመት ሲከበር በአደባባይ እንዲወገድ ተደርጓል። ሀሰን አዳን ልክ የዛሬ ዓመት ነበር ከፍተኛ ተቀጣጣይ ቦምብ የተጠመደበት የኪራይ የጭነት መኪና እያሽከረከረ ሰው ወደሚበዛበት የሞቃዲሾ ጎዳና በመግባት ፍንዳታውን የፈጸመው። ጥቃቱን አስመልክቶ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን ባይኖርም፣ ሀሰን አዳን ቀደም ሲል የአልሸባብ ሚሊሻዎች መሪ ከመሆኑ አኳያ ከጥቃቱ ጀርባ ቡድኑ ሳይኖር እንደማይቀር ይታመናል። በፍንዳታው ውዶቻቸውን ካጡት ሶማሊያውያን መካከል የስድስት ህጻናት ልጆች እናት የሆነችው ፎዊሳ ሳላህ ኡስማን አንዷ ነች። የፎይሳ ባለቤት ወይም የስድስቱ ህጻናት አባት አስከሬን እንደሌሎቹ ሰለባዎች ሁሉ አልተገኘም።በከፍተኛው ፍንዳታ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል። ፎይሳ ውዷን ካጣች ዓመት ቢቆጠርም፣ መጽናናትን እምቢ አንዳለች ነው። ትናንት በመኖሪያ ቤቷ ተገኝተው ላነጋገሯት የቢቢሲ ጋዜጠኞች፦“አሁንም በጥልቅ ሀዘን ላይ ነኝ።ልቤ እንደተሰበረ ነው።ምንም ነገር መሥራት አልችልም” ስትል እያለቀሰች ተናግራለች። የተከሳሽ ሀሰን አዳን ይስሀቅን ጉዳይ ሲከታተል የነበረው ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም፣ ተከሳሹ በትናንትናው ዕለት -የገደላቸው ሰላማውያን የሙት ዓመታቸው

የዓዲግራት ዩንቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ተገቢውን ትምህርት ማግኘት ባለመቻላቸው ትምህርታቸውን አቋረጡ።

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 05 ቀን 2011 ዓ/ም ) በዓዲግራት ዩንቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች በተቋሙ አስተዳደር ለሚደርስባቸው አስተዳደራዊ በደሎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጊዜያት ቢጠይቁም ምላሽ ማግኘት አልቻሉም። ይህን ተከትሎ ትምህርታቸውን በተገቢው ሁኔታ መከታተል ባለመቻላቸው ለማቋረጥ መገደዳቸውንና አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠን ሲሉ ለጤና ጥበቃ ሚንስቴር በደብዳቤ አሳውቀዋል። የመማር ማስተማሩ አስመልክቶ በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳሉት የ6ኛ ዓመት ተማሪዎች ባለፉት 9 ወራት ብቻ ለ5 ወራት ከመማር ማስተማር ውጪ ነበሩ። የ5ኛ እና የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች /በበኩላቸው በተመሳሳይ ተገቢውን የመማር እድል በማጣታቸው ከተመሳሳይ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወደኋላ ቀርተዋል። ዩንቨርሲቲው በበኩሉ የአስተማሪ ስፔሻል ሃኪሞች እጥረት፣ ያሉትም ጥቂት ስፔሻሊስት ሃኪሞች የሥራ መደራረብና የደመወዝና የጥቅማጥቅም መብት አለመከበር፣ ከሌሎች ዩንቨርሲቲዎች የሚያመጣቸው የተጋባዥ መምህራን ጋር በተመሳሳይ የደመወዝና በጥቅማጥቅም ጉዳይ አለመስማማት ያስከተለው የተጋባዥ መምህራን እጥረት፣ ዩንቨርሲቲው የራሱ የሆነ የማስተማሪያ ሆስፒታል የሌለው ሲሆን የዓዲግራት ጠቅላላ ሆስፒታልም ከተማሪዎቹ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑ፣ በሆስፒታሉ በቁጥርም ይሁን በዓይነት በቂ የሆነ ታካሚዎች አለመገኘትን፣ በሆስፒታሉ በቂ የሆነ የህክምና መገልገያ እና የማስተማሪያ ቁሳቁስ አለመኖር፣ የተመደበለትን በጀት በራሱ ማንቀሳቀስ አለመቻሉን በምክንያትነት አቅርቧል። የዩንቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ የሚያቀርቡትን ጥያቄዎች ያለመቀበል፤ ወይም ከተቀበሉ በኋላ መፍትሔ ያለመስጠት፣ ለህክምና ትምህርት የሚሰጡት በጀት ማሳነስና ለችግሮቹ ትኩረት ያለመስጠትና በመጠናቸው ልክ አለመረዳትና በቸልተኝነት በማለፍ ችግሮቹ እንዲባባሱ አድርገዋል። የሕክምና ትምህርት ከፍተኛትኩረት የሚሻ የትምህርት መስክ በመሆኑ መንግስት ትኩረት በመስጠት ለጥያቄያቸው መፍትሔ እንዲሰጠን ሲሉ ለጤና ጥበቃ ሚንስቴር እና በግልባጭ ለዓዲግራት ዩንቨርስቲ ቦርድ፣ ለዓዲግራት ዩንቨርስቲ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት፣ ለዓዲግራት ዩንቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እናለ ዓዲግራት ዩንቨርስቲ ሕክምና ትምህርት ቤት በደብዳቤ አሳውቀዋል።

የቀደሞው የመረጃና ደህንነት ሰራተኛ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጠባቸው።

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 05 ቀን 2011 ዓ/ም ) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ በተዘጋጀው የድጋፍና የምስጋና ሰልፍ ወቅት የተፈጸመውን የሽብር ድርጊት አቀነባብረዋል ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጠ። ባለፈው ቀጠሮ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቤት ውስጥ የተገኘውን ቦምብ እና በመስቀል ዓደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል በማመሳከር አጠናቆ ለማቅረብ የአስር ቀናት ቀጠሮ መውሰዱ ይታወሳል። ነገርግን መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ቀናት ውስጥ የቴክኒክ ምርመራውን ማጠናቀቅ አለመቻሉን ለችሎቱ በመግለጽ ተጨማሪ የአስር ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ለችሎቱ አመልክቷል። ተጠርጣሪው አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ ለመርማሪ ፖሊስ ተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ተሰጥቶታል። የዛሬውም የመጨረሻ ቀጠሮ ተብሎ ነበር። መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቅ አይገባውም። በተጨማሪም አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የፍርድ ቤቱን ሂደት በአካል ቀርበው ሳይከታተሉ የስም ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙብኝ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድልኝ ሲሉ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የከሰሳሽ መርማሪ ፖሊስን እና የተከሳሽን ቃል ካዳመጠ በኋላ የተዛባ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ በህግ እንደሚያስጠይቅ በመግለጽ፤ ይህን በሚፈጽሙት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ብሏል። ለመርማሪ ፖሊስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ፖሊስ የጠየቀውን የአስር ቀናት ቀነ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በአማሮ ወረዳ 3 የ መከላከያ ሰራዊት አባላት በታጣቂዎች ተገደሉ

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 05 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች በሰራዊቱ አባላት ላይ ጥቃት የፈጸሙት የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው ቢሉም፣ በመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የለም። የግድያው መንስዔ ላለፉት 16 ወራት የዘለቀው በአማሮ ወረዳ የሚካሄደው በጉጂና በኮሬ ማህበረሰቦች መካከል ያለው ግጭት እንደገና በማገርሸቱ ነው። ባለፈው አርብ በስራ ላይ በነበሩ የኮሬ ተወላጆች ላይ በተፈጸመ ጥቃት አንድ የ10 አመት ታዳጊ ወጣት ሲገደል 2 ሌሎች አርሶአደሮች ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለዋል። ግጭቱ በዳኖ ቀበሌም ቀጥሎ በኮሬ በኩል አቶ ጌዲዮን ሊባ እና ኢለሙሳ አየለ የተባሉት ግለሰቦች የቆሰሉ ሲሆን፣ ግጭቱን ለማብረድ ጣልቃ በገቡት የመከላከያ አባላት ላይ በደረሰ ጥቃት 2 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወዲያውኑ ሲገደሉ፣ አንደኛው ደግሞ ቆስሎ በህክምና ላይ እያለ ህይወተሩ አልፏል። ሌላ አንድ ወታደርም በከባድ ሁኔታ ቆስሎ ሆስፒታል ተኝቷል። የመከላከያ ሰራዊት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ሁለት የታጠቁ ሃይሎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። የመከላከያ አባላቱ የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል። በቡርጂና ጉጂ ብሄረሰቦች መሃል በተደረገው የተኩስ ልውውጥም እንዲሁ በቡርጂ በኩል አንድ አርሶ አደር በከፍተኛ ሁኔታ ቆስሏል። ከአማሮ ዲላ፣ ከቡርጂ ሃገረማርያም የሚወስዱ መንገዶች ለአመት ከአራት ወር ያክል በመዘጋታቸዉ የሁለቱም ወረዳ ህዝቦች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰቃዩ ነው። የመከላከያ ኢታማዦር ሹሙ ጄ/ል ሳዕረ መኮንን ሰራዊታቸው በአካባቢው ተሰማርቶ ጸጥታ እያስከበረ እንደሚገኝና ይህ ሰራዊት ወደ ቡራዩ፣ አዲስ አበባና በሶሚሊ እና ኦሮምያ ድንበሮች አካባቢ ተልዕኮ ግዳጁን ሲወጣ እንደነበር ገልጸዋል።

Friday, October 12, 2018

በራያ ህዝብ ላይ የሚደርሱት የመብት ጥሰቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። አሁንም 23 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ናቸው።

 ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም )ካለ ሕዝብ ፈቃድ ከወሎ ክፍለሃገር ተወስዶ ወደ ትግራይ እንዲካለሉ የተደረጉት ራያዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት የሚያነሱትን የማንነት ጥያቄዎች ለማዳፈን በትግራይ ክልል የሚደርስባቸው መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በአዲሱ ዓመት የትምህርት ዘመን ህገ መንግስቱ የሰጠን መብት ይከበርልን፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን እንድንማር ይፈቀድልን ያሉ 23 ትምህርት ቤቶች በህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት እንደተዘጉ ናቸው። የእነሱን ፈለግ በመከተል ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ይዘጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። የራያን ህዝብ የማንነት ጥያቄዎች ለማዳፈን በማኅበረሰቡ ውስጥ ታዋቂ የሆኑ፤ በትግራይ ክልል ውስጥ በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ የራያ ተወላጅ የሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በመጠቀም ማንነት ጥያቄውን በትግራይ ክልል ውስጥ በማድረግ የወረዳ ጥያቄዎችንም ጭምር እንመልሳለን። የሚሉ መረጃዎችን በማሰራጨት የኅብረተሰቡን የማንነት ጥያቄ በልዩ ዞን ለማስመሰልና ጥያቄውን ለማፈን ሙከራ እየተደረገ ነው። የኅብረተሰቡ ጥያቄ በትግራይ ክልል ውስጥ የልዩ ዞንና የወረዳ ጥያቄ ሳይሆን፤ የማንነት ጥያቄው በታሪክም፣ በትውልድም፣ በስነልቦናም፣ ከምንተሳሰረው ህዝብ ጋር የመኖር ጥያቄ ነው። የልዩ ዞን በትግራይ ክልል ተመለሰ አልተመለሰ ኅብረተሰቡ በዛ አይስማማም። በምንም ዓይነት በየትኛውም አስተዳደር ቢሆን በምንም መስፈርት በየትኛውም ዓይነት የአስተዳደር እርከን ከዛ ክልል ጋር የመኖር ጥያቄ ሳይሆን ከማንነቱ ጋር ከሚተሳሰረው የወሎ ህዝብ ጋር የመቀላቀል ጥያቄ መሆኑን የራያ ሕዝብ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገዘው ሕዳሩ አስታውቀዋል።

አርበኞች ግንቦት7 በሃረር ከተማ ስብሰባ እንዳያካሂድ ተከለከለ

 ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም )ክልሉ ለድርጅቱ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓም በጻፈው ደብዳቤ “ በጸጥታ ምክር ቤት ጉዳዩ ታይቶ በክልሉ ባለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር ተገምግሞ የተጠየቀው ፍቃድ አለመፈቀዱን እንገልጻለን” ብሎአል። ክልከላውን በማስመልከት ልክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ጋቢሳ ተስፋዬና ለጸጥታ ክፍል ሃላፊው አቶ አበበ መብራቱ ስልክ በተደጋጋሚ ብንደውልም ሊመልሱልን አልቻሉም። የአርበኞች ግንቦት7 የአመራር አባል የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በሰጡን አስተያየት፣ ክልሉ የጣለው እገዳ የተጀመረውን ለውጥ የሚያጨልም ተደርጎ መታየት የለበትም ያሉ ሲሆን፣ አገሪቱ ሽግግር ላይ ስላለች አንዳንድ ቦታ ላይ ለውጡን ለመቀልበስ የሚፈልጉ ሃይሎች ሴራ መሆኑን በመረዳት ከክልሉ አስተዳደርና ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየተነጋገርን አገር የማረጋጋት ስራ እንሰራለን ብለዋል። ክልከላው በአርበኞች ግንቦት7 ላይ ብቻ ለምን ሆነ? ሌሎች ድርጅቶችስ ለምን አልተከለከሉም በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ድርጅቱ የሚከተለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ባለፉት 27 አመታት ሲራመድ ከነበረው አስተሳሰብ ጋር የተለዬ በመሆኑ የተፈጠረ ድንጋጤ” ሊሆን ይችላል ብለዋል። አርበኞች ግንቦት 7 ቅዳሜ ጥር 3 በአዳማ የድጋፍና የውይይት ፕሮግራም እንደሚያካሂድ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በንቃት ተሳታፊ የነበሩት ሼህ ወርቁ ኑሩ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አረፉ

( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪነታቸው በደቡብ አፍሪካ ጆበርግ ከተማ ውስጥ የበረው አንጋፋው አገር ወዳድ ሼህ ወርቁ ኑሩ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት ተሳታፊ የነበሩት ሼህ ወርቁ ኑሩ በደቡብ አፍሪካ ስደተኞች ተወዳጅና አሰባሳቢ አባት ነበሩ። በኢትዮጵያ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የሰብዓዊ መብት መጣስን፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አፈና በዜጎች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ሰቆቃ በማውገዝ የዜጎች መብት እንዲከበር ሳይሰለቹ ድምጻቸው ከሚያሰሙት የሃይማኖት አባቶች መሃከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። የኢሳት ዝግጅት ክፍል ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።

Thursday, October 11, 2018

መንግስት ኦነግን ትጥቅ ያስፈታል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011) መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲል ኦነግን ትጥቅ ለማስፈታት እንደሚገደድ የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ መንግስት የታጠቁ ሃይሎች በሃገር ውስጥ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ ሁለት መንግስት እንዲኖር አይፈቅድም ብለዋል።
ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማድረግ የወሰነ ሃይል በመሳሪያ ጭምር እንደማይንቀሳቀስ የገለጹት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኦነግ ትጥቅ ለመፍታት አልተስማማንም የሚለውን አቋሙን እንዲመረምር የአፍ ወለምታም ከሆነ ይህንኑ እንዲያርም ጥሪ አቅርበዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ ሃገር ቤት ሲገባ በቦሌም ሆነ በዛላ አምበሳ የገቡት አባላትና አመራሮቹ ያለትጥቅ መግባታቸውን ያስታወሱት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ካሳሁን ጎፌ የትኛውም የፖለቲካ ሃይል መሳሪያ ይዞ እንዲንቀሳቀስ እንደማይፈቀድም አስታውቀዋል።
የተመለሱት የኦነግ ወታደሮች በመንግስት እጅ ሆነው በስልጣን ላይ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

በሃዋሳ አሮጌው ገበያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በእሳት ወደመ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011) በአዋሳ ከተማ የሚገኘው አሮጌው ገበያ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወደመ።
በገበያው የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የከተማው ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው የደረሱት እሳቱ ከተነሳ ከ1 ሰአት ተኩል በኋላ መሆኑም ታውቋል።
ከአዋሳ ከተማ መቆርቆር ጋር አብሮ እንደተመሰረት የሚነግርለት ገበያ በከተማው አዲስ የገበያ ስፍራ በመመስረቱ አሮጌው ገበያ በመባል ይጠራል።
በዚህ ስፍራ ለረጅም ዘመናት በንግድ ስራ የተሰማሩ የከተማው ነዋሪዎች ሀብት ንብረት አፍርተው ኖረዋል።
እድሜ ልክ  ያፈሩትን ንብረት ግን በአንድ ሌሊት ማጣታቸው ትልቅ ሀዘን ሆኖባቸዋል።
እሳቱ ከምሽቱ አንድ ሰኣት አካባቢ  ከፍራሽ ተራ እንደተናሳ የተገለጸ ሲሆን ፣ ልብስና ጫማ መሸጫ መደብሮች በተለምዶ ታይዋን ተራ፣ጥራጥሬ መሸጭ፣የባህል አልባሳት መሸጫ፣ አትክልት ተራ መደበሮች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታውቋል።
የወደመው ንብረት ግምቱ ምንያህል እንደሆን ነዋሪዎች በዚህ ሰዓት ማወቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የከተማው ማዘጋጃ ቤት እሳቱን ለማጥፋት ያደረገው ሙከራ እጅግ ደካማ እንደነበር ገለጸዋል።
ጨምረውም  የእሳት አደጋ ባለሙያዎቹ አደጋው ከደረሰ በኋላ የተገኙት ከተለያዩ መጠጥ ቤቶች ሲሆን በወቅቱም ሰክረው እንደነበር ጠቅሰዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ ማሰልጠኛ ሊወጡ ነው።

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011)ከአዲስ አበባ ከተማ የታፈሱትና ወደ ጦላይና ሌሎች ማሰልጠኛዎች የተወሰዱት ወጣቶች ስልጠናቸውን ጨርሰው በቅርቡ እንደሚወጡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወጣቶቹ የተያዙት ፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩና ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል።
አንድም የታሰረ ወጣት የለም ያሉት ኮሚሽነሩ ወጣቶቹ የተያዙት እንዲታሰሩ ሳይሆን ከህገወጥ ተግባር እንዲወጡና ስለህግ የበላይነት ስልጠና እዲያገኙ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የአዲስ አበባ ወጣቶች የተያዙት ፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወ፣ መሳሪያ ለመንጠቅና በተለያዩ ወንጀሎች ላይ በመሞከራቸው ነው።

Wednesday, October 10, 2018

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጥሪ አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 28/2011) በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች  ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የህብረተሰቡ እገዛ ያስፈልገኛል ሲል  የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጥሪ አቀረበ ።ከ90ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ከ523 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግም ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ትናንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ማህበሩ ባለፋት ጊዜያት በርካታ  ድጋፎች ቢያደርግም የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል ብሏል።
እናም ሕብረተሱ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል ፡፡
በእለቱም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር  ለአንድ አምቡላንስ መግዣ የሚውል  የ1.2 ሚሊየን ብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የትሕዴን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ ናቸው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 28/2011)ከ2ሺህ በላይ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትሕዴን/ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
ወታደሮቹን ጭነው ከሚጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች አንዱ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ሶስት ወታደሮች መሞታቸው ታውቋል በኢትዮጵያ መንግስትና በትህዴን መካከል በቅርቡ አስመራ ላይ ውይይት መደረጉን ተከትሎ በዛሬው እለት በዛላምበሳ ለገቡት ወታደሮች አቀባበል እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በ1993 ዓመተምህረት የተመሰረተው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን በትጥቅ ትግል 19ዓመታትን ቆይቷል።
የመጀመሪያ መሪውን በግድያ ሁለተኛውን በኩብለላ ያጣው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን የህወሀትን አገዛዝ በመሳሪያ ትግል ለማስወገድ የተቋቋመ እንደሆነ ይገልጻል።
ህወሀት ለህዝብ የገባውን ቃል በማጠፍ ጭቋኝ ስርዓት ሆኗል በሚል ጫካ የገቡት የትህዴን ታጋዮች በኢትዮጵያ እኩልነት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የሚያስችል ትግል እያካሄደ እንደነበረ ንቅናቄው ካሰራጫቸው ጽሁፎች መረዳት ይቻላል።
ሁለተኛው መሪው ሞላ አስገዶም ከህወሀት ደህንነቶች ጋር በመሆን የተወሰኑ ወታደሮችን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መኮብለላቸው የሚታወስ ነው።

የምርጫ ሕግ ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ ለውይይት ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 29/2011) የኢትዮጵያን የምርጫ ሕግ ለማሻሻል የተዝዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ለውይይት ቀረበ።
የምርጫ ቦርድ አባላት ከተቃዋሚዎችና ከገዢው ፓርቲ በእኩል መጠን ይሳተፉበታል የተባለው ረቂቅ ሕግ ቅሬታዎችን የሚያስተናግድ የምርጫ ፍ/ቤት እንደሚቋቋም ያስረዳል።የፍርድ ቤቱ ተግባር ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚመረምርና ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነም ተመልክቷል።
አዲስ የተረቀቀውና ለውይይት የቀረበው የምርጫ ሕግ ማሻሻያ ሰነድ የሃገሪቱን የምርጫ ስነ-ስርዓት መቀየርን ጭምር ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተገኘው መረጃ ያመለከታል።
የሃገሪቱን የምርጫ ስርዓት ለመለወጥ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ጭምር እንደሚያስፈልግ የታወቀ ቢሆንም የቀረበው ረቂቅ ሕግ እስከ ሕገ-መንግስት ማሻሻያ የዘለቀ እንደሆነም ተመልክቷል።

Ethiopia: Scaffolding on Lalibela rock-hewn churches damages structure

ESAT News (October 9, 2018)
Scaffolding erected ten years ago at the site of UNESCO heritage rock-hewn churches of Lalibela is causing structural damages to the historic site, priests and residents of the tourist town said.
The priests and residents of Lalibela who took to the streets on Sunday to vent their concern said the scaffolding that was put together for the purpose of protecting the historic site from natural disasters was actually causing more damages to the rock-hewn churches.
The residents say they have communicated their concerns to authorities but nothing has been done to reverse the damages being done on the churches.

በጅግጅጋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ንብረታቸው የወደመባቸው ባለሃብቶች የካሳ ጥያቄያቸው እስካሁን መልስ አለማግኘታቸውን ገለጹ

( ኢሳት ዜና መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከ300 በላይ የሚሆኑትና በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ አሌ እንደመሩት በሚታመነው ግጭት ንብረታቸው የወደመባቸው የከተማዋ ነጋዴዎች፣ በአጠቃላይ ከ700 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ካሳ ከመንግስት ይጠብቃሉ። መንግስት ካሳ ለመስጠት ፈቃደኛ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ መልስ ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ችግር መደረጋቸውን ነጋዴዎች ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ የተቋቋመውን የክልሉን አስተዳደር ባለስልጣናት ለማናገር ብንሞክርም አልተሳካልንም።

በቄለም ወለጋ ወረዳ የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ኦነግ እንደሆኑ የሚገልጹ ወታደሮች ነዋሪዎችን የግል የጦር መሳሪያዎችን እንዲያስረክቡና ገንዘብም እንዲሰጡ እያስገደዱ ነው

( ኢሳት ዜና መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ/ም ) ኢሳት ያነጋገራቸው በቄለም ወለጋ ደምቢዶሎ አካባቢ ፣ በሰዮ ወረዳ፣ ወልጋይ፣ ቢቢካና ቀስሪ መንደሮች የሚኖሩ በ1977 ድርቅ ወቅት ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ሄደው የሰፈሩና በአካባቢው ለአመታት የኖሩ ዜጎች ፣ በአካባቢው የሚንቀቀሳቀሱ ወታደሮች፣ “ከአሁን በሁዋላ አካባቢውን የሚያስተዳድረው ኢህአዴግ ሳይሆን እኛ ነን፣ ኢህአዴግን አናውቀውም፤ የግል የጦር መሳሪያ ያላችሁ፣ መሳሪያችሁን አስረክቡ፣ ገንዘብም ክፈሉ” እያሉ እንደሚያስገድዱዋቸው ገለጸዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የቀበሌ አስተዳደሩን የኦነግ ታጣቂዎች ተረክበው እየሰሩ ሲሆን፣ የኦዴፓ መሪዎች በአካባቢው ባለመኖራቸው የደህንነት ስጋት ገጥሟቸዋል። መንግስት እውቅና ሰጥቶን ለረጅም ጊዜ የታጠቅነውን የነፍስ ወከፍ መሳሪያ አስርከቡ መባላቸውን የተቃወሙት ነዋሪዎቹ፣ መንግስት ፈቅዶ የታጠቅነውን መሳሪያችሁን አስረክቡ ቢለን ለማስረከብ ፈቃደኞች ነን ብለዋል። የኦነግ ወታደሮች ህዝቡን እየሰበሰቡ ኢህአዴግ እንደማያውቁትና ማንኛውንም ነገር ለኦነግ ወታደሮች እየነገሩ መፍትሄ እንደሚያገኙ እየተናገሩ መሆኑንም ያነጋገርናቸው በርካታ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊትም ሆነ የመንግስት ሹም አለመኖሩን፣ ትናንት ምሽት የቀበሌውን አስተዳደሪ ይዘው በመምጣት መሳሪያ አላችሁ ወይ እያሉ ሲጠይቁ ማምሸታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኦዴፓ የገጠር ዘረፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ኦነግ ትጥቁን ካልፈታ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ መጻፋቸው ይታወቃል። ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ትናንት ፓርላማውን ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግርም፣ መንግስት ህግን ለማስከበር ጠንካራ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀመር ገልጸዋል። የኢህአዴግ ጉባኤ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን በድጋሜ መሪ አድርጎ በመረጠበት ወቅት ጠ/ሚኒስትሩ ባሰሙት ንግግር መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር የተጠናከረ እርምጃ

Monday, October 8, 2018

Ethiopia to issue visa on arrival to Africans

ESAT News (October 8, 2018)
Ethiopia says it will meet the deadline set by the African Union for African travelers to get visa on arrival instead of applying prior to their trip.
The African Union has set a goal for a visa free travel within the continent by 2020.
Seychelles is so far the only country that requires no visas to all Africans.
Speaking at the opening of a bicameral parliament, President Mulatu Teshome says the country would strive to meet the deadline for a visa free Africa which he said help create continental unity.
The President said a visa free travel will also help boost the country’s tourism by increasing the volume of travelers to the country

በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቤት መስሪያ ብድር ሊሰጥ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 28/2011)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቤት መስሪያ ብድር ለመስጠት መወሰኑን ገለጹ።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊኒ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደምበኞቹን ለማገልገልና እራሱንም ለማሳደግ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሃገሪቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቅርንጫፍ ባንኮች ያሉት ግዙፍ የገንዘብ ተቋም ነው።
የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ከ3 መቶ ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ነው የሚነገረው። በሃገሪቱ ካለው አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 67 በመቶው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይገኛል።
በመላ ኢትዮጵያ ከተሰጡ ብድሮች ደግሞ ንግድ ባንኩ 53 በመቶውን ይሸፍናል።
እናም በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የጀመሩትን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መሰረት በማድረግ ለዲያስፖራው የቤት መስሪያ ብድር አመቻቻለሁ ብሏል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊና ሰሞኑን ከዲያስፖራው አባላት ጋር ባካሄዱት ውይይት ባንኩ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለቤት መስሪያ የሚሆን ብድር ይመቻችላቸዋል ብለዋል።

በቡራዩ ተፈጸመውን ወንጀል ያቀነባበሩ ግለሰቦች በአሸባሪነት ተከሰሱ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 28/2011) በቡራዩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያቀነባበሩና የፈጸሙ ግለሰቦች በአሸባሪነት መከሰሳቸው ታወቀ።
ግለሰቦቹ በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ከቡራዩ በመጡ ወጣቶች መካከል ግጭት እንዲከሰት በተለይ ፓስተር በተባለው የአዲስ አበባ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን አቃቤ ሕግ ገልጿል።ከቡራዩ የመጡትን ወጣቶች በማደራጀትና ሽጉጥ በመተኮስ ግጭት እንዲከሰት ማድረጋቸውን በፍርድ ቤት የቀረበው ክስ ያስረዳል።
በተጠርጣሪዎቹ ቤት 74 ገጀራና ቢላዋ መገኘቱም ተመልክቷል።
ሳምሶን ጥላሁን፣አለሙ ዋቅቶላ፣ቡልቻ ታደሰ፣ሃሺም አሚር፣ሽፈራው እና አሊ ዳንኤል የተባሉት 6ቱ ተከሳሾች በሳምንቱ መጨረሻ በፌደራሉ የመጀምሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት መቅረባቸውን የገለጸው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ግጭቱን በማነሳሳት፣በማስተባበርና ጥቃት ፈጻሚዎችን በመንግስት ተሽከርካሪ በማሸሽ አብይ ተዋናዮች መሆናቸውን አመልክቷል።

በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አደጋ ላይ ወድቋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 28/2011)በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አደጋ ላይ በመውደቁ ሕግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚፈጸም ተገለጸ።
አወዛጋቢ የሆኑትና በአፋኝነታቸው የሚጠቀሱ አዋጆች በዚህ አመት እንዲሻሻሉ ዝግጅት መጠናቀቁም ተመልክቷል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2011 አዲስ አመት የመጀመሪያ ስብሰባውን ሲያደርግ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ባደረጉት ንግግር እንዳመለከቱት የፖለቲካ ምህዳሩን የማስፋቱ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
በየአካባቢው ያለውን ግጭትና የተከተለውን የሰዎች ሞት የዘረዘሩት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሕግ የበላይነት አደጋ ላይ መውደቁንም አመልክተዋል።
ሃገሪቱን ከቀውስ ለመታደግና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ መንግስት ሕግ የማስከበሩን ተግባር እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ከ900 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመታደግ ከ 10 ዓመት በፊት የተሰራው የጸሀይ እና የንፋስ መከላከያ ጣሪያ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን የደብሩ መነኮሳት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

( ኢሳት ዜና መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪዎቹ ባካሄዱት ትዕይንተ ህዝብ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪዎች እንዳሉት ለ 5 ዓመት ተብሎ የተሰራው ከፍተኛ ክብደት ያለው ጊዚያዊ ጣሪያ ከጥቅሙ ይልቅ ሊያመጣ የሚችለው ጥፋት ሃሳብ ላይ ጥሏቸዋል የቅዱስ ላሊበላ ገዳም መነኮሳትም ሆኑ የላስታ ህዝብ በዓለም ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የባህል የቅርስ ተቋም የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የተጋረጠባቸውን ስጋት በተመለከተ ለሚመለከተው አካል ከ 20 ጊዜ በላይ አቤቱታ ሲያቀርቡ ኖረዋል፡፡

Friday, October 5, 2018

Ethiopia: Re-elected as chairman of ruling party, Abiy Ahmed garners vote of confidence to continue reforms

by Engidu Woldie
ESAT News (October 5, 2018)
Ethiopia’s ruling party, the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), re-elected the incumbent Prime Minister, Dr. Abiy Ahmed as its chairman until the next congress. The decision by the the Congress of the four party coalition will, by default, allow Ahmed to continue in his position as the Prime Minister.
The re-election of Abiy Ahmed as chairman of the Front that was conducted at the end of a three day Congress in the Southern city of Hawassa has also given him the vote of confidence to continue his political and economic reforms he has begun when he assumed the position six months ago.

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምርቃ ተማሪዎች ከፍያ ላይ 125 በመቶ የክፍያ ጭማሪ አደረገ

( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) ተማሪዎቹ ለኢሳት በላኩት መረጃ እንዳመለከቱት ዩኒቨርስቲው በድህረ ምረቃ ተማሪዎች ክፍያ ላይ 125 በመቶ ጭማሪ በማድረጉ በኑሮአቸው ላይ ጫና ፈጥሯል። ለጥናት ወረቀት ወይም ፕሮጀክት በክሬዲት 600 የሚክፍሉ ሲሆን ለ30 ክሬዲት እስከ 18 ሺ ብር ይከፍላሉ። ተማሪዎቹ የክፍያ መጠናቸው አቅምን ያላገናዘበ በመሆኑ እንደተቸገሩ ገልጸዋል::

በአፍ መፍቻ ቋንቋችን እንድንማር ይፈቀድልን ያሉ የራያ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቆሙ። በአድማው 23 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።

( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) በዘንድሮ የ2011 ዓ.ም አዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታቸው መግባት የነበረባቸው የራያ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ካልሆነ አንማርም ማለታቸውን ተከትሎ ከ1ኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ያሉ ትምህት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ዝግ ሆነዋል። ሕዝቡ በህገመንግስቱ የተሰጠን መብት የትግራይ ክልል ሊከለክለን አይገባም ብለዋል። አላማጣ ከተማን ጨምሮ እስከ 23 የሚደርሱ ትምህርት ቤቶች በሕዝቡ አቋም እንዲዘጉ መደረጋቸውን የራያ ሕዝብ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አዘዘው ሕዳሩ ገልጸዋል። በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ባልሆነ ቋንቋ አንማርም ማለታቸው ያስቆጣቸው የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ተማሪዎችን እና ወላጆችን የማባበል ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም። ይህ ያስቆጣቸው የዞን ባለስልጣናት የትምህርት ቤቶችን ርዕሰ መምህራንን እና ምክትል ርዕሰ መምህራንን በመጥራት እናንተ የማግባባት እና በማኅበረሰቡ ላይ ጫና መፍጠር ባለመቻላችሁ ምክንያት የተፈጠረ አድማ ነው በማለት ማስፈራሪያና ተግሳጽ ተሰጥቷቸዋል። የትምህርት ቤቶቹ አስተዳዳሪዎቹ በበኩላቸው ከአሁን በኋላ ሕዝቡን ማስገደድ እንደማይችሉ እና እራሳችሁ ከፈለጋችሁ ማስገደድ ትችላላችሁ ሲሉ ለዞኑ

ዶ/ር አብይ አህመድና አቶ ደመቀ መኮንን ኢህአዴግን እንዲመሩ በድጋሜ ተመረጡ

( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) በሃዋሳ በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ ጉባኤ ዶ/ር አብይ አህመድ ድምጽ ከሰጡ 177 ሰዎች ውስጥ የ176 ሰዎችን ድምጽ በማግኘት ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፣ አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ 149 ድምጽ በማግኘት ምክትል ጠ/ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል። የህወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል 15 ድምጽ በማግኘት የምክትል ጠ/ሚኒስትርነቱን ቦታ አጥተዋል። ከምርጫው በፊት የዶ/ር አብይ አህመድንና የአቶ ደመቀ መኮንን በድጋሜ ተመርጠው የተጀመረው ለውጥ እንዲቀጥል የሚሹ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በጉባኤው ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተው ክርክር ተደርጎባቸዋል። አዴፓ የወልቃይት ጠገዴ እና የራያ ህዝብ የማንነት ይከበርንል ጥያቄ እንዲሁም የሱዳን ድንበር ጉዳይ እልባት እንዲያገኙ ሃሳብ አቅርቦ ሞግቷል። አሁን ያለው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ርዕዮት እንዲሁም በአማራ ህዝብ ላይ የሚሰነዘረው የጥላቻ ንግግር እና የተሸዋረረ አመለካከት እንዲስተካከልም ጠይቋል። የኦዴፓ ተወካዮችም ከሶማሊ ክልል ጋር ያለው የድንበር ውዝግብ

Wednesday, October 3, 2018

ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ

( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለ3 ቀናት የሚቆየውን ኢህአዴግ ጉባኤ በአዋሳ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ፓርቲያቸው የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በምን መልኩ ተግባራዊ እንደሚያደርግንና ወዴት አቅጣጫ ሊወስደው እንዳሰ በተናግረዋል። “ አገራችን የቀደመውን ጠብቀውና አዲስም አክለውበት ለመጪው በሚያስተላልፉ ተተኪ ወጣቶች እየተመራች፣ እየተገነባች የ21ኛው ክፍለ ዘመን አብሪ ኮከብ ለመሆን ብቅ ባለችበት የለውጥ ዘመን ላይ ትገኛለች።” የሚሉት ዶ/ር አብይ፣ “የበለጸገች የጋራ ቤታችንን ለልጆቻችን ማድረስ የምንሻ ከሆነ ዝርፊያውንና የመጠላለፍ ፖለቲካውን ትተን ተግተንና ታጥቀን በጋራ መስራት የኖርብናል። እኩልነትና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ እውን ሆና ማየት የምንሻ ከሆነ ዘር እና ሃይማኖትንን መሰረት አድርገን አናጥቃ።” ብለዋል። “ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን እኔ ሰራሁዋት ሊል አይቻለውም፤ ኢትዮጵያ በሁላችንም ደም እና ላብ የተሰራች በመሆኗ፣ ባለቤቶቿ ሁላችንም ነን። ትናንት የሁላችንም አባት እናቶች ለዚህ አገር ደማቸውን ገብረዋል። እንኳን ዛሬ በህይወት ቆመን ይቅርና ሁላችንም ካለፍን በሁዋላ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና ትቀጥላለች።” ሲሉ ኢትዮጵያ ሳትፈርስ እንደምትቀጥል ራዕያቸውን አስቀምጠዋል። ዶ/ር አብይ ሲቀጥሉም “ የሃሳብ ብዝሃነትን መቀበል የብሄርብሄረሰብ ብዝህነትን የመቀበል ያህል ለአገራችን ሰላምና ብልጽግና አስፈላጊ” በመሆኑ፣ “ በተፎካካሪዎቻችን ሃሳብ ላንስማማ “ ብንችልእንኳን፤ የሚያሻግረን አዋጭ አማራጭ ግን ሃሳብ እንዳይፈስና ድምጻቸውን ማገድ ሳይሆን፣ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ታግሎ ሃሳባቸውን በላቀ ሃሳብ አሸንፎ መውጣት ብቻ ነው።” ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከእንግዲህ በሚያራምዱት ሃሳብ እንደማይዋከቡና ሃሳባቸውም እንደማይታፈን ተናግረዋል። “የአገር መጻኢእጣ ፋንታ በታሪክ ብቻ አይወሰንም። የተደረገውን በመደጋገምና አዲስ ነገርም በመጣ ቁጥር እንዳልተገራ ፈረስ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ለውጡን የምንገዳደር ከሆነ አገራችን የምትመኘውን ፈጣንና ሁለንተናዊ ለውጥ ማረጋገጥ አንችልም።” ሲሉም ለውጡን ለማይቀበሉ የድርጅታቸው አባላት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አሁን ያለውን ፌደራሊዝም በተመለከተ ሲናገሩ ደግሞ “እንደ ኢትዮጰያ ላለ ፈርጀብዙ ብዘሃነትን የተላበሰች አገር ፌደራሊዝም የተሻለ የአሰተዳደር ስርዓት ነው። የፌደራል መንግስት አወቃቀር ደግሞ የአሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆንይ ኖርበታል። ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ማስተናገድ ከቻልን እንደኛ አገር ላለነባራዊ ሁኔታፌደራሊዝም ተመራጭ የአስታዳደር ስርዓት መሆኑ አያጠያይቅም።” ያሉት ዶ/ር አብይ፣ ክልላዊ አስተዳድሮች ሁሉንም ብሄሮች በእኩልነት የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት እንደሌለባቸውና ይህ ሲሆን ዜጎች በየትኛውም የአገራቸው ክፍልያ ለስጋት ተንቀሳቀስው መስራትና ሃብት ማፍራት የሚያስችላቸውን መተማመን የሚያገኙ በመሆናቸው አብሮነታችን ይበልጥ እየጠነከረ የምናስባትን ጠንካራ አገር መስራት እንችላለን።” ብለዋል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትርክት ውስጥ የብሄር ማንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነት እስካሁን ድረስ ሚዛን ጠብቀው መሄድ ባለመቻላቸውም፣ ሁለቱንም ማንነቶች እንደሚተካኩ ሳይሆን እንደሚተባበሩ ማንነቶች ማየት እንደሚገባ ዶ/ር አብይ ተናግረዋል። በአገራችን ውስጥ ከፍተኛ የሞራል እና የግብረገብነት ዝቅጠት መኖሩን የገለጹት ዶ/ር አብይ፣ “መሪዎች፣አስተማሪዎች፣ የእምነትአባቶች፣ የአገርሽማግሌዎች፣ ወላጆች፣ ታዋቂሰዎች፣ ፖለቲከኞችና የጎሳ መሪዎች ሁሉ በንጹህ ህሊና፣ በስነምግብር፣ በሞራል ልእልና፣በሃገርና በወገን ፍቅር፣በቃልና በግብር ምሳሌዎች” ሆነው ህዝብን ከጥፋት መታደግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው አሰፋ በኢሕአዴግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ አልተገኙም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ለሕወሃት ስራ አስፈጻሚነት የተመረጡ የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ በኢሕአዴግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንዳልተገኙ ተነገረ።

በፌደራል መንግስት የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው ሲነገርባቸው የቆዩት አቶ ጌታቸው አሰፋ በሕወሃት ስራአስፈጻሚ ሆነው መመረጣቸው ብዙዎቹን እያነጋገረ ይገኛል።
አቶ ጌታቸው አሰፋ ላለፉት 18 አመታት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ ለተፈጸሙ መንግስታዊ ግድያዎችና በዜጎች ላይ ለደረሱ ሰቆቃዎች ተጠያቂ ናቸው።
ከስልጣን ከወረደ በኋላም በሃገሪቱ አለምረጋጋት እንዳይፈጠር በተፈጸሙ ጥቃቶች እጃቸው እንዳለበት ይጠራጠራሉ።
አቶ ጌታቸው አሰፋ በብዙዎች ዘንድ ስውሩ ሰው በሚል ይታወቃል።
በየትኛውም መገናኛ ብዙሃን የማይቀርቡትና በአደባባይ የማይታዩት የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ ፎቶአቸው በይፋ እንዳይታይም ሰደረግ ቆይቷል።
በህወሃት የ27 ዓመታት የአገዛዝ ዘመን በተፈጸሙ መንግስታዊ ግድያዎችና ሰቆቃዎች ዋነኛ ተጠያቂ ተደርገው ይወሰዳሉ።
ይህ ብቻ አይደለም ከስልጣን ከወረዱ በኋላም በእነ ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ እንቅልፍ የላቸውም የሚባሉት ጌታቸው አሰፋበመቀሌ መሽገው እንደሚገኙ ይነገራል።
በፌደራል መንግስቱ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው የሚነገርላቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ ባለፈው ጊዜ ከመቀሌ ወደ ሱዳን አምርተው እንደነበርም የኢሳት ምንጮች ገልጸው ነበር።
አቶ ጌታቸውን በተመለከተ በወቅቱ የተጠየቁት የህዉሃት ምክትል ሊቀመንበርና የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዜአብሔር ለተከታታይ 15 ቀናት እንዳላዩኣቸውና በዚያን ሰዓትም የት እንዳሉ እንደማያውቁ መናገራቸውም ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ ኣንዳለም ባልተጠበቀ ሁኔታ የህዉሃት ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመረጡት አቶ ጌታቸው አሰፋ በሃዋሳ በተከፈተው የኢህአዴግ ጉባኤ አለመገኘታቸው ተነግሯል።
የኢሳት ምንጮች እንዳሉት አቶ ጌታቸው አሰፋ መገኘት በሚጠበቅባቸው የኢህአዴግ ጉባኤ አለመገኘታቸው በፌደራል መንግስቱ እንደሚፈለጉና ስጋት እንዳለባቸው ማረጋገጫ ሆኗል።
እራሳቸውን በተመለከተ የተጠየቁት የህዉሃት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋዊ መግለጫ ሳይኖር ሚዲያዎች ሃሜት ማውራታቸው ትክክል አይደለም ብለዋል። በአቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ ስለመመስረቱም የማውቀው ነገር የለም ነው ያሉት።
የቀደመውን የደህንነት ሃላፊ ፈልጎ ህዉሃት ጋር የመጣ የመንግስት-አካልም አለመኖሩን ገልጸዋል።
እናም አቶ ጌታቸው አሰፋ አውሮፕላን ካላመለጠው በኢህአዴግ ጉባኤ ይገኛል ሲሉም ነው የተናገሩት።
ይህም ሆኖ ግን አቶ ጌታቸው አሰፋ በጉባኤው ላይ ባለመታየታቸው የእርሳችው ነገር አሁንም ያልተፈታ እንቆቅልሽ እንደሆነ ይገኛል።

ግሎባል አልያንስ ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉ ዜጎች የገንዘብ ማሰባብሰብ ዘመቻ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ግሎባል አልያንስ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለተፈናቀሉ ከ70ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የገንዘብ ማሰባብሰብ ዘመቻ በይፋ መክፈቱን አስታወቀ።

አለም ዓቀፍ መብት ለኢትዮጵያውያን ግሎባል አሊያንስ በጎ ፈንድ ሚ አማካኝነት ለከፈተው ዘመቻ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ወጣቶች ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመነጋገር ለቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቃዮች የተለያዩ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተገለጿል።

አቶ አህመድ አብተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011)የፖሊሲ ምርመራና ጥናት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አህመድ አብተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾመ።

የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በሆኑት በዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ፊርማ የተሾሙት አቶ አህመድ አብተው ዶክተር ይናገር ደሴን ይተካሉ ተብሏል።
አዲስ ፎርቹን የባንኩን ምንጮች ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ አቶ አህመድ አብተው ከመስከረም 9/2011 ጀምሮ የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን የቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት ዶክተር ይናገር ደሴ ስፍራውን ለቀዋል።
ዶክተር ይናገር ደሴ በአሁኑ ወቅት የብሔራዊ ባንክ ገዢ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በቦርድ ሊቀመንበርነትም ሆነ አባልነት መቀጠል እንደማይችሉም ተመልክቷል።
ዶክተር ይናገር ደሴ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነትን የተረከቡት ከአቶ በረከት ስምኦን ሲሆን አቶ በረከት ስምኦን ለ6 አመታት በቦርድ ሊቀመንበርነት ሰርተዋል።
ከእሳቸው በፊት አቶ አባይ ጸሐዬ የነበሩ ሲሆን ከአቶ አባይ ጸሃዬ በፊት አቶ አሰፋ አብርሃ በቦርድ ሊቀመንበርነት መስራታቸው ይታወሳል።
በሃገሪቱ ትልቁና ቀደምት በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የሕወሃት ሰዎች በነበራቸው የበላይነት ለኤፈርት በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ ሲሰጡና የተበላሸ ብድር በማለት እዳ ሲሰርዙ ቆይተዋል።
75 አመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ሺ 288 ቅርንጫፎችና 32ሺ ሰራተኞች እንዳለው ታውቋል።
ባለፈው አመት 11 ቢሊየን ብር እንዳተረፈ የተገለጸ ሲሆን ጠቅላላ ሃብቱ ከ560 ቢሊየን ብር በላይ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ አዲስ ስራ አስኪያጅ ተሾመ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ምትክ አዲስ ስራ አስኪያጅ ተሾመ።

የኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ለግድቡ ግንባታ በዋና ስራ አስኪያጅነት የሾሙት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን መሆኑ ታውቋል።
ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳንና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ በምክትል ስራ አስኪያጅነት መሾማቸውም ይፋ ሆኗል።
አዲሶቹ ተሿሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ታውቋል።
በምክትል ስራ አስኪያጅነት የተሾሙት ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን ከኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት በኋላ በተጠባባቂ ስራ አስኪያጅነት ሲሰሩ መቆየታቸውንም ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ መረዳት ተችሏል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሐምሌ 19 ቀን 2010 አምተምህረት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ይታወሳል።
ፖሊስ አደረኩት ባለው ምርመራ ኢንጂነሩ ስመኘው ራሳቸውን እንዳጠፉ መግለጫ መስጠቱም አይዘነጋም።

Tuesday, October 2, 2018

በከፋ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ

( ኢሳት ዜና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም )የአካባቢው ባለስልጣናት ለኢሳት እንደተናገሩት ባለፉት 3 ቀናት ማንነታቸው የማይታወቁ ታጣቂዎች በከምባታ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነው። የቡልካቡል ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ታደለ ለኢሳት በስልክ እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ቀናት ከ15 ያላነሱ ሰዎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተገድለዋል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ሸሽተዋል። ችግሩ ላለፉት 2 ዓመታት የቆዬ ቢሆንም፣ ሰሞኑን ጥቃቱ መጨመሩን ሊመቀንበሩ ተናግረዋል የታጣቂዎችን ማንነት እንደማያውቁ የገለጹት ሊቀመንበሩ ፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የኦሮሞ፣ የአማራና የሌሎች ብሄር ተወላጆች ወደ ኦሮምያ ክልል በመግባት ላይ ሲሆኑ፣ የክልሉ መንግስት ተፈናቃዮችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ ነው። መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው የገባ ቢሆንም፣ ዜጎች ግን ጥቃቶችን በመፍራት አካባቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው።

አዴፓ ሊቀመንበሩንና ምክትል ሊቀመንበሩን መረጠ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011) አዴፓ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።
የቀድሞው ብአዴን አዲሱ አዴፓ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌንና አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መምረጡም ተመልክቷል።ደኢሕዴንም ወይዘሮ ሙፍርያት ካሚልንና አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን በድጋሚ መርጧል።
ደኢሕዴንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ፍጹም አረጋን ጨምሮ 65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መምረጡም ታውቋል።
የቀድሞው የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ የአሁኑ አዴፓ አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ ደጉ አንዳርጋቸውን ጨምሮ 13 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ አቶ ብናልፍ አንዱአለም፣አቶ ተፈራ ደርበው እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል

የለውጥ እንቅስቃሴውን የሚያዳፍኑ አመራሮች ህዝቡን እያሰቃዩ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011) በአፋር፣ ጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የለውጥ እንቅስቃሴን የሚያዳፍኑ አመራሮች ህዝቡን እያሰቃዩ ናቸው ተባለ።
የአፋራ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅትና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥተዋል።በሶስቱ ክልሎች ያሉት አመራሮች ለውጡን እያደናቀፉት በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል የአፋር ወጣቶች በህወሃት የሚንቀሳቀሰውን የጨው ምርት ንግድ ማገታቸውን የደረሰን መረጃ ያመልክታል።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቲና የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ፕሬዝዳንት አቶ ገአስ አህመድ ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሶስት ክልሎች የቀጠለውን የጭቆና አስተዳደር መንግስት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
በሌላው የኢትዮጵያ አከባቢዎች እንደታየው የለውጥ ሂደት በአፋር ጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ሊታይ አልቻለም ያሉት የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች የህወሀት ዘመን አሰራር አሁንም በክልሎቹ ቀጥሏል ሲሉ ተናግረዋል።

ከቤንሻንጉል የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ70ሺህ በለጠ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011) ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ70ሺህ መብለጡ ተገለጸ።
የሞቱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ40 በላይ መድረሱ ታውቋል።ሁለት ነፍሰጡሮች በሽሽት ላይ እያሉ መንገድ ላይ መውለዳቸውም ተመልክቷል።
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሼ ዞን አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው ሲመለሱ በተሰነዘረባቸው ጥቃት አራት አመራሮች መገደላቸው ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት እንደሆነም ተመልክቷል።
መስከረም 16 ቀን 2011 አራት የካማሼ ዞን ባለስልጣናት በታጣቂ ሃይሎች መገደላቸውን ተከትሎ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ማሻቀቡን  የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ገልጸዋል።
በአብዛኛው የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች በተፈናቀሉበት በዚህ ክስተት ሁለት ነፍሰ ጡር እናቶች መንገድ ላይ መገላገላቸውም ተመልክቷል።
በአጠቃላይ የተፈናቃዮቹ ቁጥር 70ሺ መድረሱም ታውቋል።

በወልቃይት ከፍተኛ ወከባና እስር እየተፈጸመ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011) በወልቃይት ከፍተኛ ወከባና እስር እየተፈጸመ መሆኑ ተገለጸ።
ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በወልቃይት የአማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰው ወከባ ድብደባና እስር በመሸሽ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መሰደዳቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።ሰሞኑን ከ100 በላይ የአማራ ተወላጆች ከወልቃይ ተፈናቅለው ዳንሻ መግባታቸውም ታውቋል።
ሌሎች ወደ 50 የሚሆኑትም ወደ አብደራፊ መሸሻቸውን ተፈናቅዮቹ ገልጸዋል።
ህወሀት ወልቃይት የትግራይ ነው፣ ወልቃይትን ለማዳን ታጠቁ የሚል ዘመቻ መጀመሩም ተሰምቷል።
በወልቃይት ሰባት የወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች በማቋቋም የአማራ ተወላጆችን ጭምር ስልጠና እንዲወስዱ እያስገደደ እንደሆነም ተገልጿል።
ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት ወልቃይትን ለማዳን በሚል ውስጥ ለውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማድረጉን በተመለከተ መረጃዎች ሲወጡ ቆይተዋል።
ወልቃይት የትግራይ ናት በሚል እንደአዲስ በተጀመረው ዘመቻ በወልቃይት የአማራ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ መዋከብ እየተፈጸ መሆኑን ነው ለኢሳት የደረሰው መረጃ የሚያመልክተው።

በኢሕአፓ ስም አዲስ አበባ የገቡት ሰዎች ድርጅቱን አይወክሉም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011)በኢሕአፓ ስም በአዲስ አበባ አቀባበል የተደረገላቸው ሰዎች ድርጅቱን የሚወክሉ አይደሉም፥አባላችን አለመሆናቸውም ይታወቅልን ሲል ህጋዊ ነኝ ያለው ፓርቲ ያወጣው መግለጫ አመለከተ።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)’’አንድና አንድ ብቻ ነው”በሚል የወጣው የድርጅቱ መግለጫ እንዳመለከተው በአቶ መርሻ ዮሴፍ ስም አዲስ አበባ የገባው ቡድን እራሱን በአንጃነት የፈረጀ ነው።
እናም አርማውም፥ስሙም በሕግ የተመዘገበ ኢሕአፓ የተባለ ፓርቲ እያለ፥ አባላት ያልሆኑ ሰዎችን የድርጅቱ አመራሮች ናቸው በሚል በአዲስ አበባ አቀባባል መደረጉ ትክክል አይደለም ሲል መግለጫው አመልክቷል።

Monday, October 1, 2018

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብዛት ያላቸው ነባር አመራሮቻቸውን አሰናበቱ

( ኢሳት ዜና መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ/ም ) ጉባኤያቸውን በማካሄድ ላይ ያሉት የቀድሞው ብአዴን በአዲሱ ስያሜ የአማራ ዲሞክራሲ ፓርቲ፣ አዲፓ፣ የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያ ፓርቲ እና ህወሃት በርካታ ነባር አመራሮቻቸውን አሰናብተዋል። ደኢህዴን የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጨምሮ 23 ሰዎችን ሲያሰናብት፣ ከታዋቂዎቹ መካከል ሽፈራው ሽጉጤ፣ ሲራጅ ፈጌሳ፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ሬድዋን ሁሴንና ሽፈራው ተክለማርያምን አሰናብቷል። ህወሃት በበኩሉ የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ሚካኤል አብረሃና አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይን ጨምሮ 12 ሰዎችን ከድርጅቱ አሰናብቷል። የአማራ ዲሞክራቲክ ፓርቲ በበኩሉ ከበደ ጫኔ፣ ፍሬህይወት አያሌው፣ ጌታቸው አምባዬን አሰናብቷል። ህወሃት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ሊቀመንበር እንዲሁም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር፣ ም/ሊ ቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ሲወስን ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ አለም ገብረዋህድ፣ አቶ አስመለሽ ወልደስላሴ፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ አለምባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት ሆነው ተመርጠዋል። እነዚህ ሰዎች ድርጅቱን ወክለው በኢህአዴግ ስራ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከ60 ሺ በላይ ሰዎች ሰዎች ሲፈናቀሉ የማቾችም ቁጥር እያሻቀበ ነው

( ኢሳት ዜና መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ/ም ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሺ ዞን አመራሮችና በኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት መካከል ቀደም ብለው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ክልሉ ለመመለስ ድርድር አድርገው ሲመለሱ የተገደሉ 4 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለስልጣናትን መገደል ተከትሎ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ በክልሉ የሚኖሩ ከ60 ሺ በላይ የኦሮሞ፣ አማራና ሌሎችም ብሄሮች ተወላጆች ተፈናቅለዋል። እስካሁን ድረስ ከ12 ያላነሱ ሰዎች ሲገደሉ በርካታ ዜጎችም ቆስለዋል። ለባለስልጣኖች ግድያ የኦሮምያ ክልል የኦነግ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ ኦነግ በበኩሉ አስተባብሏል። በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ፣ በተንካራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ሲቃጠሉ ከ4 ያላነሱ ሰዎች ህይወት አልፏል። በምስራቅ ወለጋ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር እስከ 60 ሺ የሚደርስ ሲሆን፣ የተፈናቃዮች ቁጥር ከ100 ሺ ሊያልፍ እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው። የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዳስነበቡት፣ ግጭቱ በመንዲ ከተማ የሁለቱ ክልል ባለስልጣናት ውይይት አድርገው ሲመለሱ ፣ ቢላ በተባለ ቦታ ላይ በኦነግ_ስም የታጠቁ ወታደሮች ባለስልጣናቱን በያዙት መኪና ላይ ተኩስ ከፍተው የከማሲ ዞን አስተዳዳሪውን ጨምሮ 4 ሰዎችን በመግደላቸው የተፈጠረ ነው። በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱትን ታጣቂዎችን መንግስት እስካሁን ለምን ትጥቅ እንዳላስፈታቸው የታወቀ ነገር የለም። አስመራ የነበረው ዋናው የኦነግ አመራር በሰላማዊ ትግል ለመታገል ወስኖ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል። በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች አዲስ አበባ ከሚገኘው የኦነግ አመራር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኑረው አይኑረው የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ኦነግ ግን እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጽሙ ታጣቂዎች እንደሌሉት በመግለጽ ላይ ነው።

Several killed and thousands displaced in Western Ethiopia

ESAT News (October 1, 2018)
At least 20 people have been killed and about 50,000 displaced over the weekend in areas bordering the Oromo and Benishangul Gumuz regions.
The weekend violence followed the killing of four officials from Benishangul region in an ambush in the Oromo region on Wednesday.