Saturday, February 6, 2016

በኦሮሚያ በጉጂ ዞን ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጋምቤላና በመላው ኢትዮጵያ የድንበር አከባቢዎች ውጥረቱ ተባብሷል::

ለስር ነቀል ለውጥ የትግል ስትራቴጂ የሚነድፍ የሚቀይር ወይም የሚቀይስ ምነው ጠፋ???‪#‎Ethiopia‬
በኦሮሚያ በጉጂ ዞን ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጋምቤላና በመላው ኢትዮጵያ የድንበር አከባቢዎች ውጥረቱ ተባብሷል:: ‪#‎Oromoprotests‬‪#‎Gambella‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክፍለሃገር የተጀመረው ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን በጉጂ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ተቃውሞው ተፋፍሞ የቀጠለ መሆኑ ሲታወቅ በሚድሮክ የወርቅ ማእድን ማውጫ በስሩ የሚገኘው የጉጂ ዞን ነዋሪዎች በገዛ አከባቢያችን ጥቅማችን ተደፍሯል የመስራት ሕልውናችን ተገፏል ጉልበታችን እና የተፈጥሮ ሃብታችን በሕወሓት እና በቢስነስ አጋሩ በአላሙዲ እየተበዘበዘብን ስለሆነ ሚድሮክ ለቆ ይውጣልን ያስረክበት የሚል ድምጻቸውን ያሰሙ ሲሆን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የጅምላ ግድያው እንዲቆም ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ::

በጋምቤላ ውጥረቱ ያየለ ሲሆን በዲማ ወረዳ ሕወሓት አፍሶ ካሰራቸው ነጋዴዎች 21 ሰዎች ውስጥ ከስምንቱ ከእያንዳንዳቸው 15.000 ብር እያስከፈለ ንብረታቸውን ጠቅልለው ከአከባቢው እንዲወጡ በከባድ ማስጠንቀቂያ የፈታቸው ሲሆን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሃገራት ኤምባሲዎች በጥር ወር ጀምሮ እስከ አሁን የካቲት 2016 ድረስ የዘለቀው የጋምቤላው የእርስ በእርስ የጎሳ ግጭት መቀጠሉን እና ወደ አከባቢው የሚንቀሳቀሱ ዜጎቻቸው እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛሉ::
በጋምቤላ ኑዌር ዞን አራት ወረዳዎች አኮቦ ዋንታዎ ጂካዎ ላሬ እንዲሁም በአኙዋክ ዞን ጆሬ ወረዳ በዲማን ጎጌ ኢታንግ በተባሩ የደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያ አከባቢዎች በጎሳ ጦርነት ስላለ ምእራባውያን ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል::የእንግሊዝ መንግስት ለዜጎቹ ባስተላለፈ መልእክት በሰሜን ኢትዮጵያ በኦርትያ ድንበር አዲግራት 10 ኪሎሜትር የቱሪስት መዳረሻ በሆኑት አክሱም ደብረዳሞ የሃ አፋር ደንከል መስመር በኦጋዴን እና በኢትዮጵያ ኬንያ ድንበሮች በጋምቤላ ክልል እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ የድንበር መስመሮች 10 ኪሎሜትር መዳረሻ በምስራቅ ኢትዮጵያ ጅጅጋ ከተማ አፍደር እና ሊበን የሶማለ ኬንያ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር መዳረሻ በደቡብ ምእራብ ሸዋ ላይ አስፈሪ እና አደገኛ ሁነታዎች ስላሉ ዜጎቹ በካርታው በተመለከቱ አከባቢዎች እንዳይንቀሳቀሱ መክሯል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment