Sunday, June 29, 2014

መሬትም ፎቶ ማንሳት የተከለከለበት አገር

የጦማሪያኑን የፍርድ ውሎ የሚከታተለው ሰው ዛሬም እንደወትሮው በጠዋት ነው የተገኘው፡፡ አራት ሰዓት ካለፈ በኋላ የጦማሪያኑ ጠበቃ ‹‹መዝገብ ቤቷ ስለሌለች ነገ ከሰዓት ተብሏል›› ብለው ሲነግሩን በርካታ ህዝብ በተገኘበት አንዲት መዝገብ ቤት በመቅረቷ ብቻ የፍርድ ውሎው እንዲራዘም መደረጉ ገርሞን ስለጉዳዩ እያወራን ለጥቂት ደቂቃዎች ግቢው ውስጥ ቆየን፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እየመጡ ነው ተባለ፡፡
የውሎው ትዕይንት እዚህ ላይ ነው የተጀመረው፡፡

ሶስቱም ጦማሪያን ሲመጡ ህዝቡ በጭብጨባ ተቀበላቸው፡፡ በድንገት እዚህ እዚያ የሚራወጡት ፖሊሶች ወደተሰበሰበው ሰው እየሮጡ በመምጣት የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አባል የሆነችውን ምኞት መኮንንን ‹‹ፎቶ ግራፍ አንስተሻል፡፡›› በሚል ማንገላላት ጀመሩ፡፡ በኃይል እየጎተቱ ሲወስዷትም ዮናታን ተስፋዬ ‹‹እኔን ውሰዱኝ›› ብሎ ምኞትን በኃይል እየገፈተሩ የሚወስዱት ፖሊሶች መሃል ገባ፡፡ ፖሊስ ግን እሱንም ማንገላላት ጀመረ፡፡ እሱንም አብረው ወሰዱት፡፡ ምኞትና ዮናታን ጦማሪያኑን ተከትለው ችሎቱ ወደሚገኝበት ቦታ ከተወሰዱ በኋላ ፖሊሶቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስፈራራት ጀመሩ፡፡

ፖሊሶቹ ከሚመጡበት በኩል የርዕዮት ዓለሙ አባት ጠበቃ አለሙ፣ እህቷ እስከዳር አለሙ፣ ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ፣ 6 ያህል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት አባላትና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ‹‹ወዴት ነው የምንሄደው?›› በሚል እንደማይወጡ አሳወቁ፡፡ ፖሊሶቹ ‹‹ታዘነ ነው፡፡ ትወጡ እንደሆነ ውጡ!›› እያሉ ማስፈራራት ጀመሩ፡፡ ከፊት ያሉት ሰዎች ‹‹ችሎት መከታተል መብታችን ነው!›› ብለው አንወጣም ሲሏቸው እነ ምኞት ላይ የተወሰደውን እርምጃ ትክክለኛነት ለመግለጽ ፎቶ ማንሳት ክልክል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ማስፈራራት ቀጠሉ፡፡ በተለይ አንዱ ፖሊስ ‹‹ያለ ፈቃድ ፎቶ ማንሳት አይቻልም፡፡ ሳይፈቀድ መሬቱንም ቢሆን ፎቶ ማንሳት አይቻልም›› ያለበት ሁሉንም ያስገረመ ነበር፡፡ በዚህ ፖሊስ አባባል የተሰበሰበው ሁሉ እያረረም ቢሆን ፈገግ ብሎበታል፡፡


ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ

ኢሳት ዜና፦ ከምእራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ ወረዳ እንዲሁም ከቀሌም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከአካባቢው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ፣ ችግራቸውን ለአማራ ክልል ርእሰ ማስተዳድር እንዲሁም ለፌደራሉ መንግስት ቢያመለክቱም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል።

ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም። ከመንግስት የሚሰጠው መልስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም ተፈናቃዮች ገልጸዋል

የተፈናቃይ ተወካዮች እንደሚሉት ከፍተኛ ችግር ከነበረበት ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት2 በነበረው ጊዜ ለደረሰው የሰው ህይወት እንዲሁም ለጠፋው ከፍተኛ ንብረት የአካባቢው ባለስልጣናት እና በክልሉ ተሰማርቶ የሚገኘው ልዩ ሃይል እጅ አለበት። ባለስልጣናቱ የችግሩ አሳሳቢነት ሲነገራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የተፈናቃዮች ተወካዮች ተናግረዋል።

በተለይም ጉዳዩን እንዲያጣራ በቅርቡ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ማስረጃዎችን አስቀድሞ ይፋ እያደረገና የምስክሮችንና የጠቁዋሚዎችን ስሞች አስቀድሞ ይፋ እያደረገ ህዝቡ በድጋሚ እንዲጋጭ ጥረት እያደረገ ነው በማለት ተወካዮች ገልጸዋል።

በጊምቢና በቄለም ያሉ ዘመዶቻቸውን በስልክ ለማግኘት መቻላቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮች፣ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ መሆኑን እንደነገሩዋቸው አስረድተዋል።

ከኦሮምያና ከፌደራል የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማክሰኞ ወደ ጊምቢ በማቅናት ነዋሪውን እያነጋገሩ ነው። እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተፈናቃዮችን በተመለከተ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።

በጊምቢ ተነስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲወድም፣ አንድ ፎቅና ሁለት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ቤቶችም ተዘርፈዋል።


ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል። ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን  ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
 ኦቻላ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበረ ጊዜ፣ massakre 13. desember 2003. የ 1000 በላይ  የኣባወራዎች መኖሪያ ቤቶች በገዥው ስርዓት ወታደሮች ሲቃጠልና ከ400 የኣኙዋክ ንጹሃን ተወላጆች በጥይትና በስለት ሲታረዱ በስፍራው  ነበር። ይሄንንም ተከትሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ስልጣኑን በመተው መሰደዱንና ከዚያም ከቤተሰቡ ጋር  በኖርዌይ ”ትሮንዳሄም” በተባለ ቦታ  በስደተኝነት በመግባትና ፈቃድ ጠይቆ በ2009 ዓ.ም የኖርዌጂያን ዜግነት ተሰጥቶት ነበር።የኦኬሎን የፍርድ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሪፖርተር የተሰኘው  ጋዜጣ ችሎቱ  ጁላይ 1 ይውላል ብሎ ቢገልጽም፣ የእኛ Dagbaldet በሲዊድን ያለውን የኢትዮጵያ ኣምባሳደር ለማግኘት ሞክረን ያልተሳካልን ሲሆን፤ ዓለም ኣቀፉን የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅትንም ሆነ በኣዲስ ኣበባ ካለውም የኖርዌይ ኤምባሲ ትክክለኛ የችሎት ጊዜውን ማረጋገጥ ኣልተቻለም።

Saturday, June 28, 2014

ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ ክስ መሰረተች

የህወሐት ገዥ አካል እርሷን እና ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ወደ እስር ቤት እስከወረወረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ እና አሳታሚ ሆና ስትሰራ በቆየችው ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ በጣም ጠንካራና ማስረጃ የሞላው ክስ አቅረባለች፡፡ ሁለቱም ሰርካለም እና እስክንድር (በአሁኑ ጊዜ በሀሰት የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመታት እስራት ተበይኖበት ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው በታዋቂው የ “መለስ ዜናዊ የቃሊ እስር ቤት”በመማቀቅ ላይ ያለው) በዘመናዊ የአፍሪካ የነጻ ጋዜጠኞች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በገዥው አካል ጥቃት የተፈጸመባቸው እና ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትን ያገኙ ሰላማዊ ጋዜጠኞች እስክንድርና ሰርካለም ናቸው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውሰጥ እስክንድር እያንዳንዱን ታዋቂ እና ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ የፕሬስ ሽልማቶች አሸናፊ ነበር :: ከሁለት ሳምንታት በፊት በተወካዩ አማካይነት የተቀበለውን የ2014 ወርቃማ የብዕር የነጻነት ሽልማት ጨምሮ በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

Friday, June 27, 2014

በኢትዮዽያ የዘረኝነት መንስኤዎቹና የሚያስከትለው አደጋ

ሀገራችን ኢትዮዽያ የተለያዩ ቋንቋዎች ፣ የተለያዩ ባህሎችና የተለያዩ እምነቶች ያሉባት ሀገር እንደመሆኗ መጠን እነዚህ ባህሎቿ፣ ቋንቋዎቿ እና እምነቶችዋ ያለመታደል ሆኖ በእኩልነት ተከብረው የማያውቁባት ሀገር ሆና ቀጥላለች። የዘረኝነት መንስኤው ዝርዝሩ ብዙ ቢሆንም ዋነኛው ግን ኋላ ቀር የሆነው የሀገራችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ሁኔታ ነው። ምንጩ ድህነትን ማሸነፍ፣ ፍትህ ማስፈን፣ መብቶች ማስከበር ያልቻለ ያልተሟላ የሀገርና የመንግስት ግንባታ ድክመት ነው። ዛሬም ወደኋላ እየተመለስን በታሪክ የተካሄድ ጦርነቶችንና ወረራዎችን እያነሳን የምንካሰሰው እነሱን ምክንያት እያደረግን የዘር ፖለቲካ ለመቀስቀስ የተመቸን ሌሎች እንደ ኢትዮዽያ በጦርነትና በወረራ የተፈጠሩ ሀገሮች መገንባት የቻሉትን የበለፀገ የዜጎች መብቶች የተከበሩበት ሀገር መገንባት ባለመቻላችን ነው። ብልጽግና፣ እድገትና የዜጎች መብት በእኩልነት መከበር እንዴት ማህበራዊ መግባባትን፣ መቻቻልን፣ ሀገራዊ የሆነ አንድነትን መፍጠር እንደሚችል በአለማችን ብዙ ሀገሮችን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል።

Thursday, June 26, 2014

አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ

ኢሳት ዜና፦ በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት  አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል።

የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣  እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።
በስልጠናው የብአዴን ታሪክ አብሮ መቅረቡንና ሰልጣኞችም የብአዴንን ታሪክ በማወቃቸው መርካታቸውን ሰነዱ አክሎ ይዘረዝራል።

“ግልጽነት ያልተያዘባቸውና በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተከታታይ ውይይትና ስራ የሚጠይቁ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ድረስ ብአዴንን የማይቀበሉ እና ከ97 ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ድምጾች አሉ፣ ነገር ግን የመንግስትን የሃይል እርምጃ ተከትሎ በፍራቻ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሎአል።” ሲል አስቀምጧል።
“በውይይቱ ወቅት የታዩ የአመለካከት ችግሮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በርካታ ችግሮች ተዘርዝረው ቀርበዋል። ” በ1989 ዓም የነበረው የመሬት ክፍፍል ለቢሮክራቶች ለምን 4 ቃዳ መሬት ተሰጠ? በአማራ ክልል ብቻ የአርሶ አደር መሳሪያ ለምን ተነጠቀ? ልማቱ ወደ ትግራይ ይሄዳል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አስመራንና አሰብን መያዝ ነበረብን” የሚሉት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰልጣኞች መቅረቡን ያወሳል።

ሰነዱ በስልጠናው የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችንም ይዘረዝራል። ሰልጣኙ እርስ በርስ በመተጋገዝ፣ በመማማር ተሞክሮውን በማካፈልና በመተራረም የነበረው ሁኔታ በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ለመንግስት ህዝቡ በአብዛኛው ጥላቻ ማሳየቱ” የሚል ሰፍሮአል።

የብአዴን አመራርና አባላት ” በአብዛኛው ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ የለም ” ብለው እንደሚያምኑ፣ “ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ደንታ እንደማይሰጣቸው”፣ እንዲሁም “መንግስትን በትክክል ዋጋ ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ” በሰነዱ ማብቂያ ላይ ተገልጿል።

ሰነዱን ለኢሳት የላኩትን የኢህአዴግን ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ በህዝብ ስም ለማመስገን እንወዳለን።

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!!!!

ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።

ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።

የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።

ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።

ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።

ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።

ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።

የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!


Wednesday, June 25, 2014

የመጨረሻዉ መጀመሪያ


የአገራችንን አንድነት ሊያላሉና ኢትዮጵያ የሚለዉን ታሪካዊ ስም ከታሪክ ዉጭ ማድረግ ከሚችሉ አደገኛ የወያኔ ባህሪዮች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ዘረኝነቱና ለአገር አንድነትና ዳር ድንበር መከበር ያለዉ የግድየለሽነት ባህሪይ ነዉ። ዛሬ ወያኔ በአራቱም ማዕዘን በየቀኑ አየጨመረና እያየለ የሚሄደዉን የህዝብ ቁጣ ለማብረድና አፋፍ ላይ ለደረሰዉ ስርዐቱ ተጨማሪ ግዜ ለመግዛት የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ከዚሁ ከዘረኝነት ባህሪይዉ የሚመነጪ እርምጃዎች ናቸዉ። ወያኔ ዕድሜዉ ሊበረክት የሚችለዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎች መግባባት ሲያቅታቸዉ መሆኑን ያዉቃል፤ ስለዚህም በተቻለዉ መጠን ኢትዮጵያዉያንን የሚለያዩና ግጭት ዉስጥ የሚከትቱ አጀንዳዎችን አየፈጠረ ይወረዉርልናል። ከእነዚህ አገር አጥፊ የወያኔ አጀንዳዎች ዉስጥ አንዱ ህዝብን በዘር ከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዲጋጭ ማድረግ ነዉ። ለምሳሌ በቅርቡ ደቡብ ኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ዉስጥ በንግዱ ህብረተሰብ ላይ የነጋዴዎችን አቅምና ትርፍ ያላገናዘበ ግብር በመጫን በአንድ በኩል ነጋዴዎቹ በዞኑ አስተዳዳሪዎች ላይ እንዲነሱ በማድረግ በሌላ በኩል ደግሞ የዞኑ አስተዳዳሪዎች ነጋዴዎቹን የምትሰሙን ከሆነ ስሙን አለዚያ ክልሉን ለቅቃችሁ ሂዱ የሚል አስነዋሪና የዜግነት መብትን የሚጋፋ መልስ እንዲሰጡ በመገፋፋት በጌዲኦ ብሄረሰብና በዲላና አካባቢዉ በብዛት በንግድ ስራ ላይ በተሰማራዉ የጉራጌ ማህበረሰብ መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ለማድረግ ሞክሯል። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥም እንደዚሁ የጋምቤላ ህዝብ ከጋምቤላ ዉጭ ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡትን ኢትዮጵያዉያን ክልሉ የእናንተ አይደለምና ለቅቃችሁ ዉጡ ብሎ እንዲያሰገድድ በመገፋፋት በኢትዮጵያዉያን መካከል ቂምና ጥላቻ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፉት አምስት አመታት ወያኔ ጋምቤላ ዉስጥ ገበሬዉን እያፈናቀለ መሬቱን ለዉጭና ለአገር ዉስጥ በተለይ ለትግራይ ባለኃብቶች በርካሽ ዋጋ ማስረከቡ የሚታወስ ነዉ። ይህ ባዕዳንን ጋምቤላ ላይ እያሰፈረ ኑና እረሱ እያለ የሚለምን ነዉረኛ አገዛዝ ነዉ ዛሬ ኢትዮጵያዉያንን ከጋምቤላ ዉጡ እያለ የሚያሰገድደዉ።

ጅቡ ሞቷል፡ ቀበሮው እየበላ ነው!

ህወሓትን ስንቃወም የደርግ ናፋቂዎች ይሉናል። ህወሓትን መቃወም ደርግን መደገፍ ነው እንዴ? ደርግን ሳንደግፍ ህወሓትን መቃወም አንችልም እንዴ?ጅቡ ግን ሞቷል። በድን ሁኗል። ሬሳ ነው ያለው። በጎቹ ደግሞ ጅቡ በህይወት እያለ ከቀበሮ በላይ በግ-በሊታ መሆኑ ያውቁታል። ጅብ በአንዴ ብዙ በጎች (ቀበሮ ከሚበላው በላይ) ይበላ እንደነበር በደንብ ያውቃሉ።እናም ቀበሮው “እኔ ስበላቹ የምትጮሁ ከሆነ ጭሆታቹ ጅብን ይጠራል። ጅብ ደግሞ ከኔ በላይ ይበላል። እኔ በቀን አንድ በግ ይበቃኛል። ጅብ ግን በአንዴ ይጨርሳችኋል። ስለዚህ ጅብ እንዳይሰማችሁ አትጭሁ። ዝም ብላቹ ብቻ ጅቡን እንዳይነሳ ጠብቁት፣ ተከላከሉት” ይላቸዋል። በጎችም አምነው ተቀብለው የሞተውን የጅብ በድን እንዳይነሳ ይጠብቃሉ። ቀበሮውም እነሱን አንድ በአንድ ይበላል። ሲበሉ አይጮሁም። ምክንያቱም ከጮሁማ ጅብ ድምፃቸው ሰምቶ ከሞት ይነሳል። ተነስቶ አንድ በአንድ በቀበሮ ሊበሉ የነበሩ በጎች በጅብ በአንዴ ሊበሉ ነው። ጅቡ ግን ሞቷል። አሁን ያለው ቀበሮ ነው። በጎቹ እኛ ህዝብ ነን። ቀበሮው ህወሓት ነው። ጅቡ ደግሞ ደርግ ነው። ጅቡ ሞቷል። ቀበሮው እየበላ ነው። በጎቹ ደግሞ በቀበሮው እየተበሉ የሞተውን የጅብ አስካሬን እንዳይመለስ ሳይጮሁ እየጠበቁ ነው።የሐውዜን ጨፍጫፍ የህወሓት እጅ ነበረበት ማለት ደርግ ጨፍጫፊ አልነበረም ማለት አይደለም። ህወሓት መጥፎ ነው ማለት ደርግ ጥሩ ነበር ማለት አይደለም። ደርግ ሰዎች በልቷል። ህወሓትም ሰዎች እየበላ ነው። በህወሓትና ደርግ ያለው ልዩነት ደርግ ላይመለስ ሞቷል፤ ህወሓት ግን አለ። ስለዚህ ያሁኑ ጥረታችን በህይወት ካለው ህወሓት ጥቃት ራሳችን መከላከል እንጂ የሞተውን ደርግ መኮነን አይደለም። ምክንያቱም ደርግ ባናነሳውም ተመልሶ አይመጣም። ስለዚህ ደርግ ስጋት ሊሆን አይችልም። ያሁኑ ስጋት የህወሓት አገዛዝ ነው።ጅቡ ሞቷል፡ ቀበሮው እየበላ ነው። ጅብን ፈርተን በቀበሮ አንበላም። ጅቡም ቀበሮውም ሊበሉን ልንፈቅድላቸው አይገባም። በጅብም በቀበሮም ከተበላን ያው መበላት ነው። መሞት ነው። ስለዚህ በሁለቱም መበላት የለብንም። ጅቡ ሞቷል፤ ቀበሮው ቀርቷል። የሞተውን ጅብ በመፍራት በህይወት ያለውን ቀበሮ ሲሳይ መሆን የለብንም። ጅብም አንፈልግም፣ ቀበሮውም አንፈልግም። ስለሞተው ጅብ እያወራን ግዜያችን አናጠፋም። ምክንያቱም ሞቷል። ስለ ቀበሮው ግን እንናገራለን። ምክንያቱም ሊጠፋን ይችላል።እረኛ የሌለን በጎች ሆንን! በጅብ ተበላን። አሁንም በቀበሮ እየተበላን ነን። እረኛችን ከወዴት አለህ?ድምፃችንን በማሰማት ከቀበሮ አራዊት ራሳችን እንጠብቅ።
በጎች!

Sunday, June 22, 2014

ጋዜጠኛዋ ከአምባሳደር ጋር ያረገችው ቃለ ምልልስ

  ራኒያ ባደዊ በቃለምልልስ ወቅት አምባሳደር ማህሙድ ድሪር ላይ ስልክ በማቋረጣ ከስራ መታገዷ የሚታወስ ነው።

ጋዜጠኛዋ ከአምባሳደር ጋር ያረገችው ቃለ ምልልስ በ አማርኛ እንደሚከተለው አዘጋጅተናል።

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር ከጋዜጠኛዋ ጋር አድርገውት በነበረው ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንደምትቀጥልና የግድቡ ግንባታ በግብጽና ሱዳን ላይ የሚያሳድረው አንዳችም ጎጂ ተጽእኖ እንደሌለው የባለሙያዎች ቡድን ማረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አምባሳደር ማህሙድ ጋዜጠኛዋን በአነጋገሯ ላይ የሚታየውን ዝቅ አድርጎ የማየትና የንቀት አነጋገር እንድታስወግድ ነግረዋታል፡፡ ጋዜጠኛዋ ከአምባሳደር ማህሙድ ድሪር ጋር አድርጋው የነበረው ቆይታ የሚከተለውን ይመስል ነበር…፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- የተከበሩ አምባሳደር እንዴት አመሹ ?

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- እንደምን አመሸሽ፡፡ በመጀመሪያ ሚንስትሩን ለአዲሱ የሥልጣን ቦታዎ በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያሎት እላለሁ፡፡ በሚንስትር መስሪያ ቤቱና በኢትዮጵያ መካከል የተለመደው መልካም ግንኙነት ይቀጥላል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከበርካታ የግብጽ የሚንስትር መሥሪያ ቤቶች ጋር ተባብረን እየሰራን ነው፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- በጣም ጥሩ፡፡ ይህ ማለት ሁለቱም ልዩነታቸውን አቻችለው ግማሽ መንገድ በመጓዝ መተባበር ይችላሉ ማለት ነው ?

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- በመጀመሪያ ደረጃ…ከሚንስትሩ ጋር ስታወሪ በነበረበት በተደጋገመ ፖለቲካዊ ቃና ነው እያወራሽ ያለሽው፡፡ እኛ ግን አሁን [አቋረጠችው]

ጋዜጠኛዋ፡- የትኛው…በምን መልኩ፡፡ እስኪ ግለጽልኝ፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- ማየት ያለብን አጠቃላዩን የኢትዮ-ግብጽን ግንኙነት እንጂ ጉዳዩን ከህዳሴው ግድብ ጋር ብቻ አያይዞ ማየት ተገቢ አይደለም፡፡ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከዚያም በላይ የላቀ ጉዳይ ነው፡፡ ግድቡ የግብጻውያንን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል የሚለው ሀሳብ በሁለቱ ሀገራት ድርድር ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ እኛ አሁን የደረስንበት…[አቋረጠችው]

ጋዜጠኛዋ፡- እና…የግብጻውያንን ሕይወት አደጋ ላይ የማይጥል ከሆነ ለምንድነው ግብጽ ልዑካኖቿን ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- ይቅርታ…እባክሽን መጀመሪያ እንድጨርስ ፍቀጅልኝ፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- ቀጥል፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- ይሄን ግድብ እንገነባለን፡፡ እናም እንቀጥልበታለን፡፡ ግብጽና ሱዳንንም አይጎዳም፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- ህምምም [በማሾፍ]…እሺ የተከበሩ አምባሳደር…እንደገና የእኔ ጥያቄ…እናንተ ኢትዮጵያውያን ይሄ ግድብ ግብጽ ላይ ችግር አይፈጥርም የምትሉ ከሆነ…እና ለምንድነው ይሄ ሁሉ የኮሚቴ መሰብሰብና ኢትዮጵያ ሄዶ መደራደር ያስፈለገው፡፡ የግብጽ መንግሥት ነገሩ አልገባውም ማለት ነው…? እናም ጊዜውን እያባከነ…እና ምንድነው ነገሩ…፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- አይደለም…አይደለም፡፡ በአንጻሩ ነገሩን በጨለምተኝነት እያየሽው ነው፡፡ እስካሁን የደረስንበት ሁሉ በጎ ነው፡፡ በመጀመሪያ በኢትዮጵያ አነሳሽነት፣ አለማቀፍ ባለሙያዎችን ጨምሮ ከኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የተውጣጡ ባለሙያዎች ያሉበት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቋመ፡፡ ቡድኑም ግድቡ ግብጽንና ሱዳንን እንደማይጎዳና ዓለማቀፍ መስፈርቶችን እንደሚያሟላ ገለጸ፡፡ ሌላው ደግሞ ስለግድቡ ስናወራ ድህነትን ስለመዋጋት እያወራን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለግድቡ ስናወራ ከኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር ተያይዞ አካባቢውን ስለሚያሰጋው የኃይል አቅርቦት እያወራን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በግብርና ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት ከውኃ ሀይል ኤሌክትሪክ ከማመንጨት የተሻለ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆነ ስልት የለም፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- እሺ…እሺ የተከበሩ…ግብጽ በተደጋጋሚ ልማትን ወይም የኢትዮጵያውያን ኑሮ መሻሻልን እንደማትቃወም ገልጻለች፡፡ ግብጽ ልማትን ትደግፋለች፡፡ እናም የመስኖ ሚንስትሩ እንዳሉት ግብጽ ግድቡ ላይ የተወሰነ ስልጣን እንዲኖራት ትፈልጋለች፡፡ እናም በግድቡ ቴክኒካል አስተዳደር ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን፡፡ ግብጽ በሁሉም ጉዳይ ላይ ትስማማለች፡፡ ከዚያ በፊት ግን ግድቡ ወደ በፊቱ ሁኔታ እና መጠን ይመለስ…ያም ማለት አሁን ያለበት 47 ቢሊየን በሰዓት ሳይሆን…[አምባሳደር ማህሙድ አቋረጧት]

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- ይቅርታ…ይቅርታ፡፡ ይሄን ነገር እኮ አልፈነዋል፡፡ ይሄ አሁን የሚመለከተን ጉዳይ አይደለም፡፡ አሁን የሚመለከተን [አቋረጠቻቸው]

ጋዜጠኛዋ፡- አልፈነዋል ስትል ምን ማለት ፈልገህ ነው፡፡ ይህ ማለት አንቀበለውም ማለትህ ነው ወይንስ፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- የሚመለከተን የባለሙያዎቹ ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሀሳብ መተግበር ነው፡፡ እናም ይቅርታ አድርጊልኝና ግብጽ ግድቡ ላይ ይኑረኝ ያለችውን የማስተዳደር ድርሻም በተመለከተ ይሄን የመወሰን ስልጣን የኢትዮጵያ እንጂ የግብጽ አይደለም፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- አሃ…ይሄ ማለት ግድቡን በጋራ እንድናስተዳድረው አትፈልጉም ማለት ነው…፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- ነገርኩሽ…ይሄ የኢትዮጵያ ውሳኔ ነው፡፡

ጋዜጠኛዋ፡- እንደገና ልጠይቅህ፡፡ እንደሚገባኝ አሁንም አሁን ባለው የግድቡ መጠን ላይ ሙጭጭ ብላችኋል፡፡

አምባሳደር ማህሙድ ድሪር፡- ስለግድቡ ምንም የምታውቂ አይመስለኝም እናም ደግሞ በንቀት ስሜት ነው የምትናገሪው፡፡ ይሄ ደግሞ በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለው ንግግር አንዳችም የሚጨምረው ነገር የለም፣ ማንንም አይጠቅምም [አቋረጠቻቸው]

ጋዜጠኛዋ፡- ሚስተር አምባሳደር…መጠንዎን ያለፉ ይመስለኛል፡፡ የእኔን ቃላት ማረም የእርስዎ መብት አይመሰለኝም፡፡ እኔም የእርስዎን ቃላት አላረምክዎትም፡፡ የግብጽ ህዝብ የሚያገባውን ጉዳይ አስመልክቼ መጠየቅ መብቴ ነው፡፡ የተራቀቁ ጥያቄዎች አይደሉም፡፡ መጠየቅ መብቴ ነው ሚስተር አምባሳደር፡፡ እናም ስጠይቅ ወይ መመለስ አለበለዚያም መልስ መስጠት አልፈልግም ማለት፡፡ ጠየቅኩህ - እናም ወይ መልስ አልያም መልስ መስጠት አልፈልግም በል - ያንተ መብት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ መብት የለህም፡፡ የተከበሩ…ከመጠንህ አልፈሀል፡፡ እናም አመሰግንሀለሁ፡፡ በጣም አመሰግንሀለሁ፡፡

ወዲያውኑ ጋዜጠኛዋ አምባሳደሩ የሚሉትን ሳትሰማ ስልኩን ጆሯቸው ላይ ዘግታዋለች፡፡ በዚህ መሃል ስልኩ ከመዘጋቱ በፊት አምባሳደር ማህሙድ “አይደለም…ይልቁንም አንቺ ራስሽ እንደጋዜጠኛ ወሰንሽን አልፈሻል” ሲሉ ተሰምቷል፡፡

በአዋሳ ችግር የገጠመው አንድነት ፓርቲ 

ኢሳት ዜና :-በመጪው እሁድ በአዋሳ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው አንድነት፣ ሶሰትአባሎቹ እንደታሰሩበት አስታውቛል።

አዲስ አበባ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 3 ሰዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።

መስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ለመስጠት በሂደት ላይ በመሆኑ መቀስቀስ አትችሉም መባላቸውን የገለጹት አቶ ያሬድ፣ የእውቅና ጥያቄ ካስገቡ አንድ ወር ሞላቸው በመሆኑ በመስተዳድሩ የቀረበውን ምክንያት እንደማይቀበሉት ተናግረዋል።

የመስተዳድሩ ባለስልጣናት አዋሳ ከተማ ውስጥ የድምጽ ማጉያ  መጠቀም አይቻልም የሚል አቋም እንዳላቸው የገለጹት አቶ ያሬድ፣ ሰልፉን እሁድ እንደሚያካሂዱ በእርግጠኝነት ገልጸዋል።

አንድነት “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል አላማ ሰልፉን የሚካሂድ ሲሆን፣ በኦሮምያ መንግስት የወሰደውን እርምጃ፣ በክልሉ ከማንነት ጋር በተያያዘ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ፣ የሙስና መበራከትና ሌሎችም ጉዳዮች አንስቶ ያወግዛል።

መድረክ በቅርቡ በአዋሳ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወሳል።


Saturday, June 21, 2014

ፍትህ ያጡ የምዕራብ ወለጋ ተፈናቃዮች

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ከቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ ተከትሎ ኢሳት ከጊምቢ በታች በሚገኘው አሹ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን እንዲሁም ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግሮ እንደተረዳው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖች በብዙ መቶዎች ይቆጠራል።
አሹ ቀበሌ ውስጥ የሚኖረው በንግድ ስራ የሚተዳደረው ወጣት እንደተናገረው ወንድሙ አካባቢውን ለቆ ባህርዳር ቢገባም፣ እርሱና ቤተሰቡ ግን ለመውጣት አልቻሉም። ” መውጣት መግባት አልቻንልም፣ ንብረት ተቃጥሎአል፣ ሰዎችም ተገድለዋል” የሚለው ወጣቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት እጅ አለበት ብሎ እንደሚያምን ገልጿል። ድርጊቱን የሚፈጽሙትን ወጣቶች የሚያደራጁት ልዩ ሃይሎች፣ ፖሊሶችና ባለስልጣኖች መሆናቸውን ከድርጊታቸው መረዳት ይችላል ብሎአል
ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል  ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ፖሊሶች ልበሳቸውን ቀይረው እየመጡ ድርጊቱን የሚፈጽሙትን እንደሚያበረታቱዋቸው ገልጿል
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተፈናቃዮችን ቢያነጋገሩዋቸውም፣ ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡዋቸው አለመቻላቸውን ተፈናቃዮች ተናግረዋል ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የመኢአድ የሰሜን ቀጠና ሃለፊ ኢንጂነር ሽፈራው ዋሌ የክልሉ መንግስት ሰዎቹን በአድማ በታኝ ፖሊስ ከመስተዳድሩ አካባቢ እንዲርቁ ማድረጉን ገልጸዋል
ተፈናቅለው ወደ ባህርዳር ከመጡት መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውንም ኢ/ር ሽፈራው ገልጸዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የአማራ ክልል እና የኦሮምያ ክልል ባለስልጣኖችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የኦሮምያ  የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ራብያ ኢሳ ተፈናቃዮቹ መቶ የማይሞሉ መሆናቸውን ገልጸው ፣ አንድ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ እና 2 የሌሎች ብሄር ተወላጆች መሞታቸውን ገልጸው መንግስት ሌሎችም እንዳይፈናቀሉ፣ የተፈናቀሉትም እንደሚለሱ የአማራ ክልልና የኦሮምያ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል

Friday, June 20, 2014

ለመለስ ፋውንዴሽን ማሰሪያ እየተባለ በግዴታ የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈልገው በእጅጉ እንደሚልቅ ታወቀ


ኢሳት ዜና :-ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በሚል በአገሪቱ ያሉ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው በአማካኝ ከ17 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ከህዝብ እንዲሰበስቡ ቢታዘዙም የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈለገው 300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች ትርፉ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። በአማራ ክልል 106 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያ 2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ይሰበሰባል። በኦሮምያ ደግሞ ከ205 በላይ ወረዳዎች ሲኖሩ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል። በትግራይ ከ38 ወራዳዎች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ በደቡብ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ሲዋጣ፣ በአዲስ አበባ የሚወጣው ደግሞ እስከ 2 ቢሊዮን ብር ይደርሳል። በመላ አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎች ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣ ሲሆን፣ ለፋውንዴሽኑ ከተበጀተው 300 ሚሊዮን ብር ውጭ ያለው ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅና ቁጥጥር የሚያደርግ አካል አለመኖሩንም ምንጮች ገልጸዋል። ደሃውበምግብውድነት: ነጋዴውበግብር አርሶአደሩ በማዳበሪያ እዳ እየተሰቃዩ ባለበት ጊዜ ይህን መክፈል አይቻልም በማለት ተቃውሞ ያስነሱ ሰዎች፣ ተቃውሞቸአውን የሚሰማቸው አካል አላገኙም። አንዳንድ ዜጎች ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ለኢሳት በመላክ፣ ዝርፊያው እንዲቆም ህዝቡ ተቃውሞ እንዲያሰማ እየጠየቁ ነው። የመለስ ፋውንዴሽን፣ የቀድሞውን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን የሚዘክሩ ስራዎችን የመስራት አላማ አለው። ፋውንዴሽኑ በህዝብ ፈቃድ እና ከመንግስት በሚሰጥ ገንዘብ ይሰራል ተብሎ ቢነገረም፣ ህዝቡ ለማዋጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በግዴታ እንዲያዋጣ እየተደረገ ነው። ከህዝብ ፈቃድ ውጭ የተሰራ ፋውንዴሽን ፣ ኢህአዴግ እስካለ ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ ፋወንዴሸኑ ከደሃው ኢትዮጵያዊ ገንዘብ መሰብሰቢያና ሃብት ማካበቻ መሆኑንም አክለዋል።


ጦማሪያኑን እና ጋዜጠኞቹን በተመለከተ ችሎቱ ለፖሊስ ጠንካራ ትዕዛዝ አስተላለፈ


በቁጥጥር ስር ከዋሉ ባለፈው ቅዳሜ (ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም) 50ኛ ቀናቸውን በእሰር ያሳለፉት ስድስቱ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ለአራተኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶባቸዋል። ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከዞን 9 ጦማሪያን መካከል ዘላለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሲሆኑ፤ ጋዜጠኞቹ ደግሞ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ እና አስማማው ወ/ጊዮርጊስ ናቸው። በዕለቱ ችሎቱ መርማሪ ፖሊስ የሚያቀርባቸውን ተደጋጋሚ ምክንያት አጠንክሮ በመፈተሽ በቀጣይ ቀጠሮ ፈፅሟቸው ሊመጣ የሚገቡ አራት ተግባራትን በግልፅ በማስቀመጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀለ ችሎት በዕለቱ የቀረቡት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ፖሊስ የመሰረተባቸውን የሽብርተኝነት ክስ በተመለከተ የደረሰበትን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት ነበር። በችሎቱ ጥበት ምክንያት አንዳችም የውጪ ሰው ወደ ውስጥ ሳይዘልቅ የተከናወነው ችሎቱ በብዙዎች ዘንድ “የዝግ ችሎት ነው ወይ?” የሚያሰኝ ጥያቄን ቢያስነሳም ለጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ በጥብቅና የቆሙት ጠበቃ አመሃ መኮንን ግን ችሎቱ ጠባብ በመሆኑ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በዕለቱ በግቢው ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች ዲፕሎማቶችና የታሳሪዎቹ ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተው ነበር።
ፍርድ ቤቱ የማዕከላዊ ፖሊስ በታሳሪዎቹ ላይ ካለፈው ቀጠሮ መልስ አገኘዋቸው የሚላቸውን መረጃዎችና ሰራዋቸው የሚላቸውን ተግባራት በተመለከተ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፤ በከፊል ሰነዶችን ማስተርጐሙን፤ በከፊል የባንክ ማስረጃዎችን ማግኘቱንና በከፊል የቴክኒክ ማስረጃዎችን ስለማሰባሰቡ ቢገልፅም በደፈናው ግን “ብዙ ስራ ሰርተናል፤ ብዙ ስራም ይቀረናል” ሲል ለፍርድ ቤቱ ማስታወቁን ጠበቃው ከችሎት መልስ ተናግረዋል።
በዚህም ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎች ሲቀርቡ፤ በጥቅል መቅረብ እንደሌለባቸውና በዝርዝር እንዲቀርብለት ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም ጥቅል ማስረጃን ማድመጥ እንደማይፈልግ አስታውቋል። ፖሊስ ለስራው መጓተት አሁንም እንደቀደመው ጊዜ ካቀረባቸው ምክንያቶች ውስጥ የምስክሮችን ቃል ስለአለመቀበሉ፤ ተባባሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል መቸገሩንና ወደ ክልል ሀገር ሄደውብኛል በሚል አባሎቹን ልኮ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተከታተለ መሆኑን ከመግለፁም በተጨማሪ አሁንም ሰነዶችን አስተርጉመን አልጨረስንም ሲል አብራርቷል።
የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ ለአራተኛ ጊዜ በጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታውሰው፤ የቱንም ያህል ውስብስብ ወንጀል ቢሆን ተጠርጣሪዎቹ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው 50 ቀናት በቂ ናቸው የሚል መከራከሪያ አሰምተዋል። ጠበቃው አክለውም ይህ የሚያሳየው ፖሊስ ከመነሻው አንድም ማስረጃ ሳይሰበስብ ልጆቹን የያዛቸው መሆኑና ይህም ሕግን የጣሰ ተግባር ነው ሲሉ አስረድተዋል። ሌላው በጠበቆች በኩል የቀረበው አቤቱታ ፖሊስ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ተመሳሳይ ምክንያቶች በመሆናቸው የቀረቡትን ምክንያቶች ውድቅ አድርጐ ተጠርጣሪዎቹን በዋስ እንዲለቅ፤ አልያም ፍርድ ቤቱ ሕጋዊ ምክንያት አለኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ ይህ የመጨረሻ የጊዜ ቀጠሮ ይሁንልን ሲሉ ስለመጠየቃቸው ጠበቃው ተናግረዋል።
የግራ ቀኙን ኀሳብ ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም፤ ፖሊስ በተደጋጋሚ ከሚያነሳቸው ምክንያቶች ውስጥ አራት ጉዳዮችን በመምረጥ በቀጣዩ ቀጠሮ እልባት ሰጥቷቸው እንዲመጣ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ እነዚህ አራት ተግባራትም ተባባሪዎቻቸውን አልያዝንም፣ የምስክሮችን ቃል አልተቀበልንም፣ ሰነዶች ተተርጉመው አልመጡልኝምና ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ በባንክ የተላከላቸውን ገንዘብ በተመለከተ ደብዳቤ ጽፈን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው የሚሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ከዚህ በኋላ ለጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያት ሆነው ሊቀርቡ እንደማይችሉ በመግለፅ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የጊዜ ቀጠሮውን የመጨረሻ ነው እንዳላለ ጠበቃው ተናግረዋል።
በሌላም በኩል የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው መሰናክል መኖሩንና፤ በተለይም ጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስ የወገብ ሕመም ያለበት መሆኑን በመግለፅ ወንበር ወደክፍሉ እንዲገባለት መጠየቁን ነገር ግን አሁንም ድረስ አለመፈፀሙን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱም በበኩሉ መርማሪ ፖሊሶቹ በዚህ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ያዘዙ ሲሆን፤ የተጠርጣሪዎቹን ቤተሰብ መጐብኘትን በተመለከተ ከተደራራቢ ስራና ከአስተደደር ጋር የተያያዘ መሆኑን በመጥቀስ የመከልከል ደረጃ ግን አልተደረሰም ሲል የተፈጠሩት ክፍተቶች እንደሚያሻሽሉ አስረድቷል። የጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስን ጥያቄ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በጤና ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለም በሚል የሰጠውን ትዕዛዝ ለመፈፀም እንደሚቻል አሳውቀዋል።
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ፖሊስ የጠየቀውና ተጨማሪ 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።
ምንጭ፦ ሰንደቅ ጋዜጣ


Thursday, June 19, 2014

ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም /ኢየሩሳሌም አርአያ /

ዝማም ትባላለች፤ የሕወሐት ታጋይ ናት። ባለቤቷ አቶ ቢተው በላይ ይባላሉ። ቢተው እስከ1993 ዓ.ም የደቡብን ክልል በበላይነት ሲያሽከረክሩና ሲመሩ የቆዩ ናቸው። በመጋቢት 93 ከአቶ መለስ ጋር በተፈጠረ የፖለቲካ ውዝግብ ከሌሎች ጋር ተነጥለው ወጡ። ከዚያም ከደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ ጋር በሙስና ተከሰው ዘብጥያ ወረዱ። ፍ/ቤት መቅረብ እንደጀመሩ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ጋር ለዜና ዘገባ ስንመላለስ የቢተውን ባለቤት ዝማምን ተዋወቅኳት። በክልል 14 ቢሮ ተመድባ ነበር የምትሰራው። ባለቤትዋ ከታሰረ በኋላ ግን ዝቅ ተደርጋ በቀበሌ ደረጃ ተመደበች። ዝማም በርካታ ምስጢሮችን ታውቃለች። አርከበ ወደ ከንቲባነት ሊመጡ እንደሆነና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን አቀብላኝ በኢትኦጵ ጋዜጣ ሰርቼዋለሁ። ..ዝማምን ዛሬ እስር ቤት የሚገኘው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴና አየር መንገድ ያለው ሃይሌ አጠመዷት። የሕወሐት ነወረኛ ደህንነቶች ጋር መጠጥ እየተጋተች አንሶላ እንደተጋፈፈች ስገልጽ ከልብ እያዘንኩና ይህን ዘገባ ለምታነበው ሴት ልጇ እየተሸማቀቅኩ ነው። ነገር ግን ይህን ነውረኛ ድርጊቷን ባልዋ አቶ ቢተው እስር ቤት ሆኖ ያውቅ ነበር። እቤቱ ውስጥ በፓርቲው አንጃዎች ይካሄድ የነበረ ስብሰባ እየተቀረጸ አቶ መለስ ዘንድ ተልኳል። ይህ ሁሉ በዝማም የተከናወነ ነበር።… ሳይታወቅ የቆየውን “ኢየሩሳሌም አ..” የብእር ስም በመጠቆምና ለነወ/ስላሴ አሳልፋ በመስጠት የግድያ ሙከራ እንዲፈጸምብኝ ያደረገችው ዝማም ናት። ንጉሴ የተባለ መቶ/አለቃ ተገድሎ ሬሳው ጅብ እንዲበላው የተደረገው በዝማም የሴራ ተባባሪነት ነው። (ታሪኩ ረጅም ሲሆን ይህን ጠንቅቀው የሚያውቁት መጽሃፍ ጽፈው ሲያበቁ ይህን ታሪክ አለማካተታቸው ያሳዝናል) ..እንደ ዝማም ሁሉ ባለቤትዋ ከ6 አመት እስር በኋላ ሲፈታ ያሳየው መገለባበጥ አሳፋሪ ነበር። ከአቶ መለስ ተጠግቶ የአፋር ክልል ባለስልጣን ሆነ። ከዚያም ወደ መከላከያ ኢንጂነሪንግ አመራ። ጭራሽ በዚህ ዓመት በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ “አስታራቂ” ሽማግሌ ሆኖ ተሰየመ። የስብሃት ተከታይነቱንም አረጋገጠ። ባልና ሚስት እጅግ የለየለት ርካሽ ቁማር የተጫወቱ ናቸው። …ባለፈው ሳምንት አንድ ወጣት ልጃቸው በሞት መለየቱን ሰማሁ። ከነርሱ ተግባር ጋር ልጁ የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በመሞቱ ከልብ አዝኛለሁ። ፈጣሪ ነፍስ ይማር!!
(ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም ይህቺ ናት)


Wednesday, June 18, 2014

የሀገራችን 11 በ100 እድገት ሲለካ

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ኢትዮጵያን ከዓለማችን ደሃ ሀገራት ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡
Multidimensional Poverty Index (MPI) የተባለውና የዓለማችንን 108 በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የድህነት ደረጃ የፈተሸው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ጥናት ኢትዮጵያን ከ108ቱ ሀገራት ከኒጀር ብቻ በልጣ ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

ደረጃው በትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥኑ 10 መስፈርቶች ሲኖሩት ከ10ሩ መስፈርቶች አንድ ሦስተኛውን እንኳ ያላገኘን ደረጃው ዘርፈብዙ ደሃ (Multi-dimensionally poor)ሲለው፣ ከመስፈርቱ ዝርዝር ውስጥ አንድ ሦስተኛው ያህል የተሟላለትን ደግሞ ለኑሮ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) ይለዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ህዝብ 87.3% ያህሉ ዘርፈብዙ ደሃ በሚለው ክልል ውስጥ ሲገኝ 58.1%ቱ ደግሞ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) በሚለው ክልል ውስጥ እንደሚገኝ የጥናት ውጤቱ ያስረዳል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ውስጥ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉላቸው (Destitute) ዜጎቿን ቁጥር በመቀነስ ረገድ ጥሩ ውጤት ብታስመዘግብም ኢትዮጵያ አሁንም የ76 ሚሊየን ዘርፈብዙ ደሃ ህዝብ ሀገር ናት ይላል የጥናት ውጤቱ፡፡

ይህም ቁጥር በዓለማችን ካሉ መሰል በርካታ እጅግ ደሀ ሕዝብ ከያዙ ሀገራት ማለትም ከህንድ፣ ቻይና፣ ባንግላዴሽ እና ፓኪስታን በመቀጠል ኢትዮጵያ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ የደረጃው ዝርዝር የገጠሪቱን ኢትዮጵያ አስመልክቶ 96.3% የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ ሲገልጽ በአንጻሩ ከከተማ ነዋሪው 46.4 %ቱ በድህነት ውስጥ እንዳለ ያስረዳል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚስተዋለውን የድህነት ደረጃ አስመልክቶም በሶማሊያ 93% በኦሮሚያ 91.2% በአፋር 90.9 % በአማራ 90.1 % በትግራይ 85.4 % ህዝብ በድህነት ውስጥ እንዳለ ይገልጻል፡፡ ከተሞችንም በተመለከተ አዲስ አበባ ከሌሎች ከተሞች ይልቅ አነስተኛ ደሃ (20%)ያለባት ስትሆን ድሬዳዋና ሐረር ደግሞ አነስተኛ ደሃ በመያዝ በ54.9% እና በ57.9% ይከተላሉ፡፡

 ወደ 5000 የሚጠጉ ቤቶችን መንግስት ለማፍረስ ቀይ ቀለም እየቀባ ነው 

(ዘ-ሐበሻ) ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ቀበሌ 1 በተለምዶ ስሙ ሃና ማርያም ጀርባ በሚገኘው ልዩ ስሙ ቃሬሳና ኮንቶማ ሰፈር ወደ 5000 የሚጠጉ ቤቶችን መንግስት ለማፍረስ ቀይ ቀለም የቀረባ ሲሆን ክፍለከተማውን ነዋሪውን አናውቃችሁም ትነሳላችሁ ማለቱን ተከተሎ ከ 1000 በላይ ኢትዮጵያውያን መድረሻ አጣን በሚል የኢሕ አዴግ ተለጣፊ ነው ወደ ሚባለው ወደ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማምራት ሰልፍ የወጡ ሲሆን፤ ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን መጥቶ ቪድዮ እስከሚቀርጽ ድረስ ከተበቁ በኋላ የሕዝቡን እሪታ “የሰብአዊ መብት መጣስ ጉዳይ መሆኑን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል፤ ለአሁኑ ግን 10 ኮሚቴ መርጣችሁ ተነጋግረን መልስ እንሰጣችኋለን” ማለታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታውቀዋል።

የጉዳዩ ባለቤቶች ከአዲስ አበባ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩልን መረጃ መሰረት በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤት ማፍረሱ የተጀመረ ሲሆን ሕዝቡ ካለምንም መተኪያ መድረሻ አታሳጡን እያለ እሪታውን ቢገልጽም ፖሊስ በአካባቢው መጥቶ ወጣቶችን በቆመጥ እንደደበበደ ታውቋል። በአካባቢው ያለው ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሕዝቡ እየተቃወመ መንግስትም ካለምንም መተኪያ “አናውቃችሁም፤ ከአካባቢው ልቀቁ” በሚል ማፍረሱን መቀጠሉን ነዋሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ጠቁመው፤ ወጣቶቹም ከፖሊስ ጋር ግብግብ ላይ መሆናቸውን ገልጸውልናል።


በመጥፋት ላይ ያለው የወልቃይት ጠገዴ ፀለምት ህዝብ

የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንግዳ ሆነው ቀርበው የነበሩት አንጋፎቹ ፖለቲከኞች አቶ ቻላቸው አባይ እና አቶ ጎሹ ገብሩ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብና እየተፈፀሙበት ስላሉት ኢሠብዐዊ ድርጊቶች ዙሪያ ሠፊ ውይይት አካሂደው ነበር ውይይቱ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ስለአካባቢው ፖለቲካ ከፍተኛ መረጃ የሚሠጥ ከመሆኑም በላይ አሳዛኝ የሆኑ እውነታዎች የተነሡበት ነበር፡፡

የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በትግርኛ አጠራሩ ህወሀት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ግፎችን በወልቃይት ህዝብ ላይ እንደፈፀመ ያስረዱት ተወያዮቹ በ1984 በአካባቢው ይኖር የነበረው ቁጥሩ ከ83,000 በላይ እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ወቅት ይህ አሐዝ ወደ 48,000 እንደወረደ ለማወቅ ተችሏል 35,000 ያህል የወልቃይት ጠገዴ ፀለምትን ህዝብ ምን ዋጠው መቼም ሁሉም ሠው በእርጅና እና በበሽታ ሞቷል አይባልም ቢሞትስ አካባቢው ላይ ሟች ብቻ ነው እንዴ ያለው ተወላጅ አይኖርም የወልቃይት ማህፀኖች ልጅ አያፈሩም?

ህወሀት ገና ጫካ በነበረበት ሠዓት ከድርጅቱ አመራሮች አንዱ የሆነው ስብሐት ነጋ መኮንን ባዘዘው ወይም በትግል ስሙ ዮሴፍ ባዘዘው የተባለን አባቱ የወልቃይት እናቱ የትግራይ ሰው ከሆኑ ቤተሰብ ውስጥ የተገኘን ታጋይ የወልቃይት ህዝብን ከትግራይ ጋር የመገንጠል ፍላጎት እንዲያጣራ እና ጥናት እንዲሠራ በሚል ወደወልቃይት ይላካል ሪፖርቱ ግን ለእነ ስብሐት ነጋ እና ጓደኞቹ አስደንጋጭ ነበር አንድም የወልቃይት ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር አብሮ በመሆን ከኢትዮጵያ መገንጠል እንደማይፈልግ በማሳወቁ የህወሀት አመራሮች ጥርስ ውስጥ እንደገባ አቶ ቻላቸው እና አቶ ጎሹ ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ቂም በቀል ውስጥ የገባው ህወሀት አቶ ልጅዓለም የተባሉ የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን መግደል፣ማሠር እና ማሳደድ ጀመረ፡፡ የወልቃይት ህዝብ ከሞት ለማምለጥ በርካታ ጥረትን ቢያደርግም ተሳክቶለት ከሞት የተረፈው ግን እጅግ ጥቂቱ ነው፡፡

የወልቃይት ህዝብ በብዛት ይኖርባቸው ከነበረባቸው አካባቢዎች አንዷ ሁመራ ነች በሠላሙ ጊዜ የወልቃይት ህዝብ ለእርሻ ምቹ የሆነውን የሁመራን መሬት አርሶ ይኖር እንደነበር የገለፁት ፖለቲከኞቹ በወቅቱ ከሁመራ ህዝብ ከ80 በላይ የወልቃይት ተወላጅ እንደነበር በአሁኑ ወቅት በአስደንጋጭ ሁኔታ በሁመራ የሚኖር የወልቃይት ህዝብ 11 ቤተሠብ ብቻ ነው፡፡ ይህንን የወልቃይት ህዝብ ችግር ኢህአዴግ ሐገሪቱን ከተቆጣጠረበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግስት በየጊዜው ሪፖርት ቢያደርጉም የመንግስት ባለስልጣናት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የወልቃይት ህዝብ እንደጨፈጨፉ እና እንዳሳደዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከመንግስት በላስልጣናት መካከል ህወሀት ከመከፋፈሉ በፊት የመከላከያ ሚኒስቴር የነበረው አቶ ስዬ አብርሐ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሔ የህዝቡ ጉዳይ በድምፀ ውሳኔ እንደሚፈታ ይናገሩ እንደነበር ገልፀው አቶ ገብሩ አስራት ግን እጅግ አስነዋሪ የሆነ ስድብ የወልቃይትን ህዝብ ሲሳደቡ እንደነበር አውስተዋል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በርካታ ስድተኛ የወልቃይት ተወላጅ ወደአለበት ኮሎምቦስ አሜሪካ መጥተው የነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቴዎድሮስ አድሐኖም ከ2000 በላይ የወልቃይት ተወላጆችን አነጋግራለው ብለው አስበው የነበሩ ቢሆንም የስብሠባ አደራሹ ውስጥ የተገኘው የወልቃይት ተወላጅ ቁጥር 13 ብቻ ነበር፡፡ በሌላ በኩል በ2007 እ.ኤ.አ በሟቹ ጠ/ሚኒስቴር ትዕዛዝ በኮሎምቦስ የወልቃይት ተወላጆችን ለመደለል ኮሎሞቦስ የተገኙት የወልቃይት ዞን አስተዳዳደሪ የነበሩት አቶ ፈረደ የሺወንድም ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ ገልፀው ወደሀገራቸው ለሚመለሱ ወልቃይቶች የእርሻ መሬት እና ትራክተር እንደሚያመቻቹ የገለፁ ቢሆንም በወልቃይቶች ወያኔ ድሮውንም አጭበርባሪ ስለሆነ ማመን የለብንም በማለታቸው ጥቂቶችን ብቻ አሳምነው ሄደዋል እርሳቸውን ተከትለው ወደሑመራ የተጓዙት ዲያስፖራዎች በትግራይ ክልል አመራሮች ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸው ዳግም ስደተኛ ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው የወልቃይት መሬት ወደትግራይ ቢጠቃለልም እና ስልጣን ላይ ያሉት በርካቶቹ የትግራይ ተወላጆች ቢሆኑም ከአዜብ መስፍን በስተቀር የወልቃይት ህዝብን ከድቶ ባለስልጣን የሆነ እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የወልቃይት ህዝብ ጎንደሬ፣ አማራ እና ኢትዮጵያዊ እንጂ ትግሬ አለመሆኑን ገልፀው በአሁኑ ሠዓት በመሬቱ ዙሪያ ህዝበ ውሳኔ ይካሄድ ቢባል እንኳን በስፍራው የሰፈሩት አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸው ምንም ፋይዳ የለውም ካሉ በኋላ የወልቃይን ህዝብ ችግር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ መፍታት ያለበት ጉዳይ ነው ኢትዮጵያ በቅርቡ ነጻ ትወጣለች የወልቃይት ህዝብ ጉዳይ ካልተፈታ ግን ነፃ በምትወጣው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የወልቃይት ተወላጅ ማግኘት ከባድ ይሆናል ።

ሁን አቢስኒያውይ


የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉት ዜጎች ለክስ የሚያበቃ በደል አልደረሰባቸውም አለ።

ኢሳት ዜና፦ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሰረቱት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሄር ምድብ በዋለው ችሎት የታየ ሲሆን ፣ በቀረበው ክስ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤንሻንጉል ክልል መንግስት መልስ ሰጥተዋል።

ከሳሾች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ቀየ በህገወጥ መንገድ በመፈናቀላቸው ሃብትና ንብረታቸውን ማጣታቸውን በጠበቃቸው አማካኝነት ተናግረዋል።

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ከሳሾቹ ቤት ንብረት አለማፍራታቸውን ጠቅሶ፣ ምንም ለክስ የሚያበቃ ነገር ሳይኖራቸው ጉዳያቸው ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ላይ ያነጋገርናቸው ጠበቃው ዶ/ር ያእቆብ ሃይለማርያም  የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‘ጉዳዩ የሚመለከተው የክልሉን መንግስት እንጅ የፌደራሉን አይደለም’ በማለት የሰጠው መልስ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል። የህገመንግስቱ አንቀጽ 52 ማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም የፌደራል መንግስቱን እንደሚያገባው፣ በዚህም የተነሳ የፌደራል መንግስቱ አይመለከተኝም ማለት እንደማይችል ገልጸዋል።

ዶ/ር ያእቆብ   ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ‘ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ያደረጉትን ለፍርድ እናቀርባለን’ በማለት ተናግረው  እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን እየታየ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ነው ሲሉ አክለዋል።


Tuesday, June 17, 2014

የትግራይን መስቀል ስለመሸከም ….ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

…ዕለቱ የሁለት ሺ ሶስት ዓመተ ምህረት የመስቀል በዓል የተከበረበት ማግስት፤ ሰሜናዊቷ የኤርትራ አዋሳኝ ወልቃይት ገና ከእንቅልፏ ሙሉ ለሙሉ ባለመንቃቷ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ጎፈሪያቸው የተንጨ(ባረረ ፋኖዎች በውስጧ ካሉ ተቋማት ወደ አንዱ እያመሩ ስለመሆኑ የጠረጠረች አትመስልም፤ ከኤርትራ የተነሱት ፋኖዎች መዳረሻ በወረዳዋ ታዋቂ የሆነው አወርቅ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመሆኑ፤ ማንም ልብ ሳይላቸው ልክ እዚያው እንደደረሱ፣ ከፊሎቹ በሰለጠነ ወታደራዊ ስልት ትምህርት ቤቱን ከአጥር ውጪ በመክበብ ድንገተኛ ጥቃት የሚሰነዝር ኃይል ከመጣ ለመከላከል ሲያደፍጡ፤ የተቀሩት ደግሞ ወደ ውስጥ በመግባት በግቢው የሚገኙ መምህራን ሜዳው ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ፤ በጥቂት ደቂቃዎችም ውስጥ ሁሉም በተባለበት ቦታ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በዕቅዱ መሰረት መፈፀሙን በጥንቃቄ ሲከታተል የነበረው የቡድኑ መሪ በቅድሚያ ስለራሱና ጓደኞቹ ማንነት እና ስለወከሉት ድርጅት አጭር ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የትግሉን ዓላማ በስፋት አብራርቶ አስረዳ፤ ሌሎች ጓዶቹም የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ዋና ዋና ርዕሶች የሚገልጹ በአማርኛና ትግርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን የማደል ስራቸውን በማጠናቀቃቸው እንደአመጣጣቸው በሽምቅ ተዋጊ ስልት ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡ ይህ በሆነ በአስራ ሁለተኛው ቀን (መስከረም 30) ደግሞ እዛው ወረዳ ወደሚገኝ ሌላ ትምህርት ቤት ለተመሳሳይ ዓላማ ድንገት ተመልሰው መጥተው ነበር፤ ሆኖም መንገድ ላይ ካደፈጡ ፖሊሶችና ታጣቂዎች ጋር ፊት ለፊት ተገጣጥመው በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ከእነርሱ ወገን አንድ ሲሰዋ፤ ከፖሊስ አባላት አንድ ቆስሏል፤ አንድ መምህርም በገዛ ቤቱ በተቀመጠበት በተባራሪ ጥይት ቆስሏል፤ ፋኖዎቹም የዚያ ቀን ዓላማቸው ከሽፎ ወደመጡበት የኤርትራ በርሃ ተመልሰው ለመሄድ ተገድደዋል…Temesgen Desalegn “Fact” Ethiopian Amharic newspaper editor

በ10 እስር ቤቶች የተከሰተው ኩፍኝ 9 ሰዎችን ገደለ

 ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው ከ4000 በላይ በሚገመት ታራሚዎች ላይ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች 9 እስረኞች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
“መንግሰት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ በቂ የማረሚያቤት ሰራተኛ የለኝም ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ፤ የህክምና አገልግሎት አይሰጥም” በሚሉ ሰበቦች  አደጋው እንዲባባስ እና ለእስረኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ መረጃው ያመለክታል።
የኢትዩጵያ የቀይ መስቀል ቡድን በሁለቱ ክልሎች በሚገኙ 16 እስር ቤቶች መንቀሳቀሱም ታውቋል፡፡
በአንድ ክፍል እስከ 50 እስረኞች ታጭቀው በህመም እንደሚሰቃዩ ፤ ለህመማቸውም ተገቢ ህክምና እንዲያገኙ የሚያግዛቸው አካል እንደለሌ መረጃው አመልክቷል።
ከሟቾቹ ውስጥ 3ቱ የሱማሌ ዜጎች ናቸው።
በያዝነው አመት በፌደራል ደረጃ 252 ሺ 104 ኢትዩጵያውያን በእስር ላይ እንደሚገኙ የፌደራል ማረሚያ ቤት የ9 ወር ሪፖርት ያመለክታል።  በክልሎች የታሰሩት እስረኞች ቁጥር ግምት ውስጥ ሲገባ በመላ አገሪቱ ከ600 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ታስረው ይገኛሉ።

በሃረር ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ ዘይት ችግር ተከሰተ


ኢሳት ዜና :-ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በከተማዋ በተለይም ቀበሌ 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19 እንዲሁም በሸንኮራ፣ ጀጎልና ቀለዳምባ አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመከሰቱ ህዝቡ የጀኔሪካን ውሃ በውድ ዋጋ ለመግዛት ተገዷል።
የክልሉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት ከሃረር በ75 ኪሜ ርቀት ላይ አሰሊሶ  በሚባለው ቦታ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ካስቆፈራቸው 17 የውሃ ጉድጓዶች መካከል 6 ቱ በመደፈናቸው ችግር መፈጠሩ ታውቋል። በስራ ላይ ከሚገኙት 11 ጉድጓዶች መካከል 2ቱ ተመሳሳይ የመደፈን እጣ እየገጠማቸው ነው።
ጉድጓዶቹ ከመቆፈራቸው በፊት ባለሙያዎች አስቀድመው አስጠንቅቀው የነበረ ቢሆንም፣ በከተማው ውስጥ አጋጥሞ የነበረውን አሳሳቢ የውሃ ችግር ለመቅረፍ በሚል በፖለቲካ ውሳኔ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው እንዲገነቡ ተደርጓል።
በሌላ ዜና ደግሞ መንግስት የሚያከፋፍለው ዘይት በከተማው ውስጥ በመጥፋቱ ፣ ቀድሞ 115 ብር ይሸጥ የነበረው ዘይት ነጋዴዎች 175 ብር እየሸጡ ሲሆን በአገር ውስጥ የሚመረተው ዘይት ደግሞ በሊትር 40 ብር እየተሸጠ ነው።
በከተማዋ የተከሰተውን የውሃ እና የዘይት እጥረት በተመለከ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ቀጣዩ ኢታማዦር ማን ነው?

‹‹ደመወዝ አነሰኝ ብሎ ጭማሪ የሚጠይቅ ካለ አሁንኑ ከሰራዊቱ መልቀቅ ይችላል፡፡›› ይህ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም የሆነው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ሁለተኛው የሰራዊት ቀን በተከበረበት ሰሞን ባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ ከተሰበሰቡት የሰራዊቱ አባላት መካከል የደመወዝ ጭማሪን በተመለከተ ለተነሳለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ የተናገረው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ዘመናዊ ውትድርናና የጦር ስልት ሰልጣኝ ወታደሮችንና መኮንኖችን በተደራጀ ስልጠና ማፍራት መጀመሯ ይጠቀሳል፡፡ በሀረርና ሆለታ የጦር አካዳሚዎች በመታገዝ ዘመናዊ የውትድርና ሳይንስ ትምህርት መሰጠት የተጀመረው በዚሁ በንጉሱ ዘመን ነበር፡፡ በዚህ መልኩ እየተደራጀ የመጣው የሀገሪቱ ሰራዊት እስከ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን መምጣት ዘመን ድረስ የሀገሪቱ ብሄራዊ ሰራዊት ሆኖ ለመዝለቅ ችሏል፡፡ ሆኖም የደርግ ውድቀትን ተከትሎ በነበረው ጊዜ አያሌ የሰራዊቱ አባላት ለስደትና ሞት እንዲሁም ለብተና ለመዳረግ በቅተዋል፡፡

(በእርግጥ ቀደም ብለው የተማረኩትን የቀድሞው የሰራዊቱ አባላት በኢህአዴግ ውስጥ ማግኘት እንደሚቻል ኩማ ደመቅሳ (የፖሊስ መቶ አለቃ እነደነበር ይነገርለታል)፣ እና ተራ ሚሊሻ እንደነበር የሚነገርለት አቶ አባዱላ ገመዳን ከፊት መስመር ላይ በማስቀመጥ መጥቀስ ይቻል ይሆናል፡፡ እንደነዚህ ያሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ደርግ ከመውደቁ በፊት ከድተው የህወሓትንና የኢህዴንን ታጋዮች የተቀላቀሉት ናቸው፡፡)

እናም በጊዜው ታጋዮች ሀገሪቱን በሙሉ ለመቆጣጠር መቻላቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰራዊት (የደርግ ሰራዊት ብቻ ብሎ ማቃለሉን አልፈለግሁትም) ሜዳ ላይ ተበትኖ እንደቀረ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም የኢህአዴግ ሰራዊት ሲያሸንፍ ሊያስተምሩት የሚችሉ አንዳንድ የቀድሞው ሰራዊት አባላት መኮንኖችን ብቻ አስቀርቶ ሌላውን ወደጎን ገፍቶታል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ሙሉ ለሙሉ ሲፈርስ ያለቀው ሰራዊት አልቆ በዚያው የሸሸውም የመን ላይ ለእስር ተዳርጎ ከፍተኛ ስቃይ መጋፈጡ የአደባባይ እውነት ሆኖ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያለ አንዳች ባህር ኃይል፣ ያለ አንዳች የተፈጥሮ የባህር በር የቀረች ሀገር ለመሆን ተዳርጋለች፡፡ አሁን ያለው መከላከያ ሰራዊታችን የምድርና የአየር ኃይልን ብቻ ያቀፈ ነው፡፡ የምድር ኃይሉ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ በቀድሞ ታጋዮችና በቅርብ ጊዜ ምልምሎች የተደራጀ እንደሆነ ሲነገርለት፣ አየር ኃይሉ ላይ ግን ኢህአዴግ እንደገባ የአየር ኃይል ሳይንስን እንዲያስተምሩት የመረጣቸውን ጥቂት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትን በውስጡ የኋላ ደጀን አድርጎ ይዞ መቆየቱ ይነገራል፡፡

Monday, June 16, 2014

እባክዎትን ያንብቡት  (የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአቶ አንዷለም አራጌ መልእክት)

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

“‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።…”
ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ። የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር።

…እስክንድርን እና አንዷለምን አስጠራናቸው፡፡ ሁለቱም ሲያዩን ደስ አላቸው፡፡ በተለይ በተለይ የእስክንድር ፈገግታ በጣም ደማቅ ነበር። ተከፋፍለን ከሁለቱም ጋር ሃሳቦችን መለዋወጥ ጀመርን፡፡ እስክንድር በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሸላሚ በመሆኑ

‹‹እንኳን ደስ ያለህ››

አልኩት።

የወ/ሮ አዜብ መስፍን ነገር

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ለሕወሐት ማ/ኮሚቴ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች አስታወቁ። ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ በፓርቲው የነበራቸው ተሰሚነትና የበላይነት እየተሸረሸረ በመምጣቱና ከኤፈርት ሃላፊነታቸው በመነሳታቸው እንዲሁም ጓጉተውለት የነበረው የአዲስ አበባ ከንቲባነት ስልጣን በማጣታቸው፣ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት ለፓርቲው የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በተጨማሪ አዜብ ይተማመኑባቸው የነበሩት ሹማምንት ከስልጣን እየተገፉ ገሚሶቹም እስር ቤት መወርወራቸው እንዲሁም በስብሃት ነጋ ቡድን እየተወሰደባቸው ያለው ፖለቲካዊ የበላይነት መቋቋም ስለተሳናቸው ከፓርቲው በግዜው መሰናበት እንደመረጡ ከምንጮቹ መረዳት ተችሏል። አዜብ መስፍን ላቀረቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ፓርቲው በቅርቡ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያመለከቱት ምንጮች፣ አያይዘውም ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ አዜብ በሲውዲን ወይም አሜሪካ ቨርጂኒያ በገዙት መኖሪያ ቤት ጠቅልለው ሊገቡ እንደሚችሉ አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከኢታማጆር ሹመታቸው በማስነሳት በምትካቸው በቅርቡ ሌ/ጄ ተደርገው የተሾሙትን ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀልን ለመተካት መታቀዱን ምንጮች ጠቁመዋል።
ከእየሩስአሌም አርአያ

 ከጠበቃ አምሐ ጋር በፍርድቤት ውስጥ የተደረገ ቃለ ምልልስ

የስድስቱን ጦማርያንና የሁለቱን (የኤዶምና የተስፋለምን)ጉዳይ በመከታተል በፍርድ ቤት እየወከሏቸው የሚገኙት የህግ ባለሞያ አቶ አምሐ ሁልግዜም የህግ ደምበኞቻቸው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ግቢው ውስጥ ውጪ ለምንጠብቃቸው ጋዜጠኞች በዝጉ ችሎት ምን እንደተከናወነ ያለምንም መሰላቸት ያስረዳሉ፡፡በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎም ጠበቃው ከዋናው ግቢ ውጪ አሰፍስፈን ለጠበቅናቸው ጋዜጠኞች መረጃ አድርሰውናል፡፡ለተባባሪነታቸው፣ድካም ሳይነበብባቸው፣አንተ ወይም አንቺ ከየትኛው ሚዲያ ነህ/ሽ ሳይሉ ለሚዥጎደጉድላቸው ጥያቄ ምለሽ በመስጠታቸው ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡

ጥያቄ —በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ፖሊስ አዲስ ያቀረበው ነገር ምንድን ነው ? ጠበቃ አምሐ –አዲስ ያቀረበውን ነገር በዶክመንት መልክ አላቀረበም፡፡በቃል ያሉት የተወሰኑ ምስክሮችን መስማት መጀመራቸውን፣ለባንክ ቤቶች ለጻፍነው ደብዳቤ ከአንዳንዶቹ ምላሽ አግኝተናል፣የተወሰኑ ዶክመንቶችን አስተርጉመናል ነው ያሉት፡፡ነገር ግን ምን ያህል ምስክሮችን ለመስማት አቅደው ምን ያህሉን ማድመጥ እንደቻሉ አልተናገሩም፣ያስተረጎሟቸው ዶክመንቶች ጠረጠርንበት ለሚሉት ወንጀል ያለው አስረጂነት /ተቀራራቢነት ምን እንደሆነም አልገለጹም ፡፡ ጥያቄ– ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ጊዜያት በፖሊስ ለሚጠየቀው የምርመራ ጊዜ እየፈቀደ ነገር ግን ቀጠሮ የተፈቀደበት ምርመራ ሳይከናወን ሲቀር ፖሊስ መጫን አይችልም ? ጠበቃ አምሐ — የእኛም ትልቁ መከራከሪያ ይህው ነበር፡፡ፖሊስ ቀጠሮ የጠየቀበትን ምክንያት ሳይሰራ የተለያዮ ሰበቦችን እያቀረበ ደምበኞቼን እያጉላላ ነው ብለናል፡፡አሁን ግን ፍርድ ቤቱ ጠንከር ያለ ትዕዛዝ በመስጠት ይህው ትዕዛዝም መዝገቡ ላይ እንዲሰፍር አድርጓል፡፡አሁን የተሰጠው የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ ጊዜም የመጨረሻው እንደሚሆን ፍርድ ቤቱ ገልጻል፡፡እኛም ይህ ትዕዛዝ መዝገብ ላይ መስፈሩን አረጋግጠናል፡፡ ጥያቄ– በየቀጠሮው ዳኞች እተቀያየሩ መቅረባቸው አሁን ተስፋ የሚያደርጉት ነገር ላይ ተጽእኖ አይፈጥርም ? ጠበቃ አምሐ — አይፈጥርም በማለት መናገር አልችልም፡፡ለምሳሌ ከዚህ ቀደም አንድ ዳኛ ከመነሻው ክሳችሁን በሽብርተኝነት ያላደረጋችሁት በመሆኑ አሁን መለወጥ አትችሉም በማለት ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ሊመራ እንደሚችል ተናግረው ነበር፡፡

Sunday, June 15, 2014

የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኛው ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ያለምንም ክስ ላለፉት 50 ቀናት ፖሊስ የምርመራዬን አልጨርስኩምና ተጨማሪ ቀጠሮ ይሰጠኝ ጥያቄና በፍርድ ቤቱ መፍቀድ የተነሳ እየተጉላሉ የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያን እና ጋዜጠኛው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ተጨማሪ 28 ቀናት ፖሊስ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታውቀዋል።

በፌደራል ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ የቀረቡት ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ሲሆኑ ጉዳያቸውን ለመከታተልም በርካታ ሰዎች ፍርድ ቤት መገኘታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። እንደዘጋቢዎቹ ከሆነ ባልተነገረ ክስ ላለፉት 50 ቀናት በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙት ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ መንፈሳቸው ጠንካራ እንደነበር ለማየት ተችሏል። የታሳሪዎቹ ወላጆችና ሴቶች በፍርድ ቤቱ ሲላቀሱ እንደነበር ያስተዋሉት ዘጋቢዎቻችን ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ ብዙዎችን እንዳበሳጨ ጠቁመዋል።

ዘ-ሐበሻ

የግንቦት 7 ሳምንታዊ ርዕሰ አንቀፅ

የወያኔ ጉጅሌ ራሱ ከሳሽ፣ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ በሚገዛት ሀገራችን ውስጥ የሚያካሂደው ግፍ አንድ ህዝብ ሊሸከመው ለሚችለው በላይ ሆኗል።

የወያኔ ሹማምንትና በዘር ለዝርፊያ የተሰማራው ድርጅታቸው በቅርቡ ደግሞ ስዘርፍ አያችሁኝ በሚል ቁጣ ከአንደበታቸው በላይ ምንም ባልታጠቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ አልፎ ግለሰብ ተማሪዎችን በማሳደድ ሰቆቃ መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በዚህ ሰአት በርካታ ተማሪዎች በታወቁና ባልታወቁ እስር ቤቶች ታጉረዋል። ብዙዎቹ ከትምህርት ገበታ ካላንዳች ጥያቄ ተባረዋል እየተባረሩም ይገኛሉ።

ከወያኔ ግፎች ሁሉ በእጅጉ የሚዘገንነው ሌሎችን በመወንጀል ማሰቃየትና መግደል በፈለገ ቁጥር ራሱ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ ወንጀሉን በሌሎች ላይ ለማመኻኘትና ለመቅጣት የሚጠቀሙበት የሃሳብ ዘዴ ነው።

በአለምያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ የደህንነት አባሎች ቦንብ አፈንድተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ የሚፈልጓቸውን ወጣቶች ቦንብ ሲያፈነዱና ሲጠምዱ ያዝናቸው በማለት ከዚህ በፊት በዊክሊክ መረጃ እንደተለቀቀው የተለመደ በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃ ይፈጽማሉ። ሌላው ቀርቶ ቦምብ አፈነዱ ተብለው የተከሰሱት ተማሪዎች በገዛ ጓደኞቻቸው ላይ ቦምብን የሚወረውሩበት ምክንያት የላቸውም።

ወያኔ ተማሪዎቹን አረመኔና እብድ ለማስመሰል የሰራው የራሱ ትንሽዪ ድራማ ወይም ሌላኛው አኬልዳማ መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ደግሞ እንዲህ አይነት የወሮበላ ስራ እንደሚሰራ እንዳላዪ የሚያዩት ለጋሽ ሀገሮች ሁሉ ያጋለጡት፣ የሚያውቁት የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንብቷል።

በዚህ መሰሪ ወንጀል ያዝናቸው ብለው ከአሰሯቸው ተማሪዎች ውስጥ የቦኮ ትቤ ተወላጅ የሆነ ኑረዲን ሃሰን የተባለ የአለመያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በድብደባ አሰቃይተው ከገደሉት በኋላ ራሱን ገደለ ብለው አስክሬኑን ለቤተሰቦቹ ሸጠውታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ተማሪዎች የደረሱበት እና የገቡበት ተፍጧል።

ይህ ሰቆቃ መጠኑን አልፏል! ግፍ በዚሁ እንዲቀጥል ከሆነ ደግሞ መቆም የሚችልበት ተግባር ባለመፈጸማችን ሁላችንም የዚያች ሀገር ልጆች ከታሪክ ወቀሳ እና ከህሊና ጸጸት አናመልጥም። ወያኔዎች በዘር ከፋፍለው በየተራ ስለሚያጠቁን ነው ይህ የሽብር አገዛዛቸው እድሜ ያገኘው። ይህን አደገኛ ክፍተት ካልዘጋነው መከራው ቀጥሎ ያሰቃየናል።

ግንቦት 7 የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ አገራችን ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ማስተናገድ እንዲበቃት ልጆቿ ተባብረን እንድንነሳ ደጋግሞ ጥሪውን ያቀርባል።

ለወያኔ የተመቸነው በየተራ ለመጠቃት አንዱን ብሄረሰብ በሌላው በማስፈራራትና ጥርጣሬ በመንዛት ለመግዛት የቀየሰው ዘዴ ሰለባ መሆናችን ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ፤ የወያኔ የግፍ ቀንበር እንዲሰበር ሰፊ ህብረት ፈጥረን ከመታገል ውጪ አማራጪ የለንም ይላል።

የወያኔ ግፍ ይብቃ!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!


ከወያኔ ጥገኝነት ነፃ መሆን የማይችሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በአብዮቱ መባቻ ዓመታት ከደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት›› ጋራም በቁርኝት ሠርተዋል
ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው!!
(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፱፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ሊኾኑ እንደማይችሉና መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ ቢገባ ሕገ መንግሥቱን እንደማይፃረር አቋም ይዘው መከራከራቸው ተገለጸ፡፡

የፓትርያርኩ አቋም የተንጸባረቀው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ለቀናት ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደነበር የስብሰባው የፋክት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ለካህናት ስለተከለከሉ ተግባራት አስመልክቶ፣ ጳጳሳትና በቤተ ክርስቲያኒቱ በሓላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ካህናት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ አባልነት ወይም አራማጅነት ነፃ መኾን እንደሚገባቸው ይደነግጋል፡፡

ስለ አንቀጹ አግባብነትና አስፈላጊነት በተሰጠ ማብራሪያ፣ ‹‹እስከመቼ ድረስ አንድ ላይ ተጣብቀን እንኖራለን፤ ሕገ መንግሥቱ እንደሚለው ነፃ መኾን አለብን፤ ነፃ መኾናችንን ለማረጋገጥ ጳጳሳትና በሓላፊነት ደረጃ ያሉ ካህናት ከፖሊቲካ እንቅስቃሴ አባልነትና አራማጅነት ነፃ እንዲኾኑ መከልከል አለብን፤›› መባሉ ተዘግቧል፡፡

ፓትርያርኩ አንቀጹን በመቃወም ‹‹ከመሐንዲስ፣ ከዶክተር ነፃ ልንኾን እንደማንችለው ከመንግሥት ጥገኝነትም ነፃ ልንኾን አንችልም፤›› የሚል አስተያየት መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡ አያይዘውም በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ እንጂ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጣልቃ ቢገባ ድንጋጌውን እንደማይፃረር የሚያሰማ አቋም አራምደዋል ተብሏል፡፡

አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ የመጨረሻ ወሳኝና ላዕላይ የሥልጣን መዋቅር ከኾነው ከቅ/ሲኖዶሱና አባላቱ ይልቅ ከመንግሥት ጋራ አላቸው የሚባለው ያልተገራና ያልተገደበ ግንኙነት የሊቃነ ጳጳሳቱን ቁጣ ቀስቅሷል በተባለበት ኹኔታ ይህን አቋም ማራመዳቸው እያነጋገረ እንደሚገኝ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Patriarch Abune Mathias formerly known as Aba Teklemariam with Dergue’s Renewal committee membersሌሎች የፋክት ምንጮች በበኩላቸው፣ ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጋራ አላቸው በሚል በተቺዎቻቸው የሚጠቀሰው ልክ ያልኾነና ያልተገራ ግንኙነት ጵጵስና ከመሾማቸው አስቀድሞ የሦስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በነበሩባቸው የአብዮቱ መባቻ ዓመታትም፣ የወቅቱን የሥርዓት ለውጥ በቤተ ክህነቱ ለማሥረጽና ተቃዋሚዎች (በተለይ ኢዲዩ) የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተጉዘው የፈጸሙትን ተግባር በአስረጅነት ይጠቅሳሉ፡፡*

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
*YeTahisas Girgir ena Mezezuበግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከ፲፱፻፵፰ – ፶፫ ዓ.ም. በአገር ግዛት ሚኒስቴር የሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መምሪያ ሓላፊ ሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ ብርሃኑ አስረስ ‹‹ማን ይናገር የነበረ… የታኅሣሥ ግርግርና መዘዙ›› በሚል ርእስ በቅርቡ ለኅትመት ባበቁት መጽሐፍ፣ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የፊት ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም እንደነበር የጠቀሱት በስሕተት ይመስላል፡፡

በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በወልቃይት፣ በፀገዴና በአርማጭሆ ቆላ ደርግን በመቃወም የተንቀሳቀሰውን የኢዲዩ ኃይል ለማቆምና ደገኛው ከቆለኛው ጋራ እንዳይተባበር ለመምከር በደርግ ተመልምለው ወደ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ካቀኑት መካከል በወቅቱ አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት አኹን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንዱ የቡድኑ አባል እንደነበሩ የመጽሐፉ አዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

አባ ተክለ ማርያም በወቅቱ ‹‹የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቡነ ቀሲስ፣ በኋላ አቡነ ማትያስ ናቸው›› የሚሉን ጸሐፊው፣ ከአባ ተክለ ማርያም ጋራ አለቃ ቀለመ ወርቅ(የቤተ ክህነት ደብተራ ይሏቸዋል) በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት ‹‹ለሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደነበር›› አስፍረዋል፡፡

የሕዝብ ተሰሚነት አላቸው በሚል ከጠቅላይ ግዛቱ ሰባት አውራጃዎችና የጎንደርን ከተማ በመወከል ከተመረጡት መካከል በወቅቱ የደብረ ታቦር አውራጃ ተወካይ አቶ(በኋላ ሊቀ ማእምራንና ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በኅብተረሰብ ተሳትፎ ላይ መመሥረት በሚል ሐዋርያዊ አገልግሎቷን በሶሻሊስታዊ መንፈስ ለመቃኘት ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ ጸሐፊ) አበባው ይግዛው አንዱ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

Patriarch Abune Mathias with renewal committeesከዘመቻው ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ስብሰባ የተደረገው በጎንደርና ደብረ ታቦር ላይ ብቻ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ብርሃኑ፣ ‹‹ኢዲዩ እየበረታ መጥቷል፤ እኛም በሰላም ተነጋግረን ደገኛውንና ቆለኛውን እንዳይተባበር ማድረግ አልቻልንም፤›› በማለት ዘመቻው ስኬታማ እንዳልነበር ጠቅሰዋል፤ አያይዘውም ‹‹ኹለቱ የሃይማኖት ሰዎች የተመለሱት አንድም አስተያየት ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ (ገጽ 400 – 421)
***************************************************

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ካሱ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሠሩት ጥናት፣ የሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት (በኋላ ብፁዕ አቡነ ማትያስ) ደርግ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የለውጥ ጊዜያዊ ጉባኤ›› (the EOC provisional council or Renewal Council) በሚል ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ አባል የነበሩ ባይኾኑም የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ከነበሩት ዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በነሐሴ ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ምክትል ሊቀ መንበር ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ቀጥተኛ መመሪያና ቁጥጥር የተቋቋመ ነበር፡፡ ከኹለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋራ ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው ጊዜያዊ ጉባኤው፣ ቅዱስነታቸው በአራት መዋቅሮች(የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ፣ የውጭ ጉዳይና ልማት ኮሚሽን) የቤተ ክህነቱን አስተዳደር ለማጠናከር ያቋቋሙትን ኮሚቴ በመጋፋት ለውጥና መሻሻል ያመጣል ያለውን የራሱን ባለአምስት ኮሚቴዎች (የሕግና አስተዳደር፣ የስብከተ ወንጌልና ትምህርት፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የታሪክና ባህል ጉዳዮች እና የአቤቱታ ሰሚ) መዋቅር ዘርግቷል፡፡

ከጊዜያዊ ጉባኤው ጋራ ያልተግባቡትና የማሻሻያ መዋቅሩን ያልተቀበሉት ቅዱስነታቸው በወርኃ የካቲት ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጊዜያዊ ጉባኤው ለደርጉ ባቀረበው የክሥ ሪፖርት ‹‹ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ›› በሚል ዐዋጅ ከመንበረ ፕትርክናው ተገፉ፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱና በጊዜያዊ ጉባኤው መካከል ሽኩቻ የተካሔደበት ቀጣዩ የፕትርክና ምርጫ በጊዜያዊ ጉባኤው በኩል ታጭተው የቀረቡትን ሐዋርያዊውን ባሕታዊ አባ መላኩ ወልደ ሚካኤል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመንበሩ ሠየመ፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሹመት፣ በአህጉረ ስብከት ዝውውር እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሹመት በቀጥታ ይቆጣጠር የነበረ ከመኾኑም በላይ ከደርጉ ጋራ እጅና ጓንት ኾነው በአባልነት የሠሩ አባላቱ በዋና ሥራ አስኪያጅነትም ተቀምጠው ነበር፡፡ ጵጵስና እስኪሾሙ ድረስ የቅዱስነታቸው አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት ከጊዜያዊ የሃይማኖት ጉባኤው ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራት ብቻ ሳይኾን ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተነቃንቀው ስለ አብዮቱ ካስተማሩና የሥርዓት ለውጡን የሚቃወሙ እንደ ኢዲዩ ያሉ ኃይሎች የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ከቀሰቀሱ የደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት› አንዱ ነበሩ፡፡
(ዘሀበሻ)


የወያኔ ባለስልጣን ልጆች እና የነእስክንድር ልጆች

ሰኔ 1 ቀን 1997ዓ.ም፤ በአዲስ ከተማ ት/ቤት የተጀመረው ተማሪዎችንና ንጹሃን ዜጐችን በግፍ የመግደል እርምጃ ተከትሎ አብዛኛው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን ከየት/ቤቱ በአጃቢ ያስወጡ ነበር። ወደ ካቴድራል ት/ቤት በሁለት ኮብራ ተጭነው የተላኩ 20 ልዩ የፌዴራል ፖሊሶች የጄ/ል ሰአረና የጄ/ል ብርሃነ (ወዲ መድህን) ሴት ልጆችን አጅበው ሄዱ። ሁለቱ ሴት ልጆች በማግስቱ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው ዓርብ ሰኔ 3 ቀን በረሩ። የብዙ ባለስልጣናት ልጆች በተመሳሳይ እንዲወጡ ተደረገ። ..29ሺህ የአሜሪካ ዶላር በተርም እየተከፈለላቸው መማር ቀጠሉ። የአዜብ ልጅና የእህቷ ልጅ፣ (በነገራችን ላይ አርአያ መኮንን ይባላል፤ በ1995ዓ.ም ቦሌ ከሩዋንዳ ፊት ለፊት ጥቂት ገባ ብሎ አዜብ ለዚህ ወጣት በ7 ሚሊዮን ብር ቪላ ቤት ገዝታ በስጦታ አበርክታለች። የቪላው ኪራይ ሂሳብ በስሙ ባንክ ይገባለታል) ..የአርከበና ስብሃት ልጆች በቨርጂኒያ፣ የሽፈራው ጃርሶ ልጆች በካሊፎርኒያ፣ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ወንጀለኛውና 5ሚሊዮን ዶላር ሰርቆ የወጣው ተስፋዬ መረሳ ልጆች በኒዮዎርክ….ወዘተ በተቀማጠለ ኑሮና በውድ ክፍያ መማር ያዙ። ባለፈው አመት በነርስ የተመረቀችው የጄ/ል ሰአረ ልጅ ሐመልማል ሰዓረ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ጄኔራሉ ተገኝተው ነበር።…ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንለፍ።

እስክንድር በላባቸው ሰርተው ሃብት ካፈሩ ጥሩ ቤተሰቦች የተገኘ ልጅ ሲሆን የተማረው በሳንፎርድ ት/ቤት ነው። ከዚያም አሜሪካ መጥቶ ትምህርትና ህይወቱን ቀጠለ። “አገር አማን” ብሎ በዘመነ ኢህአዴግ አገር ቤት ገባ። ተደጋጋሚ እስርና ድብደባዎችን አሳለፈ። እነሆ “አሸባሪ” ተብሎ ከሌሎች ንፁሃን ጋር በእስር እየማቀቀ ይገኛል። እነ ጄ/ል ሰአረና መሰሎቻቸው በመቶ ሺህ በሚቆጠር ዶላር ልጆቻቸውን በአሜሪካና አውሮፓ ሲያስተምሩና ሲያንደላቅቁ፣ እንዲሁም ልጆቻቸውን ለማስመረቅ ሲገኙና ሲደሰቱ በአንፃሩ በመፃፉና ሃሳቡን በመግለፁ ብቻ እስር ቤት የተወረወረውና ናፍቆት ልጁን እንዳያሳድግ የተደረገው እስክንድር ነጋ ጭራሽ ቤተሰቡ ያወረሱትን ቤት በግፍ እንዲነጠቅ ተደረገ። በጄኔራሎቹና ባለስልጣናቱ ሰፈር ግን በሚሊዮን ብር የተገነባ ቪላ፣ ልጆቻቸው የሚንደላቀቁበት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር…ወዘተ አለ። ይህ ከህዝብ የተዘረፈ የአገር ሃብት ነው!! የጄ/ል ሰዓረ ባለቤት ኰ/ል ፅጌ በስማቸው በገርጂ የተገነባውና ሰባት ሚሊዮን ብር የፈጀው ቪላ ሲገኝ የሚገርመው የቅጥር ግቢው ወለል በእምነበረድ መሸፈኑ ነው።

ሌላው በሙስና የታሰሩት የደህንነት ሹሞቹ ወ/ስላሴና ገ/ዋህድ..መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ቦንቦች እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የቤት ካርታ ወዘተ መገኘቱን ገዢው ፓርቲ ይፋ አድርጓል። ዛሬ ጠያቂ ባይኖርም ቅሉ ነገር ግን ጄኔራሎቹና ባለስልጣናቱ እንደነ ወ/ስላሴ ዘርፈው ያካበቱት ለመሆኑ አያጠያይቅም።

የሚገርመው መፅሐፍትና ጋዜጣ የተገኘበት የእስክንድር ቤት ሲወረስ በአንፃሩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና ሚሊዮኖች ተገኘበት ያሉትን የዘራፊዎቹን የሙስና ቤት አልነኩም።… እንደ እስክንድር ሁሉ አቶ አንዱአለም፣ አቶ በቀለ፣ ውብሸት፣ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች እነ አቡበከር.. በሙሉ ልጆቻቸውን እንዳያሳድጉ የተደረጉ የህሊና እስረኞች ናቸው!! እንዲሁም ጄ/ል ሰአረ በምሳሌነት ተጠቀሱ እንጂ የአብዛኛው ባለስልጣን ከዘረፋ የተገኘ ህይወት ተመሳሳይ ነው። የአንዳንዶቹ ባለስልጣናትና ልጆች የአሜሪካ ውሎና ኑሮ የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ እንዳለ ሳልጠቁም አላልፍም።
(ከእየሩስአሌም አርአያ)


Saturday, June 14, 2014

አስገዳጁ የፋይናንስ አዋጅጸደቀ

የታክስንገቢን  የማሳደግ ዓላማ በመያዝ በመንግሥትና በግል ድርጅቶች በየዓመቱ ወጥ የሆነ የፋይናንስ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የሚያስገድደውን ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው አጽድቆታል፡፡ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ በመባል የሚታወቀው ይህው አዋጅ ዓላማው የደርጅቶችን የፋይናንስ እንቅስቃሴ መረጃ ወጥነት ባለውና በተደራጀ መልኩ እንዲቀርብ ማስቻል ሲሆን እግረመንገድም መረጃዎቹ የታክስ ገቢን ለማሳደግ ያለመነው፡፡ ይህንለማስፈጸምም “የኢትዮጽያየሂሳብአያያዝናኦዲትቦርድ” የሚባልራሱንየቻለተቋምበሚኒስትሮችምክርቤትየሚቋቋምሲሆንቦርዱከፋይናንስሪፖርትጋርበተያያዘየመቆጣጠርናለኦዲተሮችፈቃድየመስጠትሥራዎችንያከናውናል፡፡በዚህአዋጅየተደነገገውንየተላለፈእስከብር 50ሺህወይንምበሶስትዓመታትእስራትእንደሚቀጣአዋጁደንግጓል፡፡ መንግሥትብዙውንጊዜበተለይልማታዊየሚላቸውየግልባለህብቶችናነጋዴዎችጭምርታክስናግብርንያጭበረብራሉበሚልበየጊዜውወቀሳይህአዋጀርእንዲህኣይነቱንተግባርእንደሚታደግእየተገለጸነው፡፡ባለፉትዓመታትአንዳንድገዥውንፓርቲየተጠጉነጋዴዎችታክስበመሰወርናበማጭበርበርከቀድሞዎቹገቢዎችናጉምሩክባለስልጣንከፍተኛኃላፊዎችጋርክስእንደቀረበባቸውየሚታወስነው


የቤተክርስያን ገንዘብ የዘረፈ ህወሓት

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ “አይናለም” የተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደን “የመለስ ፓርክ” ተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹ “የመለስ ፓርክ” መባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል።
ባለፈው ወር ነው። “ከመለስ ፓርክ” የተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነ ይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ታሰረ፤ ቅጣት መሆኑ ነው። ህዝቡ የታሰረው ፖሊስ ጣብያ አልነበረም፤ ፖሊስ ጣብያ አይበቃውማ። በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ (ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ እናቶች በቃ ሁሉም) በረኻ ላይ በፖሊሶች ተከቦ ታስሮ ይውላል። ዝናብ ይደበደባል፤ ፀሓይ ይመታል። ህዝቡ ግን ይህን ሁሉ ስቃይ ችሎ በቃሉ ፀና። ካድሬዎቹ ከስምንት ቀናት በኋላ ተስፋ ቆርጠው ተውት። ህዝቡ ግን ተቀይሟል።

ከተወሰነ ግዜ በኋላ የማዳበርያ ጉዳይ መጣ። መዳበርያ ዉሰዱ ተባሉ። አንወስድም አሉ፤ በአንድ ቃል። ህዝቡ ያቀረበው ምክንያት መዳበርያ ለመግዛት ገንዘቡም ፍላጎቱም የለንም የሚል ነው። ካድሬዎች ህዝቡን ለማስፈራራት ሞከሩ፣ አሰሩ፣ አዋረዱ። አልተሳካላቸውም። የካድሬዎች የመጨረሻ ሓሳብ ህዝቡ ለማዳበርያ የሚሆን ገንዘብ ከሌለው ከቤተክርስያን ታቦት እንዲበደር ጠየቁት። ህዝቡ አሻፈረኝ አለ። ከታቦት ተበድረን ማዳበርያ አንገዛም፣ ከእግዚአብሄር ቤት ተበድረን ለመንግስት አንሰጥም አሉ።

ካድሬዎችም ማዳበርያው በተሽከርካሪ ጭነው ጣብያው (ቀበሌው) ላይ አራገፉት። ህዝቡም የምንከፍለው ገንዘብ የለንም አለ። ካድሬዎቹ ደግሞ የአይናለም ህዝብ ታቦት የሚገኝበት “መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን” ጋ በመሄድ ለማዳበርያው ዋጋ የሚሆን ገንዘብ ይወስዳሉ። የታቦቱ ቄሶች ዝርፍያ ተፈፅሞብናል በሚል ተግባሩን ይቃወማሉ። ቄሶቹ አርፈው እንዲቀመጡ ይነገራቸዋል። አሁን ለማዳበርያው የሚሆን ገንዘብ በቤተክርስትያኑ ተወስዷል። ህዝቡም ተቃውሟል። አሁን የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ህወሓትም እያስፈራራቸው ነው። ቤተክርስትያን ተዘርፏል ብለው ተቃውሞ ያሰሙ ቄሶች ግን ታስረው ይገኛሉ።

እንዲህ ነው ዝርፍያ። ህወሓት የዝርፍያ ባህሏን እስካሁን ድረስ አጠናክራ ቀጥላለች ማለት ነው።


Friday, June 13, 2014

የወያኔን የልማት ስኬት እንዲመሰክሩ የተጠሩ ሰዎች ያልተጠበቁ ችግሮችን አነሱ

በመጪው ምርጫ ለአሸናፊነት ያበቃኛል በማለት ኢህአዴግ በተለያዩ አካባቢዎች  የተመረጡ ሰዎች በአምስት አመታት ውስጥ ስለተሰሩ ስራዎች  እንዲመሰክሩ በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተጠበቁ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው።
በደብረብርሃን ሰሞኑን ተካሂዶ በነበረው ውይይት ህዝቡ የተለያዩ የማህበራዊ አግልግሎት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንስቷል። ርዕሰ መምህር ከፈለኝ ዘውዴ እንደተናገሩት በከተማዋ ውስጥ ከ15 ሺ ያላነሱ ነዋሪዎች ለ7 ዓመታት መብራት ሳያገኙ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
አቶ አባይነህ የተባሉ ነዋሪም እንዲሁ በከተማው ውስጥ የሚታየውን የመብራት እና የስልክ አገልግሎት ችግሮችን አንስተዋል ተስፋየ ዘነበ የተባለ ነዋሪ ደግሞ የከተማው ወጣት በልማቱ ተጠቃሚ አለመሆኑን ገልጿል ወርቁ ገብረኪዳን የተባለ ሰው ደግሞ የጨለማው ሰፈር በሚባል ቦታ እንደሚኖሩ ገልጸው መብራት ካጡ 8 ዓመታት መቆጠሩን ተናግረዋል።
አቶ ወርቁ በከተማቸው የሚታየውን የኑሮ ውድነት አንስተው  መልካም አስተዳደር አለ ብሎ ለመናገር አይቻልም ብለዋል በህዝቡ አስተያየት የተደናገጡት የኢህአዴግ ሹሞች ለደጋፊዎቻቸው ድል ያለ ግብዣ ሲያዘጋጁ ነቀፌታ ሲያሰሙ የዋሉትን ከግብዣው አግልለዋቸዋል።
ኢህአዴግ ምርጫ 2007ትን አስታኮ የህዝብ ድጋፍ ያስገኛሉ የሚላቸውን እርምጃዎች ሁሉ እየወሰደ ነው።

በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ  ግጭት ተቀሰቀሰ


በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ ሃሙስ  ሰኔ 5 ፣ 2006 ዓም  የተነሳው ግጭት ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የወረዳው ባለስልጣናት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሌሎች አካባቢ ተወላጆችን አካካቢውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በረካታ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በአሁኑ ጊዜ ቴፒ ከተማ ውስጥ ሰፍረው እንደሚገኙ ታውቋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ ባይታወቅም አንድ ፖሊስ መገደሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
የፌደራል እና የክልል ፖሊሶች በአካባቢው የፓትሮል ቅኝት እያደረጉ ሲሆን፣ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ተቋርጧል።
ግጭቱ የተነሳው የወረዳው ባለስልጣናት ጻኑ የሚባለው በደቡብ ክልል ስር የሚገኘው አካባቢ የጋምቤላ መሬት ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንና ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሰዎችን በማስወጣት የአካባቢውን ተወላጆች ለማስፈር በመፈለጋቸው ነው። የጋምቤላ ክልል ሰፋፊ መሬቶች ለውጭ ባለሀብቶች እና ለህወሃት የቀድሞ ታጋዮችና በስልጣን ላይ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በስፋት መሰጠቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
እስካሁን ድረስ ምን ያክል ሰዎች እንደተፈናቀሉ በቁጥር ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም። አካባቢው በቡና ምርቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ በርካታ የደቡብ፣ የአማራና የሌሎች ብሄረሰቦች ተወላጆች ይኖሩበታል።

Thursday, June 12, 2014

በሲኤም ሲ የተደረገው ፍተሻ

ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት እየገባ መታወቂያ የጠየቀ ሲሆን የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ፓስፖርት፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን ፣ የቀጣሪ ድርጅታቸውን ስምና አድራሻ፣ መታወቂያና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተጠይቀዋል።
ተመሳሳይ ፍተሻዎች በሌሎች አካባቢዎች ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ።
በቅርቡ የምእራብ መንግስታት አልሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። መንግስትም 2 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መያዙን አስታውቋል።
አልሸባብ በሶማሊ ክልል  33 የመንግስትን ወታደሮች መግደሉ ይታወሳል። ይህንን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ በመንግስትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል በተደረገው ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

ሚሚ ስብሐቱ እና የሙታን ዲሞክራሲ (በዶ/ር ዳኛቸው)

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሚሚ ስብሐቱና ጓደኞቿ “የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ” በተሰኘ ፕሮግራም እኔ ላይ ለሰነዘሩት ስድብ በዋናነት መልስ ለመስጠት ሳይሆን ዘለፋቸውን በሚካሄዱበት ሰዓት እግረ መንገዳችውን ባነሱት የፖለቲካ አተያይ ላይ ሒስ ለማቅረብ ነው፡፡ይህንንም እንድል ያስገደደኝ እኔ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተደውሎ ለቀረበልኝ ጥያቄ በሰጠሁት መልስ ላይ ወይም ባነሳሁት ሐሳብ ላይ ትችት በማቅረብ ፈንታ በእኔ ስብዕና ላይ አሉታዊ በሆነ መልኩ ዘለፋ በመሰንዘራቸው ነው፡፡

ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የሰጠሁት አስተያያት ዋና ፍሬ ነገር እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ “በሁለተኛ ሹም ሽር የተከናወኑትን የስልጣን መደላደል በምናይበት ጊዜ ህወሓት እንደ ቀድሞው በእጅጉ ተጠናክሮ ብቸኛ የሆነውን ስልጣኑን ተመልሶ ይዟል፡፡”
እንግዲህ እነ ወ፨ሮ ሚሚ ስብሐቱ በዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ላይ ትችት በመሰንዘር ፋንታ የተሾሙትን ሰዎች ስም እየጠቀሱ ግነት በተሞላበት አኳኋን ማንነታቸውን ማለትም ችሎታቸውን፣ክህሎታቸውን ፣ዕውቀታቸውን ሲክቡ በአንፃሩ እኔ ያቀረብኩትን ሐሳብ ሳይተቹ ለአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የማይመጥን (የወረደ) አስተያየት በማለት አልፈውታል፡፡

እሑድ በሚተላለፈው ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡት ወ፨ሮ ሚሚ እና ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ቢሆኑም ሁለቱ ሰዎች እንደ ሰው በፕሮግራሙ ላይ የሚያንፀባርቁት የራሳቸው የአስተሳሰብ ልዕልና የሌላቸውና ለሚሚ ልሳን ለማዋስ ወይም “ለማከራየት” የተሠማሩ ስለሆነ ይህ ጽሑፍ እነርሱን ሳይሆን በቀጥታ እርሷን የሚመለከት ይሆናል፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ ግን ትችቴን ከመጀመሬ በፊት አንድ ነጥብ አንስቼ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡ይኸውም እነሚሚ በግለሰብ ደረጃ ለሰነዘሩት ዘለፋ በአደባባይ መልስ መስጠቱ ተገቢ አይደለም፡፡በመሆኑም “እኔ እንዲህ ነኝ፤እንዲያ ነኝ” ብሎ ስለራስ መናገር ከባሕልም አኳያ ሆነ ከሞራል እይታ አንፃር ተገቢ ሆኖ አናገኘውም፡፡ሆኖም ግን ሚሚ ካነሳችው “ዳኛቸው ‘ይገባኛል’ የሚለው ሹመት ስላልተሰጠው ነው፡፡ ኢሕአዴግን የሚተቸው” ለሚለው ገለፃ ፅብቴን ጥዬ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት ራሴን በመከላከል “አይ እኔ ሹመት አልፈልግም” የሚል መልስ ለመስጠት ሳይሆን እዚህ በቆየሁባቸው ፮ ዓመታት ሹመት የሚፈልግ ሰው ማድረግ የሚገባውን ነገር አጥቼው ወደ ሒስና በመንግስት ላይ ትችት ወደ መሰንዘር የሄድኩበት እንዴት ሊመስላት እንደቻለ መገረሜን ለመግለፅ ያክል ነው፡፡

ምናልባትም በመንግስት ለመሾም፣ለመደጎምና ለመመስገን ያለውን መንገድ በሞኖፖል “እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው” የምትል ከሆነ ስለ እኔ ሹመት ከጃይነት ያለችው እውነት ሊሆን ይችላል፡፡

Wednesday, June 11, 2014

የግንቦት 7 አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ


የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደና ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ውሳኔዎችን ካሳለፈ በኋላ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄው አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄው ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸውን መንገዶች፤ ያቀዳቸውን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪው የትግል ወቅት የሚጠይቀውን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዛዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸውን አበይት ውሳኔዎች አሳልፏል።

የግንቦት 7 አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የንቅናቄዉን የአለፉት አምስት አመታት ጉዞና በዚህ በአራተኛው ጉባኤ ላይ የሃላፊነት ዘመናቸውን የጨረሱትን የንቅናቄው ምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ዕቅድና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል። በሪፖርቱ ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ካካሄደ በኋላ፣ ጉባኤው ለመረጣቸው አዲስ የአመራር አባላት ንቅናቄው ያሰበውን ግብ እንዳይመታ አንቀው የያዙትን እንቅፋቶች ሊወገዱ የሚችሉበትን ሁኔታዎች ተነጋግሮ መግባቢያ ላይ ደርሷል።

ከዚህም በተጨማሪ ንቅናቄው ጥንካሬ ባሳየባቸው መስኮች አቅሙን አጠናክሮ በይበልጥ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ ከንቅናቄው የሚጠብቀውን የታሪክ አደራ እንዲወጣ አሳስቧል።  በጉባኤው ወቅት አባላት ያደረጉት አመራሩን የመንቀፍ፤ አቅጣጫ የማሳየት፤ ሀሳብ የማመንጨትና በአጠቃላይ በጉባኤው በቀረቡ ጉዳዮች ላይ ያሳዩት ንቁ ተሳትፎ ንቅናቄው በህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት ዘርፎች ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍም እያደገ መምጣቱን በግልጽ አሳይቷዋል።

የግንቦት 7 አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ከምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ሪፖርት በተጨማሪ፤ የኦዲትና የስራ ቁጥጥር፣ እንዲሁም የስነ ስርአትና የግልግል ኮሚቴ ሪፖርቶችን አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ካካሄደ በኋላ በሪፖርቶቹ ላይ አስፈላጊውን ትችት አካሂዳ አጽድቋቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የንቅናቄውን ስትራቴጂና ይህንኑ ስትራቴጂ ተሸክሞ በተግባር የሚተረጉመውን መዋቅር በአጽንኦት ከፈተሸ በኋላ በስትራቴጂው ላይ መጠነኛ ለውጥ በማድረግ የስትራቴጂውንና የመዋቅር ለውጡን ተቀብሎ አጽድቋል። ይህ የንቅናቄው አራተኛ ጉባኤ ንቅናቄውን ላለፉት ሁለት አመታት የመሩትንና ያገለገሉትን የምክር ቤት፤ የስራ አስፈጻሚ፣ የኦዲትና የስራ ቁጥጥር፣ የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ በማሰናበት፣ በምትካቸዉ ንቅናቄውን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚያገለግሉ ሊቀመንበርና ዋና ጸሃፊ፣ የምክር ቤት አባላት፤ የኦዲትና የስራ ቁጥጥር፤ እንዲሁም የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላትን መርጧል።

አራተኛዉ የግንቦት 7 መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበትን አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር ከመረመረ በኋላ፣ ዘረኛዉን የወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ የሚደረገው ትግል፣ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገሮችም ስለሆነ፣ የንቅናቄው አባላት ወያኔ ባለበት ሁሉ ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል አጠናክረው ከቀጠሉ፣ የወያኔ ስርአት ያለምንም ጥርጥር የሚሸነፍ መሆኑን በማሳሰብ፣ ወያኔን በማስወገድ ተግባር ላይ በያሉበት እንዲያተኩሩ አሳስቧል።

ከተለያዩ አገሮች የመጡ የግንቦት 7 አባላትን ያሰባሰበዉ አራተኛዉ የግንቦት 7 መደበኛ ጉባኤ የትግል ቃል ኪዳን የታደሰበት፤ የመስዋዕትነት ዝግጅት የታየበትና አባላት የትግልና የስራ ልምድ የተለዋወጡበት፣ ከምን ግዜዉም በላይ የተሳካና የተዋጣለት ጉባኤ ነበር። በመጨረሻ፣ የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ለአባላቱና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ የትግል ጥሪ በማስተላለፍ ደማቅ በሆነ ስነሰርአት ተፍጽሟል።



የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣


Tuesday, June 10, 2014

በሃረር በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ግጭት ተነሳ

ኢሳት ዜና፦ በቀበሌ 19 ልዩ ስሙ ሃመሬሳ ወይም መድፈኛ ጀርባ በሚባለው አካባቢ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓም በቁፋሮ ላይ የነበረ አንድ የግሪደር ሹፌር የተከማቹ አስከሬኖችን አግኝቷል።

የ2ቱ አስከሬን ምንም አይነት የመበስበስ ምልክት አለማሳየቱን የገለጸው ወኪላችን፣ ግለሰቦቹ በቅርቡ የተገደሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሎአል። አንደኛው ሟች እጆጁን ወደ ሁዋላ ለፊጥኝ ታስሮ የተገኘ ሲሆን ሌላው ደግሞ አይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነዋል።

የአራት አስከሬኖች አጽምም እንዲሁ አብሮ መገኘቱን የገለጸው ወኪላችን ፣ ቀደም ብለው የተገደሉ መሆናቸውን መረዳት እንደሚቻል ገልጿል።

ህዝቡ አስከሬኖቹ እንዳይነሱ እና ምርመራ እንዲካሄድባቸው ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ፖሊስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ አስከሬኖቹን በማንሳት ከዋናው ቦታ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ቦታ ላይ እንዲቀበሩ አድርጓል። በቅርቡ የተገደሉትን የሁለቱን አስከሬኖች ማንነት ለማወቅ አልተቻለም።

የግሪደሩ ሾፌር አስከሬኖቹን እንዳየ ራሱን በመሳቱ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

ኢሳት  በሃረር ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ሁለት ወጣቶች አድራሻቸው መጥፋቱን መዘገቡ ይታወሳል።

ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ደግሞ የአወዳይ ህዝብ ዛሬ  ሰኔ 3 ወደ አካባቢው በመኪና ተጉዞ ከደረሰ በሁዋላ ተቃውሞ አሰምቷል። የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በአስለቃሽ ጭስ እና በተኩስ ተቃውሞውን የተቆጣጠሩት ሲሆን፣ ህዝቡ በወሰደው እርምጃ በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ሳላሃዲን ግራ አይኑ አካባቢ በድንጋይ ተመትቶ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

አካባቢው በክልሉ የኢንዱስትሪ መንደር የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስም ለተደራጁ የባለስልጣናት ዘመዶች መሰጠቱን የዘገበው ወኪላችን፣ ለግንባታ የሚውሉ እቃዎች የተጠራቀሙበት መጋዘን በህዝቡ እንዲቃጠል ተደርጓል።

የህዝቡ ጥያቄ “አስከሬን እንዴት የትም ይጣላል፣ ትክክለኛ ቦታ ተፈልጎ በክብር ሊያርፍ ይገባል” የሚል መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።

የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ወደ አካባቢው ተጉዘው ለማረጋጋት ሙከራ አድርገው ባለመሳካቱ ፖሊሶች ህዝቡን በሃይል ለመበተን መገደዳቸውን ወኪላችን አክሎ ገልጿል።

ሀመሪሳ ከአወዳይ ወደ ሃረር መግቢያ ሲሆን አካባቢው ጫካ እና ሜዳ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

ሰማዕታትን እንዘክር፤ እራሳችንንም እንጠይቅ!

ሰኔ 1997 በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የተለከፉ የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው። ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፋፍኖ የቆየው የህወሓት እውነተኛ ባህርይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በወርሃ ሰኔ አደባባይ ወጣ። በሀውዜን ላይ የደረሰውን የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ቡድን ሌላ ሀውዜን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈጠረ። ይኸኛው ሀውዜን ግን በአንድ ቦታ ተወስኖ የቀረ አልነበረም። ጭፍጨፋው በአዲስ አበባ ተጀምሮ ወደ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አዋሳ፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞችና ገጠሮች ተዛመተ። “አግዓዚ” የተሰኘው ገዳይ ሠራዊት በሰላማዊ እናቶችና አባቶች፤ ወጣቶችና ህፃናት ላይ ዘመተ። ደብተርና እርሳሶቻቸውን እንደያዙ ከትምህርት ቤት የሚመለሱ እምቦቃቅላ ህፃናትን ሳይቀር በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ።
በ1997ቱ ሚያዝያ መጨረሻና ግንቦት መጀመሪያ ላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታና ተስፋ ተሞልቶ ነበር። የሚያዝያ 30 ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እና የግንቦት 7 ጨዋነት የተላበለው ምርጫ የፈጠሩት ተስፋ ቃላት ሊገልጹት በሚችሉት በላይ ነበር። ሆኖም በህወሓት የተመራው የሰኔው ጭፍጨፋ ያንን ሠናይ ስሜት አደፈረሰው፤ አጨለመው።
በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የታወረው ወያኔ ከራሱ አባላት ሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው መኖሩ አይታየውም። በህወሓት ጎጠኞች እሳቤ መሠረት ወጣት ሽብሬ፣ ህፃን ነቢዩ፣ ወ/ሮ እቴነሽ፣ ሌሎች እናቶችና አባቶች ሰዎች አይደሉም። ስለሆነም ያለአንዳች ምክንያት ተገደሉ። እስከዛሬ ድረስም ከገዳዮች መካከል አንዱ እንኳን ተጠያቂ አልሆነም። በግልባጩ ገዳዮች በመግደላቸው ተሾሙ፤ ተሸለሙ። ይህ ሁሉ ያሳምማል።
የሰኔ 1997 ሰማዕታትን የምናስባቸው በጥልቅ ሃዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትና እልህ ጭምርም ነው። ወገኖቻችን እንደሰው ባለመቆጠራቸው ተገደሉ። አሁንም እንደሰው የማይቆጠሩ በመሆኑ ሙት ዓመታቸውን መዘከር ወንጀል ነው። መቸ ነው ይህ ውርደት የሚያበቃው?
ሰማዕታት ወገኖቻችን የሕይወት ዋጋ ከፍለው ዘረኝነትን የማስወገድ ሸክም እኛ ላይ ጥለዋል። እኛስ ይህንን ኃላፊነት ለመሸከም ብቁዎች ነንን? እያንዳንዳችን የገዛ ራሳችንን እንጠይቅ።
ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕቶቻችን !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ወያኔ ያሰራቸው አራቱ ሀኪሞች

     ቪኦኤ እንደዘገበው  በቅርቡ በስራ አፈጻጸም ተግባሩ ተሸላሚ ከሆነው ከነቀምቴ ሆስፒታል አራት ሃኪሞች ታስረው በነቀምቴው የምሥራቅ ወለጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የታሰሩት ሐኪሞችም ዶ/ር አዳም ለማ- የቀዶ  ጥገና ሐኪም፣ ዶ/ር ኢሣያስ ብርሃኑና ዶ/ር በላይ ቤተማርያም -የማኅፀንና የፅንስ ስፔሻሊስቶች፣ ዶ/ር ታመነ አበራ- የቀድሞ የሆስፒታሉ የሕክምና ዳይሬክተርና አሁን ለስፔሻላይዜሽን የጥቁር አንበሣ ፕሬዚደንት ሐኪም ሲሆኑ፤የተሰናበቱት ኮሪያዊ ሐኪም ደግሞ  የአጥንት ስፔሺያሊስት የሆኑት ዶ/ር ሪም ጆንግ ሆ ናቸው።
እንደ ቪ ኦ ኤ ሪፖርት ሁሉም ሐኪሞች በነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ አገልግለዋል፡፡ ኮርያዊው ሐኪም ከሥራ ሲሠናበቱ፤ አራቱ ኢትዮጵያዊያን ግን በቁጥጥር ሥር ውለው ነቀምቴ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
​የእነዚህ ለረዥም ዓመታት አገልግሎት ሰጥተዋል የሚባሉ ሐኪሞች ከሥራቸውና ከደመወዛቸው መታገድ፣ አልፎም መታሠር መነጋገሪያ እየሆነ ነው፡፡
ሐኪሞቹ ስለታሰሩበት ምክንያት የተጠየቁት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ቃል አቀባይ ኮማንደር አበበ ለገሰ  ሐኪሞቹ ከሙያዊ ሰነ ምግባር ውጪ  ትክክል ያልሆነ ህክምና እና ቀዶ ጥገና በመስጠት ለሶስት  ሴቶች ሞት ምክንያት እንደሆኑ በሟች ቤተሰቦች የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
በቅርቡ የነቀምት ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ዾክተር ጫላ አኦላኔ በበኩላቸው መንግስት የእናቶች ሞት የመቀነስ እቅድ አቅዶ ሳለ በኛ ሆስፒታል ግን  ባለፉት ስድስት ወራት ከወሊድ ጋር በተያያሰ 16 እናቶች መሞታቸው ከእቅዱ በተቃራኒ እየሄደ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩ በሐኪሞች ቸልተኝነት እና በቂ የህክምና ክትትል ካለመስጠት  የመጣ መሆኑን እና አለመሆኑን ማጣራት ስለሚያስፈልግ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።
የሐኪሞቹ ቤተሰቦች ግን ውንጀላውን አይቀበሉትም።በስራቸው ጣልቃ በመግባት ሐኪሞቹን ማዋከብ የተጀመረው ቀደም ብሎ መሆኑን የተናገሩት ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንዲት የዶክተር አዳም ለማ ቤተሰብ ተናግረዋል።
ሞተዋል ከተባሉት ሶስት ሴቶች መካከል አንዷን ቀዶ ጥገና ያደረጉላቸው ዶክተር አዳም መሆናቸውን እንደምሳሌ ያወሱት የቤተሰብ አባሉዋ፤ ታማሚዋ ያረፉት በተደረገው የእንቅርት ቀዶ ጥገና ሳይሆን ህመሙ ከባድ እና በደማቸውና ወደ ሌላ አካላቸው የተሰራጬ ስለነበር ነው ብለዋል።
የሙዋች አስክሬን ወደ ምኒልክ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስዶ ሟች የሞቱት በህክምና አሰጣጥ ችግር ሳይሆን በሳንባ ካንሰር መሆኑ ተረጋግጡዋል ያሉት የቤተሰብ አባሉዋ፤ ሐኪሙ ምንም ችግር እንደሌለባቸው በሪፖርት የተገለጸ ቢሆንም ፖሊሶች “መታሰር አለባቸው”በማለት ክ25 ዓመታት በላይ በከተማዋ ያገለገሉትን እና በማህበረሱ ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት ያላቸውን ሐኪሞች እንዳሰሩዋቸው ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ተሸለመ

ኢሳት ዜና :-የ2014 “የጎልደን ፔን ኦፍ ፍሪደም” ሽልማት አሸናፊ የሆነው እስክንድርነጋ ዛሬ ሽልማቱን ተቀበለ።
በጣሊያን ቶሪኖ በተካሄደው የሽልማት ስነ-ስር ዓት  ላይ  እስክንድርን ወክሎ ሽልማቱን የተቀበለው በቃሊቲእስርላይየነበረው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነው።
“ምኞቴ ይህን ሽልማት እኔ እንድቀበለው አልነበረም” በማለት ንግግሩን የጀመረው ማርቲን፣ “ዛሬ ጠዋት ስነሳ  ምናለ፦“ ተፈታሁኮ፤ ሽልማቱን እኔ ራሴ ልቀበል እመጣለሁ” የሚል ስልክ ከአዲስ አበባ በስልክ ብሰማ ብዬ ተመኝሁ” ብሎአል።
“ይህ ግን አልሆነም፤ ከሰ ዓታት በፊት እስክንድር ነጋ  በዱላቸው የታሰሩባትን ክፍል ግድግዳ እየመቱ  በማይክራፎን “ቆጠራ!ቆጠራ!” እያሉ በሚጮኹ የወህኒ ጠባቂዎች ድምጽ ነው ከመኝታው የተነሳው” ያለው ማርቲን፣ የሙያ ባልደረባውን  ወክሎ ሽልማቱን ሊቀበል  በስፍራው መገኘቱን ግልጾአል።
“ምንም እንኩዋን  ከሲያ እስር ቤት ነጻ እንደሆንኩ ባስብም፤ ከትስታዎቹና ከእስር ቤቱ ድምጾች ፈጽሞ ነጻ ልሆን አልችልም”ሲልም ማርቲን ተናግሮአል።
ማርቲን በሲሁ ንግግሩ እስክንድር በእስር ቤት እየደረሰበት ያለውን ስቃይ  እና የቃሊቲ እስር ቤትን አስከፊና አስቀያሚ ገጽታዎች  በበቂ ሁኔታ ለታዳሚዎቹ አሳይቶአል።
እስክንድር ህግን ጥሰሀል ተብሎ ለእስር የተዳረገው መንግስትን በመተቸቱ እንደሆነ ያወሳው ማርቲን፤ “ይህ የሚያም ቀልድ ነው”ብሎ አል።
“ይህ የጎልደን ፔን ሽልማት፤ ከ1000 ቀናት በላይ በእስር ላሳለፈው ለእስክንድር ነጋ ብቻ ሳይሆን እስክንድርን  ለእስር ለዳረገው ለጋዜጠኝነት ሙያ ጭምር የተሰጠ ክብር እንደሆነ ይሰማኛል” ሲልም ለሽልማቱ ያለውን አክብሮት ገልጾአል።
እስክንድር በአካል ከደረሰበት ቅጣት በላይ ከቤተሰቡ እና ከሚወደው ብቸኛ ልጁ በመለያዬት የደረሰባት የመንፈስ ቅጣት የከፋ እንደሆነም ማርቲን አመልክቱዋል።
እስክንድር የተማረ እና በሌላ ሙያ ሊሰማራ እየቻለ በጨቁዋኞች እጅ እየተሰቃየ የሚገኘው ለእውነት ባለው የጸና አቁዋም እና ለሀገሩ ባለው ፍቅር ምክንያት እንደሆነም ገልጾአል።

Monday, June 9, 2014

በምግብ ማደግ ማለት በውሸት ማደግ ነው እንዴ ጎበዝ???!!!

ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ አመታት በተለይም ባለፉት አስር አመታት የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በድርብ አኃዝ አደገ፤ ኢትዮጵያ በ2015 ዓም መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ትሰለፋለች፤ በኤሌክትሪክ ኃይል እራሳችንን ችለን ለጎረቤት አገሮች እንተርፋለን፤ በቅርቡ ደግሞ በምግብ ምርት እራሳችንን ቻልን የሚሉ በአይን የማይታዩና በእጅ የማይዳሰሱ የ”ላም አለኝ በሰማይ” ክምሮች እየከመረ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመደለል ሞክሯል። የአገሩ ኤኮኖሚ በእጥፍ አደግ ሲባል ችግርና መከራዉ በሦስት እጥፍ የጨመረበት የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንኳን መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ሊሰለፍ ከሦስቱ ዕለታዊ ምግቦች አንዱን በቅጡ መብላት ተስኖት መብራት በሳምንት አንድ ቀን ብቻ እያገኘ “ጽድቁ ቀርቶብኝ በወጉ በኮነንከኝ” እያለ ጨለማ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብሎ የመከራ ዘመን መቁጠር ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንመራሀለን ከሚሉት የወያኔ መሪዎች እጅ እጅ ብሎ የሰለቸዉ ነገር ቢኖር እንደሰዉ በእግሩ ቆሞ የሚሄደዉ ዉሸታቸዉና ቅጥፈታቸዉ ነዉ። የወያኔ መሪዎችና እዉነት አንድ ላይ ታይተዉ ስለማያዉቁ ህዝብ አይኑ እያየ የሆነዉን ነገር አልሆነም ወይም ጭራሽ ያልተሞከረዉን ነገር ሆነ ብለዉ ሲዋሹ ለአፋቸዉም ለሰብዕናቸዉም አይሳሱም። ለምሳሌ ሠላማዉ ዜጎችን በጅምላ ገድለዉ ብርድልብስ ጠቅልለዉ እየቀበሩ ማንንም አልገደልንም፤ መብቱን የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፈኛ በጥይት እየጨፈጨፉ – ባንክ ተዘረፈ፤ መሬታችንን ለምነዉ ለሱዳን እየሰጡ – የተሰጠ መሬት የለም፤ አኝዋክን ከመሬቱ አፈናቅለዉ መሬቱን ለባዕዳንና ለቤተሰቦቻቸዉ በርካሽ እየቸበቸቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመሬት ቅርሚያ የለም እያሉ የዋሿቸዉ ግዙፍ ዉሸቶች ከብዙዎቹ ቂቶቹ ናቸዉ።

“ስለ ….. ሲባል ምርጫ ይቅር” …. ትግሉም ይቁም ወይ? (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

“ስለ …. ሲባል ምርጫ ይቅር” በሚል እንድ ፅሁፍ ፋክት ላይ ወጥቶ አንብቤ ለምን? ብዬ ልፅፍ አስቤ ተውኩት፡
፡ ምክንያቱም በፋክት መፅሔት ላይ አምደኞች የሃሣብ ፍጭት ማድረግ የተለመደ ቢሆንም ሰሞኑን ግን የበዛ
ይመስላል ከሚል ነበር፡፡ ይህ አንድ ዘርፈ ብሉ ጥሩ ጎን አለው፡፡ አንዱ አምደኞቹ ከአንድ ፋብሪካ የወጡ ሳሙና
ዓይነት ያለመሆናቸውን ያሳያል፡፡ሌላው የፋክት መንፈስ ብለው ለሚቃዡትም ሆነ፤ ከመሬት ተነስተው
ለሚፈርጁት የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው፡፡ ጉዳቱ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቅ ለምትል መፅሄት የተወሰነ
ሃሳብ በተወሰኑ ሰዎች የሚቧቀሱባት ከሆነች ደግሞ አንባቢን አማራጭ እንዳያሳጣ የሚል ፍርሃት ስለአለኝ፡፡ ይህ
ሁሉ ዳር ዳርታ እኔም ተውኩት ወዳልኩት የሃሣብ ፍጭት ለመቀላቀል ሰበብ ፈልጌ ብቻ አይደለም፡፡ በቅርቡ
“ሰለ … ሲባል ምርጫ ይቅርብን” በሚል በወዳጄ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ያቀረበውን ሃሳብ ባልቀበለውም
በፋክት ላይ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እናደርጋለን ብዬ እያሰብኩ ሳለ በፌስ ቡክ የውስጥ መዘገቢያ
እንዲሁም በግል የሚያገኙን ሰዎች ምርጫ እንዳትወዳደሩ የሚል አንዳንዱ ምክር አንድ አንዱ ደግሞ ትዕዛዝ
መሰል መልዕክቶች በብዛት ይደርሱኝ ጀምረዋል፡፡ ውሳኔው ልከም ይሁን አይሁን የምርጫ ጉዳይ የሚወሰነው
በፓርቲ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የግል አስተያየቴን መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ ለዚህም ነው “ሰለ … ሲባል ምርጫ ይቅር” ከተባለ እኔም እንደቅድመ ሁኔታ ትግሉም ይቁም ወይ? በሚል ጥያቄ የጀመርኩት፡፡

በእኔ እምነት ምርጫ መወዳድር ያለመወዳደር የሚባል አማራጭ የለም፡፡ የአንድ ፓርቲ ስራ ምርጫ መወዳድር ነው፡፡ የሰው ልጅ ሞት እንዳለ እያወቀ ሞትን ረስቶ በህይወት እንደሚኖረው ማለት ነው፡፡ ለፓርቲዎች ያለመወዳደር የሚባል ነገር እንዳለ ረስተው ለምርጫ ውድድር መዘጋጀት ዋናው ስራቸው መሆን አለበት፡፡ ፓርቲዎች ምርጫ ላለመወዳደር የሚያበቃ ነገር እንዳይኖር ተግተው መስራትን ትተው፤ ላለመወዳድር ሰበብ የሚፈልጉ ከሆነ እንደ አሸዋ የበዛ ሰበብ ማቅረብ አይገድም፡፡ ከዚህ ሰበብ ውስጥ ግን አንድም ተሰፋ አይገኝም፡፡ ምርጫውም የሰነፍ ነው የሚሆነው እንጂ ባስቸገሪ ሁኔታ ጀግና ለመሆን ለሚታትር ታጋይ የሚመጥን አይደለም፡፡ በሀገራቸን ኢትዮጵያ ለምርጫ የእኩል መወዳደሪያ ሰፍራ ሳይኖር ምርጫ መወደዳር አስቸጋሪ እንደሆነ መረዳት ለማንም የሚገድ አይደለም፡፡ ትግል የሚባለው ነገርም የመጣው ይህ አስቸጋሪ ሁኔታ በመኖሩ ነው፡፡ በአሜሪካን ወይም በሌሎች በዲሞክራሲ በዳበሩ አገሮች የሚደረግ የፖለቲካ ተሳትፎ ትግል አይባልም፡፡ ታጋዮች ማድረግ ያለባቸው ታዲያ ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ ለማስወገድ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያስፈልገውን ማድረግ ነው፡፡ ክቡር የሆነውን የስው ልጅ ህይወት ከማጥፋትና ንብረት ከማውደም በመለስ ማለቴ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ ቢባል በምርጫ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ናቸው ብዬ የማምናቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በማንሳት ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡

ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ በ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው የተጻፈ

ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡

ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት የነበረውን ድርሰት ወያኔ ሐሰት እንደሆነ እያወቀ ነገር ግን ላለው ተመሳሳይ የጥፋት ዓላማ ከወደቀበት በማንሣት የፈጠራ ሠማዕታትን የሚዘክር የመታሰቢያ ሐውልት አስገንብቶ አስመርቋል፡፡ እንደሚታወቀው ፋሺስት ጣሊያን አስቀድሞ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ክፍል በኋላም መላውን ኢትዮጵያን ይዞ በነበረበት ወቅት ሕዝቡን አዳክሞ ቅኝ አገዛዙን ለማጽናት እንዲያስችለው በፋሺስታዊና የቅኝ አገዛዝ ስልት (Strategy) ሕዝቡን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በሞያ ወይም በሥራ ዓይነቶች ሳይቀር ከፋፍሎ ያናቁር ለማፋጀትና ለማባላት ይጥር እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡

ፋሺት ጣሊያን ይህ እኩይ ሴራው ያሰበውን ያህል ሳይሠምርለት ቀርቶ በጀግኖች አርበኞቻችን ድል ተመትቶ ተባረረ፡፡ ነገር ግን ሰላዮቹ ሚሲዮኖችና ሀገር አሳሾቹ ሀገራችንን ለመበቀል ሰላምና አንድነት እንዳይኖራት ለማድረግ ብዙ እኩይ ፈጠራዎቻቸውን እውነት አስመስለው በመጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ዛሬ አሸባሪዎቹ ወያኔ ኦነግና ሻቢያ የኦሮሞን ሕዝብ በሔጦሳና በጨለንቆ ተፈጽሞብሀል የሚሉትን በጅምላ ጡት እጅና ብልት የመቁረጥ ቅጣት ወይም ግፍ ተፈጽሟል ብሎ የጻፈ ሚሲዮን ወይም አሳሽ አንድ እንኳን የለም፡፡ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች እከሌ እከሌ የተባለ ታሪክ ጸሐፊ እንደዚህ በሚለው መጽሐፍ እነደጻፈው እያሉ የጠቀሷቸውን መጻሕፍትም ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቻችንን ሳይቀር አስቸግረን መጻሕፍቱ አሉበት በተባሉ ቦታዎች አፈላልገን ስናነብም በሚገርም ሁኔታ ከሚሉት ጋራ ጨርሶ የማይገናኝና የሌለ ፈጠራ ሆኗል፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል ወገን?

ይሄን ብለው የሚያወሩ ወገኖች ዐፄ ምኒልክ ሀገርን መልሶ አንድ ለማድረግ በዘመቱበት ወቅት ከጦር አበጋዞቻቸው ዋናዋናዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች እንደነበሩ አያውቁም፡፡ ለምሳሌ የጦሩ አበጋዝ (ዋና ሹም ወይም ኃላፊ) ራስ ጎበና ዳጬ ነበሩ፡፡

ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ በ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው የተጻፈ

ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡

ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት የነበረውን ድርሰት ወያኔ ሐሰት እንደሆነ እያወቀ ነገር ግን ላለው ተመሳሳይ የጥፋት ዓላማ ከወደቀበት በማንሣት የፈጠራ ሠማዕታትን የሚዘክር የመታሰቢያ ሐውልት አስገንብቶ አስመርቋል፡፡ እንደሚታወቀው ፋሺስት ጣሊያን አስቀድሞ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ክፍል በኋላም መላውን ኢትዮጵያን ይዞ በነበረበት ወቅት ሕዝቡን አዳክሞ ቅኝ አገዛዙን ለማጽናት እንዲያስችለው በፋሺስታዊና የቅኝ አገዛዝ ስልት (Strategy) ሕዝቡን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በሞያ ወይም በሥራ ዓይነቶች ሳይቀር ከፋፍሎ ያናቁር ለማፋጀትና ለማባላት ይጥር እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡

ፋሺት ጣሊያን ይህ እኩይ ሴራው ያሰበውን ያህል ሳይሠምርለት ቀርቶ በጀግኖች አርበኞቻችን ድል ተመትቶ ተባረረ፡፡ ነገር ግን ሰላዮቹ ሚሲዮኖችና ሀገር አሳሾቹ ሀገራችንን ለመበቀል ሰላምና አንድነት እንዳይኖራት ለማድረግ ብዙ እኩይ ፈጠራዎቻቸውን እውነት አስመስለው በመጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ዛሬ አሸባሪዎቹ ወያኔ ኦነግና ሻቢያ የኦሮሞን ሕዝብ በሔጦሳና በጨለንቆ ተፈጽሞብሀል የሚሉትን በጅምላ ጡት እጅና ብልት የመቁረጥ ቅጣት ወይም ግፍ ተፈጽሟል ብሎ የጻፈ ሚሲዮን ወይም አሳሽ አንድ እንኳን የለም፡፡ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች እከሌ እከሌ የተባለ ታሪክ ጸሐፊ እንደዚህ በሚለው መጽሐፍ እነደጻፈው እያሉ የጠቀሷቸውን መጻሕፍትም ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቻችንን ሳይቀር አስቸግረን መጻሕፍቱ አሉበት በተባሉ ቦታዎች አፈላልገን ስናነብም በሚገርም ሁኔታ ከሚሉት ጋራ ጨርሶ የማይገናኝና የሌለ ፈጠራ ሆኗል፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል ወገን?

ይሄን ብለው የሚያወሩ ወገኖች ዐፄ ምኒልክ ሀገርን መልሶ አንድ ለማድረግ በዘመቱበት ወቅት ከጦር አበጋዞቻቸው ዋናዋናዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች እንደነበሩ አያውቁም፡፡ ለምሳሌ የጦሩ አበጋዝ (ዋና ሹም ወይም ኃላፊ) ራስ ጎበና ዳጬ ነበሩ፡፡

የማያልቀው የወያኔ ባለስልልጣናት ጕድ


      በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊክ ግዛት በሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ኮሚኒቲ ማእከል ግንቦት ሃያን በማስመልከት በተድረገ ዝግጅት ላይ ለመታደም የዘመቱት የወያኔ ባለስልጣናት በገዛ ወዳጆቻቸው ተዋርደው ተመልሰዋል። በፖለቲካው መስክም ይሁን
በሴሰኝነታቸው እድል ያልሰመረላቸው የወያኔ ባለስልጣናት አብሯቸው ከተጓዘው አንዱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለት ከፕሮቶኮል ውጪ በመንቀሳቀሱ የራያው ተወላጅ አቶ ተከስተ በትደጋጋሚ
ለ4 ጊዜ ቡጢ ሲያቀምሳቸው በክፍተኛ ደረጃ በማእከሉ ውስጥ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር።ጸጋየ በርኸ
ሁኔታውን ለማረጋጋት ቢሞከርም ከሌሎች የጸጋዬ ባለሟሎች ጋር ግብግብ በመያያዝ .. እኔ ወዲ ራያ በማለት አቶ ተከስተ በጸጋዬ እና ተከታዮቹ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በትግራይ የራያ ተወላጅ እና የቀድሞ የሕወሃት አባል የሆኑት አቶ ተከስተ
ባለቤታቸው ይዘው በዝግጅቱ ላይ የመጡ ቢሆንም በወቅቱ በነበረው ክፍተኛ የመጠጥ ብዛት ከልክ በላይ የጠጡት አለቃ ጸጋዬ በቆንጆ የራያ ልብስ ደምቃ በሹሩባ ያጌጠችው የአቶ ተከስተ ሚስት አይናቸው ገብታ እንዲያመጡላቸው ቢያዙም የሰው ሚስት
እንደሆነችና ባለቤቷ አብሮ እንዳለ ቢነገራቸውም ሊሰሙ ባለመቻላቸው ያለችበት ቦታ ድረስ በስካር መንፈስ ሰተት ብለው ሲሄዱ ነገሩ የገባው የቀድሞ የሕወሓት አባል አቶ ተከስተ በቡጢ ተቀብሏቸው መሬት ላይ ዘርግፏቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊኪ የሚገኘው የትግራይ ኮሚኒቲ ለሁለት ተከፍሎ የወያኔ መሪዎችን በማፋጠጥ ክባድ የፖለቲካ ኪሳራ እንደተፈጠረ ወዳጆቻችን ገልጸውልናል። ሕወሓት በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድርጊት ለነገ ልጆቻችን ቂም ማትረፍ ነው ወደዳችሁም ጠላችሁን ሕዝቡ ተለያየ ብላችሁ እያሰበችሁ ከሆነ አትሳሳቱ ሁሉ አድፍጦ እየጠበቀ ነው ድንገት የፈነዳ እለት ይበቀላቹሃል። በቀሉም ለትግራይ ተወላጆች ይተርፋል መፍትሄ አምጡ በማለት የመከሩ ሲሆን በሌላው ወገን ደሞ አማራው አድብቷል የአማራው ጅብ እንዳይበላችሁ እናንተ እርስ በርስ እየተባላችሁ ነው አታናቆሩ ሲሉ መካሪዎችን ሮሮ አስምተዋል።ከእራት በፊት በቤተክርስቲያናት መካከል የተከፋፈለውን አካል ለማስታረቅ የሞከሩት የወያኔ ባለስልጣናት በፍጹም ለማስማማት ባለመቻላቸው በአቡነ ማትያስ ስም ለማስፈራራት ቢሞክሩም መሳቂያ ሆነዋል።
       የተዋህዶ ቤትክርስቲያን በመንደርተኖች የተክፈለች ሲሆን የአድዋ እና የተንቤን ተብለው የሚጠሩት ቤተክርስቲያኖች ሲኖሩ በኮሚኒቲ ማእከሉ ውስጥ ያለውን ከሕወሓት ቢሮ ጋር አብሮ የተጣበቀውን አድዋዎች ሲያስተዳድሩት ተንቤኖች ደሞ የራሳቸውን ቤተክርስቲያን በመመስረት ተገንጥለው
ወተዋል። ይህንን ግኡዳይ ለመፍታት እና ወደ አንድነት ለማምጣት በቦትው የተገኙት የፖለቲካ ባለስልጣናት አለቃ ጸጋዬ እና የአባይ ወልዱ ባለቤት እንዳልተሳካላቸው ሲታወቅ ከተንቤን ተወላጆች ጠንካራ ሂስ ቀርቦባቸዋል።
   
Ethioforum.org

Friday, June 6, 2014

የደህንነት ኃይሎች የጋዜጣ አዙዋሪዎች ላይ እርምጃ መወሰድ ጀመሩ

በቅርቡ ገዥው ፓርቲ የግሉን ሚዲያ ለማፈን እንዲያስችል ጋዜጣ አዙዋዎችና አከፋፋሎችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለማደራጀት የሚያስችል አሰራር እንደጀመረ ታውቋል፡፡ በዚህ አሰራር መሰረት ገዥው ፓርቲን የሚተቹ ጋዜጦችና መጽሄቶች ከገበያ በማስወጣት በቀጣዩ ምርጫ የሚደርስበትን ጫና ለመቀነስ እንደፈለገም ሲነገር ቆይቷል፡፡

ይህ በአዙዋሪዎች ላይ ሊወሰድ የታቀደው እርምጃ ዛሬ አመሻሹ ላይ የጀመረ ሲሆን በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጋዜጣ አዙዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታግተው አምሽተዋል፡፡ በእገታው ወቅት የደህንነት ኃይሎች ‹‹ለማዞር የተደራጃችሁበትንና ፈቃድ የተሰጣችሁበትን ወረቀት አምጡ›› በማለት ወደ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው እንደነበርና አዙዋዎቹም ‹‹መደራጀት አይጠበቅብንም፣ ጣቢያም አንሄድም›› ብለው የደህንነቶቹን ትዕዛዝ መቃወማቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የሚተቹትን ጋዜጦችና መጽሄቶች እንዲያዞሩ እንደማይፈልግና እሱ የሚፈልገው እያደራጀ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ እርምጃው መጠኘ ሰፊ መሆኑን የጠቆሙት ታጋቾቹ ‹‹መንግስት ይህንን ለመተግበርም በእኛ ብቻ ሳይሆን ጋዜጣ በምናስነብብባቸው ካፌዎች ላይም ጫና ተጀምሯል፡፡ ካፌዎቹ ለአንድ ሰው ከአንድ ጋዜጣ በላይ እንዳንሰጥና አንዳንዶቹም ጭራሹን እንዳናስነብብና እንዳንሸጥ እየከለከሉን ነው፡፡›› ያሉት አዙዋሪዎቹ እስካሁን ይወሰዳል የተባለው እርምጃ ዛሬ በግልጽ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ


Thursday, June 5, 2014

በሁለት ዙር የሰለጠኑ 235 የድረ ገፅ መረጃ ማዛባት የሚችሉ ፕሮፓጋንዲስቶች በስራ ላይ መሆናቸው ታወቀ፡

 ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በመላ ሐገሪቱ በኢንተርኔት ድረ ገፅ መንግስት እየደረሰበት ያለውን ትችት ለመቀነስና ፤ የተደበቁ መረጃዎች ተጋላጭነታቸውን ለመቆጣጠር በማሰብ የሰለጠኑ ወጣቶች ስራ መጀመራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡

ኢህአዴግ በአዳማ ናዝሬት በሁለት ዙር ያሰለጠናቸው 235 ብሎገሮች በፊስ ቡክና በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች፣ተቃዋሚ የሚመስሉ ስያሜዎችን በማውጣት ህዝብ የማደናገር፤ መንግስትን በሚቃወሙ መረጃዎች ላይ ምላሽ የመስጠት ፤ መንግስትን የሚደግፉ መረጃዎች በየጊዜው በመረጃ መረቡ ለህዝብ እንዲደርስ የማድረግ ተልእኮ ተሰጥቷዋል።

ስልጠናውን የወሰዱት ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ ምርጫውን ያካሄዱት የመንግስት ኮሚኒኬሺን እና የኢህአዴግ ሊግ ናቸው፡፡ ሰልጣኞቹ ተጠሪነታቸው በክልሉ ላሉ የኢህአዴግ መሪ ፓርቲዎች ሲሆን፣ የመንግስት ከሚኒኬሺን መስሪያቤት በበኩሉ መረጃዎችን በበላይነት የማረም እና የማስተካከል ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

በቅርቡ በተካሄደ የመጀመሪያው ዙር አፈፃፀም የአማራ ክልል መልካም ውጤት ማስመዝገቡን ፤ በፊስቡክ አመራርነት ለቤነሻንጉል ጉሙዝ ተሞክሮ ማካፈሉ መደነቁን የመንግስት ኮሚኒኬሺን ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን በባህር ዳር ላይ በተካሄደው የመንግስት ከሚኒኬሺን ባለሙያዎች ግምገማ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የኢህአዴግ የስልጠና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲሱ ለገሰ ደግሞ  ከኢሳት ከሚወረወረው የጦር ፕሮፓጋንዳ መዳን የምንችለው በኢቲቪ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ሚዲያው ነው ሲሉ ለተመራቂዎች ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ ሰልጣኞቹ 2 ሺ 350 የፊስ ቡክ ፤ የቲውተር ፤ እና የብሎግ አካውንቶችን  ከፍተዋል።


በደብረዘይት ነዋሪዎች በግዴታ ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተደረጉ

ኢሳት ዜና እንደዘገበው በደብረ ዘይት ነዋሪዎች ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ መገደዳቸው አስግቶዋቸዋል። በከተማዋ ቀበሌ አንድ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት ፖሊሶች ከስቪል ሰራተኞች ጋር በመሆን ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ብሄር እና ሃይማኖት ሲመዘግቡ ውለዋል።
“የምዝገባው አላማ ሰዎችን እየመረጡ ለማፈናቀል ሊሆን ይችላል” በማለት ስጋታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ብሄርን መመዝገቡ ለምን እንዳስፈለገ ሲጠይቁ ከላይ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
አንዳንድ አስተያየት የጠየቅናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ምዝገባው  ከመጪው ምርጫ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በክልሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው አለመረጋጋት እና በገዢው ፓርቲ እንደተቀነባበረ የሚታመኑ አልፎ አልፎ የሚነሱ አካባቢን ማእከል ያደረጉ ግጭቶች በቀበሌው ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ተጨማሪ የስጋት ምንጭ ሆኗል።
ምዝገባው በመላው የክልሉ ከተሞች ይካሄድ አይካሄድ ለማወቅ አልተቻለም

Wednesday, June 4, 2014

በምዕራብ ኦሮምያ ዞን የፌደራል ፖሊሶች ከህዝብ ጋር መጋጨታቸው ተሰማ

 ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ አቡና  በሚባል ወረዳ የፌደራል ፖሊሶች ነዋሪዎችን መደብደባቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁትንም ይዘው ማሰራቸውን የአካባቢዎች ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
የግጭቱ መነሻ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብሮአል የተባለው መንጌ ጉደታ እንዲፈታ ህዝቡ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።
ወጣቱ እግሩ በድብደባ ብዛት መሰበሩን የሚገልጹት አካባቢው ነዋሪዎች፣ ነዋሪዎች ወጣቱ ካልተለቀቀ ፖሊስ ጣቢያውን እናቃጥላለን ማለታቸውን ተከትሎ በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽሟል።
ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ወጣቶችም ተይዘው ታስረዋል።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው መሰማራቱንና ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።

ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች የሆኑት ሁለቱ የወያኔ ጉጅሌዎች



አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል።

በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ተሰምቷል። ካገር መውጣት የማይችሉም አሉ።

አባ ዱላ /ጃርሳው/

አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲረከቡ በማክረር አካሄድ የሚታወቁት አቶ ጁነዲን ያዋቀሩትን ካቢኔ በመበተን ሥራቸውን አንድ ብለው ጀመሩ። አዲስ ካቢኔ ሲገነቡ የመረጡት አዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ (የተቃዋሚ) ፓርቲ አባላትን በማስኮብለል ነበር። ህወሃት ለሁለት በተበረገደበት ወቅት ለአቶ መለስ ቡድን ድጋፍ በመስጠት ቅድሚያ የያዙት አባ ዱላ ባስቀመጡት ውለታ መሰረት ኦሮሚያ ላይ ያሻቸውን እንዲያደርጉ የሟቹ መለስ ድጋፍ ነበራቸው። በዚህም ድጋፍ ሳቢያ ኦሮሚያ ላይ የሚፈልጉትን ሲያደርጉ ከተባረሩት መካከል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሙክታር ከዲር ይገኙበታል።

Tuesday, June 3, 2014

የዞንዘጠኝ ጦማርያን ተጨማሪጊዜተጠየቀባቸው።


 ኢሳት ዜና :-እሁድ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የ 28 ቀናት ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማርያን  ማህሌትፋንታሁን፣አቤልዋበላናበፍቃዱኃይሉ  ናቸው።
ጦማርያኑ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው  ፖሊስ  ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ሲጠይቅባቸው  በመሀል ዳኛዋ ውድቅ ተደርጎ  የ15 ቀናት ቀጠሮ  መሰጠቱ አይዘነጋም።
ይሁንና  ችሎቱ ከትናንት በስቲያ እሁድ በአራዳ ምድብ ችሎት ሢሰየም ውሳኔውን ያሳለፉት ዳኛ ከቦታው እንዲነሱ እና በቦታቸው ሌላ ዳኛ  እንዲተኩ ከመደረጉም ባሻገር፤ ፖሊስ የዛሬ 2 ሳምንት ያቀረበውና  በፍርድ ቤቱ  ውሳኔ የተሰጠበት ጥያቄ  ዳግም ተነስቶ እና በአዲስ ተተኪው ዳኛ ተቀባይነት አግኝቶ  ጦማርያኑ ተጨማሪ የ 28 ቀናት የቀጠሮ ጊዜ ተጠይቆባቸዋል።

የሕዳሴ አብዮት! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ላይ ለመድረሷ በብዙሃን ዜጐች ዕይታም ሆነ፤ ሂደቱን በተከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ምሁራን ምልከታ የማይታበል ሐቅ ሊሆን መቃረቡ በዚህ ተጠየቅ ለማነሳው አጀንዳ ገፊ-ምክንያት ነው፡፡ በአናቱም ባለፈው ሳምንት ‹‹የ‹ቀለም› አብዮት ናፍቆት›› በሚለው መጣጥፍ ላይ ለማሳያነት የጠቀስኳቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ነገረ-ንዋያዊ ችግሮች ተደማምረው፣ ሀገሪቷን በርቀት እንደታዘብናት ሶቪየት ሕብረት፣ አሊያም በቅርበት እንዳስተዋልናት ሶማሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት የመፈራረሷን አይቀሬነት ማስረገጣቸውን ልብ እንላለን፡፡ ከዚህ ክፉ የታሪክ ዕጣ ለመታደግም ከሁለት አስርታት በላይ ያስቆጠረውን ይሄን አሮጌ ሥርዓት መቀየር ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ዛሬ ግልፅ እውነታ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለዘመናት በገዥነት የተንሰራፋው የፖለቲካ ባሕልም አብሮ ካልታደሰ ነገሩ-ሁሉ ‹‹ታጥቦ ጭቃ…›› ከመሆን አለመዝለሉ ነው፡፡Temesgen Desalegn “Fact” Ethiopian Amharic newspaper editor

Monday, June 2, 2014

ህወሓቶች በጣም ደንግጠዋል


ባሁኑ ሰዓት በብዙ የሑመራ አከባቢዎች፣ ማይጨው (ሽኮማዮ)፣ ዓዲጎሹ (ተከዘ)፣ ሐውዜንና አፅቢ ህዝቡን ለመቆጣጠር ፖሊሶችና ምልሻዎች ተሰማርተዋል። ትናንት ማታ (ቅዳሜ ማታ) አቶ መሰለ ገብረሚካኤል (የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አስተባባሪ) ፊታቸው በሸፈኑ ታጣቂዎች ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ትናንት ቅዳሜ በእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ የዓረና ልሳን ለህዝብ ሲያድሉ የነበሩ የዓረና አመራር አባላት አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ፣ አቶ ኃይለኪሮስ ታፈረና መምህር ይልማ ኩኖም በህወሓት አስተዳዳሪዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ተደብድቦ በፖሊስ ታስረዋል። አቶ ገረችአል ግደይ (አባ ሐዊ) የተባለ ያከባቢው አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስን እንዲታሰር ስለወሰነ በሚል ምክንያት በዉቅሮ ከተማ ታስሮ ይገኛል። አሁን የእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ አከባቢ በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው።

ሁለትና ከሁለት በላይ ሁኖ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። በአፅቢ ወንበርታ ላለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመግታት የተቃውሞው መሓንዲስ የተባለውን አቶ ሕድሮም ሀይለስላሴን በሰበብ አስባቡ ለማሳሰር ዝግጅት መጀመሩ ከህወሓት ፅሕፈትቤት መረጃ ደርሶኛል። በሐውዜን ከተማ ዓረና ተብሎ የተጠረጠረ ሁሉ ድብደባ ተፈፅሞበታል። ከሐውዜን እንዲወጣም እየተደረገ ነው። አሁን እሁድ ግንቦት 24, 2006 ዓም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በእግሪሓሪባ መንደር ብዙ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተዋል። አቶ ሙኡዝ ፀጋይ የተባለ ያከባቢው የዓረና አስተባባሪ ቤት ተከቧል። መንቀሳቀስ አይችልም። በያንዳንዱ የእግሪሓሪባ መኖርያቤት በር ሦስት ፖሊሶች ይገኛሉ። ዛሬ በህዝቡና አስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈጥሮ ነበረ። ባጠቃላይ ባሁኑ ሰዓት በትግራይ አለመረጋጋት አለ። ይህን ሁሉ ችግር እየፈጠረ ያለ ግን ህወሓት ራሱ ነው። ከሰለማዊ ተቃውሞ ዉጭ ምንም ዓይነት ዓምፅ በሌለበት ህዝቡ ሊያምፅ ይችላል በሚል ስጋት ብቻ የፀጥታ ሃይሎች እያሰማራ ነው። ህዝቡም ተደናግጧል። እኛ ግን ብዕር እንጂ ጠመንጃ አልያዝንም።

በትግራይ አስቸኳይ መፍት ሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተባራክተዋል። መነጋገር ይኖርብናል።

አብረሃ ደስታ




Sunday, June 1, 2014

ሰበር ዜና፦

         ከሁለት ወር በፊት ወደ ጣሊያን በመብረር ላይ የነበረ የኢትዬጵያ የመንገድ አውሮፕላን አቅጣጫ በማስቀየር ሲውዘርላንድ ጀኔቭ እንዲያርፍ በማድረግ የጥገኝነት ጥያቄ ኣቅርቦ የነበረው ረዳት ፓይለት ሀይለመድህን አበራ ያቀረበውን የጥገኝነት ጥያቄ የስዊዝ መንግስት ተቀበለ።
       የኢትዮጵያ መንግስት ፓይለቱን ወደ ኢትዮጵያ ለመመስ ሰፊ ጥረት እያደረገ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፓይለቱ ጥገኝነት እንዲያገኝ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ሰልፍ ሲጠይቁ መቆየታቸውም ይታወቃል። ፓይለቱ  በአሁኑ ሰአት በሙሉ ጤንነት ላይም እንደሚገንኝ ለማወቅ ተችሏል በተጨማሪም የፓይለቱ የፍርድ ሂደትም በቅርቡ እንደሚጀምርም ለማወቅ ተችሏል።