Monday, February 15, 2016

በአንድ ክፍለከተማ ብቻ 81 መሃንዲሶች በከፍተኛ ሙስና መዘፈቃቸው ተሰማ

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ 81 መሃንዲሶች በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ተገኝተዋል። የመሃንዲሶቹ ስም እስካሁን ይፋ ባይሆንም፣ መሃንዲሶቹ ከባለስልጣናት ጋር እጅግና ጓንት በመሆን በመሬት ሽያጭ ከፍተኛ ሃብት አፍርተዋል።
በመሃንዲሶቹ ላይ እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም። ከእነሱ ጋር በመሆን የአዲስ አበባን መሬት በመቸብቸብ የጥቅም ሰንሰለት ፈጥረዋል በተባሉ ባለስልጣኖች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ይሁን አይሁን ለማወቅ አልተቻለም።

No comments:

Post a Comment