Tuesday, February 16, 2016

የኖርዌይ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ ኦሮሚያ በሚያደርጉት ጉዞ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ

ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
መቀመጫውን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ ያደረገው የኖርዌይ ኤምባሲ ዜጎቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ ማክሰኞ አሳሰበ።
...
በክልሉ በምዕራብ አርሲ ዞን አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎች ማሳሰቢያን ያሰራጨው ኤምባሲው የጸጥታ ስጋት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች መሆኑንም አመልክቷል።
በክልሉ ያሉም ሆነ ወደ ክልሉ ለመጓዝ እቅድ ያላቸው የኖርዌይ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄን በማደረግ በጉዞአቸው ላይ ማስተካከያን እንዲያደርጉ ኤምባሲው ጠይቋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት በልዩ ሁኔታ በመከታተል ላይ የምትገኘው ኖርዌይ፣ በአውሮፓ ህብረት በመመረጥ የሃገሪቱን አጠቃላይ የደህንነትና የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እየተከታተለች እንደሆነም ታውቋል።
ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ስታወጣ የቆየችው ሃገሪቱ በአውሮፓ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ በምታደርገው ጥረት ተደማጭነት ያላት ሃገር መሆኗንም ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment