Friday, February 5, 2016

በጉጂ ዞን ሚድሮክን በማውገዝ ተቃውሞው ተባብሶ ሲቀጥል፤ በአዲስ አበባ ሚድሮክ ፕሮጀክቱን ተነጠቀ።

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጉጅ የተለያዩ ወረዳዎች አደባባይ የወጡ የተቃውሞ ሰልፈኞች በዋኘኝነት ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኩባንያ ከአካባቢው እየፈጸመ ነው ያሉትን የወርቅ ማእድን ዝርፊያ ተቃውመዋል።
"በሰልፉ ላይ የነበሩ ገበሬዎች፦" ኦኮቴ የኛ መሬት ነው፤ አል አሙዲ የኛ ጠላት ነው" የሚል መፈክር ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
"ኦኮቴ" የሸህ መሀመድ አል አሙዲ ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኩባንያ ማእድን ከሚያወጣባቸው ቦታዎች አንዱ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚድሮክ ኩባንያ በአዲስ አበባ የሚያካሂደውን የመንገድ ስራ ተነጠቋል።...
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከጥራትና አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሁለት ስራ ተቋራጮችን ኮንትራት ማቋረጡን የጠቀሰ ሲሆን፤ እርምጃ የተወሰደባቸው ኩባንያዎች ሚድሮክ ኮንስትራክሽን እና ትድሃር ኮንስትራክሽን መሆናቸውን ገልጿል።
የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ሃይሌ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በቦርዱ ውሳኔ መሰረት ስራው እንዲነጠቅ መደረጉን ተናግረዋል።
ኩባንያው ከመገናኛ ካፒታል ሆቴል ጀምሮ እስከ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ ያለውን መንገድ ለመስራት ውል ገብቶ ሥራውን ቢረከብም፥ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ግንባታውን ባለማከናወኑ ግንባታው እንዲነጠቅ መደረጉን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
ትድሃር ኮንስትራክሽን በተመሳሳይ የተረከባቸውን የመንገድ ፕሮጀክቶች በተቀመጠለት ጊዜ አጠናቆ ባለማስረከብና በታክስ ማጭበርበር ወንጀል መከሰሱን ተከትሎ ስራውን እንደተነጠቀ ተገልጿል።
ከዚህም ባሻገር የመንገድ ፕሮጀክት ስራ ያጓትታሉ በሚል ምክንያት ሳትኮን ኮንስትራክሽን፣ አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽንና ኢትዮ ጄንራል ኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ በሚያወጣቸው ማንኛውም ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ መከልከላቸው ተወስቷል።

No comments:

Post a Comment