Wednesday, September 27, 2017

በነገሌ ቦረና አካባቢ ውጥረት መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

(ኢሳት ዜና መስከረም 17 ቀን 2010 ዓም) በነገሌ ቦረና አካባቢ ውጥረት መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ
በኦሮምያ ክልል በነገሌ ቦረና ትናንት ወረቀት መበተኑን ተገልጾ ውጥረት መስፈኑ ታውቋል። ወረቀቱን የሶማሊ ልዩ ሃይል ጦር እንደበተነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ወረቀቱ “ ነገሌ ቦረና የሶማሊ ክልል መሬት በመሆኑ፣ ማንኛውም የኦሮሞ ተወላጅ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ” የሚል ይዘት ያለው መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ይህንን ተከትሎ ከትናንትና ጀምሮ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንደሚታይ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

መንግስት የውጭ እዳውን እንዲቀንስ አይኤም ኤፍ ገለጸ

(ኢሳት ዜና መስከረም 17 ቀን 2010 ዓም) መንግስት የውጭ እዳውን እንዲቀንስ አይኤም ኤፍ ገለጸ
የአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ምንም እንኳ የመካከለኛ ጊዜ እድገቱ አወንታዊ ገጽታ የሚኖረው ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰአት የሚታየው የበጀት ክፍተት መስተካከል እንዳለበት እንዲሁም ከብድር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ን ለመቅረፍ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ገልጿል። የመንግስት የገንዘብ ፖሊሶች የበጀት ክፍተቱንና የውጭ እዳውን በመቀነስ በኩል ትኩረት ማድረግ አለበት ያለው የገንዘብ ተቋሙ፣ ይህን ለማድረግ በመንግስት የሚገነቡና ከፍተኛ ብድር የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች እንዲቀንሱ መክሯል። 
አሁንም የማህበራዊ አገልግሎት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው አይ ኤም ኤፍ፣ ይሁን እንጅ የግል ባለሀብቶችን በማሳተፍ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል አመልክቷል። የገንዘብ ፖሊሲው መጥበቅ እንዳለበትም ድርጅቱ መክሯል። 
አይ ኤም ኤፍ አሁን ያለው አወንታዊ የኢንቨስትመንት ከባቢ መሰረታዊ የሚባሉ ለውጦችን በመውሰድ ሊሻሻል እንደሚገባው የገለጸው አይ ኤም ኤፍ፣ በተለይ የገንዘብ ምንዛሬው ከገባያ ለውጡ ጋር ተያይዞ እንዲሄድ መደረጉ ፉክክር እንዲኖር እንደሚያደርግና ኢኮኖሚውን እንደሚጠቅመው ገልጿል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 በመቶ ማደጉንም ድርጅቱ አስታውቋል።

ከባሌ ዞን ለተፈናቀሉ ከሶስት ሺ በላይ የሲዳማ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) ከባሌ ዞን ለተፈናቀሉ ከሶስት ሺ በላይ የሲዳማ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ። በህወሃት መንግስት የእጅ አዙር ትዕዛዝና ግፊት በኦህዴድ አስፈጻሚነት በታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለው ማፈናቀል ሕጻናትን ጨምሮ ነፍሰጡር እናቶችና ደካማ የሆኑ አዛውንቶች ከፍተኛ ጉዳት ላይ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ወገናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቀው የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈናቀሉት የሲዳማ ብሔር ተወላጆችን ቀይ መስቀል ለጊዜው እየረዳቸው መሆኑ ታውቋል። መፈናቀሉ የተከሰተው ከ15ቀናት በፊት ቢሆንም ትኩረት ሳያገኝ በመቅረቱ ችግሩ አሳሳቢ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል። ከባሌ ዞን አንጌቶ ወረዳ የተፈናቀሉት 1700 አባዎራዎችን ጨምሮ 3200 የሲዳማ ተወላጆች ያሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የሲዳማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በክልላዊ መንግስቱና በፌደራሉም ጭምር የተደረገ ድጋፍ ባለመኖሩ ወገኖቻችን አደጋ ላይ ወድቀዋል ሲል አስታውቋል። የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ በቀለ ወዮ መፈናቀሉ ከመፈጸሙ በፊት ግድያ እንደነበረ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ የውጭ ድጋፍ

ብአዴን አጠቃላይ ስብሰባ በ4ኛ ቀን ውሎው በገጠመው የከፋ ተቃውሞ ወደ ዋናው የስብሰባ አጀንዳ መግባት እንደተሳነው ታወቀ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) የብአዴን አጠቃላይ ስብሰባ በ4ኛ ቀን ውሎው በገጠመው የከፋ ተቃውሞ ወደ ዋናው የስብሰባ አጀንዳ መግባት እንደተሳነው ታወቀ። የራያ ጉዳይ ተጨምሮበት ስብሰባው በጭቅጭቅና ሃይለቃል በተሞላበት ምልልስ በቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የግጨው፣የወልቃይትና የራያ ጉዳይ እያለ ሌላ አጀንዳ አያስፈልገንም ያሉት ተሳታፊዎች የብአዴንን መሪዎች በጥያቄ ወጥረው መያዛቸው ተሰምቷል። በተለይ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ የሚወረወሩት ተራ የሚባሉ አይነት ስድቦች ስብሰባውን የከፋ እንዲሆን ማድረጉን ነው ምንጮቹ የገለጹት። የትግራይ የበላይነት ጉዳይም ሌላው የውዝግብ ርእስ መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ዕሁድ የተጀመረውና ለ10 ቀናት የሚዘልቀው የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን አጠቃላይ ጉባዔ ወደ አጀንዳ መግባት ሳይችል 4ኛ ቀኑን ተሻግሯል። ይህ ጉባዔ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የባለፈው ሳምንት ስብሰባ ያለስምምነት መበተኑን ተከትሎ የተጠራ ቢሆንም በተቀረጹት የጉባዔው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ለመነጋገር ከተሳታፊዎች ተቃውሞ በመቅረቡ ለአምስተኛ ቀን መተላለፉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በብአዴን የተቀረጹትና ለውይይት የተዘጋጁት ሁለቱ አጀንዳዎች እየሰራን እንታደሳለን የሚለውና የንቅናቄውን የ2010 የስራ ዕቅድ የተመለከተ ነበር። ሆኖም ተሳታፊዎች የግጨው፣ የወሎ ራያና የወልቃይት ጉዳይ እያለ ሌላ አጀንዳ አያስፈልግም በማለቱ እስከዛሬ ዋናዎቹ አጀንዳዎች ሳይነኩ ቀርተዋል። የትግራይ የበላይነት በዚህ ስብሰባም አንገብጋቢ ርዕስ ሆኖ በተሳታፊው ተነስቷል። ባለፈው ሳምንት ያለስምምነት የተበተነውና ብአዴንን ያንገጫገጨው ስብሰባ ንቅናቄው በሶስት ሃይሎች ተወጥሮ ወደፊት እንዳይራመድ እንዳደረገው ይነገራል። ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት ጥብቅና በመቆም የሚታወቁና ከአማራው ይልቅ ለህወሀት ጥቅም

በኦሮሚያ ክልልና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010)በኦሮሚያ ክልልና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የማጣራት ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑንም ሃላፊው ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በጎረቤት ሶማሌ ላንድ የሚኖሩ ከሶስት ሺ የሚበልጡ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን መንግስት በይፋ አስታውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ለውጭ መገናኛ ብዙሃን በሰጡትና ከፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ መረዳት እንደተቻለው በግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ተገድለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች በግጭቱ ተገድለዋል በማለት በግጭቱ ከፍተኛ እልቂት መከሰቱን

Monday, September 25, 2017

የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ስልጣን እለቃለሁ በማለት ተናገሩ

(ኢሳት ዜና መስከረም 15 ቀን 2010 ዓም) የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ስልጣን እለቃለሁ በማለት ተናገሩ
ምንጮች እንደገለጹት የጸጥታ ዘርፍ ሃፊው አቶ ፍሰሃ ወ/ሰንበት ፣ በብአዴን አባላት ሳይቀር መገለላቸውን፣ ያራሳቸውን ወገን እንደሚያሳፍኑ እንዲሁም በክልሉ ህዝብ ላይ በደል እንደሚፈጽሙ ተደርጎ እንደሚነገርባቸው፣ በክልሉ ህዝብ ዘንድም እንደ አማራ እንደማይታዩ በምሬት ተናግረዋል።
ሃላፊው ይህን የተናገሩት ከሃላፊነት የሚነሱ እና በምትካቸው የሚሾሙትን የክልሉን ባለስልጣናት ለመለየት ኮሚቴ መቋቋሙን ተከትሎ፣ ከሃላፊነት እነሳለሁ በሚል ስጋት ስለገባቸው ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ። ፍሰሃ ወልደሰንበት ከሙስና ጋር በተያያዘ የእስር ፍርድ የተወሰነባትን የህወሃት የደህንነት አባል የሆነቸውን ሰላም በሪሁን በልዩ ትእዛዝ ከእስር በመፍታት ወደ ስራዋ እንድተመለስ በማድረጉ ተገምግሞ ነበር።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ወደ ትግራይ ለእርቅ የሄዱትን የብአዴን ባለስልጣናት እና የአገር ሽማግሌ የተባሉትን ግለሰቦች፣ “ፈሪዎች “ብለው ተችተዋል የተባሉት የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪን አቶ ሰማ ጥሩነህንና ምክትል ፕሬዚዳንቱን አቶ ተስፋዬን ከስልጣን ለማንሳት እና እርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ምንጮች ተናግረዋል:፡

በደብረታቦር ትላንት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወጣቶችና የሀይማኖት አባቶች ታፍሰው መወሰዳቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010)በደብረታቦር ትላንት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወጣቶችና የሀይማኖት አባቶች ታፍሰው መወሰዳቸው ተገለጸ። በኢየሱስ ደብር የሚተከለውን የመረጃ ቋት ማማ በመቃወም ወደቤተክርስቲያን መስቀል ይዘው በተመሙ ነዋሪዎች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው በርካታ ሰዎች ቆስለዋል። ደብረታቦር ቁጥሩ የበዛ የመንግስት ሃይል የገባ ሲሆን ቤት ለቤት በመዘዋወር ወጣቶችን አፍሰው ወስደዋል። ተቃውሞውን አስተባብረዋል በሚልም የተወሰኑ የሃይማኖት አባቶች መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የኢየሱስ ደብር ቤተክርስቲያን አባት አባ ብርሃን በድጋሚ ከታሰሩ በኋላም ወዴት እንደተወሰዱ የታወቀ ነገር የለም። መነሻው በደብረታቦር ኢየሱስ ደብር ቅጥር ግቢ ለመትከል የታቀደውና ግንባታው የተጀመረው የመረጃ ቋት ምሶሶ ነው። የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች ባልተጠየቁበት፣ ምዕመናን ባልመከሩበት ሁኔታ መንግስት ለክልሉ ቴሌቪዥን አገልግሎት የሚሆን ምሶሶ በቤተክርስቲያኒቱ ግቢ ለመትከል ከውሳኔ ላይ በመድረስ እንቅስቃሴ

የጸጥታ ሃይሎች ወገን ለይተው በድንበር ግጭት መሳተፋቸው የሀገራችንን አንድነትና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት አስጊ እንዳደረገው ኢሶዴፓ ገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010) የጸጥታ ሃይሎች ወገን ለይተው በድንበር ግጭት መሳተፋቸው የሀገራችንን አንድነትና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት አስጊ እንዳደረገው ኢሶዴፓ ገለጸ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቻ ከወሰን አካባቢ ግጭቶች ርቀው በሚኖሩ አካባቢዎች የሚካሄደው ግድያና ማፈናቀል ተጠናክሮ መቀጠሉ እንዳሳሰበውም ኢሶዴፓ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያን አንድነትና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ከሁሉም ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም ባለፉት 26 የኢህአዴግ የአገዛዝ አመታት ሕዝባችንን ከፋፍሎ የሚገዛበት ስልቱን እየቀየሰና እየተገበረ ብሔሮችና ብሔረሰቦች እንደዚሁም አጎራባች ክልሎች እርስ በርስ የሚጋጩበትን ሁኔታ ፈጥሮ በመቆየቱ የሀገራችንን አንድነትና የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ጥሎት

Thursday, September 21, 2017

በኦሮምያና በሶማሊ ክልል ድንበር ላይ ተኩስ እንደነበር ተገለጸ

(ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2010ዓም) በኦሮምያና በሶማሊ ክልል ድንበር ላይ ተኩስ እንደነበር ተገለጸ
የኦሮምያና የሶማሊ ክልል መሪዎች የሰላም ስምምነት መፈራራቸውን ከገለጹ በሁዋላ አሁንም ግጭቶች አለመቆማቸውን ወኪላችን ዘግቧል።
ትናንት ጭናክሰን ወረዳ ቆቦ ላይ ከባድ ጦርነት መካሄዱን የአካባቢውን ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ግጭቱ በመባባሱ የምስራቅ እዝ አዛዡ ጄ/ል ማሾ በዬነ ወደ አካባቢው ለመጓዝ ተገዷል። ግጭቱ በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላትና በህዝቡ መካከል የተካሄደ ነው። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ ለማወቅ አልተቻለም። ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግጭቱ እየተባባሰ ሊሄድ የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። በሁለቱ ክልሎች መካከል የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ግልጽ አድልኦ በማድረግ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆችን እየያዙ በማሰር ላይ ናቸው። 

የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች የተጣለባቸውን ግብር እንደማይከፍሉ አስታወቁ

(ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2010ዓም) የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች የተጣለባቸውን ግብር እንደማይከፍሉ አስታወቁ
በመላ አገሪቱ የሚገኙ የደረጃ “ሐ” ነጋዴዎች በዘፈቀደ የተጣለባቸውን ግብር በመቃወም አድማ ካደረጉ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ለደረጃ “ለ” ነጋዴዎች የግብር ውሳኔ እየደረሳቸው ሲሆን፣ አሁን አዲሱ ተመን የደረሳቸው ነጋዴዎች እንደማይከፍሉ እያስታወቁ ነው። 
በወልድያ የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ከዚህ በፊት ይከፍሉ ከነበረው ግብር በ10 እጥፍ ጨማሪ ተደርጎባቸው እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል። ቀድሞ 10 ሺ ብር ግብር ይከፍል የነበረ አንድ ነጋዴ፣ አሁን 100 ሺ ብር ክፈል መባሉን፣ አንድ ጓደኛው ቀድሞ 6 ሺ ብር ሲከፍል ቆይቶ አሁን 80 ሺ ብር ክፈል መባሉን ተናገሯል። ከአግልግሎት ሰጪ ተቋማት ውጭ ያሉ ነጋዴዎች ደግሞ ከ100 ሺ እስከ 2000 ሺ ግብር ተጥሎባቸዋል። 
ህዝቡ ምንም አይነት ግብር አንከፍልም በማለት እንደ ደረጃ “ሐ” ሁሉ ቅሬታ እያቀረበ መሆኑን ነጋዴዎች ተናግረዋል።
በተለያዪ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ የደረጃ “ሐ” ነጋዴዎች ግብራቸውን አለመክፈላቸውን ሰመጉ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

በኬንያ ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትዕዛዝ በርካታ ስቃይና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች አጋለጠ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010)በኬንያ ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትዕዛዝ በርካታ ስቃይና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች አጋለጠ። የሂዩማን ራይትስ ዎች ከፍተኛ ተመራማሪ ፍሌክስ ሆርን እንደገለጹት ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ረጅም እጅ ባላቸው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አማካኝነት በኬንያም እየኖሩ ይገረፋሉ፣ከፍተኛ ስቃይም እየደረሰባቸው ይገኛል። በተለይ በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኬንያ ፖሊሶችን በገንዘብ እየደለለ ስደተኞቹን አሳስሮ ወደ ሀገር ቤት በግዴታ እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑንም ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል። ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ኑሮ በኬንያ ስቃይና መከራ ሆኖባቸዋል። እስራትንና ግድያን ፈርተው ወደ ኬንያ የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸው ግፍ ተከትሏቸዋል። ወደ ናይሮቢም መግባቱን የሒዩማን ራይትስ ዎች ተመራማሪ ፍሌክስ ሆርን ገልጿል። እንደ ሰብአዊ መብት ተመራማሪው ገለጻ በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለስልጣናት የኬንያ ፖሊሶችን በገንዘብ እየደለሉ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ይዘቶች ብሔሮችን ከብሔሮች ጋር የሚያጋጩና ጦርነት ቀስቃሽ ናቸው በማለት አስጠነቀቀ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ይዘቶች ብሔሮችን ከብሔሮች ጋር የሚያጋጩና ጦርነት ቀስቃሽ ናቸው በማለት አስጠነቀቀ። በህወሃቱ ነባር ካድሬ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፊርማ የወጣው ማሳሰቢያ በጥቅል የተቀመጠና ዝርዝር ይዘት የሌለው በመሆኑ ሆነ ብሎ ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅና ለማስፈራራት የወጣ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በኦሪገን ዩኒቨርስቲ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዕጩ ዶክተርና መምህር አቶ እንዳልካቸው ሃይለሚካኤል ለኢሳት እንደገለጹት ከዚህ ማሳሰቢያ በኋላ ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎች ይኖራሉ። በህወሃት ነባር ካድሬ ዘርአይ አስገዶም የሚመራው የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን በሚሰራጩ ይዘቶች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስለማሳሰብ በሚል ርዕስ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ያሰራጨው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አገዛዙ የገባበትን አጣብቂኝ እንደሚያመለክት ለኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡ የዘርፉ ሙያተኞች ገልጸዋል። በኦሪገን ዩኒቨርስቲ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዕጩ ዶክተርና መምህር አቶ እንዳልካቸው ሃይለሚካኤል ለኢሳት እንደገለጹት የተላለፈው መመሪያ በስራ ላይ ካለው ህገ-መንግስት አንቀጽ 29 ጋር የሚጻረር፣ጥቅልና ለማንኛውም አይነት ትርጉም ክፍት ነው ብለዋል። እንዲህ እንዲሆን የተፈለገው ሆን ተብሎ በታቀደ ሁኔታ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱንና

የኢትዮጵያን የግብርና ስርአት ለማሻሻልና አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቢልና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን እንዲሁም በሌሎች ለጋሾች የሚሰጠው ድጋፍ ከተግባራዊ ስራ ይልቅ ለአማካሪ ድርጅት በሚደረግ ክፍያ እየባከነ መሆኑን ምንጮች ገለጹ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) የኢትዮጵያን የግብርና ስርአት ለማሻሻልና አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቢልና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን እንዲሁም በሌሎች ለጋሾች የሚሰጠው ድጋፍ ከተግባራዊ ስራ ይልቅ ለአማካሪ ድርጅት በሚደረግ ክፍያ እየባከነ መሆኑን ምንጮች ገለጹ። የኢትዮጵያ ግብርና ማበልጸጊያ ማእከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሊድ ቦምባ የዘመዶቻቸው ንብረት ለሆነውና ፈርስት ኮልሰንታሲ ለተባለው ድርጅት በእርዳታ የሚመጣውን ገንዘብ እያሻገሩ እንደሆነም ተመልክቷል። የጉዳዩን አሳሳቢነት በተመልከተ የሚመለከታቸው አካላት ለጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ለቢልና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን አቤቱታ ማቅረባቸውንም ለኢሳት የደረሰው ዜና ያመለክታል። የኢትዮጵያን ግብርና ለማዘመንና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በቢልና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን ድጋፍ የተቋቋመው የግብርና ማበልጸጊያ ተቋም ስራን በሃላፊነት እንዲመሩ አቶ ካሊድ ቦምባ የተባሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ተወላጅ ወደ ኢትዮጵያ መሄዳቸውንና ለሶስት አመት በኮንትራት እንዲሰሩ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል። ሆኖም ግለሰቡ የኮንትራት ጊዜያቸው ካለፈ ሶስት አመት ቢቆጠርም ምንም አይነት የተጨበጠ ነገር ባለመታየቱ ጥረቱ መክሸፉን ምንጮቹ ይገልጻሉ፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አቶ ካሊድ ቦምባ አሁንም በሃላፊነታቸው ላይ መሆናቸውን መረጃው

ካናዳ ከአምባገነኑ የህወሃት አገዛዝ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረምር በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ጠየቁ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010)ካናዳ ከአምባገነኑ የህወሃት አገዛዝ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረምር በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ጠየቁ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ አሜሪካ ለህወሀት መንግስት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ጥያቄውን ያቀረቡት በካናዳ ቶሮንቶና በጀርመን ፍራንክፈርት ባካሄዱት የተቃውሞ ትዕይንት ነው። እነዚህ የተቃውሞ ትዕይንቶች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል የተዘጋጁ ሲሆን ባለፈው ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲም መካሄዱ የሚታወስ ነው። በዓለም ዓቀፍ የነጻነት ትግል ድጋፍ ጥሪ ግብረሃይል የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ተካሂዷል። ባለፈው ሰኞ በካናዳ ቶሮንቶ በተካሄደው ትዕይንተ ህዝብ ኢትዮጵያውያን በህወሀት መንግስት የሚፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማውገዝ የካናዳ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቋርጥ ጠይቀዋል። የኢሬቻውን ጭፍጨፋ አንደኛ ዓመት በማስታወስ በተካሄደው በዚሁ ትዕይንተ ህዝብ በህወሀት መንግስት በየማጎሪያ እስርቤቶች የሚሰቃዩትን ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ መሪዎችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ስም በማንሳት የካናዳ መንግስት በህወሀት ላይ ጫና እንዲፈጥር ጥሪ አድርገዋል። የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሃና በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጅምላ ግድያ ትኩረት

Wednesday, September 20, 2017

በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ህዝበ ውሳኔ አያስፈልገንም ባሉ አራት ቀበሌዎች በመንግስት ታጣቂዎች ወከባ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010)በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ህዝበ ውሳኔ አያስፈልገንም ባሉ አራት ቀበሌዎች በመንግስት ታጣቂዎች ወከባ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ። የህወሀት/ብአዴን ካድሬዎች በአራቱ ቀበሌዎች ተሰማርተው ህዝቡን እያስፈራሩት መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። ባለፈው ዕሁድ በተካሄደውና ከ8ቱ ቀበሌዎች በ7ቱ የህዝብ ድምጽ የተነፈገው የህወሀት ቡድን ቀድም ብለው ህዝበ ውሳኔ አያስፈልገንም ያሉት 4 ቀበሌዎች በቅማንት አስተዳደር ስር እንዲሆኑ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ላይ በመሆኑ በአካባቢው ውጥረቱ ማየሉ ታውቋል። ከባለፈው ዕሁድ ህዝበ ውሳኔ በኋላ ሰሜን ጎንደር ጭልጋ የወታደራዊ ቀጠና መስሏል ይላሉ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች። የህዝቡን ውሳኔ ለመቀልበስና ህዝበ ውሳኔ መደረግ በማያስፈልግባቸው ቀበሌዎች በአስገዳጅነት ለማድረግ የህወሀት መንግስት የሃይል ርምጃን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ወደ አካባቢው ተሰማርቷል። ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከዕሁዱ ህዝበ ውሳኔ በኋላ ከተገደሉት 4 ሰዎች በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ከሸዲ ወደ ሽንፋ በሚወስደው መንገድ ላይ 2 ሰዎች ተገድለው ተገኝተዋል። ምርጫም አያስፈልገንም ያሉ 4 ቀበሌወች በቅማንት ስም በህወሀት

በደቡብና ኦሮምያ ድንበር አካባቢ በተነሳው ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ45 በላይ ደረሰ

(ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2010 ዓም) በደቡብና ኦሮምያ ድንበር አካባቢ በተነሳው ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ45 በላይ ደረሰ
ኢሳት ያነጋገራቸው የአካባቢው ተወላጆች እንደገለጹት በአማሮ ወረዳ አካባቢ ከሃምሌ 16 ቀን ጀምሮ በተነሳው ግጭት እስካሁን በተጠናከረው መረጃ 46 ሰዎች ሲገደሉ ከ50 በላይ ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ተኝተዋል። 2 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ፣ ከ1500 ያላነሱ ቤቶች ተቃጥለዋል ወደ 100 ሺ የሚጠጉ ዜጎች ተፈናቅለው ተራራ ላይ ለመስፈር ተገዷል። 
በጉጂ በኩል 25 ሰዎች፣ በኮሬ 17 እንዲሁም በቡርጂ በኩል 4 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አሃዙ በቡሌ ሆራ የተገደሉትን 6 ሰዎች አያካትትም።
በአሁኑ ሰአት አካባቢውን የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች ተቆጣጥረውት እንደሚገኙና በመጠኑም ቢሆን ግጭቱ መቀነሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ተፈናቃዮች ምንም አይነት እገዛ ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ተራራ ላይ የወለዱ እናቶች መኖራቸውንም ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ከአማሮ ወደ ዲላ የሚወስደው መንገድ ዝግ እንደሆነ መብራትም ግጭቱ ከተነሳ ጀምሮ መቋረጡን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በ10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የሚሰበሰው እርዳታ በቂ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2010 ዓም) በ10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የሚሰበሰው እርዳታ በቂ አይደለም ተባለ
የፖለቲካ መሪዎች ባስነሱት ግጭት የተነሳ ለተፈናቀሉ ከ50 ሺ በላይ ዜጎች የእለት እርዳታ የሚሆን ገንዘብ በተለያዩ ወገኖች እየተሰባሰ ቢሆንም፣ የእርዳታው መጠን ከችግሩ መጠን ጋር ሲነጻጻር እጅግ አነስተኛ ነው። በምስራቅ ሃረርጌ እና በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ህዝቡ በቻለው አቅም እርዳታ በማሰባሰብ ልገሳ እያደረገ ሲሆን፣ እስካሁን እየተሰጠ ያለው እርዳታ ከተፈናቃዮች ቁጥር ጋር ሲተያይ እጅግ አነስተኛ ነው። በተለይ የእርዳታ ማሰባሰቡ ስራ እየተራዘመ በሄደ ቁጥር የሚደርሰው ጉዳትም ከፍተኛ ስለሚሆን፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ተፈናቃዮች ጠይቀዋል። ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን ቦታዎች ለመመልከት የቻለው ዘጋቢያችን፣ ሁኔታው እጅግ ከባድ መሆኑን ገልጿል። በተለይ ሃረር ሰፍረው በሚገኙ ተፈናቃዮች መሃል ከምግብ እጥረትና ከጽዳት ጋር በተያያዘ የኮሌራ በሽታ ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት ማየሉን ገልጿል።

የጸጥታ አካላት በዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ

(ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2010 ዓም) የጸጥታ አካላት በዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ
በደብረታቦር ከተማ የጸጥታ አካላት በምሽት ነዋሪዎችን በመደብደብ ንብረት እንደሚዘርፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ሰሞኑን በከተማው በተደረገ ስብሰባ ላይ ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማዋ በህገመንግስቱ የተቀመጠው የሃያ አራት ሰዓት የመንቀሳቀስ መብት የለም፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ የሚገኝ የከተማዋ ነዋሪም ሆነ እንግዳ በከተማዋ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በታጠቁ ወታደሮች እንደሚደበደብ፣ ከዚያም አልፎ ንብረቱን እንደሚዘረፍ ገልጸዋል፡፡

የአባይ ወንዝ ከ25 ሔክታር በላይ በእምቦጭ አረም መወረሩ አስደንጋጭ እንደሆነባቸው የባህርዳር ነዋሪዎች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010) የአባይ ወንዝ ከ25 ሔክታር በላይ በእምቦጭ አረም መወረሩ አስደንጋጭ እንደሆነባቸው የባህርዳር ነዋሪዎች ገለጹ። አረሙን ለመከራከል ደግሞ የፌደራል መንግስቱ የሚጠበቀውን ያህል ምላሽ አለመስጠቱ ችግሩ እየተባባሰ እንዲመጣ አድርጎታል ይላሉ። ከጣና ሃይቅ አልፎ በመሄድ የአባይ ወንዝን እየወረረ ያለውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የፌደራል መንግስቱ የሚጠበቅበትን እንዳልሰራ በአማራ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናት የቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ የኢሳት ወኪሎች ያናገሯቸው የባህርዳር ነዋሪዎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። የባህርዳር ኢሳት ወኪሎች ተዘዋውረው ካናገሯቸው መካከል በቱሪዝም አስጎብኝነት የተሰማሩትና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ግለሰብ የባህርዳር ከተማ መስተዳድር የአባይ ወንዝ ከ25 ሄክታር በላይ በእምቦጭ አረም እንደተወረረ ይፋ ማድረጉ ተገቢ ነው ብለዋል። ሆኖም ግን ለዚህ የድረሱልኝ ጥሪ የፌደራል መንግስቱ ምላሽ አለመስጠቱ በሀገሪቱ ውስጥ ኢፍትሃዊነት እንደሰፈነና እኩልነት እንደሌለ የሚያመላክት ነው ብለዋል። አያይዘውም

አርበኞች ግንቦት7 በበለሳ ጫካ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል አቃቢ ህግ አስታወቀ

(ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2010 ዓም) አርበኞች ግንቦት7 በበለሳ ጫካ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል አቃቢ ህግ አስታወቀ
በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ይፋዊ እውቅና ባይሰጥም፣ የተቃዋሚ አባላት ናቸው እየተባሉ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ግለሰቦችን በሚገልጽበት ጊዜ የተቃዋሚ ሃይሎች በአገር ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ለመሆኑ ማረጋገጫ እየሰጠ ነው።
ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር ደምቢያ ወረዳ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የተለያዩ ጥቃቶችን ፈጽመዋል በሚል ፍርድ ቤት የቀረቡ 14 ዜጎች፣ ከኤርትራ በመጡ የአርበኞች ግንቦት7 አባላት ስልጠና እንደተሰጣቸውና የተለያዩ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ እንደነበር ገልጿል። የአርበኞች ግንቦት7 አባላት በበለሳና በአርማጭሆ ወረዳዎች ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የገለጸው አቃቢ ህግ፣ እነዚህ ሃይሎች ለተከሳሾች ስልጠና መስጠታቸውን አትቷል።
በአማራ ክልል ምንም አይነት የአርበኞች ግንቦት7 ህዋስም ሆነ የማሰልጠኛ ቦታ የለም በሚል ተደጋጋሚ መግለጫ ሲሰጥ የነበረው አገዛዙ፣ በለሳ አርማጭ እንዲሁም ጯሂት አካባቢ የሚገኙ ጫካዎች ለወታደራዊ ስልጠና መዋላቸውን አቃቢ ህግ ገልጿል። አንድ ነጋዴና 13 አርሶአደሮች በ ደምቢያ ወረዳ ፣ መንድባ ጫካ ውስጥ ወታደራዊ ቤዝ መስርተው ከኤርትራ በመጡ አሰልጣኞች ወታደራዊ ትምህርት ወስደው በቻይና ኮንትራክተሮች በሚገነባው የሰራባ የመስኖ ፕሮጀክት ላይ ጠቃት ፈጽመው 2 ሰዎችን መግደላቸውን ገልጿል። 

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሰርባ መስኖ ተፋሰስ ፕሮጀክት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ባላቸው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ላይ ክስ መሰረተ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሰርባ መስኖ ተፋሰስ ፕሮጀክት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ባላቸው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ላይ ክስ መሰረተ። በክስ መዝገቡ ላይ እንደተብራራው ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ አምስት ቆስለዋል። ባለፈው ዓመት መጋቢት 25/2009 ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት በወቅቱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሃላፊነት እንደሚወስድ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል። መጋቢት 25 2009 የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን በደምቢያ ወረዳ ሰርባ በሚገኘው የመስኖ ፕሮጀክት ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት፡ ፕሮጀክቱ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት ንብረት የሆነው የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ድርጅት ኢፈርት የሚያከናውነውና ከፍተኛ የህዝብ ሀብት በዘረፋ ለህወሀት የሚገባበት መሆኑ በምክንያትነት ተጠቅሷል። በህዝብ ማዕቀብ የተደረገበት የዳሽን ቢራ ለማጥመቂያ የሚሆነውን ግብዐት የሚያበቅልበት የመስኖ ፕሮጀክት መሆኑም ለጥቃት ኢላማ መደረጉን በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል። በዚህም ከስርዓቱ ጋር የጥቅምና የዓላማ ግንኙነት አላቸው በተባሉ የፕሮጀክቱ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን አርበኞች ግንቦት

At least 46 killed in South Ethiopia ethnic clashes

Image may contain: one or more people, people standing and outdoorESAT News (September 20, 2017)
At least 46 people were killed in ethnic fights in Southern Ethiopia while over 50 were injured since clashes began in July.
ESAT learnt that the conflict has wiped out two localities in Southeren Ethiopia with hundreds of houses set on fire and displacing thousands of locals.

Tuesday, September 19, 2017

በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አዲስ ውጥረት መቀስቀሱ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 9/2010) በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አዲስ ውጥረት መቀስቀሱ ተሰማ። ባለፈው ዕሁድ የተሰጠውን ህዝበውሳኔ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ውጥረት እስከአሁን የአራት ሰዎችን ህይወት ማጥፋቱ ተሰምቷል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመንግስት ሰራዊትም ወደ አካባቢው መግባቱ ታውቋል። ያለህዝብ ይሁንታ ቀደም ብለው የተካለሉት 42ቱ ቀበሌዎች ላይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ከህዝብ ግፊት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ግጭት መፈጠሩ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል። በህዝብ ተቃውሞ ውድቅ በተደረጉት 4 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግባቸው በህወሀት መንግስት በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩ ለግጭቱ መንስዔ እንደሆነ የአካባቢው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በሰሜን ጎንደር የቅማንትና የአማራን ማህበረሰብ ለመለየት በሚል የተካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ ግጭት እያገረሸ ይገኛል። ምክንያቱ ደግሞ የቅማንት ኮሚቴ አባላት የሚባሉና በሕወሃት የሚመሩ ታጣቂዎች የምርጫው ውጤት ለምን አቅጣጫውን ቀየረ በሚል ሕዝቡን በማስጨነቃቸው ነው ተብሏል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት ሕወሃት በአካባቢው ከተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሊማር አልቻለም። እንዲያውም በአካባቢው ግጭት በመፍጠር ሕዝበ ውሳኔ

ከሶማሊ አሁንም የ ኦሮሞ ተወላጆች እየተፈናቀሉ ነው ወደ ጅጅጋ የተላኩ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ወደ ኦሮምያ እንዲመለሱ ተደርጓል።

የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ ፣ ባለስልጣኖቹ እንደፈጠሩት የተናገሩትን ግጭት ለማስቆም ቃል በገቡ በማግስቱ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት የጥቃት ዘመቻውን አድማስ በማስፋት ከዛሬ ሊሌት ጀምሮ ከፍተኛ የቆዳ ስፋት ባላቸው በምስራቅ ጉጂ ዞን በሚገኙት ዳዋ እና ቡሌ ካሃር ቀበሌዎች ጥቃት መፈጹምን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ የታጠቁ የአካባቢው ነዋሪዎች የአጸፋ እርምጃ የወሰዱ ሲሆን፣ ግጭቱ ወዲያውኑ ቆሟል።

የሃረሪ ክልል ባለስልጣናት ሽጉጥ ተማዘዙ

የኦሮሞ ህዝብ በሃረሪ ክልል ባለስልጣናት የሚደርስበትን ጭቆና በመቃወም የተለያዩ ሰልፎችን ማድረጉን ተከትሎ፣ ከሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ጎን በመቆም በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ጭቆና እንዲባባስ አድርገዋል በሚል እንዲሁም በተለያዩ የዝርፊያ ወንጀሎች ሲወነጀሉ የቆዩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ሃምዛ ሙሃመድ ከስልጣን መባረራቸውን ተከትሎ ፣ እርሳቸውን ለማስተዋወቅ በተጠራው ስብሰባ ላይ የፕሬዚዳንቱ ጠባቂ ሽጉጥ በማውጣት በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ደቅኗል። 
። ግለሰቡ ከሁለት ሳምንት በፊት ኦህዴድ አዲስ አበባ ላይ ባደረገው ስብሰባ ላይ መነሳታቸውን ቀደም ብሎ መረጃው የደረሰን ሲሆን፣ ዛሬ በይፋ ከስልጣን መነሳታቸውንና በምትካቸው አቶ ጋቢሳ ተስፋዬ የሚባሉ ሰው መሾማቸውን እርሳቸውን ለማስተዋወቅ በተደረገ ዝግጅት ላይ ለማረጋገጥ ተችሎአል።
አዲሱን ምክትል ፕሬዚዳንት ለማስተዋወቅ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱላሂ ጠርተውት በነበረው ስብሰባ ላይ፣ የክልሉ የኦህዴድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለማየሁ ምጄና እና የክልሉ የፍትህና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው አቶ ጀማል፣ “ አክራሪዎችና ክልሉን የሚበጠብጡ በመሆናቸው በዚህ ስብሰባ ላይ ሊገኙ አይገባቸውም” የሚል አቋም የያዙት ፕሬዚዳንቱ ፣ በቦታው የተገኙት ሁለቱ ባለስልጣናት ከስብሰባ እንዲወጡ ሲጠይቁ “አንወጣም” በማለታቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ጠባቂ ሽጉጥ መዝዞ እንዲወጡ ለማስፈራራት ሞክሯል። በዚህ ድርጊት የተበሳጩት አቶ አብዱማሊክም እንዲሁ ሽጉጣቸውን የመዘዙ ሲሆን፣ ጉዳዩ ወደ ደም መፋሰስ ሳያመራ በግልግል ተቋጭቷል። በሁኔታው የተበሳጩት አዲሱ ተሷሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ “ እነሱ በሌሉበት ስብሰባ አልሳተፍም” በማለት፣ የትውውቁን ዝግጅቱን ረግጠው ጥለው በመውጣት ስብሰባው ተበትኗል።

ወደ ኬንያ የተለከው ስኳር እየተበላሸ ነው

ኢትዮ-ኬንያ ድንበር ላይ ስኳር ጭነው ላለፉት 43 ቀናት የቆሙት 110 መኪኖች፣ የጫኑት ስኳር እየተበላሸ እንሱም ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሹፌሮች ገልጸዋል። 
በአገር ውስጥ ከፍተኛ የስኳር እጥረት ተፈጥሮ ባለበት በዚህ ወቅት ለውጭ ምንዛሬ ሲል 100 ሺ ኩንታል ስኳር ለኬንያ መንግስት የሸጠው አገዛዙ፣ ስኳሩ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ የውጭ ምንዛሬውም ሳያገኝ፣ ጉዳቱ ለሹፈሮችና ለቤተሰቦቻቸው መትረፉን 110 ባለንብረቶች፣ 110 ሹፌሮችና የሹፌሮች ቤተሰቦች እና እረዳቶች በገራ በመሆን ለኢሳት በላኩት አቤቱታ አመልክተዋል።
ከነሃሴ 3 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ስራ የቆሙት አሽከርካሪዎች ጉዳያቸውን ከማህበራቸው ጀምሮ በሚኒስቴር ደረጃ እስካሉ ባለስልጣናት ቢያቀርቡም የሚሰማቸው አላገኙም። “ በባንክ እዳና በእቁብ የተገዙት መኪኖች 

በኢሬቻ በዓል የተገደሉ ንጹሃን ዜጎች ሞት እንዲያጣራ እና ለመጪው የኢሬቻ ክብረ በዓልም ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች ባለፈው ዓመት መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ የኢሬቻ በዓል ክብረ በዓል በማክበር ላይ እያሉ በግፍ የተገደሉት እና የተጎዱ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጉዳይ በዓለምአቀፍ ማኅበረስብ ገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል። በዘንድሮው ዓመት ለሚደረገውም የኢሬቻ በዓል ላይ ተመሳሳይ እልቂት እንዳይፈጸም ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲል አሳሰበ። ሂውማን ራይትስ ወች በሞቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ያለቁበትን ዘግናኝ እልቅት ሊከሰት የቻለው የጸጥታና ደኅንነት ኃይሎች መውጫ መንገዶችን በመዝጋት አስለቃሽ ጋዝና ከመጠን በላይ ኃይል በመጠቀማቸው መሆኑን ከቪዲዮ መረጃ ጋር አያይዞ አርቅቧል።
በሰው በተጨናነቀው በዓል ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ኃያሎች ''በእሳት ላይ ነዳጅ አርከፍክፈዋል'' ሲል ለእልቂቱ መባባስ ቀዳሚው ተጠያቂዎች ታጣቂዎቹ መሆናቸውን በ33 ገጽ ሪፖርቱ አትቷል። ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርባ ሚሊዮን
የሚሆኑት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በሚያከብሩት የኢሬቻ በዓል የዝናቡን ማክተም እና የጸደይን መግባት አስመልክቶ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው። በወቅቱ ተረጋግጠው ከሞቱት በተጨማሪ ነፍጥ ባነገቡ የጸጥታ ኃይሎች ሆን ተብሎ ተተኩሶባቸው የተገደሉ ብዙሃን ሰላማዊ ኤጎች መኖራቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።

Monday, September 18, 2017

ያለህዝብ ፍቃድ በፖለቲካ ውሳኔ በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ተጠየቀ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) ያለህዝብ ፍቃድ በፖለቲካ ውሳኔ በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ተጠየቀ። ትላንት በ8 ቀበሌዎች በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ 7ቱ ቀበሌዎች በነባሩ የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ስር መቆየትን መምረጣቸው ተገልጿል። ይህን ተከትሎም ቀደም ሲል በህወሃት መንግስት በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ በመጠየቅ ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ምርጫ ቦርድ የትላንቱን ህዝበ ውሳኔ ውጤት በፌደሬሽን ምክርቤት በኩል እንደሚገለጽ አስታውቋል። የጎንደር ህዝብ አንድነቱን ዳግም ባስመሰከረበት የትላንቱ ህዝበ ውሳኔ ሳይዘናጋ በህወሀት መንግስት የተወሰዱትን ሌሎች አካባቢዎችንም እንዲጠይቅ ጥሪ እየተደረገ ነው። የቅማንትን ልዩ አስተዳደር ለመትከል በሚል የተዘጋጀውና በ8ቀበሌዎች ትላንት የተደረገው ህዝበ ውሳኔ ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ መለጠፋቸው ታውቋል። በውጤቱም መሰረት ሰባቱ ቀበሌዎች በቀደመው አስተዳደር ስር መቀጠልን የመረጡ ሲሆን ኳቤር፣ ሎምየ የተባለው በጭልጋ ወረዳ የሚገኝ ቀበሌ ብቻ ቅማንት ተብሎ ሊተከል ወደታቀደው አስተዳደር ለመሆን ድምጽ መስጠቱ ነው የተገለጸው። በአጠቃላይ የትላንቱ ህዝበ ውሳኔ

ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የተፈናቀለበትን ግጭት ለመፍታት ሁለቱ ክልሎች በድጋሜ ቢስማሙም አሁንም ግን ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው

(ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2010 ዓም)ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የተፈናቀለበትን ግጭት ለመፍታት ሁለቱ ክልሎች በድጋሜ ቢስማሙም አሁንም ግን ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው
በ2009 ዓም በኦሮምያ ብቻ ከ400 ሺ በላይ ፣ በሶማሊ ክልልም እንዲሁ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተፈናቀሉበትን ችግር ለመፍታት የኦሮምያ ክልል መሪ አቶ ለማ መገርሳና የሶማሊው ክልል መሪ አቶ አብዲ ሙሃመድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል። ሁለቱም መሪዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ካወጁ በሁዋላ፣ ዛሬም በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች የጭነት መኪኖችን እየተከራዩ ሃረር ከተማ መግባታቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል። 
የሶማሊው ክልል መሪ ግጭቱን ለመፍታት መስማማታቸውን ከአቶ ለማ ጋር በመሆን በገለጹበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እርሳቸውም ሆኑ ቃል አቀባያቸው ሲናገሩት እንደነበረው፣ በአወዳይ ለተከሰተው ግድያም ሆነ በአጠቃላይ ለተፈጠረው ችግር የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርገዋል። የኦሮምያው መሪ አቶ ለማም እንዲሁ ግጭቱ የህዝብ ለህዝብ ሳይሆን በመሪዎች የመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን እንደ ሶማሊ ክልል አቻቸው ለግጭቱ በቀጥታ የሶማሊ ክልል መሪን ተጠያቂ አላደረጉም።

ደቡብ አሮምያ አዋሳኝ ቦታዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉት ዜጎች ተረስተዋል

(ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2010 ዓም)በደቡብ አሮምያ አዋሳኝ ቦታዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉት ዜጎች ተረስተዋል
ከሃምሌ 16 ቀን 2009 ዓም በጉጂ ኦሮሞ ማህበረሰብ እና ደቡብ ክልክ አማሮ ወረዳ በሚገኘው ኮሬ ማህበረሰብ እንዲሁም በጉጂና በቡርጂ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ እስከ 100 ሺ ዜጎች ተፈናቅለው በተለያዩ ተራራዎች ላይ ሰፍረው እንደሚገኙና ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እንደተጋለጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። እርዳታ የሚሰጣቸው አካል በመጥፋቱም ለችግር ተዳርገዋል። 
ግጭቱ ባለፈው ሳምንት እጅግ በመባባሱ ሁለት የፌደራል ፖሊሶችን ጨምሮ ከሁሉም ወገን ከ20 ያላነሱ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
(ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2010 ዓም)የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የአማራ ክልልን ክፉኛ እየተፈታተነው ቢሆንም አመራሩ ትኩረት ሰጦ እየሰራ አለመሆኑ ተነገረ፡፡
በፌደራል የሰቆጣ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ሲኒየር ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሲሳይ ሲናሞ ሰሞኑን ባቀረቡት ጥናት እንደገለፁት በአማራ ክልል አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ካሉት ህፃናት ውሰጥ 46 ነጥብ 5 በመቶ በመቀንጨር የተጠቁ ናቸው፡፡ 
እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ ከሁለት ህፃናት አንዱ ቀንጭሯል ፡፡ ዶ/ር ሲናም እንደሚሉት እነዚህ ህፃናት ታዳጊዎች ናቸው፡፡ ነገ ክልሉን ብሎም ሀገሪቱን የሚረከቡ ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች በመቀንጨር ተጐዱ ማለት በቀጣይ ሕይወታቸው የትምህርት ውጤታቸው ደካማ ይሆናል፤ በስራ መስክም የሚያስመዘግቡት ውጤት፣ ተፈጥሯዊ ችሎታቸውና የማምረት ክህሎታቸው ይቀንሳል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ክልሉ ከሚያገኘው ሠራተኛ ማህበረሰብ ግማሽ ያህሉ በዚህ ሂደት ውሰጥ የሚያልፍ ይሆናል፡፡ ይህም ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ትልቅ አደጋ ነው፡፡በተለይ ጉዳቱ በሰቆጣ ተፋሰስ ባሉ 23 ወረዳዎች ላይ የከፋ ነወ፡፡ “በዚህ አካባቢ እድሜያቸው አምስት አመት ውሰጥ ከሚገኙ ህፃናት መካከል ከ60 በመቶ በለይ የሚሆኑት

አርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄውን ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚመሩትን መሪዎችን ይፋ አደረገ

(ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2010ዓም)አርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄውን ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚመሩትን መሪዎችን ይፋ አደረገ
ንቅናቄው በኤርትራ ሲያደርግ የነበረውን ጉባኤ ሲያጠናቅቅ ድርጅቱን ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚመሩትን መሪዎች በ4 ዘርፎች ከፋፍሎ ይፋ አድርጓል። እነዚህ ተመራጮች የስራ አስፈጻሚዎች ይሆናሉ።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሊቀመንበርነት በሚመሩት በዚህ የሃላፊነት ተዋረድ፣ ኮማንደር አሰፋ ማሩ የህዝባዊ ተጋትሮ ዘርፍን በአዛዥነት፣ አርበኛ ታጋይ ገበየሁ አባጎራውና አርበኛ ታጋይ ታደለ ወንድም በምክትል አዛዥነት ይመሩታል። በፖለቲካው ዘርፍ ደግሞ አርበኛ ታጋይ ኤፍሬም ማዴቦ በዘርፍ ሃላፊነት፣ አርበኛ ታጋይ ንአምን ዘለቀና አርበኛ ታጋይ አበበ ቦጋለ በምክትል ዘርፍ ሃላፊነት ይመራሉ። የህዝባዊ እምቢተኝነቱን ዘርፍ ዶ/ር ታደሰ ብሩ የሚመሩት ሲሆን፣ አርበኛ ታጋይ ቸኮል ጌታሁንና አርበኛ ታጋይ አብርሃም ልጃለም በምክትል ሃላፊነት ያገለግላሉ። የንቅናቄውን ጽ/ቤት ደግሞ አርበኛ ታጋይ መኳንንት አበጀ በሃላፊነት እንዲሁም አርበኛ ጃንከበድ ዘሪሁን እና አርበኛ ታጋይ መላኩ ተሾመ በምክትል ሃላፊነት እንደሚመሩት ንቅናቄው ገልጿል።

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን ከ50 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን ከ50 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። በሁለቱም ክልሎች አካባቢዎች በነበረው ግጭት የሞቱት ሰዎች ልክ በውል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱ ግን ግምቶች አሉ። እየተባባሰ በሄደው ግጭት ሳቢያ ሲወዛገቡ የነበሩት የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶች በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አማካኝነት የጋራ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱ ፕሪዝዳንቶች መግለጫ ከሰጡ በኋላ ውጊያ መካሄዱንና አንድ የጸጥታ ሀይል ተገድሎ ከ 1500 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተነግሯል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ለተከሰተው ደም አፋሳሽ ግጭት የሁለቱም ክልሎች ቃል አቀባዮች ይፋዊ በሆነ መንገድ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ ሰንብተዋል። ከኦሮሚያ በኩል የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ሰላማዊ ሰዎችንና ሁለት የወረዳ አመራሮችን መግደሉን ተከትሎ የተባባሰ ግጭት መሆኑ ሲነገር ቆይቷል። በሶማሌ በኩል ደግሞ አወዳይ በተባለ አካባቢ 50 የልዩ

ዝነኛው የሙዚቃ ሰው ቴዲ አፍሮ በከፍተኛ ድምጽ የኢሳት የ2009 የአመቱ ምርጥ ሰው በሚል ተመረጠ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) ዝነኛው የሙዚቃ ሰው ቴዲ አፍሮ በከፍተኛ ድምጽ የኢሳት የ2009 የአመቱ ምርጥ ሰው በሚል ተመረጠ። በኢሳት የ2010 የአዲስ አመት ፕሮግራም ላይ በተካሄደው ስነስርአት የኢሳት የሙሉጌታ ሉሌ መታሰቢያ የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት ለድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በኪነጥበብ ባለሙያዎች አማካኝነት ተበርክቷል። በኢሳት የ2010 አዲስ አመትን አስመልክቶ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው ከነሀሴ 8 እስከ ጳጉሜ 4/2009 በኢሳት የስልክ መስመር፣ኢሜልና ፌስቡክ ድምጻቸውን ከሰጡ 2072 መራጮች ውስጥ ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን 1384 ድምጽ በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው በ2ተኛ ደረጃ ሲመረጥ በወህኒ የሚገኙት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶክተር መረራ ጉዲና በሶስተኝነት ደረጃ የመራጮችን ድምጽ አግኝተዋል።

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ያረቀቁትንና የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚመለከተውን ረቂቅ የአሜሪካ ምክር ቤት እንዲያጸድቀው ጠየቁ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ያረቀቁትንና የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚመለከተውን ረቂቅ የአሜሪካ ምክር ቤት እንዲያጸድቀው ጠየቁ። አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን እልቂት በገንዘብ መደገፍዋን እንድታቆም ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። ዛሬ ወደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመጓዝ ጥሪያቸውን ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን ሰልፈኞች በኢሬቻ አመታዊ በአል ላይ ያለቁ ኢትዮጵያውያንን ለማሰብ፣እንዲሁም የሰሞኑን ዕልቂት በማውገዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ የረቀቀው ኤች አር 128 በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የፖለቲካ አፈና የተመለከተ በመሆኑ ይህንን ከ60 በላይ የኮንግረሱ አባላት የደገፉትን የአሜሪካ ምክር ቤት ተቀብሎ እንዲያጸድቀውም ጥሪ ለማቅረብ ሰልፈኞቹ ወደ አሜሪካ ምክር ቤት ካፒቶል አምርተዋል።

የብሪታኒያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን/ቢቢሲ/የሚዲያ አፈና ባለባቸው ሀገራት በጀመረው የማስፋፊያ ፕሮግራም መሰረት በኢትዮጵያ በ3 ቋንቋዎች አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010)የብሪታኒያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን/ቢቢሲ/የሚዲያ አፈና ባለባቸው ሀገራት በጀመረው የማስፋፊያ ፕሮግራም መሰረት በኢትዮጵያ በ3 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የኢትዮጵያና የኤርትራ አድማጮችን ኢላማ ያደረገው የቢቢሲ ፕሮግራም አገልግሎት በኢንተርኔትና በፌስቡክ ይፋ ተደርጓል። በቀጣይም የሬዲዮ ስርጭት እንደሚጀምር ተገልጿል። በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው እና በተለያዩ የአለም ቋንቋዎች የሚደመጠው ቢቢሲ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ አድማጮች በ3 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ቢቢሲ አገልግሎቱን ለጊዜው መስጠት የጀመረው በኢንተርኔት መስመርና በፌስቡክ በኩል መሆኑን አስታውቋል። በቀጣይነት ደግሞ በኢትዮጵያ በ3ቱም ቋንቋዎች በአጭር ሞገድ በዚህ አመት መጨረሻ የሬዲዮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። የሬዲዮ አገልግሎቱ በእያንዳንዱ ቋንቋ ለ15 ደቂቃ የሚሰራጭ ሆኖ ሌላ ተጨማሪ የ5 ደቂቃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት በሬዲዮ እንደሚሰጥም የአፍሪካ ቢቢሲ የአርትኦት ቡድን ሃላፊ ዊል ሮስ ገልጸዋል። የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ፍራንሲስ አንስዋርዝ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ገለልተኛና ሚዛናዊ ዘገባዎችን የፕሬስ ነጻነት በተገደበባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ማሰራጨቱ ደስታ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያና የኤርትራ አድማጮችን አላማ ያደረገው የቢቢሲ ስርጭት በወቅታዊ ጉዳዮችና ዜና ላይ ያተኩራል። ከዚህ ባሻገርም በተለይ ወጣቶችን ማእከል ያደረጉ የመዝናኛ፣የስራ ፈጠራና እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች እንደሚካተቱበት የቢቢሲ የስራ ሃላፊዎች ገልጸዋል። ቢቢሲ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋዜጠኞች ጋር በመተሳሰር ብቁ ባለሙያ ለማፍራትና ነጻና ገለልተኛ የሚዲያ አውታር ሆኖ ለመስራት መታቀዱንም ነው የተናገሩት። የቢቢሲ ጋዚጠኞች ስራቸውን በኢትዮጵያ ሲያከናውኑ ከአገዛዙ ባለስልጣናት ፈቃድና እውቅና ስለማግኘታቸውና ምናልባትም ዘገባዎቻቸው የህወሃት መንግስትን ባያስደስቱ ሊደርስባቸው ከሚችለው ችግር እንዴት ሊታደጋቸው እንደሚችል የተገለጸ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በተለይ የምርጫ 97 ውጤት መጭበርበርን ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት 5 ጋዜጠኞች በሕወሐት መራሹ አገዛዝ በዘር ማጥፋት ወንጀል መከሰሳቸው እና በኋላም በአሜሪካ መንግስት ተጽእኖ ክሱ መነሳቱ ይታወሳል።

Sunday, September 17, 2017

Oromos worst affected by Ethiopia's inter-ethnic clashes

Oromos worst affected by Ethiopia's inter-ethnic clashesA prominent Ethiopian blogger has disclosed that members of the Oromo ethnic group were the worst affected by recent ethnic tensions – between the Oromia and Somali regional governments – in the country.
Daniel Berhane, who is also editor of the Horn Affairs news portal, wrote on his Facebook wall that he had received information pointing to the fact that “the displacement of Oromo residents is actually an eviction.”

በኦህዴድ በኩል ገንዘብ ያዋጣችሁ ሰዎች ለሃረር ኦሮሞ መርጃ ያዋጣችሁት ገንዘብ ለአምቦ መግረፊያ ጅራፍ ሊገዛበት እንደሚችልም በሃሳባችሁ ያዙት!

…ሁለቱ ሰዎች በመግለጫቸው ላይ ያሉትን ሰማሁኝ… በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት አንዱ ፖለቲከኛ ሌላኛው ደግሞ ምንም ፖለቲካ አለማወቃቸው ነው። አቶ ለማ መገርሳ በጣም ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ በርካታ ሺዎች የተፈናቀሉበትን ነውር 'በአንዳንድ ግለሰቦች የተከናወነ ነው…' ብለው ሲያድበሰብሱት አቶ አብዲ ኢሌ ግን 'ይሄ ድርጊት ከአመራሮች ድጋፍ ውጪ ሊፈጸም አይችልም' ከማለታቸውም በላይ፤ ከጅግጅጋ እና አካባቢው ኦሮሞ ስለሆኑ ብቻ እየተፈናቀሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለአወዳዩ 'ጥቃት' ምላሽ እንደሆነም በገደምዳሜ ተናግረዋል።

Wednesday, September 13, 2017

(ኢሳት ዜና፣ መስከረም 3 ቀን 2009 ዓም) የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸሙ ያለውን ጥቃት የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎችና አድማዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ዛሬ በነበረው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች በአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት መገደላቸው ያስቆጣቸው ዜጎች ተቃውሞአቸውን በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ ላይ ናቸው። በባቢሌ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሎአል። ተቃውሞውን ለመበተን ፖሊሶች ወደ ሰልፈኞች ተኩሰዋል።
በሃረር ደግሞ ሱቆች እንዲሁም በከተማዋ የሚሰሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ስራ በማቆም ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ውለዋል።
በርካታ ወታደሮች ቁጥጥር እያደረጉ በሚገኙባት ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ በመልካ ጀብዱና በአንዳንድ ቀበሌዎች ሱቆች ተዘግተዋል። የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጧል።
በካራሚሌ በነበረው ተቃውሞ 1 ሰው ሲገደል 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ወኪላችን የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ ገልጿል።

ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከአለም አገራት የመጨረሻውን ደረጃ ያዘች

(ኢሳት ዜና፣ መስከረም 3 ቀን 2009 ዓም) 
የአለም የኢኮኖሚ ፎረም 130 አገራትን በማወዳደር ባወጣው ሪፖርት፣ ዜጎቻቸውን በትምህርት በማነጽና እውቀታቸውን በመጠቀም ደካማ ስራ ከሰሩት አገራት መካከል ኢትዮጵያን በግንባር ቀደምነት ጠቅሷል። በአፍሪካ ሩዋንዳ፣ ጋና፣ ካሜሩን እና ሞሪሺየስ በተከታታይ 71፣72፣ 73 እና 74 ኛ ደረጃ በመያዝ የተሻለ ስራ የሰሩ አገራት ተብለው ሲወደሱ፣ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ስራ ከሰሩ የአፍሪካ አገራት መካከል 127ኛ ደረጃ በመያዝ ደካማዋ አገር ተብላለች። 
በስልጣን ላይ ያለው ገዢ ቡድን አገሪቱ በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገበች በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን ቢናገርም ፣ የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ግን ከትምህርት ጥራት ጀምሮ ያሉ መስፈርቶችን በመጠቀም ባደረገው ምርመራ ኢትዮጵያ እጅግ ደካማ አፈጻጸም የታየባት አገር ናት ሲል ገልጿል።

በኬንያ 60 ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ ተያዙ

(ኢሳት ዜና፣ መስከረም 3 ቀን 2009 ዓም) 
በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 60 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።
የናይሮቢ የፖሊስ ኮማንደር ጆሴፍ ኮሜ ፣ ''ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች እሁድ እለት ነው ናይሮቢ የገቡት። በስተምስራቅ ናይሮቢ በኪዮሌ ሚሃንጎ አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው ባሉበት ነው የያዝናቸው” ብለዋል። 

Kenya detains 60 Ethiopian immigrants


Photo: File
ESAT News (September 13, 2017)
Kenyan police say they have arrested 60 Ethiopian immigrants from a residential estate in Nairobi.
According to a report by the Xinhua News Agency, Kenyan security officers said the Ethiopians were found hiding in a house at Mihang’o area in Kayole, east of capital city.

Tuesday, September 12, 2017

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የኦሮሞ ተወላጆች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸው ታወቀ።

(ኢሳት ዜና –መስከረም 2/2010)የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የኦሮሞ ተወላጆች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸው ታወቀ። ይህን ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ሀረር ከተማ መሸሻቸው ተገልጿል። በምስራቅ ኢትዮጵያ በሶማሌና ኦሮሚያ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭትም መባባሱ ተሰምቷል። በምስራቅ ሀረርጌ በርካታ ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በደደርና አወዳይ በትንሹ 3 ሰዎች ተገድለዋል። በኦሮሞና ሶማሌ ክልል ወሰኖች ዙሪያ የተጀመረው ውጊያ በቀጠለበት ከሶማሌ ክልል የኦሮሚያ ተወላጆች እንዲወጡ መደረጋቸው በኦሮሚያ የተነሳውን የህዝብ ጥያቄና የፖለቲካውን አቅጣጫ ትኩረት ለማስቀየስ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ለኢሳት በደረሰው መረጃ በሶማሌ ክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ትዕዛዝ የኦሮሞ ተወላጆች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ሃረር ምስራቅ እዝ ጽ/ቤት እንዲሰፍሩ ተደርጓል። ይህ ዘገባ እስኪጠናቀር ድርስ ባለው መረጃ በርካታ ነዋሪዎች ከሶማሌ ክልል ሸሽተው ወደ ሀረር ከተማ ገብተዋል። የምስራቅ እዝ የጦር አባላት

የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከነገ በስቲያ ሲጀምር የግጨው ስምምነትን ተከትሎ ባለው ተቃውሞ ዙሪያ እንደሚመክር የኢሳት ምንጮች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010) የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከነገ በስቲያ ሲጀምር የግጨው ስምምነትን ተከትሎ ባለው ተቃውሞ ዙሪያ እንደሚመክር የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በሰሜን ጎንደር የቅማንት የሕዝበ ውሳኔ ከመካሄዱ በፊት በአካባቢው ውጥረት መከሰቱም የማእከላዊ ኮሚቴው መነጋገሪያ አጀንዳ ይሆናል ተብሏል። ማእከላዊ ኮሚቴው በቀጣይ ጊዜ ከስልጣን በሚወገዱ አባላት ዙሪያም ይመክራል። የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በሶስት ቡድን የተከፈለ በቅርበትና በአካባቢ ልጅነት የተደራጀ የስልጣን መሳሳብ ያለው እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በአንድ ወገን የወሎ ተወላጆችና ለሕወሃት ቅርበት ያላቸው እነ አቶ አለምነህ መኮንን በሌላ ወገን በጸረ ሰላም አካባቢ ከሚፈረጀው ጎንደር የመጡና ለአማራ ሕዝብ የሚቆረቆሩ ተደርገው የሚታሰቡ ናቸው። በአዲስ አበባ ፌደራል መንግስት ስልጣን ላይ ያሉና መሃል ሰፋሪዎች እንዳሉም ይነገራል። በዚህ ሶስት ምድብ የተከፈለው የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ታዲያ ከነገ በስቲያ ጀምሮ ማለትም ከመስከረም 4 እስከ መስከረም 8/2010 ድረስ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ምንጮች ገልጸዋል። የስብሰባው ዋና አጀንዳም በክልሉ በተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ አፈጻጸምና ከዚህ ጋር ተያይዞም የትግራይና የአማራ ክልሎችን በሚያወዛግቡ የግጨው

በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሀዝ አድጎ በሐገሪቱ የኢኮኖሚ መናጋት እየፈጠረ መሆኑን የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010) በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሀዝ አድጎ በሐገሪቱ የኢኮኖሚ መናጋት እየፈጠረ መሆኑን የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ገለጹ። የማእከላዊ ስታስቲክስ ማእከል በበኩሉ በተለይ ከፍተኛ የእህል ዋጋ ግሽበት በመኖሩ የኢኮኖሚ ቀውስ መከሰቱን ገልጿል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የዋጋ ግሽበቱን ከ8 በመቶ በታች አደርገዋለሁ እያለ ሲዝት ቢቆይም በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ መጠን ጨምሮ 10 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ታውቋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ባለፉት 22 ወራት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነው። የግሽበቱ መንስኤ ደግሞ ከእህል ምርት ማነስና የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመሩ ነው ተብሏል። የፎርቹን አዲስ ጋዜጣ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የታየባቸው እህሎች ጤፍ፣በቆሎ፣ገብስ፣ስንዴና የመሳሰሉት ናቸው። የማእከላዊ ስታስቲክስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢረሳው ይገዙ

አንድ በኢትዮጵያ በማእድን አሰሳ ላይ የነበረ አንድ የእስራኤል ኩባንያ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መሰረተ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010)ዘሔግ ኔዘርላንድ በተመሰረተው በዚህ ክስ አይ ሲ ኤል የተባለው የእስራኤል ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት የ198 ሚሊየን ዶላር ካሳ መጠየቁም ተመልክቷል። የእስራኤሉ ኩባንያ አይ ሲ ኤል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ በኔዘርላንድ ዘሔግ ክሱን የመሰረተው ስምምነቱ የተካሄደው በኔዘርላንድ በመሆኑ እንደሆነም አስታውቋል። በኢትዮጵያና በኔዘርላንድ መካከል የተፈረመውን የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ከለላ ስምምነት የጣሰ ድርጊት እንደሆነም አክሏል። አላና ፖታሽ የሚባል የካናዳ ኩባንያ በኢትዮጵያ የአፋር ክልል የጀመረው የፖታሽ ማእድን አሰሳ በመሳካቱ ለ5 አመታት የ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ቶን የፖታሽ ማዕድን ክምችት መኖሩን አረጋግጦ የማዕድን ልማቱን ለማከናወን እንደ

የሶማሊ ልዩ ሃይል በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ግድያ የሚያወገዝ ህዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው

(ኢሳት ዜና መስከረም 2 ቀን 2010 ዓም)
ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በአቶ አብዱ ሙሃመድ ኡመር የሚመራው የሶማሊ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች በግዛት ማስፋፋትና በድንበር ይገባኛል ስም በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆችን መግደላቸውንና ጥቃቱም መቀጠሉን ተከትሎ፣ ድርጊቱን የሚያወግዙ ተቃውሞዎች በተለያዩ ከተሞች ሲካሄድ ውሎአል።
በአወዳይ፣ ደደር ፣ ቆቦ፣ ጭናክሰን፣ ሃሮማያ፣ ሂርና፣ ጨለንቆ፣ ጉርሱምና ሌሎችም ከተሞች ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ሲሆን፣ ህዝቡ በዝምታ እያስጠቃን ነው የሚሉትን ኦህዴድን ፣ ከሶማሊ ታጣቂዎች ጀርባ ሆኖ ጥቃቱን ያቀነባብራል ያሉትን ህወሃትንና እና የሶማሊ ክልል

በደቡብ ኦሞ ዞን ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ ነው

(ኢሳት ዜና መስከረም 2 ቀን 2010 ዓም)
በጅንካና በተለያዩ የዞኑ ከተሞች የሚገኙ ነጋዴዎች በዘፈቀደ የተጣለውን ግብር አንከፍልም በሚለው አቋማቸው መጽናታቸውን የአካባቢው ነጋዴዎች ገልጸዋል። የዞኑ መሪዎች ፣ የነጋዴዎች ማህበር አመራሮችን በመጥራት ነጋዴዎችን እንዲያሳምኑ ቢማጸኑም የማህበሩ አመራሮች ግን “ በማናውቀው መንገድ የተጣለውን ግብር ለማስከፈል የማሳመን ስራ የመስራት ሃላፊነት ወይም ግዴታ የለብንም” በማለት መልስ ሰጥተዋል። በነጋዴዎች ማህበር መልስ ያልተደሰተው አገዛዙ፣ ከነጋዴዎች መካከል የተወሰኑትን በመምረጥና ኮሚቴ በማቋቋም ፣ ነጋዴዎችን በተናጠል እየጠራ ለማግባባት ቢሞክርም አልተሳካለትም። አብዛኞቹ ነጋዴዎች፣ በአገዛዙ የተወከሉትን ነጋዴዎች “ አርፋችሁ ተቀመጡ” በማለት ማስጠንቀቂያ እየሰጣቸው ሲሆን፣ ቀደም ብለው ግብራቸውን የከፈሉ አንዳንድ ነጋዴዎች “አሁን አገዛዙ ግብር በግማሽ ቀንሻለሁ” ብሎ ሲናገር ሃፍረት እንደተሰማቸውና አንዳንዶችም አገዛዙ ባቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ ገብተው ሌሎችን ነጋዴዎች ለማሳመን ሲሞክሩ መታየታቸውን ምንጮች

Sunday, September 3, 2017

ቴዲ አፍሮ መግለጫ አወጣ – “አንድ ዜጋ የሠርግ ወይም የልደት በዓሉን ለማክበር ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ከመንግስት ፍቃድ የመጠየቅን ያህል ሥራ…”


የተወደዳች ወገኖች በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን በዛሬው ዕለት ነሐሴ 28 – 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ልናካሒድ የነበረው የ ” ኢትዮጵያ ” አልበም ምርቃት አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ ተጠናቆና ጥሪ ለተደረገላቸው ዕንግዶች የመግቢያ ወረቀት ታድሎ ካበቃ በኃላ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ጉድዩ ይመለከተኛል የሚለው የመንግስት አካል መረሃ ግብሩን ማካሔድ እንደማንችልና ፍቃድ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ዝግጅቱ እንዳይካሄድ መከልከሉን ለክብሯን ወገኖቻችን ስናሳውቅ የተሰማንን ከፍተኛ ሀዘን በመግለጽ ነው ።