Thursday, February 4, 2016

በቡሌ ሆራ የጉምሩክ ጽ/ቤት ተቃጠለ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦረና ዞን በቡሌ ሆራ ወረዳ አንድ መኪና ኮንትሮባንድ ጭኖ አልፏል በሚል ምክንያት የጉምሩክ ጠባቂዎች መኪናውን እናስቆማለን በሚል የተኮሱት ጥይት አቶ ንጉሴ ጉዬ የተባሉትን ሰው ጭንና ትከሻቸው ላይ ማቁሰሉን ተከትሎ ለወትሮውም  ቋፍ ላይ የነበረው ህዝብ  ወደ አደባባይ በመውጣት ጉሙሩኩን ሙሉ በሙሉ አቃጥሎታል።


ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ በታዬበት በዛሬው ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይት በመተኮስ ተቃውሞውን የበተኑት ሲሆን፣ አቶ አለሙ የቦ የተባሉ ሰው ቀኝ ታፋቸው ላይ በጥይት ተመትተው ሆስፒታል ገብተዋል።

ህዝቡ አጋጣማዊውን ተቃውሞውን ለመግለጽ እንደተጠቀመበት የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment