Wednesday, February 3, 2016

22 የሚሆኑ የወልቃይት አማራ ብሔር ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በማእከላዊ ታስረው በሽብር ተከሰው ተፈቱ::

ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢ ሽማግሌዎች ሰኞ ጥር 23 ቀን 2008 ወደ መዲናችን መግባት ችለው ነበር፡፡
የትግራይ ክልል ኮሚቴዎቹና ኅበረተሰቡ በወጡትበት ይቅርታ ጠይቀው በቶሎ ካልተመለሱ እርምጃ እንደሚወስድ በትግርኛ ቴሌቪዥን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ይታወሳል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ቁጥራቸው 22 የሚሆኑ ተወካዮች ለፌደሬሽን ምክር ቤትና ለፌደራል ጉዳዮች ቢሮ አቤቱታቸውን ለማሰማት ከቀኑ 7፡00 ላይ ሃያ ሁለት አካባቢ ከጓደኞቻቸው ተለይተው ሒደው ነበር፡፡ ነገር ግን እስከ ምሽት 2፡00 መመለስ አልቻሉም፡፡
ምሽት 2፡30 ሲሆን 22ቱም የኮሚቴ አባላት መሉ በሙሉ መታሠራቸውን ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ የታሠሩበትን ፖሊስ ጣቢያ እያጣራን ሲሆን እስካሁን እንደታሰሩ ስማቸው የደረሰን የወልቃይት ኮሚቴ አባለት

1. ኮ/ል ደመቀ
2. አቶ አታላይ ዛፌ
3. አቶ ተሰማ ረታ
4. አቶ ይለፍ በየነ
5. አቶ አደራጀው ዋኘው
6. አቶ አባይ ግርማይ
7. አቶ ሸፈቀ አደም
8. አቶ ሙሉ ንጉሤ
9. አቶ ለገሠ ሐጎስ
10. አቶ አማረ ዓለሙ
11. አቶ መንግሥቱ እንዳለው
12. አቶ ካሣ ጥሩ
13. አቶ ፈጠነ ገብሩ
14. አቶ አታላይ ገብረእግዜር
15. አቶ ኢብራሒም መሐመድ
16. አቶ ማእዛ ገብሩ
17. አቶ ልዩእሸት አስፋው
18. አቶ ጌታቸው አደመ
19. አቶ ጣሒር
20. ወ/ሮ ኪሮስ
21. አቶ መብራቱ
22. አቶ አዲሱ ናቸው፡፡
እላይ የተጠቀሱት ስማቸውን ለጊዜው ያገኘዋቸው ብቻ ሲሆኑ ተጨማሪ ታሳሪ መኖር አለመኖሩን እያረጋገጥኩ ነው፡፡
‹‹ሕወሓት ጭቆና ነው እንድታገል ያደረገኝ ይላል፤ እኛ ላይ ግን ከጭቆናም አልፎ ዘር ማጥፋት ፈጽሞብናል›› የወልቃይ የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች
ሁሉም የኮሚቴው አባላት ከማእከላዊ እስር ቤት አሁን ወጥተዋል። የተወሰኑትን በስልክ አግኝቻቸዋለሁ፤ በሽብር ወንጀል እንደተከሰሱ ነው የነገሩኝ!!

No comments:

Post a Comment