Friday, August 31, 2018

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ለማስታረቅ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ


(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 24/2010)ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱትን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከድርጅቱ አመራሮች ጋር ለማስታረቅ እንቅስቃሴ የጀመሩ ባለሃብቶችና ፖለቲከኞች ተቃውሞ ገጠማቸው።

አቶ በረከትም ሆነ አቶ ታደሰ ካሳ በኢትዮጵያ ደረጃም ሆነ በአማራ ክልል ለፈጸሟቸው ወንጀሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ቢጠበቅም እናስታርቃለን የሚሉ የአማራ ክልል ባለሃብቶች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተቃውሞ እንደገጠመው ታውቋል።

እርቁ እንዲወርድ ባለሃብቶችን ይዘው እንቅስቃሴ የጀመሩት አቶ አዲሱ ለገሰና የተወሰኑ የጎንደርና የባህርዳር ባለሃብቶች ናቸው ተብሏል።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ነሐሴ 17ና 18/2010 አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰን ለጊዜው ከአባልነት አግዷል።

በመጪው መስከረም አጋማሽ ይካሄዳል እስከተባለው የድርጅቱ ጉባኤ ድረስ የታገዱት ሁለቱ የብአዴን ነባር አመራሮች ከድርጅቱ አዲስ አመራሮችና ማዕከላዊ ኮሚቴው ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል። በተለይም አቶ በረከት ስምኦን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ወጥተው የብአዴን አመራሮችን ብቃት የላቸውም፣የስልጣን ጥመኞችም ናቸው ማለታቸው ውዝግቡን እንዲካረር አድርጎታል።

የብአዴን ጽሕፈት ቤት ሃላፊው አቶ ምግባሩ ከበደና የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአቶ በረከትን ሃሳብ በማጣጣል የተባረሩት ሕግንና ደንብን መሰረት በማድረግ ነው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በብአዴን አመራሮች የተባረሩትን አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ካሳን ከድርጅቱ አዲስ አመራሮች ጋር ለማስታረቅ የተወሰኑ የጎንደርና የባህርዳር ነጋዴዎች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል።

በብአዴን መስራችና ነባር አመራር አቶ አዲሱ ለገሰ አነሳሽነት የተጀመረው እንቅስቃሴ ከጎንደር 3 ነጋዴዎች ከባህርዳር ደግሞ ሁለት ነጋዴዎችን ያካተተ መሆኑ ነው የተነገረው።

እናም ይህን እንቅስቃሴ የተረዱት የአማራ ክልል ነዋሪዎች ነጋዴዎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያለበለዚያ ግን ሒደቱን ለማስቆም እንቅስቃሴና ትግል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በአማራ ክልል ሕዝብም ሆነ በኢትዮጵያ ላይ ላደረሱት መጠነ ሰፊ ጥፋትና ወንጀል ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።

ጣልቃ የሚገቡ ሚኒስትሮች ፍትህን ሲያዛቡ ቆይተዋል ተባለ


(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 25/2010) በኢትዮጵያ ያለ ስራ ሃላፊነታቸው በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ሚኒስትሮች ፍትህን ሲያዛቡ መቆየታቸውን የቀድሞው የሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ገለጹ።

 ከነዚሁ ሚኒስትሮች መካከልም ያለሃላፊነታቸው የታክስ አቤቱታ የሚሰሙ፣ጨረታ ተከለከልኩ ያሉትን አቤቱታ በመቀበል በአማላጅነት ጣልቅ የሚገቡት አቶ በረከት ስምኦን ነበሩ ብለዋል።

ወይዘሮ አና ጎሜዝ አቶ በረከት ለፍርድ ይቅረቡ አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 25/2010) አቶ በረከት ስምዖን ለፍርድ እንዲቀርቡ በአውሮፓ ፓርላማ የፖርቹጋል ተወካይ ወይዘሮ አና ጎሜዝ ጠየቁ።

ህዝብን የጨፈጨፈ ስርዓት ዋነኛው ባለስልጣን የነበሩት አቶ በረከት ስምዖን ለፍርድ መቅረብ አለባቸው፡፡

አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ይህን ተፈጻሚ እንደሚያደርገው እጠብቃለሁ ብለዋል ወይዘሮ አና ጎሜዝ።

Thursday, August 30, 2018

ኦነግና ኦፌኮ ጥምረት ለመመስረት ድርድር ጀመሩ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ጥምረት እንደሚፈጥሩ የታወቀው፣ አስመራ የሚገኘውን በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን የኦነግ አመራር ቡድን ለመቀበል ስለሚደረገው ዝግጅት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ኦነግ የትጥቅ ትግሉን በማቆም በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እንደወሰነ፣ በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ጋር ባደረገው ውይይት አስታውቆ ነበር። በሌላ በኩል መቀመጫቸውን ኤርትራ ያደረጉና ለአመታት

የአዲስ አበባ ህዝብ ብሄር የማይጠቀስበት መታወቂያ ሊያገኝ ነው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) መስተዳድሩ የመታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 3/2010ን በማሻሻል፣ ለነዋሪዎች ብሄርን የማይጠቅስ መታወቂያ ለማደል በመዘጋጀት ላይ ነው። ከ27 አመታት በሁዋላ ብሄር ያልተጠቀሰበት መታወቂያ በመያዝ የአዲስ አበባ ህዝብ የመጀመሪያ ይሆናል። መታወቂያ ላይ ብሄርን መጥቀስ ልዩነትን የሚያሰፋ፣ ግለሰቦች በብሄራቸው እየተለዩ ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያደርግና ኢትዮጵያዊነትን አሳንሶ ብሄርን የሚያጎላ ፣በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ አንድነትና ለዜጎች ህብረት የማይጠቅም ነው በሚል ትችት ሲቀርብ ቆይቷል። አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ መክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ብሄርን ከመታወቂያ ላይ ማንሳታቸው በነዋሪዎች ዘንድ ድጋፍ እያስገኘላቸው ነው። ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሲሆኑ የኢትዮጵያን አንድነትና የህዝቦችን ትስስር ለማጠናከር የገቡትን ቃል በተለያዩ ፖሊሲዎች ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ፖሊሲዎቸውን የሚደግፉ ዜጎች ይናገራሉ። የአዲስ አበባ መስተዳደር የወሰደው እርምጃ በሌሎችም የክልል እና የፌደራል ከተሞች ተግባራዊ እንዲሆን ግፊቶች ቀጥለዋል። እስካሁን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ይህን አሰራር ለመለወጥ ያቀደ ክልል ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።

ፍርድ ቤት አቶ አብዲ ኢሌና ግብረአበሮቻቸው ያቀረበትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድመው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ እና ሌሎች 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና መብት ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። 19ኛው የወንጀል ችሎት የተከሳሾችን የዋስትና ጥያቄ ለማየት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጅ የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የማያሰጥ መሆኑን የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ፣ አቶ አብዲ በእስር ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉና ለመስከረም 4 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል የክልሉ ፖለስ አዛዥ የነበሩት ፈርሃን ተሃሪ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ኮሚሽነሩ ሄጎ የሚል የወጣቶች ቡድን በማዘጋጀት በክልሉ ረብሻ እንዲነሳ በማድረግ ለሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የመከላከያ ስራዊት ንብረት የሆነ አውሮፕላን ተከስክሶ 18 የሰራዊት አባላት እና ሲቪሎች ህይወታቸው አለፈ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ የበረራ ቁጥሩ 808 የሆነ የአየር ሃይል አውሮፕላን ለስራ ጉዳይ ከድሬዳዋ ወደ ደብረዘይት እየተጓዘ ለማረፍ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት ኤጂሬ በተባለው ቦታ ላይ ወድቆ የሰዎች ህይወት አልፏል። የአደጋው መንስዔም በባለሙያዎች እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል። በአደጋው 15 የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና 3 ሲቪሎች ህይወታቸው አልፏል።

18 dead in military aircraft crash, expert says weather could be blamed

by Engidu Woldie
ESAT News (August 30, 2018)
A light military aircraft crashed in central Ethiopia today killing 18 people including 3 civilians. The aircraft was travelling from the eastern city of Dire Dawa to the Ethiopian Air Force base in Debrezeit.
A brief statement by the Ministry of Defense sent to media says the aircraft crashed in an area called Ejere, 20 minutes outside Debrezeit.

Wednesday, August 29, 2018

እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት ሊቆምላቸው ነው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010)ለእቴጌ ጣይቱ ብጡል በአዲስ አበባ ሃውልት ሊቆምላቸው ነው።

ነገ በአዲስ አበባ አድዋ ድልድይ አካባቢ የሃውልቱ የመሰረት ድንጋይ እንደሚጣልም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በአስተዳደሩ ቱሪዝምና ባህል ቢሮ የወጣው ደብዳቤ ላይ እንደተመለከተው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማና አርቲስት አለምጸሀይ ወዳጆ የመሰረት ድንጋዩን ያኖራሉ።

የአቶ በረከት የዝወራ ዘመን አክትሟል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ--ነሐሴ 23/2010)በአቶ በረከት ይዘወር የነበረው የብአዴን የአመራር ዘመን ማክተሙን የአማራ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ።

ሃላፊው ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ አቶ በረከት የድርጅቱ መስራች በመሆናቸው እናከብራቸዋለን ነገር ግን እሳቸው በሞግዚትነት የሚያሽከረክሩት ድርጅት እንዲሆን ግን አንፈቅድም ብለዋል።

Strike at Ethiopia’s mega electric dam continues

by Engidu Woldie
ESAT News (August 29, 2018)
Workers at Ethiopia’s renaissance mega electric dam continued their strike for the fifth day demanding pay increases and an end to workplace abuses.
Construction at the dam, also known as the Grand Ethiopian Renaissance Dam, has been going on for eight years despite initial plans to complete the project in five years.
The dam has always been controversial both at home and with riparian states like Egypt that fear the project will cut into their water share of the Nile.
Contracts to the project has been monopolized by EFFORT and METEC, party conglomerates run by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), an ethnic party in power in Ethiopia until recently. Accusations are mounting against the two companies relating to embezzlement and monopoly of supplies to the national project by a party that also

Five killed in Tepi in ethnic violence

ESAT News (August 29, 2018)
Five people were killed in a renewed ethnic attack in Tepi town, 360 miles southwest of Ethiopia’s capital Addis Ababa.
A resident who spoke to ESAT on the phone from the town said three people were killed last week and another two were killed yesterday in what he said was an attack by the Shekacho against other groups.
The resident said the people in the town demand justice and an end to the domination of political power by the Shekachos, who are indigenous and consider others as settlers. He said the police, courts and government offices were all controlled by the Shekachos and other groups could not get fair justice. He also claimed other groups were deprived of job and other opportunities.
Three residents of the town were killed two weeks ago after an attack by the indigenous people against other ethnic groups. Two people were also injured in the attack.
The resident who spoke to ESAT accused that the special forces of the region have colluded with the Shekachos in attacking other groups.

አቶ አብዲ ኢሌ ፍርድ ቤት ቀረቡ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚወነጀሉት አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። አቶ አብዲን ጨምሮ ወይዘሮ ራሃማ መሐመድ፣ አቶ አብድራዛቅ ሰህኒ እና አቶ ሱልጣን መሐመድ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ባለስልጣኖቹ ከጤና ጋር በተያያዘ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ለመመልከት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፖሊስ ግለሰቦቹን ለፍርድ ያቀረበው ዜጎችን እየለዩ በማፈናቀል፣ ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ፣ አብያተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ በማድረጋቸው መሆኑን ጠቅሷል። አቶ አብዲ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ በክልሉ ውስጥ ሲፈጸሙ ለቆዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዋነኛው ተጠያቂ ተደርገው ይቆጠራሉ። ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣቸው የተለያዩ የምርመራ ሪፖርቶች የክልሉ ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ ሲያሳስብ ቆይቷል።

በአማሮ ወረዳ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኮሬና በአጎራባቹ የጉጂ ብሔረሰቦች መሃከል ከ15 ወራት በላይ ያስቆጠረዉን ግጭት ለማስቆም እርምጃ በመወሰድ ላይ መሆኑን ተከትሎ፣ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል። ሰልፈኞች ብሄርን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ ይቁም፣ ለ 15 ወራት የተዘጋው ከዲላ አማሮ አዲስ አበባ መንገድ ይከፈትል፣ እየሞትንም ቢሆን ሃገራዊ ለዉጡን በመደገፍ ተደምረናል፣ያለ ሕዝብ ፍላጎት በቀድሞ አመራሮች አስገዳጅነት የተቋቋመዉ የሰገን አካባቢ ሕዝቦች

የአባይ ግድብ ሰራተኞች ያስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰራተኞቹ አድማውን የጀመሩት ከደሞዝ እና ከአግልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ነው። ሰራተኞቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የበረሃ አበል መስተጓጎል፣ የሚከፈላቸው ክፍያ እና የሚሰሩት ስራ አለመመጣጠን ና የደህንነት ጅግሮች አድማውን እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ይገልጻሉ። ማኔጅመንቱ ሰራተኞችን ለማወያየት እቅድ መያዙን አስታውቋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን የግንባታ ፕሮጀክት በመቀማት ለሌሎች ልምድ ላላቸው ኩባንያዎች ለመስጠት ፍላጎቱ እንዳላቸው አሳውቀዋል። የአባይ ግድብ ግንባታ ምን ያክል እንደተጠናቀቀ ባይታወቅም፣ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት ከ7 አመታት በሁዋላ አንድ ወይም ሁለት ተርባይኖች ተንቀሳቀስው ሃይል ማመንጨት አለመጀመራቸው የግንባታ ሂደቱ መጓተቱን የሚያሳይ ነው።

የአባይ ግድብ ሰራተኞች ያስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰራተኞቹ አድማውን የጀመሩት ከደሞዝ እና ከአግልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ነው። ሰራተኞቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የበረሃ አበል መስተጓጎል፣ የሚከፈላቸው ክፍያ እና የሚሰሩት ስራ አለመመጣጠን ና የደህንነት ጅግሮች አድማውን እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ይገልጻሉ። ማኔጅመንቱ ሰራተኞችን ለማወያየት እቅድ መያዙን አስታውቋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን የግንባታ ፕሮጀክት በመቀማት ለሌሎች ልምድ ላላቸው ኩባንያዎች ለመስጠት ፍላጎቱ እንዳላቸው አሳውቀዋል። የአባይ ግድብ ግንባታ ምን ያክል እንደተጠናቀቀ ባይታወቅም፣ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት ከ7 አመታት በሁዋላ አንድ ወይም ሁለት ተርባይኖች ተንቀሳቀስው ሃይል ማመንጨት አለመጀመራቸው የግንባታ ሂደቱ መጓተቱን የሚያሳይ ነው።

የአባይ ግድብ ሰራተኞች ያስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰራተኞቹ አድማውን የጀመሩት ከደሞዝ እና ከአግልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ነው። ሰራተኞቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የበረሃ አበል መስተጓጎል፣ የሚከፈላቸው ክፍያ እና የሚሰሩት ስራ አለመመጣጠን ና የደህንነት ጅግሮች አድማውን እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ይገልጻሉ። ማኔጅመንቱ ሰራተኞችን ለማወያየት እቅድ መያዙን አስታውቋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን የግንባታ ፕሮጀክት በመቀማት ለሌሎች ልምድ ላላቸው ኩባንያዎች ለመስጠት ፍላጎቱ እንዳላቸው አሳውቀዋል። የአባይ ግድብ ግንባታ ምን ያክል እንደተጠናቀቀ ባይታወቅም፣ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት ከ7 አመታት በሁዋላ አንድ ወይም ሁለት ተርባይኖች ተንቀሳቀስው ሃይል ማመንጨት አለመጀመራቸው የግንባታ ሂደቱ መጓተቱን የሚያሳይ ነው።

Monday, August 27, 2018

የኢትዮጵጣ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቦሌ ፣ በባህርዳርና መቀሌ የሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ ቢመቱም ፣ የበረራ አገልገሎት ግን አልተቋረጠም። የስራ ማቆም አድማ መነሻው ከደሞዝና ከተለያዩ ጥቅማጥቆሞች ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱ ለጥያቄያቸው በቂ ምላሽ አልሰጠም። የሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን አድማ በመቱ ሰራተኞች ቦታ በጡረታ የተገለሉና በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት ያቋረጡ ሰዎችን በማሰማራት ችግሩን ለመቅረፍ እየሞከረ ነው።

አቶ አብዲ ኢሌ በተለያዩ ወንጀሎች ይጠየቃሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር አብዲ ዒሌ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች እንደሚጠየቁ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

አቶ አብዲ ዒሌ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ አስታውቋል።

ብአዴን ወሳኝ የሚባሉ ርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 21/2010) የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝ የሚባሉ ርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ።

በዚሁም መሰረት የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ እንደሚሻሻልና የድርጅቱ ስያሜም እንደሚለወጥ ገልጿል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው ያልተለመደ መግለጫ ብአዴን የሚመራበትን ርዕዮት ሊቀይር እንደሚችል አስታውቋል።

የቀድሞ የብአዴን ከፍተኛ አመራርና የኢህአዴግ ቁልፍ ሰው አቶ በረከት ስምዖን የመንቀሳቀስ መብቴ ተገድቧል ሲሉ ገለጹ።

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010)
ታዲያስ አዲስ ከተሰኘ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ አሁን ባለው ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ ገደብ ተጥሎብኛል ብለዋል።

አቶ በረከት የመንቀሳቀስ መብታቸውን የገደበው የመንግስት አካል ይሁን ሌላ በግልጽ ያስቀመጡት ነገር የለም። የብአዴን የአሁኑን አመራር ክፉኛ የወቀሱት አቶ በረከት ስምዖን የተበላሹ አመራሮች ናቸው ሲሉም ኮንነዋቸዋል።

አሁን በመሪነት የተቀመጡት የብአዴን ሰዎች ወደ አደገኛ አቅጣጫ እያመሩ በመሆኑ ህዝቡ ሊያስቆማቸው ይገባል በማለት ገልጸዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጳጉሜ አራት አዲስ አበባ ይገባል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮችንና አባላትን ለመቀበል በአዲስ አበባ የተዋቀረው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።

በመላው ዓለም ያሉት የንቅናቄው አመራርና አባላት ጳጉሜን አራት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ለማወቅ ተችሏል።

ትላንት በአዲስ አበባ የስብሰባ ማዕከል በተካሄደው የአቀባበል ኮሚቴው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መገኘታቸው ታውቋል።

የዛላ አንበሳ ድንበር በዜጎች ስምምነት ተከፈተ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 21/2010) ለበርካታ አመታት ሲያወዛግብ የቆየው የዛላ አንበሳ ድንበር በዜጎች ስምምነት መከፈቱ ተሰማ።

ይህንን ተከትሎም የሃይማኖት አባቶችን፣የሃገር ሽማግሌዎችን፣ሴቶችንና ወጣቶችን ያካተተ ቡድን በኤርትራዋ የንግድ ከተማ ሰናፌ ወደ ምትገኘው ሰርሃ ከተማ መጓዙ ተሰምቷል።

Friday, August 24, 2018

BREAKING: Bereket Simon, Tadesse Kassa suspended from Amhara party

by Engidu Woldie
ESAT News (August 24, 2018)
The central committee of the Amhara National Democratic Movement (ANDM) has announced that founding members of the Movement, Bereket Simon and Tadesse Kassa (Tadesse Tinkishu) have been suspended from membership of the central committee until its next meeting in September.
At the end of a two day congress, the ANDM central

Thursday, August 23, 2018

ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የ ኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሀልቤግ የተሰኘው የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የሶማሊላንድ የደህንነት ባለስልጣናት ሀርጌሳ ውሰጥ ነው ሁለት የአብዲ ኢሌይ የካቢኔ አባላትን ይዘው ያሰሩት። የታሰሩት ባለስልጣናት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የነበሩት ኢብራሂም አድም ማሃድ እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊው አብዲልማጅድ አህመድ ጃማ ናቸው። ባለስልጣናቱ የተያዙት፤የክልሉ ርእስ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌይ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ሲያመልጡ ነው።

የሶማሌ ክልል ሕዝብ በአቶ አብዲ ኢሌይ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሢደርስበት የቆየውን ግፍና በደል ያለማሳለስ ሲታገሉና ሲያጋልጡ የቆዩት አክቲቪስት ሙስጠፋ ኡመር በርዕሰ ብሔርነት ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ተመረጡ።

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ክፍል ውስጥ በጎረቤት ሀገራት እያገለገሉ የነበሩት የ 45 አመቱ አቶ ሙስጠፋ ኡመር ፣በአብዲ ኢሌይ ለስደት ከተዳረጉ የክልሉ ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው። ከክልሉ ከሥራ ተባረው ወደ አዲስ አበበ በመምጣት መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ ሥራ የጀመሩት አቶ ሙስጠፋ በፈላጭ ቆራጩ የአብዲ ኢሌይ አገዛዝ በክልሉ በወገኖቻቸው ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ግፎችን ከማጋለጥ ባለማቆማቸው ነው ወደ ጎረቤት ሀገር ለስደት የተዳረጉት። ካሉበት የስደት ቦታ ሆነው የአክቲቪዝም ትግላቸውን በመቀጠላቸውም የ70 ዓመት

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በመስቀል አደባባይ ላይ በደረሰው ፍንዳታ በመምራትና በማስተባበር እጃቸው አለበት የተባሉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ በተጠየቀባቸው መሰረት ፍርድ ቤት የ2 ሳምንታት የቀጠሮ ጊዜ ሰጥቷል። የተጠርጣሪው ጠበቆች ግለሰቡ ከተያዘ 43 ቀናት ያለፈው በመሆኑ የዋስ መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ ተከራክረዋል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩ ከግድያ እና ሽብር ተግባር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ እንደሚያስፈልግ

በባስኬቶ እና መሎ ወረዳዎች መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም አገርሽቶ ዋለ።

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በሁለቱ ወረዳዎች ተወላጆች መካከል ትናንት ረቡዕ የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በግጭቱን እስካሁን ሶስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡ ለረጅም ጊዜ ሁለቱ ማህበረሰቦች ለረጅም ጊዜ በፍቅር አብሮ ይኖር እንደነበሩ የሚገለጹት ነዋሪዎች፣ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በዘር ፖለቲካ መታመስ መጀመራቸውንና የአሁኑ ግጭትም ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ ተናግረዋል። አንዳንዶች የማሎ ወረዳ ነዋሪዎች ደግሞ

Wednesday, August 22, 2018

አቃቢ ህግ በሰኔ 16 የመስቀል አደባባይ ፍንዳታ ክስ መመስረት አለመቻሉ ተዘገበ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራውን አጠናቆ ለዓቃቤ ሕግ ቢያስረክብም፣ ዓቃቤ ሕጉ ክስ ከመመስረት ለድጋሚ ምርመራ ለመርማሪ ቡድኑ መዝገቡን መመለሱን ለፍርድ ቤት ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል። አቃቢ ህግ የምርመራ መዝገቡን የመለሰበት ምክንያት በቦምብ ፍንዳታው ጉዳትየደረሰባቸው ከ100 በላይ ቢሆንም፣ መርማሪው ፖሊስ ግን የ40 ሰዎችን ቃል ብቻ የተቀበለ በመሆኑ ነው።

በሃረር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶችና ተወላጆች ወደ ክልላቸው እየተመለሱ ነው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደዘገበው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ወደ ክልላቸው በመመለስ ላይ ናቸው። ህወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ሊነሳ ይችላል በሚል ቅስቀሳ የትግራይ ተወላጆች ከአካባቢው እንዲለቁ ማድረጉን የሚገልጸው ወኪላችን፣ ይህንን በማመን ባለፉት 3 ሳምንታት በርካታ ባለሀብቶች መውጣታቸውን ገልጿል። በህወሃት በኩል

በደቡብ ክልል ባስኪቶ ልዩ ወረዳ ላይ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የባስኪቶ ሁለት ፖሊሶች ማሎ ወረዳ ላይ መታሰራቸውን ተከትሎ የባስኪቶ ወረዳ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን ለማሰመት አደባባይ ወጥተዋል። መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውን እንዲሁም በማሎ ወረዳ ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጥይት የተጎዱ ነዋሪዎች መኖራቸውም አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሶማሊ ክልል የመብት ተሟጋቾች እየተካሄደ ባለው የሶህዴፓ ግምገማ ደስተኞች እንዳልሆኑ እየገለጹ ነው

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ክልሉን ለረጅም ጊዜ ሲያስተዳድር የነበረው ሶህዴፓ፣ በሊቀመንበሩ በአቶ አብዲ ሺዴ አማካኝነት ግምገማ እያካሄደ ቢሆንም፣ የመብት ተሟጋች የክልሉ ተወላጆች እንደሚሉት ግን በክልሉ መሰረታዊ የሆነ መዋቅራዊ ለውጥ የማምጣት ፍላጎት ይኖራል ብለው ለማመን እየተቸገሩ ነው። የሶህዴፓ አመራሮች እና አባላት በግምገማው ወቅት እጅግ በርካታ ወንጀሎችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ ክልሉን በጊዚያዊነት የሚመሩትን ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት በተሃድሶ ስም መልሶ ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚደረገው ሩጫ በክልሉ ውስጥ የህዝብ

Tuesday, August 21, 2018

BREAKING Ethiopia: Arrest warrant issued on former spy chief Getachew Assefa

by Engidu Woldie
ESAT News (August 21, 2018)
An Ethiopian court has issued an arrest warrant on former spy chief, Getachew Assefa, whom ESAT sources say has escaped to neighboring Sudan.
Our source close to the government also said Getachew Assefa has been staying in a hotel in his hometown, Mekele, Tigray region for a month. He he has not been seen at the ongoing meeting of the ruling party, EPRDF.

Ethiopia: Authorities arrest over 170 people for inciting violence

ESAT News (August 21, 2018)
Authorities in Ethiopia’s restive Oromo region have arrested 171 people accused of inciting deadly violence and ethnic motivated attacks in the region.
Head of political affairs with the regional party, OPDO, Addisu Arega told local media that the suspects were arrested in several towns in the region accused of killings, inciting violence and looting.
Among those arrested were seven suspects of a mob lynching in Shashemene last week. A mob attacked a young man, accusing him of carrying a bomb on his person. The man was then hanged upside down on a utility pole and beaten to death.

ከሆሊስቲክ ፈተና ጋር በተያያዘ አድማ ያደረጉ ተማሪዎች ታገዱ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ/ም ) በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ከሆሊስቲክ ወይም ከማጠቃለያ ፈተና ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩትን አድማ ተከትሎ ሰኔ 7 ቀን 2010ዓ.ም ከግቢ መባረራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሰሞኑን ከታማኝ ምንጮች የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ዓመት ሶስተኛ ዓመት የነበሩ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ትምህርት እንዳይከታተሉ የእግድ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ታውቋል። በዩኒቨርስቲው አሰራርና ልምድ በዚህ ዓመት ሶስተኛ ዓመት ያስተማረ መምህር በቀጣይ ዓመት የአራተኛ ዓመት ተማሪዎችን በማስተማር እንደሚቀጥል የሚታወቅ ቢሆንም፣ በዚህ ዓመት የአራተኛ ዓመት ተማሪዎችን የሚያስተምሩ መምህራን ሌላ ምደባ እደተካሄደ አረጋግጠዋል፡፡ በ2011 ዓ.ም ዩኒቨርስቲው የአራተኛ ዓመት የቴክኖሎጂ ተማሪዎች እንደማይኖሩት፣ በዚህ አሰራር ከቀጠለና አቋሙን ካልቀየረ በ2012 ዓ.ም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ምንም ተመራቂ ተማሪ እንደማይኖር ምንጮች ገልጸዋል።

የተጀመረው ሰላም እንዲቀጥል ካስፈለገ በስሜት መነዳት እንዲቆም አመራሩ የአሰራር ሂደቱን ማስተካከል አለበት ተባለ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ/ም ) የተለያዩ መድረኮች ሲካሄዱ በህብረተሰቡ ሚቀርቡ ጥያቄዎችን በመከታተል ምላሽ አለመሰጠቱ ፣በወጣቱ ዘንድ በስሜት የመነዳት ሁኔታ እንዲከሰት እያደረገ መሆኑን ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በተካሄደ ህዝባዊ ውይይት ላይ ተገልጿል። ህብረተሰቡን ወደ ከፍተኛ ንዴትና ስሜት ውስጥ የሚያስገባው የአመራሩ ቸልተኝነት እንደሆነ የሚናገሩት አስተያዬት ሰጪ፣ የህዋሃት መሪዎች ከአሁን በፊት የህብረተሰቡን ጥያቄ በቸለተኝነት በመመልከት የክልሉ አመራሮች ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ፈለጋቸውን እንዲከተሉ በማድረግ የሰሩትን ስራ መድገም አይገባም ብለዋል። አሁንም ህዝብን የሚያስቆጣን ነገር አመራሩ ለይቶ ማወቅና የሚከሰቱ ቸግሮችን በፍጥነት መፍታት ካልቻለ በስሜት የሚነዱ ወጣቶች በየጊዜው መፈጠራቸውና ለክልሉም ሆነ ለሃገሪቱ ስጋት እንደሆኑ አስተያዬት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ አመራሩ ራሱን መፈተሸ አለበት የሚሉት አስተያዬት ሰጪ ወጣቱ በስሜት መነዳት እንዲያቆም ና የተጀመረው ሰላም አምዳጨልም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሰሞኑ የጅግጅጋ ግጭት በአብዲ ኢሌይ ኃይላት የተከፈተባቸውን ጥቃት በመሸሽ ሀረር ከተማ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ በመቶ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ ጅግጅጋ ተመለሱ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢሳት ወኪል ከሥፍራው እንደዘገበው ፣ተፈናቃዮቹ ወደ ጅግጅጋ እንዲመለሱ የተደረገው ከተማው በመረጋጋቱና የአካባቢው ሰላም ወደ ቀድሞው ሁኔታ በመመለሱ ነው። በአብዲ ኢሌይ ሲመሩ የቆዩት የልዩ ኃይል አባላት በፈጸሙት ጥቃት ከአርባ በላይ ሰዎች መገደላቸውና አስራ አንድ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው ይታወቃል። ይሁንና የተፈጸመውን ድርጊት በጥብቅ ከማውገዝ ጀምሮ ተፈናቃዮችን ዳግም እስከ ማቋቋም ድረስ በተደረገው ጥረ ኢትዮጵያውያን ሀይማኖትና ዘር ሳይለያቸው ከዳር እስከ ዳር በአንድነት መቆማቸው ብዙዎችን አስደስቷል። በዚህ ሂደት ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን ጨምሮ ሁሉም የእምነት ተቋማት፣ የጅግጅጋን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ይገኙበታል። በአሁኑ ወቅትም የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተፈናቃዮቹን እስከመጨረሻው ለመርዳት ርብርብ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ የእስልምና አባቶች እስልምና የሰላምና የአንድነት ምንጭ መሆኑን ሰበኩ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሮ በዋለው 1ሺ 439ኛው የኢድ አል አድሃ ( አረፋ) በአል ላይ የተገኙት የሃይማኖቱ አባቶች እስልምና የሰላምና አንድነት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላምን በመጠበቅ፣ የአገሩን አንድነት በመጠበቅ አገሩን ማሳደግ እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካይ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ተናግረዋል። ሃጂ ኡመር እስልምና ማለት ሰላም ነው፣ የሰላም መፍለቂያ ነው፣ የአንድነት መፍለቂያ ነው፣ የመተባበር፣ የመከባበር መፍለቂያ ነው ብለዋል። ሃጂ ኡመር አክለውም እያንዳንዱ ለራሱ የሚያስደስተውን ለሌላው ወንድሙ ካልተመኘ ትክክል አይደለም ያሉ ሲሆን፣ በራሳችን እንዲሆን የማንፈልገውን በሌሎች ላይ እንዲደርስ ማድረግ ከእስልምና አስተምሮት ውጭ ነው። ሃጂ ኡመር ሙስሊሙ ማህበረሰብ አርቆ ማየት እንዳለበት ወደ አንድነት ወደ ሰላምና ልማት መመለስ እንደሚገባው ሃይማኖታዊ፣ አባታዊና አገራዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኡስታዝ አቡበክር አህመድም እንዲሁ እስልምና ሰላም መሆኑን ጥቅሰው በየትም መልኩ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ፣ ሁከት እንዳይነሳ መመሪያ ያስተላለፈ ሃይማኖት በመሆኑ፣ በእኛ እጅ አደጋ ሊደርስ ለጥፋት ምክንያት ልንሆን አንችልም ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች በተለያዩ አካባቢዎች የደረሱ የእምነት ተቋማት ቃጠሎዎችን የሚያወግዝዙ መፈክሮችን ይዘው ወደ አደባባይ ወጥተዋል። የደሴ ሙስሊሞችም እንዲሁ በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዘው፣ የመቅበሪያና የመስገጃ ቦታዎችን አጥተው የተቸገሩ የአክሱም ሙስሊሞችም ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

Monday, August 20, 2018

''ኢትዮጵያ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን አቅጣጫ ስታ አደገኛ ጉዞ ላይ ናት።

Mesay Mekonnen
 መፍትሄው ወደ ቦታችን መመለስ ነው።'' ወ/ሮ ፈትለወርቅ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሀላፊ። ህወሀት በጥፍሯ ቆማ እየፎከረች ነው። የፓርላማ የኢህአዴግ ተጠሪ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴም ''ህዝበኝነት'' እያለ ዶ/ር አብይን ከፍ ዝቅ አድርጎ ሲያብጠለጥል ሰማሁት።

የመለስን ሞት ስድስተኛ ዓመት እያሰቡ ያሉት ህወሀቶች ድንኳን ጥለው ለቅሶ ተቀምጠዋል። ቤተመንግስቱን ማጣታቸው በሚገባ አንገብግቧቸዋል። ሊቀበሉት

Rights watchdog renews call for justice in Somali region

ESAT News (August 20, 2018)
The Human Rights Watch urge the Ethiopian government to investigate rights abuses in the Somali region of Eastern Ethiopia, including investigations on former and current regional officials, and bring perpetrators to justice.
Renewing its call for justice in the Somali region, the rights watchdog said “the government of Ethiopia should commit to an in-depth, independent fact-finding mission into many years of rights abuses and violations of the laws of war in eastern Ethiopia’s Somali region.”

የጋምቤላ ወጣቶች ወይም በእነሱ አባባል ዳልዲሞች ከዶክተር አብይ አሕመድ ጋር መነጋገር እንፈልጋለን ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶቹ ዛሬ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ክልሉል እያስተዳደረ ያለው አካል ላይ ላዩን የለውጡ ደጋፊ በመምሰል፤ ከአዲሱ የዶክተር አብይ አስተዳደር ጋር መደመራቸውን በይፋ የሚገልጹ ወጣቶችን ማሰር ጀምሯል። ወጣቶቹ ወይም ዳልዲሞቹ ሰሞኑን በጋምቤላ ተሳብሰበው ባወጡት መግለጫ፤ በሕወሓት የተፈጠረው እና በጣም ጨቋኝና በዝባዥ የሆነው የክልሉ ገዢ መደብ በቃል ደረጃ “ተደምሬያለሁ” እያለ በተግባር ግን ለዶር አብይ ድጋፍ ለማሳዬት የወጡ የጋምቤላ ወጣቶችን ማሰሩን በማውገዝ፣ የታሰሩት ወጣቶች በቶሎ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። እንደ

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቅ ዙሪያ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ሚና ጉልህ ድርሻ እንደነበረው የንቅናቄው ዋና ጸሀፊ ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ገለጹ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ) አቶ አንዳርጋቸው ይህን የገለሱት በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ታላቅ ስብሰባ ላይ የኤርትራ መንግስት የነጻነት ትግሉን በማገዝ በኩል ላደረገው ድጋፍና ውለታ ምስጋና ባቀረቡበት ጊዜ ነው። አንዳንድ ወገኖች ኤርትራና ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ ወደ እርቅ የመጡት በውጭ ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሆነ መላምት ሢሰነዝሩ ቢደመጡም፤ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ግን ሀገራቱ ወደ እርቅና ፍቅር የመጡት ያለ አንድም የውጭ ኃይላት ሸምጋይ እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል።

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ኦነግ ስም የሚደረጉ ህገ ወጥ ድርጊቶች ድርጅቱን እንደማይወክል የኦነግ ቃል አቀባይ ገለጹ።

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ) ቃል አቀባዩ አቶ ቶሌራ አደባ ኦነግ ሰላም ለማወክ እንደማይንቀሳቀስ በመጥቀስ፤ በክልሉ አንዳንድ ቦታዎች የሚታዩ ህገወጥ ድርጊቶች ግንባሩን እንደማይወክሉ አረጋግጠዋል። “ኦነግ የኦሮሞን ህዝብ ሰላም እና ደህንነት ለማደፍረስ ሳይሆን ህዝቡን ከስጋት እና ሮሮ በማውጣት” ነው የሚሠራው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ግንባሩ ዓላማውም ለህዝቡ የሚመኝለትን ሰላም እና ዴሞክራሲማጎናጸፍ እንደሆነ አስረድተዋል።

በቀጣዩ የህወኃት ጉባኤ፣ ለውጡን የማይደግፈው ቡድን ስልጣን ላይ ከወጣ በሀገሪቱ ሰላም አይኖርም” ሲሉ ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ አስጠነቀቁ ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድሞው ኢታማዦር ሹም በወቅቱ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣በክልሉ በትግራይ ወጣቶችና ምሁራን ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ የለውጥ ጥያቄዎች እየተሰሙ መምጣታቸውን በመጠቆም፣ ይሑንና ሕዝቡ የለውጡ አጋር እንዳይሆን በህወኃት አመራሮች ተጠፍንጎ መያዙን አስረድተዋል። “ህወሓት ዋነኛውን ስልጣን ይዞ በነበረበት ወቅት ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲያዊ መብትቶችን ረግጦ ነው ሲገዛ የቆየው”

Wednesday, August 15, 2018

ለሱዳን ተላልፈው የተሰጡ የኢትዮጵያ መሬቶች በአቶ አባይ ጸሀዬ ፊርማ የተፈጸሙ መሆናቸው ተጋለጠ። ይህንን የሚያሳየውና የአቶ አባይ ጸሀዬ ስምምነት የተገለጸበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል።

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) ስምምነቱን የተፈራረሙት አቶ ደመቀ መኮንን እንደሆኑ ተደርጎ ለዓመታት ሲገለጽ የነበረው ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነም የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ አስታውቋል።
አቶ አባይ ጸሃዬ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ የተፈራረሙት ሰነድ ላይ መሬቶቹ በአስቸኳይ ለሱዳን ተላልፈው እንዲሰጡ የሚል ትዕዛዝ እንዳለበትም መረዳት ተችሏል።
በኢትዮጵያ ድንበር ጉዳዮች ኮሚቴ የተገኘው ሰነድ እንደሚያመለክተው በአቶ ደመቀ መኮንን ፊርማ የተፈጸመ ነው የተባለው ስምምነት ትክክለኛ እንዳልሆነ ተረጋግጧል።
ሰነዱን የፈረሙት የህወሀት አመራርና በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩት አቶ አባይ ጸሀዬ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
8 አንቀጾች ባሉት ሰነድ ላይ እንደተመለከተው በኢትዮጵያ ይዞታ ስር የሚገኙ ሶስት የእርሻ መሬቶች በአስቸኳይ ለሱዳን እንዲሰጡ አቶ አባይ ጸሀዬ በፊርማቸው ተስማምተዋል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር መሬት መስጠት አቆመ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) የአዲስ አበባ መስተዳድር መሬት መስጠት ማቆሙን በይፋ አስታወቀ።
የተጀመሩ ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ከኮንዲሚኒየምና መሰል የቤት ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ እንደሚወጣም መስተዳድሩ ግልጽ አድርጓል።
በኢንደስትሪ ግንባታ ጭምር የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው በተገለጸበት በዚህ መመሪያ ከበቂ ቅድመ ዝግጅት በኋላ ጉዳዮቹን መልሶ ማየት እንደሚቻልም ተመልቷል።
ከግል የኢንደስትሪ አልሚዎች ጥያቄ በተጨማሪ የሰነድ አልባና አግባብ ባለው እክል ሳይፈቀዱ የተያዙ ቦታዎችን በተመለከተም የከተማው አስተዳደር አገልግሎት እንደማይሰጥም በይፋ ተገልጿል።
መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ማህበራትን በተመለከተም የቅድመ ማጣራት ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ አግልግሎት እንደማይሰጥም የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

አቶ ተስፋዬ ኡርጌ እየተካሄዱ ካሉ ግጭቶች ጋር በተያያዘ ምርመራ ተጀመረባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ባለስልጣን የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ካሉ ግጭቶች ጋር በተያያዘም ምርመራ እንደተጀመረባቸው ተገለጸ።
አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት በማስተባበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።
ግለሰቡ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የግዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ወህኒ ቤት ተመልሰዋል።
ተጠርጣሪው አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በውጭ ሃገር ካሉ ቡድኖች ጋር አላቸው በሚል የተጀመረባቸው ምርመራም መቀጠሉ ተመልክቷል።
ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ለማድረግ በተጠራውና ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ሕዝባዊ ትዕይንት በተወረወረ የእጅ ቦምብ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።

የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን አዲስ የዋጋ ታሪፍ ጭማሪ ማስተካከያ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ተጨማሪ የዋጋ ታሪፍ ሊጥል ነው። ከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ ተጠቃሚዎች በአዲሱ ተመን እስከ 350 በመቶ ጭማሪ ክፍያ ይጠየቃሉ። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት (EEU)፣ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ፓወር (EEP)፤ ከውሃ፣ መስኖ እና ኤሌትሪክ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ጥናቱን ማድረጉን አስታውቋል። በአዲሱ የዋጋ ማስተካከያ መሰረትም በፊት ድርጅቱ ከሚያገኘው ከ7 እስከ 10 ቢሊዮን ብር ገቢ ወደ 35 ቢሊዮን ብር ያስገባል ተብሎ ታቅዷል። የዋጋ ማስተካከያው ከ13 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መደረጉን የኢትዮጵያ መብራት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ ለካፒታል ጋዜጣ ተናግረዋል። ዋና ስራስኪያጇ አዲሱ የዋጋ ጭማሪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳይጎዱ ከለላ ይሰጣል ብለዋል። ‘’በአጠቃላይ 2.9 ሚሊዮን ደንበኞች አሉን። ከእነዚህ ውስጥ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ከ50 ኪሎ ዋት በታች ተጠቃሚዎች ናቸው። በእኛ ጥናት መሰረትም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ያደረገ ነው። ይህ ቁጥርም ከአጠቃላይ

በጅግጅጋ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ባንዲራና መገንጠልን የሚቀሰቅሱ ባነሮች በብዛት እየታተሙ መሆናቸው ተገለጸ። ኮማንድ ፖስቱ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) በስፍራው ያሉ የኢሳት ወኪሎች ባደረሱን መረጃ መሰረት፣ ቀደም ሲል አብዲ ኢሌ ያደራጃቸው ሄጎ የእተባሉ የሚጠሩት ቡድኖች፤ ትናንትና በጅግጅጋ ከተማ የመንግስት መኪኖችን ጭምር በመጠቀም እና የኦብነግን ባንዲራ በማውለብለብ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረዋል። እነዚሁ ቡድኖች ክልሉን ለማረጋጋት ከተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ግጭት መፍጠራቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት በመሳሪያ ኃይል የበተኗቸው ሲሆን፣ በተኩስ ልውውጡ በፖሊስ መኪና ላይ የኦብነግ ባንዲራ ሰቅሎ ሲያሽከረክር የነበረ የሂጎ አባል ቆስሏል። የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ሰሞኑን በሀረርጌ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት 41 ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል። ምንጮች እንደሚሉት ከሂጎዎ ጋር የተፋጠጠው መከላከያ ብቻ አይደለም። ህዝቡም የቡድኑ አባላት እየፈጸሙት ያለውን ህገወጥ ተግባር ለመመከት ባለ በሌለ አቅሙ እየታገላቸው ነው። በትናንትናው ዕለት ሕዝቡ ከሂጎዎች ጥቃት ድንጋይ በመወርወር ራሱን ሲከላከል መከላከያ ሰራዊት ወደቦታው ደርሶ ግጭቱን ቢያበርድም፣ ሂጎዎቹ በፍጥነት በመኪና ከአካባቢው ተሰውረዋል። አዲስ የተቋቋመው የክልሉ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ጄነራል ሀሰን፣ የኦጋዴ ብሄራዊ ነጻነት

የዓባይ ግድብን እየሠራ የነበረው ሳሊኒ የኮንስትራክሽን ኩባንያ መንግስትን ከአስር ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መጠየቁ ተሰማ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) የዓባይ ግድብን የሜካኒካል ስራ ኃላፊነት የወሰደው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን በምህጻረ ቃሉ ሜቴክ፣ በኮንትራት የወሰደውን ሥራ በተቀመጠለት ጊዜ እና በትክክል ሰርቶ ማስረከብ ባለመቻሉ የጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ሌሎች ስራዎችን መቀጠል አልቻለም ሲሉ ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት ውሉ ያልተጠበቀለት ሳሊኒ ኩባንያ የኢትዮጵያን መንግስት ከ350 ሚለየን ዩሮ በላይ ካሳ እንደጠየቀ ለፕሮጀክቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት ሳሊኒ ኮንስትራክሽን የጠየቀው የካሳ ክፍያ፣ 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ይሆናል። አጠቃላይ ግድቡ 84 ቢሊየን ብር ይፈጃል የተባለመሆኑ ሲታወስ፣ አሁን ሳሊኒ የጠየቀው ካሳ ከአጠቃላይ የግድቡ ወጭ 8 ነጥብ 8 በመቶ ይሸፍናል። ምንጮቹ እንዳሉት፣ ግድቡ በጠቅላላው ስራ ይጀምራል በተባለበት ጊዜ ሜቴክ ኃላፊነቱን በወሰደው የሜካኒካል ስራው ችግር ምክንያት አስራ ስድስቱም ተርባይኖች መስራት አለመቻላቸው መንግስትን ጭምር እጅግ ያስደነገጠ ሆኗል። የግድቡ ዋና መሃንዲስ የነበሩት ኢንጂነር ስመኜው በቀለ በቅርቡ በመኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ይታወቃል። ፖሊስ ምርመራውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እየቀጠለ እንደሆነና ውጤቱን በቶሎ ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ቢገልጽም፣ እስካሁን ድረስ ባለመነገሩ፣ ሕዝቡ በፖሊስ ላይ ግፊት እያደረገ ይገኛል።

ለሃይማኖታዊ የሃጂ ፀሎት የሚጓዙ ምእመናን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ መንገላታት ደረሰባቸው።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ) መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በማድረግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገቢውን የበረራ መስፈርቶችን አሟልተው ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመብረር ሲጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸው በረራቸው እንዲሰረዝ በመደረጉ ለከፍተኛ እንግልትና ለተጨማሪ ወጪዎች ተጋላጭ ሆነዋል። አብዛሃኞቹ እድሜያቸው የገፋ አቅመ ደካማ አዛውንቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ህመምተኞች፣ ከክፍለ ሃገር ድረስ የመጡ የሃጂ ተጓዦች፣ የሚሄዱበት ስለሌላቸው በአየር ማረፊያው ግቢ ውስጥ በርሃብና ማረፊያ እጦት መንገላታቸውን ታውቋል። መንገደኞቹ ካለምንም በቂ ማረፊያ አልባሌ ቦታዎች ላይ በየአግዳሚው ላይ እንዲተኙ መገደዳቸው እንዳሳዘናቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ዝና ያለው ብቻ ስለሆነ ሳይሆን አገራቸውንም ጭምር ለማገዝ ባላቸው ፍላጎት፤ በአገራቸው አየር መንገድ ለመብረር ምርጫ ቢያደርጉም ድርጅቱ ግን እንደ ዜጋም እንደ ደንበኛም አሳፋሪ ተግባር ፈጽሞብናል ይላሉ። በረራው አስቀድሞ መስተጓጎሉን ሊያሳውቀን ይገባ ነበር። ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ የሚቀበሉን ዘመድና ጓደኞቻችንም እኛን በመጠበቅ አብረውን እየተንገላቱ

Ethiopia: Number of IDPs reach 2.8 million

ESAT News (August 15, 2018)
The United Nations Children’s Fund (UNICEF) says the number of internally displaced persons (IDPs) in Ethiopia has increased to 2.8 million from 1.6 million at the beginning of the year.
In its Horn of Africa situation report yesterday, UNICEF said there are nearly rae also 920,000 refugees in Ethiopia.
It said there are 16.3 million people in need of humanitarian services in the Horn of Africa. While 8.2 million children are in need of humanitarian services, at least 6.2 million children are at risk of dropping out of school, according to the humanitarian agency.
It warned that seasonal flooding from July to September is expected to affect 2.5 million people in the region.

Ethiopia: Police investigating suspects overseas in foiled assassination attempt on PM

ESAT News (August 15, 2018)
The federal court of first instance in Addis Ababa gave additional 8 days to police that is investigating suspects in foreign countries linked to the June 23 assassination attempt on the life of Prime Minister Abiy Ahmed.
Police has requested the court for additional 14 days to further investigations on the prime suspect, Tesfaye Urgie, who ironically was the head of the anti-terrorism task force wirth the Ethiopian National Intelligence and Security Service (NISS), the country’s spy agency.
Police told the court, which allow them 8 days of the requested 14 days, that they had new leads showing Urgie might have a hand in other deadly attacks and clashes in the country besides having a leading role in the June 23 assassination attempt on Dr. Ahmed at a support rally at Meskel Square in central Addis Ababa. Police also said more time was needed to investigate suspects who live in foreign countries that they believe had worked in tandem with Urgie.

Tuesday, August 14, 2018

“በክልላችን ባለፉት ሁለትና ሶስት ወራት ብቻ ለውጡን የማይመጥኑ አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባራት እየተከሰቱ ስለሆነ ፣ለውጡ እንዳይቀለበስ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል”ሲሉ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አሣሰቡ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶችን አስመልክተው በፌስቡክ ገጻቸው በተለይ ለክልሉ ለውጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት ፣ባለፉት ሁለት እና ሦስት አመታት ተኪ የሌለውን ህይወታችሁን ጭምር ከፍላችሁ ዛሬ የነፃነት፣ የፍትህ እና የእኩልነት ድባብ እንድንጎናጸፍ፤ እንዲሁም የአንድነት፣ የመከባበር ፣ የፍቅር እና የይቅር ባይነት መንፈስ እና ተስፋእንዲለመልም አስችላችኋል በማለት አወድሰዋል። ትግላችሁ፣ ጥላቻ፣ ቂም በቀልና ጭቆና ቦታቸውን ለፍቅር፣ ለይቅርባይነትና ለነፃነት እንዲለቁ በማድረግ ማንም ባልገመተው ፍጥነትበለውጥ ተስፋ እንድንሞላ አድርጎናል ሲሉም አድናቆታቸውን ገልጸዋል። “አሁን የምንገኝበት ወቅት ለውጡ ከተስፋ ተራምዶ የኋላ ማርሽ በማያስገባበት ደረጃ ላይ አልደረሰም” ያሉት አቶ ንጉሡ ይልቁንም አልፎአልፎ የምናስተውላቸው ድርጊቶች የተስፋችንን ጭላንጭል የማጨለም፤ እርምጃችንን የመግታት እና ወደ ኋላ የመጎተት አደጋ እየደቀኑናቸው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። እንደ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው ገለጻ፣ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በዚያ የከፋው የግጭት፣ የሁከት እና የብጥብጥ ጊዜ እንኳን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የራስን ንብረት የማውደም እና በርካታ ተሽከርካሪዎችን የማቃጠል እርምጃዎች ተወስደዋል::

“የወልቃይትን ጉዳይ ብንሸሸው፣ ብንሸፋፍነው ሊተወን አልቻለም” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተናገሩ።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህን ያሉት፤ ከአማራ ክልል ምሁራን ጋር በባህር ዳር ከተማ እያደረጉት ባለው ውይይት ላይ ጉዳዩን አስመልክቶ ለተሰነዘረባቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው። ከተሳታፊ ምሁራኑ መካከል አንዱ “የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነታችን ይከበር በማለት ፌዴራል መንግስት ድረስ እየሄደ ጥያቄ ሲያቀርብ ከላይ የሚሰጠው ምላሽ ግን ‘’ህወሓትን ጠይቁ” የሚል ነው። በወልቃይት ጉዳይ የብአዴን አቋም ምንድነው?” በማለት ነው ጥያቄ የሰነዘሩት። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ በወልቃይት ጉዳይ ብአዴን እስካሁን ዋነኛ ጠያቂ እንዳልነበረም አምነዋል። “ይሁንና የወልቃይትን ነገር ብንሸሸው፣ብንሸፋፍነው፣ ምን ብንለው መሄጃ የለንም” ያሉት አቶ ገዱ “መፍትሔው ያ ህዝብ የፈለገውን ማንነት እንዲመርጥና እንዲከበርለት ነጻነት መስጠት ነው” ብለዋል። “የወልቃይት የማንነት ትያቄ ከአማራ ህዝብ ጥያቄ በላይ የሌላም ሆኗል” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ሕዝቡ በነጻነት እንዲወስን ከማድረግ የተሻለ መፍትሔ እንደሌለ አስረድተዋል። ወልቃይት የትግራይ ክልል ግዛት ነው የሚል አቋም የሚያራምደው ህወሃት፣ ከአሁን በኋላ በወልቃይት ጉዳይ ምንም አይነት ጥያቄ መነሳት የለበትም በማለት ደጋግሞ እያስጠነቀቀ ይገኛል። አንዳንድ የድርጅቱ አባላትና

በአዳማ ከተማ በተፈናቃዮችና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተወሰኑ መጠለያ ቤቶች ተቃጠሉ።

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) ተፈናቃዮቹ ህገወጥነትን እያስፋፉ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይከሳሉ። ተፈናቃዮች በበኩላቸው መንግስት የገባልንን ቃል ያክብር፤ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን ብለዋል። ከሶማሌ ክልል በአብዲ ኢሌ ልዩ ተዕዛዝ ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው በግዳጅ ተፈናቅለው በአዳማ ከተማ በመንግስት በተሰራላቸው መጠለያ ቤቶች ውስጥ ነዋሪ በሆኑት ተፈናቃዮችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። በግጭቱም የተፈናቃዮቹ የተወሰኑ መጠለያ ቤቶች በእሳት መቃጠላቸው ታውቋል። ለግጭቱ መቀስቀስ ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ ጊዜያት የሚፈጽሙት ህገወጥ ዝርፊያና ሥርዓት አልበኝነት መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በአካባቢው ገንደ ጋራ ልዩ ስሙ ዶሮ እርባታ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ነዋሪዎች እንዲሁም በግብርና ሙያ በሚተዳደሩት የቀጨማና አካባቢው አርሶ አደሮች እህል ወደ ገበያ ይዘው በሚመጡት ወቅት ይዘረፋሉ፤ አካላዊ ጥቃቶችም ይደርስባቸዋል። በከተማዋ መውጫ ላይ በድንጋይ መጥረብ ካባና አሸዋ ሥራ ላይ በህጋዊነት የተሰማሩት ሰራተኞችን ጨምሮ አሽከርካሪዎችን በግዳጅ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይጠየቃሉ። ይህን ህገወጥነት በማይቀበሉት ላይም ጥቃት ለማድረስ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው ነዋሪዎቹ በምሬት መናገራቸውን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። በተለይም ፍልሰተኞቹ ነዋሪዎች ላይ የሃይማኖታዊ ግጭት የማስነሳት ስጋት መፍጠራቸው ለትናትናው እረብሻ መቀስቀስ ምክንያት ሆኗል። በከተማዋ ዳርቻ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

በቴፒ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ 4 ሰዎች ተገደሉ

Image may contain: 1 person, sitting and selfie(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010) በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን በቴፒ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ 2 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
ብሄር ተኮር ባሆነው በዚሁ ጥቃት የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል። ነዋሪው ራሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ መጀመሩንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
መኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የደኢህዴን ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በከተማዋ ተገኝተው ሁኔታውን ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱም ታውቋል።
በዘር አትከፋፍሉን በሚል የከተማው ነዋሪ ተቃውሞን እያሰማም ነው ተብሏል።
በሸካ ዞን ዘርን ያተኮረ ጥቃት ሲከሰት የሰሞኑ የመጀመሪያው አይደለም። በየዓመቱ ወቅት እየጠበቀ የሚከሰት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት ምክንይስት ሰበብ የሆነ ችግር ነው።
የዘንድሮው ግን የከፋ ነው ይላሉ ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ እየወጡ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010) በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየዕለቱ ከጅቡቲ በመውጣት ወደ ሀገር ቤት እየገቡ መሆናቸው ተገለጸ።
ፋይል በምስራቅ ኢትዮጵያ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ የሚደርሰውን ጥቃት በመፍራት በርካታ ኢትዮጵያውያን ጅቡቲን ለቀው መውጣታቸውን ቀጥለዋል።
በድሬዳዋ አምስት የጅቡቲ ዜጎች ባለፈው ሳምንት መገደላቸውን ተከትሎ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥቃት እየተፈጸምብን ነው ሲሉ ለኢሳት ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ ተፈናቅለው በምስራቅ ኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል።
በጅቡቲ ከ800ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይገመታል።
አብዛኞቹ በህገወጥ መንገድ የገቡ በመሆኑ ቁጥሩ ከተጠቀሰው በላይ ሊልቅ እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።
በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ የፖለቲካ አለመረጋጋት ሲፈጠር እንደአንድ መሸሸጊያ ሆና ኢትዮጵያውያንን ስታስጠልል ቆይታለች- ጅቡቲ።
ከቀድሞው የህወሀት መንግስት ጋር በነበራት ግንኙነት ጅቡቲ ለኢስትዮጵያውያን የዲሞክራሲና የነጻነት ታጋዮች የምትመች ሀገር አልሆነችም።
ህይወታቸውን ለማትረፍ የተጠጓትን ኢትዮጵያውያን አሳልፋ ስትሰጥ እንደነበር ይታወቃል። ሰሞኑን ደጎም የምስራቅ ኢትዮጵያው አለመረጋጋት በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ለከፍተኛ ጥቃት ማጋለጡ እየተነገረ ነው።

አርበኞች ግንቦት ሰባት አቀባበል ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው

Image may contain: 4 people(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ወደ ሀገር ቤት በሚገባበት ሁኔታ ላይ የአቀባበል ኮሚቴው ዛሬ መግለጫ ሰጠ።
ኮሚቴው ከዛሬ ጀምሮ የአቀባበል መርሃግብሩን የተመለከቱ ስራዎችን በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
ናፍቆት የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአቀባበል ስነስርዓት ላይ ኢትዮጵያውያን በመሳተፍ ለንቅናቄው መሪዎችና አባላት ደማቅ አቀባበል እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ በኩል በእስር የሚገኙና በአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ስም የተከሰሱ 53 ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በአሜሪካ ኢትዮጵያውያን ለማነጋገር በመጡ ጌዜ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችንም ማነጋገራቸው የሚታወስ ነው።
በሁለቱ ወገኖች በተደረሰ ስምምነት መሰረት የንቅናቄ አመራሮች ወደ ሀገር ቤት በመግባት ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ መግለጫ ሰጥተዋል።
በአንድ ወር ውስጥ ዝግጅታችንን አጠናቀን ወደ ሀገር ቤት እንገባለን ያሉት አመራሮች ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብረን ለውጡን ከዳር እናደርሳለን ማለታቸው መዘገቡም ይታወሳል።
ዛሬ በሀገር ቤት የተቋቋመው የንቅናቄውን አመራሮች የሚቀበል አስተባባሪ ኮሚቴ መግለጫ ሰጥቷል።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ተጠየቀ

Image may contain: 1 person, smiling, text(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)የመብት ተሟጋቹ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ጥሪ ቀረበ ።
ለዚህ ታዋቂ አትሌት የጀግና አቀባበል ለማድረግ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝግጅት ማድረጋቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።
በነሃሴ 2008 ዓም በብራዚል ሪዮ ዲጄነሮ በተካሄደው ኦሎምፒክ በማራቶን ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል።
በዚሁ ወቅትም ሩጫውን ሲያጠናቅቅ በኢትዮጲያ የሚካሄዱ ግድያዎችን በአጠቃላይ የመብት ጥሰቶችን በመቃወም እጁን በማነባበር በዓለም ሕዝብ ፊት ባሳየው ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታን ማግኘቱ ይታወሳል።

ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳና ሌሎች የፖሊስ አመራሮች ዋስትና ተፈቀደ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)በመስቀል አደባባይ ሰኔ 16 በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው ታስረው የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮችም ዋስትና ተፈቀደላቸው።
አቃቤ ህግ የፖሊስ አመራሮቹ በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ለፍርድቤቱ ገልጾ ነበር።
የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል።
ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ገብረስላሴ ታፈረ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄና ኮማንደር አንተነህ ዘላለምን ጨምሮ ሌሎች የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው የነበሩ ግለሰቦች ደግሞ ከ6 ሺህ ብር እስከ 9 ሺህ ብር በሚደርስ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ውስኗል።
በዚህም የዋስትና ጉዳይን የሚመለከተው መዝገብ መዘጋቱን ነው ፍርድ ቤቱ ያስታወቀው።

Monday, August 13, 2018

ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቀሉ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) ከጅቡቲ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ።

በአብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ጥቃትን ሸሽተው የተሰደዱ መሆናቸው ታውቋል።

በምዕራብ ሀረርጌ አሰቦት በትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙት የጅቡቲ ተፈናቃዮች ምግብና ውሃ አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሻሸመኔ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንደተናገሩት በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት እጃቸው ያለበትን አካላት በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ሂደቱ ተጀምሯል።

ሁለት የሕወሃት አባላት ከሃላፊነታቸው ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) በአዲስ አበባ መስተዳድር ለረጅም አመታት በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ የነበሩ ሁለት የሕወሃት አባላት ከሃላፊነታቸው ተነሱ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ እንዲሁም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ በመሆን ከ10 አመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆዩት ሁለቱ ግለሰቦች ከስልጣናቸው የተነሱት በሳምንቱ መጨረሻ እንደሆነም ተመልክቷል።

ግሎባል አልያንስ ለደቡብ ክልል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 7/2010) ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (ግሎባል አልያንስ) ለደቡብ ክልል ተፈናቃዮች የግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ  አደረገ።

ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን  ለተፈናቀሉት የጌዲዮ ተወላጆች  እንዲሁም  በሐዋሳና ጉራጌ ዞን በተፈጠረው ግጭት  ለተፈናቀሉት ዜጎች  የተላከው ድጋፍ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አማካይነት  ለተፈናቃዮቹ መድረሱን መረዳት ተችሏል።

አቃቤ ሕግ የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ አልቃወምም አለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 7 /2010) አቃቤ ህግ የሰኔ 16ቱ ቦንብ በፈነዳበት ጊዜ ክፍተት አሳይተዋል በሚል የታሰሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የነበሩትን ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ገለፀ፡፡

Friday, August 10, 2018

ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ

(ኢሳት ዲሲ– ነሃሴ 4 /2010)በሶማሌ ክልል ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመቆጣጠር ወታደራዊ ዕዝ ወይንም ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ።

ከመከላከያ ሃይል ፣ከፌደራል ፖሊስ እና ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የተውጣጣው  ኮማንድ ፖስት በደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም እንደሚመራም ታውቋል።

በኤፈርት ንብረቴን ተነጠኩ ያሉት ባለሃብት የድርሻቸውን ጠየቁ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 4/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት በሆነው ኤፈርት ንብረቴን ተነጠኩ ያሉት ባለሃብት ድርሻቸውን ለማስከበር አቤቱታ አቀረቡ።

የአዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ጠንሳሽና በኋላም የ60 በመቶ ባለድርሻ የነበሩት አቶ ሙሉጌታ ጓዴ ሙሉ በሙሉ ድርሻቸው በሕወሃቱ ኤፈርት በመነጠቃቸው መብታቸውን ለማስከበር በእንግሊዝና በአሜሪካ ፍርድ ቤት ያደረጉትን ጥረት ለኢሳት ገልጸዋል።

የካቢኔ አባላት ሹመት ተሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 4/2010) የአዲስ አበባ ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ሰጠ። ምክር ቤቱ ሹመቱን የሰጠው የካቢኔ አባላትን በመበወዝ መሆኑም ታውቋል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሹመቱ ብቃትንና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ መሰረት ያደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።

Thursday, August 9, 2018

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ያለው የዘር መድልኦ ይበልጥ እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ፡፡

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቅርቡ የኢሳት ቴሌቪዥን “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ አመራሮች ዘንድ የሚሰራውን የተጠናከረ የሙስና አሰራር አጋልጠዋል” በማለት የተጠረጠሩ የሌላ ብሄር ተወላጅ የድርጅቱን ሰራተኞች ከኃላፊነት በማውረድ አሰራሩን ሚስጥራዊ ለማድረግ ይበልጥ እየሰራ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል፡፡ የኢሳት ቴሌቪዥን ዜና ከተሰማ በኋላ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የሚገኙት የፋብሪካው ከፍተኛ አመራሮች ፤ በተለይ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞችን በማንሳት እና ከአመራሩ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኙ “ጥቅም አደር” ሰራተኞችን በመተካት የቆዬ የዝርፊያ ተግባራቸውን

አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ ካቢኔያቸውን ሊያዋቅሩ ነው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነሃሴ 4 ቀን 2010 ዓም አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ አዲስ ካቢኔ ሊዋቅሩ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። 17 በሚሆኑ የቢሮ ሃላፊነት ቦታዎች የካቢኔ አባላት በቀጥታ እንደሚሾሙ ሲጠበቅ፣ ከተማዋን እንደፈለጉ ሲመሩ የነበሩት የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ በደቡብ ክልል የድርጅት ሃላፊው በአቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከስልጣን እንደሚነሱ የተነገራቸው ባለስልጣናት በከፍተኛ ሀዘን ተውጠው መታየታቸውን

በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ በተነሳው ተቃውሞ 5 ሰዎች ተገደሉ ፖሊሶች እርምጃውን የወሰዱት ሰሞኑን የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ነው።

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶች በሰንገጢ ቀበሌ 280 ሄክታር መሬት ይዞ የሚገኘውን ኢንቨስተር መሬት በመውረር < እኛ መሬት አጥተን ለአንድ ግለሰብ ይህን ያክል መሬት ሊሰጥ አይገባም” በማለታቸው ተቃውሞው መቀስቀሱ ታውቋል። በተርጫ ከመንገድ ስራ ድርጅት ጋር በተያያዘ የክልሉ የመገናኛ ብዙሃን ባቀረበው የተሳሳተ ዘገባ ሳቢያ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መውደማቸው ይታወቃል።

የጅግጅጋ ነዋሪዎች በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙና የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት ጥረት ቢጀምሩም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ተናገሩ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ኢሳት በስልክ ያነጋገራቸው የሶማሊ ክልል ተወላጆች በክልላቸው በተፈጠረው ድርጊት በእጅጉ እንዳሳዘናቸውና ድርጊቱም በጥቂት የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የተፈጸመ እንጅ የከተማዋን ነዋሪዎች እንደማይመለከት ገልጸዋል። ጥቃት

የቀብሪዳሃር ስደተኞች ለከፍተኛ ችግር መጋለጠቸውን ገለጹ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) በቀብሪዳህር መከላከያ ሰራዊት ግቢ የተጠለሉ ዜጎች የሰራዊቱ ቀለብ እየተመናመነ በመምጣቱ ለከፍተኛ ችግር መጋለጠቸውን ገለጹ።

ላለፉት ስድስት ቀናት ሰራዊቱ ቀለቡን እያካፈላቸው መቆየቱን ተፈናቅዮች ገልጸዋል። ከ5ሺህ በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ቤት ንብረታቸው ተዘርፏል።

በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበርና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ከደቡብ ክልልና ኦሮሚያ አወሳኝ ቦታዎች በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ አደረጉ።

ቀይ መስቀል በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አዋሳኝ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ መስጠት መጀመሩን አስታወቋል።

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010)የ“ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ” አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ።

15 አባላት ያሉት የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ምክር ቤት መቋቋሙ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይፋ ሆኗል።

ምክር ቤቱ በታዋቂው ምሁር ዶክተር አለማየሁ ገብረማርያም ሊቀመንበርነት የሚመራ ይሆናል።

ሰንደቅ ጋዜጣ ተዘጋ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) በሰንደቅ የህትመትና የማስታወቂያ ድርጅት ላለፉት 14 ዓመት ያህል በየሳምንቱ ረቡዕ እየታተመ የሚወጣው “ሰንደቅ” ጋዜጣ ተዘጋ።

 በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ  በአማርኛ ቋንቋ ታትመው ለገበያ የሚቀርቡ የግል ሳምንታዊ ጋዜጦችም “ሪፖርተር እና “አዲስ አድማስ” ብቻ ሆነዋል፡፡

Tuesday, August 7, 2018

ጂጂጋ በመረጋጋት ላይ ናት ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 1/2010)ጂጂጋ የገባው የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን በማረጋጋት ላይ መሆኑ ተገለጸ።
ላለፉት ሶስት ቀናት በቀውስ ውስጥ የቆየችው ጂጂጋ በአንጻራዊ ሁኔታ መረጋጋት እንደሚታይባት የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ኢሳት ያነጋገራቸውና በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋ።
መከላከያ ሰራዊቱ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን መጠነኛ ለውጥ እያየን ነው ብለዋል።
በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች አሁንም ተደብቀው ያሉ ነዋሪዎች ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።
በድሬዳዋም ዛሬ አንጻራዊ መረጋጋት መስፈኑን ለማወቅ ተችሏል። ትላንት የተገደሉ 5 የጅቡቲ ዜጎችን አስክሬን የጅቡቲ መንግስት መውሰዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ባለፉት ሶስት ቀናት ከ60 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ታውቋል።

ኦነግ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረመ

Image may contain: 6 people, people sitting, table and indoor(ኢሳት ዲሲ—ነሃሴ 1/2010) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረሙ ተገለጸ።
ኦነግ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ለመቀጠል መስማማቱም ተመልክቷል።
ከኦሮሞ ነጻነትግንባር ጋር የሰላም ሥምምነት ለመፈራረም ወደ አስመራ ያቀኑት የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ከፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውም ታውቋል።
ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር መሪዎች ጋር የሰላም ሥምምነት ለመፈራረም ትናንት ወደ ኤርትራ የተጓዙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እና ከሌሎች የኦነግ አመራሮች እንዲሁም ከሰራዊቱ አዛዥ ኮሎኔል ገመቹ አያና ጋር መወያየታቸውም ተመልክቷል።
በውይይቱ በተደረሰብት ሥምምነት መሰረት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ ሃገር ቤት በመግባት ሰላማዊ ትግል የሚቀጥል ሲሆን ፣የተኩስ አቁም ሥምምነትም ተፈርሟል።
ዝርዝር አፈጻጸሙን የሚከታተል የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙም ተመልክቷል።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከአርባ አመታት በፊት የተቋቋመ ሲሆን፣በ 1983 የደርግ ወታደራዊ መንግስት ሲወገድ የሽግግር መንግስቱ መስራች ነበረ።

“ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በየትኛውም መንገድ ተቀባይነት የሌለው የሕዝብ ጠላትነት ተግባር ነው” ሲል ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በከፈሉት መራር መስዋዕትነት ባለፉት አራት ወራት አገራዊ አንድነት እና መግባባት፤ እንዲሁም የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በአንፃራዊነት መከበራቸውን፤ የተጀመረው አበረታች ለውጥም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ያሳተፈ እና ባለቤት ያደረገ ጭምር ነው” ብሎአል። ይህን የለውጥ ጅማሮ ከመደገፍ እና ታሪካዊና አገራዊ አደራ ለመወጣት ከመትጋት ይልቅ በመንግስት ስልጣን እና ኃላፊነት ላይ ያሉ በአገራችን ኢትዮጵያ አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች እንዲቀሰቀሱ በማድረግ በዜጎቻችን ላይ ሰብዓዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በማድረስ ህገወጥ ድርጊቶች እንዲስፋፋ ቀስቃሽ በመሆን ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር የጥፋት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ የደረሰው ጉዳት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በአስቸኳይ ሊገታ የሚገባው ድርጊትና

በተርጫ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው።

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ትናንት የተጀመረው ተቃውሞ በመከለከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብነት ቢበርድም ፣ ዛሬም ከፍተኛ ውጥረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በከተማው ለደረሰው ጥፋት ባለስልጣናቱን ተጠያቄ የደርጋሉ። ችግሩ እንዴት እንደተነሳ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑትን መመህር ፍሰሃ ተስፋዬን አነጋግረናቸዋል።

በጅግጅጋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ከተቆጣጠረ ከትናንት ጀምሮ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ቤቶቻቸው የተዘረፉባቸው እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት የወደሙባቸው ዜጎች በብስጭት ተቃውሞ ለማድረግ ቢያስቡም፣ የአገር ሽማግሌዎች በቀልን በበቀል መመለስ ትክክል አይደለም በማለት እንዳረጋጉዋቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ ከስልጣን የተነሱ ሲሆን ፣ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአብዲ ኢሌ ታጣቂዎችና እርሱ ያደራጃቸው ሰዎች በወሰዱት እርምጃ በሶማሊ ተወላጆች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰድ እንዲቆም፣ የአብዲ ኢሌን አገዛዝ በማጋለጥ እና በመቃወምሲተገል የቆየው አብዱላሂ ሁሴን ጥሪ አቅርቧል። በሌላ በኩል ፕሬዚዳንቱ አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ውለው፣ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት እንደተወሰዱ ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ዘግቧል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በመተካት መሾማቸውን ይሁን እንጅ እርሳቸውም የአብዲ ኢሌ የቅርብ ሰው መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Monday, August 6, 2018

Scores killed in Jijiga, Dire Dawa in an attack by Liyou Police and armed youth

ESAT News (August 6, 2018)
[UPDATE: As we compile this report, the national defense forces and federal police have been given orders to restore calm and protect the public in the Somali region of Ethiopia, as per a statement by the Office of Government Communication Affairs. The Office said the order has been give based on the request by the regional government.]
Non-ethnic Somalis were targeted in an attack by the Somali region Liyou (Special) Police and an armed youth group known as “Hego,” both allied to the regional President Abdi Mohamoud Omar also known as Abdi Illey.
Abdi Illey has been at the centre of the crisis in Ethiopia’s Eastern Somali region, where he maintained power with brute force for the last ten years. Pressure has been mounting over the past few months for him to step aside. Several reports revealed the federal government has been coercing Illey over the weekend to step down which led to his Special police unit and the Hego to target non Somali residents in Jijiga killing about 30.

Ethiopia sends delegation to Asmara to negotiate with Oromo opposition group

News (August 6, 2018)
A delegation led by Ethiopian Foreign Minister Workneh Gebeyehu has arrived in the Eritrean capital Asmara to negotiate with a faction of the Oromo Liberation Front (OLF) led by Dawud Ibsa.The report by the Ethiopian Television says the delegation, which also includes president of the Oromo regional administration, Lemma Megersa, was welcomed at the Asmara International Airport by Eritrean Foreign Minister, Osman Saleh and Presidential Advisor Yemane Gebreab.
The delegation is expected to iron out differences with the OLF faction that is based in Eritrea.

Friday, August 3, 2018

በመቀሌ፣ ዓድዋ፣ አክሱምና አዲግራት አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሾፌሮችን፤ በተለያዩ የስራ ጉዳዮች ከመሃል አገር ለስራ የተሰማሩ ወጣቶችን ካለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ “ሰላዮች ናችሁ” በሚል እያሰሩ እንደሚገኙ ታውቋል

(ኢሳት ሐምሌ 27/2010)በመቀሌ፣ ዓድዋ፣ አክሱምና አዲግራት አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሾፌሮችን፤ በተለያዩ የስራ ጉዳዮች ከመሃል አገር ለስራ የተሰማሩ ወጣቶችን ካለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ “ሰላዮች ናችሁ” በሚል እያሰሩ እንደሚገኙ ታውቋል። ካለምንም ጥፋታቸው ከስራ ገበታቸው፣ ከመንገድ ላይ ታፍነው የተያዙት ዜጎችን አድራሻ የት እንደታሰሩና፤ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ ባለመቻላቸው ቤተሰቦቻቸው ስጋት ላይ ወድቀዋል። ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው

በሶማሌ ክልል ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ ተሰደዱ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) በሶማሌ ልዩ ሃይል የሚፈጸመውን ጥቃት በመሸሽ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ መሰደዳቸው ታወቀ።

ከትላንት ጀምሮ በደወሌ፣ አይሻና ሽንሌ ዞን የተሰማራውና በአብዲ ዒሌ የሚታዘዘው ልዩ ሃይል ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ህዝቡ በመሰደድ መጀመሩ ነው የተገለጸው። በጥቃቱም የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የጭልጋ ወረዳ አመራሮች ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) የመንግስትን መዋቅር በመጠቀም በአማራና ቅማንት ማህበረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱ 7 የጭልጋ ወረዳ አመራሮች መታሰራቸው ታወቀ።

በአማራ ክልል ፖሊስ የተያዙት አመራሮች በህወሀት የሚደገፈውን የቅማንት ኮሚቴ በማገዝ በአካባቢው ግጭት እንዲፈጠር ማድረጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የክብር ተናጋሪ ሆነው እንዲቀርቡ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የክብር ተናጋሪ ሆነው እንዲቀርቡ ተጠየቀ።

በመንግስታቱ ድርጅት የስዊዲን አምባሳደር ኦሎፍ እስኩግ በጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም መፍጠር የቻሉ መሪ በመሆናቸው በምክር ቤቱ የክብር ተናጋሪ እንዲሆን መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ተስፋ የቆረጥንበትን የሁለቱን ሀገራት ፍጥጫ በአጭር ጊዜ መፍትሄ የሰጡ መሪ በማለትም አምባሳደሩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ተስፋዬ ጌታቸውን ቤተሰቦች ለመደገፍ የ25 ሚሊየን ብር ስጦታ ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈውን የብአዴን አመራር አቶ ተስፋዬ ጌታቸውን ቤተሰቦች ለመደገፍ ባለሃብቶች የ25 ሚሊየን ብር ስጦታ ማድረጋቸው ታወቀ።

አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ በብአዴን በኩል ካሉ ግንባር ቀደሞች አንዱ መሆናቸውም ተመልክቷል።

Thursday, August 2, 2018

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ።(ወ/ሮ ሃይማኖት አበራ ተገኘ እባላለሁ፣የረዳት አብራሪ ኃይለ መድህን አበራ ታላቅ እህት)

Image may contain: 1 person, hat and closeupከሁሉ አስቀድሜ የአክብሮት ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡
ወ/ሮ ሃይማኖት አበራ ተገኘ እባላለሁ፣የረዳት አብራሪ ኃይለ መድህን አበራ ታላቅ እህት ስሆን የምኖረው ጀርመን ነው።
ዛሬ ለእርስዎ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ የታወጀው የምህረት አዋጅ ያሳደረብኝ ተስፋ ነው።
እንደሚያውቁት ወንድሜ ከየካቲት 2006 ጀምሮ በስዊትዘርላንድ አገር በእስርቤት እና በስደት እየተንገላታ ይገኛል። ወደ አገሩ እንዳይመለስ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድቤት የ 19 አመት ከ6 ወር እስር ፈርዶበታል።
ጉዳዩን በተመለከተ የተሟላ መረጃ እንደሚኖርዎት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአጭሩ ለመግለጽ ያህል፡ የስዊትዘርላንድ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የባለሙያ ሪፖርት መሠረት በማድረግ በወንጀል ተጠያቂ እንዳይሆን፣ ሆኖም በሕግ ጥበቃ ስር ሕክምና እንዲከታተል ወስኖበት ውሳኔውም ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ በጄኔቫ ከተማ አካባቢ በጥበቃ ስር ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለኝ መረጃ መሠረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ባይኖር ኖሮ የኢትዮጵያ መንግሥት የስዊትዘርላንዱን ፍርድ ቤት ውሳኔ በአገራችን ተፈጻሚ ለማድረግ ተስማምቶ ኃይለመድህንን ወደሚወዳት አገሩ እንዲመለስና ከናፈቁት የቤተሰቡ አባላት በተለይም ከአረጋውያን እናትና አባቱ ጋር እንዲገናኝ ማድረግ ይችል ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡

በደቡብ ክልል በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) በደቡብ ክልል የም ወረዳ በተፈጠረ ግጭት በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነገረ።
በወረዳው ዋና ከተማ ሳጃ ግጭቱ የተከሰተው የመልካም አስተዳደር ችግር በመነሳቱ ነው ተብሏል። በእምነት ሰበብም በርካታ ሰዎች ሲገደሉ ቤቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ የሚወስደው መንገድ በግጭት ምክንያት ተዘግቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
በደቡብ ክልል የም ወረዳ ሳጃ ከተማ ከሐምሌ 4 ጀምሮ ሰላም ርቋት መሰንበቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በተለይ ደግሞ ሰሞኑን ግጭቱ ተባብሶ በርካታ ሰዎች ሲገደሉ ንብረትም ወድሟል።–ቤቶች ተቃጥለዋል።

በቤንሻንጉል 108 ሲቪሎች እና ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 26/2010) በቤንሻንጉል ክልል ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ 108 ሲቪሎች እና ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ ።
የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን ዛሬ አዋሳ ላይ እንደተናገሩት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 20 ፖሊሶች እና 88 ሲቪሎች ታስረዋል።
ግጭቱን የፈጠሩት ለውጡን ያልተቀበሉ እና ሥልጣን የሚፈልጉ ናቸው ብለዋል።
ባለፈው ሰኔ የቤንሻንጉል ክልል ዋና ከተማ በሆነችው አሶሳ በተከሰተው ግጭት 14 ያህል ሰዎች ሲገደሉ ፣ወደ 70 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
ለግጭቱ መቀስቀስና መባባስ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የጸጥታ ባለስልጣናት ወዲያወኑ መታሰራቸውም ይታወሳል።
የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን በወቅቱ በሰጡት መግለጫ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ከሥራ እና ሥልጣናቸው ሲታገዱ ፣የክልሉ ልዩ ሃይል ፖሊስ ሃላፊዎችም ከስልጣናቸው መነሳታቸውን አስታውቀው ነበር።

Police say hundreds of munitions intercepted

Police in the restive Benishangul Gumuz regional state in Western Ethiopia say they have intercepted about 500 ammos for kalashnikov rifles in a public bus travelling from Goba to Asossa.
Inspector with the regional police told reporters that the ammunitions were stashed in two bags. Mohammed Ahmed said police acted swiftly following a tip from the public and the suspect is apprehended. He also said 37 illegal weapons were caught in the last three months.
Fourteen people were killed and about 70 others were wounded last month in ethnic motivated attack in the region. The regional council announced today that 108 people, including police officers, who allegedly instigated or took part in the communal violence have been arrested. Twenty of those arrested were police officers. Over fifty officials were also arrested last month in connection with the violence.
There has been an increase in the illegal movement of weapons and various mmunitions over the past few month with authorities making several arrests.
Last month authorities in North Shewa have seized several guns while being transported from the capital Addis Ababa to Northern Ethiopia.
Fifty-three Russian made Makarov pistols guns were found hidden in Isuzu truck after a tip-off from the community led to a search.

የፍቃዱ ተክለማርያም የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

Image may contain: 3 people(ኢሳት ዲሲ--ሐምሌ 26/2010) የአንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ፍቃዱ ተክለማርያም የቀብር ስነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ።
ከቀብር ስነ ስርዓቱ ቀደም ብሎ በብሔራዊ ትያትር ቤት በርካታ አድናቂዎቹና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት አስከሬኑ አሰኛኘት ተድርጎለታል።
የአንጋፋው ከያኒ ፍቃዱ ተክለማሪያም የቀብር ስነ ስርዓት አጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አድናቂቆቹ እና የጥበብ ሰዎች በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ከመንግስት ባለስልጣናት መካከልም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በቀብር ስነስርአቱ ላይ ተገኝተዋል።
አርቲስት ፈቃዱ በህይወት ዘመኑ ያበረከታቸው በርካታ ስራዎቹና የህይወት ታሪኩ በቀብር ስነ ስርዓቱ ወቅት መነበቡንም ከወጡት መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልዩነታቸውን አስወግደው በጋራ ለመስራት ተስማሙ

Image may contain: 11 people, people smiling, indoor(ኢሳት ዲሲ--ሐምሌ 26/2010) በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሱ አራት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልዩነታቸውን አስወግደው በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
ሂጅራ ፋውንዴሽን፣ በድር ኢትዮጵያ፡ ሰላም ፋውንዴሽንና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊ ህብረት በመካከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባትና ልዩነት በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ አንድነታቸውን የሚያረጋግጡ ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል።
አራቱን የኢትዮጵያ ሙስሊም ተቋማትን በመሽምገል ከስምምነት እንዲደርሱ ያደረጉት ከሀገር ቤት የመጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መሆናቸውም ታውቋል።
ትላንት እዚህ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አራቱን የኢትዮጵያ ሙስሊም ድርጅቶችን ወደ ስምምነት እንዲመጡ የሸመገሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ናቸው።
ሰብሳቢው ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ ኡስታዝ ኢንጅነር በድሩ ሁሴንና ኡስታዝ ነቢዩ አያሌው የስምምነት ውይይቱን በመምራት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የአንጋፋው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ቀብር ስነስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ 1948 ዓ.ም የተወለደው አንጋፋው የመድረክ ፈርጥ ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ባጋጠመው የኩላሊት ህመም በተወለደ በ62 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ላለፍት 42 ዓመታት የመድረክ ንጉስ እንደነበር በሙያ ባልደረቦቹና በጥበብ አድናቂዎች የተመሰከረለት ፍቃዱ ተክለማሪያም ኦቴሎ፣ ኤዲፐስ ንጉሥ፣ ሐምሌት፣ ቴዎድሮስ፣ ንጉሥ አርማህ፣ መቃብር ቆፋሪውና የሬሣ ሳጥን ሻጩ፣ የሠርጉ ዋዜማ፣ ባለ ካባና ባለ ዳባ፣ መልዕክተ ወዛደር የመሳሰሉት ወጥና ትርጉም ተውኔቶች ከተሳተፈባቸው ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ። ከተውኔናትና ቴያትር በተጨማሪም በሬድዮ የመጽሐፍት ዓለም ትረካ፣ በቲቪና በሬድዮ ተከታታይ ድራማዎችን ጨምሮ፤ በወጥ የአማርኛ ፊልሞች ላይ ተዋናይ በመሆንም አገልግሏል። ፍቃዱ ህክምናውን ባህር ማዶ ሄዶ እንዲታከም ለማስቻል በተዘጋጀው የገቢ በማሰባሰብ ስነስርዓት ላይ ያገኘውን 200 ሽህ ብር ገንዘብ ለኩላሊት ታማሚ ታዳጊ ልጅ በመስጠት ቅንነቱንና ለጋስነቱንም አስመስክሯል። አንጋፋው የጥበብ ሰው ፍቃዱ ተክለማሪያም ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹና የሙያ አድናቂዎቹ በተገኙበት የቀብር ስነስርዓቱ ተፈፅሟል። የዝግጅት ክፍላችን ለመላው ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

የአብዲ ኢሌን አገዛዝ የሚቃወሙ የክልሉ ተወላጆች ሁለተኛ ስብሰባዎችን በድሬዳዋ ከተማ ላይ በማካሄድ ላይ ናቸው።

(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)የአብዲ ኢሌን አገዛዝ የሚቃወሙ የክልሉ ተወላጆች ሁለተኛ ስብሰባዎችን በድሬዳዋ ከተማ ላይ በማካሄድ ላይ ናቸው። የክልሉ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ባለፈው አዲስ አበባ ላይ ተደርጎ የነበረው የመጀመሪያው ስብሰባ በአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የተደናቀፈ ቢሆንም፣ ዛሬ የተጀመረው የድሬዳዋው ስብሰባ ግን እስካሁን በሰላም እየተካሄደ ነው። የስብሰባው አስተባባሪዎች እንደሚሉት፣ ሶስተኛውን ስብሰባ ጅግጀጋ ላይ ለማድረግ እቅድ አላቸው። አስተባባሪዎቹ ከዚህ በሁዋላ ምንም የሚፈሩት ነገር እንደሌለና አብዲ ኢሌ ስልጣን እስኪለቅ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)ነዋሪነቱ አራዳ በመባል በሚታወቀው የደሴ ከተማ ኗሪ የሆነውን ወጣት ባዬን ለመያዝ ፖሊስ የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክር ሁኔታውን በቅጡ ባልተረዱ የአካባቢው ነዋሪዎችና በፀጥታ አስከባሪዎች መሃከል ግጭት ተቀሰቀሰ። ተጠርጣሪውን ይዘው የአዲስ አበባ ታርጋ ባላት ሲቪል መኪና ሲጓዙ በነበሩት ፖሊሶች ላይ በከተማው መውጫ ኬላ አቅራቢያ ወጣቶች ግርግር በመፍጠር የተሽከርካሪዋን መስታወት በመስበር ግለሰቡን አስመልጠዋል። የፀጥታ አስከባሪዎቹ ጉዳት ሳይደርስባቸው ማምለጣቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል። ወጣት ታዬ የተሰረቁ ንብረቶችን ገዝቶ በመሸጥ የሚታወቅና ከዚህ በፊትም በፖሊስ እንዲያዝ የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጥቶበታል። በመኖርያ ቤቱም የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪዎች ቲቪ፣ ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የተለያዩ ሁለት አይሱዙ ንብረቶችን መያዛቸው ይታወቃል። ህብረተሰቡ ከዚህ ቀደም በደህንነት አካላት ታፍነው ከሚወስዱ ግለሰባች ጋር በማመሳሰል ለወንጀለኞች ከለላ እንዳይሰጥ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል ሲሉ የከተማ ነዋሪዎች አሳስበዋል። ግርግሩን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የሚወጡና የሚገቡ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴዎች ለሰዓታት ለመቆም ተገደዋል። ተጠርጣሪውን ለመያዝ በፖሊስና በነዋሪዎቹ መሃከል ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ውጥረት መኖሩን ምንጫቻችን አስታውቀዋል።

Wednesday, August 1, 2018

ከግንቦት 7 አመራሮች ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት መደረጉ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010) ከግንቦት 7 አመራሮች ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ።
አመራሮቹም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በሃገራቸው ጉዳይ ላይ በንቃት እንደሚሳተፉም አመልክተዋል።
አክቲቪስት ታማኝ በየነ እንዲሁም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ጅዋር መሃመድ ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱም ዶክተር አብይ አህመድ ገልጸዋል።
ለሳምንት ያህል በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ከኢትዮጵያውያን ጋር ሲወያዩ የቆዩትና ዛሬ አዲስ አበባ የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰጡት መግለጫ ቆይታቸው የተሳካና ውጤታማ እንደነበርም አመልክተዋል።
በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መኩራታቸውንና ይበልጥ ሃላፊነት እንዲሰማቸው እንዳደረግዋቸውም ገልጸዋል።

ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ አዲስ አበባ ገቡ

Image may contain: 2 people(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010) ብጹእ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ከሩብ ክፍለ ዘመን ስደት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። 
ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽም ከፍተኛ አቀባበል እንደተዘጋጀላቸውም ታውቋል።
ከሩብ ክፍለ ዘመን ስደት በኋላ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስን የያዘው አይሮፕላን ዛሬ ከቀትር በኋላ 8 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎለታል።
6ኛው ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እንዲሁም የልዩ ልዩ ሃይማኖቶች መሪዎች በአቀባበል ስነስርአቱ ላይ ተገኝተዋል።
ቀሳውስትና ዘማርያን የአቀባበል ስነስርአቱን ባስዋቡበት በዚህ ትዕይንት የፖሊስና የመከላከያ የእግረኛ ሙዚቃ ቡድን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተገኝተው የአቀባበል ስነስርአቱን በሃገራዊ ሙዚቃ አድምቀዋል።

የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርን የማካለሉ ስራ እንዲጀመር ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010) በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ ያለውን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ለመፍታት የድንበር ማካለሉ በአስቸኳይ እንዲጀመር ሱዳን ጠየቀች።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤል ድሬድሪ ሞሐመድ እንደገለጹት በእርሻ ቦታ ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት የሚፈጠረውን የድንበር ግጭት ለመፍታት አስቸኳይ የማካለል ስራ መጀመር ይኖርበታል።
በሱዳን ወታደሮችና በኢትዮጵያ ገበሬዎች መካከል በተደጋጋሚ በሚከሰተው ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤል ድሬድሪ ሞሐመድ በካርቱም ከኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር ውይይት አድርገዋል።
የውይይታቸው መነሻም በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ ነው ተብሏል።
እናም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የድንበር ማካለል ጉዳይ በአስቸኳይ መጀመር አለበት ነው ያሉት።

የኪነጥበብ ባለሙያው ፍቃዱ ተክለማርያም አረፈ

Image may contain: 2 people, people smiling(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 25/2010)አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ፍቃዱ ተክለማርያም ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
በገጠመው የኩላሊት ሕመም በ62 አመቱ ሕይወቱ ያለፈው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በሙያው ከፍተኛ አድናቆትና አክብሮት ያገኘ የመድረክ ፈርጥ ነበር።
ትላንት ማክሰኞ ሐምሌ 24/2010 ከዚህ አለም በሞት የተለየው የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም አስከሬን ዛሬ ከቀትር በኋላ ከነበረበት የጸበል ቦታ አዲስ አበባ ገብቷል።
በ1948 አመተ ምህረት በአዲስ አበባ ከተማ የተወልደው የኪነጥበብ ባለሙያው ፍቃዱ ተክለማርያም ላለፉት 42 አመታት በኪነጥበቡ መስክ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረገ ባለሙያ መሆኑ ይታወሳል።