Friday, September 30, 2016

በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች የንግድ ቤቶች መታሸጋቸው ተቃውሞ አስነሳ

ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009)
በቅርቡ በጎንደርና ባህር ዳር ከተሞች በስራ ማቆም አድማ ተሳትፋችኋል የተባሉ የንግድ ድርጅቶችን ለማሸግ በንግድ ቢሮ እየተካሄደ ያለው የማሸግ ዕርምጃ ነዋሪዎችን ማስቆጣቱ ታወቀ። 
በተለይ ከአንድ ሳምንት በፊት ለሶስተኛ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ በቆየችው የጎንደር ከተማ በርካታ ሱቆች እየታሸጉ መሆናቸውን እማኞች ማስረጃዎችን በማስደገፍ ለኢሳት አስረድተዋል። 
ይሁንና የከተማው የንግድ ቢሮ የንግድ ድርጅቶቹን ለማሸግ እየወሰደ ያለው እርምጃ በነዋሪዎች ዘንድ ቁጣን እንደቀሰቀሰ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ እማኞች ገልጸዋል። 
ሆቴሎችና ሻይ ቤቱን በዚሁ የማሸግ እርምጃ ዋነኛ ኢላማ መሆናቸውን የተናገሩት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ድርጊቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ ተጨማሪ ህዝባዊ ተቃወሞ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ለኢሳት መረጃን ያደረሱ አካላት አስታውቀዋል። 

በቤኒሻንጉል ጊዛን ወደ 300 የሚጠጉ ነዋሪዎች ለደህንነታቸው ሲሉ ጫካ መግባታቸው ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጊዛን ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት እልባት አለማግኘቱን ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ ነዋሪዎች ለደህንነታቸው ሲሉ ጫካ መግባታቸውን እማኞች አርብ ለኢሳት ገለጡ። 
በነዋሪዎችና ከትግራይ ክልል መጥተው ሰፍረዋል በተባሉ 1ሺ አካባቢ ሰዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በትንሹ ስምንት ከሚሆኑ የመንግስት የጸጥታ አባላት ግድያ ምክንያት መሆኑን ሃሙስ መዘገባችን ይታወሳል። 
ድርጊቱ እልባት ሳያገኝ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን የተናገሩት የሸርቆሌ ከተማ አካባቢ ነዋሪዎች ግጭቱን ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ ነዋሪዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ወደ ጫካ መሰደዳቸውን አስረድተዋል። 

ፖሊስ የተመድ ሰራተኞች የእሬቻን በዓልን ለመከታተል ወደ ቢሾፍቱ እንዳይጓዙ አሳሰበ

ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009)
የፊታችን ዕሁድ በደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ የሚከበረውን የእሬቻ በዓል አከባባር ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት የደህንነትና የጸጥታ መምሪያ ሰራተኞች ወደ ከተማዋ እንዳይጓዙ አሳሰበ። 
መምሪያው ለሰራተኞቹ ባሰራጨው ማሳሰቢያ ተለይቶ የታወቀ የደህንነት ስጋት ባይኖርም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ቅዳሜ እኩለ ቀን ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የግል ጉዞን ጨምሮ ከማንኛውም እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ጠይቋል። 
በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ መሰንበታቸውን ያወሳው የተመድ የጸጥታና የደህንነት መምሪያ፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ራሳቸውን ከማንኛውም ህዝባዊ ስብሰባዎች እንዲያርቁ አክሎ አሳስቧል። 
በክልሉ ለወራት የዘለቀውን ተቃውሞ ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና ኤምባሲዎች ሰራተኞቻቸው ወደ አካባቢው በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ እርምጃን እንዲወስዱ ሲያሳስቡ መቆየታቸው ይታወሳል።

በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እየተደረገ ነው

ኢሳት (መስከረም 20 ፥ 2009)
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ በስቲያ እሁድ በበሾፍቱ ከተማ ለሚከበረው የእሬቻ በዓል ልዩ ሃይል ተመድቦ የጸጥታ ቁጥጥር በመደረግ ላይ መሆኑን አርብ አስታወቀ። 
የከተማዋ ነዋሪዎች የፌዴራልና የክልል የጸጥታ አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ በመሰማራት ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ፍተሻ በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ረቡዕ ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል። 
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አርብ ባወጣው መግለጫ በከተማ የበዓሉ አከባበር በሰላም እንዲስተናገድ ለማድረግ ታስቦ ልዩ ሃይል መመደቡንና ከነዋሪዎች ጋር በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር መካሄዱን አመልክቷል። 

Tensions remain high in Benishangul

ESAT News (September 30, 2016)
At least 300 people have taken refuge in a jungle in Benishangul Giumuz region in western Ethiopia following clashes with regime’s army officials, who settled in the region to carry out gold exploration.
Eight security forces have reportedly been killed on Wednesday following clashes with the local people in an area known as Sherkolle.

Security tightens ahead of Ireecha celebrations on Sunday

ESAT News (September 30, 2016)
There is huge presence of federal and regional security forces in and around Debre Zeit, a.k.a Bishoftu, 25 miles from the capital Addis Ababa, ahead of Ireecha celebrations on Sunday. Ireecha is an important annual celebration by the people of Oromo, the largest ethnic group in Ethiopia.
The United Nations Department of Safety and Security (UNDSS) office in Addis Ababa meanwhile advised its staff to stay away from large gatherings and to avoid Debre Zeit this weekend.
Vehicles and passengers entering the town are being searched and the administration of the town has informed local media that there was a boost up in security in and around Debre Zeit.

Thursday, September 29, 2016

ተጨማሪ መረጃዎች ስለ “ደህንነቱ|” መሥሪያ ቤት [ታደሰ ብሩ]

“ስለ ‘ደህንነቱ’ መሥሪያ ቤት ከማውቀው በጥቂቱ” በሚለው አጭር መጣጥፍ ላይ በርከት ያሉ የውስጥ መልዕክቶች ደርሰውኛል። በበጎም ይሁን በክፉ የፃፋችሁልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ፤ በግልም አመሰግኛቸዋለሁ።
ከተላኩልኝ አስተያየቶች በተለይ አንዱ ትኩረቴን ስቦታል። በውስጡ ተረብ ያለበት ሆኖ “የፃፍከው በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ነው፤ ‘ከማውቀው በጥቂቱ’ አልክ እንጂ ከአጠቃላይ ጉዳዮች ያለፈ የምታውቀው ዝርዝር ነገር የለም፤ ቢኖርህ ኖሮ ለነገ የምታቆይበት ምክንያት አይኖርህም ነበር፤ ቢያንስ ደጋፊዎችህን ለማስጠንቀቅ ሁለት ሶስት ስሞችን ትጠራ ነበር” የሚል ነው የመልዕክቱ ይዘት ነበር። አስተያየት ሰጪው እልህ ውስጥ ሊያስገናኝ የፈለገ ይመስላል። እኔ በቀላሉ እልህ ውስጥ የምገባ ሰው አይደለሁም፤ ሆኖም ቆም ብዬ እንዳስብበት አደረገኝ።
ስለ ህወሓት መሥሪያ ቤት ተጨማሪ ነገሮችን መናገር ህወሓትን ለማሸነፍና በምትኩ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈባት አገር ለመመሥረት ለምናደርገው ትግል ምን ያህል ይጠቅማል? ተጨማሪ ነገር ብጽፍ በዚህ እኩይ መሥሪያ ቤት ያሉ ቅን ሰዎችን ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል? የሚለውን እንዳስብበት አደረኝ። በእኔ ስሌት ከጉዳቱ ጥቅሞ በልጦ ስላገኘሁት እነሆ ተጨማሪ ነገሮች ማለት ፈለግሁ።

Ethiopia: The Myth of a Stable and Reliable Partner Under the Minority TPLF Regime [By Neamin Zeleke]

“I want the superiority of one ethnic group to end” – Ethiopia’s Olympic Silver medalist Feyisa Lilesa on Al Jazeera
“Those who make peaceful revolution impossible will make violent revolution inevitable.” – John F. KennedyNeamin Zeleke -- Satenaw

In the first installment ofthis series, the myth of a strong military under the TPLF/EPRDF regime was examined. This sequel article discusses the manifold policies and measures taken by the ruling TPLF/EPRDF’s and their consequences for peace and stability in Ethiopia and the sub region.
A myth promoting the minority TPLF regime as a reliable and stable partner in the Horn of Africa has been circulating for years among Western policy makers, think tank analysts and academics, especially in the US, UK, and other western countries. This should not come as a surprise: since 9/11, the primary preoccupation of western foreign and security policymakers has been fighting global terrorism.

በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) የሚከበረውን የእሬቻ በዓልን አስመልክቶ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት መሰማራቱ ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2008)

የፊታችን ዕሁድ በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ ለሚከበረው አመታዊው የእሬቻ በዓል አከባባር በሚል ቁጥር ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል የክልል የጸጥታ ሃሎች በከተማዋ መሰማራታቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
የበዓሉ አከባበር ዝግጅትን ተከትሎ ወደ ከተማ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ፍተሻ በመደረግ ላይ መሆኑም ታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል ከወራት በፊት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ ዙሪያዋ ባሉ የገጠር ወረዳዎች ህዝባዊ ትዕይንቶች ሲካሄዱ የንበረ ሲሆን፣ በእሬቻ በዓል አከባበር ወቅትም ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ባለመኖሩ የጸጥታ ቁጥጥር በመደረግ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተቀሰቀሰ ግጭት 8 የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2008)

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰርቀሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በነዋሪዎችና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 8 የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉት በስፍራው ወርቅ ለማውጣት በሚል በቅርቡ ከ1ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች መስፈራቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ አለመግባባት መሆኑ ተነግሯል። በዚሁ ግጭት ከተገደሉት የጸጥታ ሃይሎች በተጨማሪ ከ20-30 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል።

ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ተሰጣቸው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2008)

ከ30 የሚበልጡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሃሙስ የሌተናል፣ የሜጀርና፣ የብርጋዴር ጀነራልነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው መንግስት አስታወቀ።
በሃገሪቱ ፕሬዜዳንት ሙላቱ ተሾመ የማዕረግ እድገት ተሰጥቷቸዋል ከተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች መካከል የሜጀር ጄነራልነት ማዕረግ የነበራቸው ገብራት አየለ ቢጫ በብቸኝነት የሌተናል ጀኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።
በብርጋዴር ጀነራልነት ሲያገለግሉ ነበር የተባሉ 12 ወታደራዊ መኮንኖች ደግሞ የሜጀር ጀኔራልነት ሹመትን ያገኙ ሲሆን፣ 25 ኮሎኔሎች እንዲሁ የብርጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።

በቃሊቲ በሚገኙ እስረኞች ላይ የሚደረገው ጫና መቀጠሉ ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2008)

በቃሊቲ ወህኒ ቤት በሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚፈደረገው ጫና እና ማሰቃየት መቀጠሉ ታወቀ። የ18 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት ላለፉት 5 አመታት በዚህ ወህኒ ቤት በሚገኘው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉን እንዲሁም የማበሳጨት ዕርምጃዎች መጨመራቸውን መረዳት ተችሏል።
በቅድሚያ የጻፋቸውን ማስታወሻዎች፣ በኋላም ማናቸውንም የጽህፈት መሳሪያና ባዶ ወረቀቶች ጭምር የነጠቁት የእስር ቤቱ አዛዦች የተለያዩ ቁሳቁሶች እንዳወደሙበትም በቅርቡ ከእስር ቤት የወጣ ግለሰብ ለኢሳት አብራርቷል።

Wednesday, September 28, 2016

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የዋስትና መብት ጥያቄ በፖሊስ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)

ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ማክሰኞ ፍርድ ቤት መቅረባቸውንና ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ በፖሊስ ተቃውሞ እንደቀረበበት እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
በኮሚቴ አባሉ ላይ ምርመራን እያካሄደ መሆኑን ለችሎት ያስታወቀው ፖሊስ፣ ኮሎኔል ደመቀን በሽብርተኛ ወንጀል ድርጊት የሚጠረጥራቸው በመሆኑ ያቀረቡት የዋስትና መብት ተቀባይነት እንዳያገኝ ተቃውሞ አቅርቧል።

በወልቃይት አዲ-ረመጽ በሚገኝ ሆቴል አማርኛ ዘፈን መከፈቱን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች ዕርምጃ በመውሰዳቸው ውጥረት ቀሰቀሰ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)

በወልቃይት አዲ-ረመጽ ከተማ የሚገኘ አንድ ሆቴል የአማርኛ ዘፈን በመከፈሩ የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት የሃይል ዕርምጃ በነዋሪዎች ዘንድ አዲስ ውጥረት መቀስቀሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ረቡዕ ለኢሳት አስታወቁ።
የትግራይ ክልል ልዩ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት በዚህ ዕርምጃ የሆቴሉ ባለቤት ልጅ ክፉኛ የድብደባ ድርጊት እንደተፈጸመበትና የከተማዋ ነዋሪዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ተቃውሞ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን እማኞች ገልጸዋል።
በአዲ-ረመጽ ከተማ የተቀሰቀሰውን ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎ ነዋሪዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በመሰባሰብ ስራ እንዲስተጓጎል አድርገው መዋላቸውንም እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።

የጅምላ እስርና ግድያ እየፈጸሙ ያሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግድያና ጅምላ እስር እየፈጸሙ ያሉ ባለስልጣናት ሆነ የጸጥታ ሃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ጠየቀ።
አለም አቀፍ ህብረት ለኢሳት በላከው መግለጫ ህዝብን ማገልገል የሚገባው መንግስት ዜጋውን እየጨፈጨፈ መቀጠል ስለለለበት ስልጣንን መልቀቅ ይኖርበታል ብሏል።

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ነጻነት ከሌለባቸው አገራት አንዷ ናት ሲል አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት የሌለባቸው ሃገራት ተብለው ከተፈረጁ የአለማችን ሃገራት መካከል አንዷ ሆና መገኘቷን አንድ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋም ይፋ አደረገ።
ከ90 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ሃገሪቱ ላለፉት 10 አመታት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን አስመዝግባለች ተብላ ቢነገርላትም፣ ኢኮኖሚያዋ በአብዛኛው ነጻ ያልሆነ ሆኖ በጥናት መገኘቱ በ186 ሃገራት ላይ ያካሄደውን የጥናት ግኝት በህዝብ ያቀረበው ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን የተሰኘ ተቋም አስታውቋል።
በነፍስ ወከፍ 250 ካሬ እየተሰጣቸው ለዘመናት ከኖሩበት የእርሻ ቦታ እንዲነሱ የተጠየቁ አርሶ አደሮች የቀረበላቸው ተለዋጭ ቦታ ለኑሮ ምቹ አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ተለዋጭ ቦታው ለልማትም ሆነ ለማህበራዊ ህይወታቸው አመቺ አለመሆኑን በመግለፅ ላይ ያሉት አርሶ አደሮች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊሰጣቸው ባሰበው ምትክ ቦታና ካሳ ላይ ማስተካከያን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ለቻይና ኩባንያ ልማት ለተነሱ አርሶ አደሮች ሊሰጥ የታቀደው መሬት ለኑሮ ምቹ አይደለም ተባለ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)

የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአንድ የቻይና ኩባንያ ለልማት ሊሰጥ ካሰበው ቦታ ላይ እንዲነሱ ጥያቄ የቀረበላቸው በርካታ አርሶ አደሮች ሊሰጣቸው የታቀደው ተለዋጭ ቦታ ለኑሮ ምቹ አይደለም በማለት ተቃውሞን አቀረቡ።
የከተማዋ አስተዳደር ሁአጂየን ለተሰኘው ኩባንያ በተለይም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለቆዳ ኢንዱስትሪ ፓርት ግንባታ 164 ሄክታር መሬት ባለፈው አመት ማስረከቡ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ላለፉት 10 አመታት ያህል ጊዜ በአማካኝ አስር በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተመዝግቧል ቢባልም፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ ሁሉንም የሃገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች ተጠቃሚ አላደረገም ሲል ድርጅቱ በሪፖርቱ አስፍሯል።

Gondar uprising leader charged with terrorism

Image may contain: 1 person
ESAT News (September 28, 2016)
The leader of the the movement in the Amhara region that is campaigning to restore areas forcefully annexed to Tigray by the Tigrian-led regime has been charged with terrorism.
Colonel Demeke Zewdu, seen by many Ethiopians as the leader of the ongoing uprising against a minority regime in Amhara region, was charged Wednesday after several court adjournments.

Thursday, September 22, 2016

እኛ ሰፈር ነው አሉ… አንድ ቀን ሌባ ተያዘ… [አቤ ቶኮቻው]

gonder-2ከዛ የሰፈሩ ሰው ሁሉ ሌባ ሌባ ሌባ እያለ የአካባቢው ሰው አጅቦት ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየሄደ ሳለ በመንገዱ ርዝመት የተዳከሙት የአካባቢው ሰዎች ግማሹ ወደ ኋላ ሲቀር ግማሹ ድምጹ ሲቀንስ ግዜ ሌባው ሆዬ አልሄድም አለ። ፖሊሱም ፈጠጥ ብሎ ምን ሆነህ ነው… ሂድ እንጂ… ቢለው ይሙቅልኝ! ጭብጫቦው ሌባ ሌባ የሚለው ድምጽ ቀዝቅዟል…. አንሷል…. ብሎ ግግም አለ አሉ… የሌባ አይነ ደረቅ አሙቁልኝ ይላል ማለት ይሄኔ ነው… ሃሃ( የዚህ ታሪክ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ካለ መውሰድ ይችላል… )
በጎንደር ከተማ አንዲት ሴት ከተማውን እሳት ልትለኩስ ስትል፤ በቁጥጥር ስር ውላ በፖሊስ እና ህዝብ አጀብ ታጅባ ”እሰይ ሞቅ አለለኝ” በሚል ኩራት ታጅባ ስትሄድ አይተናታል።

በባህርዳርና ጎንደር ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ

ኢሳት (መስከረም 12 ፥ 2009)
በባህርዳርና ጎንደር ከተሞች በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ሃሙስ ለአራተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። 
የከተማዋ ነዋሪዎች በመንግስት የጸጥታ ህያሎች ይፈጸማል ያሉትን ግድያና የጅምላ እስር በማውገዝ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ መጀመሪቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸው ህዝባዊ ተቃውሞ በሁለቱ ከተሞች መቀጠሉን ለመረዳት ተችሏል። 
የመንግስት ባለስልጣናት የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ስራቸውን እንዲጀምሩ በማስገደድ ላይ ቢሆኑም የንግድ ባለቤቶቹ ስራ ላለመጀመር መወሰናቸው ታውቋል። 
ይሁንና በጎንደር ከተማ የኢሳት ቃጠሎ ለማድረስ እየተደረገ ያለው ሙከራ በነዋሪዎች ዘንድ ተጨማሪ ቁጣን እየቀሰቀሰ እንደሚከገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በከተማዋ የእሳት ቃጠሎን ለማድረስ ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩትና በቁጥጥር ስር የዋሉት አምስቱ ግለሰቦች ድርጊቱን ለመፈጸም የሚረዳ ቤንዚን እና ተቀጣጣይ ነገሮችን ይዘው እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን እማኞች ለኢሳት አስረድተዋል። 

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተመድ ጉባዔ ላይ የማህበራዊ ድረገጾች በሃገሪቱ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ

ኢሳት (መስከረም 12 ፥ 2009)
በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የማህበራዊ ድረገጾች በሃገሪቱ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ። 
በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት በማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ዙሪያ አጨቃጫቂ ነው የተባለ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። 
በዚሁ የማህበራዊ ድረገጾች ዙሪያ በጉባዔው ንግግርን ያደረጉት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ድርጊቱ የተለያዩ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች መቻቻል እንዳይኖራቸው እያደረገ ነው ሲሉ ቅሬታን ማቅረባቸውን የተባበሩት መንግስታት የዜና ማዕከል ሃሙስ ዘግቧል።
ይሁንና አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያጸደቀው አዲስ ህግ የማህበራዊ ድረገጽ አጠቃቀምን ለማፈንና ቁጥጥሩን ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ሲገልፅ ቆይተዋል። 

Wednesday, September 21, 2016

ጎንደር ቅዳሜ ገበያ ሱቆችን ለማቃጠል የተንቀሳቀሱ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፥ ሌሎች ሱቆችን ለማቃጠል 50 ያክል ሰዎች እንደተሰማሩ ታውቋል።

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009)
በጎንደር ቅዳሜ ገበያ ያልተቃጠሉ ሱቆችን ለማቃጠል ቤንዚን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ሰዎች ረቡዕ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በጎንደር እንደገና ቁጣ ተቀሰቀሰ። ግለሰቦቹ ከትግራይ ክልል መላካቸውንም ለኢሳት መረጃ ያደረሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። 
ሱቆቹን ሲያቃጥሉ ሲሉ በነዋሪዎች ከተደረሰባቸው በኋላ በፖሊስ እጅ የገቡት አራቱ ግለሰቦች ወዲያውኑ ለፖሊስ በሰጡት መረጃ ለጥፋት ድርጊት የተላኩት እነሱን ጨምሮ 50 ያህል ሰዎች መሆናቸውንም እንዳስረዱም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። 
በግለሰቦቹ ድርጊት የተሳጩትና የቀድሞዎም ቃጠሎ በዚህ ሁኔታ እንደሆነ የተገነዘቡት የአራዳና የቅዳሜ ገበያ አካባቢ የጎንደር ነዋሪዎች በቁጣ አደባባይ ወጥተዋል።
በአካባቢው የሰፈረው የአጋዚ ክፍለጦር ታጣቂ ሃይል በነዋሪው ላይ እየተኮሰ መሆኑን ይህም ማምሻውን መቀጠሉን የኢሳት ምንጮች አብራርተዋል።
በርካታ ወጣቶች መታፈሳቸውም ተብራርቷል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ የተኩስ ድምጽ ቀጥሏል።

በውጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ኢህአዴግ ከስልጣን እንዲወርድ፣ የትግራይ ተወላጆች ህዝባዊ ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ ጠየቁ

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009)
ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካና የተለያዩ ሃገራት የሆነ የትግራይ ተወላጆች ገዥው የኢህአዴግ መንገስት ከስልጣን እንዲወርድና በሃገሪቱ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም፣ የትግራይ ተወላጆች በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪን አቀረቡ። 
36 የሚሆኑ የቀድሞ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አመራሮችንና አባላትን ያካተተ አንድ ቡድን የትግራይ ተወላጆች ያላቸው አስተዋፅዖ እና ሚና እንዲጠናከር ለማድረግ ዘመቻን እያካሄደ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። 
በተለያዩ ሃገራት ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጥሪውን ያቀረበው ይኸው ቡድን የህወሃት ባለስልጣን በስልጣናቸው ለመቆየት የሚያደርጓቸውን መሰሪ ቅስቀሳዎች የትግራይ ተወላጆች እንዲያጋልጡና የሚፈጽሟቸውን ጭፍጨፋዎች እንዲያወግዙ ጥሪውን አቅርቧል። 

ኦህዴድ አቶ ሙክታር ከድርንና ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከሃላፊነት አሰናበተ

ኢሳት (መስከረም 11 ፥ 2009)
በኦሮሚያ ክልል ለወራት ሲካሄድ የቆየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በሊቀመንበርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሙክታር ከድርንና ምክትል ሊቀመንበሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከሃላፊነት አሰናበተ። 
በተሰናበቱት የኦህዴድ አመራሮች ምትክ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል። 
የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ሲካሄድ የቆየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰሞኑን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን እንዲካሄድና በአመራሮቹና በአባላቱ ላይ ግምገማ ማካሄዱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘግበዋል። 

Ex-army officer exposes torture of detainees in secret location

ESAT News (September 21, 2016)
A former member of the army who was among the thousands of youth detained by the regime from the Amhara region recounts horror stories of hard labor, hunger and disease in a secret location in a jungle in the Benishangul Gumuz regional state of Ethiopia.
Up to 2000 youth rounded up from Gondar, Bahir Dar and Chilga, among others in the Amhara region were taken to Benishangu, where they spend the day cutting stones and doing hard labor.

Thursday, September 15, 2016

የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ አገራት ወደአለመረጋጋትና ሁከት ሊገቡ እንደሚችሉ አሜሪካ አሳሰበች

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009)
የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ የአለማችን ሃገራት ለችግሩ ዕልባትን የማይሰጡ ከሆነ ወደ ዘላቂ አለመረጋጋትና ሁከት ሊገቡ እንደሚችሉ አሜሪካ ሃሙስ አሳሰበች። 
ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በስላማዊ ሰልፎች ላይ ከመጠን ያለፈ የሃይል እርምጃ እንደተጠቀመ የገለጸችው ሃገሪቱ ጭቋኝና አፋኝ የሆኑ ሃገራት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ከዜጎቻቸው ጠንካራ ተቃውሞ እየቀረበባቸው መሆኑን አስታወቀች። 
ሃሙስ በአለም ዙሪያ የተከበረውን የአለም አቀፉን የዴሞክራሲ ቀን አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነጻነትና ዴሞክራሲ የአንድን ሀገር ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው አመልክቷል። 
በሃገራቸው መንግስታት ጭቆና እየደረሰባቸው የሚገኙ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች በአሁኑ ወቅት በርካታ አማራጮችን በመጠቀም የሃገራቸው መንግስትን ግልፅና ተጠያቂ ለማድረግ እርምጃን እየወሰዱ ይገኛል ሲል የአሜሪካን መንግስት ገልጿል። 

በጎንደር ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገው ሙከራ ግጭት ቀሰቀሰ

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009)
በሰሜን ጎንደር ዞን ስር በሚገኙት የአምባ ጊዮርጊስና በለሳ አርባይ ከተሞች ነዋሪዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተሞከረው እንቅስቃሴ ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ሃሙስ ለኢሳት ገለጹ። 
ከረቡዕ ጀምሮ በከተሞቹ የተቀሰቀስው ግጭት ዕልባት አለማግኘቱን የተናገሩት ነዋሪዎች ሃሙስ ለሁለተኛ ቀን ለሰዓታት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ማምሸቱን እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። 

Security forces accused of displacing Amharas in Konso

ESAT News (September 15, 2016)
Security forces in southern Ethiopia are forcing the displacement of Amharas in Konso, in what the locals said was a deliberate attempt by regime operatives to incite ethnic violence, according to ESAT’s sources.
The displacement came as the people of Konso, who demanded self-administration, were also under attack by the forces.
Unable to respond positively to the demands of the people of Konso, security forces and operatives of the regime carried out the forced displacement of the Amharas, who have lived in harmony with the indigenous people since time immemorial. The action was said to be a ploy to divert the administrative demands of the people of Konso.
Several houses were set ablaze leading to the displacement of at least 300 Amharas from several villages, a source who wish to remain anonymous for fear of reprisal told ESAT.
Sources also said the Konsos have been providing support to the displaced Amharas and have refused to fall into the traps set by the forces to incite ethnic tensions.
The constitutional demand by the people of Konso has been met with deadly force by the regime and scores of people were killed and hundreds displaced.
(Picture obtained from social media)

Families receiving bullet riddled bodies of Qilinto prisoners

ESAT News (September 15, 2016)
Bodies of prisoners killed at a federal prison in Ethiopia two weeks ago were being given to families, who confirmed to ESAT that the cause for the death of their loved ones was bullet wounds and not the fire that gutted down the prison, as the regime claims.
The Ethiopian regime, contrary to what families of the victims found out, has said in official statements that the cause of death was fire. The government put the number of the victims at 23, but information obtained by ESAT indicate that at least 60 people were shot and killed by security forces.

በአዲስ አበባ የተጀመረው የመምህራን ውይይት ከፍተኛ ተቃውሞ የታየበት እንደነበር ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009)
በአዲስ አበበ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ት/ቤቶች ከረቡዕ ጀምሮ መካሄድ የጀመረው የመምህራን ውይይይት ከአስተማሪዎች በኩል ተቃውሞ እንዳጋጠመው መምህራት ለኢሳት አስታወቁ። 
ለዚህ ሃገር አቀፍ ውይይት እንዲሳተፉ ጥሪ የቀረበላቸው መምህራን መንግስት ወዳቀረበው የመወያያ አጀንዳ ከመገባቱ በፊት መምህራንን የቅድመ ሁኔታ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተሳታፊ መምህራን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። 
ረቡዕ የተጀመረው ይኸው የመምህራን ውይይት በቀረበው የትምህርት ስርዓት ላይ ለመወያየት አጀንዳ ቢኖረውም መምህራን በሃገሪቱ ስላሉ ተቃውሞዎችና ውጥረቶች ጥልቅ ውይይት እንዲካሄድ መጠየቃቸው ታውቋል።
ይሁንና አወያይ ተወካዮቹ ከመምህራኑ ለቀረበው ጥያቄ አግባብ ያለው ምላሽ ባለመስጠታቸው ውይይቱ አለመግባበት መፍጠሩን የውይይቱ ተሳታፊ መምህራን አስረድተዋል። 

በቂሊንጦ እስር ቤት በእሳትና በጥይት የተገደሉ ዜጎች ያለማስረጃ ለቤተሰብ እየተሰጡ ነው

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009)
በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት ደርስ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተገናኘ በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ እስረኞች ያለምንም ማስረጃ ለቤተሰብ እንዲሰጥ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። 
የማንነት ጥያቄን አስነስታችኋል ተብለው ባለፈው አመት ለእስር ተዳርገው ከነበሩት የሰሚን ጎንደር ዞን ትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪዎች መካከል በቂሊንጦ እስር ቤት ህይወታቸው ያለፈው አቶ ይላቅ አቸነፍ አስከሬን ለቤተሰብ ተሰጥቶ የቀብር ስነስርዓት መፈጸሙን ለኢሳት የደረሰ መረጃ አመልክቷል። 

የመንግስት ሃይሎች በሰገን ልዩ ዞን ጎማይዴ ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ከመኖሪያ ከቀያቸው እያፈናቀሉ ነው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 5 ፥ 2009)
በደቡብ ክልል ስር በሚገኘው የሰገን ልዩ ዞን ጎማይዴ ወረዳ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ለዘመናት በኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ከቀያቸው የማፈናቀል እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን እማኞች ሃሙስ ለኢሳት አስታውቁ። 
ሰሞኑን የጸጥታ ህያሎች የመኖሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ ያደረጉትን ድርጊት ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። 
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በዞኑ ስር የሚገኙት የኮንሶ ብሄረሰብ ያነሱትን አስተዳደራዊ ጥያቄ ወደ ሌላ አቅጣጫ ለማዞር ሆን ብለው የወሰዱት እርምጃ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። 

Wednesday, September 14, 2016

በኮንሶ በርካታ ዜጎች ተገደሉ : አካባቢው የጦርነት ቀጣና ሆኗል ተባለ

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
የመከላከያ ሰራዊት እና የደቡብ ክልል የልዩ ሃይል አባላት በኮንሶ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ባለው ጥቃት በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ25 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ይሆናል ይላሉ። ከተገደሉት መካከል አንድ አራስ ሴት በጥይት ተደብድባ ስትገደል፣ ህጻኑ በወታደሮች ተወስዷል በማለት የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።
ትናንት ብቻ ከ4 ሺ 50 በላይ ሰዎች የተሰደዱ ሲሆን፣ ዛሬም ስደቱ ቀጥሎአል በማለት የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ።
ጭፍጨፋውና እልቂቱ ሊቀጥል እንደሚችል የአገር ሽማግሌዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መምህራን በእያመቱ በሚጠራው የገዢው ፓርቲ ስብሰባ መሰላቸታቸውን ገለጹ

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
ገዢው ፓርቲ በመላ አገሪቱ የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማብረድ በሚል ትምህርት የሚጀመርበትን ጊዜ በማራዘም መምህራንን ለ2 ሳምንት የሚቆይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ በዛሬው ስብሰባ መምህራን በእያመቱ በሚደረገው አንድ አይነት ውይይት መሰላቸታቸውን ገልጸዋል።
“መምህራኑ ከትምህርት ጋር ባልተያያዘ ጉዳይ ለምን እንሰበሰባለን?” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ግዴታ መሆኑ ተነግሯቸዋል።
መምህራኑ የጧቱን ዝግጅት ተካፍለው የከሰአቱን አብዛኞቹ አለመሳተፋቸውን መምህራን ተናግረዋል

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ለ5ኛ ጊዜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
በአማራ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት መነሻ የሆኑት የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ በዛሬው እለት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በአካል ሳይቀርቡ ለአምስተኛ ጊዜ ለመስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን የሰላም አስከባሪ የነበሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እያሉ የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጪ ከቤታቸው አፍነው ሊወስዷቸው ሲሞክሩ እራሳቸውን ለመከላከል የአልሞትባይ ተጋዳይ ሆነው በሕዝቡ ትብብር ከሞት መትረፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን ኮሎኔል ደመቀ በጎንደር ከተማ ሕዝብ እና በከተማዋ ከንቲባ አማካኝነት በአደራ ተሰጥተው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ምንም ዓይነት ውሳኔ ሳይሰጣቸው በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ እየተመላለሱ ነው። የኮሎኔል ደመቀን የፍርድ ሂደት ለመከታተል ብዛት ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በከፍተኛው ፍርድ ቤት አካባቢ አስቀድመው ተገኝተዋል። ከሕዝቡ ቁጥር ባልተናነሰ የታጠቁ የአጋዚ ወታደሮች ከተማዋን ቢወሯትም በተለይ የከተማው ወጣቶች ካለምንም ፍርሃት በብዛት መገኘታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

Tuesday, September 13, 2016

የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ መንግስት እየተወሰደ ያለው ከመጠን ያለፈ ዕርምጃ እንዳሳሰበው ገለጸ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009)
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት ህጻናትን ጨምሮ በተለያዩ የፖለቲካ አመራሮችና ሰላማዊ ሰፈኞች ላይ እየወሰደ ያለው ከመጠን ያለፈ የሃይል እርምጃ አሳስቦት እንደሚገኝ ማክሰኞች በድጋሚ ገለጠ።
በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ በብሪታኒያ የተሰባሰቡ የኮሚሽኑ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የጅምላ እስራት እያካሄዱ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 
የኮሚሽኑ ሃላፊ የሆኑት ዘይድ ራድ አል ሁሴን በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የጅምላ እስራትና የሰዎች ደብዛ መጥፋት እንዲሁም የህጻናት ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ለአለም አቀፍ አካላትና በመድረኩ ለተሳተፉ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሃገሪቱ በመፈጸም ላይ ያሉ ግድያዎችን በገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ ጥያቄን ቢያቀርብም የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ድረስ ምላሽ ነፍጎ መገኘቱን ሃላፊው ለአለም አቀፍ ተቋማት ማስረዳታቸው ታውቋል። 

ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያላት አቅም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009)
የአለም ባንክ ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ያላት አቅም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንና ሃገሪቱ ከ189 የአለማችን ሃገራትይ መካከል በ148ኛ ደረጃ ላይ መገኘቱን ይፋ አደረገ። 
በአለም የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ዙሪያ ሪፖርቱን ያወጣው የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርገው የሚገኙ የውጭ ኢንቨስትመንት ደንቦችና ጥበቃዎች ከሌሎች ሃገራት ሲነጻጸሩ ደካማ ሆነው መገኘታቸውን ገልጿል። 
የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ህጎቻቸው ላይ የማሻሻያ እርምጃ ሲወስዱ ቢቆይም የኢትዮጵያ መንግስት በቂ እርምጃ ሳይወስድ መቅረቱ ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ማድረጉን የሃገሪቱ የልማት አጋር የሆነው ባንኩ በሪፖርቱ አመልክቷል።
ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ሴኔጋል፣ ቤኒንና፣ ቆፕሮስ፣ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ የህግ ማሻሻያን አድርገው የተሻለ ውጤት ማስመዘባቸውን የአለም ባንክ በአመታዊ ሪፖርት አስፍሯል። 

በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለም አቀፍ ትኩረት እያገኘ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009)
ባለፉት በርካታ ወራት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአሜሪካ መንግስት ምክር ቤት ትኩረት እያገኘ እንደሆነ አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ ምክር ቤት ተወካይ ተናገሩ። 
የኮሎራዶ ሴናተር የሆኑት ኮንግሬስ ማን ማይክ ኮፍማን ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ፣ ኢትዮ-አሜሪካውያን በየግዛታቸው ለሚገኙ የኮንግሬስ ለወኪሎቻቸው በመደወል የኢትዮጵያ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው እንዲጠይቁ ጥሪ አቅርበዋል። 
አሜሪካ አሁን ያላትን አለም-አቀፋዊ ተሰሚነት ተጠቅማ የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹን ሰብዓዊ መብት እንዲያከብር ተፅዕኖ እንድታሳርፍ ኮንግሬስማን ማይክ ኮፍማን ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ ጠይቀዋል። 

ከቂሊንጦ አደጋ የተረፉ እስረኞችን ለመጠየቅ ገደብ መጣሉ ተገለጸ

ኢሳት (መስከረም 3 ፥ 2009)
በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰውን የእስት ቃጠሎ አደጋ ተከትሎ ከአደጋው የተረፉ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ያቀኑ ጠያቂዎች በእስር ቤቱ አስተዳደር እገዳ መጣሉን ለኢሳት አስታውቁ።
የእስረኛ ቤተሰቦች የቤተሰብ አባሎቻቸውን ለመጠየቅ ወደ እስር ቤቱ ቢሄዱም የያዙትን ነገር ብቻ አቀብለው ያለምንም ንግግር እንዲመለሱ መደረጉን ከዜና ክፍላችን ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉ ቤተሰቦች ገልጸዋል። 
ባለፈው ሳምንት በቂሊንጦ እስር ቤት ላይ ደርሶ በነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሶስት ዞኖች ሙሉ ለሙሉ የወደሙ ሲሆን፣ አንደኛው ዞን ከቃጠሉ መትረፉ ታውቋል። 

በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ተጠየቀ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
በአዲስ አበባ ስታዲየም እና ዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ሰኞ የኢድ አልድሃ በዓልን ለማክበር የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በእስር ላይ የሚገኙ ሁሉም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ በመጠየቅ የተቃውሞ ጥያቄን አቀረቡ። 
የቀይ ቀለም ምልክትን የያዘ ወረቀት በመያዝ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የበዓሉ ታዳሚዎች፣ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሌሎች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አሳስበዋል። 
የሙስሊሙን ትግል በማስተባበር ላይ የሚገኘው ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ፣ ሁሉም የኮሚቴ አባላት እስኪፈቱ ድረስ የተጀመረው ግፊትና ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሰኞ የበዓል አካባበርን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። 

Monday, September 12, 2016

በድርቅ የተጠቁ 9.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አሁንም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ጋር ተዳምሮ በ9.7 ሚሊዮን ሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን እያደረሰ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። 
ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ ዕልባት አለማግኘቱን ያወሳው ድርጅቱ የኮሌራና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ድርቁን በመከላከሉ ስራ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። 
ከ200 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች ውስጥ ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቁ አደጋ እልባትን ያላገኘ ሲሆን፣ 9.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አሁንም ድረስ ለምግብ ድጋፍ ተጋልጠው እንደሚገኙ ታውቋል። 

በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ተጠየቀ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
በአዲስ አበባ ስታዲየም እና ዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ሰኞ የኢድ አልድሃ በዓልን ለማክበር የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በእስር ላይ የሚገኙ ሁሉም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ በመጠየቅ የተቃውሞ ጥያቄን አቀረቡ። 
የቀይ ቀለም ምልክትን የያዘ ወረቀት በመያዝ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የበዓሉ ታዳሚዎች፣ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሌሎች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አሳስበዋል። 
የሙስሊሙን ትግል በማስተባበር ላይ የሚገኘው ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ፣ ሁሉም የኮሚቴ አባላት እስኪፈቱ ድረስ የተጀመረው ግፊትና ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሰኞ የበዓል አካባበርን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። 

ህዝቡ የስልጣን ባለቤት አለመሆኑ አገሪቷን ለችግር እንደዳረጋት የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ገለጸ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የህዝብ ስልጣን ባለቤትነት አለመከበር እንዲሁም የዕኩልነትና የእኩል ተጠቃሚነት መርህ አለመተግባርና ዜጎችን ሁሉ ሊያሳትፍ የሚችል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት ሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት ላለችበት አሳሳቢ ሁኔታ መንስዔ መሆኑን ገልጿል። 
በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለአመታት የተከማቸ የህዝብ ብሶት ውጤት ነው ያለው ኮሚቴው፣ በስልጣን ላይ ያለው ገዢው መንግስት ለዘመናት የህዝብን ጥያቄን ሲያጣጥል ቆይቷል በማለት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። 
በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ለተገደሉ ሰዎች ሃዘኑን የገለጸው ኮሚቴው በህዝብ ዘንድ የተነሱ ጥያቄዎችን ተገቢ ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መገለጫ አስፍሯል።

በጎንደር የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ቀይ ፊኛ ከመልቀቃቸው በተጨማሪ፣ እጃቸውን አጣምረው ተቃውሞ አሰሙ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
የዘንድሮውን የኢድ አል አድሃ በዓል ለማክበር በጎንደር ከተማ የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በከተማዋ ባለስልጣናት ባለኮከብ ባንዲራን ይዘው እንደወጡ የተሰጣቸውን መልዕክት ሳይቀበሉ መቅረታቸው ታውቋል። 
ለበዓሉ አከባበር የታደሙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ወደጎን በመተው በዕለቱ የተቃውሞ መልዕክት ነው ያሉትን ቀይ ፊኛ ወደሰማይ ሲለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ መልዕክት ለዜና ክፍላችን ደርሷል። 
ቀይ ፊኛን ወደ ሰማይ መመልቀቁ ጎን ለጎን ታዳሚዎች እጃቸውን በማጣመር በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን ሲያወግዙ ማርፈዳቸውንም ከሃገር ቤት ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው መንግስትን ይቅርታ አልጠየቅሁም አለ

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲዘግብ በአሸባሪነት ተከሶ በእስር ቤት ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው መንግስትን ይቅርታ አለመጠየቁን ገለጸ። 
ጋዜጠኛ ዩሱፍ ሙያውን ሽፋን በማድረግ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት በሚል ክስ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ቤት አመታትን አስቆጥሯል። 
ከ4 አመታት በላይ በእስር የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው በመክሮ ሊፈታ ወራት ሲቀሩት ከአዲሱ ዓመት ጋር በተየያዘ በምህረት በሚል ከተለቀቁት መካከል ነው። 
ወደፊት ስራውን እንደሚቀጥልና መንግስት ዜጎችን በማፈን ሃሳባቸውን እንዳይገልጹ የሚያደርገውን ተፅዕኖ እንዲያቆምም ጥሪ አቅርቧል።

አትሌት ታምሩ ደምሴ የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን የተቃውሞ ድርጊት መድገሙን አለም አቀፍ መገኛኛ ብዙሃን ዘገቡ።

ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በመካሄድ ላይ ባለው የፓራ ኦሎምፒክ በ 1ሺ 500 ሜት የብር ሜዳልያን ያገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምሩ ደምሴ በመንግስት የሚፈጸሙ ግድያዎችን በመቃወም የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ድርጊት መድገሙ አለም አቀፍ መገኛና ብዙሃን ከስፍራው ዘገቡ። 
ሰኞ በውድድሩ ሜዳልያን ለማግኘት የበቃው አትሌቱ በአለም አቀፉ ደረጃ ተመሳሳይ መልዕክትን ካስተላለፉ አትሌቶች መካከል አራተኛው ለመሆን መብቃቱን ኢንዲፔንደንት የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። 
አትሌቱ እጁን በማጣመር በድሉ ወቅት ያስተላለፈው መልዕከት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጸሙ ግድያዎችንና አፈናዎችን ለመቃወም የሚያመለክት መሆኑን ጋዜጣው በአትሌቱ ድርጊት ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አቅርቧል። 

Friday, September 9, 2016

የጀግኖች ደም ወፍራም ነው!

ይህ መልዕክታችን ለነጻነታችሁ ለምትዋደቁት የአገራችን ድንቅ ልጆች በሙሉ ባላችሁበት ይድረስ:-

ከአርበኞች ግንቦት 7
ውድ የአገራችን ጀግኖች
ለነጻነታችሁ የምታደርጉት ተጋድሎ ወደር የማይገኝለት መሆኑን ስንነግራችሁ በኩራት ነው። ይህን ተጋድሎአችሁን በጠመንጃ ሃይል ለማፈን የወያኔ አገዛዝ የሚወስደው ፋሽስታዊ እርምጃ አልበቃ ብሎት፣ አሁን ደግሞ የስነ ልቦና ዘመቻ ከፍቶባችኋል። አባቶቻችሁን ፣ እናቶቻችሁን፣ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን በየመድረኩ እየጠራ እናንተን እንዲያወግዙ እየስገደደ ነው። አድሎአዊነትና ኢፍትሃዊነት አንገሽግሾአችሁ ያቀጣጠላችሁትን የነጻነት ትግል ለማራከስ፣ ታሪካችሁን ለማቆሸሽ ላይና ታች እያለ ነው። የእናንተ ታሪክ ግን እንደ ገዳዮቻችን ታሪክ የሚቆሽሽ አይደለም። ማንም ምን ቢል የእናንተ ስራ ወደር የማይገኝለት ዘለላም ለትውልድ ሲተላለፍ የሚኖር ነው። የእናንተ ትግል ለራሱ ክብርና ነጻነት የሚቆጭ የሰው ልጅ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባ እውነተኛ ትግል ነው። ለዚህ ነው የህይወት መስዋትነት ቢከፈልበት የሚያንስበት እንጅ ከቶውንም የሚበዛበት የማይሆነው ።

Thursday, September 1, 2016

በአምባ ጊዮርጊስ 26 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ

ኢሳት (ነሃሴ 26 ፥ 2008)
በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ ተቃውሞውን ለማዳፈን የተንቀሳቀሰው የአጋዚ ሰራዊት በአምባ ጊዮርጊስ 26 ሰዎችን መግደሉ ተነገረ። በአጋዚ ሰራዊት በተኮሰው ጥይት የቆሰሉ በርካታ የአምባ ጊዮርጊስ ነዋሪዎች ወደ ጎንደር ለህክምና ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል። 
በህወሃት ባለስልጣናት ልዩ የግድያ ትዕዛት የተሰጠው ጸጉረ-ልውጥ የሆነ ገዳይ የአጋዚ ቡድን በሰላማዊ ህዝብ ላይ በሰነዘረው ጥቃት ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 26 ሰዎችን መግደሉ የታወቀ ሲሆን፣ ከእናቶችንና ህጻናትን ውጭ አብዛኛው የተከማው ህዝብ በሽሽት ወደ ጫካ መግባቱ እማኞች ለኢሳት ተናግረዋል።