Wednesday, September 30, 2015

በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ከፍተኛ የውሃና የምግብ እጥረት መከሰቱን ሰነዶች አመለከቱ

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶችና መንግስት በጋራ በፈረንጆች አቆጣጠር ሴፕቴምበር 24 ፣ 2015 ያደረጉት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እንደሚያስረዳው ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች እጅግ አሳሳቢ የሆነ የውሃና የምግብ እጥረት ተከስቷል። ችግሩም በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንደሚጨምር ለኢሳት የደረሰው ቃለ ጉባኤ ያስረዳል። በተለይ በሶማሊ ክልል ባለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸኳይ ምግብና ውሃ ለማቅረብ እንዳልተቻለ ሪፖርቱ ይጠቅሳል። እርዳታ ለመስጠት የመከላከያ ሰራዊት ፈቃድ መጠየቅ እንዳለበትም በቃለጉባኤው ላይ ሰፍሯል።

በኦሮምያ፣ በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ፣ ቦረና፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ ሸዋ የሚገኙ 37 ወረዳዎች በከፍተኛ የውሃ እጥረት የተጠቀሱ ሲሆን፣ ውሃ በቦቴ ለማዳረስ የተደረገው ሙከራም አጥጋቢ አይደለም ተብሎአል። በአማራ ክልልም እንዲሁ ደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም ከፍተኛ የውሃ እጥረት አጋጥሟቸዋል። በትግራይ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ እና ማእከላዊ ዞኖች፣ በአፋር 11 ወረዳዎች እንዲሁም በሲቲ፣ ሃርሺንና ኖጎብ ዞኖች የውሃ እጥረቱ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ዩኒሴፍ ከክልል መሪዎች ጋር በመተባባር አደጋው የሚቀንስበትን መንገድ እያፈላለገ መሆኑ በቃለጉበኤው ተጠቅሷል።

በሳውድ አረቢያ በሃጅ ጸሎት በተፈጠረ መጨናነቅ የተነሳ የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በውል አልታወቀም

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስካሁን 13 ሰዎች እንደሞቱ ቢገልጽም፣ የመጨረሻው መረጃ ይፋ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊልቅ ይችላል።

ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሼህ አህመድ ከሳውድ አረቢያ እንደገለጹት፣ 13 ቱ ሟቾች የተለዩት ዘመዶቻቸው ባረጋገጡት መሰረት ነው።

በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ከፍተኛ የውሃና የምግብ እጥረት መከሰቱን ሰነዶች አመለከቱ

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶችና መንግስት በጋራ በፈረንጆች አቆጣጠር ሴፕቴምበር 24 ፣ 2015 ያደረጉት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እንደሚያስረዳው ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች እጅግ አሳሳቢ የሆነ የውሃና የምግብ እጥረት ተከስቷል። ችግሩም በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንደሚጨምር ለኢሳት የደረሰው ቃለ ጉባኤ ያስረዳል። በተለይ በሶማሊ ክልል ባለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸኳይ ምግብና ውሃ ለማቅረብ እንዳልተቻለ ሪፖርቱ ይጠቅሳል። እርዳታ ለመስጠት የመከላከያ ሰራዊት ፈቃድ መጠየቅ እንዳለበትም በቃለጉባኤው ላይ ሰፍሯል።

በዛምቢያ በእስር ቤት ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተላኩ

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዛንቢያ የስደተኞች ቢሮ በአገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ በመግባታቸው ክስ ከቀረበባቸውና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ሃያ ስድስት የውጭ አገር ዜጎችን ወደየትውልድ አገራቸው መመለሱን አስታውቆ፣ ከእነዚህ መካከል 16ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ከኬንያ ጀምሮ ባሉት የመሸጋገሪያ አገራት ውስጥ አያሌ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስርቤትና በታጋቾች በደልና ስቃይ እየደረሰባቸው ሲሆን ፣ ኤንባሲዎች ዜጎቻቸውን ለመታደግ የሚያደርጉት ጥረት አለመኖሩ ሰቆቃቸውን አብዝቶታል። ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው የስራ ዋስትና ማጣት፣የኑሮ ውድነት፣የዴሞክራሲና የነጻነት እጦት ሰለባ በመሆናቸው ስደትን እንደ አማራጭ እንደወሰዱት አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

በገጠር መንገዶች ላይ ሚታየው የጥራት ችግር አሁንም አለመፈታቱ ተነገረ፡፡

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ገጠር መንገድ ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ባደረገው አመታዊ የሰራተኞች ስብሰባ ላይ ችግሩ አለመቀረፉን የገለጹት ባለሙያዎችና የድርጅቱ ሰራተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ የሚያሳማው የጥራቱ ጉዳይ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁልጊዜ ሊያሻሽለው አልቻለም በማለት ባለሙያዎች ያቀረቡት የጥራት ጉዳይ መንገዶች ጥገና ተደርጎላቸው ከተሰሩ በኋላም ተገቢውን ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ በመበላሸታቸው በወረዳና ዞን አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመቸገር ተደጋጋሚ አቤቱታ እንደሚያሰሙ ተናግረዋል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በሜዳማ ቦታዎች የሚሰሩ መንገዶች ዳርና ዳር ካለው የመሬት አቀማመጥ ወደ ስር በመግባት መገንባታቸው በላያቸው ላይ ውኃ እንዲፈስና ቶሎ አገልግሎታቸውን እንዲጨርሱ የሚያደርግ አሰራር መከተል የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተለመደ ችግር እየሆነ መምጣቱን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

Tuesday, September 29, 2015

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች ስጋት ላይ ናቸው

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ ገዥው ፓርቲ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን የመልካም አስተዳደር፣ የሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን አጋልጡ በሚል ከፍተኛ ግፊት ማድረጉን ተከትሎ ትርምስ መፈጠሩ ተሰማ፡፡

የመገናኛ ብዙሃኑን መሪዎች ጨምሮ አንዳንድ ጋዜጠኞች በሙስናና ብልሹ አሠራር የሚጠረጠሩ መሆናቸው ይበልጥ ነገሩን አወሳስቦታል፡፡
ኢህአዴግ በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔ በመልካም አስተዳደር ችግሮች መተብተቡንና ሕዝቡ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠው በማመን ችግሩን ለመቅረፍ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ነበር፡፡
“ትኩረት መደረግ ያለበት በመልካም አስተዳደር ችግርን ላይ ነው፣ ችግር ፈጣሪዎችን ማጋለጥ አለብን” የሚል መመሪያ ከአለቆቻቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየሰሙ መሆኑን የሚናገረው አንድ በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኛ ፣ ይህን ዘገባ ሰርተን ችግር ቢገጥመን የተሰጠን ምንም ዓይነት ዋስትና የለም ብሏል፡፡

በአፋር የስልጣን ውዝግብ የህወሃት ደጋፊዎች ማሸነፋቸው ተሰማ

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት ነባር ታጋይና በሁዋላም የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አብዴፓን) መስርተው ክልሉን ላለፉት 24 ዓመታት ሲመሩት የቆዩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ፣ ከስልጣን ተነስተው ወደ ፌደራል ሲዛወሩ እርሳቸውን ለመተካት በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ፣ ህወሃት የደገፋቸው ቡድኖች አሸናፊዎች ሆነው መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ቀድም ብለው ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡት ወጣቱ አቶ ጣሃ አህመድ ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ቢሆኑም፣ ክልሉን በፕሬዚዳንትነት መምራት አይችልም የሚል ተቃውሞ የህወሃት ደጋፊና ታማኞች በሆኑት በጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው በአቶ ስዩም አወል፣ በአቶ ሙሃመድ አምበጣና በአቶ እስማኤል ተነስቶባቸዋል። ምንም እንኳ በኢህአዴግና በደጋፊ ፓርቲዎች አሰራር መሰረት የድርጅት ሊቀመንበር የክልል ፕሬዚዳንት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም፣ ይህ አሰራር ለአቶ ጣሃ አህመድ አልተፈቀደም።

በረሃብ የተጠቁ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኤልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሳቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕፃናትን ጨምሮ ከ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከፍተኛ በሆነ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑንና አፋጣኝ የሆነ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአውስትራሊያው ቻይልድ ፈንድ በሪፖርቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ያለው የርሃብ ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና በተለይ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች ለአስከፊ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ህጻናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ድርጅቱ አትቷል፡፡

ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ታሰረ

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ችግር በማጋለጥ እንዲሁም የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ፣ በየመን የጸጥታ ሃይሎች መታሰሩ ታውቋል።

ጋዜጠኛ ግሩም በምን ምክንያት እንደታሰረ የታወቀ ነገር የለም። ኢሳት ባለቤቱን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም።
በየመን በመካሄድ ላይ ያለውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስደተኞችን በሚመለከት የሚያወጣቸውን ዘጋባዎች ተከታትሎ በማጋለጥ በኩል ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ጋዜጠኛ ግሩም ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ተከሶ ፣ ያለፉትን 10 አመታት በየመን በስደት አሳልፏል።

በጣሊያን ፍሽስት ወረራ ወቅት ለተፈጸመው ግፍ ጣሊያን ካሳ እንድትከፍል ተጠየቀ

መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ፍሽስት ወረራ ወቅት ለተፈጸሙት ዘግናኝ ግፎች የጣሊያን መንግስትና ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁና የተዘረፉት ቅርሶችና ንብረቶች ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ዓለምአቀፍ ሕብረት ለፍትሕ ጥያቄውን አቀረበ።

በጣሊያን ወረራ ወቅት የጣሊያን ወራሪዎች በዓለም ላይ የተከለከለውን ካለስተር ቦንብ ተጠቅመው ንፁሃን ኢትዮጵያዊያንን ጨፍጭፈዋል፣የታሪክ ድርሳናትን ዘርፈዋል፣ውሃን በመርዝ በመመረዝ ንፁሃን ዜጎችንና እንስሳትን ገለዋል ። በአዲስ አበባ ውስጥ በሶስት ቀናት ብቻ ከሰላሳ ሽህ በላይ ንፁሃን ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ ሲሆን፣ ከሁለት መቶ በላይ አብያተክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊይውያን በመላ አገሪቱ በግፍ ተገድለዋል።

አርባ‬ ምንጭ የነበረው የአሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን አካባቢውን ለቆ እየወጣ ነው

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)



‪አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ‪‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡
አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡

Monday, September 28, 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘረኝነት እየተወነጀለ ነው

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትርፋማነቱ በተለያዩ አለማቀፍ የንግድ ተቋማት እየተመሰገነ ቢመጣም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ” ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ክሶችን እያቀረቡ ነው። አየር መንገዱ ጀምሮት ከነበረው የቁልቁለት ጉዞ የታደጉት አቶ ግርማ ዋቄ ስራቸውን ከለቀቁ በሁዋላ፣ በምትካቸው የተሾሙት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሄር ሰዎች ለማስያዝ እንቅስቃሴ መጀመራቸው፣ በትግራይ ብሄር ተወላጆችና በሌሎች ብሄር ተወላጆች መካከል ከፍተኛ የሆነ አድልዎ እየታዬ መምጣቱን እንዲሁም የህወሃት/ኢህአዴግን የፖለቲካ ፍልስፍና የማይከተሉ ኢትዮጵያውያን እድገት ይከለከላሉ፣ ከስራ ይባረራሉ ፣ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩም ይታሰራሉ።

ቤት ሰሪ የመንግሰት ሰራተኞች አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ የ1997ቱን ምርጫ ውጤት ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ የነበረው ኢህአዴግ የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የቤት ፈላጊዎችን በማህበር ካደራጀ በሗላ ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ እንዲቆጥቡ በማድረግ ከ9 ዓመታት በሗላ የቤት መስሪያ ቦታቸውን ለቤት ሰሪዎች ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጅ ቤቱን መስራት የሚችሉት መንግስት ባወጣላቸው የቤት እቅድ መሰረት ባለፎቅ ቤት ብቻ መሆኑ ቤት ሰሪዎችን ድንጋጤ ላይ ጥሎአቸዋል። የቤቱን መሰረቱን ካላወጣችሁ የቆጠባችሁት 80ሺ ብር አይመለስላችሁም በመባላቸው ፣ እነዚህ ከ90 በመቶ በላይ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት የቤት ፈላጊዎች የቤቱን መሰረት ለማውጣት የሚያስችል ገንዘብ እንደሌላቸውና የሚኖሩበት የኪራይ ቤት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋው እየጨመረ መምጣቱን በመግለፅ ለዘጠኝ ዓመታት የቆጠቡት ገንዘብ እንዲመለስላቸው በምሬት ቢጠይቁም ምላሽ አላገኙም፡፡

ለመስቀል የታሰበው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በድጋሚ ተሰረዘ።

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለአዲስ አመት ዋዜማ በላፍቶ ሊያዘጋጀው የነበረው ኮንሰርት በመሰረዙ በአድናቂዎቹ ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ ሳይረሳ ፣ አሁን ደግሞ ለመስቀል በአል ያዘጋጀው ኮንሰርት በድጋሚ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳይካሄድ መከልከሉን የፎርቺን ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቢኔ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አቶ ፈለቀ ነጋሽ የ አዲስ አመት ኮንሰርቱ የተሰረዘው በአስተባባሪዎቹ የፈቃድ ጥያቄ የቀረበው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሆኑ አኳያ አስተዳደሩ ባጋጠመው የስራ መደራረብ ሳቢያ እንደሆነ ለጋዜጣው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ብሪታኒያ በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ልትልክ ነው።

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን እንዳስታወቁት ወታደሮቺ የሚላኩት አልሸባብን እየተዋጉ ላሉት የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ድጋፍ ለመስጠት ነው።

በመሆኑም እስከ 70 የሚደርሱ የ እንግሊዝ ወታደሮች በቅርቡ የሰላም አስከባሪ ልኡኩን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ብሪታኒያ ከዚህም በተጨማሪ እስከ 300 የሚደርሱ ወታደሮቿን በደቡብ ሱዳን እንደምታሰፍር የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
ውሳኔውን አስመልክቶ በመንግስታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ ድጋፍ እንደሚቸራቸው የተገመቱት ዴቪድ ካሜሩን ወታደሮቹ ወደ ስፍራው መንቀሳቀሳቸው ወደ አውሮፓ የሚደረግን ህገወጥ የስደተኞች ዝውውር ለመግታት እንደሚረዳም ተናግረዋል።

ሁለት የሶማሌ የጦር አውሮፕላኖችን መተው የጣሉት የቀድሞ አየር ኃይል ጀግና አረፉ

የኮለኔል ባጫ ሁንዴ የህይወት ታሪክ

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአንቦ አካባቢ በጊንጪ ከተማ ተወለዱ ።በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በ1965 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኢትዮጵያ አየር ሃይል በአውሮፕላን ጥገና አገራቸውን ለማገልገል ተቀጥረው ስልጠናቸውን እንደጨረሱ ከክፍላቸው ያመጡት ውጤት የላቀ በመሆኑ እና የተዋጊ አውሮፕላን በራሪ ለመሆን ባሳዩት ከፍተኛ ፍላጎት ሙያው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት በማሟላት ወደ በረራ ትምህርት ቤት ገቡ።Colonel Bacha Debele
የሚፈለግባቸውን የበረራ ትምህርት እንደጨረሱ ወደ ተዋጊ ስኳድሮን በመመደብ የኤፍ 86 አውሮፕላን ሲበሩ ቆይተው የኢትዮጵያ አየር ሃይል F-5E የሚባል አዲስ አውሮፕላን ሲገዛ ወደ አሜሪካን አገር ተልከው በዚሁ አውሮፕላን ስልጠና በመውሰድ እና በማጠናቀቅ ወደ አገራቸው ተመልሰው በወቅቱ አገራችንን የወረሩትን የሱማሌ ወራሪዎች ጋር ፍልሚያ ውስጥ በመግባት በአየር ላይ ውጊያ ሁለት የሱማሌ ሚግ አውሮፕላኖችን መትተው የጣሉ ሲሆን በዚህም ላሳዩት ከፍተኛ ጀግንነት ከኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሜዳ የላቀ ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ሆነዋል።

Sunday, September 27, 2015

” በአለም ላይ እንደኛ ጀግኞቹን የገደለ ህዝብ የለም” ፕሮፍ መስፍን ወልደማርያም

pro.Mesfin

”ፕሮፍ መስፍን ወልደማርያም በአዳፍኔ እንዳሉት”ፕሮፍ መስፍን ወልደማርያም በአዳፍኔ እንዳሉት በአለም ላይ እንደኛ ጀግኞቹን የገደለ ህዝብ የለም አሉ ትክክል ነዎት ፕሮፍ አንዳንድ ሠዎች ጀግኖችን ህዝብ አልገደላቸውም የሚሉ አሉ የፕሮፍ መልስ ጀግኖች ሲገደሉ ህዝብ ምን አደረገ ?
የያኔውን እንተወውና ዛሬ እኛ ምን አደረግን ?
ፕሮፌሰር ዓስራት ወልደየስ ህክምና ተከልክለው ሲሞቱ እኛ ምን አደረግን ?
እስክንድር ነጋ ሲታሰር ምን አደረግን ?
አንዱለም ሲታሰር ምን አደረግን ?
ተመስገን ሲታሰር ምን አደረግን ?
ሳሙኤል አወቀ ሲገደል ምን አደረግን ?
ዘመነ ምህረት ተዘቅዝቆ ሲገረፍ ምን አደረግን ?

ጦላይ የሰለጠኑ የሕወሓት ደህንነቶች ወደየመጡበት አህጉር ተላኩ::

ምኒሊክ ሳልሳዊ  በሕወሓት ተመልምለው ከውጪው አለም የሚኖሩ ዲያስፖራ የሕወሓት ደጋፊዎች የደህንነት እና ስለላ ስራዎችን ስልጠና በጦላይ ከጨረሱ በኋላ ወደየመጡበት አህጉር መመለሳቸው ምንጮች ጠቁመዋል::ከሰሜን አሜሪካ አውሮፓ እና መካከለኛ ምስራቅ እንዲሁም ከአፍሪካ ተመልምለው የመጡ እና በስራ ፈትነት በዲያስፖራው መሃል ሲኖሩ የነበሩ የሕወሃት ደጋፊ ዲያስፖራዎች የደህንነት እና ስለላ ስልጠና ለአንድ አመት ከስድስት ወር በኋላ ከተከታተሉ በኋላ ወደየመጡበት ተመልሰው ለስራ እንደተላኩ ታውቋል::

በዲያስፖራው መሃል ተሰግስገው የጥላቻ እና የጠባብነት መርዝ ለመርጨት እንዲሁም ሰርገው በመግባት የዲያስፖራውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለመሰለል በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በየሃገሩ የሚያደርጉትን የቢዝነስ እንቅስቃሴ እና ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ እንዲያጠኑ እና ሪፖርት እንደሚያደርጉ ታውቋል::የወያኔው ጉጅሌ መንግስት በዲፕሎማሲው መስክ የተለያዩ የበለጸጉ ሃገራትን በብሄራዊ ጥቅማቸው በመያዝ ዜጎችን ለብሄራዊ ውርደት በመዳረግ በምእራባውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት አለው::ቢሆንም አብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ለአገዛዙ ከፍተኛ ጥላቻ ስላላቸው ድጋፋቸውን መንፈጋቸው በአባይ ቦንድ ሽያጭና በተለያዩ አጋጣሚዎች ያላቸውን ተቃውሞ ማሳየታቸው ይታወቃል::

Friday, September 25, 2015

አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርበው ህዝብ ቁጥር ጨምሯል

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው።

የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለድርጅቱ የሚደወሉ ስልኮች በእጥፍ ጨምሯል። ምንም እንኳ አብዛኛውን ጥሪ የሚያደርጉት ወጣት ወንዶች ቢሆንም፣ ጎልማሶችና ሴቶችም ይገኙበታል ሲል የመረጃ ክፍሉ ለኢሳት ገልጿል።
ድርጀቱ ትግሉን እንቀላቀል ለሚሉት ሃይሎች ” በአገር ውስጥ ሆነው ራሳቸውን እንዲያደራጁ ምክር እንደሚሰጥ ” የገለጸ ሲሆን፣ ሁኔታዎችን ላመቻቹ ወጣቶች ደግሞ ጉዞአቸውን በምን መንገድ ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚገልጽላቸው ገልጿል።
የደሚት ሊቀመንበር ሞላ አስጎደም መክዳት ለድርጀቱ በሚደውሉ ሰዎች ቁጥር ላይ ያመጣው ተጽእኖ እንደሌለ የገለጸው የመረጃ ክፍሉ፣ እንዴያውም ህዝቡ በቁጭት ስሜቱን እና ድጋፉን ሳያቋርጥ እንዲገልጽ አድርጎታል ሲል አክሏል። ህዝቡ በአገር ውስጥ ባለው አፈና በመማረር አስቸኳይ ለውጥ እንዲመጠብቅ የሚገልጸው ድርጅቱ፣ ትግሉ ትእግስትንና ጽናትን የሚጠይቅ በመሆኑ ታግሶ በውስጥ የሚያደርገውን ትግል እንዲገፋበት ጠይቋል።

የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማስረጃ (TVET) እንደ ትምህርት ማስረጃ እንደማይቀበለው ገለጸ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤምባሲው የ2015 የዲቪ ሎተሪ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ማስረጃን እንደሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃነት ከዚህ ቀደም ሲቀበል መቆየቱን በማስታወስ ከአሁን በኃላ የማይቀበል መሆኑን አስታውቆአል፡፡

ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት የአሜሪካ መንግስት የትምህርት መስፈርት ለውጥ ሊያደርግ የተገደደው በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ የአሜሪካንን ስታንዳርድ የሚጠብቅ ባለመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በቴክኒክና ሙያ የሰለጠኑ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የ2015 የዲቪ ዕድለኞች ወደአሜሪካ መግባት አይችሉም፡፡

ሀዲያ ውስጥ በአባ ሰንጋ በሽታ ሰዎችና ከብቶች እየሞቱ ነው

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን “አባ ሰንጋ” የተሰኘው የከብቶች በሽታ ተከስቶ በርካታ ሰዎችና ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን እንዳጠናቀረው መረጃ እስካሁን በበሽታው አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። በበሽታው እጅግ በርካታ ከብቶች እያለቁ በመኾናቸውም የ አካባቢው ህዝብ መጪውን የመስቀል በዓል ከስጋ ተዋጽኦ ውጪ እንዲውል ተገዷል።
በአሁኑ ወቅት ለተወሰኑ ከብቶች ክትባት መስጠት የተጀመረ ቢኾንም በሽታው በፍጥነት እየተዛመተ መኾኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። ከመስቀል በዓል ጋር ተያይዞ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት መፈጠሩንም ዘጋቢያችን የላከው መረጃ ያመለክታል።

በከፍተኛ ወጪ የሚገነባው ፈጣን የአውቶቡስ መስመር ተቃውሞ ገጠመው

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ በየካቲት ወር 2008 ጀምሮ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ

ፕሮጀክት ከአዋጪነት አንጻር በሚገባ በጥናት ያልታየና በአሁኑ ሰዓት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን የሚያሳጣ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ፕሮጀክቱ ከዊንጌት፣ በጎፋ ገብርኤል አድርጎ ወደ ጀሞ የሚዘልቅ ለከተማ አውቶቡስ ብቻ የተከለለ መስመር ለመገንባት የታቀደ ሲሆን ፣ ይህ ፕሮጀክት በጠቅላላው 60 ሚሊየን ዩሮ
ይፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡ ፕሮጀክቱ በየካቲት ወር 2008 ተጀምሮ በ15 ወራት ጊዜ

በኬንያና ማላዊ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ላይ ናቸው


መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ኢዞሎ ግዛት ውስጥ ድንበር አቋርጠው ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተጨናነቀ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ዘግቧል።

በኬንያ ኢዞሎ ጂኬ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት 450 እስረኞች መካከል 300 ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እስር ቤቱ ከ 150 የበለጡ እስረኞችን መያዝ እንደማይችል የኢዞሎ ግዛት ምክትል ኮሚሽነር ገልጸዋል።
በኬንያ ውስጥ የሚገኙ ሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪዎችን አድኖ ለመያዝ እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ባለስልጣኑ፣ የእስር ጊዜያቸውን የጨረሱ ሰማንያ ኢትዮጵያዊ እስረኞች ባለፈው ወር ወደ አገራቸው መጠረዛቸውንና መቶ ሃያ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በሜሩ ግዛት ውስጥ ፍርድቤት መቅረባቸውን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙት ዜጎቹን ለማስለቀቅም ሆነ ለመጎብኘት ምንም ዓይነት ጥረት እስካሁን ድረስ አላደረገም።

‹‹ኢህአዴግም ሞላን ከሚያስከዳ ይልቅ ሌላ ሰው ቢሞክር ይሻለው ነበር›› ተማም አባቡልጉ (ጠበቃ)

mola Asgidom

‹‹ሞላ (አስገዶም) ግን ምን አይነት ሰው ነው? ንግግር አይችልም፡፡ ሚዲያ ላይ ሲቀረብ፣ ምን እንደሚነገርና ምን እንደማይነገር እንኳን ለይቶ አያውቅም፡፡ ‹‹መግለጫው››ን በአጋጣሚ አይቼ በመገረም ‹‹አጃኢብ›› ስል ነበር፡፡ [ፈገግታ ያጀበው ሳቅ] …ኢህአዴግም ሞላን ከሚያስከዳ ይልቅ ሌላ ሰው ቢሞክር ይሻለው ነበር፡፡ የሞላ ትርጉሙ አልታየኝም፡፡ የብርሃኑ (ነጋ/ፕሮፌሰር) ኤርትራ መምጣት ሞላን አነስተኛ (Insignificant) አድርጎታል፡፡ ሰውየው ለዓመታት እንዲሁ ተቀምጦ የነበረ ይመስለኛል፡፡

አቡነ ጴጥሮስ ወደ ቦታቸው ይመለሱ!

የጀግንነት ፣ የአማኝነት ፣ የአይደፈሬነት ፣ የእውነት ፣ የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ቦታቸው ይመለሱ ፡፡ አገራቸውን በእብሪት ሊወር የመጣን ፋሽስት ንጉስን ተከትለው ማይጨው በመውረድ በጦር ሜዳ የተፋለሙ ከሽንፈት ማግስት ንጉስኑና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እግሬ አውጭኝ ብለው ሲፈተለኩ ወደ ደብረ ሊባኖስ በመውረድ በፆም ፣ በጸሎት ብሎም ሕዝቡን በማስተማርና አርበኞችን በማበረታታት የወራሪውን ድብቅ ሴራ ያጋለጡ መንፈሳዊ አባት ነበሩ ፡፡ ታዲያ ሕዝባዊ ቅቡልነታቸውን ያየው ወራሪው ፍሽስት አርበኞችን አውግዘው የኢጣሊያብ ወራሪነት ቢቀበሉ የተደላደለ ኑሮ እንደሚገጥማቸው ሲያረዳቸው

Wednesday, September 23, 2015

የአባይን ግድብ እንዲያጠና የተሰየመው የሆላንዱ ኩባንያ ስራውን በገለልተንነትና በጥራት ለመስራት ባለመቻሉ ኮንትራቱን ማቋረጡን ገለጸ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ዴልታሬስ ኩባንያ ከፈረንሳዩ ቢአር ኤል አይ ኩባንያ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ጥናት እንዲያካሂድ በግብጽና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወክሎ ነበር። ይሁን እንጅ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት በምን መንገድ መካሄድ አለበት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር ሲነጋገሩ ቢቆዩም መስማማት አልቻሉም። ኩባንያው ከኢሳት ለቀረበለት የጽሁፍ ጥያቄ በሰጠው መልስ ” ጥናቱን በጥራትና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለማካሄድ እንደ ቅድመ ሁኔታ ብናሰቀምጥም፣ ሌላው ኩባንያ የሚቀበለው አልሆነም” ብሎአል። ዴልታሬስ ገለልተኛ ተቋም እንደመሆኑ ፣ ይህንን ውስብስብና ጠቃሚ ፕሮጀክት በጥራት ለማካሄድ ያሳየው ፍላጎት ተቀባይነት በማጣቱ ከስምምነቱ መውጣቱን ቢገልጽም፣ ውሳኔውን በተመለከተ እስካሁን ከሁለቱም መንግስታት መልስ እንደላገኘ ተናግሯል።

ዴልታሬስ የሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ሁለቱም አገራት እስካሁን በይፋ የተናገሩት ነገር የለም። ይሁን እንጅ በግብጽ የተመረጠው ዴልታሬስ ኩባንያ ያነሳው የገለልተኝነትና የጥራት ጥያቄ፣ ግብጾች በፈረንሳዩ ኩባንያ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርጋቸው ነው። በኢትዮጵያ በኩል የተመረጠው የፈረንሳዩ ኩባንያ በሆላንዱ ኩባንያ ለቀረበው ጥያቄ በይፋ መልስ አልሰጠም፣ ጥናቱን እንደሚቀጥል ወይም እንደማይቀጥል አላስታወቀም።

የጸረ ሙስና ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን የባለሥልጣናትን ሐብት ምዝገባ መረጃ ለመገናኛ ብዙሃን ክፍት ለማድረግ ፍላጎት አለመኖሩን ተናገሩ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮምሽነሩ ሰሞኑን በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ ከ95 ሺህ በላይ ተሿሚ፣

ተመራጮችና የመንግስት ሠራተኞች ሐብት ኮምሽኑ መመዝገቡን፣ እንዲሁም ከ14 ሺህ በላይ ሐብት አስመዝጋቢዎች የቤተሰቦቻቸውን ሐብት አሳውቀው ማስመዝገባቸውን አረጋግጠዋል፡፡ «ይህ መረጃ ለምን ይፋ አይደረግም» ለሚለው ጥያቄም ሲመልሱ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር ግዴታ እንደሌለባቸው በመግለጽ በግል መረጃ ለሚጠይቁ ሲሰጥ መቆየቱንና ይህ አሰራርም እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ኮምሽኑ በ2007 በጀት ዓመት ብቻ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ከኮምሽኑ አቃቤ ሕግ በተጠየቀው መሰረት 137 የሃብት አስመዝጋቢ መረጃዎችን በጹሑፍ መልስ መስጠቱን ገልጿል፡፡

በውቤ በረሃ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ቦታቸውን በግዳጅ ሊነጠቁ ነው

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ እየታሸጉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።

የከተማው አስተዳደር ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና እያንዳንዳቸው 25,000 ብር በማዋጣት በባንክ እንዲያስቀምጡ እንዲሁም በየወሩ ከ2000 ብር በላይ ገቢ እንዲያደርጉ ያቀረበውን ሐሳብ መቀበላቸውንና ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ ፣ በንግድ ቦታቸው ላይ ግንባታ ተካሂዶ እያንዳንዳቸው 25 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ሁሉ ታጥፎ በቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኑ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ክልል ከፍተኛ የስኳር እጥረት ተከሰተ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት እልባት ባያገኝም፣ በደቡብ ክልል እጥረቱ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝቡ ለሻሂ የሚሆን ስኳር ማግኘት አለመቻሉን እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል ግን በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ስልት የቡድን መሪ የሆኑ ነጋዴዎች፣ መንግስት የሚያከፋፍለውን ስኳር፣ እየጫኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንደሚያሻግሩት ነዋሪዎች ይገልጻሉ። መሰረታዊ የሚባሉትን የዘይትና ስኳር አቅርቦቶችን መንግስት ራሱ በዘረጋው የማከፋፋያ መንገድ እየሸጠ መሆኑ ይታወቃል።

የተናገሩት ከሚጠፋ… (በኤፍሬም ማዴቦ – ከአርበኞች መንደር)

በኤፍሬም ማዴቦ

ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት። ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters
ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ።

ጦርነቱ ከሰሜን እስከ ኦጋዴንና ጋምቤላ ተፋፍሞ ቀጥሏል።


ጦርነቱ ከሰሜን እስከ ኦጋዴንና ጋምቤላ ተፋፍሞ ቀጥሏል።ይህ በንዲህ እንዳለ እንደውስጥ አወቅ ምንጮች ኤርትራ ወያኔን ለማንበርከክ የዛተች ሲሆን ለኢትዮዽያ ህዝብ የሚከተለውን ያክብሮት መልክት አስተላልፋለች።
“ወያኔ በሉኣላዊት አገር ኤርትሪያ ጦርነት ቢያውጅ
የ ኤርትራ ህዝብና መንግስት ሊወስደው የሚችለው
እራስን የመከላከል እርምጃ የሚያነጣጥረው ወንድሙ እና እህት በሆነው
የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሳይሆን በህወዓት ላይ ብቻ መሆኑን ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘብልን እንወዳለን፥፥”

Tuesday, September 22, 2015

በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 3ቱ የጋምቤላ ተወላጆች እንዲፈቱ አለማቀፍ ድርጅቶች ጠየቁ

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ መንግስት የአለም ባንክ የቋንቋ አስተርጓሚውን ፓስተር ኦሞት አግዋን ጨምሮ አሽኔ አስቲንና ጀማል ኦማር ሆጀሌ የተባሉ ለጋምቤላ ህዝብ መብት መከበር የሚታገሉ ሰዎች የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ለስብሰባ ወደ ናይኖቢ ኬንያ ሲያመሩ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ መያዛቸውን በመጥቀስ፣ ግለሰቦቹ የቀረበባቸው የሽብረተኝነት ክስ ውድቅ ሆኖ በአፋጣኝ እንዲፈቱ 6 አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የምግብ ዋስትናን በተመለከተ በአንድ የአገር ውስጥ እና በሁለት አለማቀፍ ድርጅቶች የተዘጋጀው ስብሰባ ” የሽብርተኞች ቡድን ስብሰባ” የሚል ስያሜ ሰጥቶ ፣ በስበሰባው ላይ ለመሳተፍ የሚሄዱ 7 ሰዎችን ያሰረ ሲሆን ፣ ከእነሱ መካከል 4ቱ ተፈትተዋል ሲሉ ድርጅቶች በመግለጫው ላይ ጠቅሰዋል።
መግለጫውን ያወጡት 6ቱ ድርጅቶች ሂውማን ራይትስ ወች፣ ብሬድ ፎር ኦል፣ ግሬይን፣ አኝዋ ሰርቫይቫል፣ ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት እና እንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተራንሽናል ናቸው።

ረሃቡ የጠናባቸው ሰዎች ወደ ጎዳና እየወጡ ነው

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ከድርቅ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ረሃብ ተከትሎ በርካታ ዜጎች ወደ ከተማ እየፈለሱ ሲሆን፣ እርዳታ ማግኘት ባለመቻላቸው ጎዳና ላይ ማደር መጀመራቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያሰማሩዋቸው ባለሙያዎች በዞኑ 80 ሺ ህዝብ መራቡን ሪፖርት ሲያደርጉ፣ የዞኑ የመንግስት ባለስልጣናት በተቀራኒው በዞናቸው ምንም የተራበ ሰው የለም የሚል ሪፖርት አቅርበዋል።

የመንግስትን ቀጣይ እቅድ አስመልክቶ ለውውይት የተጠራው የአዲስ አበባ ህዝብ “ያልተጠበቁ” ጥያቄዎችን አነሳ

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የኢህዴግ ድርጅት ጽ/ቤት ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ዙሪያ በከተማው 10 ክ/ከተሞች በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎችን በሚያወያይበት መድረክ ፣ ነዋሪዎች አወያይ ካድሬዎችን ያስደነገጡ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ የ10 ወረዳዎችን የህብረተሰብ ክፍል በያዘው የወረዳ 9 አዳራሽ በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ስብሰባውን የተካፈሉ ዜጎች ለኢሳት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የመኪና አደጋ ከፍተኛ ገዳይ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ

መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመኪና አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ የሰዎችን ሕይወት ቀጣፊ ከሆነባቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ አገር መሆኗን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት በሪፖርቱ ገልጿል።ድርጅቱ ከመቶ ሺህ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 3 ሺ 874 ሰዎች ለሞት እንደሚጋለጡና 80 % የሚሆነው የአደጋው ምንጭ የአሽከርካሪዎች ጥፋት ሲሆን፣ የተቀረው 20 በመቶ ደግሞ በመንገድ ችግሮች መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል።

ባለፈው ዓመት ብቻ ከ17 ሺ 052 በላይ የተሽከርካሪ አደጋ ተከስትዋል። አምና ብቻ በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር 418 ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺ 676 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው ፣ 194 ሚሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመትም ደርሷል።
ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር ኢትዮጵያ በመኪና አደጋ ሳቢያ የሰው ሕይወት ከሚጠፋባቸውና የንብረት ውድመት ከሚደርስባቸው አገራት መካከል ቀዳሚዋ አገር ተብላለች።

Monday, September 21, 2015

በጋምቤላው ግጭት 126 ሰዎች መገደላቸውን መንግስት ገለጸ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቃቢ ህግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ቀድም ብሎ 60 ሰዎች መገደላቸውን ከጠቀሰ በሁዋላ፣ አሻሽሎ ባቀረበው ክስ 126 ሰዎች በወረዳ አመራሮች ትእዛዝ መገደላቸውን ጠቅሷል።

በማዣንግ፣ ጎደሬና ሚጤ በሃላፊነት ላይ የነበሩ የወረዳ አመራሮች ” ደገኞች ቦታችንን ለቀው ይውጡ፣ ደገኞች በማዣንግ ዞን ውስጥ የያዙትን የእርሻና የቡና ተክል መሬት ለማዣንግ ብሄር ተወላጆች ያካፍሉ” የሚል ንግግር መድረጋቸውንና በዚህም ሳቢያ ግጭት መቀስቀሳቸውን ይዘረዝራል።
ደገኞች እየተባሉ የሚጠሩት የሌሎች አካባቢ ተወላጆች ቡናችንንና አትክልቶቻችንን አናካፍልም በማለታቸው የፖሊስ አባላትና ሚሊሺያዎች እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው በክሱ ላይ ተመልክቷል። ባለስልጣናቱ ብሄረሰቡን መሳሪያ በማስታጠቅ እርምጃ እንዲወሰድ በሰጡት ትእዛዝ ፣ ለአንድ አመት ያክል ደም አፋሳሽ ግጭት ተከስቷል። ግጭቱን ተከትሎ ከ7 ሺ ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
መኢአድ በወቅቱ ከ600 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሶ ነበር። የአካባቢው ተወላጆች በበኩላቸው የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችና ወታደራዊ መኮንኖች የአካባቢውን መሬት መቀራመታቸው ለግጭቱ መነሳት መንስኤ ነው ይላሉ።

ለሚፈናቀሉአርሶ አደሮችጩኸታቸውን የሚሰማአካል አልተገኘም

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :­ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለከተማ ቤቶች መስሪያ፣ ለልማት ወይም ህገወጥ ግንባታ በሚል አርሶ አደሮች ያለምንም ክፍያ ከይዞታ መሬታቸው እየተፈናቀሉ ማህበራዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በኦሮምያ ክልል በ አዳማ ከተማ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች ቦታቸውን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን፣ በርካታ ቤቶችም ፈርሰዋል። በማሳ ያለው ሰብል ሲደርስ መሬቱን ለመቀማት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቅዳሜ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ስብሰባ ቢደረግም፣ ምክትል ከንቲባው በአቤቱታ አቅራቢዎች ላይ ” ብትፈልጉ ውጭ ማደር ትችላላችሁ ” በማለት ተሳልቀዋል።
በሰሜን ሸዋ በጫጫ ወረዳ ደግሞ አጅማ ወንዝን ለመገደብ በሚል ሰበብ ከነብር ዋሻ እስከ አሞራ ገደል ባሉት አካባቢዎች የሚገኙ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አርሰዶአሮች እንዲነሱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል። አርሶ አደሮቹ ” ሆን ተብሎ እኛን ለመበታታን የታቀደ ነው” በማለት የመንግስትን ድርጊት አጥብቀው ተቃውመዋል። ለሸንኮራ ልማት በሚል በተለያዩ ክልሎች የሚፈናቀሉ አርሰዶአሮች ለኢሳት የድረሱልን ጥሪዎችን ቢያሰሙም ፣ እስካሁን መፍትሄ የሚሰጥ አካል ሊገኝ አልቻለም። ተስፋ የቆረጡ አርሶደሮች እና ቤቶቻቸው በህገወጥ መንገድ የፈረሰባቸው ወደ ከተሞችና ወደ ውጭ አገራት እየተሰደዱ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የወያኔን ስርዓት በመቃወም በርካታ ወጣቶች የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጅትን ተቀላቀሉ።



hadesti
በዚህ ሳምንት ውስጥ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስርዓት በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጂት መቀላቀላቸውን ከማሰልጠኛ ማዕከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።በደረሰን መረጃ መሰረት የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል መቀላቀላቸውን የገለፀ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል
1 ተክላይ ታፈረ ገብረዋሂድ ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን ናዴር አዴት ወረዳ አዲ ላኪያን ቀበሌ አዲ በዛ አካባቢ
2 በሪሁ ገብረየሱስ ሃድጉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ቀበሌ አዲስ ተስፋ ሰፈር ደንጎሎ ከተባለው መንደር
3 ነፀረ-አብ አባዲ ፍስሃ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህዳይ አድያቦ ወረዳ ገመሃሎ ቀበሌ ሁመር ከተባለው ሰፈር
4 ፍስሃ ገብረስላሴ ገብረ መድህን ከማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ቤተ ገበዝ ቀበሌ ዝባን እንዳቦይ ገብራት ከተባለው አካባቢ
5 ጉዑሽ ሃይለ ገብረስላሴ ከስሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ማይ አድራሻ ከተባለው ቀበሌ
6 አወት ገዛኢ ፈዳይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎመከዳ ወረዳ ዛላንበሳ ከተማ

በአማራ ክልል በግንባታ ስራ የተሰማሩ ተቋራጮች በጤና ጥበቃ ቢሮው አሰራር መማረራቸውን ተናገሩ፡

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ዓርብ መስከረም 7/2008 ዓ.ም በድንገት በጠራው የተቋራጮች ስብሰባ፣ በክልሉ የሚገነቡ የጤና ተቋማትን በመስራት ላይ ያሉ ተቋራጮች በሙሉ ሰብስቦ ፤የግንባታ ስራዎች በመጓተታቸው ምክንያት ከልዩ ልዩ ግብረ ሰናይ መንግስታት የተገኘ የዕርዳታ ገንዘብ በየጊዜው ተመላሽ መሆኑ ቢሮውን አሳስቦታ ብሏል። ተቋራጮች በተቻላቸው ፍጥነት ግንባታቸውን በማጠናቀቅ በዕርዳታ የተገኘውን ገንዘብ ከመመለስ እንዲያድኑት ጠይቋል፡፡
የክልሉ የጤና ጥበቃ ቢሮ የዘርፉ ሃላፊዎች ግንባታው እንዲፋጠን ቢጠይቁም፣ ከተቋራጮች የተገኘው ምላሽ አስደንጋጭ ነበር፡፡በርካታ ተቋራጮች በለቅሶና በምሬት በጤና ቢሮው የደረሰባቸውን በደል በመግለጽ ለመጓተቱ ተጠያቂው ቢሮው መሆኑን ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡
የጤና ጥበቃ ቢሮው በአብዛኛው ‹‹ በጀት የለም!! ›› በማለት ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወር ያመላለሳቸው ተቋራጮች በምሬት ሲናገሩ ፤ ጤና ጥበቃ ቢሮው የሰሩበትን ገንዘብ በወቅቱ ባለመክፈሉ በተያዘው ጊዜ ስራውን ጨርሰው ለማስረከብ አልቻሉም፡፡በዚህም ምክንያት በየፕሮጀክቱ ለሚሰሩ ሰራተኞችና ሙያተኞች ከተገቢው በላይ ክፍያ ለመፈጸም መገደዳቸውን ገልጸው፤ የሚከፍሉት በማጣት ንብረታቸውን እሰከ መሸጥ መድረሳቸውን በለቅሶ ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡

ሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።


Getachew Reda sitt bilde.
ሥግብግቦቹ የብአዴን መሪዎች ከወያኔ ጋር አብረው የዐማራ ሕዝብን እያጠፉ ይገኛል
የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም።ለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን። እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

ዶ/ር አረጋዊ በርኼ ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ከህወሃት በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብላቸውም እንዳማይቀበሉት ገለፁ

የቀድሞው የህወሃት መስራችና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አባል የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ህወሃት ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሞ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ፣ ከድርጅቱ የለቀቁ የቀድሞ አባሎቹን በማነጋገር ወደ ድርጅታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ገልጸዋል።
ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ የውስጥ ችግር መዳከሙን የሚገልጹት ዶ/ር አረጋዊ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት እርሳቸውም ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በተደጋጋሚ እንዳናገሯቸው ይሁን እንጅ እርሳቸው የሚታገሉለት አላማ ጥሪውን እንዳይቀበሉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

Saturday, September 19, 2015

ወደ ኢትዮጵያ የሸሹት የትሂዴን አባላት ከ70 የማይበልጡ መሆናቸው ታወቀ


mola Asgidom
ኢሳት ዜና (መስከረም 7, 2008)
ባለፈው ሳምንት ትግል በቃኝ በሚል ታጣቂዎችን አስከትለው እጃቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም ይዘውት የሄዱት ታጣቂ ብዛት 70 ብቻ መሆኑን እንዲሁም ከድርጅቱ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከአቶ ሞላ በቀር እጃቸውን የሰጠ ኣንደሌለ ተገለጠ።
አርብ ጻጉሜ 6 ቀን 2007 አም በኢትዮጵያ አዲስ አመት ዋዜማ ከኤርትራ ወደሱዳን የተሻገሩትና ከዚያም ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን የሰጡት አቶ ሞላ አስገዶም፣ ለዘመቻ በሚል ከንቀሳቀሷቸው 115 ወታደሮች 45ቱን መመለስ እንደተቻለ ተመልክቷል። 
የትሕዴን ም/ሊቀመንበር የነበሩትና አሁን በተጠባባቂነት የድርጅቱን የመሪነት ስፍራ የጨበጡት አቶ መኮንን ተስፋዬ እንደተናገሩት ከአቶ ሞላ በስተቀር አንድም የትሕዴን አመራር ለኢትዮጵያ መንግስት እጁን አልሰጠም።

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል

“ሕዝብ አስፈቅደን ውጊያ እንጀምራለን” ሃይለማርያም

omhajer

በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።
የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግንአልሸሸጉም።
አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።

Friday, September 18, 2015

በአዲስ አበባ ዛሬ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ፈንጂ ተገኘ በሚል የወያኔ ደህነቶችና ፖሊሶች ወከባ ሲፈጥሩ ዋሉ


አምባሳደር ቪኪ ሐልድስተን ከዚህ ቀደም የስርኣቱ ደህነቶች ራሳቸው ፈንጂ ጠምደው ማፈንዳታቸውን መናገራቸውን ዊክሊክስ አጋልጦ ነበር ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 በልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል ታክሲ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት በሩ አካባቢ ዛሬ አርብ መስከረም 7 ቀን 2008 ከቀኑ 5 ሰዓት ተኩል ጀምሮ አነስተኛ ፈንጂ ተገኘ ተብሎ ህዝቡ በፖሊሶች ከአካባቢው እንዲርቅ በማድረግ ብዛት ያላቸው ደኅንነቶችና ፖሊሶች አካባቢው ተቆጣጥረውት መዋላቸውን የህብር ሬዲዮ ምንጮች ከስፍራው ገለጹ።

ህዝቡም ግማሹ በድንጋጤ ሲሯሯጥ አንዳንዱ ‹‹ይሄማ የተለመደ ድራማ ነው!›› በማለት ችላ ብሎ ውሸት በመሆኑ ተጠግቶ ለማየት ሲሞክር ፖሊሶቹም ግማሾቹ እየሳቁ ‹‹ እረ ሂዱ ›› በማለት በፌዝ ህዝቡን ሲያባሩ ማየታቸውን እነዚሁ ምንጮግ ገልጸው በዚህ ሳቢያ ንጹሃን ተወንጅለው ቢታሰሩ ያስገርማል ሲሉ ከወዲሁ ምንጮቻችን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በካዛንችስ በርካታ የንግድ ቤቶች እየፈረሱ ነው

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ውስጥ በንግድ እንቅስቃሴያቸው ከሚታወቁት አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው ካዛንችስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤቶች በብዛት የፈረሱ ሲሆን፣ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነዋሪዎች ስጋት ገብቷቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት አገልግሎት አሰጣጥና የክፍያ ስርዓት መመሪያ አወጣ፡፡

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዋጋ ቁጥጥር ውሳኔው አንዳንድ ት/ቤቶች አደናግጦአቸዋል፡፡

መመሪያው ፍትሐዊነት ጎድሎታል ያለውን የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ሁኔታ ሰርኣት የሚያሲዝ ነው ቢባልም ፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው።
አዲሱ መመሪያ ከስርኣተ ትምህርት ውጪ ልዩ ልዩ የትምህርት ኣይነቶችን ማስተማርና ለዚህም ክፍያ መጠየቅ ይከለክላል፡፡ ክፍያ ሲጠየቅ ለ10 ወራት ብቻ መሆኑን፣ የክረምትና የቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርቶች ወላጆች ሙሉ ስምምነት ካልጸደቀ ስራ ላይ ሊውል እንደማይችል ደንግጎአል፡፡ በአጠቃላይ ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማስተማር ወይንም አንድን ትምህርት በሌላ ቋንቋ በማስተማር ስም ተጨማሪ ክፍያ መሰብሰብ የተከለከለ መሆኑን አስቀምጦአል፡፡
ይህን መመሪያ በማያከብሩ የትምህርት ተቋማት ላይ የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆአል፡፡ መመሪያው ሊወጣ የቻለው ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን የማባባስ አሉታዊ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ተደጋጋሚ ቅሬታ በመቅረቡ ተከትሎ ነው ተብሎአል።
የአንድ የግል የትምህርት ተቋም ርዕሰ መምህር ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን በሰጡት አስተያየት የትምህርት ቢሮው ግብታዊ ውሳኔ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን መስማታቸውን በመጥቀስ በሁኔታው ለመስማማት አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተጋነነ ዋጋ ተጠይቆአል ሲባል ለምንድነው የተጠየቀው ብሎ መልሶ መጠየቅ ይገባል ያሉት መምህሩ፣
ባለሃብቶች ከፍተኛ መዋዕለንዋይ አውጥተውና ተቋም አደራጅተው፣ በውድ ዋጋ መምህራንን ቀጥረው ወጪያቸውን የሚያካክስና ተገቢ የሆነ የትርፍ ህዳግ የጠበቀ የአገልግሎት ክፍያ መጠየቃቸው አግባብ ነው ብለዋል፡፡
መንግስት የነጻ ኢኮኖሚ መርህ እከተላለሁ፣ በገበያ ስርኣት እመራለሁ በማለቱ እሳቸው የሚያስተምሩበት ተቋም ባለቤት ከውጭ ሀገር ወደሀገር ውስጥ በመመለስ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋያ አፍስሰዋል፡፡ ዛሬ ይህ የነጻ ገበያ መርህ በዋጋ ቁጥጥር የሚተካ ከሆነ ከኢንቨስትመንቱ ከመውጣት ውጭ አማራጭ የለንም ብለዋል፡፡
በየጊዜው ት/ቤቱ ዋጋ ሲጨምርም ከወላጆች ጋር ተመካክሮ ችግሩን አሳምኖ ነው ያሉት መምህሩ፣ በግብታዊነት እንደሚጨመር፣ አሻጥር እንዳለ አድርጎ ት/ቤቶችን ሃላፊነት በጎደለው መልኩ ማብጠልጠልና መመሪያ አውጥቻለሁ እያሉ ማስፈራራት ከአንድ መንግስታዊ አካል የሚጠበቅ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
አንድ በአጸደ ህጻናት የትምህርት ስራ የተሰማሩ ግለሰብ ስለጉዳዩ ከሰዎች ሰምተው መደንገጣቸውን በመጥቀስ በአሁኑ ሰኣት ምንም ዓይነት አስተያየት ለመስጠት እንደሚቸገሩ ተናግረዋል፡፡

ህወሃት ኢህአዴግ በመዳከሙ የቀድሞ አባሎቹን ለማሰባሰብ ሙከራ እያደረገ ነው ተባለ

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የህወሃት መስራችና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አባል የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ህወሃት ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሞ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ፣ ከድርጅቱ የለቀቁ የቀድሞ አባሎቹን በማነጋገር ወደ ድርጅታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ገልጸዋል።

ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ የውስጥ ችግር መዳከሙን የሚገልጹት ዶ/ር አረጋዊ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት እርሳቸውም ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በተደጋጋሚ እንዳናገሩዋቸው ይሁን እንጅ እርሳቸው የሚታገሉለት አላማ ጥሪውን እንዳይቀበሉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

የውጭ ምንዛሬ ገቢው እቅድ የማይጨበጥ ህልም ነው ተባለ

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከያዝነው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የወጭ ንግዱን ከ3 ወደ 12 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ መታቀዱ አሁን ሀገሪቱ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ እጅግ የተጋነነና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ያተኮረ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ባለሙያው እንደሚሉት በመጀመሪያው የመንግስት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ ማለትም በ2007 ዓ.ም የወጭ ንግዱን ገቢ 10 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ ብዙ ጥረቶች ቢደረጉም ከ3 ቢሊየን ዶላር ባላይ ማሳካት አልተቻለም፡፡ ሀገሪቱ የተለመዱትን የግብርና ውጤቶች ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጫትና

በኩዌት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔው ጸናባት

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በኩዌት ሱላቢካት ከተማ ውስጥ የአሰሪዋን ልጅ የ19 ዓመቷን ወጣት ሲሃም ማህሙድ በስለት በመግደል ወንጀል ተከሳ የነበረችው የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ወጣት ራቢያ ማህሙድ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ውሳኔ መፅናቱን የአገሪቱ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

ግድያውን ለመፈጸም ያበቃት ሟቿ መኝታ ክፍልዋ በተደጋጋሚ ጊዜ በመምጣት በር በመዝጋት ጥቃት የምትፈጽምባት መሆኑንና ይህ ተደጋጋሚ ጥቃት በፈጠረባት ስሜት የተነሳ በስለት ወግታ መግደሏን ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች።
ሟቿ የቀድሞ የኩዌት ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን ተጫዋችና የአገሪቱ የወጣቶችና የስፖርት ምክትል ኃላፊ ማህሙድ ፍሌዝ ልጅ ስትሆን፣ በወቅቱ ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች ወደ ኩዌት እንዳይገቡ እገዳ እንዲጣል ሲጠይቅ ነበር።
የኢህአዴግ መንግስት የሞት ፍርድ ለተፈረደባት ኢትዮጵያዊት ምንም ዓይነት የህግ እገዛ አላደረገላትም።

በኮንጎ ብራዛቪል ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በመላው የአፍሪካዊያን ጫወታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው።

በ5 ሺ ሜትር የወንዶች የሩጫ ውድድር ጌትነት ሞላ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፣ ርቀቱን በ 13 ደቂቃ 21 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ልዑልሲ ገብረስላሴ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
በ1 ሺ500 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድርም ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በድጋሚ ድል ቀንቷዋቸዋል።
ዳዊት ስዩም 4 ደቂቃ 16 ሰኮንድ 69 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ርቀቱን በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ፣ ሌላዋ ሯጭ በሶ ሳዶ ደግሞ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

አስገዶም መግለጫ ከዚህ የወዲ ካለዉ እዉነታ ጋር ያለው ተቃርኖ: :( ተስፋሁን አለምነህ ከኤርትራ በርሃ)



ከነበረው ሃላፊነት አንፃር ምንም የሚያዉ ቀዉ ነገር የለም ማለት አይቻልም :: እንጅ ከነበረዉ ሃላፊነት ይሁን የሚመጣጠን ግንዛቤ ስለለዉ በመክዳቱና በመግለጫዉ የተናገረዉ የለዉጥ ሃይሉን የሚጎዳ ነገር የለዉም :: ፕሮፌሰር ፈሪ አሁን ነዉ ማለት ምን ማለት ነዉ ? የፈሪነት መገለጫዉ ምንድን ነዉ? በእኔ እምነት ፈሪ አይደሉም :: ፈሪ ናቸዉ እንበል እሽ የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ አንዴት ይፈራል? ትግል አይደል ወዲ የህዝብ አስገዶም ከዳ ማለት ትህዴኖች ከሃዲ ናቸው … ማለት ነዉ? አይደለም :: ስለ ጥምረቱ የአለውን ሌላዉ አዴሃንን መጥራት ሲያቅተው ጥምረቱ ዉስጥ የሌለ ድርጅት እያነሳ መቀባጠሩ የትናትን እዉነት ማስታወስ የማይችል ገልቱ መሆኑን ያመለክታል ::
እንዳለዉ ተብሎ ሊጠቀስ ሞላ የሚችል እዉነት መግለጫዉ የለዉም :: ወያኔ እንዲሆንለት የሚፈልገዉን ነዉ የተናዘዘዉ ::
ምን አልባት የትናት እዉነት ለሚዘነጋ ዝንጉ ኤርትራ ዉስጥ  የተመለከታቸዉን ተራራ ማስታወሱንም እጠራጠራለሁ :: 
የትጥቅ ትግሉን በጥልቀት ለተመለከተው ህዝባዊ መሰረት ይዞል :: ባይሆን ወያኔ በመቅበዝበና ይህ ባሰልች ኘሮፖጋንዳ ወዲ 
አስገዶምን ባላናዘዘዉ: : 
ኤርትራ ዉስጥ የሚካሄደዉ ትግል መልኩን እየቀየረ ነዉ :: ወረዳ ተይዞ የትግሉ ገዠ ባለቤት ህዝብ የሁሉ ነገር ሞተርነቱን ሲያሳይ ደናቁርት ቦታ አይኖራቸዉ :: ዘመድ ከዘመዱ..ብለዉ መኮብለሉ የሚጠበቅ ነው :: ንዛዜውም ቢሆን ለተገነዘበው ይህን ያስረዳል :: ክደት ሞላ 
ፈጠመ :: ወያኔ ዘፈነ: : እሱ ስለሄደ ወያኔ ከመዉደቅ አትድንም ::

ምኞትና ተግባር ምንና ምን ናቸው? በጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ



በአዲሱ አመት ዋዜማ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ቂሊንጦ እስርቤት ከእህቴ ጋር ሄጄ ነበር፡፡ ስማችንን እና የምንጠይቃቸዉን እስረኞች ስም ካስመዘገብን በኋላ መታወቂያችን አሳይተን ወደዉስጥ ልንገባ ስንል መታወቂያዉን የምትመለከተዉ ፖሊስ ስማችንን ካነበበች በኋላ “ቆይ ቆይ የእናንተማ መጠየቅ አለበት” አለችንና መታወቂያችንን ይዛ ከበር መለሰችን፡፡ ከበሩ አጠገብ በሚገኝ ጎብኝዎች ወረፋ በሚጠብቁበት የእንጨት መቀመጫ ላይ አረፍ እንዳልን በሃሳብ ላይ ታቹን ማለት ጀመርኩ፡፡ እንድንገባ ይፈቅዱልን ይሆን ወይስ የቃሊቲዎቹ እንዳደረጉት “ፍቃድ የላችሁም” የሚል አስቂኝና አናዳጅ መልስ በመስጠት ይመልሱን ይሆን? ለሚለዉ ጥያቄ መልሱ እኔዉ ጋር ያለ ይመስል አጎንብሼ ማሰቤን ቀጠልኩ፡፡ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ “ማረሚያ ቤቱ” ለእስረኛ ቤተሰቦች መልካም ምኞቱን የገለፀበት ወረቀት ተለጥፎ ተመለከትኩ፡፡ ከአራት አመታት በላይ በመኖር የእስርቤቶቹን አሰራር አዉቀዋለሁና ተመሳሳይ የመልካም ምኞት መግለጫ የያዘ ወረቀት ለእስረኛዉም ተለጥፎ እንደሚሆን አልተጠራጠርኩም፡፡

በወናጎ ከተማ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገዱ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 16፣ 2008 ዓም በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ወናጎ ከተማ ከንግድ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ አድጎ ወደ ብሄረሰቦች ግጭት በማምራቱ በርካታ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ የተለያዩ የንግድ ቤቶችም ተዘርፈዋል። የከተማው ባለስልጣኖች ሆን ብለው ቀስቅሰውታል በተባለው በዚህ ግጭት፣ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ነን የሚሉ ሰዎች፣ የሌላ አካባቢ ብሄረሰቦች አካባቢያችንን ለቃችሁ ውጡ በማለት ግጭት መፍጠራቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ግጭቱን ማዬሉን ተከትሎ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ከተማው የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የከተማው ነዋሪዎችን ይዘው አስረዋል። በርካታ ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል።
ዛሬ መዋል የነበረበት የአካባቢው ገበያ አልዋለም። ሱቆችም ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ አልተከፈቱም። በዞኑ ውስጥ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ግጭቶች እየተሱ ደም አፋሰዋል። የዚህን ዜና ዝርዝር ተጨማሪ መረጃ እንደደሰረን በነገው እለት እናቀርባለን።

የሲፒጄው ተወካይ የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች አደነቁ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት፣ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ቶም ሮድስ፣ የዞን 9 ጸሃፊዎች የዚህን አመት የአለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሽልማት የሚገባቸው በርካታ ጋዜጠኞች አሉ ሲሉ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እየከፈሉ ያለውን መስዋትነት አወድሰዋል።

የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችን ለመሸለም የፈለግነው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፕሬስ አፈና ለአደባባይ በማብቃት ተጽኖ ለመፍጠር ነው ያሉት ቶም ሮድስ፣ ለዞን 9 ጸሃፊዎች የተሰጠው አለማቀፍ ትኩረት እንዲሁም በቅርቡ የተወሰኑ ጸሃፊዎች መፈታታቸው በእስር ላይ ያሉትን ሌሎች እስረኞች ትኩረት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል ብለዋል።
ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንደኛ መሆኑዋን የጠቁሰት ቶም ሮድስ፣ ሽልማቱ የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ስሜት ይቀይረዋል ተብሎ ብዙም ባይታመንበትም፣ ኢትዮጵያ ከውጭ መንግስታት ከፍተኛ የእርዳታ ገንዘብ የምታገኝ በመሆኑ፣ የአለማቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ይረደዋል ብለዋል።
የተወሰኑ የዞን 9 ቡድን አባላትና ርእዮት አለሙን የመሰሉ ታዋቂ ጋዜጠኞች ሲፈቱ የፕሬስ ነጻነቱ ይሻሻላል ብለን ተስፋ ብናደርግም፣ የሰፉ ጌታቸውን የመሳሰሉ በሽብርተኝነት ተከሰው 7 አመት ሲፈረድባቸው ስናይ ደግሞ ሁኔታዎች እየተበላሹ መሄዳቸውን እናያለን ብለዋል። ብዙ ጋዜጠኞች በመታሰራቸውና አብዛኞቹም ከአገር በመልቀቃቸው ፣ ጠንካራ ድምጾችን የሚያሰሙ ጋዜጠኞች መጥፋታቸውንም ተወካዩ ገልጸዋል።
ሚ/ር ቶም ሮድስ ኢትዮጵያ በነበሩበት ወቅት ጋዜጠኛ ውበሸት ታዬንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለማግኘት ለማግኘት ሙከራ ቢያደርጉም እንዳልተሳካለቸው ተናግረዋል።

ኢህአዴግ ከሚያደርገው የካቢኔ ሹምሽር አዲስ ነገር ላይጠበቅ ይችላል ተባለ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፊታችን መስከረም 24 ቀን በኢህአዴግ መቶ በመቶ የተያዘው ፓርላማ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአቶ

ሃይለማርያም የጠ/ሚኒስትርነት ሹመት ካጸደቀ በሃላ በጠ/ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚካሄደው የካቢኔ ሹም ር አዲስ ነገር ይዞ አይመጣም ተብሎአል። ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን እንደተናገሩት ግንባሩ በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግሮች በተጨማለቁ የካቢኔ አባላት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ካልቻለ ለህልውናው አስጊ ነው፡፡ ሕዝቡ በአሁኑ ሰዓት ባለው ስርዓት እጅግ የተማረረበት ወቅት ላይ መሆኑን የጠቀሰው አባሉ፣ ባለፈው ግንቦት ወር ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ባልተካሄደበትም ሁኔታ ጥቂት የማይባል ሕዝብ ኢህአዴግን አለመምረጡ በቂ ማሳያ ነው ብሏል፡፡
በኢህአዴግ ውስጥ ሶስት ዓይነት አሰላለፍ የያዘ ሃይል መኖሩን የጠቆመው ምንጫችን፣ አንዱና ዋናው በሙስናና ብልሹ አሰራር ራሱን ያበለጸገ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ራሱን አብዮታዊ ዴሞክራት አድርጎ የሚቆጥረውና ሙሰኞችን የሚቀናቀነው ሃይል ነው፡፡ ሶስተኛው ቡድን መካከል ላይ ሆኖ ወዳመዘነበት የሚያጋድል ወላዋይ አቋም ያለው መሆኑ በግንባሩ ታምኖበታል ያለ ሲሆን ፣ እነዚህ ሃይሎች እርስበእርስ የሚደርጉት ፍልሚያ በአሁኑ ሰዓት አፍጥጦ እየታየ ነው ሲል ያክላል።
ኢህአዴግ በርካታ ባለስልጣናቱ፣
ከፍተኛ ስልጣን ላይ ሆነው በሙስና የተዘፈቁ ፣ በጥቅም የተሳሰሩ፣ ከፍተኛ የገንዘብና የጥቅም ቡድኖችን ከላይ እስከታች መፍጠር የቻሉ በመሆናቸው ግንባሩ በቀላሉ ማስወገድ የሚችልበት አቋም ላይ አለመሆኑን የጠቀሰው አባሉ፣ የመልካም አስተዳደርና የጸረ ሙስና ዘመቻ መፈክሮች እንደከዚህ ቀደሙ ከመፍክርነት ሳያልፉ የሚከስሙ ናቸው ብሎአል፡፡
የፖሊስ፣ የመከላከያና የደህንነት ተቋማትን ጨምሮ በሁሉም መንግስታዊ ተቋማት በሙስናና ብልሹ አሰራር የራሳቸውን መንግስታዊ መስመር የዘረጉ ሹማምንት የሰዎችን ሰብኣዊ መብት የሚጥሱ፣ እንደፈለጉ የሚያስሩና የሚፈቱ በመሆኑ ስርዓቱን አደጋ ውስጥ እንደጣሉት መናገሩን ዘጋቢያችን በላከው ዘገባ ጠቅሷል።

የህንዱ ፓወር ግሪድ ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተከፍሎት ስራውን ለቀቀ

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ድርጅትን እንዲያስተዳደር ለሁለት አመታት 21 ሚሊዮን 700 ሺ ዶላር ወይም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለው ፓወር ግሪድ ይህ ነው የሚባል ስራ ሳያከናውን ተሰናብቷል።

በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የመብራት መጥፋት ሊሻሻል ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ፣ ቀድሞውንም ይህን ያክል ገንዘብ ማውጣት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ስራ አስኪያጅ የሚሾሙትና የሚያወርዱት ዶ/ር ደብረጺዮን ፣ በህንዱ ኩባንያ ቦታ አቶ ጎሳዬ መንግስቴን በስራ አስኪያጅነት ሹመዋል።
መንግስት የመብራት መቆራረጡን ለመቅረፍ በያመቱ ቃል ቢገባም ሊሳካለት አልቻለም። በመንግስትና በግለሰቦች የተገነቡ የተለያዩ የማምረቻ ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ እጥረት ስራ ሳይጀመሩ ለወራቶች መቀመጣቸውን በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።

Thursday, September 17, 2015

ሰበር ዜና በህብረቱ ሐይሎችና በወያኔ መካከል ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው

2015asee

በአርበኞች ግንቦት 7 በትህዴን እንዲሁም በህብረቱ ሐይሎች ከፍተኛ ድል የተደረገ ነዉ አማጽያኑ ገዢ መረት ተቆናጠዋል ህዝባዊ ወያኔ የሚመራዉ ሰራዊት በመበታተን እየሸሸ ነዉ፤
ምንጮቻችን ኢእንደሚገልጹት ከሆነ የአማጺያኑ ሰራዊት በእልህና በድፍረት ፊት ለፊት እየተጋፈጡ ነዉ፤ የከባድ መሳሪያ በማዕሉባ ወረዳ ላይ እየተምዘገዘገ ነዉ፥፡
በኤርትራ ውስጥ በሁመራ ድንበር አካባቢ ከአምሓጀር ከተማ በስተ ጀርባ ማዕሉባ ከማለዳው 4:30 ጀምሮ እስከ አሁንዋ ሰዓት ድረስ በከፍተኛ ደረጃ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን ከነብስ ወከፍ እስከ ከባድ መሳራ ልውውጥ እየወረደባት ነዉ ከተማዋ በወያኔ ፌደራል እና የአካባቢ ሚሊሻ እንዲሁም መከላከያ ትርምስምስ ዉስጥ ገብታለች 
ድል ለኢትዮጵያዊያን !! ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 እና ለህብረቱ ሰራዊት!!!

Wednesday, September 16, 2015

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለህዳር 21 ተቀጠሩ


‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ዛሬ መስከረም 5/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ በድጋሜ ለህዳር 21/2008 ዓ.ም ብይን ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የአቃቤ ህግን ምስክርና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት እየደረሰብን ነው ያሉትን አቤቱታ ለፍርድ ቤት ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ ‹‹የሽብር ተከሳሽ ስለሆንን ብቻ ህክምና ተከልክለናል፤ በማንነታችን ጥቃት እየተፈጸመብን ነው›› ሲሉ ችሎት ፊት ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካይ ያለውን በማስጠራት ‹‹ማስታወሻ ያዝና አጣራ›› በማለት አልፎታል፡፡
በሌላ መዝገብ የሽብር ተከሳሽ የሆነው በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ በፍቃዱ አበበ በበኩሉ ቀሪ የመከላከያ ምስክሮቹን ለማሰማት ለህዳር 16/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

” ከእንካሰላንታው ባሻገር” ኤርሚያስ ለገሰ


የሰሞኑን የኢትዬጲያ ፓለቲካ ለተከታተለ ሰው የትግሉ ጫፍ ወዴት እየሔደ እንደሆነ ለመገመት አያዳግተውም። …በአንድ በኩል ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት የበላይነቱን ያስጠበቀው አናሳ እና ዘረኛ ቡድን አሁንም ከማንም በላይ የደም ሀረጉን በመምዘዝ ለመሰባሰብ እየተጋ ያለበት ነው። …በሌላ በኩል ሁሉን አቀፍ ትግል የመረጡ በብሔርም ሆነ በሕብረ ብሔራዊነት የተደራጁ ሀይሎች ሀይላቸውን በማቀናጀት በጋራ ለመስራት እየተመካከሩ ያለበት ሁኔታ ነው። እነዚህ ሁለት እንቅስቃሴዎች ከፓለቲካ ፓርቲ እና የድርጅት ህልውና ባሻገር ከኢትዬጲያ ህዝብ የነጳነት ትግል መቀጠልና ወደ ኃላ መመለስ ጋር የተቆራኙ ናቸው። ርግጥም የእነዚህ ሁለት አካላት የፍልሚያ ውጤት የወደፊቱን የኢትዬጲያ እጣ ፋንታ የመወሰን እድሉ ከፍተኛ ነው።

ንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡
ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡
ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን አስቸግሮ ከሚያውቅ ግለሰብ ጋር በሚዝናኑበት ባር ውስጥ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሁለቱ ሴት ጓደኛሞች መዝናኛ ባሩ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከመውጣታቸው በፊት፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ለመግባት ተስማምተው መሄዳቸውን ታስታውሳለች፡፡ ክፍሉ ራሱን የቻለ መዝጊያ ኖሮት መፀዳጃ ክፍሎቹም ራሳቸውን የቻሉ መሆናቸውን የገለጸችው የዓይን እማኟ፣ አንዱን ክፍል በሚከፍቱበት ወቅት ዩኒፎርም የለበሰው ፖሊስ ውስጥ ሆኖ ስላዩት ይቅርታ መጠየቃቸውን ትገልጻለች፡፡
ይቅርታቸውን ተቀብሎ እንደወጣ እነሱ ወደ መፀዳጃ ክፍሎቹ ገብተው ከደቂቃ በኋላ ሲወጡ የዋና ክፍሉን በር ቆልፎ ፖሊሱ መፀዳጃ ክፍል ውስጥ እንደጠበቃቸው አስረድታለች፡፡ ወደ ሰሎሜ ተጠግቶ ‹‹አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድነው?›› ብሎ በጥፊ እንደመታትና እንደወደቀች የገለጸችው የሟች ጓደኛ፣ እሷ በሁኔታው ተደናግጣ ወደ መፀዳጃ ክፍሉ ገብታ መቆለፏን ትናገራለች፡፡ በክፍሉ ውስጥ እንዳለች የተኩስ ድምፅ መሰማቱን፣ የማቃሰት ድምፅ ስትሰማ መውጣቷን ገልጻለች፡፡

Tuesday, September 15, 2015

“ሞላ ለጥቂት አመለጠን” የትህዴን ጊዜያዊ ሊቀመንበር ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ዛሬ ለኢሳት ይናገራሉ።

”ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ7ዓመት ግምገማ እያደረግን ቆይተናል። በዚህም ሞላ በፖለቲካ አመራር ድርጅቱን አዳክሞታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ በሚፈልግበት ጊዜ ላይ በተካሄደው በዚሁ ግምገማ ሞላ ከፍተኛ ተቀውሞ ከድርጅቱ አመራሮችና አባላት ደርሶበታል። ”

”ይዞ የወጣው ታጋይ ቁጥሩ ተጋኗል። ያም ቢሆን ለስራ ተብለው(የኪነት ቡድኑ ለበዓል) የተታለለ ነው። በተቻለን መጠን አብዛኛውን መልሰናል። የተዋጋው ከእኛው ጋር ነው። ከሻዕቢያ ጦር ጋር የሚባለው ፈጠራ ነው።”
“ሞላ ለጥቂት አመለጠን”
12038189_955749471137362_5635600479759143858_n

ሰበር ዘና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ ወንጀለኛዉ ቡድን በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኤርትራዉያንን ሊሰበስብ ነዉ።

ይህዉ የኢትዮጵያና የኢትያዊያን ጠላት ወያኔ በተለይም ከፍተኛ የሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎችና አባላት አሉበት በሚባሉ የአለም ሐገራት የሚገኙ ተቃዋሚ ኤርትራዊያንን ኢላማ ያደረገ ሚስጢራዊ ስብሰባ ለማድረግ መወሰኑን እንዲሁም ከብሐራዊ መረጃ ለየሐገራቱ የኢትዮጵያ ኢንባስሲ ሰራተኞች ትእዛዝ መተላለፉን የደረሰን መረጃ አመለከተ።

17/09/2015 በደቡብ አፍሪካ የሚጀመረዉ ይህዉ ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ በኖርዌይና ስዊድን እንደሚቀጥል ታዉቋል። በመሆኑም ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለነዚሁ ኤርትራዊያን ልብ ማማለያ ይሆን ዘንድ ወደ ሐገር ቤት የሚገቡበት ፓስፖርት (travel document) ፣ የገንዘብ ድጎማ፣ የመሬት አቅርቦት እና የንግድ ፈቃድ (work permit) ፣ የአስመጪ እና ላኪ ፍቃድና እገዛ (import and export license) የሚሰጥ ሲሆን በተለየ መልኩ ዋና ትኩረቱ በኤርትራ መንግስት ላይ አለም አቀፍ ተቃዉሞ ለማስነሳት መሆኑ ታዉቋል