Friday, February 26, 2016

በደብረብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)

በአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ-ብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በትንሹ 14 ሰዎች መገዳላቸውን ፖሊስ አርብ አስታወቀ።
አንድ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከሌላ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው አደጋው ሊደርስ መቻሉንና፣ ሌሎች ሶስት ሰዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፅኑ በመጎዳታቸው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን ፖሊስ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምርመራን እያካሄደ እንደሆነ ገልጿል።
ሃገሪቱ ያላት ተሽከርካሪ ቁጥር ከህዝቧ ቁጥር አንጻር አነስተኛ ቢሆንም እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን በአለም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment