Tuesday, February 23, 2016

የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹና የኤምባሲው ሰራተኞች በአምቦና በሞጆ ሻሸማኔ በሚወስድ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አሳሰበ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተባብሶ የቀጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹና የኤምባሲው ሰራተኞች በአምቦና በሞጆ ሻሸማኔ በሚወስድ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አሳሰበ።
በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ ለደህንነት ስጋት እየሆነ በመምጣቱ ኤምባሲው የጉዞ ማሳሰቢያን ለማሰራጨት እንደተገደደም አስታውቋል።

ተደጋጋሚ ማሳሰቢያን ስትሰጥ የቆየችው ኖርዌይም ዜጎቿ በክልሉ በሚያደርጉት እንቀስቃሴ ላይ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ አሳስባለች።
የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ በምዕራብና በምስራቅ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንዲሁም ከዝዋይ እስከ ሃዋሳ ባሉ አካባቢዎች አስቸኳይ ካልሆነ በስተቀር ጉዞን እንዳያደርጉ አሳስቧል።
መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ሌሎች ኤምባሲዎችና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወኪሎችም ለሰራተኞቻቸው ተመሳሳይ ማሳሰቢያን እያወጡ እንደሆነ ከሃገር ቤት ከተገኘ መርጃ ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment