Tuesday, February 23, 2016

ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቁ እየተባባሰ ነው ሲል ተመድ አስታወቀ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
በተያዘው ወር ለበልግ ወቅት ሲጠበቅ የነበረው ዝናብ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክልሎች በበቂ ሁኔታ መዝነብ ባለመጀመሩ ድርቁ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታውቋል።
በሰሜንና ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሲጠበቅ የነበረው የበልግ ዝናብ በአግባቡ ባለመዝነቡም ድርቁ ቀጣይ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

በድርቁ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች ለእርሻ የሚሆን የዘር እህል የሌላቸው በመሆኑም ችግሩ ተደራራቢ መሆኑን የገለጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቋል።
ለተያዘው ወር ብቻ ከ220 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የእርዳታ አቅርቦት እንደሚያስፈልግም ድርጅቱ አክሎ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment