Sunday, August 31, 2014

ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል ተሰደደ

በጌታቸው ሺፈራውበተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች የራሱ “አዲስሚዲያ” ብሎግን ጨምሮ በተለያዩ ድህረ-ገፆች አዘጋጅ እና ፀሐፊ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል መሰደዱ ታወቀ፡፡ ጋዜጠኛው ቀደም ሲል የፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ፣የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢሳው መፅሔት ባልደረባና አምደኛ፤ በኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣና በቅርቡ ወደህትመት የገባው ቀዳሚ ገፅ ጋዜጣ ላይም የተለያዩ የፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ በራሱና በብዕር ስም እንደሚፅፍ ይወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተመሰረተውና በመንግስት ከፍተኛ ቁጥጥርና ጫና ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) መስራች አባል፤ በኋላም የማኀበሩ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ይታወቃል፡፡ጋዜጠኛው ከዚህ በፊትም በመንግስት ደህንነት ኃይሎች በምሽት እገታ እንደገጠመው፣ ከስልክ ጠለፋ እስከ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስበት እንደነበር ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም፤በተለይ ከጥቅምት 2006 ዓ.ም. ከአዲሱ ጋዜጠኞች ማኀበር መመስረት ሂደት ጀምሮ እና በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. 3 ጋዜጠኞችን እና 6 የዞን 9 ብሎገሮች በመንግስት ከታሰሩ በኋላ የመንግስት ደህንነቶች ክትትል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ቀጣዩ እስር እሱ ላይም ሊፈፀም እንደሚችል በመረዳት ለቅርብ ጓደኞቹ አሳውቆ ነበር፡፡ብስራት ባለፈው ነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አርብ ጠዋት አዲስ ባወጣው የስልክ መስመር የማዕከላዊ ስልክ ጥሪ ካስተናገደ በኋላ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጭ መሆኑን በማሳወቅ ለሰኞ እንደሚቀርብ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ባለፈው እሁድ ድንገት ሀገር ጥሎ መሰደዱ ታውቋል፡፡በቅርቡ ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች የእስር ስም ዝርዝር ውስጥ የማኀበሩ አመራሮች መኖራቸውና በቀጣይም መንግስት በአመራሮቹ ዙሪያ መረጃ እየሰበሰበ መሆኑ ምንጮች አረጋግጠው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የማኀበሩ ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ፣ ገንዘብ ያዥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም እና መስራች አባል ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤልን ጨምሮ በ2006 ዓ.ም. ብቻ 25 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ፤3 የውጭ ዜጎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡


Saturday, August 30, 2014

ስልጠና ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ተማሪዎች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን ማንሳት መቀጠላቸውን ሰልጣኞቹ ገለጹ፡፡

‹‹ለግራዚያኒ ዘብ የቆመው ኢህአዴግ እንዴት ኢትዮጵያዊ ይባላል?››
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) Via ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

• ‹‹ተቃዋሚዎችን እያሰራችሁ እንዴት ተቃዋሚ የለም ትላላችሁ››
• ተማሪዎቹን በፖሊስና ደህንነት እያሸማቀቁ ነው
• ‹‹ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት አገር ሉዓላዊ ልትባል አትችልም››
• ‹‹አንቀጽ 39 ከህገ መንግስቱ ይውጣ››
• ‹‹ለግራዚያኒ ዘብ የቆመው ኢህአዴግ እንዴት ኢትዮጵያዊ ይባላል?
• ተማሪዎቹን በፖሊስና ደህንነት እያሸማቀቁ ነው


ኢህአዴግን ደግፈው የሚከራከሩ ተማሪዎች ቁጥር በማነሱ ፖሊስና ደህንነቶች ሲቪል መስለው እንደሚከራከሩና የሚጠይቁትንና ጠንካራ አስተያየት የሚሰጡትን ተማሪዎች ለብቻቸው እየጠሩ እያሸማቀቁ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ተማሪዎች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን ማንሳት መቀጠላቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ባለፉት የስልጠና ጊዜያት ኢህአዴግን ላለፉት 23 አመታት አይተነው ለውጥ ስላላመጣ ስልጣን ሊለቅ ይገባል፣ የአሰብ ወደብ ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው፣ የሸክ ኑሩ ግድያ ሴራ ነው፣ የባህርዳሩ ግጭት የብአዴን ሴራ ነው የመሳሰሉት ጥያቄዎች መነሳታቸው ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆናቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የህገ መንግስት ማሻሻያ በደብረማርዎስ ከተማ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች ህገ መንግስቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል፡፡

በተለይም አንቀጽ 39 ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ልዩነት ለመፍጠር ህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠ አንቀጽ በመሆኑ ህገ መንግስቱን ለማሻሻል የተቀመጡት ውጣ ውረዶች ሳይገድቡት ከህገ መንግስቱ ሊወጣ ይገባል›› ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹አንቀጽ 39 እንዲሁ ከሚቀየር የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝበ ውሳኔ አድርጎበት ከህገ መንግስቱ ቢወጣም የተሻለ ነው፡፡›› የሚል ሀሳብ ያቀረቡ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ ብሄራዊ ቋንቋ ተማሪዎቹ ‹‹ኢትዮጵያን ያህል አገር ለምን ብሄራዊ ቋንቋ አይኖራትም?›› ብለው የጠየቁ ሲሆን አሰልጣኞቹ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት መሆኑን ተናግረው ከማለፍ ውጭ ለጥያቄው መልስ መስጠት እንደተቸገሩ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹ህገ መንግስቱ ሲረቀቅ የብሄራዊ ቋንቋ ጉዳይ የተረሳው ሆን ተብሎ ነው፡፡ ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት አገር ከሌሎች ብሄራዊ ቋንቋ ካላቸው አገራት ጋር እኩል ሉዓላዊ ልትሆን አትችልም›› ሲሉ አስተያየት መስጠታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ ነው? መጋቢት 6/2005 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ፣ ባለራይ ወጣቶችና በአቶ ታዴዎስ ታንቱ የተመራ የአገር ተቆርቋሪ አካል ለግራዚያኒ የቆመውን መታሰቢያ ተቃውሞ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታቱ ሀውልት ጀምሮ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ የሚያመራ ሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡ ይሁንና ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት ፖሊስ ሰልፉን በኃይል በመበተን ተሳታፊዎቹን ማሰሩ ይታወቃል፡፡

በስልጠና ላይ የሚገኙት ተማሪዎቹም ‹‹ኢትዮጵያውያንን የቀጠፈውን የቅኝ ገዥ ጀኔራል ላይ ተቃውሞ እንዳይነሳ የፈለገና፣ በእሱ ላይ ተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት የሞከሩትን የደበደበና ያሰረው ኢህአዴግ እንዴት ኢትዮጵያዊ ሊባል ይችላል? ኢህአዴግ ለግራዚያኒ ጠበቃ ቆሞ እንዴት ኢትዮጵያዊ ይባላል?›› ይባላል የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹን እያሰራችሁ አሰልጣኞች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ትክክል አለመሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ እንደሌለም ተገልጾአል፡፡ በተቃራኒው ተማሪዎቹ በተቃዋሚዎቹ ላይ የሚደርስባቸውን ጫና እና የታሰሩትንም በምሳሌነት በማንሳት ‹‹ተቃዋሚዎቹን እያሰራች እንዴት ተቃዋሚ የለም ትላላችሁ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ኢህአዴግ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት አቅም እንደሌለውና አፋኝ እንደሆነ የሚገልጹ አስተያየቶችንም ተነስተዋል፡፡ ተማሪዎቹን ማሸማቀቁ ቀጥሏል በተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ጥያቄ እንዳይጠይቁ ማሸማቀቁ እንደቀጠለ ነው ተባለ፡፡ በተለይ በልደታ ግቢ በመሰልጠን ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ጥያቄ ሲጠይቁም ሆነ አስተያየት ሲሰጡ ስለማንነታቸው አላስፈላጊ ዝርዝር ጥያቄዎችን እየተጠየቁ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ኢህአዴግን ደግፈው የሚከራከሩ ተማሪዎች ቁጥር በማነሱ ፖሊስና ደህንነቶች ሲቪል መስለው እንደሚከራከሩና የሚጠይቁትንና ጠንካራ አስተያየት የሚሰጡትን ተማሪዎች ለብቻቸው እየጠሩ እያሸማቀቁ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከአፈናው በተጨማሪ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች የሚሰለጥኑትን ተማሪዎችን በመደለያነት ሙዚቃ፣ ከፍተኛ ወጭ የወጣበት ምግብና የመዝናኛ ምሽቶች እየተደረጉላቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመላ አገሪቱ በስልጠና ላይ ለሚገኙት ተማሪዎች ስልጠና የሚሰጡት ከወራት በፊት በመቀሌ ስልጠና የተሰጣቸው የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡


በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!

ኢትዮጵያዊያንን በዘር እና በሀይማኖት ለያይቶን እርስ በርስ እያጋጨን በመግዛት ላይ ያለውን ወያኔን ለማሸነፍ እና ከምትኩም ከራሷ ጋር የታረቀች፤ ፍትህ የሰፈነባት፤ እኩልነት የተረጋገጠባት እና በኃያላን አገሮች እርጥባን ሳይሆን በራሷ አቅም የምትተማመን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎት መተባበር እንዳለባቸው ሲነገርና ሲወተወት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በህወሓት የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ እና በፓለቲካ ባህላችን ኋላቀርነት ምክንያት እስካሁን የተደረጉ የትብብር ጥረቶች የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ቀድሞ የተደረጉት ጥረቶች የተጠበቀውን ውጤት አለማስገኘት ተስፋ ሳያቆርጠን ከእያንዳንዱ ጥረት ልምድ እየወሰደን የኢትዮጵያዊያን አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ የትብብር ጥረቶችን ማድረግ ያለብን መሆኑ ያምናል። በዚህም መሠረት የትብብር መርህ ነድፎ ትግል ውስጥ ካሉ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲነጋገር እና ሲደራደር ቆይቷል። እንደሚታወቀው የንቅናቄዓችን አበይት የትብብር መርሆች ሁለት ናቸው። መርህ አንድ፣ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገለው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ መሆኑ ማመን ነው። መርህ ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የሚገባው በሕዝብ ነፃ ምርጫ ብቻ መሆኑን መቀበል ናቸው።

ይድረስ ለወዳጄ… (6ኛው ተከሳሽ ዘላለም ክብረት – ከቂልንጦ እስር ቤት – ክፍል ሁለት)

የኔ ፅጌረዳ ሰላም ላንች ይሁን! እንዴት ነሽልኝ? ባለፈው የፃፍኩልሽን ቧልታይ የበዛበት ደብዳቤ አነበብሽው ይሆን? ዛሬ ደግሞ ስለክሴ፣ ስለከሳሼና ስለአጠቃላይ ሁኔታዎች ልጽፍልሽ አሰብኩ፡፡

ዘላለም ክብረት

ግርምቴከታሰርኩበት ሚያዝያ 17/2006 ጀምሮ በጣም ሲገርመኝ የነበረው ነገር የፖሊስ/የመንግስትና የሕግ ታላቅ እኩያ ነው፡፡ መንግስት ሁሌም ሕግን ለማሸነፍ በሙሉ ድል ‹ተጠርጣሪዎ› ለመክሰስ ችሏል፡፡ ከተያዝኩበት ደቂቃ ጀምሮ አውቆ በሚመስል መልኩ የተለያዩ የፍትሕ አካላት እያንዳንዱን የሕግ አንቀፆች በተግባር ሊጥሏቸው ማየቴ ነበር የመገረሜ ምክንያት፡፡ለሕጎቹና ለሕግ አካላቱ ቅርብ በመሆኔ ምክንያት የመንግስት አካላቱ ይወስዷቸው የነበሩትን የተለያዩ ርምጃዎች በሕጉ አይን በማየቴ ሊሆን ይችላል የሕግ ጥሰቱ እጅግ ጎልቶ የታየኝ፡፡

የፍተሸ ፈቃድ (Search Warrant) ከእሰር ማዘዣ (Arrest Warrant) ጋር በአንድ ወረቀት ላይ ተደባልቆ በመምጣቱ ገና ከመታሰሬ ነው የሕጉ ነገር ያሳሰበኝ የጀመረው፡፡ ሕግ ስንማር የፍተሻ ፈቃድ ከእስር ማዘዣ ተለይቶ እንደሚመጣ፣ በፍተሻ ፈቃዱ ላይ ሊፈተሸ የተፈለገው ነገር በግልፅ ሊቀመጥ እንደሚገባ፣ ፍተሻ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መከናወን እንዳለበት …ብንማርም ‹ፖሊስ› በታሰርኩበት ወቅት አንዱንም የሕግ አንቀፅ ላለማክበር ያሰበ በሚመስል መልኩ የፍተሻ ፈቃድን ከእስር ፈቃድ ሳይለይ፣ ፍተሻውን ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ በመጀመር፣ በፍተሻው ምን ማግኘት እንደሚፈልግ የማይገልፅ የፍተሸ ፈቃድ በማሳየትና እኔ ስጠይቅም ለመናገር ፍቃደኛ ባለመሆን… ሕጉን‹ንዶ ንዶ› የኔን የግለሰቡን መብቶች በዜሮ በማባዛት ‹ወንጀልን የመከላከል ርምጃውን› ጀመረው፡፡ በፍተሻ ወቅት የሚፈለገው ነገር ምንነት አለመገለፁም ፖሊስ ‹ለጠረጠረኝ› ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል፣ በዛቻና በአድማ የመናድ ወንጀል እንደ ኤግዚቢት የያዛቸው ‹ማስረጃዎች› ምንነት ይገልጣቸዋል፡፡በፍተሻ ወቅት ፖሊስ ከቤቴ በኤግዚቢትነት ከያዛቸው ‹እቃዎች› መካከል 90 በመቶው ገበያ ላይ ያሉ መጽሐፍት ሲሆኑ ከነዚሀም መካከል የPaulo Coelho “By the river paedra I set down and wept’ PV.I.Lenin ‘what is to be done’ የአፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል፣ የፍቅረስላሴ ወግደረስ ‹እኛና አብዮቱ›… ጨምሮ ሌሎች መፅሀፍት የሚገኝበት ሲሆን፤ የተለያዩ የሙዚቃ ሲዲዎችም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ታስረው ዋሉ ።

ፖሊስ እና ደህንነቶች የተቃዋሚ አመራሮችን በሰበብ አስባቡ ማንገላታቱን ቀጥሏል።በዛሬው እለት የመኢአድ አመራሮች ታስረው መዋላቸውን የድርጅቱ ምንጮች አስታውቀዋል፡፤ አመራሮቹ ለእስር በማያበቃ እና በፈጠራ ክስ አዲስ አበባ ሰራተኛ ሰፈር መግቢያ ከጣይቱ ሆቴል ፊት ለፊት ካለው የወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ከጽ/ቤታቸው ትፈለገላችሁ ተብለው ከተወሰዱ በኋላ ሲያጉሏሏቸው ውለው በዋስ እንደተለቀቁ ተናግረዋል።አመራሮቹ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባን ይመኢአድ ቢሮ ማህተሞች እና ሰነዶች ይዞ እንደጠፋ የሚታወቀው መቶ አልቃ ሃይለማርያም የተባለ ግለሰብ ከደህንነቶች ጋር በማበር ወደ ጽ/ቤቱ ፖሊሶችን በማምጣት ‘ወላሞ ‘ብለው ሰድበውኛል የብሄር ብሄረሰብ መብት በተከበረባት ሃገር …ወዘተ በሚል የፈጠራ ክስ ድርጅቱን እና አመራሮቹን ወደ እስር ቤት አስወስዶ ቃል እንዲሰጡ ያደረገ ሲሆን ማስረጃ ባለመገኘቱ ማስረጃ እስኪመጣብሚል ተለቀዋል። ፖሊስ የተቃዋሚ አመራሮችን በማይረባው እና በምማፈለግ አጋጣሚን እየፈለገ ማንገላታቱን ቀጥሏል።

እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ ተከለከሉ

እነ የሽዋስ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ ተከለከሉ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ መከልከላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ታሳሪዎቹ በሳምንት ሁለት ቀን (ረዕቡና አርብ) በጠበቃቸው እንዲጎበኙ ፈቅዶ የነበር ቢሆንም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ደንበኞቻቸውን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንተው ሳያገኟቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡ ተማም አባ ቡልጉ ወደ ማዕከላዊ ባቀኑባቸው ቀናት ‹‹ሌላ ቀን ታገኛቸዋለህ፣ ስብሰባ ላይ ነን›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እያቀረቡ ቀኑን ሙሉ ሲያስጠብቋቸው እንደነበርና በተለይ በዛሬው ቀን ነሃሴ 23 ደንበኞቻቸውን ለማግኘት እየጠበቁ ከዋሉ በኋላ ‹‹ከፈለክ ችሎት ላይ ታገኛቸዋለህ፡፡ ከዚህ ማግኘት አትችልም›› ተብለው እንደተመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ታሳሪዎች በጠበቃቸው፣ በኃይማኖት አባታቸው፣ በጓደኛና በዘመድ የመጎብኘት መብት አላቸው፡፡ በሳምንት ይህን ቀን ተብሎ በህግ አልተወሰነም፡፡›› በሚል በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው የሚጎበኙት መባሉም ስህተት ነበር ያሉት አቶ ይድነቃቸው ‹‹ጭራሹን እንዳይጎበኙ መደረጉ ደግሞ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገ ወጥ ድርጊት ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Friday, August 29, 2014

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ምን ያህል እንዳከረረ (ክፍል 1) – ግርማ ካሳ

የ «ጌታቸውን » የአቶ መለስን ራእይ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በትጋት እየፈጸሙት እንደሆነ በስፋት እያየን ነው። የአቶ መለስ ራእይ ጭቆና፣ አምባገነንነት፣ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር፣ ሜዲያዉን መጨፍለቅ ነው። የአቶ መለስ ራእይ በእርቅና በፍቅር አገርን ማሳደግ ሳይሆን፣ ማክረር በዜጎችን ላይ መጨከን ነው።
የፍቅርና የሰላም መጽሀፍን (መጽሐፍ ቅዱስን) በየቀኑ አነባለሁ በሚሉት በአቶ ኃይለማሪያም አገዛዝ ግን፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በመለስ ጊዜ ከነበረው በባሰ ሁኔታ በጣም እያከረረ መጥቷል። በርግጥም አቶ ኀያለማሪያም የአቶ መለስስ ፎቶ እየተሳለሙ ቃል እንደገቡት፣ የአቶ መለስን ራእይ በትጋት እያስፈጸሙ ናቸው።
ምን ያህል አገዛዙ እንዳከረረ የሚያሳይ አንድ ጉልህ ማስረጃ፣ በተለይም በሜዴያዉ አንጻር እንዳቀርብ ይፈቀድለኝ። በምንም አይነት ሕወሃት/ኢሕአዴግ እንዲነገርና እንዲጻፍ ከሚፈለገው ውጭ መጻፍ እንደማይቻል እያየን ነው። ኢቲቪ የመሳሰሉቱ ደግሞ እንደ ሰዉ ለሰው ድራማ ያሉትን ከማየት ዉጭ፣ አስቀያሚ ሜዲያዎች ሆነዋል። በጣም አስቀያሚ !!!!! እነ ሪፖርተር፣ አዲስ ፎርቹን የመሳሰሉቱ፣ የአገዛዙ ቱጃሮች ማስታወቂያ የሚያወጡበት፣ በአገዛዙ እየተደገፉ የሚንቀሳቀሱ፣ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ኮድን የማይተገብሩ፣ በአጋር ጋዜጠኖች ላይ የሚደርሰው ግፍ የማይሰማቸውና የማይቆረቆሩ፣ ለይስሙላ የሜዱያ ነጻነት አለ ለማስባል ለአገዛዙ የፖለቲካ ፍጆታ የሚዉሉ፣ በአደርባይነት የተሞሉ ፣ ጋዜጠኖች ሊባሉ የማይገባ ጋዜጦች ናቸው።
በአቶ መለስ ጊዜ የታሰሩ ጋዜጠኖች
1. ርዮት አለሙ (የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ)
2. እስክንደር ነጋ
ከ2002 ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ጊዜ የተሰደዱ ጋዜጠኖች
1. አብይ ተከለማሪያም ( አዲስ ነገር)
2. መስፍን ነጋሽ (አዲስ ነገር)
3. ታምራት ነገራ (አዲስ ነገር)
4. አቤ ቶኪቻው (አዉራምባ ታይምስ)
5. ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ተሰዶ ነበር ፣ አሁን ሰላም ነው ብሎ ተመልሷል
ከ2002 ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ጊዜ እንዳይታተሙ ወይም ክስ የተመሰረተባቸው ጋዜጦች
1. አዲስ ነገር
በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ወደ ወህኒ የተወሰዱ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች (ሁሉም በሽብተኘት የተከሰሱ)
1. ተስፋለም ወልደየስ
2. አጥናፉ ብርሃኔ
3. ዘላለም ክብረት
4. ኤዶም ካሳዬ
5. ናትናኤል ፈለቀ
6. ማህሌት ፋንታሁን
7. አቤል ዋበላ
8. በፍቃዱ ኃይሉ
9. አስማማዉ ወልደጊዮርጊስ
በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኖችና ብሎገሮች
1. ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ( የሎሚ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
2. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
3. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር)
4. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ (የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ)
5. ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)
6. ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)
7. ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
8. አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሮዝ አሳታሚ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ )
9. አቶ ኢብራሃም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ)
10. እንዳለ ተሺና (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ )
11. ሀብታሙ ሥዩም (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ዓምደኛ)
12. ዳዊት ሰለሞን (ታዋቂ ብሎገር)
13. ዘሪሁን ሙሉጌታ ( የሰንደቅ ጋዜጣ ረፖርተር)
በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ሕተመታቸው የተቋረጠ ወይንም ክስ የቀረበባቸው
1. ፍትህ ጋዜጣ
2. ፍኖት ነጻኘት ጋዜጣ
3. የአዲስ ጉዳይ መጽሔት
4. የፋክት መጽሄት
5. የሎሚ መጽሄት
6. የጃኖ መጽሄት
7. የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ


የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መበራከት

መንግሥት በአንዳንድ የግል ጋዜጦች ላይ ክስ ከመሠረተ እና ባለፈው ግንቦትም ዘጠኝ ጋዜጠኞች እና የድረ ገፅ አምደኞች ከታሰሩ ወዲህ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።

ባለፉት ጊዚያት ሀገር እየለቀቁ የወጡት ግን ጋዜጠኞች ብቻ አይደሉም፣ ብዙ ወጣቶችም በተለያዩ መንገዶች መሰደዳቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ያሳያሉ። ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ድርጅት፣ የ«ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ፣ ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ የሚወጡበት ጉዳይ ከሰብዓዊ መብት ጋ የተያያዘ ነው ይላሉ።
ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን በየመን ፣ በኬንያ እና ታንዛንያ፣ እንዲሁም በሱዳን እና በሊቢያ በኩል እያደረጉ አደገኛ በሆነ ጉዞ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ደቡባዊ አፍሪቃ እና አውሮጳ ለመግባት ይሞክራሉ፣ በዚሁ ሙከራቸው ወቅት በየበረሃው እና በየጫካው ወድቀው የሚቀሩት እና ባህር የሚበላቸው ጥቂቶች እንዳልሆኑ እና የሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ሰለባም እንደሚሆኑ በየጊዜው የዜና ምንጮች የሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ያሳያሉ፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት በዚምባብዌ በኩል አድርገው ደቡብ አፍሪቃ የገቡ 24 ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ ስላልነበራቸው በሀገሪቱ ፖሊስ መያዛቸው የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያውያኑ ራሳቸውን ለዚህ ሁሉ መከራ የሚያጋልጡበት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ድርጅት፣ «ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ ገልጸዋል።
« ሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል። የመጀመሪያው፣ መንግሥት ማንኛውንም ትችት ወይም ተቃውሞ በቸልታ የማለፍ ልማዱም ሆነ አሰራር በፍፁም የለውም። እና ከማንኛውም ትችት የሚሰነዝር ቡድን ጋ የሆነ ግንኙነት ካለህ፣ ምንም እንኳን ግንኙነቱ ደካማ ቢሆንም፣ የመንግሥት ክትትል ዒላማ ልትሆን ትችላለህ። ሁለተኛው ደግሞ፣ የፍትሑ አውታር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ነው ፣ እና አንዴ በመንግሥት ክስ ከቀረበብህ ወደ ወህኒ መውረድህ የማይቀር ነው፣ ስለዚህ ብዙዎቹ የረጅም ዓመታት የእስራት ቅጣት እንዳይደርስባቸው መሸሹን መርጠዋል። »

የ«ሲ ፒ ጄይ» ቶም ሮድስ
ለብዙዎች ሀገር እየለቀቁ መውጣት ከሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ቶም ሮድስ በሚቀጥለው ዓመት በሀገሪቱ የሚካሄደው ምርጫ ማበርከቱንም ቶም ሮድስ ይናገራሉ።
« ምርጫ በሚቀጥለው ዓመት ግንቦት ወር ይደረጋል። ይህም፣ ምንጮች እንደነገሩኝ፣ በመንግሥቱ ውስጥ ያሉት ፣ ሥልጣን እንደያዙ ለመቆየቱ ስለሚፈልጉ፣ ሊነሳ የሚችል ማንኛውንም ትችት ለማፈን እየሞከሩ ነው። ተመሳሳይ ሁኔታ ካሁን ቀደም አይተናል። እአአ በ2005 ዓም ተቃዋሚው ወገን ምርጫውን ሳያሸንፍ አልቀረበትም የተባለው ምርጫ ውጤት ክርክር ባስነሳበት ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታ ተመልክተናል። እና ከዚያን ጊዜ ወዲህ እምነት ያጣው መንግሥት፣ በሥልጣን ለመቆየት ሲል ጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን የሲቭል መብት ተሟጋችቾችን እና ጠበቆችንም ጭምር ለመምታት ወደኋላ አላለም። »
ቶም ሮድስ፣ ጋዜጠኞች እና ብዙ ወጣቶችን ከስደት እና በሰበቡ ከሚደርስባቸው መከራ እና ስቃይ ለመታደግ የኢትዮጵያ መንግሥት ፖሊሲውን ሊከልሰው ይገባል ባይ ናቸው።
«መንግሥት አንዳንድ ፣ ለምሳሌ፣ እአአ በ2009 ዓም የወጣውን የፀረ ሽብርን የመሳሰሉትን ሕጎች ዳግም ማጤን ይኖርበታል። ፖሊሲውን በጥሞና ስንመለከተው፣ በሀገሪቱ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ፍትሓዊ አሰራር የተጓደለበት ሁኔታ ሰዎች በሕጉ ሥርዓት ላይ እምነት እንዳያድርባቸው አድርጓል። ይህ ባይሆን ኖሮ ብዙ ሰው ሀገር እየለቀቀ ሲሸስ ባልታየ ነበር። እርግጥ፣ ጉዳዩ የተወሳሰበ ነው። የሀገሪቱ መንግሥት ልማትን በተመለከት ጉልህ መሻሻል አድርጓል። በዚህም የተነሳ በኤኮኖሚ ምክንያት መውጣት የሚገደዱት ኢትዮጵያውያን በጣም ትንሽ ነው። ይሁንና፣ የልማቱ እንቅስቃሴ የሚደረገው ለሰብዓዊ መብት መከበር ትኩረት ሳይሰጥ ነው። ይህም ሰዎች ሀገራቸውን እንዲወጡ ያስገድዳል። መንግሥት የሚሰራበት የመሬት መቀራመትን ፖሊሲ ምን ያህል ብዙ ወጣቶችን እንደሚነካ መመልከት ይበቃል። »

የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብቱን ይዞታ እንዲያሻሽል እና የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚገባ ድርጅታቸው በተደጋጋሚ ቢያሳስብም፣ እስካሁን ይህ ነው የሚባል የረባ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል ግፊት ባለማሰረፉ ቶም ሮድስ አልተደሰቱም።
« በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሰራር ብዙ ጊዜ ቅር ተሰኝቼአለሁ። ምክንያቱም የሚናገሩት እና የሚያደርጉት የተለያየ ነውና። እና ለምሳሌ ዩኤስ አሜሪካ እና ብሪታንያን የመሳሰሉ ዓበይት ለጋሽ ሀገራት ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡት ያቀዱትን ግዙፍ ርዳታ፣ የሰብዓዊ መብት ይዞታን ከግንዛቤ ሳያስገቡ ሊሰጡ አይገባም። »
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ


ኢትዮጵያ አስገዳጁን ውል ከግብጽና ሱዳን ጋር ተፈራረመች

ኢሳት ዜና :-የግብጽ ጋዜጦች እንደዘገቡት ኢትዮጵያ ለወራት ውድቅ ስታደርገው የነበረውን ስምምነት ከግብጽ ጋር
ተፈራርማለች። አዲሱ ስምምነት የአባይ ግድብ ግንባታ በውጭ አገር ገለልተኛ አጥኚዎች እንዲጠናና ኢትዮጵያም የጥናቱን ውጤት እንድታከብር የሚያስገድድ ነው።
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሲደራደሩ የቆዩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ከወራት በፊት ሱዳን ላይ ተካሂዶ በነበረው የሰላም ስምምነት ላይ
ግብጽ ግድቡ በውጭ አገር ባለሙያዎች እንዲጠና ያቀረበቸውን አጀንዳ ውድቅ ማድረጓን ገልጸው ነበር። ኢትዮጰያ ግድቡ ከመጀመሩ በፊት በቂ ጥናት እንደተካሄደበት
እንዲሁም ገለልተኛ አካል አጥንቶ ችግር እንሌለበት መግለጹን ስታስረዳ ቆይታለች። ይሁን እንጅ ሰሞኑን በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ በፊት የያዘቸውን አቋም ቀይራ
በግብጽ አቋም በመስማማት አስገዳጅ ውል ፈርማለች። ውሉ የግድቡ ግንባታ ሳይቋረጥ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ሲሆን፣ አዲሱ አጥኚ ቡድን ግድቡ በግብጽ ላይ ችግር ያስከትላል
ብሎ ካመነ ኢትዮጵያ የግድቡን ዲዛይን ለመቀየር ትገደዳለች።
ኢትዮጵያን ይህን አስገዳጅ ውል ለመፈረም ምን እንዳስገደዳት በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።


የጋዜጣ አዙዋሪዎች ስራ ሊያቆሙ ነው

ኢሳት ዜና :-በቅርቡ መንግስት በፋክት፣ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ እንቁ፣ ጃኖ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ፍትህ ሚኒስትር ክስ መመስረቱን ተከትሎ ሚዲያዎቹ ከህትመት በመውጣታቸው ምክንያት ስራ ሊያቆሙ መሆኑን የጋዜጣ አዙዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ሳሪስ፣ ቦሌና ካሳንቺስ የሚገኙ የጋዜጣ አዙዋሪዎች በርካታ አንባቢ የነበራቸው መጽሄቶችና ጋዜጦች ከገበያ በመውጣታቸው፣ ሌሎቹን ጋዜጦችና መጽሄቶች በማዞር ህይወታቸውን መምራት ስለማይችሉ የጋዜጣ ማዞር ስራቸውን አቁመው ሌላ ስራ ለመፈለግ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይ በስርጭት ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው የነበሩት ፋክት፣ አዲስ ጉዳይና ሎሚን በመሸጥም ሆነ በማከራየት አብዛኛውን ገቢያቸውን ያገኙ እንደነበር የገለጹት የጋዜጣ አዙዋሪዎች አሁን ያሉትን ጋዜጦችና መጽሄቶች በህዝቡ ዘንድ እምብዛም ተነባቢ ባለመሆናቸው በዚህ ስራ ህይወታቸውን መምራት እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡ የፍትህ ሚኒስትር ሚዲያዎቹን ከከሰሰ በኋላ ማተሚያ ቤቶች ቀሪዎቹን ጋዜጦችና መጽሄቶች አናትምም በማለታቸው በርካታ ሚዲያዎች ከገበያ መውጣታቸው ጋዜጣ አዙዋሪዎቹ ስራ እንዲያጡ ምክንያት መሆኑ ተገልጾአል፡፡

አዙዋሪዎቹ በእነዚህ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ ከመወሰዱ በፊትም ቢሆን ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በመሆናችሁ የእነሱን አቋም የሚያንጸባርቁ ጋዜጣና መጽሄቶች ለህዝብ እንዲደርስ እያደረጋችሁ ነው፣ ከአጥፊ ኃይሎች ጋር እየተባበራችሁ ነው›› በሚል እርምጃ ይወሰድባቸው እንደነበርና አሁን በመጽሄትና ጋዜጦች ላይ የተወሰደው እርምጃ ሰርተው መኖር እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው መግለጻቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
የእነዚህ ሚዲያዎች በመዘጋታቸው የገቢ ምንጫቸውን ከማጣታቸው በተጨማሪም በሚዲያው ላይ የተወሰደው እርምጃ በእነሱም ላይ የማይወሰድበት ምክንያት እንደሌለ ባለፉት ጊዜያት የደረሰባቸው በደል ማሳያ መሆኑን በመግለጽ ስራውን ሊያቆሙ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ከወራት በፊት ገዥው ፓርቲ የሚቀጥለው ምርጫ ተከትሎ ሚዲያዎች ወደ ክፍለ ሀገር እንዳይደርሱ አከፋፋዮችንና አዙዋሪዎችን በማደራጀት ሚዲያዎችን ከስራ ለማስወጣት እንዳቀደ መገለጹ ይታወቃል፡፡


Thursday, August 28, 2014

ሰበር ዜና የኢትዮዽያ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲውዲን አለማቀፍ ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው።

አስራሦስት የኢትዮዽያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የጦር መኮንኖች በሲዊዲን አለም አቀፍ የጦር ፍርድቤት ተከሰሱ።
እነሱም
1-አርከበእቁባይ
2-በረከት ስምሆን
3-አባዱኣ ገመዳ
4-ሳሞራ የኑስ
5-አባይ ፀአዬ
6-አሰፋ
7-ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ
8-አሰን ሺፋ
9-ሙሉጌታ በርሄ
10-ነጋ በርሄ
11-ወርቅነህ ገበየው
12-ኮማንደር ሰመረና አንድ ስማቸው ያልተገለጠ ሰው በግድያ፡ አስገድዶ መድፈር በስቃይ፡ ሰዎችን በማንገላታት፡ በህገወጥ ሁኔታ በማሰር ፡በሙስና ክስ ቀርቦባቸዋል።


ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተማሪዎች መታሰራቸውን ተገለጸ

ኢሳት ዜና :-የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በተለያዩዩኒቨርስቲዎች የተጀመረውን የፖለቲካ ስልጠና ተከትሎ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ከ100 በላይ እንዲሁም ከወለጋ የኑቨርስቲ 5 ተማሪዎች ታፍነው ተወስደዋል። የፖለቲካ ስልጠናው አጀንዳ የአገር አንድነት የሚል አላማ ቢኖረውም ፣ በተግባር እየታየ ያለው ግን ተማሪዎችን እየለዩ ማሰር ነው ነው ብሎአል።

ከአምቦ ዩኒቨርስቲ የተያዙ ተማሪዎች ሰንቀሌ እየተባለ ወደ ሚጠራ እስር ቤት ተወስደዋል። ተማሪዎቹ ስለ አገር አንድነት ከመነጋጋር በፊት በቅርቡ ጓደኞቻቸውን የገደሉ ፖሊሶች ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። ከአራት ቀናት በፊት ደግሞ 5 የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች 4866 ኢቲ የሚል ታርጋ ባለው መኪና ተጭነው መወሰዳቸውንና እስካሁን ድረስ ያሉበት ቦታ አለመታወቁን የሰብአዊ መብት ሊጉ ገልጿል። በኢሉ አባቦር ዞን ፣ በዶራኒ ወረዳ ፣ ኢሊሞ ቀበሌ ደግሞ ከ10 ቀናት በፊት ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጾ፣ ዋቅቶላ ጋርቤ፣ ሲሳይ አማና፣ ቲኪ ሱፋ፣ ኢታና ዳጋፋ፣ ባድሩ ባሻ ፣ ከማል ዛሊ፣ ራሺድ አብዱ ፣ ዘትኑ ዋቆ፣ ዳጋፊ ቶሊ፣ አዳም ሊቂዲ፣ ኢንዱሽ መንግስቱ፣ ዲቢሳ ሊባንና ኦፍታ ጂፋር የተባሉት ነዋሪዎች በኢሊሞ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ ብሎአል።

ባለፈው ሚያዚያና ግንቦት ወር በክልሉ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በሽዎች ከታሰሩት መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት በአካባቢ ፍርድ ቤቶች እንዲፈቱ ውሳኔ የተላለፈ ቢሆንም፣ የመንግስት ባለስልጣኖች ጣልቃ በመግባት እንዳይፈቱ ማድረጋቸውን የገለጸው ሊጉ፣ በደምቢ ዶሎ 64 ፣ በአምቦ 10፣ በሲቡ ሲሪ እና ዲጋ ወረዳዎች ደግሞ 40 እስረኞች እንዲፈቱ ትእዛዝ ቢተላለፍም ፣ የወረዳ ባለስልጣኖች ውሳኔውን ሽረውታል። አንዳንዶች ከፌደራል በመጡ ባለስልጣናት ከ6 እስከ 10 አመታት የሚቆይ ፍርድ እንደተፈረደባቸው፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ለእስረኞች ጥብቅና የቆሙ ጠበቆች ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽመውን ከፍተኛ የሰበአዊ መብት ጥሰት እንዲያቆም አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና መንግስታት ጫና እንዲያደርጉ በመግለጫው አመልክቷል። በታሰሩት ዙሪያ መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።


Wednesday, August 27, 2014

ሙስና ለሶስት የሰነጠቃቸው ቡድኖች

ወያኔ ኢህአዴግ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ላይ ፊጥ ካለ ድፍን 23 ዓመት ቆጠረ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ በአንቀልባ አዝሎ ለሥልጣን ያበቃው ዛሬ አምርሮ የሚጠላው ሻዕቢያ ነው፡፡ ወያኔ እና ሻዕቢያ ውሃ በወንፊት እንቅዳ ባሉበት የፍቅር ዘመን እነኢሳያስ አፈወርቂ ኦፊሻል ባልሆነ መንገድ ጥሬ ሥጋ ለመቁረጥ በየሳምንቱ አዲስአበባ ይመላለሱ እንደነበር የቅርብ ሰዎች የሚያስታውሱት ነው፡፡ወደ ሰሞነኛ ጉዳይ እንመለስ ጄኔራል ባጫ ደበሌ አሜሪካን ሀገር ቤት ገዛ የሚል ገራገር ዜና ሰሞኑን በማህበራዊ ድረገጾች ሳነብ አባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል ብዬ በውስጤ አጉተምትሜያለሁ፡፡ የሌባው ቡድን መስረቅን እንደመብት ቆጥሮ በአዲስአበባ ከተማ ቀብረር ያለ ህንጻ በዘመድ አዝማዱ ሰም ሲገነባ ትንሽ እንኳን ሼም እንደሌለው ስትታዘብ ጄኔራሉ በአድራጎቱ አፍሮ ትንሽ ራቅ፣ ደበቅ ለማለት የመፈለጉን ነገር ታመሰግናለህ፡፡ የሌባው ቡድን 5ሺ ብር የማትሞላ ወርሃዊ ደመወዝ ይዞ ልጆቹን በውጪ ሀገር ውድ ት/ቤት ጭምር ሲያስተምር፣ ሚስቱ የሚሊየን ብሮች መኪና ስታሽከረክር፣ ባለቅንጦት ቪላ ገንብቶ ሲንጎማለል ስታይ ጄኔራሉ አንድ ቤት ቢገዛ ታዲያ ምን ይጠበስ ልትል ትችላለህ፡፡ እናም የመከላከያ ወታደሮችን ይጭነቃቸው እንጂ ጄኔራሎቹማ ዛሬ ቢጠሩዋቸው የማይሰሙ ቱጃሮች ሆነዋል፡፡ የሚገርመው ግን እነዚህ ጄኔራሎች ነገ ጥቅማቸውን የሚነካ ነገር ቢመጣ ብረት ላለማንሳታቸው ልማታዊ መንግሥታችንም እንኳን እርግጠኛ መሆን አለመቻሉ ነው፡፡ ኢህአዴግ ነፍሴም «ሙስናን እንዋጋለን» በሚል መፈክር ታጥሮ የሚኖረው ለዚህ ሳይሆን ይቀራልን?!በአሁን ወቅት ገዥያችን ኢህአዴግ ለሶስት የመሰንጠቅ አዝማማያ እየታየበት ይገኛል፡፡ቡድን አንድ የደረጀው የሌባ ቡድንን ያቀፈ ነው፡፡ ይህ ቡድን ከፍተኛ መንግሥታዊ ሥልጣኑን የተቆጣጠረ ስለሆነ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ማንኛውንም የኃይል እርምጃ የሚወስድ፣ ጥቅሙ ሲነካ ወይንም ይነካል ብሎ ሲሰጋ ሰዎችን የሚያስር፣ የሚያሳድድ የጨካኞች ስብስብ ነው፡፡ እስከታችኛው ድረስ የራሱ መዋቅር የዘረጋና ብዙ ጀሌዎች ያሉት በመሆኑ ተጽእኖው የሰፋ ነው፡፡
ቡድን ሁለት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በአንድ ወቅት እንዳመነው ነገ ይቀናኝ ይሆናል ብሎ የተቀመጠ ተስፈኞች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የሌባው ቡድን ስላላስጠጋው አምርሮ እየተቃወመና ብሶቱን እየገለጸ ያለና እንደእስስት ገላውን የሚቀያይር ቡድን ነው፡፡ በተመቸው ጊዜ የሚደግፍ፣ ያልተመቸው ሲመስለው የሚቃወም እበላ ባይ የአደገኛ ሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ቡድን በአመዛኙ በታችኛው እርከን ላይ ተከማችቶ የሚገኝ በመሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማባባስና በማወሳሰብ ዘወትር ቢወቀስም ምንም ለውጥ ማምጣት ያልቻለ ነው፡፡
ሶስተኛው የኢህአዴግ አባልም ደጋፊም ሆኖ እውነተኛ ዜጋ ሲሆን ሁለቱን ወገኖች የሚጠላ፤ ግን ተጋፍጦ ለመታገል አቅምና ድፍረት ያጣ ነው፡፡በሒደት አንዱ ነጥሮ መውጣቱ የማይቀር ነው፡፡
( የእኔ የለጣፊው አስተያየት- አጠቃላይ ድርጅቱ የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም

የሰማሁት ለጆሮ ይዘገንናል አርአያ ተስፋማሪያም

ከአንድ ሰው ጋር ለረጅም ሰአት አወራን። ይህ ኤርትራዊ (ያደገው ኢትዮጵያ ነው) ከነወ/ስላሴ፣ መላኩ ፈንታ፣ ገ/ዋህድ ..ሌሎች ጋር “ኔትዎርክ” እያለ የሚጠራው የዘረፋ ቡድን አባል ነበር። የዘረፋው ዋነኛ መሪዎች፣ የኋላ ደጀኖችና የጥቅም ተካፋዮች ከሆኑት አዜብ መስፍንና በረከት ስሞኦን ይጠቀሳሉ። ለ15 አመት እንዴት አገሪቷን እንደተቀራመቷት ሲናገር መስማት ይዘገንናል። የሚገርመው መለስ ዜናዊ በሚገባ ይህን የዘረፋ ኔትዎርክ አሳምረው ማወቃቸው ነው። ከአንድ ባለስልጣን በቀር ሁሉም እስከአንገቱ በሙስና ተጨማልቋል፣ በሃብት ደልቧል ይላል። በቀድሞ የኮሜኒኬሽን ሚ/ር የተፃፈውን መፅሐፍ በተመለከተ ሲናገር « ስለዘረፋ ሩብ ያክል አልተፃፈም። እንዳውም አልፃፈም ማለት እችላለሁ። መጠነ ሰፊና ተከታታይ መፅሐፍ ሊወጣው የሚችል ዘረፋ (ሙስና) ተፈፅሟል፤ ገ/ዋህድ ቤት የተገኘው የሚሊዮኖች ኖት ሁሉም ባለስልጣን ዘንድ መጠባበቂያ ተብሎ የሚቀመጥ በመሆኑ አይገርምም። ዋናው ገንዘብ እኮ አልተነካም! የሁሉም ባለስልጣን ገንዘብ አገር ውስጥ የለም..» ይላል።

ይህ ኔትዎርክ እንዲበጣጠስ የተደረገው በበረከት ስሞኦን ሲሆን ይህን በማድረግ ስልጣናቸውን ታድገዋል ሲል ያክላል። ..አሜሪካ ሸሽቶ የመጣው ይህ ሰው ለረጅም ሰዓታት ያወጋኝን በጥቂት ገፆች ፅፌ የምጨርሰው አይደለም። ከዚህ ይልቅ በኢሳት ወጥቶ ቢናገር ሁሉም ወገን የዝችን አገር መሪዎች ጉድ ሊያውቅ ይችላል ብዬ አስብኩ። አንዳንድ የሚጨርሳቸው ጉዳዮች ስላሉ እነሱን ካስተካከለ በኋላ በሚዲያ እንዲወጣ ለማድረግ ይሞከራል።


ሀገሬን ትቸ የትም አልሰደድም!! አንዱአለም አራጌ

Gashaw Mersha
ዛሬ ጧት ከጓደኞቼ ጋር በመሆን ታላቁን የነጻነት ታጋይ አንዱአለም አራጌን፤ብዕሩ የማይነጥፈውን የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠዬቅ ወደ ቃሊቲ ማጎሪያ ቤት (እነሱ ማረሚያ ቤት ይሉታል(በነገራችን ላይ እስክንድር ምኑ እንደሚታረም አይገባኝም)) ተጉዘን ነበር፡፡ ልብስ ለማስወለቅ ምንም የማይቀረውን ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ ከውጭ ሲያዩት የሲኦልን ሽንቁር የመሰለው ማረሚያ ቤት ጋር ስንደርስ እስክንድር ነጋ በምትሃታዊው ፈገግታው በጥቁር ኮፍያ ታጂቦ ጠበቀን፡፡ አንዱአለም የተደራረበ ቱታ አድርጎ ከእንቅልፉ ተነስቶ የመጣ ይመስል ነበር፡፡ እስክንድር በውብ ፈገግታው ደምቆ ‹‹እስክንድር እባላለሁ›› ብሎ ሲጨብጠኝ እልህ የተቀላቀለበት ሳቅ ሳቅኩ፡፡ ኧረ አውቅሃለሁ አልኩት በትህትና፡፡ እንዴት ብዬ እስክንድርን አለማወቅ እችላለሁ፡፡ ሰላምታ ተለዋውጠን ወደ አንዱአለም ዞርን፡፡ የፋክት መጽሄት አምደኞቹ ሙሉነህና ዳዊት እስክንድር ጋር በጋዜጠኛ ቋንቋ ማውራት ሲጀምሩ እኔና ጓደኞቸ በፖለቲከኛ ቋንቋ አንዱአለም ጋር ማውራት ጀመርን፡፡ ስለ ሰሞኑ የጋዜጠኞች ስደት፤ስላለው የፖለቲካ ትኩሳት እንደ አቅሚቲ አወራነው አንዱአለምን፡፡ ስለ ስደት ስናወራ አንዱአለም እንዲህ ሲል በኩራት ነገረን፡፡ ‹‹እኔ ሀገሬን ለቅቄ የትም አልሰደድም፤ መሞት ካብኝም ከእውነቴና እምነቴ ጋር እዚሁ እሞታለሁ›› አለን፡፡ ስደት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል አጽንኦት ሰጥቶ ተረከልን፡፡ ‹‹እኔ ወደ አንድነት ስመጣ ሊያስሩኝ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነበርኩ›› ይላል አንዱአለም፡፡ ራስ ወዳድነት እስካልጠፋ ድረስ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው ሲል ስለሚከፈለው መስዋዕትነት ተረከልን፡፡ ልጆቹንና አፍላ ትዳሩን ትቶ ለእድሜ ልክ እስራት የተዳረገው አንዱአለም ምንም የጸጸት ስሜት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀብታቸውን በግልጽ እንዲለዩ የዓለም ባንክ አሳሰበ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት ተከፍሎ የተፈጠሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ሀብታቸውን በግልጽ ለይተውና ተካፍለው የየራሳቸውን የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ የዓለም ባንክ ማሳሰቡን ምንጮች ገለጹ፡፡

የዓለም ባንክ ማሳሰቢያውን የሰጠበት ምክንያት ለአገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት (Grid) ማጠናከሪያና ማስፋፊያ የሰጠው ብድር በአግባቡ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን ለማረጋገጥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

እ.ኤ.አ. በግንቦት 2012 የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የ200 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል፡፡

በስምምነቱ መሠረት የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ፈጻሚ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መሆን የጀመረው እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2013 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ሥራው ከተጀመረ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ለሁለት በመክፈል ራሳቸውን የቻሉ ሁለት ተቋማትን ፈጥሯል፡፡ የተፈጠሩት ሁለት ተቋማት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ናቸው፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ መዘጋጀቷ ተሰማ

ኢትዮጵያ በተዘዋዋሪ መሸጡ አያሳስበኝም አለች

የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ለመግዛት ከተስማማው አንድ መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ መጠኑ ይፋ ያልተደረገ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡

የሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ ኩባንያን ዋቢ ያደረገው ኢነርጂ ቢዝነስ ሪቪው ድረ ገጽ ባስነበበው ዘገባ መሠረት፣ በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል ከከሰላ ግዛት ተነስቶ ወደ ኤርትራ የሚዘረጋ የ45 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋት ተጀምሯል፡፡

ያልተገራው ገሪ …. ኢቲቪ

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ አገራት ነጻነታቸውን አግኝተው የዓለም ቀጣይ ኃያል አገራትን ተቀላቅለዋል፡፡ አብዛኛው የዓለም ማህበረሰብ ዴሞክራሲያዊ በሆኑ ስርዓቶች ለመተዳደር እድል አግኝቷል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ግን ስልጣን ከያዘ ማግስት በህግ ፈቀድኩት ያለውን የሚዲያ ነጻነትን ጨምሮ በማፈን፣ በዛው በርሃ ውስጥ በነበረው ‹‹ውርጋጥነቱ›› ቀጥሏል፡፡ አሁንም ቢሆን ‹‹ሲቪል›› ነኝ ብሎ የሚያስበው በአፈሙዝ ነው፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራትነቱን እያስወራ በተግባር ግን የአምባገነኖች ቁንጮ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአጠቃላይ በርሃ ከነበረበትም በባሰ አሁንም እንዳፈተተው በኢትዮጵያውያን ላይ ስልጣኑን የሚያስጠብቅለትን እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ኢህአዴግ አልተገራም፡፡

እንዲያም ሆኖ ግን ሌሎቹን ስለ መግራት ያወራል፡፡ ትናንትና ማታ (ነሐሴ 19/2006) በልሳኑ ያሳየው ‹‹ያልተገሩ ብዕሮች›› የተሰኘ ፊልም የሚያሳየውም ይህንን ከአለ-አቅም መንጠራራትን ነው፡፡ ኃይሌና ገና በጋዜጠኝነት ተመረቁ የተባሉ ወጣቶች የእነ ፕሮፌሰር መስፍንን፣ የእነ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራን፣ የእነ ተመስገን ደሳለኝን፣ የእነ ዓለማየሁ ገላጋይን ብዕር ‹‹ሊገሩ›› ሲፍጨረጨሩ ማየት በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡

Tuesday, August 26, 2014

ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞንም ተሰደደ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰሞኑን በጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከብ ተከትሎ በርካታ ጋዜጠኞች ከአገር መውጣታቸው ይታወሳል። በተለይም ገዢው አካል በአምስት የፕሬስ ውጤቶች፣ ሎሚ፣ አፍሮ ታይምስ፣ እንቁ፣ አዲስ ጉዳይና ጃኖ ፕሬሶች ላይ ግልጽ የሆነ ህገ ወጥ ጥቃት እያደረሰባቸው በመሆኑ አስራ አንድ ጋዜጠኞች አገር ለቀው ለመሰደድ በቅተዋል። አሁን ደግሞ ሌላኛው እና 12ኛው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአገር ለመውጣት መገደዱን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ ከላከው መረጃ ለማወቅ ችለናል።

ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን በተለይ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ይደረጉ የነበሩ ሰላማዊ ሰልፎችን በመከታተል የጽሁፍ እና የፎቶ ዘገባ በማቅረብ የሚታወቅ ጋዜጠኛ ነው። ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ባለፈው እሁድ አትላንታ ከሚገኘው ማህደረ አንድነት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “በቀጣይ እርምጃ ሊወስዱብኝ እንደሚችሉ መረጃ ስለደረሰኝ ከአገር ለመውጣት ተገድጃለሁ።” በማለት ገልጿል። (ሙሉውን ቃለ ምልልስ እንደደረሰን እናቀርባለን)

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማዋከብ፣ በማሰር እና ለስደት በመዳረግ ከአለም አስር መጥፎ አገሮች ተርታ የተመደበች መሆኗን የሲ.ፒ.ጄ እና ሌሎች የፕሬስ ተቋማት ደጋግመው ይገልጻሉ።

ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞንን በቀጥታ በማግኘት መርዳት ለምትፈልጉ የኢሜይል አድራሻው dawit341@gmail.com መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናሳውቃለን።

በትግራዮች እና በአፋሮች መካከል በተነሳ የድንበር ይገባኛል ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተዘገበ

(ዘ-ሐበሻ) አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአፋር ክልል በሰሜን ዞን በኮናባ ወረዳ ነዋሪዎች እና በትግራይ ክልል የአፅቢ ወንባርታ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል ግጭት የተቀሰቀሰ ሲሆን እስካሁን የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል።
(የሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያን የሚያስ ተዳድርበት ካርታ)
(የሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያን የሚያስ ተዳድርበት ካርታ)

አኩ ኢቢን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ ባደረሰው መረጃ በኮናባ ወረዳ የዋህደስ ቀበለ አፋሮችና በአፅቢ ወረዳ ኦሳት ቁሼት ከ1 አመት በፊት የድምበር ይገባኛል ያለመገግባባት የነበረ መሆኑ በተደጋጋሚ የተዘገበ ሲሆን ዛሬ ከሳዓት በኋላ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 8:30 ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ግጭት ላይ ይገኛሉ።
በድንበር ይገባኛል ግጭት የተነሳ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከዚህ ቀደም ንጹሃን ዜጎች ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን አሁንም በአፋሮች እና በትግራዮች መካከል የተነሳው ግጭት ሥርዓቱ የፈጠረው የዘረኝነት አስተዳደር ውጤት ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።
ለዘ-ሐበሻ መረጃውን ያደረሰው አኩ ኢቢን ኮናባ መተው እየተዋጉ ያሉት የወታደር ልብስ የለበሱ የሚሊሻ አባላት ናቸው ሲል እስካሁን በዚህ ግጭት 1 ሰው ሲሞት 2 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ብሏል። በሞተው ሰው ጉዳይ ዘ-ሐበሻ ከመንግስት ወገኖች ለማጣራት ያደረገችው ጥረት ባይሳካም የድንበር ግጭቱን ለማብረድ ከመንግስት በኩል እየተደረገ ያለው ዝግመተኛ ሥራ የአካባቢውን ነዋሪዎች እንዳስቆጣ ምንጮች ገልጸውልናል።
በዚህ ግጭት ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን።


የደቡብ ጎንደር የመኢአድ ዋና ጸሃፊ ባልታወቁ ሰዎች ታፍነው ተወሰዱ

ኢሳት ዜና :-የመኢአድ የሰሜን ጎንደር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት ለኢሳት እንደገለጹት

የደቡብ ጎንደር ዋና ጸሃፊ አቶ ጥላሁን አድማሴ ባለፈው ቅዳሜ 8 ሰአት ላይ በ6 ፌደራል ፖሊሶች ታፍኖ መወሰዱን ገልጸዋል።

ፖሊሶቹ መሳሪያ አለው በሚል ፍትሻ አድርገው የነበረ ቢሆንም ምንም አለመገኘታቸውንና አቶ ጥላሁንን ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዳቸውን  አቶ ዘመኑ

ገልጸዋል።

በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር እየደረሰ ያለው ግፍ በዚህ አያበቃም ያሉት አቶ ዘመነ፣ በጭልቃ ወረዳ ሰብሳቢው 3 አመት ተወስኖበት በይግባኝ እንዲፈታ

መደረጉን፣ ሊሞ ከምከም ወረዳ ይፋግ ከተማ ላይ ሞላ ወረታ የተባለ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ተደብድቦ መገደሉን፣ አርባያ ከተማ ላይ ሞላ የሚባል

የድርጅት ጉዳይ ሃለፊ መታሰሩን፣ የደቡብ ጎንደር ሰብሳቢ ቤታቸው ፈርሶባቸው መግቢያ ማጣታቸውን እንዲሁም እርሳቸውን እየተከታተሉዋቸው መሆኑን

ገልጸዋል።የፓርቲው አባላት መንግስት የሚያከፋፈልውን ስኳር እና ሌሎች እርዳታዎችን እንዳያገኙ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

አቶ ዘመነ እንደሚሉት መኢአድ በአካባቢው ከፍተኛ ህዋስ መመስረቱና ገዢው ፓርቲ በመጪው ምርጫ እንደማያሸንፍ በመረዳት እየወሰደ ያለው እርምጃ

ነው ብለዋል።


የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ራሳቸውን እያገለሉ ነው

ኢሳት ዜና :-የኮንዶምኒየም ቤቶች በወቅቱ ዕጣ ወጥቶ ለሕብረሰቡ ማስተላለፍ ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ ቆጣቢዎች

በመሰላቸትና ተስፋ በመቁረጥ ከፕሮግራሙ ራሳቸውን እያገለሉ መሆኑ ተሰምቷል።

የአዲስአበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቱ ሰዎች በተለያየ ምክንያት እየለቀቁ መሆኑን አምነው ነገር ግን ከተስፋ መቀረጥ

ጋር እንደማይገናኝ ለመንግሥት መገናኝ ብዙሃን አረጋግጠዋል፡፡ እንደእሳቸው ገለጻ በድጋሚ ከተመዘገቡ 993ሺህ የኮንዶምኒየም ፈላጊዎች መካከል 7ሺ ያህሉ

በገዛ ፈቃዳቸው ፕሮግራሙን በማቋረጥ የንግድ ባንክን የቁጠባ ደብተር መልሰዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከቁጠባ የተሻለ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከያዛቸው ፕሮግራሞች አንዱ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቁጠባ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎም የአዲስአበባ ከተማ

አስተዳደር ከአንድ ዓመት በፊት በድጋሚ ባካሄደው የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ መሠረት ተመዝጋቢው በየወሩ የተወሰነለትን ገንዘብ በንግድ ባንክ በኩል

እንዲቆጥቡ፣ ይህን መቆጠብ ያልቻሉ የቤት ባለቤት መሆን እንደማይችሉ በደነገገው መሠረት በርካታ ነዋሪዎች ገንዘብ ማስቀመጥ ጀምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ቤቶቹ

መቼ እንደሚተላለፉ አለመታወቁ፣ ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ቀድሞ የገባውን ቃል ማለትም ቤቶቹ የሚተላለፉት በዕጣ ብቻ ነው የሚለውን በሚሸረሽር መልኩ

ለፖለቲካ ዓላማው ሲል ቤቶቹን አንዴ ለመንግሥት ሠራተኛች  ሌላ ጊዜ ለሹማምንቱ ቅድሚያ እሰጣለሁ በማለት በፈለገው ጊዜ እያነሳ የሚሰጥበት አሰራር መስፈኑ

ቆጥቤ የቤት ባለቤት እሆናለሁ የሚለው ተስፋ እንዲጨልም ማድረጉን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች ቤቱን ላላገኝ የመንግሥት ፕሮፖጋንዳ መሳሪያ አልሆንም በሚል ከቁጠባው በመሸሽ ላይ ሲሆኑ የተወሰኑት ደግሞ ጨርሶ ከፕሮግራሙ

ራሳቸውን ማግለል መጀመራቸው ታውቋል፡


የዋጋ ንረቱ አለመረጋጋት ከፍተኛ አመራሩን ውጥረት ውስጥ ከቷል

ኢሳት ዜና :-ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ መደረጉ ከተነገረ  በኃላ ይበልጥ የተባባሰውንየዋጋንረትለማስታገስመንግሥትእየወሰዳቸውያሉትየሃይልእርምጃዎችውጤትባለማምጣታቸውከፍተኛአመራሩውጥረትውስጥ
ከመወደቁጋርተያይዞአምራች፣አስመጪናአከፋፋይነጋዴዎችዋጋአለመጨመራቸውንለሕዝብእንዲናገሩ እየተገደዱ ነው።
በሰኔ ወር አጋማሽ የሲቪል ሰርቪስ ቀን ሲከበር ከአንድ ዓመት በላይ ተጠንቶ የዋጋ ንረት በማያስከትል መልኩ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉ በጠ/ሚኒስትርኃ/ማርያምደሳለኝከተነገረበሃላበዋናነትበሸቀጦች፣በምግብናበቤትኪራይዋጋላይከፍተኛንረትመከሰቱየመንግሥትን ጭማሪ ዋጋቢስነት ያሳየ ከመሆኑም በላይተ አማኒነቱንም
ጎድቶአል፡፡

በተለይየጭማሪውመጠንእጅግዘግይቶሲነገርገዥውፓርቲበራሱአባሎችናደጋፊዎችጭምርእየተተቸመምጣቱከፍተኛአመራሩንአደናግጦአል፡፡በዚህም መደናገጥ

በየመንደሩየሚገኙተራሱቆችንከማሸግናነጋዴዎችን ከማሰርጀምሮበራዲዮናበቴሌቪዥንነጋዴውንየማጥላላትናየማስፈራራትስራዎችንሲያከናውንየቆየቢሆንም

የዋጋንረቱአሁንምቢሆንሊረጋጋአልቻለም። የንግድ ሚኒስቴር ከደመወዝ ጭማሪው በፊት ዋጋ ጨምረው የነበሩ የቢራ ፋብሪካ አመራሮችን በመጥራት ምክንያታቸውን በጠየቃቸውወቅትየግብዓትዋጋመናርእንዳጋጠማቸውበመጥቀስምክንያታዊጭማሪማድረጋቸውንቢያስረዱምይህ

ምክንያትበሚኒስቴሩበኩልአልታመነበትምበማለትዋጋቸውቀድሞወደነበረበትእንዲመልሱበቅርቡባዘዘውመሠረትፋብሪካዎቹያደረጉትንጭማሪ ለማንሳትተገደዋል፡፡

ባለፈውማክሰኞነሃሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ምየንግድሚኒስቴርበተመሳሳይሁኔታከአምራች፣አስመጪእናአከፋፋይድርጅቶችጋርበዋጋንረቱጉዳይከመከረበኃላአብዛኛው

ነጋዴዎችዋጋአልጨመርንምማለታቸውንተከትሎ በተለይየመንግሥት መገናኛ ብዙሃንን በመጥራት እያንዳንዱ ነጋዴ ዋጋ አለመጨመሩን በቴሌቪዥን እየተቀረጸ

ለሕዝብእንዲናገርናይህምንግግሩበመንግሥትመገናኛብዙሃንእንዲተላለፍአደርጎአል፡፡

የአንድየግልአምራችፋብሪካተወካይለዘጋቢያችን እንደገለጹትበእለቱሰብሰባአለተብለውወደንግድሚኒስቴርማምራታቸውንአስታውሰውነገርግንእዚያሲሄዱዋጋ

ጨምራችሃልበሚልከፍተኛማስፈራራትናዛቻየታከለበት ስብሰባአጋጥሟቸዋል።

በዚህስብሰባምዋጋየጨመሩነጋዴዎችካሉዋጋቸውንበአስቸኳይካለስተካከሉ ፈቃዳቸውንእስከመሰረዝናበወንጀልአስከመጠየቅየሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው

በግልጽእንደተነገራቸው ፣በኋላምእያንዳንዳችንእንደሌባበቴሌቪዥንእየተቀረጽንዋጋአልጨመርንምእያልንእንድንናዘዝ አስገድደውናልብለዋል፡፡

ያለምንምምክንያትዋጋበመቆለልየራሱንገበያየሚያበላሽነጋዴአለብለው እንደማያምኑየጠቆሙትአስተያየትሰጪውነጋዴዎችምሆኑአምራቾችዋጋለመጨመር

የሚገደዱትአስመጪከሆኑበዓለም ገበያላይዋጋከፍናዝቅማጋጠምንተከትሎበተዋረድዋጋሲጨምርናፋብሪካዎችደግሞየጥሬዕቃዋጋማሻቀብ
ሲያሳይነውብለዋል፡፡

ይህችግርደግሞአምራቹወይንምነጋዴውብቻተሸክመውይቆዩየሚለውየመንግሥትጥያቄ የንግድሥራውንይበልጥየሚጎዳእንጂመፍትሔአይደለምሲሉአስረድተዋል፡፡

የመከላከያናየፖሊስአባላትንጨምሮከሁለትሚሊየንበላይየሚደርሰውየመንግሥትሠራተኞችየተደረገውየደመወዝ ጭማሪየሐምሌወርንያልተከፈለሂሳብጨምሮበዚህ

ወርመጨረሻለመክፈል ቃል መገባቱን ይሁን እንጅ እስካሁን የክፍያ ትእዛዝ አለመተላለፉን በትናንት ዘገባችን ገልጸን ነበር። ይሁን እንጅ በዛሬው እለት የሲቪል ሰርቪስ

ባለስልጣናት ስለ አከፋፈሉ የፊታችን ሰኞ ገለጻ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሎአል።

አብዛኛውሠራተኞችጭማሪውተጋንኖየተወራለትያህልአለመሆኑናካለውየኑሮውድነትጋርሊመጣጠንካለመቻሉጋር ተያይዞበግልጽቅሬታውንበመናገርላይመሆኑን ተከትሎ

መንግሥትሌሎች አማራጮች እንዲታዩ መመሪያ ማስተላለፉን መዘገባችን ይታወቃል።


የወልድያ ከተማ ህዝብ ብሶቱን አሰማ

ኢሳት ዜና :-የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ከከተማው ህዝብ ተወካዮች፣ ከኢህአዴግ አባላትና ከተለያዩ የመስሪያ

ቤት ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነዋሪዎች የተለያዩ ችግሮችን አንስተዋል። አንድ አስተያየት ሰጪ የጤና ተቋማት መድሃኒት በማጣታቸው አግልግሎት

እየሰጡ አለመሆኑን ተናግረዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የመብራት ችግር የከተማው ችግር መሆኑን ገልጸዋል

ኮብልስቶን ለይስሙላ ተብሎ የሚሰራ በመሆኑ ለህዝቡ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አንድ ሴት አስተያየት ሰጪ ገልጸዋል

ኢህአዴግ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርጋቸውን ስብሰባዎችን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።


የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል (ሥርዓቱን ለ 20ዓመት አይተነዋል መቀየር አለበት!)

የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው
የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም
የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል
የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም

አዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ የአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ስልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡

የኢኮኖሚ እድገት

ተቃውሞ ከገጠማቸው ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ እድገት አለ የለም የሚለው ሲሆን ተማሪዎቹ ‹‹በአክሱም ዘመን ገናና የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚው መስክ ጭራ›› መሆኗን በመግለጽ እድገቱ አለ መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጨምረውም “በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የማይችል ማህበረሰብ ይዘን አድገናል ማለት አንችልም” በሚል እድገት አለመኖሩን ተከራክረዋል፡፡ “ሀገራችን ውስጥ የምግብ፣ የቤት፣ የትምህርት፣ የኔትወርክና ሌሎች ችግሮች አሉ፡፡ ስኳርና ዘይት ለመግዛት ህዝብ ቀበሌ ተሰልፎ ነው የሚውለው፡፡ በ400 ብር ደምወዝ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ህዝብ ያለባት ሀገር የሌሎችን እድገት ፈዛ እያየች ያለችን ሀገር አድጋለች ልንል አይገባም” ማለታቸው ተገልጾአል፡፡

በተመሳሳይም “2 በመቶ የሚሆነው የአሜሪካ አርሶ አደር ዓለምን በሚመግብበት በአሁኑ ወቅት 85 በመቶ አርሶ አደር ይዘን ለምን እንራባለን?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንም የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡ ተማሪዎቹ “አድገናል ብለን ራሳችን ማወዳደር ያለብን ከ40 አመት ከነበረ ስርዓት ጋር መሆን የለበትም፡፡ እድገታችን መለካት ካለበት ከሌሎች አገራት ጋር ነው፡፡ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት በ2020 እንመደባለን ከተባለ መንግስት መቀየር ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ይህን ስርዓት ለ20 አመት አይተነዋል፡፡ ባለፉት አመታት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለምና በ2020ም ለውጥ ያመጣል ብለን አንጠብቅም” የሚል ጠንካር ያለ ሀሳብም አቅርበዋል፡፡

እድገት ላይ ነው የሚባለው የኮንስትራክሽን ዘርፍ የጥራት ደረጃው ዝቅተኛ መሆኑን በተለይ በዘርፉ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች አንስተዋል፡፡ ተማሪዎቹ “እድገት የምንለው የህንጻዎችን ወደላይ ማደግ ወይንም መብዛት ሳይሆን የማህበረሰቡን አስተሳሰብና አኗኗር ዘይቤ መቀየር ነው” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት ገዥው ፓርቲ የቻይናን ፈለግ ተከትሎ እድገት ማስመዝገቡን በመቃወም “ቻይና ከ2.3 እስከ 2.7 በመቶ እያደገች እንደሆነ ይነገራል፡፡ የእሷን ፈለግ ተከተለች የተባለችው ኢትዮጵያ ከ11.2 በመቶ በላይ አደገች ነው የሚባለው ከየት አምጥተነው ነው? ወይስ እንደ ቀን አቆጣጠራችን እድገታችንም ይለያያል?” ሲሉም አሰልጣኖቹን ጠይቀዋል፡፡

የባህር በር

ተማሪዎቹ ለኤርትራ መሰጠቱ አግባብ እንዳልሆነ፣ የባህር በርና ወደቡ ለኢትዮጵያ ቀጣይ እድገት፣ ደህንነትና ታሪክ አንጻር አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ገዥው ፓርቲ በባህር በር ላይ ያለውን አቋምና ፈጸመ ያሉትን ስህተት ተችተዋል፡፡ ወደብ አልባ በመሆናችን ኢኮኖሚያችን ወደኋላ መቅረቱንም አንስተዋል፡፡ በሌላ በኩል “በአገራችን የሚመረቱ ሰብሎችና ፍራፍሬዎች ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡት ከውጭ ከተላከው ሲተርፍ ነው” በማለት በኤክስፖርት ዘርፍ ያለውን ችግር፣ አገር ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን የኑሮ ውድነት ከዚሁ ችግር መመንጨቱን ጠቅሰዋል፡፡

የትምህርት ጥራት

ተማሪዎቹ የራሳቸውን ተሞክሮ በመጥቀስ የትምህርት ስርዓቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመከራከሪያነት አቅርበዋል፡፡ “ለተማረ ሰው ክብር እየተሰጠ አይደለም” በሚል የእነሱም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ መሆኑን ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም “የሚያስተምሩን አስተማሪዎች የእውቀት ደረጃ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው፡፡ በየ ዩኒቨርሲቲው በአመራር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች እውቀት የላቸውም” በማለት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተደቀነውን አደጋ አንስተዋል፡፡

ዲግሪ ይዘው በስራ ፈጠራ ስም በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲደራጁ የሚደረገውን የተቃወሙት ተማሪዎቹ “የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተደራጅተው ካፌ ከፈቱ፣ ኮብልስቶን አነጠፉ ሲባል ነው የምንሰማው፡፡ ለዚህ ስራ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ መማር አያስፈልገውም፡፡ ይህን ስራ ለመስራት የሶስት ወር ስልጠና በቂ ሆኖ እያለ ዩኒቨርሲቲ መማር ባላስፈለ” ሲሉ የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት እንደገጠመው መግለጻቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡


Kenyan police discover Getachew and Debretsion behind the killing of Ethiopians in Kenya

On the afternoon of June 9, an unlikely incident in Garrissa helped to reveal the faces and reasons behind a spate of mysterious killings that have rocked the county. That afternoon, a man approached Hassan Yusuf Intabur in his shop on Guled Street in Garissa Town, pulled out a gun concealed in his right hip, and shot him in the head. The gunman then pumped seven more rounds into Intabur’s body until his gun jammed. When this happened, members of the public who had taken cover spotted an opportunity to apprehend the suspect. But the attacker had another weapon. From a plastic paper bag he was carrying, he fished out a grenade, removed the pin and hurled it towards the crowd that was surging towards him. However, his backup failed him, too. The grenade landed softly in the soil, and failed to detonate. With nothing left to thwart the mob, the attacker took off on foot, with wananchi hot on his heels. There was pandemonium in the town as the crowd pursued the attacker who, though fleet-footed, seemed a stranger to the town since he did not know seem to know where to escape to. They eventually caught up with him, tackled him to the ground, and gave him a thorough beating before the police arrived to save him from imminent death.

Monday, August 25, 2014

ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል ፕ/መስፍን ወልደ ማርያም

ጉልበት አራዊት የሚተዳደሩበት ሕግ ነው፤ ሕገ አራዊት የሚባለው አራዊት የሚተዳደሩበት ጉልበት ነው፤ በአራዊት ዓለም ማናቸውም ነገር በጉልበት ያልቃል፤ በሰዎችም መሀከል ጉልበት አድራጊ-ፈጣሪ ሆኖ ጎልቶ ሲወጣ የአእምሮንና የኅሊናን መዳከም ወይም ጭራሹኑ አለመኖር ያመለክታል፤ ጉልበት አለን በማለት፣ ወይም ተመችቶናል በማለት፣ ወይም ጠያቂ የለብንም በማለት የማንኛውንም ሰው ሰብአዊ መብቱንና ሰብአዊ ክብሩን መግፈፍ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል፤ አንደኛ ጉልበት እንጂ አእምሮና ኅሊና እንደሌለ፣ ሁለተኛ ጉልበት እንጂ ሕግ እንደማይከበር፣ ሦስተኛ በአንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተም በሰዎች ላይ አታድርግ የሚለውን ሕግ መጣስን ያሳያል፤ በመጨረሻም፣ ዘግይቶም ቢሆን በራስ ላይ ቅሌትን መጋበዝን ያስከትላል፤ የሌላውን ሰውነት ስናረክስ ሰውነትን በጠቅላላው ማርከሳችን ነው፤ ሰውነትን በጠቅላላው ስናረክስ ራሳችንን ከነጉልበታችን ማርከሳችን ነው፤ ራሳችንን፣ ሰውነታችንን ካረከስን በኋላ ዋጋ የለንም፤ ለራሳችን ዋጋ ከሌለን ለሌለች ሰዎችም ዋጋ አንሰጥም፤ ያኔ ክፉ በሽታ ይይዘናል፤ እግራችን ስር በወደቀ ሰው ስቃይ የምንደሰትና የምንስቅ፣ የምንፈነድቅ እንሆናለን፤ ያን ጊዜ የለየለት በሽተኛ ሆነናል።

የኢሳት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እህት የግፍ ሰለባዋ

የግፍ ሰለባዋ አስቂኝና ጥርስ የማታስከድን ወጣት ናት። ከእሷ ጋር ለደቂቃ አይደለም ለሰዓታት አብረህ ብታሳልፍ አይሰለችህም፤ በሳቅ ታንከተክትሃለች። አነጋገሯ ፈጠን..ፈጠን ያለ ነው። ..የሷ ቀልዶች አይረሱኝም።..በ1998 ዓ.ም የደረሰባት ነገር እጅግ አሳዛኝ ነው። የተቃዋሚ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የቅንጅት ደጋፊዎችና ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ እስር ቤት ሲጋዙ አጋጣሚ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለሁለት ወር ገደማ እጁን ሳይሰጥ ተሰውሮ ነበር። የገዢው ባለስልጣናት (በረከትና መለስ ናቸው) ያሰማሯቸው ደህንነቶች ሲሳይን ፍለጋ ብዙ ሲማስኑ ነበር። ያላሰሱትና ያልተከታተሉት ሰው የለም፤ በመጨረሻ ግን እህቱን አፈኑ። እየደበደቡ ወደ ወለጋ ወሰዷት። ሴት ልጅ ልትቋቋመው ከምትችለው በላይ በዱላ አሰቃይዋት። « ሲሳይ የት ነው ያለው? ተናገሪ?» ሲሉ ፍዳዋን አስቆጠሯት። ምንም እንደማትውቅ ነገረቻቸው። ምንም ሲያጡ ወለጋ ላይ ፀጉሯን ላጭተው፣ በድብደባ ጐድተውና አቁስለው፣ እጅግ አዳክመው ጫካ ውስጥ አውሬ እንዲበላት ጥለዋት ሄዱ። ራሷን የሳተችው አቦነሽ (ቴሌ) ፈጣሪ ነፍስሽ ይትረፍ ሲላት ገበሬዎች አገኟት። ተሸክመው ወሰዷት። በመኖሪያ ጐጆዋቸው እንድታገግም አደረጉ። ከዚያም ስልክ ወደ አዲስ አበባ አስደወሉላት። ጋዜጠኞች ስፍራው ድረስ ሄደው አመጧት። ..እነሆ ከ8 ዓመት በኋላ ሌላ ክስ ከሙያ ባልደረቦችዋ ጋር ተመሰረተባትና በዚህ ሰሞን አገር ጥላ ተሰደደች። ይህ ግፍ መቆሚያው የት ይሆን!?…ስለተሰደዱት ጋዜጠኞች እመለስበታለሁ።

ወያኔ እስካሁን ድረስ የግንቦት ሰባት የሃገር ቤት መዋቅር በፍጹም እጇ ላይ እንዳልገባ ተረጋግጧል።



ከመጭው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ እንደሚያሰጋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ለሕወሓቱ አለቃ ጸጋይ አርብ እለት የቀረበው ሪፖርት መግለጹን ምንጮች ጠቁመዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በወያኔ ውስጥ ስልጣኔን አጣለሁ እፈረካከሳለሁ የሚለው ከፍተኛ ሽብር የፈጠረው ፍራቻ እየተባባሰ መሄዱን እና ወያኔ ለመጭው አርባ አመታት እቆያለሁ የሚለውን ሃሳቡን ሊያኮላሽብኝ ይችላል ያለውን ሁሉ እርምጃ ቢወስድ ምንም አይነት ውጤት እንደማያገኝ እና በይበልጥ ጥላቻ እያሰፋ እንደሚመጣ በተሰበሰበው የመረጃ ሪፖርት ተገልጿል ።

የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያስተባብሩ ከሆነ ሕዝቡ የሚከፈለውን መስእዋትነት ለመክፈል ወደኋላ የማይል መሆኑን የጠቆመው ሪፖርት የከተማው የተማረውም ያልተማረውም ሕብረተሰብ በወያኔ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስላለው ለመጭው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ ያሰጋል ሲል ሪፖርቱ ተናግሯል። እንደ ምንጮቹ አገላለጽ ክሆነ የሃገር ቤት ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና መኢአድ ይህንን እንቅስቃሴ ያስተባብራሉ የሚል የሕዝቡንም አትኩሮት መሳብ እንደቻሉ ሲታወቅ አንድነት እና መድረክ ፓርቲ ውስጥ ያሉ እና ያሰጋሉ የሚባሉ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱ መቀጠሉን ሪፖርቱ አውስቷል።

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በአዛዦቻቸው ላይ ውጥረት ፈጥረዋል ጄኔራል አበባው ታደሰን እና የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ ስብሰባ መካሄዱ ጥያቄ አስነስቷል

በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት መፈተሩን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ተሰምቷል:: በወታደራዊ ጥቅማ ጥቅም እና በህገመንግሥቱ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ እና ዝም መባሉ ዉስጥ ውስጡን እየተብላላ ያለው የመኮንኖቹ ጥያቄ እንዳይፈነዳ የተሰጋ ሲሆን ከፈነዳ ሰራዊት ለሶስት ቦታ እንደሚከፈል ለምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

መኮንኖቹ በትምህርት በስራ እና በማእረግ እድገት በቤተሰብ እንክብካቤ በደሞዝ ጭማሪ እና በሕገመንግስታዊ የህዝብ መብቶች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለአንድ ብሄር አባላት ብቻ ተመድበው እየተሰራባቸው ነው ከተማ ውስጥ ታጥቀው የመሸጉ እና ህዝብን እያጠቁ የሚገኙት የአንድ ብሄር አባላት ናቸው እንዱሁም ከሃገራዊ ጥቅም ይልቅ የፓርቲ ጥቅም እየተስተዋለ ነው: ወታደሩ የጦር ሳይንስን እና ዲሲፕሊን በጎደለው መልኩ እየተስተዳደረ ነው በሰራዊቱ እና በሃገሪቱ ሁሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሽፋን እና ማዘናጊያ በማድረግ የሙስና እና የዘረፋ መስፋፋት መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ጄኔራል መኮንኖች አላቸው የተባለው ንብረት ይጣራ በሃገሪቱ የፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማንሳታቸው ታውቋል::የመከላከያ አባላቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሱት ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው::

Sunday, August 24, 2014

በቅርስነት የተመዘገበ ሕንፃ በልማት ምክንያት እንዲፈርስ መታዘዙ ተቃውሞ አስነሳ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውንና በቅርስነት የተመዘገበውን ታዋቂው ሎምባርዲያ ሬስቶራንት ያለበትን ሕንፃ ጨምሮ፣ በ10.6 ሔክታር ላይ የሚገኙ ግንባታዎችን ለማፍረስ ለተነሺዎች የመጨረሻ

ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያው ባለፈው ዓርብ አብቅቷል፡፡ በተለይ የሕንፃው ባለቤት የሆነው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲና የሕንፃው ተከራዮች የአስተዳደሩን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡

ተቃውሞ አቅራቢዎቹ ሕንፃው በቅርስነት የተመዘገበ ሆኖ ሳለ እንዲፈርስ መወሰኑ አግባብ አይደለም እያሉ ነው፡፡

ሕንፃው በ1921 ዓ.ም. የተገነባ ሲሆን፣ ሕንፃውን የገነቡት የመናዊው ታዋቂ ነጋዴ ሼክ አህመድ ሳላህ አልዛህሪ ናቸው፡፡ ሕንፃው ከ85 ዓመታት በላይ ከማስቆጠሩም በተጨማሪ የሥነ ሕንፃ ቦርድ በቅርስነት አስመዝግቦታል፡፡

የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት በጻፈው ደብዳቤ፣ በተመሳሳይ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የሼክ አህመድ ሳላህ ቤት በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ በቅርስነት እንዲመዘገብ መደረጉን አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሕንፃው በቅርስነት ስለመያዙ፣ እንዲሁም የሚመለከተው አካል ለቅርሱ ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ነገር ግን የልደታ ክፍለ ከተማ፣ የከተማ ማደስና መሬት ባንክ ጽሕፈት ቤት ለዚህ ማሳሰቢያ ትኩረት እንዳልሰጠ ታውቋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ለምለም ገብረ ሚካኤል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሕንፃው ቅርስ መባሉ አያሳምንም፡፡ ይልቁኑም በአካባቢው በሚካሄደው መልሶ ማልማት ከ40 እና ከ50 ፎቅ በላይ ከፍታ ያላቸው ሕንፃዎች ስለሚገነቡ መፍረሱ አግባብ እንደሆነ ተከራክረዋል፡፡ ‹‹እነዚህ ግንባታዎች በማዕከላዊው የከተማው ክፍል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እንዲገነቡ በተያዘው ዕቅድ መሠረት የሚካሄዱ ናቸው፤›› ሲሉም አቶ ለምለም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያካሂደው መልሶ ማልማት ከብዙ ቅርሶች መፍረስ በኋላ፣ ልማቱ ቅርሶችን ታሳቢ ባደረገ መንገድ እንዲከናወን በቅርቡ መመርያ ማስተላለፉ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን አሁንም የሚካሄዱ ልማቶች መንግሥት በቅርስነት ላስመዘገባቸው ግንባታዎች ትኩረት ገና አልሰጠም ሲሉ በርካታ ባለሙያዎች ይተቻሉ፡፡

የሕንፃው ባለቤት የነበሩት ሼክ አህመድ ሳላ አልዛህሪ በደቡብ የመን ረዳአ በተባለ ቦታ በ1873 ዓ.ም. ነው የተወለዱት፡፡ የአዲስ አበባ ፕሬስ በ1998 ዓ.ም. ባሳታመው የፊታውራሪ ተክለ ሃይማኖት ተክለ ማርያም ግለ ታሪክ፣ እንዲሁም ‹‹ከእንጦጦ ሐሙስ ገበያ እስከ መርካቶ›› በተሰኘ መጽሐፍ ላይ የሼክ አህመድ የሕይወት ታሪክ ተጽፏል፡፡

በመጽሐፉ እንደተገለጸው ሼክ አህመድ ታዋቂ ነጋዴ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ለኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ዕቃዎች የጉምሩክ አስተላላፊነት ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ያስተዳድሩ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ለኢትዮጵያውያን አርበኞች ደጀን ነበሩ፡፡

ሕንፃው ሁለት ፎቅ ከፍታ ሲኖረው፣ ቀደም ሲል በሆስቴልነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለመኖርያነት፣ ለንግድና ለቢሮ አገልግሎቶች ይሰጣል፡፡


Saturday, August 23, 2014

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው



ነገረ ኢትዮጵያ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደሴ፣ ወልደያ፣ ደብረታቦርና ሌሎችም የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ባገኘችው መረጃ መሰረት የተነሱትን ዋና ዋና ተቃውሞወች እንደሚከተለው አቅርባለች፡፡

አርሶ አደሩ አሁንም ድረስ ኢህአዴግ እየተደረገ ያለው የመሬት ድልደላ የፓርቲው አባል አይደሉም የሚባሉት አርሶ አደሮችን መሬት አልባ በማድረግ ለደጋፊዎቹ እየሰጠ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተገልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ቅንጅትን መርጣችኋል እየተባሉ አሁንም ድረስ ጫና እየደረሰባቸው እንደሚገኝና፣ ይህም ለምርጫው ዝግጅት እንዳይሆን ተማሪዎቹ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የእምነት ነጻነት በርካታ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሶስት አመታት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻቸው እንዲሰማ ቢጥሩም መንግስት እየወሰደው ያለው አፈና አግባብ አለመሆኑን፣ በተለይም በርካታ ቁጥር ያለውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ በጅምላ አሸባሪ ብሎ መፈረጅ ስህተት መሆኑን በተማሪዎቹ ተነስቷል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹ኢህአዴግ ማህበረ ቅዱሳንን አሸባሪ የሚልበት ምክንያት ምንድን ነው?›› የሚል ጥያቄ የተነሳ ሲሆን የግቢ ጉባዔ የማህበረ ቅዱሳን አንድ ክንፍ ነው ተብሎ በመፈረጁ አዲስ ህግ ወጥቶ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ በጾም ወቅት ይሰጠን የነበረው አገልግሎትን ጨምሮ እምነታችን እንዳንተገብር መከልከላችን ለጣልቃ ገብነቱ ማሳያ ምክንያት ነው›› ብለዋል፡፡

Friday, August 22, 2014

ጄ/ል ባጫ ደበሌ በሜሪላንድ ግዛት የ350ሺህ ዶላር ቤት ገዙ

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ጄ/ል ባጫ ደበሌ በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት በ350ሺህ ዶላር ቤት መግዛታቸው ታውቋል። የባጫ ባለቤትና አንድ ልጃቸው እንደሚኖሩበት ሲታወቅ ልጃቸው በተርም ከ20ሺህ ዶላር በላይ እየተከፈለለት እንደሚማር ማወቅ ተችሏል።

በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ከተዘፈቁ የመከላከያ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑት ባጫ ደበሌ በቦሌ ከለንደን ካፌ ፊት ለፊት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ ገንብተው እንደሚያከራዩ ይታወቃል። በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት አሰብን ለመቆጣጠር ይገሰግስ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ከመለስ ዜናዊ በተላለፈ ትእዛዝ ግስጋሴው እንዲገታና ወታደራዊ እቅዱ እንዲኮላሽ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ባጫ ደበሌ መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ያረጋግጣሉ።

ባጫ የአቶ መለስን “ሃሳብ” ተግባራዊ በማድረጋቸው በሙስና ሃብት ጥግ መድረስ ችለዋል ሲሉ ምንጮቹ ያክላሉ።


ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሲታፈሱ አመሹ

ለዘ-ሐበሻ የዘገበው ኢትዮጵያ ሃገሬ ጅዳ በዋዲየሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ ውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባርዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሷ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኗም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን ባሻገር ስደተኛው ምንም አይነት ማቋቋሚያም ሆነ ድጋፍ እንዳላደረጉላቸው ይነገራል። በተለይ የስደት አለም ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው ለሃገር የበቁ እናቶች ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉበት አስዛኝ ታሪክ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሆድ አላውሷል ። መንግስት በወቅቱ አዲስ አበባ በስደተኞቹ እንዳትጨናነቅ የስደተኞቹ ጉዳይ በየክልሉ ባለስልጣናት የታያል በሚል ሽፋን በመቶሺህ የሚቆጠረውን ስደተኛ በየጉራጉሩ ወሽቆ ነገሮቹን ለማድበስበስ ቢሞክረም አብዛኛው ወገኖች በቋፍ ላይ ያለቸውን ህይወታቸውን ለመታደግ አቀም ያለው አይቀሬውን ሞት በመጋፈጥ፡ በህይወቱ ቆርጦ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት ቀይ ባሀርን በጀልባ አቋርጧ ለዳገም ስደት ተዳርጓል።በአንጻሩ በሰው ሃገር ወልዶ ከብዶ በወቅቱ ያገኛት በነበረች የዕለት ገቢው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የስደት አለም ጎጆውን አሞቆ ያለጥሪት ይኖር የነበረው አባወራ ያቺን ቀውጢ ውቅት መቋቋም ተስኖት የቤተሰቦቹን ህይወት ከወረበሎች ለማዳን ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ ቢልም ያለጠበቀው ገጥሞት የሞቀ የስደት ዓለም ትዳሩን መቅኔ ያሳጣውን የመንፉሃው ሁከት እየረገመ በገዛ ሃገሩ ሰማይ ተድፍቶበት ለልጆቹ የዕለት ጉርስ ዳቦ መግዣ አጥቶ የህጻናቱን ስቃይ እና መከራ ላለማየት እግር ወዳ መራው ሲኳተን በረሃ በልቶት እደወጣ የቀረውን ከሳውዲ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ቤት ይቁጠረው ። ይህ ባለበት ሁኔታ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት የተጠናከረ የቤት ለቤት ፍተሻ ከ1 ሺሕ በላይ ህገ ወጥ ሰዎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን የሚናገሩ ምንጮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጉዳዩን የበለጠ አሰደንጋጭ ያደረገዋል ። የፀጥታ ሃይሉ ከህብረትሰቡ በሚቀርብላቸው መረጃ መስረት ዘመቻውን በቀጣይነት በሪያድ ከተማ በተለምዶ ነሲም አል ሃማም እና ጉቤራ እይተባሉ የሚጠሩ መንደሮችን በማማከል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።። ከአንድ ወር በፊት በሪያ ድ ከተማ የአንድ ወህኒ ቤት ግርግዳ ደምርሰው ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ቁጥሩ በወል የማይታወቅ እስረኞች ማምለጣቸው ይታወሳል ።በዛሬው ዕለት መንፉሃ ውስጥ በተካሄደው የቤት ለበቤት ፍተሻ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደርሰ እንግለት ወደ ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ባደረኩት ጥረት አንድ ስሜ እንዳይገለጽ ያሉ ዲፕሎማት የቤት ለቤት ፍተሻው በኢትዮጵያውያኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ገልጸው በዘመቻው ወቀት ከፍተኛ የሳውዲ ፀጥታ ሃይል መኮንኖች እና የመዲናይቱ ባለስልጣናት የቀርብ ክትትል እና ቁጥጠር ያደርጉ እንደነበር በማውሳት እርምጃው በባህር የመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በሌላቸው ህገወጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና በየትኛውም ዜጋ ላይ ምንም አይነት እንግለት ያለተፈፀመ ጥናቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደነበር አረጋግጠናል ብለዋል ።በማስከተል ትላንት የሻኞቸውን ኢትዮጵያውያን ደግማችሁ ዛሬ ስትሸኙ ምን ይሰማችሃል ላልኳቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡኝ ተሰናብተውኛል። ዛሬ ማለዳ መንፉሃ ውስጥ በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተካሄደ በተባለው የቤት ለበቤት አፈሳ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ወህኒ ከሚገኙ ወገኖች መረጃ በማሰባሰብ በሰፊው ለመዘገብ የማደርገው ጥረት ይቀጥላል ።

በባቲ ኦሮሞዎች እና የአጎራባች አፋር ክልል ነዋሪዎች ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ

ኢሳት ዜና :-በባቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ቡርቃ በተባለ ቀበሌ አካባቢ የሚኖሩ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች
ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በተኩስ እየተጋጩ በሁለቱም ወገን ሰዎች እየሞቱ ቢሆንም ፤የሁለቱ ክልል መሪዎች ጉዳዩን ለመፍታት ምንም ዓይነት
ጥረት አለማድረጋቸው እንዳሳዘናቸው የባቲ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
በቡርቃ ቀበሌ የተቀበረ ወርቅ አለ ተብሎ መነገሩ ለግጭቱ መባባስ ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች፣ የኦሮምያ ዞን መሬቱን
ለባላሀብቶች ሰጥቶ በማስቆፈርላይእያለበአካባቢውየሚኖሩትየአፋርተወላጆችድርጊቱንበመቃወምበቁፋሮበተሰማሩትሰራተኞችላይተኩስ ከፍተው
ጉዳት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በተኩስልውውጡምቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ከመገደላቸውም በተጨማሪበንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አክለው ተናግረዋል።
አካባቢውን በግል የተደራጁ የአፋር ታጣቂዎች የተቆጣጠሩት ሲሆን የባቲ ወረዳ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ችግሩን ለመፍታት ቦታውን ከተቆጣጠሩ
ታጣቂዎች ጋር ቢነጋገሩም ታጣቂዎች ማንኛውንም ትእዛዝ ከአፋር መንግስት እስካልመጣ ድረስ አንነጋገር ምበማለታቸው በአጎራባች ክልሎቹ
የጠረፍ ከተሞች መካከል ሊካሄድ የነበረው የሰላም ውይይት በተደጋጋሚከሽፏል።
የሁለቱ ክልል መንግስታት አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው ለመፍታት ባለመፈለጋቸው ነዋሪዎቹ ወቀሳ አቅርበዋል።
በሁለቱ ክልል ድንበር ያለው ውጥረት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የአይን እማኞች ለዘጋቢችን ገልፀዋል፡፡


Thursday, August 21, 2014

‹‹ይድረስ ላንቺ››

መነበብ ያለበት ዘላለም ክብረት ከቂልንጦ ማረሚያ ቤት የላከው አስገራሚ ደብዳቤ

ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ
በዘላለም ክብረት
ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡
‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››
የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡
እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)
ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት

ከወያኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠናዎች የተረዳነው:- ወጣቱ ለለውጥ ዝግጁ ነው፤ የቀረው ድርጅት ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመሠረቱበት ዓላማ የእውቀትና ጥበብ መበልፀጊያና ማስፋፊያ እና የምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ነው። እውቀትና ጥበብ እንዲበለፅጉ እና የምርምር ሥራዎች እንዲዳብሩ የአካዳሚ ነፃነት መኖሩ ቁልፍ ጉዳይ ነው። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር መምህራኑም ተማሪዎቹም በነፃነት ማሰብ፣ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ማንሳት እና ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለመሻት መመራመር አይችሉም። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር የተለያዩ እይታዎችንና ንድፈሀሳቦችን በገለልተኛነትና በሀቀኝነት መመርመር አይቻልም። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአካዳሚ ነፃነት እንዲኖር ተቋማቱ ከፓርቲ ፓለቲካ ገለልተኛ መሆን ይኖርባቸዋል። አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ከሆነ ተቋሙ የፓርቲው ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነ ማለት ነው። ዛሬ በአገራችን የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ሁኔታ ይህ ነው። የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወያኔ ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነዋል። ይህ አጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

ሰማያዊ ፓርቲ “ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!” አለ

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫው ለተማሪዎች በግዳጅ እየተሰጠ ያለውን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ ኢሕአዴግ እየሰራ ያለውን ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን አለ። መግለጫው እንደወረደ እነሆ፦ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡

አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ ( ግርማ ካሳ)

ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ ሃብታሙ አያሌውም፣ «የግንቦት ሰባት ተባባሪ ነው» በሚል ነው ለመክሰስ ነው ዝግጅት እየተደረገ ያለው።

አብርሃ ደስታ እና ሃብታሙ አያሌው ፣ «ግንቦት ሰባትን ይደግፋሉ» የሚል ክስ ከቀረበባቸው፣ በተዘዋዋሪ መንገድ «ከሻእቢያ ጋር ወዳጆች ናቸው» ማለት ነው። ታዲያ የሻእቢያ ወዳጅ የሆነ ሰው፣ የኤርትራን መገንጠል ተቃዉሞ፣ ወይንም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት መከበር እንዳለበት በማስመር ይናገራል ወይ ? እስቲ የጸረ-ሽብርና የአገር ደህንነት ተብዬው ምላሽ ይስጠን !!!

መለስን ቅበሩት!(ተመስገን ደሳለኝ)

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

Wednesday, August 20, 2014

የዓረና-መድረኽ ሰለማዊ ሰልፍ ለሁለተኛ ግዜ ተከለከለ…!

ዓረና-መድረኽ ለእሁድ 18 / 12 /2006 ዓ/ ም በመቐለ ከተማ ሊያካሂደው ያሰበው ህዝባዊ ሰለማዊ ሰልፍ ኣስቀድመው የተያዙ የህዝብ በኣላትና መንግስት የያዛቸው ዝግጅቶች፣ ህጋዊ ያልሆነ በከተማው ኣስተዳደር የተዘጋጀ የሰለማዊ ሰልፍ ስነ ስርዓት ፎርም መሙላት ኣለባቹ በሚል ተልካሻ ምክንያት እንዳይካሄድ ኣዝዘዋል።

መቐለ ህወሓት ደግፈህ ካልሆነ ተቃውመህ ሰልፍ የማታደርግባት ብቸኛ የኢትዮዽያ የክልል ከተማ ናት። ህወሓት የመቐለ ጎዳናዎች በየቀኑ ማርሽ ባንድ ኣጅቦ እየዞራቸው እንደሚውል የከተማው ኑዋሪ የሰለቸበት ተግባር ነው።

ህወሓት ጠንቋይ ሰለማዊሰልፍ ከፈቀድክ ከስልጣንህ ትወርዳለህ ብሎ የተናገረው እስኪ መስል ድረስ ሊፈቅድ ኣልቻለም። ለነገሩ ኣባባ ታምራት ኣንድ ወቅት “…ከኣንድ ሰው በቀር ሁሉም የኢኣዴግ ሚኒስትሮች መጥተው ሰግደውልኛል….” ማለቱ ይታወቃል።

መቐለና የመቐለ ህዝብ ተቃውሟቸው በሰለማዊ መንገድ፣ ባደባባይ እንዲገልፁ ኣልተፈቀደላቸውም።
ከዚህ በፊትም ሰላም የሚያስከብር በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለት ሰለማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ መከልከላቸው የሚታወስ ነው።

ህወሓት በ 1968 ዓ/ ም ያወጣው ፕሮግራሙ “… የትግራይ ህዝብ ሃሳቡ፣ ተቃውመውና ድጋፉ በነፃነት በሰለማዊ ሰልፍ እንዲገልፅ እታገላለው..” የሚል ነበረው። ክልከላው ሊዚህ ዓለማ የተሰዉ ከ60 ሺ ሰማእታት ከንቱ የሚያስቀር ተግባር ነው።

የተከበራቹ ኢትዮዽያውያን ህወሓት መቐለ ከተማ ብቻው የሚፈነጫባት ከተማ ኣድርጓታልና መቐለ ከተማ ሰለማዊ ሰልፍ ይፈቀድ…! ብላቹ ሰልፍ ኣድርጉልን።

ይኸው እኛም ይሄ መብት ለማረጋገጥ ተግተን እየታገልን እንገኛለን።
የክልከላው ደብዳቤ ትናንት የተሰጠን ሲሆን እነሱ ግን ወድያው እንደደረሳቸው መልስ የሰጡበት ለማስመሰል ወጪ የተደረገበት ቀን ወደሁዋላ መልሰው ፅፈውታል።

ለምን እንደዚህ እንዳደረጉ ስንነግራቸው ኣምሽተው እንደፃፉትና ቢሮኣችን እንዳላገኙን ሳያፍሩ ነግረውናል።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!


ከቤተ ክርስቲያኑም በላይ ‹‹ቤተ ክርስቲያን››

ከጌታቸው ሽፈራው

ባለፈው ሰኞ ዕልት ነው፡፡ ምን አልባትም ከአንድ ሰዓት በላይ ሊያስጠብቀን የሚችለውን የታክሲ ሰልፍ ትተን ከቤተ መንግስቱ በስተ ቀኝ ያለውን መንገድ ይዘን ወደ አራት ኪሎ አቀናን፡፡ በስተመጨረሻም ስላሴ በተክርስቲያን ደረሰን፡፡ በወቅቱ ማን የት ጋ እንደተቀበረ የተሻለ መረጃ የነበረው ብርሃኑ ተክለያሬድ የአስጎብኝነቱን ሚና እየተወጣ ነው፡፡ ‹‹እዚህ ጋር 60ዎቹ የተቀበሩበትን ነው፣ እዚህ ጋር አብዲሳጋ፣ እዚህ ጋ ጥላሁን ገሰሰ፣ ይህኛውን አዳራሽ ደግሞ ለሰርግ ያከራዩታል…..››፡፡

ብርሃኑ ቀጥሏል! ‹‹‹ስብሃት ገብረግዚያብሄርም እዚህ ነው የተቀበረው፡፡››

ለቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባለት ጥሪ ቀረበ

በየወረዳዎች የተለጠፉት ማስታወቂያዎች ” በተለያዩ ጊዜያት በአገር መከላከያ ሰራዊት ስታገለግሉ የነበሩና በተለያዩ ጊዜያት ወደ ወረዳችን የተመለሳችሁ የሰራዊት አባላት በሙሉ የወረዳው አስተዳደርና ጸጥታ ጽ/ቤት ለመዝግባ ስለሚፈልጋችሁ እስከ
ነሃሴ 21 እየቀረባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን” ይላሉ።

ማስታወቂያዎቹን ለማውጣት ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ ባይሆንም፣ መከላከያን እየከዱ የሚጠፉ የሰራዊት አባላት በመበራከታቸውና አዳዲስ ተመልማዮችም በመጥፋታቸው ምናልባትም ነባሮችን የመመለስ ስራ ለመስራት ሳይሆን አይቀርም ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።


7 ጋዜጠኞች ሃገር ጥለው ተሰደዱ

(ዘ-ሐበሻ) መንግስት ሰሞኑን በነጻው ፕሬስ አባላት ላይ የጀመረውን ሰዶ የማሳደድ ተግባር ሰለባ የሆኑት 7 ጋዜጠኞች ሃገር ጥለው መውጣታቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ሰበር ዜና አመለከተ::
ከሰሞኑ በፍትህ ሚ/ር ክስ የተመሰረተባቸው እነዚሁ ጋዜጠኞች የሎሚ መጽሔት, የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣና እና የጃኖ መጽሔት አዘጋጆች ሲሆኑ እነርሱም
1ኛ. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው
2ኛ. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ
3ኛ. ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ
4ኛ. ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ
5ኛ. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ
6ኛ. ጋዜጠኛ ሰብለወንጌል መከተ
7ኛ. አቦነሽ
የተባሉ ሲሆን ዝርዝሩን ወደ በሁዋላ ይዘን እንመለሳለን::

የ ኢቦላ ቫይረስ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ያስተላለፉት ቀጭን ትዛዝ አነጋጋሪ ሆኖዓል።

ሄኖክ የሺጥላ
በምዕራብ አፍሪካ የተነሳውን የኢቦላ ቫይረስ ተከትሎ የተለያዩ ሃገራት ወረርሽኙ ወደታየባቸው ሀጋሮች የሚያደርጉትን ማንኛውም አይነት የአየርም ሆነ የየብስ፣ የንግድና የቱሪዝም ፣ የትምህርትና የስልጠና እና ሌሎችንም አይነት የንግድ ይሁን መሰል ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች አቁመዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ፣ አይዞዋችሁ ፣ ወደተባለው አደገኛ መንደር መሄዱ አይደልም መፈራት ያለበት ፣ መፈራት ያለበት ቦሌ ላይ የምናደርገው የቁጥጥር ስርዓት ነው ፣ በዚህ ደሞ ሃሳብ አይግባችሁ እኛ እንኩዋን ኢቦላን አንዳርጋቸው ጽጌንም ቢሆን ይዘናል እያሉን ያሉ ይመስላሉ። አክለውም እንደው ባጋጣሚ ይሄ ኢቦላ የተባለው ቫይረስ ቢገኝ እንኩዋ ባ’ስር አልጋና በሃያ ዶክተሮች ታጥቀን እየጠበቅነው ነው እያሉ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት “The World Health Organization (WHO)” ቫይረሱ ሊያመጣ የሚችለውን እልቂት እየተናገረ ፣ በይበልጥም የህክምና ጠበበብቶች በአማካይ ለ 21 ቀናት ቫይረሱ ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ሳያሳይ በተጠቂው ግለሰብ ላይ የመቆየት እቅም እንዳለው እየተናገሩ፣ የኛ ጠቦቶች ( ማለቴ ጠበብቶች ) ግን ተጠቂውን ( ወይም ለነሱ ታጣቂውን ) የምንለይበት ልዩ ዘዴ ስላለ አትቸገሩ እያሉን ነው።

እኔ እምለው ኢቦላም ላይ ከፍተኛ ክትትል ለማድረግ በሽታው ከዔርትራ መነሳት ነበረበት ማለት ነው? መንግሥቴ ምነው ያልተጠመደ ቦንብ ከምታፈነዳብን ምናለ ይቺን ኢቦላ ከመፈንዳቱዋ በፊት ብታክሽፍልን ? ወይስ የምርጫ ታዛቢዎች ወደ ሀገሪቱዋ እንዳይገቡ ለማድረግ እየተዶለተ ያለ ነገር አለ? መቼም እናንተ እኮ ስለ ሰው ሕይወት ያላችሁ ግንዛቤ ጅብ ስለ አህያ ስጋ ያለውን ያህል ግንዛቤ እንደማይሆን እጠረጥራለሁ ። እኔን የገረመኝ ግን እነዚያ 20 ዶክተሮች እነማን ይሆኑ ? ምናልባት ስርዓቱን በመቃወማቸው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ምስኪኖች?

ለማንኛውም ኢቦላ ክላሽንኮቭ ተሸክሞ ፣ ቦምብ ታጥቆ ፣ በጾረና በኩል የሚመጣ ዋርድያ ወይም ጀሌ ወይም ማንጁስ አይደለም ፣ የኢቦላን ምንነት ለመረዳት ቢያንስ ሚንስትሪን ማለፍ የግድ ይላል ። በአምስተኛ ክፍል እውቀት ግን እንኩዋን ኢቦላን የሆድ ድርቀትን መረዳት የሚከብድ ይመስለኛል ። ለናንተ አይነቱ ድፍን መሀይም የዚህ በሽታ ጥፋት እና ክፋት ሊታያችሁ ያልቻለው ደሞ ነገሮችን ሁሉ የምታዩት የታንክ ሰንሰለት ባያችሁበት አይናችሁ ስለሆነ ነው ። ህዝቡ ግን ዝም ብሎ እንደሚታረድ በግ የሆነ ይመስለኛል ። ማን ያውቃል መጥፍያችሁስ ቢሆን?


ሕወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ አይሁድ ስርአትን የመዘርጋት ምስጢራዊ እቅድ አለው።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በአሁን ወቅት ስብሃት ነጋ የያዘውን ስልጣን የቀድሞው የኢንስቲትዩቱ ፕረዝዳት የነበረው ዶክተር ክንፈ አብርሃ እንደሞተ ወያኔ ዶክተሩን የሚተካ ሰው በማጣቱ በትም ተቸግሮ ስለነበር ቦታውን እንዲይዝ የተፈለገው የትግራይ ተወላጅ ስለነበር አቶ መለስ ዜናዊ በዘር ቆጠራ ሲያጠያይቁ አንድ በሃይለስላሴ ጊዜ ወደ ካናዳ ለትምህርት ሂደው ደርግ ሲመጣ በዛው በጥገኝነት የቀሩ ህይወታቸውን ሙሉ ወርልድ ባንክ የሰሩ እና የተማሩ በጡረታ የሚኖሩ ዲያስፖራ አዛውንት ኢትዮጵያን በዘረኝነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ብቻ የሚያውቛትን ዶክተር የትግራይ ተወላጅ አስጠርቶ ሊሾማቸው አስቦ አልተሳካለም። ለምን ?

እኚህ ካናዳ በጡረት የሚኖሩ አዛውንት በጊዜው የመለስ ዜናዊን ጥሪ ተቀብለው ወደ አዲስ አበባ መጥተው ነበር ። ገና ከአይሮፕላን ወርደው ወደ ኤርፖርቱ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም በሆቴሎች በመንገዶች ላይ የተመለከቱት በዞሩባቸው መስሪያ ቤትች ያሉ ነገሮችን በመታዘብ አስደንጋጭ ገተመኝ ሆኖባቸው ነበር ። ሁሉንም ሲያዩት ከአንድ ብሄር እና ከአንድ ቤተሰብ የተሳስረ ሃገሪቷ የአንድ ሰው ንብረት በሚመስል መልኩ ብሰንሰለት አደጋ ውስጥመሆኗን ሲናገሩ ተደምጠዋል። የአገሪቱ ተቋማት በአንድ ቋንቛ ተገጣጥመው እንደተሰሩ አላቂ ምርቶች አዲስ አበባ በመሰለ ሜትሮ ፖሊቲይን ከትማ ውስት መመልክታቸው እጅግ አስደንግጧቸው ነበር።

የአዲስ አበባ ፖሊሶች ለስልጠና እንዲከቱ ተደረገ

ኢሳት ዜና :-ለፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በኮልፌ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከተጠናቀቀ በሁዋላ መደበኛ ፖሊሶች ደግሞ በተለያዩ የማሰልጠኛ ቦታዎች በግዳጅ ገብተው ስለመንግስት ፖሊሲና እቅድ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው።

በኮልፌ በአዛዥ ፖሊሶች ሲጠየቁ የነበሩት ጥያቄዎች በመደበኛ ፖሊሶች ተጠናክረው መቅረባቸው ታውቋል። ከትናንት ጀምሮ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ግንቦት 20 እየተባለ በሚጠራው ትምህርት ቤት ውስጥ 500 የሚደርሱ ፖሊሶች ገብተዋል። እያንዳንዱ ፖሊስ ለ12 ቀናት ስልጠና የሚሰጠው ሲሆን፣
ለእያንዳንዱ ፖሊስ ለ12 ቀናት 800 ብር በጀት ተመድቦላቸዋል። ይህ ገንዘብ ለምግብ፣ ለምኝታ እና ለሌሎችም ወጪዎች ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ከስልጠና ቦታው መውጣት፣ ምግብ ከውጭ አስመጥቶ መብላት እና ለሻሂ እረፍት በሚል ወደ ውጭ መውጣት አይፈቀድላቸውም። 46 የሚሆኑ ነፍሰ ጡር ሴት
ፖሊሶች ቤታቸው እየሄዱ እንዲያድሩ ቢጠይቁም የተፈቀደላቸው ግን 15 ብቻ ናቸው። ፈቃድ ከተከለከሉት መካከል የ3 ወር አራሶችም እንደሚጘኙበት ታውቋል። በዚሁ መሰረት ከስልጠናው በሁዋላ ቤታቸው እንዲያድሩ ሲፈቀድላቸው ሌሎች ፖሎሶች ግን በስልጠናው ቦታ ማደርና መዋል ግድ ይላቸዋል።

የተመደበላቸው በጀት አነስተኛ መሆኑና ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት የሚቀርብላቸው ምግብ ደረጃውን ያልጠበቀ ነው በማለት ቢቃወሙትም፣ አሰልጣኞቹ ግን ይህ ተደረገው ፖሊሱ ለመንግስት ያለውን ታማንነት ለመፈተን ተብሎ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

በንፋስ ስልክ በተካሄደው የመጀመሪያ ቀን ውይይት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ይህ መንግስት ለህዝቡና ለእናንተ ምን ያላደረገው ነገር አለ? ምን ጉድለት አለበት? የሚል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፣ ፖሊሶች መንግስት እያደረገው ያለው ነገር እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን፣ የአስተዳደሩም ሁኔታ ልክ አለመሆኑን እና ለውጥ እንደሚያሻው በድፍረት ገልጸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት ለህዝቡ ተሰሩ ያሏቸውን ስራዎች ዘርዝረው ቢያቀርቡም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፖሊሶች አጣጥለዋቸዋል። መንግስት ለአዲስ አበባ ፖሊሶች የኮንዶሚኒየም ቤት እንዲያገኙ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውና የቤት ችግራቸው እንደሚፈታላቸው ቢናገርም፣ ፖሊሶች ግን ከዚህ ቀደም የተገቡትም ቃል ኪዳኖች ተግባራዊ አልሆኑም በሚል በባለስልጣኖች በድጋሜ የተገቡትን ቃል ኪዳኖች አልተቀበሉዋቸውም።

ፖሊሶቹ የመንግስትን ስትራቴጂንና ፖሊስን እንዲያውቁ፣ በመጭው ምርጫ ላይ ፖሊሶች መንግስት እንዲያሸንፍ ጥረት እንዲያድርጉ ተነግሯቸዋል። ተቃዋሚዎች የሚናገሩት የማይረባ መሆኑንና መንግስትን መደገፍ አማራጭ የሌለው ነገር መሆኑን ገልጸዋል።

ሰልጣኝ ፖሊሶች የስልክ ጥሪ ቢደርሳቸው ስልክ ማንሳት እንደማይችሉና የተደወለላቸውን ስልክ ለተቆጣጠሪዎች የማስመዘገብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የስልክ ጥሪ የተቀበለና ጥሪውን ያላስመዘገበ ፖሊስ የዲሲፒሊን እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

በአዲስ አበባ የወጣቶች ስፖርት ማእከልም እንዲሁ 600 የሚሆኑ ፖሊሶች ለስልጠና እንዲገቡ ተደርጓል።


Tuesday, August 19, 2014

የፀጥታ ሃይሎች በጭፍን ታዛዥነት የሚጥሷቸው መሰረታዊ መርሆች

በሃገራችን ኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ሃገራችንን እንዲመራ የሚመሰረተው መንግስት በኢትዮጵያ ህዝቦች ነፃ ፍላጎት፣ በህግ የበላይነት እና በህዝቦች ፈቃድ የህዝቡን የጋራ ጥቅም፣ መብት እና ነፃነት እንዲያስከብር የሚመሰረት የፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ተቋምም ህዝባችንን በትጋት እና በህግ በታቀፈ አካሄድ እንዲያገለግል ተደርጎ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባው ህገ መንግስቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በመቀጠልም ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ህዝቦች የሃገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ረጋግጣል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ማንኛውም የውስጥ ደንብም ይሁን መመሪያ ውድቅ መሆን ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ ያሰፈረ ሲሆን በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 ደግሞ ማንኛውም የመንግስት አካልም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ለህገ መንግስቱ ተገዢ መሆን እንዳለበት በጥብቅ ያስገነዝባል፡፡
እንግዲህ በህገ መንግስቱ መግቢያና በአንቀፆቹ የተገለፁትን ሃሳቦች ጠቅለል ባለ መልኩ ከተመለከትናቸው በሃገራችን የሚመሰረተው መንግስት ህዝብን ለማገልገል የሚመሰረት ተቋም መሆኑን እና የመንግስት አካል ሆነው የሚፈጠሩ ማናቸውም ክፍሎች ለህገ መንግስቱ ተገዢዎች፣ እንዲሁም ህገ መንግስቱን በተግባር ለመተርጎም የሚፈጠሩ መሆን እንዳለባቸው እንረዳለን፡፡ በተቃራኒው ህገ መንግስቱን የማፋለስ እና የመርገጥ መብት የሌላቸው መሆኑንም እንገነዘባለን፡፡ በተጨማሪም በማንኛውም የመንግስት ተቋማት ተቀጥሮ የሚሰራ ግለሰብ ዋነኛ እና ከፍተኛ ኃላፊነቱ ህዝብን ማገልገል እና የህዝቡን ጥቅም እና ነፃነት መጠበቅ መሆኑን እንረዳለን፡፡
ከዚህ መሰረታዊ ሃሳብ ከተነሳን በመንግስት ተቋማት ውስጥ በመቀጠር የህዝብን መብት እና ነፃነት የሚጋፉ፣ ወይም የማህበረሰባቸውን መብት እና ነፃነት የሚገፍ ማንኛውንም ትዕዛዝ የሚቀበሉ፣ የሚፈፅሙ እና የሚያስፈፅሙ አካላት ቢያንስ የሚከተሉትን ሶስት መሰረታዊ የህገ መንግስት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ልንገነዘብ እንችላለን፡-
1. አንድ ግለሰብ በሃገራችን ሉዓላዊው አካል እና ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን እያወቀ የህዝብን ደህንነት እና ነፃነት የሚጋፉ ድርጊቶችን እንዲፈፅም የሚሰጠውን ትዕዛዝ መቀበሉ እሱም የህዝቡ አካል ነውና በቅድሚያ የራሱ ህገ መንግስታዊ መብት እንዲረገጥ በፍቃደኝነት የተቀበለና ለህገ መንግስቱ ክብር የሌለው መሆኑን ያረጋግጣል፤
2. ግለሰቡ የህብረተሰቡን መብት የሚጥሱና ነፃነቱን የሚያቃውሱ ድርጊቶችን እንዲፈፅም ታዝዞ ድርጊቱን ከፈፀመ የወገኖቹን የህገ መንግስት መብት የሚጥስ እና የሚረግጥ በመሆኑ ዳግም ህገ መንግስቱን ይጥሳል፤ ይረግጣል፤
3. ህገ መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል በማለት ተቃውሞ የሚያሰሙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማፈን እና ይህን መብታቸውንም ለመግፈፍ የተሰማራ ከሆነ በሶስተኛ ደረጃ ህገ መንግስቱን ይጥሳል፤
በመሆኑም እያንዳንዱ ዜጋ በሚያደርገው ድርጊት ዛሬ መንግስትን በታማኝነት ሲያገለግል ድርጊቱ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣጣም እና የህገ መንግስቱን መንፈስ የተከተለ መሆን አለመሆኑን የማጣራት ግዳጅ ያለበት ሲሆን ይህንን ችላ ብሎ ህገ መንግስቱን የሚፃረሩ ድርጊቶችን መፈፀሙ ነገ የህግ የበላይነት በሃገሪቱ ሲሰፍር እና እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች መብታችንን በፍትሃዊ ፍርድ ቤት የምናከብርበት ወቅት ሲመጣ በህገ መንግስቱ መሰረት ለፍርድ የሚቀርብ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ ይህን ከግምት በመክተት እያንዳንዱ ዜጋ ህገ መንግስቱን ተገንዝቦ የራሱን መብት አክብሮ የሌላውን ወገኑን መብት እንዲያከብር አጥብቀን በወገናዊነት ስሜት እንጠይቃለን፡፡ ታማኝነት ለህግ እና ለህገ መንግስቱ እንጂ ራሳቸውን ‹‹የህዝብ ተወካዮች›› ሲሉ ሰይመው ህዝብን ለመርገጥና መብት ለመግፈፍ ለቆሙ ጥቂት አምባገነኖች አይደለም! የአምባገነኖች አገልጋይና መሳሪያ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ‹‹ህዝብ ላይ በደል የፈጸምኩት በእነሱ ትዕዛዝ ነው›› ማለት ከተጠያቂነት አያድንም!
ህገ መንግስቱን ማክበር እና ማስከበር ህዝባዊ ሀላፊነታችን ነው!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!


የሕዳሴ አብዮት ለፖለቲካው ( አስራት አብርሃም)

ወዳጄ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የህዳሴው አብዮት አይቀሬ እርግጠኛ ሆኗል፤ እኔም ያለኝ ግምት ተመሳሳይ ነው። በመሆኑም የዛሬው ፅሁፌ የሚያተኩረው የህዳሴው አብዮት እንዴትና የት ይጀምር? በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ይሆናል። በእኔ እምነት የህዳሴው አብዮት መጀመር ያለበት ከራሱ ከተቃውሞ ጎራ ነው የሚል ነው። ምክንያቱም የለውጡን ሀይል የሚመራው ይሄ የተቃውሞ ጎራ ስለሚሆን በመጀመርያ ውስጡን ማጥራትና ማጠናከር ስላለበት ነው። ስለዚህ፣ ከሁሉም ነገር በፊት የተቃውሞ ጎራው በትክክልና በተገቢው ሁኔታ እንዲታደስና እንዲለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው። ስለፖለቲካው መታደስና መለወጥ ሲታሰብ ደግሞ እንዴት ነው የሚታደሰው? እንዴት ነው የሚለወጠው? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ ይሆናል። የመጀመርያው ነገር፣ እስካሁን ከተጓዝንበት ኋላቀርና ውጤት አልባ የትግል ስልት የሚያወጣን፣ የተለየ ያካሄድ ለውጥና የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማደረግ የሚያስችለን ብቁ የሆነ ፖለቲካዊ አመራር ወደፊት እንዲመጣ ማድረግ ነው። በተለይ ደግሞ ፖለቲካዊ ትግሉ በአስራር፣ በአደረጃጀት፣ በዴሞክራሲያዊ ባህልና በበሳል አመራር ማጠናከርና ማነፅ ቀዳሚው ተግባር ነው የሚሆነው።

የትግሉን አቅጣጫ ለማሳት የተላኩ ተኩላዎችን እንጠንቀቅ።

ይህን ሰሞን በአክቲቪስቶች ላይ የሚደረገው ዘመቻ በወያኔው ኢንሳ የተቀናጀ ነው።
በሃገራችን የተንሰራፋውን አምባገንነት ለመዋጋት ባለፉት 20 አመታት አስታውጾ ያበረከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው የማይካድ ሃቅ ነው። ከሃገር ውስጥ ከተቃዋሚ ፓርቲ አባልነት እስከ በግል ነጻነትንነስከመጠየቅ ለህዝቦች መብት ከመከራከር እስከ አገር መሰደድ የደረሱ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬም በየድህረገጹ የራሳቸውን አሊያም አባል የሆኑበትን ድርጅት አስተሳሰብ ጨምሮ በገለልተኝነት መረጃ እና ጹፍ እስከማድረስ የሚሰሩ አክቲቪስቶች ሞልተውናል። የሚያደርሱን መረጃ በትክክለኛው መንገድ ቀን ጠብቆ እውነታው የተረጋገጠ እና እንዲሁም የሚጽፉት ተጽእኖ ፈጣሪነቱ እጅግ የላቀ ነው። ለዚህ ደሞ በፖለቲካ የበሰሉ ሰዎች እና ሃገር ወዳዶች ምስክር ናቸው።

በዚህ ሰሞን ግን እያየን ያለነው አክቲቪስቶችን መወንጀል መፈረጅ ማጣጣል ማዋረድ እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው፡፤ ትላንትና ወያኔን ሲደግፉ የነበሩ እና ለወያኔ ሲቆረቆሩ የነበሩ ጸረ ዲያስፖራ ፔጆች ዛሬን አዛኝ መስለው እንዲሁም በቅርብ ጊዜ ፌስቡክን የተቅላቀል አንዱ ስም ሲነቃባቸው በሌላው እየቀየሩ ህዝብን ለማሳሳት እና የትግሉን አቅጣጫ ለማስቀየስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ለረዥም አመታት ቢያንስ ከ 10 አመት በላይ በየድህረገጹ መረጃ በመስጠት እና ጹሁፎችን በመልቀቅ ታግለው የሚያታግሉ አክቲቪስቶችን አንድ ጊዜ ሙስሊሙን ቢደግፉ ውሃብዬ ግንቦት ሰባትን ብቢእግፉ የቀድሞ ስር አት ናፋቂ ለየት ያለ መረጃ ይዘው ብቅ ቢሉ ወያኔ ወዘተ እየተባሉ ስማቸውን እየጠፋ በዝርክርክ መንፈስ ሃገራችንን እና ትግላችንን ሽንቁር ሊያበጁለት የኢንሳ ተላላኪዎች በርክተው ዘምተዋል።

ስለዚህ ይህን ሰሞን ብአክቲቪስቶች ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በወያኔ የደህንነት ተቋም ኢንሳ የተቀናጀ መሆኑን አውቀን ራሳችንን ከነዚህ ትግሉን ለመግደል ከሚራወጡ ተኩላዎች ልንጠብቅ ይገባል ፡፤ ለረዥም ጊዜ መረጅ ብመስጠት እና ጽሁፎችን በመልቀቅ ለህዝብች ልለውን በማስተማር ላይ ያሉ አክቲቪስቶችን በማክበር ለታሪክ ልናቆያቸው ይገባል። ትላንትና በየፌስቡኩ መተው አክቲቪስቶቻችንን በመዝለፍ እና በመፈረጅ ትግሉን ለማስቀየስ የሚሰሩ ተኩላዎች አጃቸውን ከታጋይ አክቲቪስቶች ላይ ሊያነሱ ይገባል።


ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ዛሬ ፍድር ቀርቦ የዋስትና መብቱ ሳይጠበቅ ለዓርብ ቢቀጠርም የትግርኛ ሙዚቃ ለምን ተከፈተ ብሎ በሰው ላይ ጉዳት አድርሷል በሚል 2ኛ የክስ መዝገብ ተከፍቶበታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

በ4/12/06 እሁድ ማታ በደህንነት ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለውና በእስር ላይ የሚገኘው ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ከሳሹን ስላላገኘሁትና የህክምና ማስረጃውን ስላልደረሰልኝ የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልኝ ያለ ቢሆንም ወጣት ጥላዬ መርማሪው የምርመራ ስራን እየሰራ አይደለም ይልቁንም ራሱ ቢሮ የያዙኝ ደህንነቶች እየመጡ መርማሪው ባለበት ከእኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ እስካልሆንክና የምንሰጥህን ተልዕኮ እስካልፈፀምክ እዚህ ትበሰብሳለህ እንጂ አትወጣም እያሉ እንደሚዝቱበት ለፍርድ ቤቱ ቢያስረዳም ፍ/ቤቱ ፖሊስ ለ16/12/2006 ፖሊስ መረጃዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ እስከዛ የዋስና መብቱ ተቀባይነት አለማግኘቱን ብይን ሰጥቷል፡፡

ወደ እስር ቤት ሊሄድ በሚዘጋጅበት በድጋሚ ተጠርቶ 2ኛ የክስ መዝገብ እንደተከፈበት እና ክሱም በ12/10/2006 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ላይ የትግርኛ ሙዚቃ እንዴት ይከፈታል በማለት በሰላም የሚዝናኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት አድርሶ ተሰውሯል የሚል ሲሆን ስለቀቀረበበት ክስ የተጠየቀው ጥላዬ እኔ ከአካባቢዬ አልተሰወርኩም ሲይዙኝም ከቤቴ በር ላይ ነው እስከዚህ ሰዓትም አላመሽም ፖሊስ እያቀረበ ያለው ክስ ከሳሽ በሌለበት ራሱ እየፈጠረ መሆኑን ፍርድ ቤቱ እንዲረዳልኝ እና የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔ ባለኝ የፖለቲካ አመለካከት ጫና ለማሳደር የተወጠነ ውጥን መሆኑን መርማሪው ራሳቸው ያውቃሉ በማለት አስረድቷል ፡፡ፖሊስ ለምን ጉዳት የደረሰበትን ግለሰብ እንዳላቀረበና 2ወር ሙሉ ፖሊስ የት ነበራችሁ ብሎ ፍ/ቤቱ ቢጠየቅም ከሳሽ ለጊዜው እዚህ ስለሌለና ልናገኘው ባለመቻላችን የህክምና ማስረጃውን እንድናቀርብ ይፈቀድልን በማለቱ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ማስረጃ ለመመልከት በ2ኛው ክስ ለ14/12/2006 ዓ.ም ለ3፡00 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፖለስ እስካሁን በጥላዬ ላይ ክስ የመሰረተውን ከሳሽን ሊያቀርብ ካለመቻሉም ባሻገር ፍ/ቤቱን የህክምና ማስረጃ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ ማለቱ አግራሞትን ጭሯል፡፡


ጠብ-መንጃ አናነሳም! (ተመስገን ደሳለኝ)

“ብሶት የወለደው” ኢህአዴግ ከሁለት አስርታት በፊት በሰሜን ተራሮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር ያደረገውን የጎሬላ ውጊያ “አጃኢብ” በሚያሰኝ ቆራጥነት በድል መወጣቱ የማይታበል እውነትነው፤ ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላም ለሚሰነዘርበት ማንኛውም አይነት የኃይል ጥቃት፣ ያውም ማቸነፍ አለማሸነፉን ሳያሰላ በፍጥነት ዘሎ ለመዘፈቅ ሲያንገራግር የተስተዋለበት ጊዜም አልነበረም፤ አሀዱ ብሎ የአመፅ ትግል ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ላለፉት አርባ ዓመታት ከጀብሃ እስከ ኢህአፓ፤ ከኦነግ እስከ ኦብነግ፤ ከትህዴን እስከ አርበኞች ግንባር፤ ከሻዕቢያ እስከ አልሸባብ… በስም ተዘርዝረው ከማያልቁ ብረት-ነካሽ ድርጅቶች ጋር ወደ ፍልሚያ ለመግባት ከመወሰኑ በፊት ሰላማዊ መፍትሄዎችን ግራና ቀኝ የመፈተሽ ትዕግስትም ሆነ ልባዊ ፍላጎት እንዳልነበረው የራሱ የታሪክ ድርሳናት ሳይቀሩ በግላጭ ይናገራሉ፡፡ በተለይም ሀገር በቀሎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች በእንዲህ አይነቱ አስገዳጅ ሁኔታ ነፍጥ አንግበው የመገኘታቸው ምስጢር በቀጥታም ሆነ በዘወርዋራው የሥርዓቱ እጅ ስላለበት መሆኑን የሚያስረዱ ማሳያዎች የበዙ ናቸው፡፡ ከነዚህ መሀል አንዱና ዋነኛው በርሱ አጋፋሪነት የፀደቀውን ሕገ-መንግስት፤ በፕሮፍ መስፍን ወልደማርያም አገላለፅ “በሕገ-አራዊት”ነት ቀይሮ በአደባባይ መብቶቻቸውን መጨፍለቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በነፃ ምርጫ ማሸነፍም ሆነ ሥልጣን መጋራትን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ…›

ሻእቢያ ከከረን እና ከአስመራ ጦሩን ወደ ተሰንይ ማስፈሩን ተከትሎ ወያኔ ተጨማሪ ጦር ሲያጓጉዝ ዋለ።


የመከላከያ ሰራዊቱ ሊከዳ ይችላል በሚል ስጋት የወያኔ ጄኔራሎች ሲመክሩ ውለዋል።

ከሩሲያ ጋር የጦር ልምምድ ስምምነት እንዳደረገ የሚነገርለት የኤርትራ ገዥ ቡድን ሻእቢያ ከባለፉት ወራቶች ጀምሮ ጦሩን ወደ ደቡባዊ የኤርትራ ግዛቶቹ በመሰብሰብ ላይ መሆኑን ተከትሎ ወያኔም እንዲሁ ባለፈው ካሰፈረው ሰራዊት በተጨማሪ ከትላንትና ጀምሮ ከባድ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና ተጨማሪ የጦር ሰራዊት በአከባቢው በማስፈር ላይ መሆኑ ታውቋል።

አሜሪካ እና ሩሲያ በአከባቢው ያላቸውን የበላይነት ለመቀዳጀት ፉክክር በገቡበት በዚህ ወቅት አከባቢው የጦርነት ቀጠና እንደሚሆን ቀድማ አሜሪካ በበረራ ደህንንነ ሰበብ ሹክ ባለችበት ሰአት እንዲሁም የሻእቢያ ተቃዋሚ ሃይሎችን ወያኔ በገንዘብ እና በቅስቁስ እየረዳ ባለበት ጊዜ በተጨማሪም በአግል ወያኔያዊ ትእቢት እየዛተ እንዳለ ሲሆን ለወያኔ ከፍተኛ ስጋት የሆኑበት ኢርታራ ውስት የመሸጉ ተቃዋሚ ሃይላት ስለሆኑበት በጭቆና የተምረረው ምከልከያ ሰራዊት ተቃዋሚዎችን ይቀላቅላል የሚል ከባድ ስጋት በሕወሓት ጄኔራሎች ላይ መከሰቱን ምንጮች ጠቁመውል።

Sunday, August 17, 2014

እንደገና ይድረስ ለሠራዊቱ

“የትግሬ” ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ራሱን የሠየመው የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን አገሪቷን እያጎሳቆለ ያለው ከሠራዊቱ ጀርባ ተንጠላጥሎ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን የተሸከመውን ሠራዊት ሳይቀር በጉስቁልናና በድንቁርና እንዲኖር ፈርዶበታል። ህወሃት ሠራዊቱ እንዲማር፤ ዘመኑ ከሚፈቅደው የቴክኖሎጂ እውቀት ጋር ራሱን እንዲያዋህድ እና በራሱ የሚተማመን የዘመነ ሠራዊት እንዲሆን ፍላጎት የለውም።አሜሪካን በአገሯ በሚገኙ የጦር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ወታዶሮችን ለማሰልጠን ፍላጎት ብታሳይም ሳሞራ የኑስና መለስ ዜናዊ እምቢ ማለታቸውን አብዛኛው የሠራዊቱ አባላት የሰሙት አይመስልም። አሜሪካን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ 42 ወታደሮችን አገሯ ወስዳ ለማስለጠን በጠየቀች ግዜ ሳሞራ የፈቀደው 13 ወታደሮች ብቻ ሂደው እንዲማሩ ነው። እነዚህም ከህወሃቶች መካከል ፊደል የቆጠሩ ተፈልገው በመገኘታቸው መሆኑም ታውቋል። በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም የትምህርት እድሉን ተከልክለዋል።

ህወሃት ከራሱ ውጪ ያሉት ሌሎች ላይ ምንም ዕምነት እንደሌለው በተለያየ አጋጣሚ ተናግሮታል። የትምህርት ዕድሉን ለምን መጠቀም እንዳልፈለጉ ሲጠየቅ ሳሞራ የኑስ “ሌሎችን አናምናቸውም አሜሪካን ሂደው ይቀራሉ” ብሎ መልስ መስጠቱም ተመዝግቦ ይገኛል። 11ኛ ክፍልን ያልዘለለው የህወሃቱ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ሠራዊቱን ታማኝና የማይታመኑ በሚል ይከፍላቸዋል። የህወሃት አባል የሆነ ወታደር ታማኝ ፤ ሌሎች የሠራዊቱ አባላት የማይታመኑ።

ከግብረሰዶማውያኑ ጀርባ (አርአያ ተስፋማሪያም)

ከጥቂት አመት በፊት በኢትዮጵያ በተለይ አዲስ አበባ የሚገኙ ግብረሰዶማውያን ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በሸራተን ሆቴል የሃይማኖት አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በስፍራው ተገኝተዋል። ፕሮግራሙ ሊጀመር 15 ደቂቃ ሲቀረው በድንገት የደህንነት ሰዎች ይገቡና ጋዜጠኞች እንዲወጡ ያደርጋሉ። ቀጥሎ ለሃይማኖት መሪዎቹ « ይህን መግለጫ መስጠት አትችሉም» ተባሉ። « ማነው ከልካዩ?..» ሲሉ ጠየቁ፤ ጭራሽ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። የተቃውሞ መግለጫው በዚህ መልኩ ተደናቀፈ። በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተጠየቀ። የሸራተኑን መግለጫ ያደናቀፈው ባለስልጣን ጣልቃ ገብቶ ሰልፉን አስከለከለ። ይህን ሁሉ ያደረጉት የወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ያረጋግጣሉ። በቅርቡ አሜሪካ መጥተው የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ በአፍሪካ ከጤና ጋር በተያያዘ አንድ ተቋም በሃላፊነት እንዲመሩ ተፈልገዋል። ከያዙት ስልጣን ፓርቲያቸው እንዲለቃቸውና አሜሪካኖቹ ወደሚፈለጉት ቦታ ዶክተሩን ለመውሰድ እቅድ መኖሩን አንዲት ከፍተኛ ሃላፊን በመጥቀስ ምንጮች ገልፀዋል።ዶ/ር ቴዎድሮስ ስለዚህ ጉዳይ ይነጋገሩ አይነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም። ዶክተሩ የተመረጡት « በኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ሆነው ብዙ ነገር ሰርተዋል፤ ለምሳሌ ኤ.ች.አይ.ቪ/ ኤድስ፣ የወሊድ ቁጥጥር፣ የጤና ተቋማት ግንባታ..» ወዘተ በሚል ይጠቅሳሉ። ነገሩ ወዲህ ነው..የሚሉ ወገኖች ባለስልጣኑ የተፈለጉት « ለግብረሰዶማውያን መብት ዘብ በመቆም አሜሪካ በዚህ ዙሪያ ለምታራምደው አቋም ዶ/ር ቴዎድሮስ በተደጋጋሚ አጋርነታቸውን በማሳየታቸውና በተጨማሪ ስለግብረሰዶማውያን መብት ደግፈው ስለሚፅፉ ነው» ይላሉ። የሚያሳዝነው ዶ/ር ቴዎድሮስ « የማሰር ሱስ የለብንም..» ከማለት አልፈው የታሰሩትን ሙስሊሞች ከጓንታናሞ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውና ቀጥሎ ለማስተባበል መሯሯጣቸው ነው። እውነት ለመብት የቆሙ ቢሆን ኖሮ ከአምላክ ድንጋጌና ተፈጥሮ ላፈነገጡ ሳይሆን ካለሃጢያታቸው በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወገኖች መሆን ነበረበት።

Friday, August 15, 2014

ኢ.ሕ.አ.ግ ያሰለጠናቸውን ሰራዊቱን አስመረቀ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አንግቦ የተነሳውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማዳን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ለዓላማቸው ጽኑ የሆኑና በወታደራዊ የጦር ስልት ከጠላት ጦር የላቀ ሠራዊት በማፍራት በሰሜን ምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ ቦታዎች በወያኔ ላይ በሚያካሂዳቸው ውጊያዎች በጠላት ጦር ላይ ከባድ ውድመትን እያስከተለ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2006 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ለወራት በሽምቅ ውጊያ የወታደራዊ ሳይንስና በፖለቲካ መስክ ያሰለጠናቸውን የአርበኛ ሠራዊት ማስመረቁትን በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን የድርጅቱን ማሰልጠኛ ሃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።

የማሰልጠኛ ሃላፊው ለዘጋቢያችን እንደገለጹለት ከሆነ በአሁኑ ዙር የተመረቁት የአርበኛ ሰራዊት በተለያዩ የአየር ንብረቶች እና መልክዓ ምድሮች በቀንም ሆነ በለሊት በሚደረጉ ውጊያዎች በቀላሉ በጠላት ጦር ላይ የበላይነትን ለመቀዳጀት የሚያስችል የሽምቅ ውጊያ ወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

የድርጅቱ ሥራ-አስፈፃሚዎች በተገኙበት የተካሄደው በዚህ የምረቃ ፕሮግራም ላይ ተመራቂ አርበኞቹ በስልጠና ወቅት በቀሰሙት ትምህርት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማዳን ተልዕኮን ከግብ ለማድረስ የበኩላቸውን አሰተዋጽኦ ለማድረግ በቁርጠኝነት መነሳታቸውን እና ለዚህም ዓላማ መሳካት የህይወት መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የድርጅቱ ሊቀ-መንበር አርበኛ መዓዛው ጌጡ ለተመራቂ አርበኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያሰተላለፉ ሲሆን ሊቀ-መንበሩ አክለውም “በዛሬው ዕለት የተመረቃችሁ አርበኞች በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ በአምባገነኑ ወያኔ አማካኝነት የተጋረጠውን የሕልውና አደጋ የመታደግ ትልቅ ኃላፊነት እና አደራ ያለባችሁ በመሆኑ ለቆማችሁለት ዓላማ በጽናት፣ በትዕግስትና በቆራጥነት የበኩላችሁን ድርሻ መወጣት አለባችሁ!” በማለት ለተመረቂ የአርበኛ ሰራዊት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው።

ፍርድ ወይስ ፍዳ !

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአናዋር መስጊድ በተነሳው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት፤ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ኢብራሂም አብዱልሰላም እና ወ/ሪ ወይንሸት ሞላ እንዲሁም የአዲስ ጉዳይ መፅሔት ፎቶ ግራፈር አዚዛ መሐመድ ከህግ አግባብ ውጪ ለተጨማሪ 48 ሰዓት በእሰር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ፡፡
ሚክሲኮ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባቀረበው የክስ አቤቱታ መሠረት በተለያየ ቀናት ከሳሽን እና ተከሳሽ መካከል ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ሐምሌ 29 እና 30 ተከሳሾች (እነ ወይንሸት) እያንዳንዳቸው 5000 ሺህ ብር የሚገመት የንብረት ዋስ አሲዘው እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ይግባኝ በመጠየቅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻር በማድረግ 30 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት አስደርጓአል፡፡ይህን የህግድ ውሳኔ የሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ነው፡፡ይሁን እንጂ የዚህን ትህዛዝ በክስ መዝግብ ውስጥ ፖሊስ ሳያካት ወይም ቀድሞ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት ሳያሳውቅ እነ ወይንሸትን ፖሊስ በራሱ ፍቃድ ብቻ እስር ቤት ሊያቆያቸው ችሎአል፡፡

ጋዜጠኛና መምህርት ፌቨን ከፈለኝ በህክምና ላይ እያለች አረፈች

• የመኪና አደጋ ያጋጠማት ጋዜጠኛና መምህርት በህክምና ላይ እያለች አረፈች
• በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቢሮ በኩል ድንገት የመጣ ሚኒባስ ታክሲ ገጭቶ ጉዳት እንዳደረሰባት ምንጮች ተናግረዋል።
• ሥርዓተ ቀብራ ዛሬ በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 8፡00 ይፈጸማል

ባሳለፍነው ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሚኒባስ ታክሲ የመገጨት አደጋ ደርሶባት ራሷን በመሳት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ እያገኘች ያለችው ጋዜጠኛና መምህርት ፌቨን ከፈለኝ ከኮማ ብትነቃም አስቸኳይ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ቤተሰቦቿና ወዳጆቿ ቢስታውቁም ትናንት አረፈች።

በኤፍ ኤም 97.1 “ሃሎ ሌዲስ” ፕሮግራም መሪነትና በስኩል ኦፍ ቱሞሮ መምህርነቷ የምትታወቀው ይህቺ ወጣት ጋዜጠኛ “እፍርታም”ና “ፍቅርን ፈራሁ” በተሰኙ የፊልም ስራዎቿም የምትታወቅ ተዋናይ ነበረች። ወጣቷ ባለፈው ሐሙስ የ“ሃሎ ሌዲስ” ፕሮግራሟን ጨርሳ ከስቱዲዮ በመውጣት ላይ ሳለች በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቢሮ በኩል ድንገት የመጣ ሚኒባስ ታክሲ ገጭቶ ጉዳት እንዳደረሰባት ምንጮቻች ተናገረዋል።

ለቀናት ራሷን ሳታውቅ የቆየችው ፌቨን፤ በጥቂቱም የነቃች መሆኗን ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ አስታውቀው ነበር፡፡ ከዶክተሮቹ አገኘነው ባሉት መረጃ መሠረት በጭንቅላቷ ውስጥ ደም በመፍሰሱ ምክንያት አስቸኳይ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያስፈልጋት ተናግረው ነበር፡፡ በሆስፒታሉ የሰርጂካል ክፍል ውስጥ ህክምናዋን በመከታተል ላይ ለነበረው ፌቨን ለማገዝ እንቅስቃሴ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ጋዜጠኛ፣ ተዋናይትና መምህርት ፌቨን ከፈለኝ –  አርፋለች፡፡

ለመላው ቤተሰቦቻና አድናቂዎቻ መፅናናትን እንመኛለን ነብስ ይማር!


Thursday, August 14, 2014

ሁጋንዳ ካንባላ ውስጥ ሦስት ኢትዮዽያን በሸብርተኝነት ተጠርጥረው ታሰሩ።

ዩጋንዳ ካምፓላ በሸብርተኝነት ተጠርጥረው የታሰሩትን ኢትዮጲያዊያን ፖሊስ ጣቢያ ያጡአቸው ወገኖች የት እንደታሰሩ ለማወቅ ባደረጉት ጥረት ወደሌላ እስር ቤት ተዛውረዋል የሚል መረጃ እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡
ጉዳያቸውም ወደፍርድ ቤት ሊመራ መሆኑን የዚህ አዲስ ወሬ ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን የታሳሪዎቹ የመኖርያ ወረቀት ያንዱ ወቅቱ ያለፈና የሌላኛው ጨርሶ ማስረጃ የለውም መባሉ ታሳሪዎቹን ለመጎብኘትና የማስፈታት ጥረት ለማድረግ አስቸጋሪ እንዳደረገው ምጮች ገልፀዋል።

የሁጋንዳ ፖሊስ ኢትዮዽያኖቹን ለማሰር ያቀረበው የአሸባሪነት ውንጀላ ከህወሀት መራሹ የኢትዮዽያ መንግስት ጋር ተያያዚነት አንዳለው ያሳወቁት ምንጮች ወደ አገራቸው ቢመለሱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ፍርሀታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል።


ወያኔ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል

አሁን በስልጣን የሚገኘው የወያኔው ስርአት ላለፉት 22 አመታት የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያለ ጆሮአችንን ቢያደነቁረውም እሱ የሚለው የዲሞክራሲ ስርዓትና ትክክለኛው ዲሞክራሲያዊ ስርአት አራምባና ቆቦ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲያዊ ስርአትን በገመድ ለክቶና መጥኖ የናንተ መብትና ነጻነት እስከመጨፈር እንጂ የኔን ስልጣንና ጥቅም የሚነካ ከሆነ ቢላ ባንገቴ ካለን ሰነባበተ:: ለዚህም ይመስላል በተለይም ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ድምጻቸውን ለሚያሰሙ ጋዜጠኞችም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኙ ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚለው::
ከዚህም የነጻነት እጦት እና ፍጹም አምባገነናዊ አፈናዎች መካከል እንደ አንድ ማሳያ የሚሆነው በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል ሲሆን ዛሬ በወያኔው ስርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚታዩት እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ሳይሆን ሃገርን ለማፍረስ እንደተዘጋጁ አሸባሪዎች ተደርገው ነው:: በጣም የሚያሳዝነውነና አደገኛው አካሄዱ ደግሞ ይህን እምነቱን ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምንና እንዲቀበል ፍጹም ህገወጥ በሆነና ከዕውነት በራቀ ውንጀላ ተቃዋሚዎችን ለማጠልሸት የሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግሉ ነው::

የስብሃት ነጋ ባለቤት ሻለቃ ፀአዱና ሟቹ ዶ/ር ልኡል-ከኢየሩሳሌም አርአያ

ሻለቃ ፀአዱ የህወሓት ታጋይ የነበረች ናት። ከኤርትራና ጣሊያን የዘር ግንድ ያላት ሻለቃ ፀአዱ የቀይ ቆንጆ ናት፤ ገፅታዋን በመመልከት ማንነትዋን በቀላሉ መገመት ይቻላል። የሽማግሌው ስብሃት ነጋ ባለቤት ነበረች። ሽማግሌው ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት የሚታወቁበት ባህርይ ሴሰኝነታቸው ነው። ከፀአዱ ጋር ከበረሃ የጀመሩት ፆታዊ ግንኙነት እስከ 1990ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ሲሆን በ <አብሮነት> ጊዜያቸው ልጆች አፍርተዋል።
በኮንኮርድ ሆቴል ጀርባ ገባ ብሎ በሚገኘው የተንጣለለ ቪላ የሚኖሩት ሽማግሌው ስብሃትና ሻለቃ ፀአዱ ነጋ-ጠባ ሲያነታርካቸው የነበረው አስገራሚ «አጀንዳ» ፈንድቶ የወጣው ከላይ በተጠቀሰው አመት ነበር። በፓርቲው ሕግ፥ “አንድ የማ/ኰሚቴ አባል በትዳሩ ላይ ችግር ሲከሰት ጉዳዩ የሚታየው በድርጅቱ አመራር ነው”፤ ከዚህ ባለፈ ወደ ፍ/ቤት መሔድ አይቻልም። በዚሁ መሰረት ሻለቃ ፀአዱ ለፓርቲው አመራር አቤቱታ ታቀርባለች። ባጭሩ ያለችው ፥« ..ባለቤቴ ስብሃት ነጋ በትዳራችን ላይ እየማገጠ ነው፤ በተደጋጋሚ ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ብመክረውም ጨርሶ ሊሰማና ሊታረም አልቻለም። … ስለዚህም የፍቺ ጥያቄዬን የፓርቲው አመራር ተቀብሎ እንዲያፀድቅልኝ እየጠየኩ..የልጆች ማሳደጊያ ተቆራጭ አብሮ እንዲወሰንልኝ አያይዤ አመለክታለው።»
ጉዳዩን የተመለከተው ከፍተኛው አመራር (የፖሊት ቢሮ) ሁለቱንም አስቀምጦ ለማስታረቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ጭራሽ ባልና ሚስቱ አስገራሚ የዘለፋ ቃላት ተወራወሩ፤ ሽማግሌው ስብሃት በሰጡት የአፀፋ መልስ «እርሷ የምትሰራውን ነው የሰራሁት…» ሲሉ አፈንድተውት አረፉት። (ሌሎቹ የቃላት ልውውጦች አፀያፊ በመሆናቸው ዘልያቸዋለሁ)

የወልቃይት ጠገዴ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትግራይ ውስጥ አንሰበሰብም እያሉ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የወልቃይት ጠገዴ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትግራይ ውስጥ አንሰበሰብም እያሉ ነው::
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ወረዳው ወደ ትግራይ መቀላቀሉን በመቃወም ላይ መሆኑን እና ከወያኔው ጦር ጋር ተፋጦ እንዳለ ከአከባቢው የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ:: በአከባቢው ከፍተኛ ጦር በማስፈር ሕዝቡን እያሸበሩ እና እያሳደዱ መሆኑ ታውቋል:: በአሁን ሰአት እንደ አዲስ ከአንገረብ ወንዝ ምላሽ በመውሰድ ለመከለል ሲሆን ወልቃይት ጠገዴ ግን እኛ አማሮች ነን ከጎንደር ነን እያለ ሲሆን ወያኔ ለመስማት ዝግጁ አይደለም ይህንን ተከትሎ የወልቃይት ህዝብ እየታሰረ ሲሆን እስካሁን ወልቃይት አማራ ነው ስላሉ ብቻ ወደ ወህኒ የተወረወሩት ታጋይ ሃጎስ ደሳለኝ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የህዝቡ ጥያቄ ትግሬዎች ተከዜን ይሻገሩልን ሲሆን የኛ የሚሉት የቦታ ስም ማይ አምባ ስላንዲ ገቸው ዳንሻ ዳራ ሻሃን ምድረገበታ አዲሳለም ናቸው ::
ወያኔ ቦታዉን ከ1984 ጀምሮ ከወልቃይት ህዝብ ላይ በመውሰድ አዘናግቶ ወደ ትግራይ የቀላቀሉት ሲሆን የትግራይ ሕወሓታዊ ካድሪእዎችን በማፍሰስ በወልቃይት ሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ ነው::ሕዝቡ ያኮረፈ ሲሆን የተወሰነው ወደ ኤርትራ ሱዳን እና አርማጮህ ተሰዷል ሸፍቷል:: የወልቃይትን ህዝብ አሳልፈው እያስገደሉ እያሳሰሩ ያሉ ግለሰቦች ለከፍተኛ ስልታን እና ለፓርላማ አባልነት እንዲያገለግሉ እየተደረገ ሲሆን ከነዚሁም ውስጥ አቶ ሹምዪእ ገብሬ አቶ መንግስቱ አቶ አዘነው ከነልጁ ባለስልጣን ሆኗል:; እንዲሁም ሕወሃት የትግራይ ክልል ውስጥ አትከልሉን ያሉትን እንዲያድኑ ለካድሬዎቹ መሳሪያ በነብስ ወከፍ አድሏል::በፊትለፊት ህዝቡ ላይ መሳሪያ በመደቀን ሕዝብን እያሸበሩ ይገኛሉ::
ወልቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ ክልል እንዲሆን የሚታገሉ
1 mengiste Alemu 2 shumye gebre 3 Desalegn G/R 4 Alemu tamalew 5 Andarge mekonen 6 sisay tela 7 ferede mola 8 melke tiruneh 9 Azanew gebrye 10 kes alemaw 11 Alemneh kide 12 Haile G/medhn 13 Tagey merzo 14 Tagay laqew ሲሆኑ
ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ አካል አይደለም የሚሉእና የሚታገሉ 1 berihun wolde 2 kasahun sisay 3 Agerew Wasie 4 Asmamaw Tafere 5 Fitalew tafere 6 Kefyalew tilahun 7 Alemaw wagnew 8 zafie asefa 9 Alemu tizazu 10 desalegn warkaw 11 fiteray G.Maryam እና ሌሎችም በበላይነት እንቅስቃሴውን እየመሩት ነው::
በአሁን ወቅት የክረምቱን መግባት ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዝምታን ቢላበስም የሚጠብቀው መስከረም እስኪጠባ በጋ እስኪሆን ድረስ ነው በአከባቢው ይህንን ያወቀው ወያኔ ሰራዊቱን እና ያስታጠቀውን ሚሊሻ በተጠንቀቅ አከባቢው ላይ አስፍሯል::እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ከሱዳን ሰራዊት ገብቷል::ይህ ደሞ አማራ ነኝ የሚለው የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ አስቆጥቷል::
በዚህ ወር ወያኔ እረፍት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ለመሰብሰብ ዝግጅት እያደረገ ነው :: የወልቃይት ጠገዴ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትግራይ ውስጥ አንሰበሰብም እኛ አማሮች ነን በማለት ጎንደር ዩንቨርስቲ ነው የምንሰበሰበው ብለዋል:: ሆኖም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ግደይ አዛናው ወደ ጎንደር ማንም ተማሪ መሄድ የለበትም ሲል አስጠንቅቋል:: ይህን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወላጆች ቁጣቸውን እንደገለጹ ታውቋል::ተማሪዎቹም ትግራይን አናውቅም ጎንደር ነው የምንሄደው በማለት ለማስጠንቀቂያው ምላሽ ሰቷል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በወያኔ አገዛዝ የተማረረ ስለሆነ ወደ ጎንደር ;አርማቾህ ;ክራክራ;እርጎዬ;ሰሮቃ;ዳባት;ደባርቅ በመሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል::


Wednesday, August 13, 2014

2007ን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሲባል እስከ ምርጫ ወይስ እስከ ዴሞክራሲያዊ መንግስት (ዳንኤል ተፈራ)

በጣም በቅርቡ አንድ ስላልነገርኩት ስሙን የማልጠቅሰው ጉምቱ የሚባል ጋዜጠኛ ወዳጄና ሌላ አንድ ጎልማሳ ጋር ኢ-ወጋዊ በሆነ መንገድ ስለተቃዋሚ ጎራው ማውጋት ይዘናል፡፡ የጨዋታችን መነሻ ደግሞ አንድነትና መኢአድ ከብዙ ውጣ ውረድና ድርድር በኋላ ከፍፃሜ ለማድረስ ደፋ ቀና እያሉበት ያለው ውህደት ነው፡፡ የተቃውሞ ፖለቲካውን በቅርበት እንደሚከታተሉ አንዳንድ ግለሰቦች አስተያየት ‹‹ውህደቱ መሳካት አዎንታዊ ጎን ቢኖረውም ዘግይቷል፡፡ በዚህ ጊዜ የውህደቱ ጣጣ አልቆ፣ የሚተባበሩት ተባብረው ወደ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ የሚገቡበት ነበር›› ይላሉ፡፡ የውህደቱ መሳካት ጥሩ ሆኖ ውህደቱም ሆነ ትብብሩ ዘለቄታ ላለው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት ወይስ ምርጫ ስለደረሰ ብቻ? የሚል ጥያቄ አንስቶ መመለስ ተገቢ ነው፡፡ጎልማሳው ሰው ቀበል አድርጎ ለተቃዋሚው ጎራ ቅርበት አለው ብሎ ስላመነ ይመስለኛል አይኖቹን እንደ ቆመህ ጠብቀኝ መሳሪያ ፊቴ ላይ ወድሮ ‹‹በተቃውሞ ጎራው በኩል ተቀራርቦ፣ ተባብሮና ተዋህዶ የመስራቱ ነገር እምብዛም ባለመለመዱ ወይም እስካሁን ባለመሳካቱ

ኤርትራ የሩሲያን የጦር ልምምድ ልታስተናግድ ነው

በመላኩ ጸጋው
በቅርቡ በተለያዩ አካባቢዎች ተከታታይ የጋራና የተናጠል የጦር ልምምድ ያደረገችውን ሩሲያን በቀጣይ በኤርትራ በቀይ ባህር
አካባቢ ልታስተናግዳት መሆኑን “ጊሲካ አፍሪካ ኦንላይን” በአውሮፓ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ከሰሞኑ
ባሰራጨው ዘገባ ገልጿል። የልምምዱ ዋነኛ ዓለማ በአንድ መልኩ የሩሲያን ጦር ዝግጁነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በኤርትራ
ወደቦች አቅራቢያ ሩሲያ ቋሚ የጦር ሰፈርን (Military base) ለማቋቋም መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። እንደ ዘገባው
ከሆነ የሩሲያ የጦር ልምምድ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኤርትራ ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ በሩስያ እንደ አንድ ስትራቴጂክ
አጋር ሀገር እየታየች መሆኗን ዘገባው አመለክቷል። እንደዘገባው
ከሆነ አሜሪካ በጅቡቲ ቋሚ የጦር ሰፈር ያላት ሲሆን በተለያዩ
ጊዜያትም ከጅቡቲ ወታደሮች ጋር የአየር ኃይልና የባህር ኃይልን
ባቀናጀ መልኩ የጦር ልምምድ ታደርጋች። ጅቡቲ የአሜሪካንን
ጦር ከማስተናገድ ባለፈ በዋነኝነትም የፈረንሳይ የጦር ሰፈር
በመሆን እያገለገለች ነው። ሱዳን በአንፃሩ ኢራን በቀይ ባህር
የሱዳን ምዕራባዊ ግዛት የባህር ኃይል ቤዝ እንድትመሰርት
ለማድረግ እንቅስቃሴ የጀመረች መሆኗን ቀደም ያሉ የዩናይት
ፕሬስ ኢንተርናሽናል UPI ዘገባዎች ያመለክታሉ። ይህ የሱዳን እንቅስቃሴ ግን በእስራኤል አልተወደደም።
ሩሲያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተከታታይ የጦር ልምምዶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። እንደ ዘጋርድያን

በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ።

ወያኔ ራሱን ለማንገስ ከሚጠራው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ጦርነት ሊካሄድ ይችላል ሲሉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።በተለያዩ አጋጣሚዎች የተነሱ የሳተላይት ፍቶዎች በማስረጃነት በመጥቀስ ይህን ሰሞን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአፍሪካ ህብረት ሰዎች እና ከአከባቢው የፖለቲካ አዋቂዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያካሂዱት ዋናው የዚሁ ጦርነት ስጋትና አከባቢው ላይ ብሄራዊ ጥቅማቸው ላይ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን በመገምገም ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካ መንግስት የሲአይኤን ሪፖርት ተከትሎ በትራንስፖርት ቢሮአቸው አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የአየር በረራ የሚከለክል ደንብ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፤ የዚህ ጉዳይ ዋነኛ ምክንያት ደሞ አከባቢው ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑና በጦርነት ቀጠና የተመዘግበ ድንገት ጦርነት ይነሳል የሚል ግምት የተወሰደበት መሆኑ በአከባቢው ከፍተኛ የሆነ ከባድ መሳሪያዎች ታንኮች እና ብረት ለበስ አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹ በመሆኑ ጦርነት አይቀሬ ስለሆነ በቋፍ ላይ ባለ የጦርነት ቀጠና ላይ አየር ማብረሩ ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ፡፤ስለዚህ እንደ ዲፕሎማቶቹ እምነት ከወያኔያዊው ምርጫ በፊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ያስጋል።

በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ ወደ ድንበር ከተማው ኩምሩክ አክባቢ በግምት 50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የወያኔው መከላከያ ሰራዊት ካምፕ አቅራቢያ በሰራዊቱ እና ከደቡብ ሱዳን ሰርገው ገብተዋል በሚባሉ ሃይሎች መካከል የ3 ሰአታት ጦርነት መካሄዱን አንድ የምእራብ እዝ መኮንን በላኩልኝ መረጃ ገልጸዋል።

ወታደሮቹ በክምፑ አከባቢ ቅኝት በሚያደርጉበት ጊዜ ድንገት የመጡ ሰርጎቦች የተባሉ ሃይሎች አከባቢውን በመውረር ከባድ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን 26 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲግደሉ በርካቶች ቆስለዋል። በዚህ የሰአታት ጦርነት እንደ መኮንኑ አባባል ከተዋጊዎቹ ወገን ጥልው የሸሹት ሁለት ሬሳ ብቻ ነው ብለዋል።

Tuesday, August 12, 2014

ፕሬስ የሌለው መንግስት ከሚኖረን መንግስት የሌለው ፕሬስ ቢኖረን እንመርጣለን

እርግጥ ነው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ለስደት ሲዳረጉ ‹‹አዲስ ዘመንንም አዲስ ነገርንም አላነብም››በማለት ነግረውን ነበር፡፡ሌጋሲያቸውን ለማስቀጠል ቤተ መንስግስት የገቡት ሃይለማርያም በበኩላቸው በአንድ ጋዜጣዊ መግለጫ የፎርቹንን ኮሪደር እንደሚያነቡ ሲናገሩ አድምጫለሁ፡፡
የቅንጅት አመራሮች በድርድሩ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እንደገቡ ብዛት ያለው የኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተጠርዞ መመልከታቸውን መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡ገዢዎቻችን ከቀድሞዎቹ ነገስታት ባነሰ መልኩ ‹‹አዝማሪ ምን አለ?››በማለት ለመጠየቅ አለመፍቀዳቸው ትርጉሙ ንቀት ብቻ ነው፡፡ህዝቡን የሚፈልጉት እነርሱ ሲናገሩ እንዲያደምጥ ብቻ እንጂ ሲናገር ሊሰሙት አይደለም፡፡ስለዚህ ጋዜጦችን አያነቡም፡፡የማያነቧቸውን ጋዜጦች አዘጋጆች ለስደት ሲዳረጉ ደግሞ ቅንጣት ታህል አትሰማቸውም፡፡
በጥቂት ወራት ውስጥ የተደረጉ ፕሬስን ከአገሪቱ ገጽ ለማጥፋት የተወሰዱና እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ተመልከቱ፡፡ጋዜጠኞች ተሰባስበው ለመመስረት ቀና ደፋ ያሉለት አዲስ ማህበር እውቅና ተነፈገው፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ሶስት ጋዜጠኞች ለእስር ተዳረጉ፣ትግራይን ህዝብ ፍዳ በሶሻል ሚዲያ ሲያጋልጥ የቆየው አብርሃ ደስታ ጨለማ ቤት ተወረወረ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስጠናሁ ያለውን ወረቀት አቅርቦ ጋዜጦችን በኒዮ ሊበራሊስትነት ከሰሰ፣ከጫካ ጀምራ የህወሃት አፍ የነበረችው ፋና የጋዜጣ አከፋፋዮች ላይ ዘመቻ ከፈተች፣ዘመቻውን ተከትሎ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ አከፋፋዮችና ጋዜጣ አዟሪዎች ስቅይት ደረሰባቸው፣ፍትህ ሚኒስትር የህትመት ውጤቶች አሳታሚዎች ላይ ከፍተኛ የወንጀል ክስ መመስረቱን ነገረን፣ክሱ መነገሩን ተከትሎ ማተሚያ ቤቶች ጋዜጦችን የማስተናገድ ፍርሃት ወረራቸው አንዳንዶቹም በግልጽ ይህን ጋዜጣ እንዳናትም ቀጭን ትዕዛዝ ደርሶናል አሉ፣ካፌዎች በግድግዳቸው ላይ ‹‹ጋዜጣ ባለማንበብዎ እናመስግናለን እና ጋዜጣ ማንበብ አይቻልም››የሚሉ ማስታወቂያዎችን መለጠፍን ስራቸው አደረጉት ፡፡
ስደት ብርቃችን አይደለምና ይህው የተወዳጇን አዲስ ጉዳይ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጆች ስደት ሰማን ፡፡ይህ ለኢህአዴግ ምኑ ነው?ፕሬስ የሌለው መንግስት እንዲኖረን የሚፈልግ በመሆኑ ደስታውን የሚችለውም አይመስለኝም፡፡ኮካዎች ምን ትላላችሁ?

ዳዊት ሰሎሞን


የስብሃት ነጋ እህት ቅዱሳን ነጋ “ቀጭን” ትእዛዝ፦

የስብሃት ነጋ እህት ቅዱሳን ነጋ ይባላሉ። የቅዱሳን ባል ደግሞ ፀጋይ በርሄ ሲሆኑ ሃለቃ ፀጋይ የፌዴራል ደህንነት ዋና ሹም ናቸው። የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የሆኑት ቅዱሳን ነጋ ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ውጭ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ነበር። የእጅ ስልካቸውን በማንሳት ስልክ ይመታሉ፤ የደወሉት በወቅቱ የኢ.ቲቪና ራዲዮ ስራ አስኪያጅ ለነበረው ዘርአይ ነበር። ቅዱሳን እንዲህ አሉ፥ « በትላንትናው ዕለት በትግርኛ ቲቪ ፕሮግራም ላይ የቀረበውን ዝግጅት ያሰናዳው ጋዜጠኛ በአስቸኳይ ከባድ ቅጣት እንድትጥልበት። አሁን ወደ ውጭ እየሄድኩ ነው፤ ስመለስ ያልኩህን እርምጃ ወስደህ ካልጠበቅከኝ.. ቅጣቱ ወደአንተ ይዞራል» ሲሉ ያንባርቁበታል። ዘርአይም « እሺ የተባለውን እፈፅማለሁ» ሲል መለሰ። ጋዜጠኛው ትግራይ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ ችግር በማቅረቡ ነበር በቅዱሳን የቅጣት ትእዛዝ የተላለፈበት። አሁን ከስልጣን የተነሳው የአቶ መለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ ካድሬው ዘርአይ ጊዜ ጠብቆ በስልክ የተላለፈችውን የቅዱሳን “ትዕዛዝ” በስልኩ ድምጿን ቀርፆት ኖሮ በቅርቡ ለሚቀርባቸው የፓርቲው ሰዎች ሲያስደምጥ እንደነበረ ማወቅ ተችሏል። ..መብት፣ ነፃነት፣ ህግና ህገ መንግስት..ወዘተ ቦታ የላቸውም። ወረቀት ላይ የሰፈሩ – ነገር ግን በተግባር የሌሉ ናቸው። ጋዜጠኞች የሚታሰሩት፣ ሌሎች ወገኖች የሚደበደቡትና የሚንገላቱት እንዲህ በስልክ ባለስልጣናት በሚሰጡት “ቀጭን” ትእዛዝ ነው። አይ አገሬ!…

እየሩሳሌም አርአያ


ከኢንጂነር ግዛቸው ካቢኔ አምስቱ ራሳቸውን አገለሉ

ኢንጂነግር ግዛቸው በሕዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀዉን፣ ለአገዛዙ ራስ ምታት የሆነው፣ የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴን አፈረሱ። በአባላትና ደጋፊዎች ዘንድም ትልቅ ድንጋጤ ተፈጥሩዋል። ከመኢአድ ጎን በመቆም አጋርነት ይገልጻሉ፣ ምርጫ ቦርድ ላይ በጋራ ጫና ለማድረግ ድርጅታቸው ያሰልፋሉ ተብለው የሚጠበቁት፣ ኢንጂነር ግዛቸው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት አገር ዉስጥ ላሉ ጋዜጦች የሰጡትን አስተያየት በመቀልበስ፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴዉን ያፈረሱ ሲሆን፣ ለውህደት በሚደረገዉ ከፍተኛ ትንቅን ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ ከልብሰዉበታል።
«ኢንጂነር ግዛቸው በአሁኑ ወቅት ከመኢአድ ጋር በመሆን፣ በጋር የሚሊዮኖች ንቅናቄን በማጡዋጣፍ ፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ፣ በምርጫ ቦርድና አገዛዙ ላይ ጫና ማሳደር ሲገባቸው፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴውን ማፍረሳቸው ሰላማዊ ታጋዮች አንገት የሚያስደፋ ነው» ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ የኢንጂነሩን ዉሳኔ የሚረዳዉና የሚጠቅመው አገዛዙን ብቻ እንደሆነም ይናገራሉ። በዚህም ያልተደሰቱት የአንድነት አምስቱ አመራሮች

ከኢንጂነሩ ካቤኔ ውስጥ መቀጠላቸው ትርጉመ ቢስ መሆኑን መረዳታቸውን በመግለጽ ለግዛቸው ደብዳቤ ያስገቡት የአንድነት አመራሮች
ተክሌ በቀለ –ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት
በላይ ፈቃዱ —ምክትል ፕሬዘዳንት
ሰለሞን ስዮም —የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ
ዳንኤል ተፈራ — የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ
ዳዊት አስራደ —የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሀላፊ ::

ፓርቲው በወጣት ተመርቶ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመጣመር እና በመተባበር የሚሰራበትን ቀን እንዴት በጉጉት እየጠበቀን እንዳለ ማን ይንገራቸው ??? የፓርቲዉን ሰምም ፣ልፋትም ለማይረባ ስልጣን ብለው ወደህዋላ ባይ ጎትቱት ምን አለ !!!እነዚያ በዓላማቸው ፀነተው በእስር የሚማቅቁት ጀግኖች አያሳዝኑዋቸዉም እንደ ? ወዴት እያመራን ነው? ምነው ኢትዮዽያኖች አንድ መሆን አቃተን ?


ኢንጅነር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት እርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ!

በኢትዮጵያ ተወካይ ያላቸው 20 የአውሮፓ አባል አገራት
ተወካዮች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ቢሮ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያስረዱ የተጋበዙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ወደባሰ ችግር ሳትገባ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡
የአውሮፓ ሉዑካን ኃላፊ የሆኑት ሚስስ ባርባራ በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኙት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ስለሚያደርገው አፈና፣ ሰብአዊ መብት ረገጣ፣ በሚዲያው ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ፣ ስለታሰሩት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን አስረድተዋል፡፡
ኢንጅነር ይልቃል ስለ ኢህአዴግ ሁኔታ በተጠየቁበት ወቅትም ‹‹ኢህአዴግ በራሱ ችግር፣ በርዕዮት ዓለም መደናበር፣ በአመራር ብቃት ማነስ ምክንያት ምርጫውን ክፍት በማድረግ ዴሞክራሲን መፍቀድ ዋጋ እንዲሚያስከፍለው ያውቃል፡፡ በሌላ ኩል ምርጫን ማጭበርበርም ጣጣ እንደሚያመጣበት ተረድቷል፡፡ በመሆኑም ምርጫ ማጭበርበርም ሆነ ምርጫውን ክፍት ማድረግ ችግር እንደሚፈጥርበት ስለሚያውቅ ከወዲሁ አፈናን መርጧል›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ኢንጅነር ይልቃል ‹‹በቀጠናው ባላችሁ ጥቅም ምክንያት ኢህአዴግን እየደገፋችሁ፣ ህግና ባህላዊ መሰረት የነበረበት አገር ወዳልሆነ አቅጣጫ እያመራች ነው›› ብለዋል፡፡ ኢንጅነሩ አክለውም ‹‹ኢህአዴግን ስለምትደግፉ፣ ወጣት ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ሲታሰሩና ህዝብ አማራጭ እንዲያጣ ሲደረግ ዝም በማለታችው የኢትዮጵያ ህዝብ የኢህአዴግ እንጅ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጎ አያያችሁም፡፡›› በሚል በህብረቱ አባላት ተወካዮች ላይ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡
የህብረቱ አባላት ‹‹ምን እናድርግ?›› በሚል ላቀረቡላቸው ጥያቄ ‹‹ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ ሙጋቤ ላይ ከወሰዳችሁት እርምጃ መካከል ትንሹን እንኳ ኢህአዴግ ላይ ብታደርጉት ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችሉ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫ በመሆኗ፣ በአፍሪካ ቀንድም ወሳኝ አፈርና ለቀይ ባህርም ያላት ቅርበት ለዓለም ደህንነት ከዚምባብዌ በላይ ጠቃሚ አገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ በመግባቷ የእናንተም ብሄራዊ ጥቅም ጭምር ነው ችግር ውስጥ የሚገባው፡፡ በመሆኑም ለኢትዮጵያውያንም ለራሳችሁም ሲባል ኢትዮጵያ የባሰ ችግር ውስጥ ከመግባቷ በፊት አንድ እርምጃ መውሰድ አለባችሁ፡፡›› በሚል እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡


የ”ብርቱው ሰው” መልዕክት – ከቃሊቲ እስር ቤት (በኤሊያስ ገብሩ)

‹‹ለእውነት መቆም ካልተቻለ ስብዕና ይወርዳል፣ ሕሊናህም ይሞታል››
‹‹የክስ እና የእስር መብዛት … የድል ጊዜ እየቀረበ መሆኑን ያሳያል››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)
‹‹እ… እስክንድር “The Iron man’’?››
የቃሊቲ ጠባቂ ፖሊስ
————————————–
ጥቁር ሰኞ (Black Monday) ከሚሉት ወገን አይደለሁም፤ በአባባሉም አላምንም፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ በሁሉም ቀናቶች ጥሩም ሆነ ጥሩ ያልሆነ ሁነቶችን ሊያስተናግድ ይችላል፡፡ ይህንን ማለት የወድድኩት ዛሬ ሰኞ በመሆኑ ነው፡፡ ብዙዎች ዕለተ ሰኞ እንደሚከብዳቸው እና እንደሚጫጫናቸው ይናገራሉ፡፡ በቀናት መጥቆር እና መንጻት ማመናችንን ትተን፣ እያንዳንዱ ቀናቶችን ለሥራ እና ለመልካም ነገሮች በአግባቡ ብንጠቀምባቸው መልካም እያልኩ ወደዋናው ርዕሰ ጉዳዬ ላምራ፡-
18 ዓመት ተፈርዶበት በቃሊቲ ወህኒ ቤት ታስሮ የሚገኘውንና እጅግ የማከብረውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በቃሊቲ ከጠየኩት አንድ ወር ገደማ ሆኖኝ ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ልጠይቄው አስቤ፣ በአዲስ የጋዜጣ ሥራ ተጠምቼ ስለነበር ሳልችል ቀረሁ፡፡ ዛሬ ግን፣ ከመኝታዬ እንደተነሳሁ የናፈቀኝን እስክንድርን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ ማምራት እንዳብኝ ወሰንኩና ጉዞዬን ጀመርኩ፡፡

Monday, August 11, 2014

ኢንጂነር ግዛቸው የመኢአድ/አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴን አፈረሱ

ኢንጂነግር ግዛቸው በሕዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀዉን፣ ለአገዛዙ ራስ ምታት የሆነው፣ የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴን አፈረሱ። በአባላትና ደጋፊዎች ዘንድም ትልቅ ድንጋጤ ተፈጥሩዋል። በአገዛዙም ዘንድ ደስታው ጨምሩዋል።
– በዉጭ አገር ያሉ የአንድነት ደጋፊዎች በኢንጂነር ገዛቸው ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ እያሰሙ ናቸው።
የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ፣ አቶ ተስፋሁን አለምነህ፣ ለሕብር ራዲዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ የአንድነት እና መኢአድ ዉህደት የሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ገልጾ፣ ገዢው ፓርቲ ምርጫ ቦርድን ተጠቅሞ የሚያስቀምጣቸው መሰናክሎችን አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገልጸዋል። ድርጅታቸው አቶ አበባው መሐሪን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ሲመርጥ፣ የምርጫ ቢርድ ሃላፊዎች በተገኙበት የተደረገ እንደሆነ የገለጹት አቶ ተስፋሁን፣ አገዛዙ ዉህድቱ እንዳይሳካና ተቃዋሚዎች ተከፋፍለው እንደለመደው የ2007 ምርጫን አጭበርብሮ ለማሸነፍ ሲል፣ ሆን ብሎ እያደርገ ነው ሲሉም ከሰዋል።
መኢአድ ሰላማዊ ሰልፎችን፣ የሥራና የትምህርት ማቆም አድማዎችን እንደሚጠራ የገለጹት ቶ ተስፋሁን፣ ትግሉ የሚጠይቀው ማናቸዉን መስወአትነት ለመክፈል አመራሩ እንደተዘጋጀም አስረድተዋል።
የመኢአድ እና የምርጫ ቦርድ ፍጥጫ በዚህ ሁኔታ እንዳለ ፣ ከመኢአድ ጎን በመቆም አጋርነት ይገልጻሉ፣ ምርጫ ቦርድ ላይ በጋራ ጫና ለማድረግ ድርጅታቸው ያሰልፋሉ ተብለው የሚጠበቁት፣ ኢንጂነር ግዛቸው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት አገር ዉስጥ ላሉ ጋዜጦች የሰጡትን አስተያየት በመቀልበስ፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴዉን ያፈረሱ ሲሆን፣ ለውህደት በሚደረገዉ ከፍተኛ ትንቅን ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ ከልብሰዉበታል።
«ኢንጂነር ግዛቸው በአሁኑ ወቅት ከመኢአድ ጋር በመሆን፣ በጋር የሚሊዮኖች ንቅናቄን በማጡዋጣፍ ፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ፣ በምርጫ ቦርድና አገዛዙ ላይ ጫና ማሳደር ሲገባቸው፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴውን ማፍረሳቸው ሰላማዊ ታጋዮች አንገት የሚያስደፋ ነው» ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ የኢንጂነሩን ዉሳኔ የሚረዳዉና የሚጠቅመው አገዛዙን ብቻ እንደሆነም ይናገራሉ።
ከኢንጂነር ገዛቸው አመራር ጋር በተገናኝም በዉጭ አገር የሚኖሩ የአንድነት ደጋፊዎች በኢንጂነር ግዛቸው አመራር ላይ ያላቸውም ከፍተኛ ተቃዉሞ እየገለጹ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል።


የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጆች ተሰደዱ

ኢሳት ዜና :-በአንባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ሳምንታዊ መጽሔት ባለቤት እና የመጽሔቱ ሶስት
አዘጋጆች ሀገር ለቀው ተሰደዋል። የመጽሔቱ ባለቤት አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ ለኢሳት እንደገለጸው፤ እርሱና ጋዜጠኞቹ በስርአቱ ሲደርስባቸው የነበረውን
ወከባና አፈና ተቋቁመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔትን ህልውና ለማስቀጠል ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ፤ መጽሔቱዋ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት ከማግኘቷም
ባሻገር በገንዘብ አቅምም ረገድ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ ችላ ነበር። አዲስ ጉዳይ እንደ አንድ ጠንካራ የፕሬስ ተቁዋም በጥሩ የእድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት
ወቅት በመንግስት በኩል ክሱ፣ወከባውና፣ ማስፈራሪያው እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው አቶ እንዳልካቸው፤ ይህም ሆኖ የህግን መስመር በጠበቀ መልኩ ሲያከናውኑ
የነበረውን ስራቸውን ለመቀጠል እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ አስፈላጊውን ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ከህግ አግባብ ውጪ እየደረሰባቸው ያለው ነገር
እንዲቆምላቸው ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ ከማቅረብ ጀምሮ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ጥረቶችን ቢያደርጉም ተገቢውን ምላሽ ከማጣታቸውም ባሻገር ይባስ ብሎ
መንግስት በኢትዮጵያ ቴለቪዥን በይፋ በመጽሔቱ ላይ ክስ እስከመመስረት መድረሱን የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ባለቤት ገልጿል። ክሱ ሳይደርሳቸው በመገናኛ ብዙሀን
መገለጹ ሁሉንም ሰራተኞች እንዳስገረመ የገለጸው አቶ እንዳልካቸው፤ ይህም መጪውን ምርጫ ተከትሎ መንግስት በፕሬሶችና በጋዜጠኞች ላይ ሊኖረው የሚችለው አዝማሚያ
እና ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል በግልጽ የሚያመላክት እንደሆነ ተናግሯል። ክሱ በኢቲቪ መታወጁን ተከትሎ ወከባውና ማስፈራሪያው እየከፋ
በመምጣቱም እርሱን ጨምሮ የመጽሔቱዋ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ፣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ እንዳለ ተሽ እና አዘጋጅና አምደኛ ሀብታሙ ስዩም ሀገር
ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል። የሰንደቅ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሆነው ዘሪሁን ሙሉጌታም ከደህንነት ሃይሎች የሚደርስበትን ማስፈራሪያ ተከትሎ በቅርቡ አገር ጥሎ ተሰዷል።
ሕገመንግሥቱንናሕገመንግሥታዊሥርዓቱንበኃይልለመናድናሕዝቡበመንግሥትላይአመኔታእንዲያጣአድርገዋል በሚል 4 መጽሄቶችና አንድ ጋዜጣ መከሰሳቸውንመንግሥት
ማስታወቁ ይታወሳል። የብሮድካስትባለስልጣንበሰኔወር 2006 ባወጣውመረጃመሰረትፋክትበወርበአማካይ 17 ሺ 993፣አዲስጉዳይ በወር 11 ሺ 750፣ሎሚበወር
11 ሺ 250 የኮፒብዛትወይንም ከፍተኛ ስርጭትያላቸውመጽሔቶችመሆናቸውን አስታውቆአል፡፡


የግንቦት 7 ደጋፊዎችን የማሰባሰብ ጥረት!!!!

የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በህሊናና የፓለቲካ እስረኞች ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ መክበድ፤ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም በሕዝብ ላይ የሚነዛው ወያኔያዊ ሽብር መብዛት፤ እስሩ፣ እንግልቱ፣ መሳደዱ፣ የሀብት ዘረፋው በየዕለቱ እየጨመረ መምጣት እና ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኑሮ እየከበደ መምጣቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር ወሳኝ የሆነ ትግል መግጠሚያ ወቅት ላይ መደረሱ አመላካች ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል መንፈስ መነሳሳት በተጨባጭ ከሚያረጋግጡ አመላካቾች አንዱ የግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባል ለመሆኑ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመር ነው። ይህንን ለውጥ ተከትሎም ግንቦት 7 የአባላት ቅበላን ሥራ ለማፋጠን የሚረዱ እርምጃዎች ወስዷል። ሆኖም ግን በአባላት ቅበላ ወቅት ሊታለፉ የማይችሉ ጥንቃቄዎች መኖር እንዳለባቸው ደጋፊዎችም እጩ አባላትም ይረዳሉ ተብሎ ይታመናል።

የከዱ የግንቦት 7 አባላት አቶ አንዳርጋቸውን እያሰቃዩ ነው ተባለ፤ * 2 መምህራንና 1 ዳኛ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ታፍነዋል

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ ለወያኔዎች ከአዲስ አበባ እስከ ደብረዘይት ትልቁን የምርመራ ስራ እየሸፈኑ ያሉት ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ጋር በኤርትራ የነበሩ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የፖለቲካ ስራ ሲሰሩ የነበሩ በኋላም ከድተው የገቡ ቅጥረኞች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቅጥረኞች ከመጀመሪያው ሰርጎ ገቦች እንደሆኑ ሳይጠረጠር ወደ ግንቦት ሰባት ከገቡ በኋላ ከአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቀደም ብሎ በመክዳት ወደ ወያኔ የተቀላቀሉ ናቸው ሲል ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።

እንደ ምኒልክ ዘገባ ከሆነ በአዲስ አበባ እና በደብረዘይት ትልልቅ ሆቴሎች ተይዞላቸው በምርጥ መኪኖች እየተንሸራሸሩ አቶ አንዳርጋቸውን በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማምጣት እውነቱን አውጣ አንተ እንደዚህ ብለኸን አልነበረም በማለት በተለያየ ጊዜ በስብሰባ እና በውይይት ወቅት የተነጋገሩትን የፖለቲካ ኦፕሬሽኖችን እና የትግል ስትራቴጂዎችን በመጥቀስ ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ እያደረሱብት ነው።

ከሕወሃት ከአንድ ብሄር ከተመለመሉ መርማሪዎች ጋር በጋራ በምርመራ ላይ የተሰማሩት ሶስቱ የግንቦት ሰባት ከሃዲ አባላት አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ላይ ያሉት -
1) ሽታው ሽፈራው ኤርትራ የነበረ የጎጃም ሰው
2) ቴዎድሮስ ስዩም ኤርትራ የነበረ ከአዲስ አበባ የሄደ
3) ኢልያስ ጥረት ጎንደር ውስጥ የነበረ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሲሰራ የነበረ ናቸው ሲል በዝርዝር የጠቆመው ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ በወያኔ ተንኮል ተተብትበው ግንቦት ሰባትን በመክዳት ለምቾታቸው የሕዝብን ትግል በጥቅም በመለወጥ በዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሱ በአዲስ አበባ እና ደብረዘይት ምርጥ ሆቴሎች ውስጥ እየተዝናኑ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አንዳርጋቸውን በቶርች በማሰቃየት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል።

ምርመርውን በመሪነት የሚያንቀሳቅሱት የሕወሓት ደህንነቶች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በአከባቤው አንዳርጋቸውን በተመለከተ ለብአዴን ይሁን ለ ኦሕዴድ ሰዎች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጣቸውና ወደ ማሰቃያ ክፍሉ ምንም እንዳይቀርቡ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ ለማረጋገጥ መቻሉን የገለጸው ጦማሪው ከአንዳርጋቸው ጋር የተያያዘውን የሃገር ውስጥ ኔትወርክ በማፈራረስ ረገድ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ከሃዲዎች እስከ ክፍለሃገር ድረስ በስፋት እየሰሩ ሲሆን እስካሁን በማፈራረስ ሙከራው ምንም አይነት ውጤት እንዳልገኙ ታውቋል ብሏል።

ጦማሪው ዘገባውን ሲቋጭም “ከአንዳርጋቸው ጋር በተያያዘ ከየክልሉ የግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ አሉ የተባሉ እየተለቀሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከጎንደር ክፍለሃገር መምህር ተስፋዬ ተፈሪ እና መምህር ጌታቸው የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንደሆነ የሚነግረው አቶ አበራ በከሃዲዎች ጥቆማ ከሃምሌ አጋማሽ ጀምሮ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የት እንደታሰሩ እንኳን እንደማይታወቅ ተገልጿል።” ብሏል።


Sunday, August 10, 2014

የአንዳርጋቸዉ ትዉስታዎች

“በእኛ እምነት ታሪክ ከነባራዊ ሁኔታ ዉጭ በምኞትና በዘፈቀደ አይሰራም። የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ነገስታቱና አምባገነኖቹ ዘሬም በዙፋናቸዉ ላይ በተገኙ ነበር። ባለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ህዝቦች መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆመዉ ከዚህ ወዴት እንደሚሄዱ ግልጽ ኢየባልሆነበት ሰዐት ሥልጣን ላይ ያለዉም ሆነ የሌለዉም የግሉን የተስፋ ጎዳናን እዉነተኛዉ የወደፊት ጎዳና አድርጎ የሚያይ ከሆነ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከታሪክ መማር አልቻልንም ማለት ነዉ”።“ከዲሞክራሲ ጋር ሲወዳደር ፍትህ ለሚለዉ ጽንሰ ሀሳብ “ኢትዮጵያዊኛ” ቃላቶች ያሉን መሆኑ የሚያስረግጠዉ ነገር ቢኖር ፍትህ ከማንነታችን ጋር የተቆራኘ መሆኑን ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ፍትህ ሲጓደል “በህግ አምላክ” ብለዉ በዳያቸዉን ለማስቆም የሚያሰሙት ጩኸት ፍትህ ከፈጣሪያቸዉ የተሰጠ ከሰብዓዊነታቸዉ ተነጥሎ የማይታይ እሴት አድርገዉ እንደሚመለከቱት የሚያመለክት ነዉ። በምድር ላይም ፍትህ የሚሰጥ ዳኛ ጠፍቷል ብለዉ ሲያስቡ እጃቸዉን ወደ ፈጣሪያቸዉ ዘርግተዉ አንተዉ ፍርዱን ስጠና የሚሉት ከፈጣሪያቸዉ ፍጹምነት የሚመነጭ እዉነተኛ ዳኝነት አለ ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ። ከዚህ በላይ ባጭሩ የተባለዉ የሚጠቁመዉ በኢትዮጵያዉያን ባህልና ስነ ልቦና ዉስጥ የፍትህ ጽንሰ ሀሳብ ያለዉን ትልቅ ትርጉምና ቦታ ነዉ”።የታሪክን ነባራዊነት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍትህ የሚሰጠዉን ከፍተኛ ቦታና ለነጻነት ያለዉን አመለካከት በተመለከተ ከዚህ በላይ ያሰማናችሁን ሁለት አዉዶች በሁለት የተለያዩ መጽሐፎቹ ዉስጥ የጻፈዉ ዛሬ ፍትህ አልባ በሆነዉ የወያኔ ስርዐት ዉስጥ ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ሲል ለፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ያለዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ነዉ። አዎ የፍትህና የነጻነት አርበኛዉ አንዳርጋቸዉ በግልጽ አንዳስቀመጠዉ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ እስከነ ስሙ ሙልጭ ብሎ በመጥፋቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ እባክህ አምላኬ “ወይ ዉረድ ወይ ፍረድ” እያለ ፈጠሪዉን እየተማጸነ ነዉ። በእርግጥም ፍትህ ፈጣሪያችን ያደለን ትልቅ ማህበራዊ እሴት ነዉ፤ ሆኖም ይህንን

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ (ከቂሊጦ እስር ቤት)

[ከመቶ ሰባት ቀናት እስር በኋላ በፍቄ ሰለ እስሩ ስለ ምርመራው እና ስለ ወደፊት ተስፋቸው ከቂሊጦ እስር ቤት የሰደዳት መልዕክት ይቺትና። እኔ ጽሁፉን ሳነብ የመጣብኝ ሃሳብ እነዚህ ሰዎች በርካታ ንጹሃንን እስከዛሬ ማንም ሳያያቸው ሲያሰቃዩ የስቃዩ ሰለባዎች ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ካልሆኑ የስቃያቸውን መጠን የሚገልጹት በእንባ እና... ''ተወው... ተወው አይነሳ...'' በሚል ምሬት ብቻ ነበር። አሁን ግን በራሳቸው ጊዜ ዘጋቢዎችን ወደ ማዕከላዊ እያስገቡ እነሆ የኢህአዴግ ''አመራር ጥበብ''ን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሰዕላዊ መግለጫ እየሰጡን ነው።

ኢህአዴግ ሆይ፤ በጥፊ በርግጫ አይገኝም ምርጫ፤ እያልን የበፍቄን ጽሁፍ ሁሉም ሰው ያነበው ዘንድ ይሄው...

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ.7

የኢህአዴግ ዲሞክራሲና የቴሌ ኔትዎርክ ተመሳሰሉብኝ

እኔ የምለው … አንዳንድ የመንግስት ተቋማት በእነሱ ብሶ ለምንድነው ቁጣ ቁጣ የሚላቸው? (“የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል” አሉ!) ከምሬ እኮ ነው… እኛ የተበደልነው አርፈን ተቀምጠን እነሱ እየተመላለሱ ይቆጡናል፡፡ (ኧረ “ፌር” አይደለም!) ያውም እኮ ሳንደርስባቸው ነው፤ ቤታችን ድረስ እየመጡ – በኢቴቪ መስኮት፡፡ ከሁሉም አንጀት የሚያበግነው ደግሞ ትላንት እኛው በድምፃችን ይመሩናል ብለን የመረጥናቸው ተወካዮቻችን፣ ማታ ማታ በቲቪ እየመጡ መቆጣታቸው ነው፡፡ (ለ90 ሚ. ህዝብ ማስጠንቀቂያ አይፃፍማ!) ይሄን ሁሉ ያስቀባጠረኝ የሰሞኑ የኢትዮ- ቴሌኮም ቁጣ የተቀላቀለበት መግለጫ ነው፡፡ (እኛ ሳንቆጣ እሱ ይቆጣን?!)
በእርግጥ መጀመሪያ የምስራቹን ነበር ያስቀደመው፡፡ ግዙፍ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶቹን በስኬት ማጠናቀቁን በድል አድራጊነት ስሜት አበሰረን፡፡ (የቴሌ ድል የእኛም ድል ነው!) እንደመሰለኝ… የቁጣው መንስኤ የኢቴቪ ጋዜጠኛ ጥያቄ ነው፡፡ “ደንበኞች አሁንም የአገልግሎት ጥራት ችግሮች አሉ እያሉ ነው” የሚል ጥያቄ ሳያነሳ አልቀረም – ጋዜጠኛው፡፡ (ግን እኮ አልዋሸም!) ይሄኔ ነው ቁጣ ቁጣ ያለው – “አገልጋያችን” ኢትዮ-ቴሌኮም፡፡
አያችሁ… እዚህ አገር ሁሉ ነገር የተገላቢጦሽ ነው፡፡ በሌላው ዓለም ቢሆን እኮ የሚቆጣው ደንበኛ እንጂ አገልግሎት ሰጪው አይደለም፡፡ የሚቆጣው ህዝብ እንጂ መንግስት አይደለም፡፡ (መንግስትማ አገልጋይ ነው!) እኔ የምላችሁ… “ደንበኛ ንጉስ ነው” የሚለው አባባል እኛ አገር “ደንበኛ እርኩስ ነው” በሚል ተቀይሯል እንዴ? …በእርግጥ የኛ አገር ነጋዴዎች ወይም አገልግሎት ሰጪዎች “The Customer is always right” (ደንበኛ ሁሌም ትክክል ነው)  የምትለዋን አባባል ሲሰሙ “መስሎሃል!” እንደሚሉ ነገረ ስራቸው ያስታውቃል፡፡ እናም …ቢቆጡን፣ ቢያንገላቱን፣ መብራት ቢከለክሉን፣ ኔትዎርክ ቢነጥቁን፣ ውሃ ቢወስዱብን፣ ታክሲ የለም ቢሉን፣ ዘይት ቢያጠፉብን፣ ስኳር ቢያስወድዱብን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ቢፈጥሩብን ወዘተ… ዝም ብለን መቀበል ብቻ ነው፡፡ ለምን “ደንበኛ ንጉስ”  ሳይሆን “እርኩስ ነው”
እናላችሁ… የኢትዮ ቴሌኮሙ ኃላፊ በኢቴቪ መስኮት ገጭ ብለው የመንግስት “የገቢ ኩራት” ስለሆነው መ/ቤታቸው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራከሩ፡፡ የኔትዎርክ ማሻሻያው “ነዳጅ እንደሚበላ አሮጌ መኪና ሆነ” (አባባሉ የእኔ ነው!) ሲባሉ… አልካዱም፡፡ “በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም ኔትዎርክ ይጠፋል” የሚለውን ቅሬታም ተቀብለዋል፡፡ በመጨረሻ ግን “እናስ ምን ይጠበስ?!” ዓይነት ምላሽ ነው የሰጡት፡፡ “ይሄን ያህል ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሰራ እኮ እንዲህ ዓይነት ችግሮች ያጋጥማሉ” አሉን፡፡ (ኔትዎርክ በዓመት አንዴ ጠፋ ብለን የምንሞላቀቅ “ቅንጡዎች”  አደረጉን እኮ!) በመካያውም… “የኔትዎርክም ሆነ ሌሎች ችግሮች በሂደት ይፈታሉ” … ብለው ገላገሉን፡፡ ይሄኔ ነው ኢህአዴግ ነፍሴ ትዝ ያለኝ፡፡ ኢህአዴግ ሁሌም ዲሞክራሲው ተንገራገጨ ወይም መልካም አስተዳደሩ ተሰናከለ አሊያም የሰብዓዊ መብት አያያዙ እያሳጣን ነው…በተባለ ቁጥር “በሂደት ይፈታል” ይለናል፡፡ የእሱ አይደለም የገረመኝ፡፡ የቴሌኮም መድገም ነው፡፡ (አወያይ መመሳሰል አሉ!)
ለዚህም ነው የኢህአዴግ ዲሞክራሲና የቴሌ ኔትዎርክ የተመሳሰለብኝ፡፡ (ሁለቱም የኋሊት ነው የሚጓዙት ልበል!) ለማንኛውም በሂደት ይፈታል ተብላችኋል – ኔትዎርኩ!!

addis admas


Saturday, August 9, 2014

የኢህአዴግ ተወካዮች ምሬታቸውን ገለጹ

በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የምክር ቤት አባላት ፣” የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን ሪፖርት አይቀበልም” ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል audio ( 00-01፡54)
የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ችግር እንዳለም ገልጸዋል። አንድ ተወካይ የመንግስት ሆስፒታሎች እየተዳከሙና መድሃኒቶች እየተሸጡ፣ ህዝቡም ከመንግስት የጤና ተቋማት ይልቅ ወደ ግል እየሄዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰባችን ምን ላይ ነው ያለውን የማጥናት ችግር አለ ያሉት ሌላው ተወካይ፣ በምዞርባቸው ቦታዎች ሁሉ ህዝቡ መውደቂያ አጣን ብሎ እንደሚጮህ ተናግረዋል። audio( 09፡57-10፣11፡41)
ኢህአዴግ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚመስል መልኩ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የህዝብ ተወካይ የሚላቸውን ሰዎች እየጠራ በማወያየት ላይ ነው።እስካሁን ድረስ በተደረጉት ውይይቶች አብዛኛው ተወያይ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ሆነ የኢኮኖሚ ና የአስተዳደር ችግሮች እንዳሉ በድፍረት መግለጹን ኢሳት ሲዘግብ መቆየቱ ይተወቃል።


የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት7 የኦህዴድ ደግሞ ከኦነግ ጋር እያበሩ ነው ሲል አቶ አዲሱ ለገሰ ያዘጋጁትና ለጠ/ሚ አማካሪዎች የተላከው ሰነድ አመለከተ

ኢሳት ዜና :-በሰነዱ ላይ ኢህአዴግ የአመራር ችግር እንዳጋጠመው፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ አለመሳካቱ
እንዲሁም በጋምቤላ
ተማኝ መሪ መጥፋቱ ተዝርዝሯል።
በሃምሌ ወር መጨረሻ የተዘጋጀው ሰነድ ግልባጭ ለጠ/ሚኒስትሩ አማካሪዎች ለአቶ በረከት ስምኦን፣ ለአቶ ደስታውና ለአቶ ኩማ ደመቅሳ ተደርጓል።
የቀድሞው ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ የፖሊሲ ስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ” የኢህአዴግን ተቃዋሚ ሃይላት ማንኮላሻ አቅም ግንባታ እና የአመራር
ግንባታና የትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የፖሊሲ አማካሪዎች የቀረበ የሚለው ባለ 39 ገጽ ጽሁፍ፣ ኢህአዴግ ከላይ እስከታች የአመራር ችግር እንደገጠመው
በዝርዝር ያቀርባል።

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በጣምራ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!

የሕውሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት ምርጫውን ለማራዘም እንደሚፈልግ በካድሬዎቹ እና ለራሱ ቀረቤታ ባላቸው ግለሰቦች በኩል ሲያስወራ የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግም የሰላማዊ ትግሉን ጨርሶ ለመዝጋት እያሳየ ባለው እኩይ እቅድ መሠረት ጠንካራ ፓርቲዎችን፣ የነፃ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ለመዝጋት ዳርዳር በማለት ላይ ይገኛል፡፡ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጠቅላላ ጉባዔውን ሐምሌ 13 እና 14 ቀን 2005 ዓ.ም ባደረገው የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ሁለት የምርጫ ቦርዱ አመራር ተወካዮች በተገኙበት ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

እነዚህ አመራሮችም ኮረም መሙላቱን በቦርዱ አካሄድ መሠረት ካረጋገጡ በኋላ ስብሰባው እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ መኢአድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህግና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት ስብሰባውን አካሂዶ እያለና ከ600 የጠቅላላ ጉባዔ አባላት 390 ታዳሚዎች በተገኙበት ስብሰባውን አካሂዶ እያለ ምልዐተ ጉባዔ አልተሟላም በሚል ሰበብ አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጠን እነሆ አንድ ዓመት አልፎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመቱን ሙሉ ለህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስልጠና በሚሰጥበት ወቅት ሁሉ መኢአድም ህጋዊነቱ ተጠብቆ ግብዣ እየተደረገለት አመራሮቹ አስፈላጊውን ስልጠና ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።
ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።
ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነው የሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።
እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።
በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣ በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።


Friday, August 8, 2014

በአዲስ አበባ እንጦጦ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከኪዳነ ምህረት ወደ እንጦጦ ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ በሰባት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አደረሰ።

እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ትናንት ምሽት 2 ስአት ከ25 ላይ ነው አደጋው የደረሰው።

በአደጋው ሶስት ሶስት ሰዎች ወዲያውኑ ህይዎታቸው ሲያልፍ ሶስቱ ደግም ወደ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ሊደረግላቸው ሲል መንገድ ላይ አርፈዋል። አንደኛው ደግሞ ዛሬ ጠዋት ላይ ህይወቱ አልፏል።

በአደጋው ህይዎታቸው ያለፈው ሁሉም መንገደኞች ሲሆኑ፥ የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

በርካታ ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑም ተገልጿል።

አውቶብሱ ከፓል ጋር ተጋጭቶ ስለነበር የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበርም ተነግሯል።


«የሕዳሴ አብዮቱን ለመቀልበስ የተደረገ ነው» ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የወያኔ መንግስት «ሕገ–መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ…» በሚል ክስ በአምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ «በሕዝብ ላይ ሽብርተኝነት የሚነዙ ሽብርተኛ ናቸው!» ብሎ ከስ ማቅረቡ ይታወቃል ይህንንም ተከትሎ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፋክት መጽሔት ባልደረባ እንዲህ ይላል

«ይህ ክስ ‹የሕዳሴ አብዮቱን ለመቀልበስ የተደረገ ነው› ክሱን በሚመለከት የደረሰን ነገር የለም። ጉዳዩን ከመንግስት መገናኛ ብዙሐን ነው የሰማነው። ይህ ለምን እንደሆነ በራሱ ግራ የሚያጋባ ነው። ምክንያቱም በተለመደው አሰራር ክስ ሲመሰረት ተከሳሹ መጥሪያ ደርሶት ቃል እንዲሰጥ ይደረጋል። ፍትሕ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠው መግለጫ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበት ሁኔታ ነው መሆኑን ነው ያሳየን። ለምን ይሆን ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ መንግስት ጋዜጠኞችን ከሀገር ማባረር ስልት አድርጐት ስለያዘው ከተከሰሱት መጽሔቶችና ጋዜጦች መካከል የተባለውን የክስ መግለጫ ሰምተው ቀድመው ከሀገር እንዲሸሹ ስለተፈለገ ነው። የተነገረው የክስ መግለጫ በእኛ ሥራ ላይ በቀጣይ የሚያስከትለው ነገር የለም።

ዞሮ ዞሮ ከዚህ ክስ በስተጀርባ ያለው ፍርሀት እየተቃረበ የመጣውን በፋክት መጽሔት በተከታታይ እየቀረበ ያለውን «የሕዳሴው አብዮት»ን ነው። መግለጫውም ይህን የህዳሴውን አብዮት ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ ነው። የሕግ ክፍተት በመኖሩ የተፈፀመ ተደርጐ መወሰድ የለበትም። በፋክት ላይ የተዘገቡት የሐሰት ወሬዎች አይደሉም። እርምጃው ፖለቲካዊ ነው። ስርዓቱ በጣም ስለተደናገጠ እየተፈረካከሰ ስለሆነ መቃብሩ አፋፍ ላይ ስለቆመ የመጨረሻው ግብአት መሬቱን የሚያውጀውን የሕዳሴ አብዮትን ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ ነው። ይህ የአፈና ተግባር ነው።»


አብርሃ ደስታ በማዕከላዊ ድብደባ እንደደረሰበትና ጨለማ ክፍል ውስጥ መታሰሩን ተናገረ 

በሃይል በማያምነው ጉዳይ እንዲፈርም መገደዱንም አስታውቋል
በሶሻል ሚዲያ ሀሳቡን በመግለጽና ስርዓቱ በትግራይ ክልል የሚፈጽማቸውን በደሎች በማጋለጥ ተለይቶ የሚታወቀው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህሩ አብርሃ ደስታ ዛሬ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፌደራል ፖሊሶች ታጅቦና እጆቹ በካቴና ታስረው ሲገባ ግቢው ውስጥ ይጠባበቁት የነበሩ ሰዎች በጭብጨባ ተቀብለውታል፡፡
የአብርሃ ችሎት ለጋዜጠኞችና ለወዳጆቹ ዝግ በመሆኑ ማንም ወደ ውስጥ እንዲገባ ባይፈቀድለትም ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጉ አብርሃ በማዕከላዊ ድብደባ እንደደረሰበትና ጨለማ ክፍል ውስጥ መታሰሩን እንዳስረዳ ተናግረዋል፡፡ከውጪ ሰዎች ጋር ትገናኛለህ የሚሉ የምርመራ ጥያቄዎች ሲቀርቡለት መቆየቱንና በማያምንበትና ባላደረገው ነገር አድርጌያለሁ በማለት እንዲፈርም መደረጉንም ለችሎቱ ማስታወቁን ጠበቃው ይፋ አድርገዋል፡፡
አብርሃን ያቀረቡት ፖሊስ የተባለውን ነገር አለመፈጸሙን በመግለጽ ተቃውሞ ማሰማታቸውንም ጠበቃው ጠቅሰዋል፡፡አብርሃ በድጋሚ የ28 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆበት እጆቹ እንደታሰሩ ግቢውን ሲለቅ አድናቂዎቹ በጭብጨባና ከጎንህ ነን ከሚል መልእክት ጋር ሸኝተውታል፡፡

Dawit Solomon


Wednesday, August 6, 2014

ዛሬ ከቀኑ 8፡00 በአራዳ ምድብ ችሎት

አራዳ ፍርድ ቤት ዛሬ እንዲህ ሆነ
-----
ዛሬ ከቀኑ 8፡00 በአራዳ ምድብ ችሎት ሐብታሙ አያሌው ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋ እንደሚቀርቡ በመነገሩ ብዛት ያላቸው ሰዎች ቀደም ብለው በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው ነበር፡፡ፖሊስ በፍርድ ቤቱ የተሰጠውን የቀጠሮ ሰዓት አክብሮ እስረኞቹን ማቅረብ በመቻሉ ላይ ብዙዎች ስጋት የነበራቸው ቢሆንም አልተሳሳቱም፡፡
መደበኛው የስራ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ከፍተኛ ታጣቂ ሃይል የፍርድ ቤቱን ቅጥረ ግቢ ተቆጣጠረው ከደቂቃዎች በኋላም አንድ ማንነቱን ቀደም ብለን ለማወቅ ያልቻልነው ቀጠን ያለ ወጣት እጆቹን ታስሮ ወደ ችሎት ገባ፡፡በኋላ ላይ ማረጋገጥ እንደቻልኩት ወጣቱ ዘላለም የሚባል ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ መርሀ ግብር ተማሪ ነበር፡፡ፖሊስ በተመሳሳይ መልኩ እነ ሐብታሙን በያዘበት ዕለት በቁጥጥር ስር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመለጠቅም ዳንኤል ሺበሺ ሁለት እጆቹ በካቴና ታስረው ነጠላ ጫማ ፣ጥቁር ሱሪና ቱታ ጃኬት ተላብሶ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡
ከጺሙ ማደግ በስተቀር ዳንኤል ፊትና አካል ላይ ምንም አይነት ለውጥ አይታይም፡፡ስሙን እየጠሩና በእጆቻቸው እያጨበጨቡ አድናቆታቸውን ለሚገልጹለት ሰዎች ጥርሱን ብልጭ እያደረገ አጸፌታውን ከመመለስ ውጪ ምንም አልተናገረም፡፡
የዳንኤልን ችሎት ለመከታተል ጋዜጠኞችና ቤተሰቦቹ ጥያቄ አቅርበው አይቻልም የሚል ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ጉዳዩን የተመለከቱት ሴት ዳኛ ቤተሰቡ እንዲገባ በማዘዛቸው ባለቤቱ ችሎቱን ተከታትላለች፡፡
የዳንኤል ጉዳይ እየታየ በነበረበት ሰዓት የሺዋስ አሰፋን የያዘችው መኪና ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ደረሰች፡፡ለደቂቃዎች ያህልም የሺዋስ በመኪናው ውስጥ እንዲቆይ ተደረገ፡፡ዳንኤልና ዘላለም እንደጨረሱና ግቢውን እንዲለቁ ከተደረጉ በኋላ የሺዋስ እንዲገባ ተደረገ፡፡ሙሉ ነጣ ያለ ቱታ ያጠለቀው የሺዋስ ግቢው ውስጥ እንደገባ ደመቅ ያለ ጭብጨባና በርታ የሚሉ መልእክቶች ጎረፉለት፡፡ፖሊሶች በጭብጨባውና በመልእክቶቹ ደስተኞች አለመሆናቸውን ቢገልጹም ከውስጥ ፈንቅለው የሚወጡ ስሜቶችን በቁጣና ማስፈራሪያ ሊያስቆሙ እንደማይችሉ የተረዱ ይመስሉ ነበር፡፡
የሺዋስ እንደሁልገዜው ዘና ያለና የተረጋጋ ነው፡፡ፈገግታውን በመርጨትና ሰላምታ በመለገስ የታሰሩ እጆቹን እያወዛዘወዘ ችሎት ገባ፡፡የሺዋስ የውስጥ ጉዳዩን ከውኖ እንደጨረሰም በተመሳሳይ የወዳጆቹና የትግል አጋሮቹ ጭብጨባና አድናቆት ታጅቦ ግቢውን ለቀቀ፡፡
በመጨረሻም ሐብታሙ አያሌው ወደ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ፣ ሐብታሙ እግሮቹ ግቢውን እንደረገጡ ተሰብስበው ለጠበቁት ሰዎች ጥልቅ ፈገግታውን በመለገስ ሰላምታ አቅርቧል፡፡‹‹እንወድሃለን፣አይዞን››የሚሉ ቃላት ከደማቅ ጭብጨባ ጋር በግቢው አስተጋቡ፣ አጃቢዎቹም ፈጠን እንዲል እየወተወቱት ችሎት አስገቡት፡፡
ከወጣት ዘላለም በስተቀር በዕለቱ ችሎት ጠበቃ ተማምና ገበየሁ ታሳሪዎቹን ወክለው ቀርበዋል፡፡ሀብታሙ በመጣበት አጀብ ግቢውን እንዲለቅ ከተደረገ በኋላ ሁለቱ ጠበቆች ‹‹ተለዋጭ ቀጠሮ ለነሀሴ 26/2006 መሰጠቱን አውስተዋል፡፡ፖሊስ በዛሬው ችሎት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምንም አይነት ማስረጃ አለማቅረቡን መረጃ ለማሰባሰብ እንዲረዳው የጠየቀው ቀን እንደተሰጠውም አብራርተዋል፡


መከሰሳቸውን ከፖሊስ ሳይሆን ከሚዲያ የሰሙት የሎሚ መጽሔትና የአፍሮታምይስ ጋዜጣ አዘጋጆች ይናገራሉ

ስለመከሰሳችን የምናውቀው ነገር የለም”
አቶ ግዛው ታዬ
የሎሚ መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር

ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ


ክሱን በተመለከተ የምናውቀው ነገር የለም። ከዚህ በፊት ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ይደወልልን ነበር። እዚያ ሄደን ቃላችንን እንሰጥ ነበር።

እኛ አሁን መገረም ነው የፈጠረብን። ሕገ-መንግስቱን አከበራለሁ የሚል መንግስት በምን መልኩ ነው የክስ ዝርዝር ሳይደርሰን፣ መጥሪያ እጃችን ላይ ሳይገባ በመገናኛ ብዙሃን ክሳችንን የሚያሰማን።

አሁን ባለው ሁኔታ ማተሚያ ቤት ገብተናል። እንደሚታወቀው ከሳምንት በፊት ነው ወደ ማተሚያ ቤት የምንገባው። ይህም የሆነበት ባለፉት ሃያ ሦስት ዓመት ውስጥ ማተሚያ ቤት ማግኘት ባለመቻላችን ነው። የወደፊቱን ተፅዕኖ ወደ ፊት እናየዋለን።

አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ለመመስረት ዘጠኝ ወር ብሮድካስት መስሪያቤት ተመላልሰን ነው። አሁን ሥራ በጀመርን በሰባት ወራችን ሊዘጉት ነው።

“የሚሆነው ሁሉ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ ነው”
ቶማስ አያሌው የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር

ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው


ፍትህ ሚንስትር ያወጣው መግለጫና ክስ ስሰማ ከልብ አዝኛለሁም አፍረያለሁም፤ ያዘንኩት ሁሉንም መፈርጅ ሊያበቃ አለመቻሉ ሲሆን ፤ ያፈርኩት ደግሞ ክስ ቻርጅ ሣይስጥ መግለጫ መውጣቱ ነው፡፡ የሚሆነው ሁሉ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ ነው፡፡

ለጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላ የተፈቀደው ዋስትና ተከለከለ

ከአሸናፊ ደምሴ

በአንዋር መስጊድና አካባቢው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በተፈጠረ ግጭትና ሁከት ተሳትፈዋል በሚል ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው ከሚገኙ 14 ተጠርጣሪዎች መካከል ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ፍርድ ቤት ትናንት ጠዋት ፈቅዶት የነበረው የ5 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በቀረበ ይግባኝ ውድቅ ሆኖ ዋስትናው ተከለከለ።

ሜክስኮ በሚገኘው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዮች የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት የዛሬ ሳምንት የተሰጣቸውን የጊዜ ቀጠሮ ተከትሎ በችሎት ካቀረቡት 14 ተጠርጣሪዎች መካከል የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛዋ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችውን ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ አራት የፖሊስ አባላት (ማለትም አንድ ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተርና አንድ ምክትል ሳጅንና አንድ የኮንስታብል ማዕረግ ያላቸው) እና ሌሎች ስምንት ተጠርጣሪዎች በችሎች ሲያቀርብ የተቀሩት ከሁለተኛው የጊዜ ቀጠሮ በኋላ ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሼባቸዋለሁ ሲል ማሰናበቱን ለፍርድ ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

አሁን ድረስ በምርመራ ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ያልቆመላቸው ሲሆን፤ በትናንት ጠዋቱ የችሎት ውሏቸውም በባለፈው የጊዜ ቀጠሮ ወቅት ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄያቸው መሠረት ፍርድ ቤቱ፤ አዚዛ መሐመድ፣ ወይንሸት ሞላ እና ኡዝታዝ መንሱር የ5 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲሄዱ ትዕዛዝ ቢሰጥም፤ በቀደመው ችሎት ያቀረባቸውንና ምላሽ ያላቀረበባቸውን የዋስትና መቃወሚያዎች ፖሊስ ለችሎቱ አቅርቦ አስረድቷል። ይኸውም ምርመራዬን አልጨረስኩምና ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ በሕክምና ላይ ያሉና ጉዳት የደረሰባቸውን የፖሊስ አባላትንም መጨረሻ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ችሎቱ ጠዋት ላይ የተፈቀደ ዋስትና በከሰዓት ላይ ውድቅ ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ እንዲመለሱ ተደርጓል።

የምርመራ ተግባራቶቼን አላገባደድኩም ሲል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮን የጠየቀው ፖሊስ በጥቁር አንበሳ እና በፖሊስ ሆስፒታል የሚገኙትንና በብጥብጡ ወቅት ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ሰዎች ሁኔታና ቃል ተቀብሎ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱን በጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ የተፈቀደለት ሲሆን፤ ለመጪው ነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።


ኢህአዴግ ለስለላ የሰጠው ቲሸርት ጣጣ አመጣ!!

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሁለት አመት በፊት “መስጂድ አይወክለንም” የሚል ቲሸርት በማድረግ ሙስሊሙን ይሰልሉ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ከአንድ ሳምንት በፊት ታስሮ ነበር። የታሰረበት ምክንያት ደግሞ ይኸው አሮጌ ቲሸርት ባመጣበት ጣጣ ነው። ዘገባውን ያቀረበው ፍትህ ሬድዮ እንደገለጸው ከሆነ፤ የቀድሞ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት አፈ ጉባኤ የነበረው አቶ ፈድሉ ሀሰን ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ በ1000 ብር ዋስ ተፈቷል። ዝርዝር ዘግርባው ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

አቶ ፈድሉ ሀሰን የታሰሩት ጁምዐ 18/11/2006 ሲሆን ቤታቸው ላይ ታጥቦ ከተሰጡ ልብሶች አንዱ “መጅሊስ አይወክለንም” የሚል ነበር :: ይህንን የተመለከተ የአካባቢው ካድሬ ወድያውኑ ፖሊስ በመጥራት ቲሸርቱ ፎቶ እንዲነሳ በማድረግ አቶ ፈድሉን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዟቸው ይሄዳሉ፡፡

ማክሰኞ 22/11/2006 ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ አቃቢ ህጉ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ “አቶ ፈድሉ ሃስን ለአመፅና ለሽብር ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ተገኝቶባቸዋል” በማለት በአስረጂነት መጅሊስ አይወክለንም የሚለውን ቲሸርት ጠቀሶል::

ዳኛም አቶ ፈድሉን ምላሽ ሲጠይቁ አቶ ፈደሉም “ይህንን ቲሸርት የዛሬ ሁለት አመት መስጂድ ገብተን እንድንሰልልበት የሰጠን ኢህአዴግ ነው በአሁኑ ሰዐት እኔ በቲሸርትነት እጠቀምበታለው” ሲል መልስ ስጥቷል፡፡

ዳኛው ጉዳዩን በማየት የዋስትና መብታቸው የፈቀዱ ሲሆን አቃቢ ህጉ ያላጣራሁት ነገር አለ ለ14 ቀን ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ዳኛው ይህንን ያህል ግዜ አያስፈልግም በማለት ለ አርብ 25/11/2006 ቀጠሮ ሰጥተው ነበር። አርብ በዋለው ችሎትም በ1000 ዋስ መለቀቃቸውን ለማወቅ ችለናል ፡፡

አቶ ፈድሉ ሀሰን ከመታሰራቸው 5 ውር በፊት ባለመግባባት ስራ እንደለቀቁ ምንጫችን ገልጸዋል፡፡

Source: Fitih Radio


Tuesday, August 5, 2014

የሕወሓት ጄኔራሎች ሲታመሱ ዋሉ ። በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል።

ምንሊክ ሳልሳዊ
በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲስች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።
ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ከመሃል አገር በተለያየ የጦር መምሪያ ውስጥ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት እና የአንድ ኮርስ ምሩቅ ናቸው የተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ የሕወሓት ጄኔራሎች ላይ ጥርሱን እንደነከሰ የሚነገርለት ኮሎኔል አለም የሚባለውን የተንቤን ተውላጅ ጨምሮ አስረ አንዱ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ገብተዋል የሚል መረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የሶስቱ ዱካ አለመገኘቱን እና ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ከየት ታፍነው በማን ታፍነው እንደተወሰዱ ሳይታወቅ በደብረዘይት የምድር ውስጥ እስር ቤት እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የሕወሓት ጄኔራሎችን ያመሳቸው ጉዳይ የተንቤን ተወላጆች ሌሎች የደቡብ እና የአማራ ተወላጆች ተያይዞ መጥፋት ሲሆን እንዲሁም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ እየላላ መጥቷል ሲሉ የደነፉበት የወታደራዊ ደህንነት ቁጥጥር መላላት ለነገው የስልጣን እድሜያቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳጠላበታ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩልን የመከላከያ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በሙሉ የሃገሪት እዞች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ፍተሻ እንዲካሄድ በዛሬው ስብሰባ ጥብቅ ትእዛዝ ያስተላለፉት የሕወሓት ጄኔራሎች በደቡብ እና በምእራብ ድንበሮች አከባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈተሹ በወጪ ገቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እና የየቀኑ ሪፖርት እንዲላክ እንዲሁም በመሃል አገር ያሉ የቶር መኮንኖች በየቀኑ ለቅርብ አለቃቸው ዝርዝር የአባላት እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥብቅ ትእዛዝ አውርደዋል።እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ደህንነቶች በየእዙ እንዲመደቡ አዘዋል።

በዚህ ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የወታደራዊ ደህንነት ሪፖርቶቹን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን።

በኦህዴድ ውስጥ የሚታየው ትርምስ ቀጥሏል

አብዛኛው የኦህዴድ አባላት በድርጅታቸው ብቃት እና በድርጅታቸው ህዝባዊ ተቀባይነት ላይ ያላቸው አመኔታ እጅግ የወረደ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።

ከድርጅቱ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው አብዛኛው የኦህዴድ ካድሬዎች ድርጅታቸው ብቃት የሌለውና በህዝቡ ዘንድ የተጠላ ነው ብለው ያምናሉ።

ካድሬዎቹ ህዝቡን ከድርጅቱ ጎን ለማሰለፍ እየከበዳቸው በመምጣቱ ብዙዎች ስራቸውንና ሃላፊነታቸውን እየለቀቁ ያለስራ መቀመጥን እስከመምረጥ ደርሰዋል። ድርጅቱ ስብሰባ ሲጠራ አብዛኛው ህዝብ ለመገኘት ፈቃደኛ ስለማይሆን፣ ካድሬዎች የመንግስት ሰራተኞችን እያስገደዱ ለስብሰባ እንዲወጡ እስከማስደረስ ደርሰዋል።
በቅርቡ የተከበረውን የሴቶች ሊግ በአል ለማዘጋጀት በታቀደበት ቀን በበአሉ ላይ የሚገኝ ሰው በመጥፋቱ፣ የበአሉ ማክበሪያ ቀን እንዲራዘም ከተደረገ በሁዋላ በሳምንቱ ካድሬዎች የመንግስት ሰራተኛ ሴቶችን አስገድደው እንዲያስወጡ ለመውጣት ፈቃደኛ ባልሆኑ ሴቶች ላይ ምዝገባ ተካሂዶ እንዲቀጡ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ከተሰጠ በሁዋላ፣ የተወሰኑ ሴቶች ተገኝተው በአዳማ በአሉን አክብረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዳማ ከተማ የደህንነት ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዋነውና ምክትሉ ከድርጅቱ አመራሮች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከስራቸው ተባረዋል።

ዋናው የደህንነት ሹም የነበሩት አቶ አብዶ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ ሰሞኑን ደግሞ ምክትላቸው አቶ ጌታቸው ኦሊ እንዲባረሩ ተደርጓል። አቶ ጌታቸው ለግምግማ በተጠሩበት ወቅት የበላይ አለቆቻቸውን ሁላችሁም ሌቦች ሆናችሁ እኛን ልትገመግሙ አትችሉም ብለው መናገራቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

በአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ሲወሰድ ለነበረው እርምጃ ሁለቱ ባለስልጣናት ዋና ተጠያቂዎች መሆናቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። ሁለቱም ባለስልጣናት ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በተፈጠረ የጥቅም ግጭት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።


“ስለእኔ አታልቅሱ!”

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

“ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፡- እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፡- መካኖችና ያልወለዱ ማኀፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁአን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፡፡” (የሉቃስ ወንጌል ም. 23 ቁ. 27-30) ከቅዱስ መጽሐፉ ይህን የመሲሁ የመጨረሻ ምክር የመረጥኩት (ምንም እንኳ ረቢው የተናገረው ስለመለኮታዊው ትምህርት ቢሆንም) ዓለማዊው ፍች የኢትዮጵያችንን የወቅቱን መንፈስ ለመረዳት ከማስቻሉም በዘለለ፤ በየጊዜው እያየን፣ እየሰማን ያለነውን የፖለቲካ ተቃውሞው የጥምዝምዞሽ መንገድ በአርምሞ ለመመርመር መልካም ምሳሌ ይሆናል በሚል እሳቤም ነው፡፡

እፍኝ በማይሞሉ ፋኖዎች ከአርባ ዓመታት በፊት “ደደቢት” በተሰኘ የሰሜን በርሃ የተመሰረተው ህወሓት ከተራዘመ የትግል ጉዙ በኋላ፤ ታጋይ ሕላዊ ዮሴፍ “እልፍ ሆነናል” እንዲል፤ ራሱን አጠናክሮ “እልፍ” በመሆን ሥልጣን ይዞ፣ የሀገሪቷን አንጡራ-ሀብት አመራሩ መምነሽነሺያው ካደረገ፣ እነሆ ሃያ ሶስት ዓመታት እንደዘበት ነጎዱ፡፡ ርግጥ ነው ይህች የዳንኪራ እና ፌሽታ ዘመን እውን ትሆን ዘንድ፣ የቡድኑ ዋና ዋና መሪዎችም ሆኑ መላው ታጋይ (የበረከቱ ተቋዳሽ ባይሆንም) በቃላት ሊገለፅ የማይችል የመከራ ዓመታትን በቆራጥነት ማሳለፋቸው የሚስተባበል ታሪክ አይደለም፡፡ ሥልጣን እጃቸው ከገባ በኋላም የአገር ጥቅም መገበርን ጨምሮ እየገደሉ፣ እያሰሩና እያሰደዱ… በሕዝብ ላይ ወደር የለሽ ጭካኔን በመፈፀም ዘላቂነቱን እንዲህ ስለማስረገጣቸውም ተወርቶ የተዘጋ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይሁንና ከዕለት ዕለት እየመረረና እየከፋ የመጣው ይህ ኩነት፣ ምድሪቷ የአንድ እውነት መዝጊያና የአዲስ ዓመት ምዕራፍ መክፈቻ ላይ መድረሷን ስለማመላከቱ ለመመስከር ጠቢብነትን አይጠይቅም፤ የዘመኑ መንፈስ እያሰማን ያለው “ፋኖ ተሰማራ”ም የሶስተኛው አብዮት ደውል ስለመሆኑ ለመረዳት የቀደሙ ነብያቶችን ትንበያ መጠበቅ አያሻም፡፡