Thursday, March 29, 2018

አዲሱ የኢህአዴግ ሊ/መንበር የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በተግባር መመለስ አለበት!

አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡ ከአርባ ቀን በኋላ እና በመጀመሪያ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለብዙ ቀናት ቀጥሎም ምክር ቤቱ ከአንድ ሳምንት በላይ የፈጀ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ ዶ/ር አቢይ አህመድን የግንባሩ ሊ/ቀመንበር አድርጎ መርጧል። የዶ/ር አቢይ የኢህአዴግ ሊ/መንበር ሆኖ መመረጥ የሚቀጥለዉ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ማን ሊሆን ይችላል በሚል በአትኩሮት ሲጠበቅ ለነበረው ጥያቄ የመጀመሪያ ዙር ምላሽ ሰጥቷል። ለመሆኑ የዶ/ር አብይ መመረጥ የተለመደው የወያኔ የሴራ አካሄድ ውጤት ነዉ? ወይስ ኢህአዴግ የህዝብን እውነተኛ የለውጥ ፍላጎት ሰምቶ መንገዱን ለማስተካከል የወሰደዉ ዕርምጃ ነዉ? የኢህአዴግ ዉሳኔ እነዚህን ጥያቄዎች ያጠቃለለ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶበት የተወሰነ መሆኑንና ያለመሆኑን በቅርቡ የምንሰማውና በተግባርም የምናየው ይሆናል።
የዶ/ር አብይ መመረጥ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት እስካሁን የህወሀት ሎሌ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ድርጅቶችና በህወሓት ውስጥም ያሉ አንዳንድ ለውጥ ፈላጊዎች በጋራ አሸንፈው ከሆነና እነ ዶ/ር አብይ በተለይ በኦህዴድ ምክር ቤት ስብሰባ መግለጫ ላይ ያወጡትን ለውጥ ፈላጊ አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ወስነው ከሆነ እሰየው ነው። የኢህአዴግ ዉሳኔ በአገራችን በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል፥ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ብሎም ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገባ ከሆነ ለውጥ ፈላጊው ህዝብ ሁሉ የሚፈልገው ነውና በአዎንታዊ መልኩ የምንወስደው ነው። 

Wednesday, March 28, 2018

በኢትዮጵያ በቅርቡ በተቋቋመው ወታደራዊ ዕዝ /ኮማንድ ፖስት/በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ሁለት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተለቀቁ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) በኢትዮጵያ በቅርቡ በተቋቋመው ወታደራዊ ዕዝ /ኮማንድ ፖስት/በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ሁለት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተለቀቁ። ከሳምንት በፊት ከእስር የተለቀቁት የኦሕዴድ ባለስልጣናት የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። በወታደራዊ እዙ ታስረው የነበሩት የኦሕዴድ አመራሮች የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሃብታሙ ቦረና እንዲሁም የነቀምት ከተማ ከንቲባ አቶ ካባ ሁንዴ ናቸው። እነዚሁ ባለስልጣናት በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ በየአካባቢያቸው ተከስቶ ከነበረው የሕዝብ አመጽ ጋር በተያያዘ መሆኑ ይታወሳል። የኦሮሚያ ባለስልጣናት መያዛቸውን ተከትሎም የፓርላማ ተወካይ የሆኑ የኦሕዴድ ተመራጮች እስሩ አግባብ አለመሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ከታሳሪዎቹ መካከል ያለመከሰስ መብት የነበራቸው የክልል ምክርቤት አባላት እንደነበሩ በመግለጽ የፓርላማ አባላቱ ተቃውመው ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ ግን የምስራቅ ወለጋ ዞን አመራሮችን በመፍታት በርካታ የታሰሩ ወጣቶችንም የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት መልቀቁ ነው የተነገረው። ይህም ሆኖ ግን አሁንም በርካታ ወጣቶች የኦሮሚያ ክልል መንግስታዊ መዋቅር አመራሮች ታስረው እንደሚገኙ ሪፖርተር ዘግቧል።

እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በርካታ ዜጎች ተጨናንቀው በሚገኝበት ክፍል ውስጥ መግባታቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ወታደራዊ እዙን ሳታስፈቅዱ ስብሰባ አድርጋችሁዋል፣ አርማ የሌለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅማችሁዋል በሚል ሰበብ በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት አቀንቃኞች ፣ ጎተራ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተጨናነቀ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል። የመብት ተሟጋቾቹ በተያዙ በመጀመሪያው ቀን ከ90 በላይ ሰዎች ተጨናንቀው በሚገኙበት ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ ከተደረገ በሁዋላ፣ በማግስቱ ተለይተው በአንድ ቢሮ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ይሁን እንጅ ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ወደ መጀመሪያውና አስከፊ ወደ ተባለው ክፍል እንዲገቡ ተደርጓል። እስረኞቹን እስካሁን ለፍርድ ያቀረባቸውም ሆነ ያነጋገራቸው አካል የለም። ባለፈው እሁድ ጀሞ በሚባለው አካባቢ በቅርቡ ከእስር ለተፈቱት ሰዎች በተዘጋጀ የምስጋና ዝግጅት ላይ በመገኘታቸው የታሰሩት፣ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሃይሉ፣ ጸሃፊ ዘላላም ወርቃገኘሁ፣ ይድነቃቸው አዲስ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አዲሱ ጌታነህ፣ ተፈራ ተስፋዬ፣ ማህሌት ፋንታሁንና ወይንሸት ሞላ ናቸው። እንዲሁም በባህርዳር ለወታደራዊ እዙ ሳያሳውቁ ስብሰባ አድርገዋል የተባሉ ከ19 ያላነሱ ምሁራን ፣ ጋዜጠኞችና የህግ ባለሙያዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። እስረኞቹ አዋጁን በመተላለፍ ለወታደራዊ እዙ ሳያሳውቁ ስብሰባ አድርገዋል በሚል በ9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ሲደረግባቸው ነበር። በእስር ላይ ከሚገኙት ወጣት ምሁራን መካከል ፣በባህርዳር ዩኒቨርስቲ መምህርና የጣና ደህንነትና የአካባቢ ጥበቃ ማህበር ፕሬዚዳንትና ተመራማሪ፣ አቶ ጋሻው መርሻ፣ የሱፍ ኢብራሂም፣ ተመስገን ተሰማ፣ በለጠ ሞላ፣ የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ንጋቱ አስረስ፣ ጋዜጠኛ በለጠ ካሴና ኢንጂነር ሲሳይ አልታሰብ ይገኙበታል።

ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢህአዴግ ለሳምንታት ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ በመጨረሻም የኦህዴድ ሊ/መንበር የሆኑትን ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል። የህወሃት ደጋፊ የመገናኛ ብዙሃን ዶ/ር አብይ እንዳይመረጥ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቢከርሙም በመጨረሻ ዶ/ር አብይ ተመርጠዋል። ዶ/ር አብይ እንዲመረጡ ብአዴን ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተም ታውቋል። የዶ/ር አብይን መመረጥ ተከትሎ ከፍተኛ ተስፋ ያሳደሩ በርካታ ዜጎች በፌስ ቡክ አስተያየቶችን እየሰጡ ሲሆን፣ በአንጻሩ የህወሃት ደጋፊ ድረ-ገጾች ለዜናው ትኩረት ሳይሰጡት ቀርተዋል። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ የግንባሩ ሊቀመንበር ምርጫ ግልፅ፣ ዴሞክራሲያዊና በትግል ላይ በተመሰረተ ሁኔታ፣ የምክር ቤቱ አባላት በሚስጥር ድምፅ በሰጡበት አካሄድ ተፈጽሟል ብሎአል። “ህዝብን ማዳን፤ሀገርን ማዳንና የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመርን ቀጣይነት ማረጋገጥ ማዕከል ያደረገ በሳል ውይይት መደረጉንና በሳል ውሳኔና ድምዳሜ “ ላይ መደረሱን ገልጿል። “ምርጫውም ኢህአዴግ ያሸነፈበት ምርጫ ነው” በማለትም ኢህአዴግ ለራሱ የአሸናፊነት ምስክርነት ሰጥቷል። በተቃውሞ ፖለቲካው ጎራ ያሉት አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችም በጉዳዩ ዙሪያ ለኢሳት የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ “አብይ ከሚናገራቸው ነገሮች ስንነሳ ለአገር የሚያስብ ጥሩ ሰው እንደሆነ ይሰማኛል። ነገር ግን የዚህ አገር ችግር

እነእስክንድር ነጋ ከነበሩበት የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ወደ እስር ቤት መወሰዳቸው ተሰማ

Image may contain: 8 people, people smilingእነእስክንድር ነጋ ከነበሩበት የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ወደ እስር ቤት መወሰዳቸው ተሰማ። ያልተፈቀደ ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል በሚል የታሰሩት እነእስክንድር ነጋ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 48 ሰዓታት እንዳለፋቸውም ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል። ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ ያወጡት ዓለም አቀፍ ተቋማት ድርጊቱን በማውገዝ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ፖሊስ ጉዳዩን ለኮማንድ ፖስት አሳውቄ ምላሽ እየተጠባበኩ ነው ማለቱም ተገልጿል። ኮከብ የሌለበትን ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል ተብለው የታሰሩት እነእስክንድር ነጋ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቀናት ተቆጥረዋል። ዕሁድ ዕለት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት መኖሪያ ቤት በተደረገው ፕሮግራም ላይ የተሳተፉት ጋዜጠኞች፣ጦማሪያውያንና የፖለቲካ መሪዎች ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ጊዜ አልፏል። በመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት ከነበሩበት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ጽህፈት ቤት ወደ መደበኛ እስር ቤት ዛሬ መግባታቸውንም ከቤተሰብ አካባቢ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። አሁን ያሉበት ሁኔታ ከባድ እንደሆነም ተገልጿል። በአንድ ክፍል ውስጥ 90 የሚሆኑ እስረኞች በሚገኙበት ጠባብ ክፍል ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን ነው ለማወቅ የተቻለው። ክፍሏ ከመጥበቧ የተነሳ ለመኝታ የሚሆን ቦታ ባለመኖሩ ቆሞ ለማደር መገደዳቸውን ቤተሰብ ገልጿል። እስክንድር ነጋን ዛሬ ያነጋገሩ ሰዎች እንደገለጹት እስረኞቹ ያሉበት ሁኔታ ለጤንነታቸው በጣም አስጊ ነው። ‘’መስማት ለሚፈልግ፣ ወይም ለሚሰማ ሰው ሁሉ

ጋምቤላ ውስጥ በመከላከያ ሰራዊቱ የተገደሉት የአኝዋክ ተወላጆች 2ሺ 500 ያህል እንደነበሩ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ገለጹ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010)ጋምቤላ ውስጥ በመከላከያ ሰራዊቱ የተገደሉት የአኝዋክ ተወላጆች 2ሺ 500 ያህል እንደነበሩ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ገለጹ። በሶስት ቀን ብቻ የተገደሉት 424 ወንዶች ሲሆኑ፣164 ሴቶች በመከላከያ ሰራዊት አባላት መደፈራቸውንም በቅርቡ ከወህኒ የወጡት አቶ ኦኬሎ አኳይ ዘርዝረዋል። በታህሳስ 1996 በጋምቤላ ጭፍጨፋ በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የወቅቱን ጭፍጨፋ በዝርዝር ተመልክተዋል። ከኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያደረጉትን ጉዞ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን ውስጥ ታፍነው ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት የተወሰዱበትንና በወህኒ ቤት የቆዩበትን ሁኔታ በዝርዝር ለኢሳት ገልጸዋል።

Tuesday, March 27, 2018

የአምቦ ዩንቨርሲቲ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት አይታይም ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቀ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሶስት ሳምንት በፊት የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም ከሕግ አግባብ ውጪ በኮማንድ ፖስቱ ተይዞ ማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው በአምቦ ዩንቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበም። ፍርድ ቤቱ የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለመጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ.ም የ14 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጠውም ፖሊስ ሊያቀርበው ፈቃደኛ አልሆነም። ጦማሪ ስዩም ክስ ያልተመሰረተበት፣ ዋስትናም ያልተሰጠው ወይንም ክሱ ያልተቋረጠ በመሆኑ ፖሊስ ሊያቀርበው ይገባ ነበር። ፍርድ ቤቱ ፌደራል ፖሊስ ያላቀረበበትን ምክንያት እንዲገልፅ፣ ተጠርጣሪውንም እንዲያቀርብ ለመጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በእለቱ ጦማሪ ስዩም ተሾመ ፍርድ ቤት ያልቀረበ ሲሆን ጉዳዩ ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚቋቋም ፍርድ ቤት እንደሚታይ ፖሊስ ለፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በደብዳቤ አሳውቋል። ፍርድ ቤቱም በፌደራል ፖሊስ ጥያቄ መሰረት የጦማሪ ስዩም ተሾመን የጊዜያዊ ቀጠሮ መዝገብ እንዲዘጋ ወስኗል። ጦማሪ ስዩም ተሾመ ከዚህ ቀደም በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለሦስት ወራት ታስሮ መፈታቱ ይታወሳል። በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ ህዝብ

ወታደራዊ እዙ በመተማ ዮሃንስ ያዘጋጀው ስብሰባ በተቃውሞ ተቋረጠ

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው እሁድ መጋቢት 15/2010 ዓ.ም፣ በመተማ ዮሃንስ በቀበሌ 03 አዳራሽ ወታደራዊ እዙ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ከመተማ ህዝብ ጋር ለማድረግ የሞከረው ስብሰባ በከፍተኛ ሁከትና ብጥብጥ ምክንያት ስብሰባው ተቋርጧል። ህዝቡ ፣ “የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ መልስ ያግኝ፣ ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው የአባቶቻችን ርስት በአስቸኳይ ይመለስልን፣ በማስፈራራት ስልጣን ማራዘም አይቻልም” የሚሉና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ህዝቡ ጥያቄዎች ሲነሱ ድጋፉን በጭብጨባና በፉጨት የገለጸ ሲሆን፣ ጸጥታ ለማስከበር የተሳናቸው የመድረኩ መሪዎች የፌድራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት ጠርተዋል። ህዝቡም በብስጭት “ፍርሃት የዘራችን አይደለም” በማለት መድረኩን እረግጦ እንደ ወጣ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ስብሰባውን ከምዕራብ እዝ ኮ/ል ተሾመ የተባለ እንዲሁም የከተማው የአስተዳደርና ጸጥታ ሃላፊ አቶ ለምለሙ ባዬ መርተውታል።

የስዩም ተሾመ ጉዳይ በልዩ ሁኔታ በሚቋቋም ፍርድ ቤት ይታያል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010)የመምህሩና ጦማሪው ስዩም ተሾመ ጉዳይ በልዩ ሁኔታ በሚቋቋም ፍርድ ቤት እንደሚታይ ተገለጸ።
መደበኛው ፍርድ ቤትም በፖሊስ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መዝገቡን ዘግቷል።
በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ልዩ ፍርድ ቤት ማቋቋም በአዋጅ የተከለከለ ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሷል በሚል ከአምቦ ዩኒቨርስቲ ወልቂጤ ካምፓስ የታሰረው ስዩም ተሾመ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሲታይ ነበር።

የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መልሶ መታሰር ተወገዘ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2010) አለማአቀፉ የፕሬስ ተቋም የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን መልሶ መታሰር በጽኑ አወገዘ።
ተቋሙ እስክንድር ነጋን ጨምሮ እንደገና የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖሊቲከኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አድርጓል።
የእነ እስክንድር ነጋ መልሶ መታሰር በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ እንደሚያስፈልግ አመላካች መሆኑን ደግሞ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል።
የአለም አቀፉ የፕሬስ ተቋም/አይፒአይ/ምክትል ዳይሬክተር ስኮት ግሪፊን እንዳሉት ከዚህ ቀደም እስረኞች ሲለቀቁ በኢትዮጵያ መልካም ነገር ይመጣል የሚል ተስፋ ተሰንቆ ነበር።

ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ--መጋቢት 18/2010)በሞያሌ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩን አለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ።
መንግስት ስደተኞቹ እየተመለሱ መሆናቸውን ቢገልጽም አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ትላንት እንዳስታወቀው በየቀኑ 500 ሰዎች እየተሰደዱ ኬንያ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
ችግሩ በተፈጠረ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት 8 ሺ 200 ኢትዮጵያውያን መሰደዳቸውን ያስታወሰው አለም አቀፉ ቀይ መስቀል በመጪዎቹ 3 ቀናት ቁጥሩ ወደ 15ሺ እንደሚያሻቅብም አስታውቋል።
የቀንድና የጋማ ከብቶችም በተመሳሳይ መሰደዳቸው ተመልክቷል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን፣ የኬንያ ቀይ መስቀልና የስደተኞች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ምዝገባ በመጋቢት ወር ብቻ ከሞያሌ ግድያ ጋር በተያያዘ ድንበር አቋርጠው ኬንያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስካለፈው ሳምንት 10ሺ 557 ደርሷል።
አሁንም በየቀኑ 100 ቤተሰቦች ማለትም በትንሹ 500 ያህል ሰዎች ድንበር አቋርጠው ኬንያ በመግባት ላይ መሆናቸውን በሰብአዊ ቀውስ ሪፖርቱ ላይ ተመልክቷል።

Friday, March 23, 2018

የህወሃት/ኢህአዴግ ስበሰባ እየጦዘ ነው። በስብሰባው ላይ አቶ አባይ ፀሃዬ በአቶ ለማ መገርሳ ላይ የሃይላንድ ውሃ ወረወረ!

በመካሄድ ላይ የህወሃት/ኢህአዴግ ስብሰባ እየጦዘ ነው። በስብሰባው ላይ በስኳር ፋብሪካዎች ግንባት ስም ከ77 ቢልዮን ብር በላይ ጭጭ አድርጎ የበላው የህወሃት ከፍተኛ ባልስልጣን አቶ አባይ ፀሃዬ በአቶ ለማ መገርሳ ላይ የሃይላንድ ውሃ ወረወረ።
በብዙው  ይህ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስቴር ለመምረጥ ነው ቢባልም ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት ጠቅላይ ሚ/ር አይመረጥም ይህንን የተረጋገጠ መረጃ ለመላው ህዝብ ይወቀው። እየተካሄደ ባለው የህወሃት/ኢህአዴግ ስብሰባ የቃላት ንትርኩ ወደ መቧቀስ ከፍ ብሏል። በተረጋገጠ መረጃ መሰረት አባይ ፀሀዬ ለማ መገርሳን በሀይላንድ ኮዳ ደበደበ። ዶ/ር አብይ ላይም የሃይላንድ ኮዳ ወርውሯል!!

የአማራ ክልል የሕዝብ ቁጥር እድገት እጅግ አዝጋሚ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010) የአማራ ክልል የሕዝብ ቁጥር እድገት እጅግ አዝጋሚ መሆኑን በኢትዮጵያው አገዛዝና በአለም አቀፍ ለጋሾች የቀረበ አንድ ሰነድ አመለከተ።
በዚህ ሰነድ መሰረት በመጪው የሕዝብ ቆጠራ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተጨማሪ 3 ሚሊየን የአማራ ህዝብ ሊጠፋ እንደሚችል ተገምቷል።
በሰነዱ እንደተመለከተው ለምግብ እጥረት የተጋለጡትን ለመለየት በተካሄደ የሕዝብ ቁጥር ትንበያ ጥናት የአማራ ክልል ነዋሪዎች 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ብቻ ናቸው።
የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ደግሞ 36. 5 ሚሊዮን መሆን ቢኖርበትም በሁለት ሚሊዮን ቀንሶ 34.5 ሚሊዮን መሆኑ በሰነዱ ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ የሕዝብና የቤት ቆጠራ የተካሄደው በ1999 ከ11 አመታት በፊት ነበር።
በሃገሪቱ ሕገ መንግስት የሕብና የቤት ቆጠራ በየ10 አመቱ መካሄድ ቢኖርበትም ሕጉ ተጥሶ ይህ ሳይደረግ ከ1 አመት በላይ አልፎታል።
በሕገመንግስቱ መሰረት ቢሆን ኖሮ የሕዝብና ቤት ቆጠራው 10 አመቱን ጠብቆ በ2009 ሊካሄድ ይገባ ነበር።

የወጪ ንግድ ገቢ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በታች መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010) በግማሽ አመት የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በታች መሆኑ ተገለጸ።
ምርት በመላክ የውጭ ምንዛሪ ከተገኘባቸው የአለማችን ሃገራት መካከል ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ በሁለተኛ ደረጃ ተመዝግባለች።
የመጀመሪያ ግማሽ አመት ሪፖርቱን ያመጣው የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከወጪ ንግድ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ 1 ነጥብ 35 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መሆኑን ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል በተጠቀሰው የበጀት ዘመን ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ምርት ከ8 ቢሊየን ዶላር በላይ በመሆኑ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ ከ6 ቢሊየን ዶላር በላይ ማሻቀቡን መረጃዎች አመላክተዋል።

አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት ነው

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010)በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሶ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት መሆኑን ገለጸ።
ከ2006 ጀምሮ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው አበበ ካሴ በተፈጸመበት ኢሰብአዊ ድርጊት ሽንቱን መቆጣጠር እንደማይችል ገልጿል።
ከወልቃይት ማንነት ጋር በተያያዘ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች አሁንም ድብደባ እየደረሰበት ነውም ተብሏል።
አበበ ካሴ በአርበኞች ግንቦት ሰባት ስም ከተወነጀለበት ክስ ሌላ በአማራ ክልል ፍርድቤትም ሌላ የቅጣት ውሳኔ እንደመጣበት ይናገራል።
በግንቦት ሰባት ስም በቀረበበት ክስ 7 አመት ሲፈረድበት በወልቃይት ማንነት ሰበብ በተወነጀለበት ጉዳይ ደግሞ 20 አመት

የሸካ ጥቅጥቅ ደን በእሳት ቃጠሎ እየወደመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የባህልና የሳይንስ ተቋም ዩኔስኮ የተመዘገበው የሸካ ጥቅጥቅ ደን በእሳት ቃጠሎ እየወደመ መሆኑ ተገለጸ።
እስካሁን 250 ሄክታር የሚሆነው የደኑ ይዞታ በእሳት የወደመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የአገዛዙ የመገናኛ ብዙሃን ደኑ በሰደድ እሳት መያያዙን ቢገልጹም የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያዎች ግን የአካባቢው የአየር ንብረት ሰደድ እሳትን የሚፈጥር አይደለም ሲሉ ይከራከራሉ።
የአከባቢው ህዝብ እሳቱን ለማጥፋት የሚችል ባለመሆኑ መንግስት በአስቸኳይ ደኑን ከጥፋት እንዲከላከል ጥሪ ተደርጓል።
ኢትዮጵያ የቀራት የደን ይዞታ በምዕራቡ አቅጣጫ የተዘረጋው ሰፊ ጥብቅ ደን ነው። 140ሺህ 377 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን የሸካ ዞንን ስፋት ግማሽ ያህል የሸፈነ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
በእንስሳት እና እፅዋት ዝርያዎች የበለፀገ እንደሆነም ይነገርለታል።

እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከ16 ሚሊየን በላይ ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 14/2010)በኢትዮጵያ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስቸኳይ እርዳታዎች የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከ16 ሚሊየን በላይ መድረሱን ለኢሳት የደረሰው የመንግስት ሰነድ አመለከተ።
እስከ ታህሳስ 2011 ድረስ ይህ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ከተባሉት ውስጥ ከ6 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ዜጎች ናቸው ።
ከሶማሌ ክልል ነዋሪዎች 80 በመቶው አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ናቸው ።
የኢትዮጵያ መንግስትና ከ80 በላይ እርዳታ ሰጪ ሃገራትና ተቋማት በጋራ ባዘጋጁት የ2018 እቅድ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ብዛት ከ16 ሚሊየን በላይ መሆናቸው ተመላክቷል።

ከ150 ያላነሱ በአብዛኛው የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው የጉምሩክ ሰራተኞች ከስራ ተቀነሱ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ከተቀነሱት ውስጥ 98 በመቶ የሚሆኑት የህወሃት ወታደሮች የነበሩ ናቸው። ብዙዎቹ የትምህርት ማስረጃቸው ብቁ አይደለም በሚል እንደተባረሩ ኢሳት ከደረሰው ደብዳቤ ለማወቅ ችለናል። ኢሳት ትናንት ባቀረበው ዘገባ በሶማሊ ክልል 38 የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው እና ከመከላከያ ወደ ጉምሩክ ተዛውረው ለ8 ዓመታት ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች መቀነሳቸውን ጠቅሶ ነበር። ከተቀነሱት መካከል 34ቱ የህወሃት ታጋዮች እንደነበሩም የጉምሩክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ይሁን እንጅ ዛሬ ባገኘው የስም ዝርዝር ደግሞ ከሶማሊ ክልል ብቻ 101 ሰዎች ሲቀነሱ፣ ከሃዋሳና ሌሎች አካባቢዎች እስከ 150 ሰዎች ተቀንሰዋል። 90 በመቶ የሚሆኑት የመከላከያ አባላት ሲሆኑ፣ አብዛኞቹም የኮሎኔልነት እና የሻለቅነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው። ዛሬ ከደረሰን የስም ዝርዝር መካከል 96 በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ብሄር ተወላጅ የህወሃት ወታደሮች የነበሩ ናቸው። ከተቀነሱት መካከል ኢሳት አንዱን ነባር ታጋይ ያነጋገረ ሲሆን፣ ታጋዩ ከመከላከያ ወደ ጉምሩክ መወሰዱንና ለ8 ዓመታት በኦጋዴን አካባቢ ማገልገሉን ተናግሯል። ይሁን እንጅ አሁን በትምህርት ማስረጃ ስም ከስራ እንደተቀነሰ እንደተነገረውና ግራ እንደገባው ገልጿል። ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ማሳወቃቸውንና መልስ በማጣታቸው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ አቤት ለማለት ማሰባቸውን ግለሰቡ አክሎ ገልጿል።

የድል ሚድድ ደጋፊ ናቸው የተባሉ የኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች ቤተሰቦች አሁንም እየታሰሩ ነው

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የሶማሊውን ክልል መሪ የአቶ አብዲ ኢሌን አገዛዝ ለመቃወምና በክልሉ ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን ለመታገል በውጭ የሚገኙ የሶማሊ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙትን ድል ሚድድ የተባለው ንቅናቄን ተከትሎ የንቅናቄው አባላትና አመራር ናቸው የተባሉ ቤተሰቦች እየተያዙ መታሰራቸው ቀጥሎአል። በቅርቡ በክልሉ ዱል ሚድድ የሚል እና ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚጠይቅ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ እንዲሁም በቅርቡ በስዊድን የሚካሄደውን ጉባኤ ተከትሎ ህጻናትን ሴቶች ሳይቀሩ መታሰራቸውን ከክልሉ የተላከልን መረጃ አመልክቷል። የክልሉ ባለስልጣናት 150 የሚሆኑ ጂዳዋቅ የተባለውን ጎሳ አባላት የአገር ሽማግሌዎች በመጥራት ተቃውሟቸውን እንዲያቆሙ አስጠንቅቋል። ከዱል ሚድድ ጋር ግንኙነት ያለው ማንኛውም ሰው መኖሪያ ቤቱ እንደሚወስደበት ትእዛዝ ሰጥተዋል። ስብሰባውን የመሩት

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን በወታደሩ ላይ የሰላ ትችት ሲያሰሙ አረፈዱ

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ በቅጽል ስማቸው ጄኔራል ሾማ እየተባሉ በሚጠሩ ወታደራዊ አዛዥ እና በፕ/ር ጨመዳ ፊኒኒሳ በተመራው የመመህራንና የሰራተኞች ስብሰባ ፣ ሰራተኞቹ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ትችት ሲሰነዝሩ ውለዋል። ከጠዋት 2 ሰአት እስከ 6 ሰዓት በቆዬው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹ በስሜት ይናገሩ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። አንድ መምህር፣ “ክቡር ጄኔራል፣ አሁን ልታስሩኝ ትችላላችሁ ነገር ግን በአለም ታሪክ ከህዝብ አብራክ የወጣ የመከላከያ ሰራዊት መልሶ የህዝብ ጠላት ሲሆን ያየሁት በኢትዮጵያ ነው፤ በግብጽ እንኳን ህዝብ ሲያምጽ ሰራዊቱ ከህዝብ ጎን ነው የቆመው፤ እኛ ጋ ግን ተቀራኒ ነው። ድንበር መጠበቅ ሲገባችሁ፣ የወጣችሁበትን ማህጸን እየጨፈጨፋችሁት ነው። በጣም አሳፈሪ ነገር ነው” ብለዋል። ሌላ መመህር ደግሞ “ ቶሎ ሳይመሽ አሁኑኑ ከህዝብ ጋር ብትወግኑ መልካም ነው፤ ክቡር ጄኔራል፣ እርስዎ ዛሬ ከሁዋላዎ ያቆሙትን ጠባቂዎ ቢጨቁኑት ነገ አፈሙዙን ወደ እርስዎ ማዞሩ አይቀርም፣ አሁን በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ነገር ይህ ነው፤ ህዝብ እየተጨቆነ ነው፣ በመንግስት ላይ ማመጹ ትክክል ነው፤ ከህዝብ ጎን መቆሙ ነው የሚያዋጣችሁ”ሲል ተሰብሳቢው ስሜቱን በከፍተኛ ጭብጨባ ገልጿል። ሌሎች መምህራንና ሰራተኞችም እየተነሱ ተመሳሳይ

በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ለሳምንት በተደገረው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ህወሃት በአቶ አባይ ጸሃዬ ዋና ተከራካሪነት ተወክሏል። ከአቶ አባይ ጀርባ አቶ ስብሃት ነጋና አቶ በረከት ስምዖን ተሰልፈው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ አድርገዋል። ኦህዴድ በአቶ ለማ መገርሳ ዋና ተከራካሪነት ሲቀርብ፣ ዶ/ር አብይ አህመድም ከአቶ ለማ ጀርባ ሆነው ክርክራቸውን አድርገዋል። ህወሃት ኦህዴድን በጎራ መደባለቅና በህዝበኝነት እንዲሁም የኢህአዴግን መስመር በመሳት ሲገመግም፣ ኦህዴድ በበኩሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ እስካሁን በተሄደበት መስመር መመለስ እንደማይቻል ተከራክሯል። የርእዮት ዓለም ክርክር በተካሄደበት ስብሰባ ላይ ኦህዴድና ህወሃት የተለያዩ አመለካከቶችን ማራመዳቸው ለነባሩ አመራሮች የሚዋጥ አልሆነም። የጠ/ሚኒስትር ሹመት ሃሳብ በተነሳበት ወቅት፣ ህወሃት እንዲህ የተዛነፈና ከመስመር የወጣ ሃሳብ ለያዙ ቡድኖች የአገሪቱን አመራር መስጠት በድርጅቱም በአገሪቱም ላይ መቅሰፍት እንዲመጣ መጋበዝ ነው ሲል፣ ኦህዴድ በበኩሉ ለህዝብ ጥያቄ ቅድሚያ በመስጠት ድርጅቱንም አገሪቱንም ከችግር የሚያወጣት መሪ ሊመረጥ ይገበዋል የሚል አቋም አራምዷል። ለጠ/ሚኒስትር እጩ ሆነው ስለቀረቡት ሰዎች ግምገማ በሚካሄድበት ወቅት፣ በዶ/ር አብይ ላይ ዋና ተቺ

Monday, March 19, 2018

ኤርትራ በኢህአዴግ የቀረበባትን ክስ አጣጣለች

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ኤርትራ ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ እያደረገች ነው በማለት በህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ በኩል የቀረበውን ክስ፣ ኤርትራ አጣጥላዋለች። “ኢትዮጵያ ችግሩን ውጫዊ ለማድረግ ከመፈልግ ይልቅ፣ እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ተቃውሞውና አለመረጋጋት ለመፍታት ብትሰራ ይሻላታል” ስትል ገልጻለች። የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረ መስቀል ለብሉምበርግ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለውስጣዊ ችግሩ ውጫዊ ምክንያት እየፈለገ፣ የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ እየሞከረ ነው ብለዋል። የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አሰፋ አብዩ በቅርቡ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ የተለያየ አይነት የጦር መሳሪያዎች እና እስከ 20 ሺህ የሚጠጉ ጥይቶች መያዛቸውን ገልጸው ነበር። የውጭ ሀይሎች በሀገር ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከትና ብጥብጥ በጦር መሳሪያ ለመደገፍ ይፈልጋሉ ሲሉ ባለስልጣኑ ተናግረው ነበር። የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልም እንዲሁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከኤርትራ የሚነሱ ሃይሎችን ለመጨረሻ ጊዜ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ተናግረው ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የሚታዬው ተቃውሞ በአስተዳደር ፣ በዲሞክራሲ እና በፍትህ እጦት የመጣ መሆኑን ኢህአዴግ በተደጋጋሚ በሰጠው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ራሰን ወታደራዊ እዝ ብሎ የሾመው ቡድን ጸሃፊ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ በኢትዮጵያ የሚታዬው ተቃውሞ “የቀለም አብዮት” መልክ አለው በማለት ለችግሩ ምዕራባውያናንን ተጠያቂ ለማድረግ ሞክረው ነበር። በኤርትራ ላይ የቀረበው ክስ አዲስ ባይሆንም፣ ኢህአዴግ ለውስጥ ችግሩ ውስጣዊ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ውጫዊ ምክንያቶችንና ውጫዊ መፍትሄዎችን ለመፈለግ መጣሩ፣ አገዛዙ የፖለቲካ መፍትሄ ለማምታት አለመዘጋጀቱን የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።

መንግስት የአገሪቱን ችግር በሃይል ለመፍታት በመሞከሩ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ሲል ኦፌኮ ገለጸ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያገራችንን ችግር እያባበሰ ስለሆነ መንግስት አዋጁን አንስቶ ከሃቀኛ ተቃዋሚዎች ጋር ድርድር እንዲያካሂድና ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር አሳስቧል። ከዚህ በፊት በአገሪቱ ታይቶ በማይታወቅ ዓይነት ከ700 ሺ በላይ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውሮ ሰርቶ የመኖር መብቱ ተጥሶ ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል እና አካባቢው እንዲፈናቀሉ መደረጉን፣ በቅርብ ጊዜ በምስራቅና ምዕራብ ሃሀርጌ በጨለንቆ፣ በአወዳይና በሃመሬሳ ወዘተ በርካታ ዜጎች መገደላቸውንና እንዲሁም በሞያሌ ፣ በምስራቅ ወለጋ፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በቄለም ወለጋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የዜጎች ህይወት መጥፋቱን ኦፌኮ ጠቅሷል። መንግስት ግድያና እስራት፣ ህዝብን ከህዝብ ጋር ማጋጨት በአስቸኳይ እንደቂኦም እንዲያደርግ፣ የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ፣ አሳተፊ የሆነ የድርድር መድረክ ተከፍቶ ለአገሪቱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ ጠይቋል።

10 ሺ የሚጠጉ የሞያሌ ከተማ ተፈናቃዮች ስደት መጠየቃቸውን ተመድ አስታወቀ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም)
ኬንያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር ባወጣው ዘገባ፣ እስካሁን 9 ሺ 700 ስደተኞች ከኦሮም ክልል ሞያሌ ከተማ ተፈናቅለው ኬንያ ገብተዋል። ስደተኞቹ 13 ሰዎች በወታደሮች መገደላቸውን እንደተናገሩ ተመድ አስታውቛል። በላይነሽ ታደሰ የተባሉ የ2 ልጆች እናት ፣ ጎረቤታቸው ከትምህርት ቤት የወላጆች ስብሰባ ሲመለስ በጥይት መገደሉን፣ በማግስቱ ሌላ ጓደኛቸው ወደ ሱቅ ሲሄድ ምሽት ላይ አንቀው መግደላቸውንና በዚህም የተነሳ ለደህንነታቸው ሰግተው መሰደዳቸውን ተናግረዋል።
80 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን የገለጸው ድርጅቱ፣ 1 ሺ 500 የሚሆኑት ስደተኞች እድሜያቸው ከ5 አመታት በታች ነው ብሎአል። አንድ ከተወለደ 6 ቀን የሆነው ህጻን መሰደዱን እንዲሁም 600 እርጉዝ ሴቶች መኖራቸውን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። በሶማሪ እና ሶሎሎ በሚባሉ የሞያሌ አካባቢዎች በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የሚገኙት ስደተኞች አፋጣኝ የሆነ ምግብ፣ ውሃ፣ የመጸዳጃ አገልግሎት፣ መጠለያና የህክምና ቁሳቁሶች እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል። ተመድ ብርድ ልብስ፣ ሳሙና፣ ጄሪካን፣ የማብሰያ እቃዎችንና የመሳሰሉትን ነገሮች አድሏል።
አብዛኞቹ ስደተኞች ሞያሌ ውስጥ በሚያውቋቸው ሰዎች ተጠልለው በመገኘታቸው የስደተኞችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ አለመቻሉንም ድርጅቱ አክሎ ገልጿል። ባለፉት 2 አመታት ብቻ ከ700 ሺ በላይ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል።

አማራ ክልል የሚታየው የነዳጅ እጥረት የክልሉን ህዝብ ፈተና ውስጥ ከቶታል የዋጋ ንረቱም እያደር በመጨመር ላይ ነው

አማራ ክልል የሚታየው የነዳጅ እጥረት የክልሉን ህዝብ ፈተና ውስጥ ከቶታል የዋጋ ንረቱም እያደር በመጨመር ላይ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በክልሉ የሚታዬው የነዳጅ እጥረት የህብረተሰቡን ኑሮ ማናጋት ጀምሯል። ነዳጅ ለማግኘት ለቀናት ወረፋ መያዝ ግድ እያለ ነው። በነዳጅ የሚሰሩ ፋብሪካዎች ስራ እያቆሙ ነው። የትራንስፖርት ዘርፉ በአጋጣመው የነዳጅ እጥረት የዋጋ ጭማሪ እያደረገ ነው። ይህን ተከትሎም የእቃዎች ዋጋ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው። በክልሉ ያለው የነዳጅ አቅርቦት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ ለክልሉ ነዳጅ የሚያቀርቡ ኩባንያዎችና በለማደያዎች በአንድ የምክክር መድረክ ላይ በአንድ ድምጽ ተናግረዋል። የአማራ ክልል የመገናኛ ብዙሃን በክልሉ የነዳጅ ፍላጐት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም፣ የነዳጅ አቅርቦቱና ስርጭቱን ግን አነስተኛ እና ኢ-ፍትሃዊ በመሆኑ ተሽከርካሪዎችና በነዳጅ የሚሰሩ ኢንዱስትሪዎች ብዙ ጊዜ ሥራ ለመፍታት መገደዳቸውን ይፋ አድርጓል። በክልሉ ለተፈጠረው የነዳጅ እጥረት በምክንያትነት የቀረቡት በክልሉ ያለው የነዳጅ ማጠራቀሚያ በደርግ ዘመን የተገነባ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ መጨመሩን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) የነዳጅ እቀባ ጥሪውን ተከትሎ ስጋት የገባቸው የነዳጅ ቦቴ ሾፌሮች በአንዳንድ ቦታዎች መቆማቸውንም የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ለመንግስትና ለፓርቲ መገናኛ ብዙሃን አምነዋል። የሞያሌ ነዋሪዎች ወደ ኬንያ የተሰደዱት ደግሞ ኦነግ በነዛው ውዥንብር ነው ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ አቶ አሰፋ አብዩ በሳምንቱ መጨረሻ በሰጡት መግላጫቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ በመጠንም በስፋትም መጨመሩን ገልጸዋል። ከመሳሪያ ዝውውሩ ጀርባ የኤርትራን መንግስትንም ተጠያቂ አድርገዋል። ከሕገወጥ መሳሪያ ዝውውሩ በተጨማሪ አሸባሪዎችም በመግባት ላይ ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ አሁንም ለመግባት የተዘጋጁና በድንበር ላይ የሚገኙ መኖራቸውንም አመልክተዋል። ሕዝቡም በተለይ ድንበር ላይ የሚኖረው ሕዝብ ለመግባት የተዘጋጁትን እንዲከለክሉም የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ጥሪ አቅርበዋል። ሳምንት ያህል በዘለቀው የነዳጅ እቀባ ርምጃ ሳቢያ አንዳንድ የቦቴ ሾፌሮች በስጋት ለመቆም መገደዳቸውን አምነዋል። ሆኖም የነዳጅ እቀባው ተጽእኖ አልነበረውም በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል። ከሞያሌ የተሰደዱትን ኢትዮጵያውያንን በተመለከተም ሰዎቹ የተሰደዱት ኦነግ ባሰራጨው ውዥንብር ተመርተው ነው ማለታቸውም ተመልክቷል። የመከላከያ ሰራዊቱ ሕዝባዊ እንደሆነ የተናገሩት የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ አቶ አሰፋ አብዩ ክላሽ ይዞ በሲቪሎች የሚገደል እንደሆነም ተናግረዋል። በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች የክልል ፖሊስና ሚሊሺያ ጭምር በኮማንድ ፖስቱ ስር በአንድ እዝ እንደሚመራም ተናግረዋል። ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውሩን ለመግታት በቅርቡ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ሕግ እንደሚወጣም በዚሁ ቃለ ምልልስ ወቅት አንስተዋል።

በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተጠራው የማስተጓጎል ዘመቻ በመጨረሻ ቀኑ ዛሬም በመካሄድ ላይ ነው።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) በሰሜን ጎንደር ሸሃዲ አካባቢ በአንድ የነዳጅ ማመላለሺያ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በአንድ ሳምንት ግዜ ወስጥ የተቃጠሉ የነዳጅ ቦቴዎች ቁጥር ሶስት ደርሷል። በአዲስ አበባ የነዳጅ አቅርቦት ባለመኖሩ ጥቂት የማይባሉ ማደያዎች ዝግ ሆነው መዋላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በጎንደር ነዳጅ ለማግኘት ታክሲዎች ረጅም ሰልፍ ይዘው መቆየታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በባህርዳር፣ ደብረታቦርና ሌሎች ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱም ታውቋል። ፎርቹን የተሰኘው አዲስ አበባ የሚታተመው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አዲስ አበባ ሰሞኑን የገጠማትን የነዳጅ ቀውስ በተመለከተ ላሰፈረው ጽሁፍ የተጠቀመው ርዕስ ‘’አዲስ አበባን ነዳጅ ጠማት’’ የሚል ነው። ምንም እንኳን የአገዛዙ ባለስልጣናት ምንም ዓይነት ተጽዕኖ እንዳልተፈጠረ ቢገልጹም በመላ ሀገሪቱ የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መኖሩን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ናቸው። የነዳጅ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች በወታደራዊ አጀብ

Thursday, March 15, 2018

በኢትዮጵያ በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ኬንያ በስደተኞች ልትጥለቀለቅ ትችላለች በማለት የኬንያ ምሁራን ስጋታቸውን ገለፁ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010)በኢትዮጵያ በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ኬንያ በስደተኞች ልትጥለቀለቅ ትችላለች በማለት የኬንያ ምሁራን ስጋታቸውን ገለፁ። በአዲስ አበባ ዙሪያ በየጎዳናው ሰዎች እየተገደሉ የአፍሪካ ሕብረት አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ እስከመቼ ዝም ይላል ሲሉም ጠይቀዋል። የአፍሪካ ህብረት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር ጥሪ በማቅረብ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ቀውስ ለማርገብ እንዲንቀሳቀስም ጠይቀዋል። ኢትዮጳያ የጭቆናው ሥረዓት ፍጻሜ ላይ ናት ሲሉም ተደምጠዋል። የኬኒያው NTV ቴሊቪዥን ትናንት ባዘጋጀው በዚህ ውይይት ላይ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኬንያ ዳይሬክተርን ጨምሮ በውይይቱ የተሳተፉት ኬንያውያን ምሁራን በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ የዘለቀው የዲሞክራሲ ዕጦት እና አምባገነናዊ አስተዳደር ዛሬ ሐገሪቱ ለገባችበት ቀውስ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያውያን ቤታቸውና የገበያ ቦታቸው ጭምር መገደያቸው እየሆነ በመምጣቱ ወደ ኬንያ ለመሰደድ ተገደዋል ያሉት የኬንያ ምሁራን ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የኬንያው NTV ትናንት ናይሮቢ ላይ ያወያያቸው ኬንያውያን ባለሞያዎች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢነቱ ለኬንያውያንም የሚተርፍ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ኬንያ በስደተኛ ልትጥለቀለቅ ትችላለች በማለትም ሁሉም በጋራ ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል። ከተወያዮቹ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሞሪንጋ እንደተናገሩት በአፍሪካ ቀንድ ፀጥታ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደ ውይይት የኢትዮጵያ ጉዳይ መነሳቱን አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ ቀውስ ስለሚያስከትለው ውጤት የአካባቢው ሐገራት ምን ያህል ዝግጁ ናቸው የሚለውን አንስተን ተወያይተናል ያሉት ዶክተር ሞሪንጋ ጭቆና ስደትና ስርዓተ አልበኝነትን እንደሚያስከትል ገልጸዋል። ከሲቪሎች አልፎ የወታደሮችን ስደት ጭምር እንደሚያስከትልም አሳስበዋል። የሚሰደዱት ሁሉ

በሞያሌ ከተማ በመከላከያ ሰራዊት የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም ያሉት የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታየ ደንዳአ መታሰራቸው ተነገረ፡፡

Image may contain: 1 person, closeup(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) በሞያሌ ከተማ በመከላከያ ሰራዊት የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም ያሉት የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታየ ደንዳአ መታሰራቸው ተነገረ፡፡ አቶ ታየ በፌዴራል ፖሊስ አባላት የታሰሩት አዲሱ ገበያ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ ስራ ሲሄዱ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ በቅርቡ በሞያሌ ከተማ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዛቸው ይታወቃል። በመከላከያ ሰራዊት አባላት በግፍ የተገደሉት ከ13 በላይ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች በስሕተት አይደልም ማለታቸውም ይታወሳል። “የመከላከያም ሆነ የኮማንድ ፖስቱ አዛዦች በህግ ሊጠየቁ ይገባል” ማለታቸውም ለእስር እንደዳረጋቸው የብዙዎች ግምት ነው። የአቶ ታዬ ባለቤት ወይዘሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል እንደተናገሩት ባለቤታቸው መታሰራቸውን እንጂ የት እንደሚገኙ የሚያውቁት ነገር የለም። እንደ ቢቢሲ ዘገባ አቶ ታየ ደንዳኣ የታሰሩበት ጉዳዩ በግልጽ አይታወቅም ቢባልም በሞያሌው ጉዳይ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ እውቅና ውጭ ለጀርመን ድምጽ ሬድዮ

አርበኞች ግንቦት ሰባት አንድ የሕወሐት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር መግደሉን አስታወቀ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት አንድ የሕወሐት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር መግደሉን አስታወቀ። ፋይል የተገደለው ከፍተኛ የሕወሃት ወታደራዊ አመራሩ የኮለኔልነት ማእረግ ያለው መሆኑ ተገልጿል። ኮለኔሉ ከመከላከያ ማዕከላዊ እዝ ሐይል የተወሰኑ ወታደሮችን በመያዝ ለከፍተኛ ተልእኮ ከሽሬ ወደ ጎንደር በማምራት ላይ እያለ የግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ትናንት ረቡዕ ሊማሊሞ ላይ በሰነዘሩት ጥቃት መገደሉን የግንባሩ ሕዝብ ግኑኝነት አስታወቋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝብ ግኑኝነት እንዳስታወቀው ኮሎኔል ሐብቶም የተባለው የሕወሀት ወታደራዊ ኣዛዥ በአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች የተገደለው በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ አለፍ ብሎ ሊማሊሞ አካበቢ ነው። ረቡዕ መጋቢት 5/2010 ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ የተገደለው ኮለኔል ሃብቶም የመከላከያ ማዕከላዊ እዝ የሀይል አመራር አባላትን ይዞ ወደ ጎንደር ለወታደራዊ ተልኮ ሲንቀሳቀስ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። ኮለኔሉ በአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ጥቃት ደርሶበት ሲገደል አንድ አጃቢውም በከፍተኛ ደረጃ የመቁሰል አደጋ እንደ ደረሰበት የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት መግለጹን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በአካባቢው የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎም ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ተልእኳቸውን ፈጽመው መሰወራቸውን በመግለጫው ተመልክቷል። የኮሎኔሉ አስከሬን ዛሬ መጋቢት 6/2010 ከረፋዱ 4 ሰአት ላይ ወደ ትግራይ መላኩንም ንቅናቄው አስታውቋል።

ሊቢያ በህገወጥ ሰው ማዘዋወር ስራ ላይ ተሰማርተዋል ባለቻቸው 250 ግለሰቦች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቷን አስታውቀች።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) ሊቢያ በህገወጥ ሰው ማዘዋወር ስራ ላይ ተሰማርተዋል ባለቻቸው 250 ግለሰቦች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቷን አስታውቀች። ሊቢያውያንና ሌሎች የውጪ ዜጎች በተጠረጠሩበት በዚህ ወንጀል ከፍተኛ የደህንነት ሰራተኞች ፣ የመጠለያ ካምፕ ሃላፊዎች እና በሊቢያ የሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞች ተሳታፊ ናቸው ሲሉ የሊቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገልጸዋል። የሙሀመድ ጋዳፊን መውደቅ ተከትሎ ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው ሊቢያ በህገጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ቶርቸርን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የሰብባዊ መብት ጥሰት እንደሚካሄድ ቢቢሲ ዘግቧል። በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ በባህር ለሚደረገው ጉዞ እንደመሸጋገሪያ የምታገለግለው ሊቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች የስቃይ መነሃሪያ መሆንዋን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። እራሱን እስላማዊ እስቴት በማለት በሚጥራው ቡድን ይከናወናል በተባለው የባሪያ ንግድን ጨምሮ እንግልትና ግድያ በርካቶች ለስቃይ መዳረጋቸውን ከስፍራው በተደጋጋሚ ከሚወጡ ዘገባዎች ሲሰማ ቆይቷል። በጣሊያን መንግስት ድጋፍ በህገጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ላይ

Tuesday, March 13, 2018

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ለተፈጠረው ቀውስ ዋናው መንስኤ የስልጣን አተያይ እና የድርጅት የመበስበስ ችግር መሆኑን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለጹ።

 ኢሕአዴግ ከግንባርነት ወጥቶ ከብሄር ድርጅትነት ወደ ሃገራዊ ፓርቲነት ለመቀየር በቀጣዩ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚቀርብም ገልጸዋል። የኢሕአዴግ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዳሉት ግንባሩ ወደ ውህድ ፓርቲነት ከመቀየሩ ሌላ የአጋር ድርጅቶችም ጉዳይ የዚሁ አካል እንዲሆኑ ታሳቢ እየተደረገ ነው። ኢሕአዴግ ወደ አንድ ውህድ ፓርቲነት ለመሸጋገር ጥናት ያስፈልጋል በሚል ትቶት የቆየውን ጉዳይ ያነሳው የሕዝቡን ተቃውሞ ለመሸንገል መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት የሕዝቡ ተቃውሞ ተባብሶ ቀውስ ውስጥ ለመግባት የተቻለው ውስጣዊ የስልጣን ብልሽትና የድርጅት የመበስበስ ችግር ኢሕአዴግን ስላጋጠመው ነው። እናም ችግሩን ለማስወገድ ኢሕአዴግ አደረጃጀቱን መፈተሽ አለበት ብለዋል። እንደ አቶ ሽፈራው ገለጻ ኢሕአዴግ ከብሔራዊ አደረጃጀት ወጥቶ በዘላቂነት ወደ አንድ አገራዊ ፓርቲነት መሸጋገር ይኖርበታል። ይህንኑ በተመለከተም የኢሕአዴግ ስራአስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ ተስማምቷል ነው ያሉት። በዚሁም መሰረት ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ፓርቲ አደረጃጀት ለመቀየር በመጪው ነሐሴ በሚካሄደው የድርጅቱ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚቀርብ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ሕይወት አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ38 ሰዎች ሕይወት አለፈ። 
አደጋው የደረሰው በደቡብ ወሎ ለጋምቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ገነቴ ሰላም በር በታባለ ቦታ ነው።
በአደጋው የ38 ሰዎች ሕይወት ከማለፉ በተጨማሪ 10 ሰዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
ተጎጂዎቹ በአቀስታ ሕዳር 11 እና በደሴ ሪፈራል ሆስፒታሎች የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገልጸዋል።
የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሱ 48 ሰዎችን አሳፍሮ ለጋምቦ ወረዳ ቀበሌ 07 ልዩ ስሙ ገነቴ ሰላምበር በተባለ ቦታ 5 ሜትር ቁልቁለት ላይ ዘሎ በመግባቱ አደጋው መድረሱ ታውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኪና አደጋ ጋር በተያያዘ የአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚሞቱና ለከፋ አደጋ እንደሚዳረጉ ይነገራል።

የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በውጥረት መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ--መጋቢት 4/2010)የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ውጥረት በተመላበት ሁኔታ መቀጠሉ ተሰማ።
አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የመምረጡ ሂደት በፈጠረው ውዝግብ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰየሙ ሒደት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ሃሳብ መቅረቡም ተመልክቷል።
በሕወሃት ሰዎች እንዲሁም ከብአዴን አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው ከህወሃት ጎን በመሰለፍ ኦሕዴድን በማጥቃት ላይ መሆናቸውም ተመልክቷል።
እሁድ የተጀመረውና የድርጅቱን ሊቀመንበር መምረጥን በዋናነት አጀንዳ ያደረገው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እንደተጠበቀው የድርጅቱን ሊቀመንበር ለፓርቲው ምክር ቤት ማቅረቡ አጠራጣሪ ሆኗል።
በብዙዎች ዘንድ የሚጠበቁትንና ምዕራባውያንም በተለይም ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ጭምር በመፍትሄነት ያቀረበቻቸውን ዶክተር አብይ አሕመድን የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ሰዎች በፍጹም የሚቃወሙ ሆነው ተገኝተዋል።

በእስር ላይ የሚገኙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መስፋፋትና የመሬት ቅርምት በመቃወማቸው ብቻ ከሚማሩበት ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከታሰሩ ተማሪዎች ውስጥ የተወሰኑት ቢፈቱም ቀሪዎቹ አስታዋሽ አጥተው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ። በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ፋኩልቲ ተማሪ የሆኑት ወየቻ ታምሩ፣ ወሰኑ ገረመው፣ ዮሃንስ ፉርጋሳ፣ ገዳ ገመቹ፣ ኢዮብ ሙሊሳ እና ሳሎ ነጋሳ በእስር ቤት በሚፈጸምባቸው ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶችን ጨምሮ ከወላጅ ቤተሰቦቻቸው እርቀው በመታሰራቸው ጠያቂና አስታዋሽ አላገኙም። ተማሪዎቹ በችግር ላይ እንገኛለን ሚዲያም ሆነ ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች እያስታወሱን አይደለም ብለዋል። ተማሪዎቹ እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት በመቀያየር እንዲገላቱ ተደርገዋል። ወንጀል ፈጽመዋል ወደተባለበት አካባቢ ሄደው እንዲዳኙ ተብሎ ሚያዝያ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ወደ ዲላ ከተማ ቢዛወሩም ሀምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም ወደ ሃዋሳ እንዲዛወሩ ተደርጎ አሁንም ካለ ፍትሕ በእስር ላይ ይገኛሉ። ከመሃከላቸው በተመሳሳይ ክስ ተከሶ የነበረው ቦረና አበራ የካቲት 7ቀን 2010 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በነፃ ሲሰናበት ቀሪዎቹ እንዲከላከሉ ቢበይንባቸውም አንከላከልም በሚለው አቋማቸው መጽናታቸውን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ተመልክቶ የቀረበው እቅድ ተቃውሞ ገጠመው

(ኢሳት ዜና ማጋቢት 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ፣ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አማኑኤል አብርሃም ፣ አቶ አጽብሐ አረጋዊ ፣ የሰብአዊ መብት ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር በተገኙበት የወቅቱን የሀገሪቱን ሁኔታ ተመልክቶ በአገዛዙ የቀረበው ስምንት ነጥቦችን የያዘው የእቅድ ዝርዝር ተቃውሞ አጋጥሞታል። በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት መካከል አንድ ሴት ተናገሪ “ከመድረክ እንደቀረበው ሳይሆን በአሁን ጊዜ ለሀገራችን ወቅታዊ ችግር ያበቃን የተደራጀ ፀረ ሰላም ሃይል ተፈጥሮ አይደለም፣ ትልቁ ችግር የራሳችንን ችግር ነው። ይህንን ለምን እንደብቃለን? ለሀገር ይጠቅማል ብለን አንድ ጉዳይ ስናነሳ የተቃዋሚ ፓርቲ ሃሳብ እና አቋም ነው ተብለን እንድንሸማቀቅ እንደረጋለን። ይሄ ችግር እያለ ፀረ ሰላም ሃይሎች ብለን መፈረጃችንን አግባብነት የለውም” ብለዋል። ሌላው ተናጋሪ ደግሞ “ የመንግስት አመራሮች ብቃት ራሱ አጠያያቂ ነው ። ብቃታቸው በደንብ መፈተሽ አለበት ። አመራሮቹ ሁል ጊዜ የውጭ ሃይሎች ሴራ ነው እያሉ እስከመቼ ያደበሰብሳሉ? አንድ የመከላከያ አባል በምን ሚዛን፣ በምን ዳኝነት ነው መሳርያ ባልታጠቁ ዜጎቹ ላይ ጥይት የሚያርከፈክፈው? ሰራዊታችን ሕዝባዊ ነው እየተባለ በየመድረኩ የሚነገረው

Monday, March 12, 2018

ደኢህዴን - የወቅቱ የህወሓት “ምርጥ ባርያ” (Tadesse Biru Kersmo)

የህወሓት መሰሪ የአገዛዝ ስልት የባርያ አሳዳሪ ሥርዓትን ይመስላል።
ህወሓት በመላው ኢትዮጵያ አገልጋዮች አሉት። እነዚህ አገልጋዮች ጌታቸው ህወሓት ያዘዛቸውን ይፈጽማሉ፤ ውረሩ ሲባሉ ይወራሉ፤ ግረፉ ሲባሉ ይገርፋሉ፤ ግደሉ ሲባሉ ይገድላሉ፤ ዝረፉ ሲባሉ ይዘርፋሉ። ህወሓት እነዚህን በቁጥር የበዙ አገልጋዮቹን የሚቆጣጠረው ከእነሱ በላይ ታማኝ በሆኑ “ምርጥ ባርያዎቹ” አማካይነት ነው። ጌታው ህወሓት ያለብዙ ድካም ኢትዮጵያዊያንን በአገልጋዮቹ፤ አገልጋዮቹን ደግሞ በምርጥ ባርያዎቹ እየተቆጣጠረ ይገዛል።
የህወሓት “ምርጥ ባርያዎች” ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ጥረት የሚያደርጉ አገልጋዮችን ይሰልላሉ፤ ያጋልጣሉ። መሰሪው ህወሓት ታማኝ አገልጋዮቹ “ለምርጥ ባርያነት” እንዲፎካከሩ በማድረግ ባሮችን በባሮች ይገዛል።
ከነፃነት እሳቤ አንፃር ሲታይ ከባርነት የከፉ ነገር ማሰብ ይከብዳል። ባርነት ሰው በመሆንና እንስሳ በመሆን መካከል ያለ ድንበር ነው። ይሁን እንጂ ባርያ መሆን ባርነት ተቀብሎ የመኖርን ያህል የከፋ አይደለም። የህሊና ነፃነት ያለው ባሪያ ነገ ነፃ ሰው የመሆን እድል አለው። ባርያነቱን የተቀበለ ባርያ ግን በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው፤ ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም። ባርነትን ከመቀበል ባለፈ ከባርያ አሳዳሪው ጋር ተሻርኮ ሌሎች የሚሰልል፤ የነፃነት ትግልን የሚያደናቅፍ ባርያ ደግሞ ከባርያ አሳዳሪው በላይ የነፃነት ጠላት ነው።

አዲ ረመጥ በሚገኘው ሱር ኮንስትራክሽን ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ምንጮች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩልን መረጃ ባለፈው አርብ አዲ ረመጥ ላይ በሚገኘውና የህወሃት ንብረት በሆነው ሱር ኮንትስራክሽ ኩባንያ ንብረት ላይ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጽሞ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ የደረሰው የሱር አማካሪ በሆነው ልደት ኮንሳልታንት የግል ድርጅት ላይ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጥቃቱ የተጎዳ ሰው አለመኖሩም ታውቋል። ይህን ተከትሎ ወታደሮች ህዝቡን ሰብስበው ጥቃቱን የፈጸሙትን ሃይሎች እንዲያጋልጥ ለማሳመን ቢሞክሩም ሳይሳካለቸው ቀርቷል። ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው የታወቀ ነገር የለም። በዚሁ ቀን ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ሰቲት ሃውስ ፊት ለፊት ከሚገኘው ህብረት ሆቴል ውስጥ በደረሰ ጥቃት አንድ የመከላከያ ፓትሮል መኪና ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ከጎኑ ቆመው በነበሩ መኪኖች ላይም ጉዳት መድረሱን አርበኞች ግንቦት 7 ባለፈው አርብ የላከልን መረጃ ያመለክታል። ሆቴሉ የመንግስት እና የመከላከያ ባለስልጣናት የሚዝናኑበት ቦታ እንደነበርም ንቅናቄው የላከው መረጃ ያስረዳል።

በሞያሌ ከተማ ዛሬም ግድያ አለመቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

 (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ በሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ13 ሰዎች በላይ መግደላቸውን ተከትሎ ግድያውና ውጥረቱ አሁንም ድረስ ያለ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትናንት ምሽት አንድ የኮንሶ ብሄረሰብ ተወላጅ ሌሊት ላይ በ10 ጥይቶች ተደብድቦ ተገድሎአል። አንድ የምዕራብ ጉጂ አካባቢ ተወላጅ የሆነ ወጣት ደግሞ በ 2 ጥይቶች ተመትቶ ቆስሏል። ባለፈው ቅዳሜ የመከላከያ ሰራዊት ለፈጸሙት ጭፍጨፋ በህዝቡ፣ ወታደራዊ አዛዦችና የአገዛዙ ባለስልጣናት የተለያዩ ምክንያቶችን እየሰጡ ነው። የከተማዋ ነዋሪዎችና የአካባቢው ሰዎች ምንም ተቃውሞ ባልነበረበት ሁኔታ ወታደሮች እርምጃ መውሰዳቸው በግድያ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ ሙከራ እና ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ነው ይላሉ። የከተማዋ ከንቲባ አቶ አስቻለው ዮሃንስ “አካባቢው ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አልነበረም ፤ ሕዝቡ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ነበር። ልጁን አውርደው መቱት ከዛ በኋላ ወደ መንደሩ እያዞሩ መተኮስ ጀመሩ።” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ኮማንድ ፖስቱን በመወከል መግለጫ የሰጡት ሌ/ጄ ሃሰን ኢብራሂም ድርጊቱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ጋር የተያያዘ ሳይሆን መደበኛ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ የነበረውን የኦነግን ሰራዊት ለመከላከል በሚል በአካባቢው የተሰማራው አንድ ሻለቃ ጦር በተሳሳተ መረጃ የወሰደው እርምጃ ነው ብለዋል። ጄኔራሉ ድርጊቱ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እንደማይያያዝና የመከላከያ ጉዳይ

በሞያሌ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በመሸሽ ኬኒያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 50 ሺህ መድረሱ ተገለጸ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010)  የአጋዚ ወታደሮች የሚፈጽሙት ግድያም ቀጥሏል። ወደ ኬኒያ በሽሽት ላይ በነበሩ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ትላንት ተኩስ የከፈተው የአጋዚ ሃይል 2 ሰዎች መግደሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል የሞያሌው ጭፍጨፋ በስህተት የተፈጸመ ነው የሚለው የአገዛዙ መግለጫ ቁጣን ቀስቅሷል። ቅዳሜ ለሞያሌ ነዋሪዎች ጥሩ ቀን አልነበረም። በጠዋት በወትሮው እንቅስቃሴዋ ላይ ተጠምዳ የነበረችው ሞያሌ ድንገት የታጠቀ ሰራዊት ዘመተባት። የአጋዚ ሰራዊት በጠራራ ጸሀይ ነዋሪውን እያሳደደ፣ ሱቅና መደብሮችን እያከፈተ በጥይት መደብደብ ጀመረ። በትንሹ 10 ነዋሪዎች ወዲያውኑ ወደቁ። በአንዳንዶች መረጃ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 17 እንደሆነ ይገለጻል። ሞያሌ ሳይታሰብ ድንገት በዘመተባት የአጋዚ ሰራዊት ዕልቂት ተፈጸመባት። ከ30 በላይ ሰዎች ቆስለው ወደ ህክምና ማዕከላት ተወስደዋል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች ምናልባትም የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ከተገደሉት መሀል በአርዓያነታቸው በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ተሸላሚ የሆኑ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር እንደሚገኙበትም ተገልጿል። ሁኔታው በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያንን ያስደነገጠና ያሳዘነ ሆኗል። ጭፍጨፋው በተፈጸመ ዕለት መግለጫ

በቄሮ የተጠራውና የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል የታቀደው ዘመቻ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በቄሮ የተጠራውና የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል የታቀደው ዘመቻ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ። ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው በዚሁ ዘመቻ ቦቴዎች ከውጭ ሃገር ነዳጅ ጭነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ይደረጋል። በሃገር ውስጥም ነዳጅ ጭነው ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል። ዘመቻው የሚጀመረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ በርካታ ሰዎች በመገደላቸው ነው። በቄሮ የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው። የአገዛዙን ገዳይና ጨቋኝ አካሄድ ለመግታት በዚሁ ዘመቻ ከውጭ ሃገር የሚገቡም ሆነ በሐገር ውስጥ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ የነዳጅ መጫኛ ተሽከርካሪዎች የጥቃት ኢላማ ይሆናሉ ተብሏል። የኦሮሚያ ቄሮዎች ያወጡት መግለጫ እንደሚያመለክተው ይህን ዘመቻ እያወቁ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ለሚደርስባቸው ጥቃት ሃላፊነቱን ራሳቸው ይወስዳሉ። እናም በተሽከርካሪዎቹ ላይ ርምጃ ከመወሰዱ በፊት ማዕቀቡን አክብረው እንዳይንቀሳቀሱ ቄሮዎች እንመክራለን ብለዋል። በቄሮዎቹ መግለጫ መሰረት የነዳጅ አቅርቦትን

) በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት የ38ቱ ሰዎች የፍርድ ውሳኔ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010 ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለሌላ ጊዜ ያስተላለፈው በስራ መብዛት እና ሰንዶችን መርምሬ ባለመጨረሴ ነው ብሏል። በእነ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 38 ተከሳሾች በፍርድቤቱ ቀነ ቀጠሮ መራዘም ያላቸውን ቅሬታ መግለጻቸው ተነግሯል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱ ሰዎችን በተመለከተ አቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን ምስክሮች ሲሰማ ነበር የቆየው። ፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ ካቀረባቸው 85 ምስክሮችን የ48ቱን በመቀበል የሌሎቹን 28 ግን ውድቅ ማድረጉም ይታወሳል። የአቃቤ ሕግ ምስክሮቹ በተከሳሾቹ ላይ ቢመሰክሩም ፣የመሰከሩባቸውን ሰዎች ማንነት አለማወቃቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጾ ነበር። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የ25 ገጽ ሪፖርትን ጨምሮ በተከሳሾች ላይ በቀረበው ማስረጃ መሰረት ፍርድ ቤቱ በ38ቱም ተከሳሾች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም በስራ መብዛትና ሰነዶችን መርምሬ አልጨረስኩም በሚል ሰበብ በቀነ ቀጠሮ አልፎታል። በዚሁም መሰረት በእነ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ በተከሰሱ 38 ተከሳሾች ላይ የጥፍተኝነትም ሆነ

በአማራ ሕዝብ ስም የተደራጁ 18 የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት በጋራ ተደጋግፎ ለመስራትና በተቀናጀ መልኩ ለመታገል መስማማታቸውን ገለጹ።

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2018) በአማራ ሕዝብ ስም የተደራጁ 18 የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት በጋራ ተደጋግፎ ለመስራትና በተቀናጀ መልኩ ለመታገል መስማማታቸውን ገለጹ። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም የአማራ ድርጅቶች አመራር ሰጭ አካል እንዲቋቋም በሜሪላንድ ሲሊቨር ስፕሪንግ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 2 /2010 ባካሄዱት ዝግ ስብሰባ መወሰናቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫው እንደተመለከተው የአማራ ሕዝብ ለሃገሩ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውለታ የከፈለ ቢሆንም በጨቋኝነት ተፈርጆ ከፍተኛ በደልና ግፍ እየደረሰበት ይገኛል። በዚሁም ምክንያት እየደረሰበት ያለውን የመፈናቀል፣የማንነትና የህልውና አደጋዎችን ለመከላከል ድርጅቶቹ በተለያየ መልኩ ተደራጅተው ሲታገሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል። እናም የምንታገልለት ሕዝብም ሆነ አላማ አንድ በመሆኑ የእስካሁኑን ትግል ውጤታማ ለማድረግ በጋራ ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል።

Sunday, March 11, 2018

አቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ በህወሃቱ ኮሎኔል አብረሃ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው አጋለጡ

 (ኢሳት ዜና
ከሚኖሩበት ሰሜን አሜሪካ ወደ አገራቸው በመግባት ከአገዛዙ ባለስልጣናት ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ ሳይኖራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ መዋእለ ንዋያቸውን በማፍሰስ በግሉ የንግድ ዘርፍ ከተሰማሩ በጣት ከሚቆጠሩ ባለሃብቶች አንዱ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ድርጅታቸው ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ሴራ ኪሳራ ላይ እንዲገባ መደረጉን ከሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
አቶ ኤርሚያስ የአክሰስ ሪል ስቴት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ባለቤት የሆኑት ኮሎኔል አብርሃ ስላደረሱባቸው የመብት ጥሰቶች ሲገልጹ” በወር የ540 ሰራተኞች 750 ሺህ ብር በወር ከፍለናል። በተግባር ግን ከ120 ሰው በላይ ተሰልፎ አያውቅም። በወር ወደ 500 ሽህ ብር የተጭበረበረ ነበር። ፖሊስ ጣቢያ ከስሻለሁ። ይህን አልፈርምም ስል በጣቱ እያሳየኝ ኤርሚያስ እኔ እኮ አሁን ግንባርህን ብልህ እኔ ባለኝ ኮኔክሽን ከእስር እንደምወጣ አታውቅም ወይ? ሲል አስጠነቀቀኝ። ፖለቲከኞችንና የሚሊቴሪ ስሞችን እየጠራ የማይደፈሩ ስሞችን ሳሞራ፣ ስብሃት እያለ እየጠራ አስፈራራኝ። የቤተመንግስቱን ጥበቃ ያደራጀሁት እኔ ነኝ፣ የኤርትራን ጦርነት መሃል ግንባር የመራሁት እኔ ነኝ

የነዳጅ አቅርቦት ለማስተጓጎል በቄሮ የተጠራ ዘመቻ

እንደሚታወቀው የወያኔው ቡድን በፓርላማውም ውድቅ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ወዲህ አጋዚ ወታደሮቹን በሰላማዊ ህዝብ ላይ በማሰማራት በየቀኑ ከህጻን እስከ አዛውንት ያሉ ዜጎቻችንን እየገደለ ይገኛል። እስካሁን ድረስ በነቀምቴ፣ በአምቦ፣ በደምቢዶሎ፣ በጊምቢ፣ በጊንጪ እንዲሁም ዛሬ ደግሞ በሞያሌ በርካታ ንጹሃን ዜጎች በአጋዚ ጥይት ተገድለዋል። ይህም ከፍተኛ የሆነ ቁጣ በህዝባችን ውስጥ ፈጥሯል። ስለዚህም ወያኔ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮቹን በፍጥነት ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ህዝባችንን እንዳይፈጅ እንቅስቃሴውን ለመግታት ብሎም የመጨቆኛ አቅም ለማዳከም የነዳጅ አቅርቦት የማቋረጥ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል ።

Friday, March 9, 2018

ባለፈው ሳምንት የተደረገውን የስራ ማቆም አድማ ተሳትፋችሁዋል የተባሉ የህሊና ምግብ ፋብሪካ ሰራተኞች ቅዳሜና እሁድ ያለ ክፍያ እንዲሰሩ ታዘዙ

(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ለገጣፎ የሚገኘው ህሊና የተመጣጠነ ምግብ አምራች ኩባንያ ባወጣው ማስጠንቀቂያ ሰራተኞች ያለ ምንም ክፍያ ቅዳሜ እና እሁድ እየገቡ የማካካሻ ስራ እንዲሰሩ ታዘዋል። ድርርጅት ከዚህ በሁዋላ ሰራተኞች በስራ ማቆም አድማ የሚሳተፉ ከሆነ ያለ ምንም እረፍት ከ4-5 ወራት እንደሚሰሩ ተነግሯቸዋል። ኩባንያው በስብሰባ አዳራሹና በእንግዳ ማረፊያ ክፍሉ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ ለጥፎ እንደሚገኝ እንዲሁም የኩባንያው ማኔጅመንት ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር የጠበቀ ግንኙት እንዳላቸው ምንጮች ገልጸዋል። “ብሌስ አግሪ ፉድ” የተባለ እህት ኩባንያ ሲከፈት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል በእንግድነት ተገኝተው መርቀውታል። በኦሮምያ የሚካሄደው የስራ ማቆም አድማ በአገዛዙ ላይ የኢኮኖሚ ጫና ለመፍጠር መሆኑ እየታወቀ እንዲህ አይነት አገዛዙን የሚደግፍ እርምጃ መውሰዱ ሰራተኞችን አስቆጥቷል።

Ethiopia: Foreign correspondent deported to UK

ESAT News (March 9, 2018)
Ethiopian authorities deported a foreign correspondent for the Bloomberg News and The Guardian.
British journalist William Davidson was based in Ethiopia since 2010.
He said in his Facebook post that authorities have refused to renew his accreditation despite his attempt to use his connections in higher offices to renew his permit. Some criticize the journalist saying his reports on atrocities committed by the repressive regime were watered down stories of the otherwise brutal episodes in deadly anti-regime protests in recent years.

ቤት ፈላጊዎች ለኮንዶሚኒየም ግንባታ በሚል ያጠራቀሙትን ገንዘብ በብዛት ማውጣት መጀመራቸው ስጋት ላይ የገባው አገዛዙ ሚኒስትሩ ይቅርታ እንዲጠይቁ ሊያደርግ ነው

(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ሪፖርተር ጋዜጣ በቅርቡ በርካታ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቁጠባቸውን እያቋረጡ ነው በሚል የሰራው ዘገባ የአገዛዙ ባለስልጣናትን በእጅጉ አስቆጥቷል። ጋዜጣው ከ900 ሺ ዜጎች በላይ ቤት ፈላጊዎች የባንክ አካውንት ከፍተው ቁጠባ ቢጀምሩም፣ 624 ሺ ተመዝጋቢዎች ቁጠባ ማቆማቸውን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ዶ/ር አምባቸው መኰንንን በመጥቀስ ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል። ዶ/ር አምባቸው ቁጠባቸውን በትክክል እየቆጠቡ የሚገኙት ደግሞ ከ100 ሺሕ አይበልጡም በማለት መናገራቸው፣ ይህን ተከትሎም ገንዘቡን ለማውጣት የሚፍለገው ቆጣቢ በመጨመሩ እና በባንኩ ህልውና ላይ ስጋት በማሳደሩ፣ ዶ/ር አምባቸው ይቅርታ እንዲጠይቁና መረጃው እንዲስተባበል ትዕዛዝ መተላለፉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሰኞ የመንግስት የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞችና የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ “በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች/የኮንዶሚኒየም/ ቤት ተመዝጋቢዎች ቁጠባቸውን እያቋረጡ ነው” በሚል የተዘጋጀው የሪፖርተር ዜና የሚኒስትሩ ዶ/ር አምባቸው የተሳሳተ መግለጫ ወይም የአፍ ወለምታ ስለሆነ፣ ይሄን የተዛባና የተሳሳተ መረጃ ራሱ የሚኒስትር ጽ/ቤቱ ሚኒስትር ዶ/ር አምባቸው ቀርበው ማረሚያ ወይም ይቅርታ እንዲጠይቁ እንዲሁም መረጃውም የውጭ ጠላቶች መጠቀሚያ እየሆነ በመሆኑ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ተነግሯቸዋል። የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች “እንዴት ሚንስትሩ ተሳሳቱ እንበል?” በሚል በመመሪያው ግራ ተጋብተው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሰሞኑን በርካታ ዜጎች ወደ ንግድ ባንክ በመሄድ ገንዘባቸውን ለማውጣት

በአዲስ አበባ ከ2500 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ተጀመረ

(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ኪዳነ ምህረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቤት ሰርተው ይኖሩ የነበሩ ከ2500 በላይ አባዎራዎችና እማዎራዎች፣ ቤታቸው በላያቸው ላይ እንዲፈርስባቸው ተደርጓል። ፈረሳውን ተከትሎ በአማካኝ ከ12 ሺ ያላነሱ ሰዎች ቤት አልባ ይሆናሉ። በመላው አገሪቱ ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ገንዘባቸውን አፍስሰው ግንባታ ከፈጸሙ በሁዋላ፣ ህገ ወጥ ግንባታ በሚል ምክንያት ቤት እና ንብረት አልባ ሆነዋል። ይህንን እርምጃ የተቃወሙ ዜጎች ለሞት፣ለእስርና ለድብደባ ተዳርገዋል። በመጀመሪያ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የአሁኑ እርምጃም ሁለተኛውን አዋጅ ተገን በማድረግ የተወሰደ ነው።

ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ጋብ ብሎ የሰነበተው የኮሬና የጉጂ ማህበረሰብ ግጭት እንደገና አገረሸ

(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሳምንታት ጋብ ብሎ የሰነበተዉና በአካባቢው የአገዛዙ ካድሬዎች አማካኝነት መለኮሱን ነዋሪዎች የሚናገሩት የኮሬና ጉጂ ኦሮሞ ማህበረሰብ ግጭት እንደገና በማገርሸቱ፣ የዜጎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ለግጭቱ ማገርሸት አሁንም የአካባቢዉ ህብረተሰብ አገዛዙን ተጠያቂ አድርጓል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከለላ በማድረግ የሁለቱ ክልሎች ድንበር በፍጥነት መካከል አለበት በሚል እንቅስቃሴ መጀሩን ተከትሎ ጋብ ብሎ የሰነበተው ግጭት እንደገና አገርሽቷል። እስካሁን ባለው መረጃ በኮሬ በኩል ጀሎ ቀበሌ ላይ የአንድ ሰው ህይወት ሲጠፋ፣ ዳቡልቶ ቀበሌ ላይም እንዲሁ የአንድ አርሶአደር ህይወት ጠፍቷል። ከአማሮ ወረዳ ወደ ዲላ ሲጓዝ በነበረ አይሱዙ መኪና ላይ በተተኮሰ ጥይትም ሶስት ሰዎች ቆስለዋል። የድንበር ማካለሉን ተከትሎ በኮሬ፣ በቡርጅና ጉጂ ማህበረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት 8ኛ ወሩን ይዟል። በግጭቱም የበርካተ ዘጎች ህይወት ጠፍቷል።

Wednesday, March 7, 2018

አምስት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በኦሮሚያ ከተነሳው አድማ ጋር በተያያዘ አምስት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት መታሰራቸው ተነገረ።
በኦሮሚያ የተጀመረው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።
ባለስልጣናቱ የታሰሩት የስራ ማቆም አድማው እንዲካሄድ ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ነው።
በኦሮሚያ ክልል በአገዛዙ የኮማንድ ፖስት አባላት የታሰሩት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት የምስራቅ ሃረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪን የሚጨመር ነው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ አድማ ቀስቅሳችኋል ተብለው ከታሰሩት መካከልም የነቀምቴ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ፣የምዕራብ ወለጋ ዞን ቄለም ወረዳ የፍትህ አስተዳደር ሃላፊም ይገኙበታል ተብሏል።

የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱና በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው በደል እንዲቆም ተጠየቀ

Image may contain: 2 people, people standing(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በወህኒ ቤት የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱና በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው በደል እንዲቆም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ጠየቀ።
ሌሎች የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች እየተፈቱ ባሉበት ወቅት የዋልድባ መነኮሳትን በወህኒ ቤት ውስጥ ማገትና ማጎሳቆል የሕወሃት መንግስት ለቤተክርስቲያኒቱ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ ነው ሲልም ሕብረቱ አመልክቷል።
“ወይባና አስኬማ የዋልድባ መነኮሳት ክብር” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ባወጣውና ለዋልድባ መነኮሳት አጋርነቱን በገለጸበት መግለጫው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የኢትዮጵያ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቹን ማውደሙን ቀጥሏል ሲልም አውግዟል።
“በኦርቶዶክስና በሙስሊም ምዕመናን ዘንድ በእውቀታቸው፣በባህሪያቸውና በአርአያነታቸው የተመሰገኑ፣የተከበሩና ተአማኒነት ያላቸውን

Tuesday, March 6, 2018

የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ ወታደሮች 3 የአጋዚ ወታደሮችን ገደሉ

(ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘዋ ጣፎ ከተማ ላይ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች 3 የአጋዚ ወታደሮችን መግደላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ፖሊሶቹ ቀን ላይ አብረው በጥበቃ ላይ እንደነበሩ የገለጹት ምንጮች፣ ምሽት ላይ የደንብ ልብሳቸውን በመቀየርና ሲቪል ልብስ በመልበስ 3 ወታደሮችን ገድለው ተሰውረዋል። ድርጊቱን ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር እንዲሰፈር ተደርጓል። ድርጊቱን የፈጸሙትን ለመያዝ በሚል የአካባቢው ወጣቶች ታፍሰው ተወስደዋል። በዚሁ አካባቢ በሚገኘው ድልድይ አቅራቢያ አንድ ቦንብ ፈንድቶ አንድ መምህር ቆስሎ ሆስፒታል መግባቱንም ምንጮች ገልጸዋል። በአጋዚ ወታደሮችና በኦሮምያ ፖሊስ አባላት መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ፣ አለመግባባቱም የጦር መሳሪያ እስከማማዘዝ እየደረሰ መሆኑን የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት “መላ በሉን” እያሉ ነው

(ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፖሊስ አባላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው። ከዚህ ቀደም ባልታዬ መልኩ የጸጥታ ሃይሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ መጋባታቸውን፣ የተደራጀ ሃይል ውስጥ ተቀላቅለው ትግሉን ማካሄድ ቢፈልጉም የመረጃ እጥረት እንደገጠማቸውና በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ፎቶግራፋቸውን ሳይቀር በማስረጃነት በመላክ እየገለጹ ነው። የመከላከያ አባላቱ የህዝቡን ትግል የሚደግፉ መሆናቸውን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመናገር ላይ ናቸው። አንዳንዶች በፍተሻ ወቅትና ወጣቶችን ሲያገኙ እባካችሁ “ለእኛም ጸልዩልን በማለት እስከመናገር መድረሳቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። መቱ ከተማን እዲቆጣጠሩ የተላኩት መከላከያዎች ‘እኛ ወንድሞቻችንን

በኦሮምያና ጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

(ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃወም በኦሮምያ ክልል እና በጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል። አድማው በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ነው። በአዲስ አበባ ዛሬም ያልተከፈቱ የንግድ ድርጅቶች መኖራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ ከጠዋት ጀምረው ድርጅቶቻቸውን የሚዘጉና የሚከፍቱ ሰዎችን ለመሰለል ሰቪል ለብሰው ቁጥጥር ሲያደርጉ የዋሉት የደህንነት ሰራተኞች የተዘጉ የንግድ ድርጅቶችን ሲመዘግቡ ታይተዋል። የመንግስትም ሆነ የፋብሪካ ስራዎች ለሁለተኛ ቀን ተስተጓጉሎ ውሏል። በተለይ ከአዲስ አበባ በ20 ኪሜ ርቀት ላይ ስራቸውን የሚሰሩ ሰዎች በትራንስፖርት እጥረት ስራቸውን መስራት አለመቻላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በመሐል አ/አ ዙርያ እስከ 20 ኪሎ ሜትር በሚደርስ እርቀት ላይ ባሉ ከተሞች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና ከዚሁ አካባቢ ተነሰተው ወደ መሐል የሚመጡ ነጋዴዎች ወደ መሐል አዲስ አበባ መግባት አልቻሉም። በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ሲሰሩ የነበሩ አሽከርካሪዎች የደህንነት ዋስትና እንደሚሰጣቸው ተገልጾ ስራ እንዲጀምሩ ወታደሮች ለማግባባት ሙከራ ቢያደርጉም ፣ ሾፌሮቹ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው አድማ እንደቀጠለ ነው

Image may contain: one or more people, sky and outdoor(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው አድማ በኦሮሚያ ክልል ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ።
አዲስ አበባ ዙሪያን ጨምሮ በምዕራብ ሸዋ፣ በወለጋ፣ በምዕራብ ሀረርጌ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በባሌና በአርሲ ለሶስት ቀናት የተጠራው አድማ ተጠናክሮ መቀጠሉን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል።
ከአዲስ አበባ ወደተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቋርጧል። በሆለታ አንድ ወጣት በአጋዚ ወታደር በጥይት መመታቱ ታውቋል።
በመቱ አቅመ ደካማ ለሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ምግብ እንዲደርሳቸው በመደረግ ላይ ነው። ከሞያሌ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው ዋናው መስመር ከዝዋይ በኋላ መዘጋቱንም ለማወቅ ተችሏል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃወምና የቀሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ በሚል የተጀመረው የስራ ማቆምና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በሁለተኛ ቀንም የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በማቆም ቀጥሏል።
ከወለጋ ነቀምት ጊምቢ፣ ደምቢዶሎ፣ ነጆና ቄሌም ወለጋ አድማውን በተጠናከረ ሁኔታ ለሁለተኛ ቀን ካስተናገዱ ከተሞች የሚጠቀሱ ናቸው።
በተቃጠሉ ጎማዎች በርካታ መንገዶች ተዘግተው የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንዲስተጓጎል ማድረጋቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ምዕራብ ሸዋም እንዲሁ የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ሃገሪቱን በጦር ማስተዳደር አይቻልም ተባለ

Image may contain: 1 person, sitting and outdoor(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) ሃገሪቱን በጦር ማስተዳደር ለመንግስቱ ሃይለማርያምም አልበጀም ሲሉ የአባገዳዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር አባገዳ በየነ ሰንበቶ አሳሰቡ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የዋህና ለሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለሃይማኖት አባቶችና ለአባገዳዎች የሚታዘዝ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ አያስፈልገውም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለ

Image may contain: fire and outdoor(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገና ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ገለጸ።
ኦፌኮ በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና የጸደቀበት መንገድ ሕገወጥ በመሆኑ አንቀበለውም ብሏል።
አዋጁ ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑም ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ኦፌኮ ገልጿል።
የኦፌኮ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
ምክንያቱ ደግሞ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና በፓርላማ የጸደቀበት መንገድ ሕገ መንግስቱን በጣሰ መልኩ መሆኑ ነው ብለዋል።
እናም ኦፌኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደማይቀበለው ነው የገለጸው።

Tillerson announces over half a billion USD in aid for Africa, Ethiopia gets $110 million

by Engidu Woldie
ESAT News (March 6, 2018)
U.S. Secretary of State, Rex Tillerson, announced today an additional aid package amounting to $533 mainly for five African countries that are faced with food insecurity and malnutrition due to ongoing conflicts and drought.
Tillerson made the announcement today in remarks at the George Mason University ahead of his trip to five African countries beginning today. The humanitarian assistance goes to Ethiopia, Somalia, South Sudan, and Nigeria, as well as countries in the Lake Chad region, according to details of the assistance obtained from the Department of State. Of the newly announced funds, nearly $184 million is for affected populations from South Sudan, more than $110 million for

Friday, March 2, 2018

122ኛው የአድዋ የድል በአል በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችና ኢትዮጵያን በሚኖሩበት የተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በአሉ በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 23/2010) በተለይ በአዲስ አበባ የነበረው አከባበር እጅግ ደማቅና ከሌላው ጊዜ የተለየ እንደነበር በምስል ተደግፎ ከተሰራጨው መረጃ መረዳት ተችሏል። የጣሊያን ወራሪ ሃይልን ለመመከት በአጼ ሚኒሊክ የተመራው የኢትዮጵያ ጦር የዛሬ 122 አመት አድዋ ላይ ኢትዮጵያን ነጻ አውጥቷል። ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ ወደ አድዋ ጦር ግንባር ሲጓዙም በጀግንነታቸው ዘወትር የሚነሱትን ባለቤታቸውን እቴጌ ጣይቱን በማስከተል ነበር።–ጣይቱ በዛን ወቅት ጀግና ለመሆን ቆራጥነት እንጂ ወንድ ሆኖ መፈጠር አይጠይቅም በሚለው የጀግና አባባላቸውም ይታወቃሉ። ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ የጣሊያን ጦርን ድል ነስተውና አሳፍረው ከመመለሳቸው ባለፈም ኢትዮጵያን ወደ ዘመናዊ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ንጉስ እንደሆኑም የታሪክ መዝገቦች ያስረዳሉ። በዛን ዘመን የወፍጮ፣የስልክ፣የፓስታ፣የውሃ ቧንቧ፣ ቀይመስቀል፣ ሆስፒታል፣ ባቡር፣ባንክ፣ሆቴልና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጉ ንጉስና የሀገር መሪ ነበሩ። ይህንን ታሪካቸውን ለመዘከርም በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች በአሉ ወደሚከበርበት ስፍራ ሲጓዙም በዛን ወቅት የነበሩ አለባበሶችን፣ጌጦችንና የጀግንነት ማሳያ የሆኑትን ጋሻና ጦር በማያዝ ነው። ትላንት አያቶቻችንና አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ዛሬ

በህገወጥ መንገድ አስቸኳይ አዋጁ በጸደቀበት ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ መከሰቱ ተሰማ።

በአምቦ፣ በነጆ፣ በወሊሶና በአዲስ አበባ አስቸኳይ አዋጁን በመጣስ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ለአድዋ በዓል አደባባይ የወጡ ወጣቶች በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ የሚያወግዙ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ እንደነበር በቪዲዮ ተደግፎ ከመጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኪሎ በሚገኘው የፓርላማ ህንጻ በተሰበሰቡበት ሰዓት ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይ የአድዋ 122ኛ ዓመት መታሰቢያ በድምቀት ይከበራል። ከፓርላማው የተሰበሰቡት ተወካዮች በአስቸኳይ አዋጁ መጽድቅ ላይ ድምጽ ሲሰጡ; ከሚኒሊክ አደባባይ የተሰበሰቡት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ደግሞ አዋጁ የሚከለክለውን ተቃውሞ የማሰማትን ገደብ ጥሰው በአገዛዙ ላይ የተቃውሞ ድምጽ እያሰሙ ነበር። ከፓርላማው ድምጽ ተገልብጦ ቁጥር ተጨምሮና የድምጽ ቆጠራው አወዛጋቢ በአሆነ መልኩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲጸድቅ በአድዋ በዓል መታሰቢያ የታደሙና አገዛዙ ላይ ጠንካራ የተቃውሞ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉት ወጣቶች በቤተመንግስት ደጃፍ በማለፍ ላይ ነበሩ። በመጨረሻም አዋጁ መጽደቁ ተነገረ። የአዲስ አበባ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴሊርሰን በመጭው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ተገለጸ።

ሬክስ ቴሊርሰን በመጭው ረቡዕ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት በሃገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ ዙሪያ ከሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ትብሏል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሬክ ቴሊርሰን ወደ አፍሪካ የሚያቀኑት ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዚሁም ጉዟቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ቻድን፣ጅቡቲን፣ኬንያንና ናይጄሪያን ይጎበኛሉ ነው የተባለው። በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናትና ከአፍሪካ ሕብረት የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩም ታውቋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክ ቴለርሰን ወደ ኢትዮጵያ ማምራታቸው ዩናይትድ ስቴትስ የሃገሪቱ ችግር ያሳሰባት መሆኑን ያመለክታል ተብሏል። አሜሪካ የኢትዮጵያው አገዛዝ የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደማትቀበለው ብትገልጽም ፓርላማው ግን እንዳጸደቀው ለማወቅ ተችሏል። በአዲስ አበባ

የኢትዮጵያው ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጽደቁን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ።

No automatic alt text available.አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳለው ፓርላማው የሕዝቡን ድምጽ ከመስማት ይልቅ አፈናን ለማራመድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጽደቁ እጅግ የሚያበሳጭና ሃላፊነት የጎደለው ነው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሐፊ ሳሊል ሸቲ የኢትዮጵያ ፓርላማ በዚህ አስቸጋሪና የፖለቲካ ቀውስ በተፈጠረበት ሁኔታ የሕዝቡን ድምጽ ሊሰማ ይገባ ነበር ብለዋል። አሁን የሚያስፈልገው የሕዝቡን ሰብአዊ መብት ማክበር እንጂ አፈና የሚያመጣው መፍትሄ የለምም ነው ያሉት። እንደ ዋና ጸሃፊው ሳሊል ሻቲ ገለጻ በኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ተደንግገው በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተፈጽመዋል። እነዚህም ግድያዎች ጅምላ እስሮችና በሃይል መፈናቀልን እንደሚጨምርም ነው የገለጹት። እናም አሁን ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ማጽደቅ ተመሳሳይ ሕገወጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት የሌላቸውን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እንዲፈጸሙ መስማማት ነው ባይ ናቸው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊዋ ፓርላማው የሕዝቡን ድምጽ ከመስማት ይልቅ አፈናን መምረጡ እጅግ የሚያበሳጭና ሃላፊነት የጎደለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት አዋጁን እንዳያጸድቁ በሕዝብም ሆነ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል በኩል ቢጠየቁም በጉዳዩ ላይ 88ቱ አባላት ቢቃወሙም 346ቱ የድጋፍ ድምጽ ሰጥተዋል። ይህ ቁጥር ግን ከፓርላማው ጠቅላላ አባላት 2/3ኛ ድምጽ እንዳልሆነ ይታወቃል። ስለሆነም ፓርላማው ቁጥሩን አስተካክሎ የ395 ድምጽ ድጋፍ ተገኝቷል ማለቱ ሁኔታውን አወዛጋቢ አድርጎታል።

Ethiopia: Regime announces Parliament voted in favor of martial law; vote tally appears controversial. by Engidu Woldie

ESAT News (March 2, 2018)
Media controlled by the regime in Ethiopia have reported that the Parliament has passed the six-month state of emergency declared by the Council of Ministers on February 16, 2018.
There are, however, uncertain and different figures reported as to how many of the members of Parliament voted in favor of passing the martial law. Even the official Facebook of the House People’s Representatives had edited news of the passing of the state of emergency three times. The number of those who voted in favor was originally reported as being 346, which falls short of the required two-third of the total in the 547 seat Parliament. The tally was changed to 395 few minutes later.

የሞት አዋጁ ጸድቋል Mesay Mekonnen

Image may contain: 1 person, standingብዙዎቻችን ትንሽ ዕድል ሰጥተናቸዋል። ምናልባት የዘመናት ሃጢያታቸውን በዚህች ቆራጥ ውሳኔያቸው ሊያካክሱ ይችሉ ይሆን በሚል ግመል በመርፌ ቀዳዳ የመሽሎክ ዓይነት የሚመስል ተስፋ ያሳደርን ጥቂቶች አይደለንም። የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር በጉልበት ለመቀጠል በሚል ያወጣውን የሞት አዋጅ ፓርላማው ተባባሪ እንዳይሆን ጥረቶች ተደርገዋል። በአብዛኛው የፓርላማ አባላት ዘንድ በስልክና በአካል በመድረስ አዋጁን በማጽደቅ የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ በሚገባ ተነግሯቸዋል። የድርጅት ማዕከላዊነትን በመስበር አዋጁን ውድቅ እንዲያደርጉት ተጎትጉተዋል። ተለምነዋል:: ቢቃወሙትም ባይቃወሙትም የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረውን የነጻነት ተጋድሎ እንደማያቆመውም በሚገባ እንዲያውቁት ተደርገዋል:: ለራሳቸው መልካም ስም ሲሉ ብቻ አዋጁን አሽቀንጥረው እንዲጥሉት ተመክረዋል::
ምንም እንኳን ከህዝብ ግፊት በተጓዳኝ የትግራይ ጀነራሎችና ደህንነቶች ማስፈራሪያ እንደነበረ ቢታወቅም በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ለየትኛውም የአገዛዙ ቁንጥጫ የማይንበረከኩ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት በግሌ ውስጤ ነበር። በመጨረሻ ግን የተጠበቀው ሆኗል። ፓርላማው ታሪክ መስራት የማይችል እንደሆነ ዳግም አስመስክሯል። የፓርላማ አባላቱ እየሰመጠ ካለው መርከብ ዘለው እንዲወርዱ የተሰጣቸውን የመጨረሻ ዕድል አልተጠቀሙበትም። አብረው መስመጥን መርጠዋል።

Thursday, March 1, 2018

በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መመልከታቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይ ተናገሩ

(ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በቅርቡ ከእስር ቤት ተፈተው ኖርዌይ ገቡ በሁዋላ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በእስር ቤት ውስጥ ብልታቸው የተኮላሸ፣ በድብደባ ብዛት መራመድ የማይችሉ እንዲሁም በደረሰባቸው ጥቃት ራሳቸውን ስተው ያበዱ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል። በአርበኞች ግንቦት7 አባልነት ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው አበበ ካሴ ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ብልቱ ላይ በደረሰበት ድብደባ በደም ተጨማልቆ መምጣቱን ማየታቸውን የተናገሩት አቶ ኦኬሎ፣ በእርሳቸውና አብረዋቸው በታሰሩ ሌሎች ጓደኞቻቸውም ላይ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው፣ በተለይ ቃሊቲ በነበሩበት ወቅት በደረሰባቸው ድብደባ የተጎዳውን አካላቸውን ኖርዌይ ውስጥ ለመታከም እየሞከሩ መሆኑ ገልጸዋል። ከደቡብ ሱዳን በአገዛዙ ደህንነቶች ታፍነው ከተወሰዱት በሁዋላ የኖርዌይ መንግስት የእርሳቸውን ደህንነት ለማወቅ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ የእስር ቤቱ ባለስልጣናት “ የለም” የሚል መልስ መስጠታቸውን የገለጹት አቶ ኦኬሎ፣ ይሁን እንጅ በድብቅ አሾልከው የጻፉት አጭር ማስታወሻ የኖርዌይ ኢምባሲ ሰራተኞች እጅ በመግባቱ አድራሻቸው ሊታወቅ መቻሉን ተናግረዋል። የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት የአገዛዙ ባለስልጣናት በህዝብ ላይ የሚፈጽሙት ጭፍጨፋ በማንሳት በእስር ቤት ውስጥ ተቃውሞ ያሰሙ እንደነበር የገለጹት አቶ ኦኬሎ ፣ ቂሊንጦ ውስጥ ድብደባ እንደተፈጸመባቸውና ጨለማ ቤት እንዲገቡ መደረጉን አውስተዋል። ከእርሳቸው ጋር ከታሰሩት መካከል ያልተፈቱ ሰዎች መኖራቸውንም አቶ ኦኬሎ ተናግረዋል። አቶ ኦኬሎ እስር ቤት በነበሩበት ጊዜም ሆነ ከእስር ቤት ከወጡ በሁዋላ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የኖርዌይ መንግስትና በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል። ከአቶ ኦኬሎ አኳይ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉውን በድረገጻችን ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ክፍል በኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል

(ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ኮማንድ ፖስት የተባለው ቡድን ተቃውሞ በነበረባቸው የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል። ትናንት የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ በኮማንድ ፖስት አባላት ከታሰሩ በሁዋላ ዛሬ ደግሞ ምክትል ከንቲባው ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። ሁለቱም ባለስልጣናት ቄሮ እየተባለ ከሚጠራው የወጣቶች ስብስብ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል መያዛቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የፓርላማ አባላት በነገው እለት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። አዋጁ ተግባራዊ ከሆነ ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን፣ ፓርላማው ከዕረፍት ተጠርቶ ድምጽ እንዲሰጥበት ይደረጋል። የፓርላማ አባላቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንያዳያጸድቁ ግፊት እየተደረገባቸው ነው በማለት ራሱን የኮማንድ ፖስት ሰክሬታሪያት ብሎ የሚጠራው ቡድን ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር። በሌላ በኩል ግን የኮማንድ ፖስት አባላትና የደህንነት ሰዎች ለፓርላማ አባላቱ ስልክ እየደወሉ አዋጁን እንዲያጸድቁት እያስጠነቀቁ ነው። በኢህአዴግ ድርጅቶች አኳያ እስካሁን ያለው አቋም በግልጽ አልታወቀም። አዋጁ በብዛት የኦሮምያና አማራ ክልሎችን ኢላማ አድርጎ የወጣ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከጸደቀ በኦሮምያ ያለውን ተቃውሞ ያባብሰዋል ተብሎ ተፈርቷል። በአዋጁ መሰረት ጸጥታን አስመልክቶ የክልል ባለስልጣናት መግለጫ መስጠት አይችሉም። ይሁን እንጅ የኦሮምያ ክልል የህዝብ ግንኙት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በነቀምቴ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ በመጻፍ መረጃ በመስጠት የመጀመሪው ባለስልጣን ሆነዋል።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በኢትዮጵያ የታወጀው ወታደሩ ስልጣን እንዳይወስድ ለመከላከል ነው ሲሉ የቀድሞዎቹ የህወሃት መሪዎች ለአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ጥያቄ ያቀረቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተቀባይነት አለማግኘታቸውንም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል። ከሳምንታተ በፊት በዩ ኤስ አሜሪካ በዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ላይ የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊታወጅ ነው የሚለውን ተባራሪ ወሬ አስተባብለው ፣የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንደማይታወጅ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣናት ማረጋገጫ ሰተው ነበር። ሆኖም ርሳቸው ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለሱ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በኢትዮጵያ ይፋ ሆነ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተርወርቅነህ ገበየሁ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ አዋጁ የታወጀበት አሳማኝ የሆነ ምክንያት ስላለ መጥቼ ላስረዳ ሲሉ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውንም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ይገልጻሉ። ሆኖም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ወደ አሜሪካ መጓዝ አስፈላጊነት አልተቀበሉትም። በአፍሪካ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ የተጓዙ የአሜሪካ ባለስልጣናት ስላሉ እነርሱ በኢትዮጵያ በኩል ሊያልፉ ስለሚችሉ አሳማኙን ምክንያት ለነርሱ

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የሙስና ደረጃ የሚያሳየውን አመታዊ ሪፓርት ይፋ አደረገ።

በሕውሃት/ኢህአዴግ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በሙስና ከተዘፈቁት ሃገራት አንዱ መሆኑን ሪፓርቱ ገልጿል። የሚዲያ ነፃነት አለመኖርና መንግስታዊ ያልሆኑ ሲቪክ አደረጃጀቶች አለመጠናከራቸው ሙሰኝነት እንዲባባስ አስተዋፅኦ አበርክቷል። መቀመጫውን ጀርመን በርሊን ከተማ ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየአመቱ የሃገራትን የሙስና ደረጃ በማውጣት ይታወቃል። ይህ ከመቶ በላይ ቅርንጫፎችን በመላው አለም በማቋቋም የአገራትን የሙስና ኢንዴክስ የሚያወጣው ተቋም ሰሞኑን የ2017 ዓመታዊ ሪፓርቱን ይፋ አድርጓል። ሪፓርቱ እንዳመላከተውም በአለም አቀፍ ደረጃ እየተመዘገበ ያለው የሙስና ሁኔታ እየተባባሰ ሔዷል። በተለይም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ ባሉት ስድስት አመታት ሃገራት ሙስናን ለመዋጋት ያደረጉት ጥረት አነስተኛ መሆኑን ሪፓርቱ ገልጿል። በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት መሰረት የፕሬስ ነፃነት እና ጠንካራ መንግስታዊ ያልሆኑ አደረጃጀቶች የሌሉባቸው ሃገራት የሙስና ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው። የነፃ ሚዲያ መኖር ከዲሞክራሲ ግንባታ ጋር አዎንታዊ ቁርኝት እንዳለው የገለፀው ይህ ሪፓርት ፣

TPLF officials told U.S. delegates state of emergency was decreed to “prevent a military takeover”: diplomatic sources

A delegate from the United States was told by TPLF officials that the state of emergency was necessary to “prevent a takeover of power by the military,” according to ESAT’s diplomatic sources.
Workneh Gebeyehu at the Atlantic Council, Washington, DC on February 15, 2018

ከፀፀት ለመዳን ነገ ”አይሆንም“ ድምጽ መስጠት (Tadesse Biru Kersmo)

ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርላማ አባል መሆን እንደ አሁን ሰቆቃ የሆነበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። የፓርላማ አባላት ድምጽ ሲሰጡ ”የመረጣቸውን ሕዝብ“ እና ህሊናቸውን አዳምጠው ሳይሆን “ጠርናፊያቸው” ባዘዘው መሠረት መሆኑ መቸም ቢሆን ምቾች የሚሰጥ ነገር ባይሆንም ነገ እንደምናየው አሸማቃቂ ጉዳይ አልነበረም። “በጠርናፊ ትዕዛዝ” ድምጽ መስጠት ነገ በዚህ ሰዓት በብዙዎች ህሊና ውስጥ የሚያደርሰውን መሸማቀቅ ያህል ያደርስ ነበር ብዬ አላስብም።