Thursday, February 4, 2016

በአዋሳ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህል አዳራሽ ክፍለከተማ አዳሪ ቀበሌ ልዩ ስሙ አድማስ መንደር በተባለ ቦታ ላይ በ30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት ጨንቅላቱ አካባቢ በፖሊስ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ የአካባቢው ህዝብም ቁጣውን ሲገልጽ አርፍዷል።


ልመንህ አበበ የተባለው የአካባቢው ነዋሪ ተልእኮ ትውልድ የሚባል የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ጠባቂ ጋር አለመግባባት መፍጠሩን ተከትሎ፣ ለግልግል መሃል የገባው ፖሊስ በወጣቱ ጭንቅላት ላይ በመተኮስ እዛው ላይ ገድሎታል። ፖሊሱ ተባርቆብኝ ነው ቢልም፣ ህዝቡ ግን ሆን ብሎ ነው የገደለው በማለት አስከሬን አይነሳም በማለት ተቃውሞውን ሲገልጽ ከቆዬ በሁዋላ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከግማሽ ሰአት በሁዋላ ህዝቡን በመደብደብ አስከሬኑን ወስደውታል።
የህዝቡ ቁጣ ከፍተኛ መሆኑን ያዩ ፖሊሶች ገዳዩን እና በአካባቢው ቀድመው የደረሱ ፖሊሶችን ይዘው መሄዳቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment