Wednesday, May 31, 2017

ከ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009)
በመላው ኢትዮጵያ ረቡዕ መሰጠት ከጀመረው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ።
ብሄራዊ ፈተናው ተሰርቆ ሊሰራጭ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ለአገልግሎቱ መቋረጥ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኳርትዝ አፍሪካ የተሰኘ መጽሄት የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ረቡዕ ዘግቧል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ችግሩ ረቡዕ ድረስ የዘለቀ መሆኑን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ለ12 ሰዓታት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ረቡዕ በከፊል መቀጠሉ ቢነገርም፣ ችግሩ በበርካታ አካባቢዎች ዕልባት አለማግኘቱን መጽሄቱ በዘገባው አስፍሯል።
የትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያን ያልሰጡ ሲሆን፣ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናው ከግንቦት 23 እስከ ሰኔ 1 ፥ 2009 አም እንደሚቆይ ታውቋል።
ባለፈው አመት ተመሳሳይ የብሄራዊ ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንዳለ የብሄራዊ ፈተናው በማህበራዊ ድረገጾች ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።
የብሄራዊ ፈተናው መሰረቅን ተከትሎም የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው በድጋሚ እንዲሰጥ አድርጎ የጊዜ ሰሌዳው ተራዝሞ እንደነበር አይዘነጋም።
ይሁንና ማክሰኞ ምሽት አገልግሎቱ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ከፈተናው መሰጠት ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽን አልሰጠም።
በአለም አቀፍ ደረጃ መጠነኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ያላት ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ ተቃውሞዎች በሚነሱ ጊዜ አገልግሎቱን ስታቋርጥ መቆየቷን ካርትዝ አፍሪካ የተሰኘው መጽሄት በዘገባው አመልክቷል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ነጻነት እንዲኖራቸው ፕሮፌሰር አድማሱ ጸጋዬ ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009)
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ስርዓት ነጻነት እንዲኖረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር አድማጹ ጸጋዬ ጥሪ አቀረቡ።
የመንግስት የፋይናንስ ህግ ማዕቀፎችም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፋፋት እንቅፋት መሆናቸውን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጻቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ዩኒቨርስቲው በራሱ እቅድ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት በሚያከናውናቸው ፕሮግራሞች የሚሰበሰበው የውስጥ ገቢ ቢኖረውም የመንግስት የፋይናንስ ስርዓት ግን ዩኒቨርስቲው የሚያመነጨውን የውስጥ ገቢ እንዲጠቀም እንደማይፈቅድ ፕሬዚደንቱ የምክር ቤቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዩኒቨርስቲው ጉብኝት ባካሄደ ጊዜ አስረድተዋል።

ለተረጂዎች ሲሰጥ የነበረ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ከሰኔ ወር ጀምሮ ሊያልቅ እንደሚችል ተመድ አሳሰበ

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀጣዩ ሰኔ ወር ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።
የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪው የሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን የእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን ድርጅቱ የድርቁን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መንግስት ባለፈው ወር ባወጡት አዲስ የተረጂዎች ቁጥር 5.6 ሚሊዮን የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 7.7 ሚሊዮን መድረሱ የሚታወስ ነው።
ይሁንና ድርቁን ለመከላከል እና ለተረጂዎች ድጋፍ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት የተጠበቀውን ያህል ውጤት ባለማምጣቱ ችግሩ እየተባባሰ ሊሄድ መቻሉ ታውቋል። የምግብ አቅርቦቱ እየተጠናቀቀ መምጣት 7.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ተረጂዎች ከሰኔ ወር ጀምሮ የምግብ አቅርቦት ላይኖር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መንግስት የድርቁን አደጋ ለመታደግ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ከወራት በፊት ቢገልጹም እየተገኘ ያለው ድጋፍ ግን እጅግ አነስተኛ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

የመን ወደ መፈራረስ እያመራች መሆኑን ተመድ ገለጸ



ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2009)
በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የመን ሙሉ ለሙሉ ወደ መፈራረስ እያመራች መሆኗን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
ሃገሪቱ ያጋጠማት የረሃብ አደጋና ዕልባት ማግኘት ያልቻለው የዕርስ በርስ ጦርነት የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና የመንግስታዊ ተቋማት መፈራረስ አደጋ እንዲጋረጥባቸው ማድረጉን የድርጅቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ሃላፊዎች ይፋ ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የየመን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሪፖርተን ያቀረቡት የማስተባሪያ ቢሮው ሃላፊ ስቴፋን ኦብሪየን በየመን ቀጥሎ ባለው የዕርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ከ 17 ሚሊዮን የሚበልጡ የሃገሪቱ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አስታውቀዋል።
ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠው ከሚገኙት መካከል ወደ 7 ሚሊዮን የሚሆኑት ለረሃብ አንድ ደረጃ በቀረው አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ሃላፊው ገልጸዋል።

Monday, May 29, 2017

በሳውዲ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አልታወቀም

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009)
በሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ከ700 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አለመታወቁ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ ያለፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 40ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ከሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመውጫ ቪዛ አግኝተዋል ቢልም፣ ሌሎች ከ700 ሺ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ለማወቅ ተችሏል።

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እገታ የተፈጸመበትን አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ማስለቀቁን ሰኞ አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009)
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እገታ የተፈጸመበትን አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ከእገታ ማስለቀቁን ሰኞ አስታወቀ። ስሙ ይፋ ባልተደረገው ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ላይ እገታውን ፈጽመዋል የተባሉ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ኒውስ 24 የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።
ሶስቱ ግለሰቦች ኢትዮጵያዊ ነጋዴውን ከጆሃንስበርግ ከተማ በቅርቡ ርቀት ላይ ከሚገኘው የኦ አር ታምቦ (O R Tambo) አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የንግድ ስምምነት እንፈጽማለን ብለው አታለው እንደወሰዱት ተመልክቷል።
ራሳቸውን ነጋዴ መስለው የቀረቡት ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊውን ነጋዴ ከአየር ማረፊያ ከወሰዱት በኋላ በአንድ መኖሪያ ቤት እጅና አይኑን አስረው እንዳቆዩት ካፒቴን ሎንጌሉ ድላሚኒ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን በመስራችነትና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው በትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ ለቀቁ

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009)
በቅርቡ የብድር መጠኑ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን በመስራችነትና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ለ10 አመታት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው በትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ መልቀቃቸው ታውቋል።
ሃላፊው ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ቢረጋገጥም ምክንያቱ ግን በኮርፖሬሽኑም ሆነ በዶ/ር ጌታቸው አልተገለጸም። መንግስታዊ ተቋም በሃገሪቱ ሰፊ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ለማካሄድ ባቀደ ጊዜ ዶ/ር ጌታቸው ፕሮጄክቶችን በመቆጣጠርና በማስተባበር ይሰሩ እንደነበር ታውቋል።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ስራውን በአዲስ መልክ ከጀመረ ከ 10 አመት በፊት ጀምሮ ፕሮጄክቶችን ለማካሄድ ከተለያዩ አካላት የወሰደው የብድር መጠን ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሶ እንደነበር ኮርፖሬሽኑ ለፓርላማ ይፋ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።

በህይወት መኖራቸው ያልታወቁት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ልዑል ገብረማሪያም ከስራቸው እንዲሰናበቱ ተወሰነ

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009)
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ያልታወቀ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ልዑል ገብረማሪያም ከስራቸው እንዲሰናበቱ ወሰነ።
ለበርካታ አመታት በፍትህ ስርዓት ውስጥ ያገለገሉት አቶ ልዑል ላለፉት ስምንት ወራት ውስጥ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ የመስሪያ ቤታቸው ባልደርቦች ዳኛው ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቁ ለፓርላማው የቀረበን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት አቶ ልዑል ገብረማሪያም በህመም ምክንያት በስራ ገበታቸው መገኘት አልቻሉም ቢባልም ጉዳዩን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አመልክቷል።

ለኢትዮጵያ ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሽልማት ተበረከተላቸው

ኢሳት (ግንቦት 21: 2009)
ለኢትዮጵያ ሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ 8 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን መቀመጫውን በዚሁ በአሜሪካ ሃገር ባደረገ ተቋም ሽልማት ተበረከተላቸው።
ማህበረ ጊወራን ዘረ ኢትዮጵያ ወይም /ሲድ/ የተባለው ይኸው ተቋም ላለፉት 25 አመታት ለሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽዖ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን በመሸለም ይታወቃል።
በሜሪላንድ ግዛት ኮሌጅ ፓርክ ዕሁድ ግንቦት 20/2019 ከተሸለሙት ስምንቱ ታዋቂ ኢትዮጵያውን መካከል አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን እና የትዝታው ንጉስ መሃመድ አህመድ ይገኙበታል።
ሌሎች ተሸላሚዎች ደግሞ ዶ/ር አምባቸው ወሮታ፣ ቻንስለር ለምን ሲሳይ፣ ዶ/ር ዛኪ ሸሪፍ፣ አቶ ቴድ አለማየሁ፣ አባ ከፍያለው አበራ፣ እና ባለፈው አመት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ማይገነት ሺፈራው ናቸው።

Friday, May 26, 2017

Ethiopians in Saudi remain in limbo as Kingdom’s deadline for amnesty approaches

ESAT News (May 26, 2017)
Ethiopians who spoke to ESAT from Saudi Arabia say they are not getting the support from their government, when they needed it most, as the deadline for the Kingdom’s amnesty to undocumented immigrants to leave the country expires at the end of June.
A woman whose name is withheld told ESAT on the phone that governments of other countries are providing their nationals free tickets while the Ethiopian Airlines has doubled its air fare.
“They increase the air fares from 800 riyal to 1700. The Ethiopian government says we can import our cargo free of tax but friends who are in Ethiopia already say they are asked to pay taxes in thousands of dollars,”
“We ask Ethiopians to pray for us,” the Ethiopian woman said from Riyad.

Air Force officer kill several soldiers in eastern Ethiopia

ESAT News (May 26, 2017)
An engineer with the Ethiopian Air Force killed at least ten soldiers at an army meeting in Gode town of the Somali region of Ethiopia, according to ESAT’S sources.
The Air Force officer is said to have been relocated to Gode and serve as a regular soldier as a demotion and punishment for being a supporter of the anti- government protests in the Oromo and Amhara regions a year ago.

ከኢሬቻ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ ግጭት አነሳስተዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ክስ ቀረበባቸው

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2009)
ከሳሽ አቃቤ ህግ ባለፈው አመት ከኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ጋር በተያያዘ ተከስቶ የነበረውን ግጭት አነሳስተዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በሽብር ወንጀል መክሰሱ ታውቋል።
ተከሳሾቹ ተፋ መልካ እና ከድር በዳሱ የተባሉ ግለሰቦች ሲሆን፣ በበዓሉ አከባበር ወቅት ከሃገር ሽማግሌዎች ድምፅ ማጉያን በመቀማትና ሁከት በማነሳሳት ለ55 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል ተብለዋል። ከሳሽ አቃቤ ህግ ሁለቱን ተከሳሾች የሽብር ወንጀል ድርጊት መፈጸም የሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ታውቋል።
ሁለቱ ተከሳሾች ከኢሬቻ በዓል አከባባር ጋር ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ምክንያት ናቸው ተብሎ ክስ ሲመሰረትባቸው የመጀመሪያዎቹ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በበዓሉ አከባበር ወቅት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሲባል በስፍራው የነበሩ የጸጥታ ሃይሎች ዕርምጃ ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት መሆኑን የበዓሉ ታዳሚዎች በወቅቱ ሲገልጹ ቆይቷል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ የአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት በየነ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2009)
የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰሞኑን የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ የአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣር አርብ ሰጠ።
ጋዜጠኛው የተላለፈበት የ 18 ወር እስራት ከእስር ቆይታው ጋር የሚቀረረብ በመሆኑ ተከሳሹ አመክሮ ታስቦለት ከእስር  ይወጣል የሚል ግምት መኖሩን የህግ አካላት ገልጸዋል። ይሁንና ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስከ አርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ ከእስር አለመለቀቁን ለመረዳት ተችሏል። ከሳሽ አቃቤ ህግ ተከሻሹ ህገመንግስቱን ለመናድ የሚያስችሉ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እንዲባባሱ አስተዋጽዖ አድርጓል ሲል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
ጋዜጠኛ ጌታቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ በጋዜጠኛ አበበ ገላው ለቀረበባቸው ተቃውሞ ድጋፍ ሰጥቷል የሚል ክስ ቀርቦበታል።

Ethiopia: Journalist gets a year and half in jail over Facebook comments

ESAT News (May 26, 2017)
A newspaper editor in Ethiopia got a year and half in jail over Facebook comments he made five years ago. Journalist Getachew Shiferaw is the second person in a week to be sentenced by an Ethiopian court that is highly criticized for being an instrument of suppression for a regime known for its dismal human rights records.
Getachew Shiferaw, the former editor of Negere Ethiopia, has already served a year and half in jail since his arrest and solitary confinement in December 2015. He is expected to be free as per the court’s ruling.

Thursday, May 25, 2017

የሰማያዩ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ታስፋየ ፌስቡክ ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች ወንጀለኛ ተብሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የ6 አመታት ከ3 ወር እስር ተፈርዶበታል

Bildergebnis für yonatan tesfayeግንቦት ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዩ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ታስፋየ ፌስቡክ ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች ወንጀለኛ ተብሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የ6 አመታት ከ3 ወር እስር ተፈርዶበታል። ዮናታን በሰላማዊ ትግል ፍጹም የሚያምን ወጣት እንደነበር የሚናገሩት የቅርብ ጓደኞቹ፣ እንደሱ የፖለቲካ እምነት ቢሆን ኖሮ እንኳንስ እስር ቤት ሊያስገባው፣ ሰላማዊነቱ፣ የሰላም ተሸላሚ ባስደረገው ነበር በማለት፣ የቀረበበትን ውንጀለና የተሰጠውን ፍርድ ኮንነዋል። በእድሜ የገፉ እና በእርሱ የሚተዳደሩ እናቱን ትቶ ለእስር የተዳረገው ዮናታን፣ የተለያዩ ሰብአዊነት ያላቸውን ሰራዎች በመስራትም ይታወቃል። ዮናታን

በሶማሊ ክልል ለተፈጸመው ከፍተኛ እልቂት ተጠያቂ የሆነውና ከሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር ከፍተኛ የሙስና ትስስር እንዳለው የሚነገርለት ጄ/ል አብረሃ ወይም በቅጽል ስሙ ኳርተር፣ በሌላው በሙስና በተዘፈቀው ጄኔራል ማሹ በየነ መተካቱ ታውቋል

ግንቦት ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ወኪላችን እንደገለጸው በሶማሊ ክልል ለተፈጸመው ከፍተኛ እልቂት ተጠያቂ የሆነውና ከሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር ከፍተኛ የሙስና ትስስር እንዳለው የሚነገርለት ጄ/ል አብረሃ ወይም በቅጽል ስሙ ኳርተር፣ በሌላው በሙስና በተዘፈቀው ጄኔራል ማሹ በየነ መተካቱ ታውቋል። ጄ/ል አብርሃ ከምስራቅ እዝ ሃላፊነት ተነስቶ የመከላከያ የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ሆኖ ተሹሟል። ጄ/ል ሳሞራ የምስራቅ እዝ ሃላፊነቱን ሲለቅ ስልጣኑን የተረከበው ጄ/ል አብርሃ፣ እዙን ለረጅም ጊዜ በመምራት ይታወቃል። በአዲስ አበባ ዘመናዊ ህንጻዎችን እና የንግድ ድርጅቶችን መገንባቱን ኢሳት የፎቶ ግራፍ ማስረጃዎችን አያይዞ መዘገቡ ይታወቃል። እርሱን የተካው ሜጀር ጄ/ል ማሾ ቀደም ብሎ የጅጅጋ ክፍለ ጦር ወታዳራዊ ኮሚሳር ሆኖ በሰራበት ወቅት፣ ሃጎስ የተባለውን ወንድሙን ከምንም አንስቶ ሚሊየነር

Wednesday, May 24, 2017

በኢትዮጵያ የተከሰተው የምግብ ዕጥረት በቅርቡ ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ሊለወጥ ይችላል ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ የተከሰተው የምግብ ዕጥረት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ሊለወጥ እንደሚችል መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገው የቅድመ ረሃብ ማስጠንቀቂያ ተቋም ረቡዕ አሳሰበ።
በአሁኑ ወቅት 7.7 ሚሊዮን የደረሰው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ተረጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም አለም አቀፍ ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ 5.6 ሚሊዮን የነበረው የተረጂዎች ቁጥር 7.7 ሚሊዮን መድረሱን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።
አለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ያለው የድርቅ አደጋ ለሰዎች ህይወት ስጋት እየሆነ መምጣቱን ሲገልፁ ቆይተዋል።

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በተመሰረበት የወንጀለኛ ክስ የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈበት

ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2009)
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእስር ላይ በሚገኘው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ በተመሰረበት የወንጀለኛ ክስ ረቡዕ የጥፋተኝነት ብይን አስተላለፈ። 
የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው በመጀመሪያ ዙር የሽብተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶ የቆየ ቢሆን፣ ከሳሽ አቃቤ ህግ ክሱን ወደ መደበኛ ወንጀል ክስ ዝቅ ማደረጉ ታውቋል። ከሳሽ አቃቤ ህግ ጋዜጠኛው በአሜሪካ ሃገር የሚገኘው ጋዜጠኛ አበባ ገላው ከአምስት አመት በፊት በሟች ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ ተቃውሞ በገለጸ ጊዜ ድጋፍን በፌስ ቡክ አስተላልፏል ሲል በክሱ ማመልከቱን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል።
የፌዴራል ከሳሽ አቃቤ ህግ በመጀመሪያ ዙር የመሰረተውን የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ወደ መደበኛ ወንጀል ክስ በመቀየር ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ መቀመጫውን በውጭ ካደረገና በሽብተኛ ወንጀል ከተከሰሰ አካል ጋር ግንኙነት (ወይም መልዕክት ተለዋውጧል) ሲል ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡ ታውቋል።
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ረቡዕ ጋዜጠኛውን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ከነገ በስቲያ አርብ የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ የተላለፈውን ብይን የፍትህ እጦትን የሚያሳይ ድርጊት ነው አለ

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ረቡዕ በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ ያስተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን በኢትዮጵያ ፍትህ እጦትን የሚያሳይ ድርጊት ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
“ጋዜጠኛው ከህዝብ በገሃድ የሚያውቀውን መረጃ ከመግለጽ ውጭ ያደረገው ነገር የለም” ሲሉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የምስራቅና የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ የሆኑት ሙቶኒ ዋንዬኬ ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ በጋዜጠኛው ላይ የሚያስተላልፈው ፍርድም ተቀባይነት የሌለውና ጭካኔ የተሞላበት ነው በማለት ሃላፊው ተናግረዋል።
“መንግስት ትችት የሚቀርብበትን የፍትህ ስርዓት እንደሚያሻሽል በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም እየሆነ ያለው ነገር ግን የፍትህ ሁኔታ እየተጓደለ መምጣት ነው” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት በዮናታን ተስፋዬ ያስተላለፈውን ተመሳሳይ የጥፋተኝነት ብይን ተከትሎ ስጋቱን መገልፁ ይታወሳል።

Monday, May 22, 2017

በጄኔቭ ጉባዔ አዳራሽ በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ ተቃውሞ አቀረበ

ኢሳት (ግንቦት 14 ፥ 2009)
የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ምርጫን በተመለከከተ በጄኔቭ በሚካሄደው ጉባዔ አዳራሽ በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ተቃውሞ ቀረበ።
ማክሰኞ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ጋዜጠኞች ከሚቀመጥበት ሰገነት የተሰማውን ተቃውሞ በአዳራሽ የነበሩ ጋዜጠኛ ወዲያውኑ በማህበራዊ መድረክ ያሰራጩት ሲሆን፣ ተቃውሞውን ያሰማው ኢትዮጵያዊ አቶ ዘላለም ተሰማ ከአዳራሹ እንዲወጣ ተደርጓል።
“ቴዎድሮስ ለአለም ጤና ድርጅት አይገባም አፍሪካውያን ደጋግማችሁ አስቡ” በማለት በጸጥታ ሃይላት በተያዘበት ወቅት ጭምር ተቃውሞን የቀጠለው አቶ ዘላለም ተሰማ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃንሞ እንዳይመረጡ ኢትዮጵያውያን የጥረቱ ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዳይመረጡ በመቃወም ከአዳራሹ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን፣ የመንግስት ደጋፊዎች በተመሳሳይ ሰልፍ ጠርተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ ወደ ናይጀሪያ ከሚጓዙ መንገደኞች ህገወጥ ተጨማሪ ክፍያን ሲቀበል እንደነበር ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 14 ፥ 2009)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ናይጀሪያ ከሚጓዙ መንገደኞች በአንድ ተጓዥ እስከ 150 ዶላር የሚደርስ ህጋዊ ያልሆነ ተጨማሪ ክፍያን ሲቀበል ቆይቷል ሲል የናይጀሪያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣንን ቅሬታ አቀረበ።
የባለስልጣኑ ሃላፊ የሆኑት ሳም አድሮግቦዬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናይጀሪያውያን መንገደኞች ተመላሽ የማይሆን የዲፖርቴሽን ክፍያን ለረጅም አመታት ሲሰበሰብ መቆየቱን ለሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ከሌጎስና አካኑ ኢቢያም አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያዎች ተነስተው በአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካዊቷ ጆሃንስበርግ ከተማ የሚያቀኑ መንገደኞች ከ75 እስከ 150 ዶላር የሚደርስ ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጉን ዘኔሽን የተሰኘ ጋዜጣ ሃላፌውን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ቆሼ አደጋ ለተረፉ ዜጎች የገንዘብና መጠለያ ድጋፍ አልተሰጣቸውም ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 14 ፥ 2009)
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ደርሶ ከነበረው አደጋ የተረፉ ሰዎች ቃል የተገባላቸው የገንዘብና መጠለያ ቤት ድጋፍ እስካሁን ድረስ እንዳልተሰጣቸው አስታወቁ። ኮንዶሚኒየም ቤቶች በስጦታ እንደተበረከተላቸው ሲገለፅ ቢቆይም፣ እነርሱ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አሁንም ከመጠለያ መውጣት አልቻሉም። ይሰጣቸው የነበረው ምግብ ከሶስት ወደ ሁለት ዝቅ ብሏል። ተጎጂዎችም ለፖሊስ ሳያሳውቁ መንቀሳቀስ አይችሉም።
ከ130 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው አደጋ ተከትሎ በርካታ መንግስታዊ ተቋማት የግል ባለሃብቶች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎች መልሶ ለማቋቋም ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ለግሰው እንደነበር በወቅቱ ቢገለጽም፣ የተጎጂ ቤተሰቦች በባንክ አካውንታቸው ውስጥ አንዳችም የገባ ገንዘብ አለመኖሩን ተናግረዋል። ገንዘቡ እንደገባላቸው የባንክ አካውንት ክፈቱ ተብለው አካውንት መክፈታቸውንም አስታውሰዋል።

አምስት የአፍሪካ ሃገራት የአለም ጤና ድርጅት አባልነት ክፍያን ባለመፈጸማቸው ቀጣዩን ዋና ዳይሬክተር በመምረጥ በሚካሄደው ልዩ ጉባዔ ድምፅ አይሰጡም ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 14 ፥ 2009)
አምስት የአፍሪካ ሃገራት የአለም ጤና ድርጅት አባልነት ክፍያን ባለመፈጸማቸው ምክንያት ማክሰኞ ድርጅቱ ቀጣዩን ዋና ዳይሬክተር ለመምረጥ በሚካሄደው ልዩ ጉባዔ ድምፅ እንደማይሰጡ ታወቀ።
ከ180 በላይ የሚሆኑ የአለም ጤና ድርጅት አባል ሃገራት ማክሰኞ በጀኔቫ በሚያካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ የመጨረሻ ሶስት እጩ ሆነው ከቀረቡ ተፎካካሪዎች መካከል አንዱን ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አምስት የአፍርካ ሃገራት የድርጅቱን አባላት ክፍያን ባለመፈጸማቸው ምክንያት ድምፅ በመስጠት ሂደት ተሳታፊ እንዳማይሆኑ ስታት ኒውስ የተሰኘ የጤና መጽሄት ከጄኒቭ ዘግቧል። ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ፣ኮሞሮስ፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳዎ፣ እና ሶማሊያ የአባልነት ክፍያው ባለፈጸማቸው ምክንያት በምርጫው ድምፅ የማይሰጡ የአፍሪካ ሃገራት መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል።

Monday, May 15, 2017

Ethiopia request delays on Nile summit

ESAT News (May 15, 2017)
The Nile Council of Presidents summit, which the Ugandan president has called for, was postponed to mid-June rather than 25 May in the Ugandan capital Kampala, after an Ethiopian request, Daily News Egypt reported quoting local media.
Ethiopia said that it needs time to study the Egyptian proposal about the Entebbe Agreement. The proposal is consistent with the international agreements and laws that organise relations between the countries of international rivers, according to the report.

ዶ/ር ቴዎድሮስ የኮሌራ በሽታ እንዳይታወቅ ደብቀዋል ተብለው በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ክስ ቀረበባቸው

ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009)
ኢትዮጵያን በመወከል ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩ ጊዜ በሃገራቸው የተከሰቱ ሶስት የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታዎች ለህዝብ እንዳይታወቅ አድርገዋል የሚል ቅሬታ በአለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ቀረበባቸው። 
የጤና ድርጅቱ አባል ሃገራት የመጨረሻ እጩ ሆነው ከቀረቡ ሶስት ተፎካካሪዎች መካከል አንዱን ለመምረጥ የሳምንት ዕድሜ በቀራቸው ጊዜ ዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የቀረበው ቅሬታ በምርጫው ሂደት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን ሊያሳድርባቸው ይችላል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።
በአሜሪካ በሚገኘው የጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ የኦ ኔል ኢንስቲትዩት ፎር ናሽናል ኤንድ ግሎባል ኸልዝ ሎው ዳይሬተር እና የብሪታኒያው ተፎካካሪ የሆኑት ሎረንስ ጎስተን የአለም ጤና ድርጅት በሃገሩ የበሽታ መከሰትን በደበቀ ተፎካካሪ የሚመራ ከሆነ ተቋሙ ተአማኒነቱን ያጣል የሚል ስጋት ስላደረባቸው ሁኔታውን ይፋ ማድረግ እንደተገደዱ ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባላት ላይ ሊሰጥ የነበረው ብይን ለሁለተኛ ጊዜ ተራዘመ

ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009)
የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባላት ላይ ሲሰጥ የነበረን የመጀመሪያ ዙር ብይን ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመ።
ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ወይም በነጻ ይሰናበቱ የሚል ብይን ሰኞ ያስተላልፋል ተብሎ ቢጠበቅም ለግንቦት መጨረሻ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል። አቃቤ ህግ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ አቀርበዋለሁ ያለው የቪዲዮ ማስረጃን ለፍርድ ቤቱ ባለማቅረቡ ምክንያት ሲጠበቅ የነበረው ብይን ሊሰጥ አለመቻሉን ለፍርድ ቤቱ መግለጹ ታውቋል።

180ሺ የእጅ ኮምፒውተሮች (ታብሌቶች) እንዲገቡ የተካሄደው የግዢ ጨረታ ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009)
መንግስት ለቀጣዩ አመት በሃገሪቱ ለሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ 180ሺ የእጅ ኮምፒውተሮች (ታብሌቶች) እንዲገቡ ያካሄደው የግዢ ጨረታ ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለጸ።
የመንግስት ግዢዎችና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሌኖቮ የተሰኘውን የቻይና ኩባንያ በተለያዩ መንገዶች በመገምገም ለጨረታው ተሳታፊ እንዳይሆን ቢወሰንም የኤጀንሲው የቅሬታ ሰሚ ቦርድ ግን ውሳኒው እንዲቀለበስ ማድረጉ ይታወሳል።
አንድ ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል የተባለው የኮምፒውተሮች ግዢ ከሌሎች አምስት ኩባንያዎች በኩልም የግልፅነት ተቃውሞ እየቀረበበት እንደሚገኝ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። 
የቻይናው ኩባንያ በቦርድ በተሰጠው ልዩ ድጋፍ ለጨረታው እንዲያልፍ የተደረገበትን አካሄድ በመቃወም ቴክኖና ሪቮርስ የተሰኙ ኩባንያዎች ያቀረቡት አቤቱታ በተመሳሳይ መልኩ ውድቅ መደረጉም ታውቋል።
የቻይናው ሁዋዌና ሌኖቮ የተባሉት ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ግምገማ እንዲያልፉ የተደረገበት አካሄድ በአለም አቀፍ ኩባንያ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል።

በአማራ ክልል ዕምነት አልተጣለባቸውም የተባሉ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነትና ከደረጃቸው ዝቅ ተደረጉ

ኢሳት (ግንቦት 7 ፥ 2009)
በአማራ ክልል ከተካሄደው የጸጥታና ደህንነት ግምገማ ጋር በተያያዘ በህወሃት ዕምነት አልተጣለባቸውም የተባሉ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነትና ከደረጃቸው ዝቅ ተደረጉ።
ከክልሉ የፖሊስ አመራሮች ከስራ የተሰናበቱም ይገኙበታል። በባህርዳርና በጎንደር ከተፈጸሙት የቦምብ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ የአካባቢው ጸጥታ አልተቆጣጠራችሁም የተባሉት የክልሉ ፖሊስ አባላት ስም ዝርዝር ኢሳት ደርሶታል።
የአማራ ክልል አመራር አባላት ከስራ ደራጃቸው ዝቅ የተደረጉትና የተባረሩት የትምክህት አስተሳሰብ ሰለባ ናችሁ በሚል እንደሆነ የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ። ጥፋታቸው ደግሞ የቦምብ ፍንዳታ አልተቆጣጠራችሁም በሚል በትምክተኝነት ስለፈረጇቸው መሆኑት ተገልጿል።

Wednesday, May 10, 2017

በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤልያስ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገለጸ

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበረው ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የጤና ችግር እንደገጠማቸው ተገለጸ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሳችኋል ተብለው ለእስር ከተዳረጉ አምስተኛ ወራቸውን የደፈኑት ሁለቱ ወጣቶች፣ ሆኖም እከሁን ድረስ የእነሱን ጉዳይ በኃላፊነት ሊወስድ የቻለ አካል አለመገኘቱ በተደጋጋሚ ሰገለጽ ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ታስረው በሚገኙበት እስር ቤት የጤና ችግር እንዳጋጠማቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ተናግረዋል፡፡

High level U.S. military delegation visits Ethiopia

ESAT News (May 10, 2017)
A high level U.S. military delegation was in Ethiopia in the first two weeks of April to assess the military cooperation between the two countries and define new policies and strategies, a reliable source told ESAT.
The source, who wish to remain anonymous due to the sensitivity of the matter, said the team has visited Addis Ababa and Mekele, the capital of Tigray.

Prominent Ethiopian activist and writer passes away

ESAT News (May 10, 2017)
Fekade Shewakena, activist, prolific writer and commentator has passed away on Tuesday in Maryland at the age of 61.
Fekade was respected by activists and politicians with opposing political allegiance, and his thought provoking commentaries and articles were conciliatory and aimed at bringing harmony to the otherwise polarized Ethiopian politics.
He has been an active participant in Ethiopian Diaspora politics since he left his country two decades ago. He was among the 42 university professors dismissed from their posts in 1993 by the current Ethiopian regime, which sees independent scholars and critics as its number one enemy.

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አበድሮ የማይሰበስበው የገንዘብ መጠን በሃላፊዎች መካከል አለመግባባት መፍጠሩ ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009)
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለተለያዩ ተበዳሪዎች አበድሮ የማይሰበስበው የገንዘብ መጠን በሃላፊዎች መካከል አለመግባባት ፈጠረ።
ባለፈው ሳምንት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉ አራት ምክትል ፕሬዚደንቶች በዚሁ ተመላሽ በማይሆን የብድር መጠን ከባንኩ ፕሬዚደንት ጋር ባለመስማማታቸው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ምክንያት መሆኑን አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት አቶ ጌታሁን ናና የባንኩ የተበላሸ ብድር (nonperforming loans) መጠን ወደ 50 በመቶ አካባቢ ሊሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ማቅረባቸው ታውቋል። 
ይሁንና አራቱ ተሰናባች ፕሬዚደንቶች ባንኩ ለተለያዩ አካላት አበድሮ የማይሰበስበው የብድር መጠን ሃላፊው ከሚገልፁት ጋር እጅጉኑ የሚለያይ እንደሆነ በመግለጻቸው ከአዲሱ ፕሬዚደንት ጋር አለመግባባታቸው ታውቋል።
በአዲሱ የልማት ባንክ ፕሬዚደንትና በስራ ሃላፊዎቹ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ አቶ ጌታሁን ናና አራቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች ከሃላፊነት እንዲነሱ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሏል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለበርካታ ተበዳሪዎች ከሚሰጠው በቢሊዮን ብር ከሚቆጠር ብድር ውስጥ ከፍተኛ ገንዘቡን በተበላሸ ብድር ስም እንደማይሰበሰብ ተመልክቷል።
የባንኩ የተበላሸ ብድር መጠን እያሰፉ መምጣት ባንኩን አደጋ ውስጥ ከመክተቱ በተጨማሪ፣ ለፋይናንስ ቀውስ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የባንክ ባለሙያዎች በበኩላቸው አዲሱ የልማት ፕሬዚደንት ከ20 አመት በላይ በዘርፉ ልምድ ያላቸው ሃላፊዎች በቁጥር ልዩነት ማሰናበቱ ተገቢ አይደለም ሲል ለጋዜጣው አስረድተዋል። ይሁንና የልማት ባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ጌታሁን ከባልደርቦቻቸው የቀረበው መከራከሪያ አሳማኝ አለመሆኑን በሰጡት ምላሽ አስታውቋል።

ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የብድርና የእርዳታ ፍሰት እየቀነሰ እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009)
የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ አለም አቀፍ ሃገራትና አበዳሪ አካላት የሚያገኘው የብድርና የእርዳታ ፍሰት እየቀነሰ መምጣቱ ጉዳዩን የሚከታተለው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ረቡዕ አስታወቀ።
በተለይ ያደጉ አገሮች በራሳቸው ችግር ምክንያት ሲያደርጉ የቆዩትን የፋይናንስ ድጋፍ እያቋረጡ መሆኑን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አዳም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል።
የብድርና የእርዳታ ፍሰቱ መቀነስ ከአጠቃላይ ወጪ አንጻር ተጽዕኖ ይኖረዋል ያሉት ሃላፊው በተለይ ከአደጉ አገሮች የሚገኘው ብድርና ዕርዳታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደነበረው አስረድተዋል።
ባለፈው አመት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው አለም አቀፍ የልማት ድጋፍ ላይ ያደረገው የገንዘብ ቅነሳ ኢትዮጵያን ተጎጂ ማድረጉ ተገልጿል።
የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በወሰደው በዚሁ የድጎማ ማሻሻያ ኢትዮጵያ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍን ያጣች ሲሆን፣ ታንዛኒያ፣ ዩንጋንዳ፣ ማላዊና ኬንያም መጠነኛ ቅነሳ ተደርጎባቸዋል።
ከአለም አቀፍ አካላት ዘንድ በሚገኝ የገንዘብ ልገሳ በጀታቸውን የሚደጉሙ ሃገራት አሜሪካ በወሰደችው ዕርምጃ የፋይናንስ ጫና ሊያጋጥማቸው እንደሚችል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ሃገሪቱ ያጋጠማትን የብድርና የድጋፍ መቀነስ ለመቅርፍ፣ የውጭ ንግድና ኢንቨሰትመንት ማስፋፋት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ሃላፊው አክለው አስታውቀዋል።

ለምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በድጋሚ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በድጋሚ ጭማሪን ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ።
በቅርቡ መንግስትና ድርጅቱ ባወጡት የተረጂዎች ቁጥር መረጃ 5.6 ሚሊዮን አካባቢ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ተረጂዎች በ2.2 ሚሊዮን በማደግ 7.8 ሚሊዮን መድረሱ ይፋ ተደርጓል።
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪ እየሰጠ ያለው ምላሽ አነስተኛ መሆንና በድርቁ በተጎዱ አካባቢዎች በበልግ ወቅት መጣል የነበረበት ዝናብ በበቂ ሁኔታ ባለመጣሉ ምክንያት የድርቁ አደጋ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል።
በዚሁ ተደራራቢ ችግር ሳቢያ የተረጂዎች ቁጥር በቅርቡ ጭማሪን እንደሚያሳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርቁን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል። 
ይሁንና የተረጂዎች ቁጥር በምን ያህል ሊጨምር እንደሚችል ድርጅቱ የሰጠው ትንበያ የሌለ ሲሆን፣ በተለይ በሶማሌ ክልል የምግብ እጥረቱና የኮሌራ በሽታ ወረርሽን እያደረሰ ያለው ሰብዓዊ ጉዳት እየከፋ መምጣቱ ተገልጿል። መንግስት በበኩሉ 7.8 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የምግብ እጥረት አስከትሎ ያለውን የድርቅ አደጋ ለመታደግ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ርብርብ እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርቧል።

የማላዊ መንግስትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማላዊ አየር መንገድን በሽርክና ለማስተዳደር ያደረጉት ስምምነት ተቃውሞ ቀረበበት

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009)
በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማላዊ መንግስት ጋር የማላዊን አየር መንገድ በሽርክና ለማስተዳደር ያደረጉት ስምምነት በማላዊ የፓርላማ አባላት ዘንድ ተቃውሞ ቀረበበት።
በሃገሪቱ ፓርላማ ተሰሚ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የፓርላማ አባሏ ጁሊያን ሉንጉዚ የሃገራቸው መንግስት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያደረገው ስምምነት ማላዊን የሚጠቅም አይደለም በማለት ውሉ መጣራት እንዲካሄድበት ጥያቄ ማቅረባቸውን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። 
የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲ አባሏ ሉንጉዚ ለፓርላማ ባደርጉት ንግግር የተደረሰው ስምምነት ማላዊን ስለመጥቀሙ የማላዊ መንግስት ሪፖርት እንዲያቀርብ አሳስበዋል።

አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁትና የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባደረባቸው ድንገተኛ ህምም ማክሰኞ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ላለፉት 23 አመታት በዚህ በአሜሪካ በስደት ይኖሩ የነበሩት አቶ ፈቃደ የኢህአዴግን ስልጣን መያዝ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከተባረሩ 42  መምህራን አንዱ እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል። በዚህ በአሜሪካ በነበሩበት ረጅም ጊዚያቶች አቶ ፈቀደ ሸዋቀና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፣ ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለያዩ መድረኮች ለህዝብ በማሳወቅም ይታወቃሉ።

Friday, May 5, 2017

Ethiopia: British doctor objects to WHO candidature of Tedros Adhanom

ESAT News (May 5, 2017)
A British medical doctor who taught medicine in Ethiopia for four years says Dr. Tedros Adhanom is the wrong candidate for the top position of the World Health Organization (WHO).
Explaining his reasons, Dr. Frank Ashall told ESAT on Friday that Dr. Adhanom, as one of a handful of people making decisions in Ethiopia, has failed to speak against millions of dollars of tobacco deals made with transnational companies. Dr. Ashall said that Dr. Adhanom had let under his watch the sale and purchase of tobacco by minors violating the country’s law and also the public advertisement of tobacco products against international accords.

US doesn’t need Ethiopia in its war on terror, says Ethiopian scholar

SAT News (May 5, 2017)
The Trump administration would be wise to delink its counterterrorism strategy from the Ethiopian regime, which barely clings to power by a state of emergency decree, says an Ethiopian scholar in a weekly op ed.
“Ethiopia’s involvement in the domestic affairs of Somalia has made the military and political situation in Somalia worse, and resulted in documented large-scale war crimes and human rights violations,” Alemayehu Gebremariam, who also goes by Al Mariam, said in an article published on “THE HILL.”

Thursday, May 4, 2017

የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብደላሂ በኢትዮጵያ ሲያደርጉ የነበሩትን ጉብኝት አቋርጠው ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ጉብኝትን በማድረግ ላይ የነበሩት የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብደላሂ ረቡዕ በሞቃዲሾ ከተማ በአንድ ሚኒስትር ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ጉብኝታቸውን አቋረጡ።
ረቡዕ የሶስት ቀን ጉብኝትን ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተው የነበሩት ፕሬዚደንቱ ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እቅድ እንደነበራቸው ታውቋል።
በአንድ ቀን ቆይታቸው ረቡዕ ምሽት በጠ/ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ይዘውት የነበረው እቅድ ግን ሳይካሄድ ቀርቷል።
ረቡዕ ዕለት በሞቃዲሾ ከተማ በተተኮሰ ጥይት የሃገሪቱ የግንባታ ሚኒስትር የነበሩት ኦባል አብዱላሂ ሼክ ሲራጅ መገደላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። የሚኒስትሩን መገደል ተከትሎ በአዲስ አበባ የነበሩት ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብዱላሂ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ሃሙስ ወደ ሞቃዲሾ ማቅናታቸው ታውቋል።

አሜሪካ ለአለም አቀፍ ድጋፍ በምትሰጠው የገንዘብ ድጎማ ላይ ያስተላለፈችው የበጀት ቅነሳ፣ ኢትዮጵያ ዋነኛ ተጎጂ ማድረጉ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009)
አሜሪካ በቅርቡ ለአለም አቀፍ ድጋፍ በምትሰጠው የገንዘብ ድጎማ ላይ ያስተላለፈችው የበጀት ቅነሳ፣ ኢትዮጵያ ዋነኛ ተጎጂ ማድረጉ ተገለጸ። ለኢትዮጵያና ኡጋንዳ የሚሰጠው ድጋፍ እንደሚቀንስም ተመልክቷል።
ሃገሪቱ በተያዘው ሳምንት ባቀረበችው የ2017/2018 በጀት እቅድ በአለም አቀፍ የእርዳታ ላይ የ31 በመቶ አካባቢ ቅናሽ ማድረጓን ዘኢስት አፍሪካን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።
በዚሁ የአሜሪካ ዕርምጃ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ከአፍሪካ ዋነኛ ተጎጂ መሆናቸው ታውቋል።

በባህርዳር ከፍንዳታ ጋር በተየያዘ በጥርጣሬ በተያዙ ሰዎች ላይ የቴሌቪዥን ቀረጻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ



ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009)
ባለፈው ቅዳሜ በባህርዳር ከተከሰተው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ በተያዙ ሰዎች ላይ የቴሌቪዥን ቀረጻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጹ። የገዢው ፓርቲ ምርት የሆነውን ባላገሩ ቢራ ለማስተዋወቅ በተጠራ የሙዚቃ ኮንሰርት አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ ፕሮግራሙ መቋረጡ ይታወሳል።
በጥርጣሪ በተያዙት ግለሰቦች ላይ ማክሰኞ የተጀመረው ቀረጻ በአማራ ክልል ቴሌቪዥን አማካኝነት እየተፈጸመ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ይህንን ሂደት በበላይነት የሚመሩት የማነ የተባሉ የአካባቢው የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ሲሆኑ፣ ታሳሪዎቹ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት የተነገራቸውን ግለሰብና ድርጅት ወንጅለው መግለጫ እንደሰጡም መመሪያ ተላልፏል።

Wednesday, May 3, 2017

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአለም ሃገራት ለመገናና ብዙሃን ነጻነት መከበር ቁርጠኝነታቸው እንዲያሳዩ ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተለያዩ አለም አቀፍ አካላት የአለም ሃገራት ለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት መከበር ቁርተኝነታቸውን በተግባር እንዲያሳዩ አሳሰቡ።
በየአመቱ ሚያዚያ 25 ፥ የሚከበረውን የአለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀንን አስመልክቶ መልዕክትን ያስተላለፉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ የአለም ሃገራት መረጃዎችና ዜጎች በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከብና ማስፈራራት በአስቸኳይ ማቆም እንዳለባቸው ጥሪን አቅርበዋል።
የነጻ መገናኛ ብዙሃን ለሰላምና ፍትህ መጎልበት ወሳኝ ነው ያሉት ዋናው ጸሃፊው፣ ጋዜጠኞች ህይወታቸውን አደጋ ውስጥ በመክተት ያልተሰሙ ድምፆች እንዲሰሙ የሚያደጉት ጥረት በመንግስታት ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የዘንድሮው የመገናኛ ብዙሃን ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ በኢንዶኔዢያ መዲና ጃካርታ ከተማ የተከበረ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ  የአለም መሪዎች ለነጻ መገናኛ ብዙሃን ጥበቃ ማድረግ እንዳለባቸው ባስተላለፉት መልዕክት አክለው ገልጸዋል።

የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብዱላሂ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈጥሯል በተባለው አለመተማመን ዙሪያ ለመምከር አዲስ አበባ ገቡ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009)
የሶማሊያው አዲስ ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብዱላሂ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈጥሯል በተባለው አለመተማመን ዙሪያ ለመምከር ረቡዕ በአዲስ አበባ ጉብኝት ማድረግ መጀመራቸውን ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል የሃገሪቱ ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ ረቡዕ ዘገበ።
ፕሬዚደንት አብዱላሂ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው በፊት በአምስት ሃገራት ጉዞ ያደረጉ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊም እጅግ አስቸጋሪም ነው ሲሉ የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ምሁር የሆኑት ጀራልድ ፕሩኒየር ለራዲዮ ጣቢያው ገልጸዋል።
ፕሬዚደንቱ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ለመምከር የወሰደባቸው ጊዜ ከዚህ በፊት የሶማሊያ ተመራጭ ፕሬዚደንቶች ሲያደርጉ ከቆየው ጋር ሲነጻጸር በጣም የዘገየ መሆኑንም ሚሰተር ጀራልድ አስረድተዋል።
ከሁለት ወር በፊት በሃገሪቱ የተካሄደን ምርጫ ለማሸነፍ የቻሉት ፕሬዚደንት አብደላሂ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሃገሪቱ እንዲወጡላቸው የተባለው አቋም ለድል እንዳበቃቸው ሲገልጹ ቆይቷል።
ይሁንና ፕሬዚደንቱ እስካሁን ድረስ በሃገራቸው ስላሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጉዳይ በይፋ የሰጡት ምላሽ የሌለ ሲሆን፣ ጉዳዩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ወቅት መወያያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ከ300 ሺ በላይ ህጻናት አስከፊ የምግብ እጥረት ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ዩኒሴፍ ገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ በአራት ክልሎች እየተባባሰ ባለው የድርቅ አደጋ ዕድሚያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ ከ300 ሺ በላይ ህጻናት በአስከፊ የምግብ እጥረት ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግስት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ገለጸ።
የአለም ባንክ በበኩሉ ተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ እያጋጠማት ያለው ኢትዮጵያ አደጋውን በዘላቂነት መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ማተኮር እንዳለበት አሳስስቧል።
አዲስ ተከስቶ ባለው በዚሁ የድርቅ አደጋ በኦሮሚያ፣ አፋር፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች ከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት አጋጥሟቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።
ባለፈው አመት የተከሰተው ይኸው የድርቅ አደጋ በመባባስ ላይ መሆኑን ተከትሎ 5.6 ሚሊዮን የነበረው የተረጂዎች ወደ 7.7 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶ በጋራ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የድርጅቱ የህጻናት መርጃ ተቋም በበኩሉ 303ሺ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ ህጻናት በአስከፊ የምግብ እጥረት ምክንያት የአካልና የጤና ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ አስታውቋል።

በሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሁለቱ ሃገራት ሰራዊቶች መስፈራቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2009)
በቅርቡ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል በድንበር ዙሪያ ቁጥጥርን ለማጠናከር የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት ሰራዊቶች በአዋሳኝ ድንበር ዙሪያ መስፈራቸውን የሱዳን ባለስልጣናት ረቡዕ አስታወቁ።
የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች ባለፈው ወር በባህር ዳር ከተማ ባካሄዱት የድንበር ውይይት በአካባቢው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የአደንዛዥ ዕፅን ይቆጣጠራል የተባለ የጋራ ሰራዊት እንዲሰፍር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።
የዚህኑ የመግባቢያ ሰነድ መፈረም ተከትሎ የኢትዮጵያና የሱዳን ወታደሮች ከካርቱም ከተማ በ300 ማይል ርቀት ላይ በሚገኝ የድንበር ዙሪያ ቁጥጥር ማድረግ መጀመራቸውን ሱዳን ትሪብዩን ጋዜጣ ዘግቧል።

Monday, May 1, 2017

Ethiopia: UNPO calls gov’t rights commission partial

ESAT News (May 1, 2017)

The Unrepresented Nations and Peoples Organization (UNPO) said the report by the Ethiopian Human Rights Commission regarding the deadly anti-government protests in the country misrepresents the number of deaths due to state-sponsored violence and considers the measures taken by security forces as mostly proportionate and appropriate.

The

የአርጆ ዴዴሳ ስኳር ፋብሪካ በሸንኮራ እጥረት ተከትሎ ምርቱን አቋረጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009)

የአርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ያጋጠመውን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት እጥረት ተከትሎ ምርቱን ሙሉ ለሙሉ አቋረጠ።

ከ2007 አም ጀምሮ ስራውን በከፊል የጀመረው ፋብሪካው ችግሩን ለመቅረፍ በግንባታው ላይ ከሚገኝ ግድብ ውሃን በመጥለፍ የሸንኮራ አገዳ ለማምረት ቢሞከርም በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ጥረቱ ሳይሳካ መቅረቱን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ካባ መርጋ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

ለዚሁ ፋብሪካ አገልግሎት አንዲሰጥ የታሰበ የመስኖ ልማት ግድብ ግንባታም በተያዘለት የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ መቅረቱ ታውቋል።

የመስኖ ልማት ግድብ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት እስኪሰጥ ድረስ የሸንኮራ አገዳ በዝናብ ለማምረት ጥረት ቢደረግም የተገኘው ምርት አነስተኛ መሆኑን የፋብሪካው ሃላፊዎች አስረድተዋል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበው ሪፖርት “ተዓማኒነት” የጎደለው ነው ሲል አንድ ተቋም ገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009)

መቀመጫውን በቤልጂየም ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም በቅርቡ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበን ሪፖርት “ተዓማኒነት” የጎደለው ነው ሲል አጣጣለው።

ይኸው Unrepresented Nation and Peoples Organization የሚል መጠሪያ ያለው ተቋም በኮሚሽኑ ሪፖርት የተደረገው የሟቾች ቁጥር በትክክለኛ ያልተቀመጠና በገለልተኛ ያልተከናወነ ነው በማለት ምርመራው በገለልተኛ አካል እንዲካሄድ ጥሪውን አቅርቧል። በኦሮሚያ፣ አማራና የደቡብ ክልሎች የተካሄዱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በተመለከተ ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀረበው ኮሚሽኑ 669 ሰዎች መገደላቸውን መግለፁ ይታወሳል።

ይሁንና የሪፖርቱ ይፋ መደረግን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ሰዎች ላይ የፈጸሙት ድርጊት ከነምስክሮች ተሟልቶ መቅረብ እንደነበረበትም አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት በጎንደር በፈነዳው ቦምብ አንድ የውጭ አገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009)

የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ ደርሶ በነበረው የእጅ ቦምብ ፍንዳታ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን ሰኞ ይፋ አድርጓል።

ይሁንና የብሪታኒያ መንግስት ጉዳት የደረሰበትን የውጭ ዜጋ ማንነት ከመግለጽ የተቆጠበ ሲሆን ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባሰራጨው የጉዞ ማሳሰቢያ አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ አስመልክቶ ኢሳት የአይን ዕማኞችን ዋቢ በማድረግ ዘገባ ማቅረቡም የሚታወስ ነው።

ቅዳሜ በባህር ዳር ከተማ በፈንዳ ቦምብ አንድ ሲቪል ሲገደል ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት መቁሰላቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009)

ቅዳሜ ባህርዳር በፈነዳው ቦምብ አንድ ሲቪል ሲገደል አንድ ኢንስፔክተርን ጨምሮ ሶስት የልዩ ሃይል ፖሊሶች መቁሰላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ዳሸን ቢራ በአዲስ ስያሜ “ባላገሩ” በሚል ራሱን ለማስተዋወቅ በጠራው የሙዚቃ ኮንሰርት አካባቢ በፈነዳው ቦምብ የሙዚቃ ኮንሰርቱ መቋረጡም ታውቋል።

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ እስራቱ ይበልጥ በባጃጅ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ላይ ያተኮረ እንደሆነም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የባጃጅ ሹፌሮች ላይ እስራቱ የጠነከረው ቦምቡ ከባጃጅ ውስጥ ተወርውሯል በሚል እንደሆነም ተመልክቷል።

Al Shabaab ambushes Ethiopian troops

ESAT News (May 1, 2017)

Al Shabaab fighters ambushed a convoy of Ethiopian troops serving the UN-mandated African Union Mission in Somalia (AMISOM) in Lower Shabelle region on Monday, according to a report by Shabelle News.

The convoy came under attack on a road near the southern village of Leego, as it was travelling to Burhakabo town in Baay region, according to locals who spoke to Radio Shabelle.

The report said the attack began with IED blast, and followed by heavy exchange of gunfire between the militants and the AMISOM soldiers. There is no immediate confirmation of the casualties.

Ethiopia: Grenade attack kills two at a concert in Bahir Dar  



ESAT News (May 1, 2017)

Two persons were killed and several others, including three police officer, were injured in Bahir Dar when a grenade exploded near the entrance to a concert hall on Saturday.

The concert, organized by Dashen Brewery, was under a boycotting campaign by the residents of Bahir Dar, who have also boycotted beer products by the Brewery, which is owned by the Amhara National Democratic Movement (ANDM), a member of the ruling coalition EPRDF.