Tuesday, December 18, 2018

አምዶም ገብረስላሴ ታሰረ

ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ በተካሄደው ስብሳባ አቶ በረከት ስሞኦን እና የሕወሓት ባለስልጣናትን የተቸው አምዶም ገብረስላሴ ታሰረ።
     ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረትየአረና የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ  አምዶም ገብረስላሴ በቁጥጥር ስር የዋለው መቀሌ አክሱም ሆቴል በተባለው አካባቢ ሲሆን፣ሰው ደብድበሃል በሚል  መታሰሩንም  መረዳት ተችሏል።አምዶም  መቀሌ አዲሸንዲህ በተባለ  ቦታ እንደታሰረ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።አምዶም ገብረስላሴ ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው  ሰብሰባ የሕወሃትን ባለስልጣናት ሲተች ንግግሩ እንዲቋርጥ መደረጉም ይታወሳል።

Friday, December 14, 2018

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት እስካሁን የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት እስካሁን የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ፡፡ ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሡ ዳምጠው ዛሬ ለሸገር እንደተናገሩት ከትናንት በስትያ አንስቶ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ግጭት ተከስቷል፡፡ በግጭቱ እስከ አሁን የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተነገረ ሲሆን ከአንድ መቶ የሚበልጡ ደግሞ ቆሰለዋል ተብሏል፡፡ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን አቶ አድማሱ ተናግረዋል፡፡

Thursday, December 13, 2018

ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ክፍል መዘጋቱ ተረጋገጠ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011) ማዕከላዊ በመባል የሚጠራው የወንጀል ምርመራ ክፍል መዘጋቱን አረጋግጬአለሁ ሲል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

ኮሚቴው ማዕከላዊን ተዘዋውሮ ከጎበኘበኋላ በሰጠው መግለጫ ማዕከላዊ ተዘግቶ ክፍሎቹ ለቡራዩ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መኖሪያነት እያገለገሉ ነው ብሏል።
የኮሚቴው አባላት አረጋገጥን እንዳሉትም በማዕከላዊ አንድም እስረኛ የለም።

በአዲስ አበባ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቤተክርስቲያን መጠለላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 4/2011) ከአዲስ አበባ በተለምዶ አጃምባ በሚባል አካባቢ ቤት ሰርተው ለዓመታት የቆዩ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ቤተክርስቲያን መጠለላቸውን ገለጹ።

ህገወጥ ናችሁ ተብለው በሌሊትበተኙበት በአፍራሽ ግብረሃይል ቤታቸው የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች በፋኑዔል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተጠልለው መኖር ከጀመሩ 15ቀናትያለፋቸው መሆኑን ለኢሳት ገልጸዋል።
በወቅቱ በድንገት በተወሰደው የማፍረስ ተግባር በተፈጠረ ግርግር

Monday, December 3, 2018

ፖሊስ ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው የተጠረጠሩባቸውን ተጨማሪ የወንጀል ተሳትፎዎች አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) መርማሪ ፖሊስ ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘውን በተመለከተ እስካሁን በሰራው የምርመራ ስራ አገኘኋቸው ያላቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ፖሊስ በዛሬው እለት ግለሰቡን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ካቀረባቸው ማስረጃዎች በተጨማሪነት አዳዲስ ያላቻውን ነው ያቀረበው።

በአፋር ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት አንድ የአፋር ወጣት ተገደለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 24/2011) በአፋር ክልል በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ኤል ውሃ አካባቢ ቡርካ በሚባል ቦታ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰላም ለማስከበር በሚል ጣልቃ በገባ የመከላከያ ሰራዊት አንድ የአፋር ወጣት መገደሉን ለኢሳት የደረሰ መረጃ አመልክቷል።

በአፋር ዛሬ የሚጀመረውንና አብዛኛውን አመራሮችን ያሰናብታል ተብሎ የሚጠበቀው የክልሉ ገዢ ፓርቲ ጉባዔውን በሚያካሂድበት ወቅት ዋዜማ የተቀሰቀሰው ግጭት ሶስተኛ ቀኑን መያዙ ታውቋል።
ጉባዔውን በሁከት በማጀብ የአቶ ስዩም አወል ቡድን የሚፈጽመው ሴራ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

በቤንሻንጉልና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ጥቃት የሚፈጽመው ኦነግ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 24/2011) በቤንሻንጉል ጉምዝና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ጥቃት በመፈጸም ላይ ያለው የኦነግ ጦር መሆኑን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስታወቀ።
ለእርዳታ የተዘጋጀ ከ2ሚሊዮን ብር በላይ በታጣቂዎች መዘረፉም ታውቋል።
በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት ቀጥሏል።
መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በግጭቱ አካባቢዎች መስፈራቸውን የቤንሻንጉል ጉምዝ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሰይፈዲን ሀሩን  ለኢሳት ገልጸዋል።

የወልቂጤ አካባቢ ወጣቶች በልዩ ሃይል እየታፈሱ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 24/2011) በጉራጌ ዞን የወልቂጤ አካባቢ ወጣቶች በአካባቢው ልዩ ሃይል እየታፈሱ መሆኑ ተሰማ።
በጉራጌና በቀቤና ብሔረሰቦች መካከል ቀደም ሲል ተቀስቅሶ የነበረው ግጭትም አሳሳቢ ወደሚባል ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ኢሳት ወደ አካባቢው ደውሎ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በፌደራል ደረጃ ጉዳዩን ለመፍታት የተደረገው ሙከራ ሊሳካ አልቻለም የሚሉት የኢሳት ምንጮች ግጭቱ እንዲባባስ የሚፈልጉ አካላት ደግሞ በአካባቢው ውጥረት እየፈጠሩ ነው ብለዋል።
ሁኔታውን ለማረጋጋት የፌደራሉ መከላከያ ሃይል በአካባቢው መሰማራቱም ታውቋል።

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት የበለጠ መጠናከር አለበት ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 24/2011)የኢትዮጵያ ችግር ከስረ መሰረቱ እንዲነቀል የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ግንኙነት የበለጠ መጠናከር እንዳለበት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ።
በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የአማራ ክልል የልኡካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ካለው የአማራ ተወላጆችና የአማራ ጉዳይ ያገባናል ካሉ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ምክክር አድርገዋል።
ከስብሰባው ተዳሚዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ችግር ከስረ መሰረቱ እንዲነቀል የእነዚህ ህዝቦች ግንኙነት የበለጠ የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች በትንሹ መገናኘት ሲጀምሩ፥መቻቻል ሲጀምሩ በሀገሪቱ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ማምጣት እንደሚችሉ አሳይተውናል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት በመጪው ምርጫ በ547 ወረዳዎች ለመወዳደር ማቀዱን አስታወቀ

አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በመጪው ምርጫ በ547 ወረዳዎች ዕጩዎቹን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተናገሩ።ንቅናቄው በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በንቃት የሚያሳትፍ ድርጅት ሊመሰርት መዘጋጀቱንም አቶ አንዳርጋቸው ጨምረው ተናግረዋል።
አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በመጪው ምርጫ በ547 ወረዳዎች ዕጩዎቹን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተናገሩ። አቶ አንዳርጋቸው ይኸን ያሉት ንቅናቄው በብሪታኒያ እና አካባቢዋ ከሚገኙ አባላቱ ጋር በመከረበት ስብሰባ ላይ ነው። ንቅናቄው በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በንቃት የሚያሳትፍ ድርጅት ሊመሰርት መዘጋጀቱንም አቶ አንዳርጋቸው ጨምረው ተናግረዋል። አዲስ የሚቋቋመው ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እና መርሐ-ግብር በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ዝግጁ ይሆናሉም ተብሏል። በትናንትናው ዕለት በለንደን ከተማ የተካሔደውን ውይይት የተከታተለችው ሃና ደምሴ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።