Tuesday, March 31, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሆኑት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው 28 ቀን ተቀጠረባቸው

(ነገረ-ኢትዮጵያ) እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ትናንት መጋቢት 21 አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው 28 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ፖሊስ እነ ብርሃኑ ተክለያሬድን ‹‹ለግንቦት 7 አባላትን መልምለው ወደ ኤርትራ በመላክና ቡድኑን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲሄዱ ተይዘዋል›› ብሏል፡፡

ጠበቃው እነ ብርሃኑ ተ/ክለያሬድ ለግንቦት ሰባት ሲመለምሉም ሆነ አባል ሲሆኑ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ እንደሌለ በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ፖሊስ ‹‹ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምመረምራቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ ሌሎች የምንይዛቸው ግብረ አበሮችም አሉ፡፡ መረጃ ያጠፉብናል፡፡›› በሚል ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ 28 ቀን ተፈቅዶለታል፡፡ ሚያዚያ 19 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ፖሊስ ሌሎች ሰዎች ይዘውት የተነሱትን መሳሪያ በማሳየትም እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ግንቦት ሰባትን ሊቀላቀሉ እንደነበር ለማሳየት በመረጃነት አቅርቧል፡፡ ጠበቃው በበኩላቸው ‹‹የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ምርመራ ለማድረግና መረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጠርጣዎቹን ማሰር ተገቢ አልነበረም፡፡ ሌሎች ሰዎች የያዙትን መረጃ እነሱን ለመክሰስ መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡›› ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

በሌላ በኩል ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የታሰረበት ቤት መብራት ስለማይጠፋ አይኑ ላይ ለከፍተኛ ችግር እንዳደረሰበት ቅሬታ አቅርቧል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ለ15 ደቂቃ ፀኃይ እንዲሞቁ ከሚፈቀድላቸው ውጭ ከታሰሩበት ቤት ውጭ መውጣት እንደማይፈቀድላቸውና ቤተሰቦቻቸውም እንዲጠይቋቸው እየተደረገ አለመሆኑን በቅሬታ አቅርበዋል፡፡


Saturday, March 28, 2015

ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ።

በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች እንደማትመለስ አረጋግጣለች። የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጅና ታማኝ የህወሃት አባል የነበረችው የስለላ ሰራተኛ፣ ከቀበሌ ተነስታ ለከፍተኛ ሃላፊነት የበቃች ታማኝ ነበረች።

Friday, March 27, 2015

“ኢህአዴግ የህዝቡ ብሶት አደጋ እንደሚያስከትል አውቋል” ስትል የአዲስ አበባ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ ም/ል ሊቀመንበር ተናገረች

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሊጉ ም/ል ሊቀመንበር በመሆን ለአመታት ያገለገለችው ወ/ት እየሩሳሌም አበረ ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ “የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሚገነፍል ድስት እፍ እፍ እየተባለ ቢያዝም፣ አሁንም
በርካታ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እያነሳ ነው” ብላለች።
የታፈነ የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲ ጩኸት አለ የምትለው ወ/ት እየሩሳሌም፣ ገዢው ፓርቲም ህዝቡ በከፍተኛ ብሶት ላይ እንደሚገኝና አደጋ ሊያስከትል እንደሚችልም ጠንቅቆ ያውቀዋል ብላለች።
ከምርጫ 97 በሁዋላ ኢህአዴግ የተሳካለት ነገር ቢኖር ተቃዋሚዎችን ማፈን ነው የምትለው ኢየሩሳሌም፣ ህዝቡ በሚታየው ነገር ሁሉ ባለመርካቱ ገዢው ፓርቲ ቁጥጥሩን በማጥበቅ የህዝቡን ብሶት ለማፈን ይሞክራል ስትል አክላለች።
ወ/ት እየሩሳሌም ድርጅቱን ጥላ ስደትን መርጣለች። ለረጅም አመታት የአዲስ አበባ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና በሌሎችም የስልጣን ሃላፊነቶች ላይ ሲሰሩ የቆዩት የኦህዴድ ድርጅት አባል የሆኑት ወ/ሮ አበባ ገብረስላሴም በቅርቡ ኢህአዴግን በመተው፣ በአሜሪካ
ጥገኝነት ጠይቀዋል። ከወ/ት እየሩሳሌም ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ሰሞኑን ይቀርባል።


በኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግር ት/ቤቶችን ከማዘጋት አልፎ ለስደት እየዳረገ ነው

ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በመቶ ሚሊየን በሚገመት ወጪ በታላቅ ፌሽታ እያከበረ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰውን የመጠጥ ውሃ ችግር ሊታደግ ያልቻለ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡

ከግብርና ሚኒስቴር የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የመጠጥ ውሃ ችግር ሕዝብን ለከፍተኛ ችግር ከመዳረጉም አልፎ የመማር ማስተማር ስራ በማደናቀፍ ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት ደርሷል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የትብብሩን ሰልፍ እውቅና ነፈገ

ህገ መንግስታዊ መብታችን ከቦሊ ቦል ስፖርት በታች ሆኗል›› አቶ አዲሱ ጌታነህ

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር እሁድ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም የ9ኙን ፓርቲዎች ትብብር በባህርዳር ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና እንዳልሰጠውና ሰልፉን ማድረግ እንደማይቻል የትብብሩ አባልና የባህርዳር ሰልፍን አስተባባሪ ለሆነው ሰማያዊ ፓርቲ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

አስተዳደሩ ለሰልፉ እውቅና እንዳልሰጠ የገለፀው ‹‹ሁለተኛውን አገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር እያስተናገድን በመሆኑ›› እና ‹‹የህዳሴውን ግድብ የቦንድ ሳምንት በከተማችን በየማዕከሉ እየሰራን በመሆኑ›› ሰልፉን ለመጠበቅ የሚያስችል የፀጥታ ኃይል የለም በሚል ነው፡፡

Thursday, March 26, 2015

በኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግር ት/ቤቶችን ከማዘጋት አልፎ ለስደት እየዳረገ ነው

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በመቶ ሚሊየን በሚገመት ወጪ በታላቅ ፌሽታ እያከበረ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች
ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰውን የመጠጥ ውሃ ችግር ሊታደግ ያልቻለ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡
ከግብርና ሚኒስቴር የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የመጠጥ ውሃ ችግር ሕዝብን ለከፍተኛ ችግር ከመዳረጉም አልፎ የመማር ማስተማር ስራ በማደናቀፍ ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት ደርሷል።
የመጠጥ ውሃ ችግር ከገጠማቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች መካከል በአርሲ ዞን በጎሎልቻ፣ መርቲ፣ .ዝዋይ፣ ዱግዳ፣ ሴሩና ደጁ ወረዳዎች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻላ ሲራሮና ሻሸመኔ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሚደጋ፣ ቁምቢያ መዩ ወረዳዎች፣ በምስራቅ
ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ እና በጉጂ ዞን በሊበንና ሰባቦሩ ወረዳዎች አስከፊ የተባለ የመጠጥ ውሃ ችግር ማጋጠሙን ሚኒስቴሩ አጋልጦአል፡፡
የመጠጥ ውሃ ችግሩ በተለይ በአርሲ ዞን በዝዋይ ዱግዳና በሴሩ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ ት/ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰ ችግር መከሰቱ ተረጋግጦአል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ ከአጋር ድርጅቶች
ባገኘው ድጋፍ ውሃ በቦቴ የማደል ስራ እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
በቦረና ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ማለትም በአሬሮ፣ ድሬ፣ ዲሎ፣ ዳስ የእንስሳት መዳከምና ሞት መከሰት የጀመረ ሲሆን በአርሲና ምዕ/ሐረርጌ ዞኖች የእንስሳቱ አቋም እየተዳከመ መሆኑ፣ የእንስሳት እንቅስቃሴም ተጀምሮ በምዕ/ሐረርጌ ዞን ከቡርቃ ዲምቱና ሃዊ
ጉዲና ወደ ዱንገታና ዋቤ ወንዝ፣ በቦረና ዞን ከተልተሌ ወደ ገራንና ኮንሶ፤ ከድሬ፤ ሚዮና ሞያሌ ወደ ኬንያ (አዋሳኝ ቦታዎች) በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል።
የኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ/ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነቱን የህዝብ ችግር ሳይፈታ ለክብረበአል በመቶ ሚሊየን ብሮችን ሲያፈስ መታየቱ አሳዛኝ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ተወላጆች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአማራ ክልል ደግሞ በሰ/ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፣ በሰ/ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ በእያንዳንዳቸው 3 ቀበሌዎች የውሃ እጥረት፣ በዋግኸምራ ዞን በሳህላ፣ ዝቋላና ሰቆጣ ወረዳዎች፣ በሰ/ወሎ ዞን በላስታና ቡግና ወረዳዎች፣ በደ/ወሎ ዞን በመቅደላ
ወረዳ በ4 ቀበሌዎች፣ በኦሮሚያ ዞን በአ/ፉርሲ ወረዳና በምስ/ጎጃም ዞን ቆላማ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ተከስቷል።
በሀረሪ ክልል በ5 ቀበሌዎችና በድሬዳዋ አስተዳደር ቆላማ ቀበሌዎችም ተመሳሳይ ችግር ተከስቷል። ችግሮችን ለመቅረፍ ውሃ በቦቴ ለማደል ሙከራ መደረጉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።


Wednesday, March 25, 2015

የወያኔ ጀኔራሎችና ባለስልጣናት ብርክ ላይ ናቸው የመቸረሻ ስብከታቸውም ኤርትራ ውስጥ ነፃነት ታጋይ ሚባል ይቅርና አንድም የሸፈተ ኢትዮጵያዊ ለም፡፡ ሻቢያ ብቻ ነው ያለው የሚል ወታደራዊ ስብሰባ ላይ ተተምዶ እደሰነበተና የየጦር ሰራዊትና ክፍሉንም እንዲዘጋጁ ተናግረዋል፡፡

የወያኔ ጀኔራሎች የተቃዋሚዎችን ሃይልና አቅም በመፍራት እና መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ነፃነት ታጋይ ወገኖቻቸው ይቀላቀላሉ ብሎ በመፍራት እንዲሁም ቤቀኑ እየሄዱ ሚቀላቀሏቸውን ኢትዮጵያዊያን ሲቪሎችና ሲቪል ልብስ እየለበሱም እስሙሉ ትጥቃቸውም የሚቀላቀሏቸውን በማየት ለቀሪው ሰራዊት ግራ ማጋቢያ አለኝ የሚለውን ሃሳቡን በማሰራጨትና ስብሰባ መዓት በማብዛት ላይ ይገኛል፡፡

ወያኔ ጀኔራሎችና ባለስልጣናት ነባር ታጋዮች ሳይቀር ተርበትብተዋል በዚህም ምክንያት
“… ኤርትራ ውስጥ ምንም ኢትዮጵያዊ የነፃነት ታጋይ ሚባል የለም… ያለው ሻቢያ ብቻ ነው ሻቢያ ደግሞ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ተላት ነው…

የጦማርያንና ጋዜጠኞቹ አቤቱታዎች ውድቅ ተደረጉ

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሦስቱ ወዳጅ ጋዜጠኞች መጋቢት 15/2007 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡

መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች ባቀረቧቸው ሁለት አቤቱታዎች ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህም አንደኛ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ካለው ማስረጃ ዝርዝር ውስጥ 12 የኦዲዮ-ቪዲዮ ሲዲዎች አያይዞ ያቀረበ ቢሆንም፣ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች እስካሁን ባለመድረሳቸው ተከሳሾች የቀረበባቸውን ማስረጃ ተመልክተው መልስ ለማዘጋጀት ሲዲዎቹ እንዲሰጧቸው ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ 4ኛ ተከሳሽ ማህሌት ፋንታሁን እና 9ኛ ተከሳሽ ኤዶም ካሳዬ በቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ ከጎብኝዎቻቸው መከልከል ጋር በተያያዘ አቅርበውት በነበረው አቤቱታ ላይ ብይን መስጠት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም ሁለቱንም አቤቱታዎች ውድቅ አድርጓል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዝባዊ ሰልፍ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዝባዊ ሰልፍ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ ሰልፉ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ይደረጋል የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ፡፡ ትብብሩ በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ቀደም ብሎ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር መጋቢት 20/2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፉን የሚያካሂድባቸው ከተሞች የሚከተሉት ሆነዋል፡፡ እነርስም፡
1. አዳማ፣
2. ጅማ፣
3. አሰበ ተፈሪ (ጭሮ)፣
4. በአማራዉ ክልል
5. ባህር ዳር፣
6. ደብረ ታቦር፣
7. ደብረ ብርሃን፣
8. ደብረ ማርቆስ
9. ደሴ፣
10. አርባ ምንጭ፣
11. ሐዋሳ፣
12. ወልቂጤ፣
13. ወላይታ ሶዶ፣
14. ዱራሜ
15. ሆሳዕና
ትብብሩ ‹‹መጋቢት 20 በፍጹም አይቀርም›› በሚል ለህዝቡ የድጋፍ ሰልፍ ጥሪ ያደረገ ሲሆን፣ ከተሞቹ የተመረጡትም ፓርቲዎቹ በየአካባቢዎች ባቀረቡት እጩ ብዛት መሰረት እንደሆነ ገልጹዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በተመረጡት ከተሞች የሚደረገው ሰልፍ በተከናወነ በሳምንቱ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ትጥቅ ትግል ፣ ሰላማዊ ትግል ፣ ሁለገብ ትግል (ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ)

(አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ናቸው። ይህ ጽሁፍም ፓርቲን ወክለው ሳይሆን ራሳቸውን ወክለው የጻፉት ነው)

ወቅታዊ አጀንዳ እና በቁንፅል የሚተው ባይሆንኝ ነው – በትግስት አንቡልኝ

ጭቆና ሲበዛ ሰዎች ብዙ መንገድን ተጠቅመው መታገል ይሻሉ፡፡ የጭቆናውን ቀንበር ለመስበር ጨቋኙን ከመግደል አንስቶ ራስን እስከማቃጠል ድረስ የሚደርሱ በርካታ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ከአገዛዝ ሰንሰለት ራስን ነፃ ለማድረግ ብዙዎች ተጨንቀው ማሰብም አይፈልጉም፡፡ በቃ ገዢውን ወዲያ አሽቀንጥሮ ጥሎ ነፃ መሆን (end of the story end of the oppression)! በተፈጥሮ ነፃ ሆኖ የተፈጠረ ሰው በሂደት እጅግ በተወሳሰበ የህይወት መስተጋብር ውስጥ ቢኖርም የጭቆናው ለከት ሲያልፍ ግን ቀስቃሽ ሳያሻው እንደቡድንም ይሁን በግል በነሲብ ወደ ነፃነት ትግል መግባቱ አይቀርም፡፡ ነፃነት ከብዙ ምክንያታዊነትም በላይ የስሜት ሀይሉ ከፍተኛ ገፊ በመሆኑ ለነፃነት የሚደረገውም እንቅስቃሴ በራሱ ድንገታዊነት ይበዛዋል፡፡ ‘መቼ’ እና ‘እንዴት’ን አያጠይቅም፤ ‘ለምን’ የሚለው ብቻ በቂው ነው፡፡

Tuesday, March 24, 2015

ጎንደር ዝምታውን ሰብሯል – የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።

ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።

ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው  ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና

አዲሱ የተባሉ  ሲገደሉ፣ ከመንግስት ታጣቂዎች በኩል ደግሞ  የልዩ ሃይል አባል የሆነው  እባበይ እንዲሁም አንድ ስሙ በውል ያልታወቀና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ተማሪ በመንግስት

ሃይሎች ተገድሏል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ምሽት ላይ አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።


Monday, March 23, 2015

ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከሌለው ከርቸሌ እንከተዋለን የሚል ማስፈራርያ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰሙ

ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከሌለው  ከርቸሌ እንከተዋለን ይህንንም ለማድረግ አቅም አለን የሚል ማስፈራርያ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንትና በጅማ ከተማ ተገኝተው ይህን አድርገን ነጻነት አመጣን ዲሞክራሲን እየቀዳን ለህዝቡ አከፋፈልን አሉ። የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች እንዳደረሱኝ መረጃ ከሆነ ሚኒ ኃይለማርያም ኔትወርክ አዘግተው በጅማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አድረዋል ።

ከንግግራቸው ውስጥ ፈገግ ካሰኘኝ ልለፍ ፣ሚኒ ኃይሌ እንዲህ አሉ ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከለለው አቅም አለን ከርቸሌ እንከተዋለን አቤት አቤት ወግ መዓረጉ እንዳይቀር እኮ ነው የትኛው አቅም ነው ? ትልቅ መስኮት የሌለው ቤት ሰርቶ እስረኛ ማጠራቀሜውን ነው ፣ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ንጹህን ህዝብ በፖሊስ ማስደብደቡን ነው ?? ድንቄም አቅም አያ!!!!! ባዶ እጁን ከሚታገል ህዝብ ጋር መሳሪያ ታጥቆ አቅም አለን ሲል ከአንድ መሪ ተብሎ ከተወከለ አሻንጉሊት የማይጠብቅ የቂል ንግግር ።
የዩኒቨርስቲ ተማሪወችን ስብሠባ እንዳይካፈሉ አግደዋቸዋል ።

አቅማችሁን ለኤርትራ መንግስት አሳዩ እንጅ ከእኛ ላይ ቦተሊካችሁን አትንፉብን ።

ለማንኛውም በተያየዘ ዜና ላይ በኤርትራ የጦር ማካማች ሎጀስቲካ ላይ ያአደረሱት የአየር ጥቃት መግለጫው ጅማ ላይ ሳይሆን ቢቢሲ ወይም አልጀዚራ ላይ ቢሆን አሸናፊነትን አልያ ውድቀትን ሊያመጣ ይችላል እንላለን።


ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም!

ከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚል ዜና ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የህዳሴዉ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ባካሄዱት ጥናት መሠረት የህዳሴዉ ግድብ ፕሮጀክት ባጋጠመዉ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ መወሰኑን የሚያወሳ ዜና ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰሩ ምንም አይነት ስራዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከየትኛዉም አገር መንግስትና መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶችና ዉሎች ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም አርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ከሚመለከቱና በሚስጢር መጠበቅ አለባቸዉ ተብሎ ከሚታመኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዉጭ ሌላ ምንም ስራ ወይም አለም አቀፍ ስምምነትና ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ በድብቅ መደረግ የለበትም የሚል የጸና እምነት አለዉ። ሆኖም ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዢዎች በከፋ መልኩ የሚገዛ የጥቁር ፋሺስቶች አገዛዝ በመሆኑ የሚሰራቸዉ ስራዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈርማቸዉ ዉሎችና ስምምነቶች የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅም የሚጻረሩና የሚጋፉ ድብቅ ስምምነቶች ናቸዉ።

Sunday, March 22, 2015

BREAKING NEWS High ranking Ethiopian military officer confirmed that Ethiopian Air Force jets bombarded two key targets inside Eritrea.

High ranking Ethiopian military officer confirmed to Awramba Times, on condition of anonymity, that Ethiopian Air Force jets bombarded two key targets inside Eritrea.
According to the official, the airstrikes were conducted separately in two key targets, at a gold mine processing facility, near the capital Asmara and a military depot in Southern AkaleGuzai, Mai Edaga.

The current regime in Eritrea is widely considered as a State Sponsor of Terrorism in the horn of Africa. On July 2012, U.S. Treasury Department had placed sanctions on several Eritrean government officials and frozen their assets for supporting al-Shabaab, Al-Qaeda’s branch in Somalia


የኢትዮጵያ ተዋጊ ጄቶች፤ የኤርትራን የወርቅ ማዕድን ማውጫ፤ ሚሻን በቦንብ ደበደቡ

ኢ.ኤም.ኤፍ) የኤርትራ ኢኮኖሚ ዋልታ እንደሆነ የሚነገርለት፣ በማይ እዳጋ የሚገኘው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ በአየር ተደብድቧል። ተያይዞ የደረሰን ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ፤ የአየር ጥቃቱን ያደረሰው በወያኔ የሚመራው ወታደራዊ ኃይል ሲሆን፤ በጥቃቱም የወርቅ ማውጫው ክፉኛ መጎዳቱን ለማወቅ ችለናል። ከአስመራ 65 ማይል ርቀት ላይ የሚገኘው የወርቅ ማዕድን በአየር መመታቱ ከተሰማ በኋላ፤ በተለይ የአስመራ ነዋሪ ስጋት ላይ ወድቋል። የሰሞኑ የአስመራ ነዋሪዎችም መነጋገሪያ፤ “በመጀመሪያ ደረጃ የአየር ክልላችን ሲጣስ በራዳር ታይቶ፤ በጄቶቹ ላይ ቅጽበታዊ ምላሽ ለምን አልተሰጠም?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ይህንንም ጥያቄ ተከትሎ “እኛስ ምን ዋስትና አለን?” የሚሉ ይገኙበታል።


ከአንድ ቀን በፊት በኤርትራ እንደሚንቀሳቀስ ይፋ ያደረገ ኃይል፤ በዚሁ የወርቅ ማዕድን ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልጾ፤ በትግርኛ የተጻፈ ወረቀት በከተማው ማሰራጨቱ ይታወሳል። በዚህ በራሪ ወረቀት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት የኤርትራን አስተዳደር በመቃወም መሆኑን ገልጾ ነበር። የአሁኑም ጥቃት ይህንኑ ተከትሎ የተሰነዘረ ይመስላል።
በአሁኑ ሰአት በማዕድን ማውጫው ላይ የደረሰው አደጋ ለህዝብ ይፋ አልሆነም። ነገር ግን በቃጠሎው ምክንያት ከርቀት የሚታየው ጭስ በሚስጥር የተያዘውን ጥቃት እያሳበቀ ነው።
ኤርትራ ከዚህ የማዕድን ማውጫ በአመት እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች። የዚህ ማዕድን ስፍራ መመታት፤ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ኃይል በእጅጉ ይጎዳዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በወያኔ የሚመራው መንግስት ጠብ አጫሪነት እንደዚሁ አነጋጋሪ ሆኗል። ጥቃቱን የሚደግፉ እና የሚቃወሙ በሁለት የተለያዩ ጎራ ሆነው፤ የሃሳብ ፍጭት በማድረግ ላይ ናቸው። በዚህ ሁሉ መሃል ግን የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ማውጫ ግቢ አሁንም በእሳተየነደደ ነው።


Saturday, March 21, 2015

በአብርሃ ጅራ አለመረጋጋቱ ጨምሯል

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና
የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው።
እስካሁን በተደረገው አፈሳ የወረዳው ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዋና ሃላፊ ተቃዋሚዎችን ይረዳል በሚል ሲያዝ፣ ከ20 ያላነሱ የመንግስት ሰራተኞችና መምህራንም ተይዘዋል። ሁለት ፖሊሶች ደግሞ አምልጠው ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለዋል።
በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ በህዝቡ ላይ ሽብር እየፈጠሩ መሆኑን ነዋሪዎች በመናገር ላይ ናቸው። በአብርሃጅራ የፋርማሲስት ባለቤት የሆኑትና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው አቶ አበራ
ጀግኔ ድንበር አቋርጠው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቅለዋል ተብሎ መወራቱ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አፈሳውንና ጥቃቱን እንዲያባብሱ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።


Friday, March 20, 2015

በጎንደር ከተማ አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ተገደለ በርካታ ሰዎችም ታሰሩ

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚሊያሻዎች ሃላፊ ኮማንደር መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 15 ወይም ፋሲለደስ ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ላይ ማንነታቸው
ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ገዳዮቹም መሳሪያውን ማርከው ከእነ ትጥቃቸው ወደ አርማጭሆ ጫካ መግባታቸው ታውቋል። የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግንባሩ አካባቢ በጥይት የተመታ ሲሆን ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።
ድርጊቱን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች አከታትለው በመተኮሳቸው ህዝቡ ሁኔታውን ለማየት ወደ አደባባይ ሲወጣ ወደያውኑ መብራት እንዲጠፋ ተድርጓል።
አዣዡ በህዝቡ ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽም እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት አሁንም በአካባቢው እያንዣበቡ መሆኑን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ታጣቂዎች ገብተዋል በሚል መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ሰራዊት በአብርሃ ጅራ፣ አብድራፊና አጎራባች ከተሞች አሰማርቶ ፍተሻ እያካሄደ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለስልጣናትም ሳይቀር ተቃዋሚዎችን ትደግፋላችሁ ተብለው ተይዘዋል።

የሃገሪቱን ሃብት የወያኔ ባለስልጣናት ከጉምሩክ መጋዘኖች ሲዘርፉ አደሩ

በሃገሪቱ አንጡረ ሃብት ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጭቆና በማድረግ ላይ የሚገኙት የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጄኔራሎች እና በደህንነት ባለስልጣናት እየተመሩ ለሊቱት ከጉምሩክ መጋዘኖች በውርስ የገቡ እቃዎችን ሲጭኑ ያደሩ መሆኑን ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል::

ለሊቱን በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የጉምሩክ መጋዘኖች የተወረሱ የመኪና መለዋወጫዎች የኤሌክትሮኒስ እቃዎች የሞባይል ቀፎዎች ውድ ጌጣጌጦች የቤት እቃዎች የመሳሰሉት በባለተሳቢ መኪናዎች አስጭነው መውሰዳቸው ሲታውቅ እቃዎቹ በሃገሪት በተለያየ አከባቢ ተበትነው እንደሚሸጡ ምንጮቹ ገልጸው ለሊቱ የጄነራል ሳሞራ የኑስ የሜ/ጄነራል ተክለብርሃን እና የአርከበ እቁባይ መኪኖች እና ጠባቂዎቻቸው እና ተላላኪዎቻቸው በየመጋዘኖቹ ሲዘዋወሩ እንደነበር እና ለዚህ ዘረፋ ተሳታፊዎቹ እነማን እንደሆኑ በግልጽ ያሳያል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል::

የወያኔ ባለስልጣናት ሕዝብን እየጨቆኑ እየዘረፉ እስከመቼ እንደሚቀጥሉ የሚያሳስብ ጉዳይ መሆንን አውቀን ህዝብን እና ሃገርን ከዘረፋ እና ከጭቆና ለማዳን ከለውጥ ሃዮች ጎን በመቆም በሃገር ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአስተባበር እና ሕዝብን በመቀሰቀስ ከአስከፊው ስርአት ነጻ ለመውጣት በጋራ መንቀሳቀስ አለብን:: ነጻነታችንን ማራጋገጥ የምንችለው እኛው ታግለን መሆኑን ማውቅ ያለብን ወስኝ ወቅት ላይ ስለሆንን በአንድነት በመቆም ይህንን የሌቦች መንግስት ስርአተ ቀብር እናጣድፈው ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን::


Thursday, March 19, 2015

በአርበኞች ግንቦት 7 – ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።

በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።

በአብርሃ ጅራ አለመረጋጋቱ ጨምሯል

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና
የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው።
እስካሁን በተደረገው አፈሳ የወረዳው ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዋና ሃላፊ ተቃዋሚዎችን ይረዳል በሚል ሲያዝ፣ ከ20 ያላነሱ የመንግስት ሰራተኞችና መምህራንም ተይዘዋል። ሁለት ፖሊሶች ደግሞ አምልጠው ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለዋል።
በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ በህዝቡ ላይ ሽብር እየፈጠሩ መሆኑን ነዋሪዎች በመናገር ላይ ናቸው። በአብርሃጅራ የፋርማሲስት ባለቤት የሆኑትና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው አቶ አበራ
ጀግኔ ድንበር አቋርጠው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቅለዋል ተብሎ መወራቱ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አፈሳውንና ጥቃቱን እንዲያባብሱ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።


‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ

ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት እና በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ያሉ 10 ሰዎች ቀርበው ነበር፡፡ መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል እና ከ1-5ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተከሳሾች በእስር ቤቱ ደረሰብን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተያየት ካላቸው ለመቀበል መሆኑን የችሎቱ የግራ ዳኛ ገልጸዋል፡፡

የተከሰሾቹን የጽሑፍ አስተያየት በጠበቃ ተማም አባቡልጉ በኩል ቀርቦ ከመዝገብ ጋር ከተያያዘ በኋላ ተከሳሾቹ በየተራ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ የግራ ዳኛው በመናገር 1ኛ ተከሳሽን ‹‹በክሱ ላይ እንደቀረበው ወንጀሉን ፈጽመሃል ወይስ አልፈጸምክም?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡
ዘላለምም ‹‹አቃቤ ሕግ ባላደረኩት ነገር ህጉን መደገፍ ስለሚሆንብኝ ምንም መልስ አልሰጥም›› ሲል ዳኛው ‹‹በሥነ ሥርዓት ሕጉ ክሱን ክደው ተከራክራል› በሚል መዝግበነዋል›› በማለት መዝገብ ላይ አሰፈሩ፡፡

Wednesday, March 18, 2015

3 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ

መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-3 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ።
ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ወጣት ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል።

ወጣቶቹ በምን ምክንያት እንደታሰሩ ለማወቅ አልተቻለም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው ይፋ መግለጫ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ የፓርቲው ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ የአንድነት የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊፓርቲ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ኢ/ር ይልቃል በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ኮሚቴው ገልጿል፡፡

የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል።


በሚስጢር የተያዘው የአባይ ግድብ ስምምነት ሊፈረም ነው

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚስጢር ሲያደርጉት የቆዩት ድርድር ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የሶስቱ አገር መሪዎች በተገኙበት በካርቱም እንደሚፈረም መረጃዎች አመልክተዋል።
የፊርማ ስነስርአቱ የፊታችን ሰኞ በካርቱም የሚካሄድ ሲሆን፣ ዝርዝር ይዘቱ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ተደርጓል። የአባይ ግድብ ከህዝብ በውዴታና በግዴታ በሚዋጣ ገንዘብ እየተገነባ መሆኑ እየታወቀ፣ ስምምነቱን ገንዘቡን ለሚያዋጣው ህዝብ ይፋ ለማድረግ ለምን እንዳልተፈለገ ግልጽ አይደለም።
ሱዳንና ግብጽ ስምምነቱ የግብጽን ፍላጎት ያረካ ነው በማለት አስተያየት በመስጠት ላይ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ” አዲስ ምእራፍ” የከፈተ ከማለት ውጭ ለኢትዮጵያ ስለሚያስገኘው ጥቅም ምንም ያለው ነገር የለም።


የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት በአሜሪካ የደረሰባቸው ተቃውሞ በጠ/ሚ ሃይለማርያም፣ ጌታቸውን አሰፋ፣ ኢሳትና ሌሎች ሃይሎች የተቀነባበረ ነው አሉ

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ተቃውሞ ያገጠማቸው አቶ አብዲ ሙሃመድ ተቃውሞውን ያቀነባበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢሳት ፣ ግንቦት7 እና የኤራትራ መንግስት በጋራ በመሆን ነው ሲሉ አካራ ኒውስ በተባለው የግል ዌብሳይታቸው ላይ በሶማልኛ ባወጡት ረጅም ጽሁፍ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞውን ሲያሰማ የነበረውን መኮንን የተባለውን ሰው ስም ከፊት በማስቀደም፣ መኮንን ጌታቸው አሰፋ ሃይለማርያም ብለው ጽሁፋቸውን ይጀምሩና ኢሳት ከጀርባ ሆኖ ሲያቀናብር እንደነበር ያትታሉ።
የተቃውሞው እቅድ መክሸፉን የሚገልጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ኢሳት ቴሌቪዥንም ፕሬዚዳንቱ ሲናገሩት የነበረውን ንግግር ጥሩ ቢሆንም ሆን ብሎ እንዳይተላለፍ ያደረገው፣ እቅዱ መክሸፉን በመረዳቱ ነው ብለዋል።
በወጣው ጽሁፍ ዙሪያ አስተያየቱን የጠየቅነው በአንድ ወቅት የፕሬዚዳንት አብዲ የግል አማካሪ፣ የሶማሊ ክልል ወጣቶች ፕሬዚዳንትና የዚህ ዌብሳይት መስራች የሆነው፣ በአሁኑ ጊዜ በስዊድ አገር በስደት ላይ የሚገኘው ሰብአዊ መብት ተማጓቹ ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ አካራ ኒውስ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 በፕሬዚዳንቱ ትእዛዝ መከፈቱንና እርሱ የውብሳይቱ ሃላፊና መስራች ሆኖ መስራቱን ገልጿል። ዌብሳይቱ ለልዩ ሚሊሺያ ከተመደበው የመንግስት በጀት ተቀንሶ መቋቋሙን የሚገልጸው አብዱላሂ፣ በዌብሳይቱ ላይ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ገንዘብ የሚከፈለውም ከክልሉ ባጀት መሆኑን ይናገራል።
አብዱላሂ ዌብሳይቱን ሲመራ በነበረበት ወቅት ያገኛቸውን ቁልፍ የቪዲዮ ማስረጃዎች በመያዝ ከአገር ከወጣ በሁዋላ፣ ዌብሳይቱ በፕሬዚዳንቱ ታናሽ ወንድም በከድር ሙሃመድ ኡመር ስም እንዲመዘገብ መደረጉን አስረድቷል። በውብሳይቱ ላይ የሚወጣውን ማንኛውንም ጽሁፍ በቃል እየተናገረ የሚያስጽፈው ፕሬዚዳንቱ መሆኑን አብዱላሂ ገልጿል።
አቶ አብዲ፣ የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተቃውሞውን አቀነባብረውታል ብሎ እንደሚያምን የገለጸው አብዱላሂ ምክንያቱ ደግሞ ከወራት በፊት ከተፈጠረው ክፍፍል ጋር ይያያዛል ብሎአል። የክልሉ የምክር ቤት አባላት 7 ለ5 በመወሰን አቶ አብዲን ከስልጣን ለማውረድ ሙከራ ቢያደርጉም፣ አቶ አብዲ ሀረር በሚገኙት በወዳጃቸው በጄኔራል አብራሃ አማካኝነት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውሷል።
7ቱ የምክር ቤት አባላት አሁንም ተሰደው አዲስ አበባ እንደሚገኙ የሚገልጸው አብዱላሂ፣ በአቶ ሃይለማርያምና በአቶ ጌታቸው አሰፋ እንደሚደገፉም ገልጿል። አቶ አብዲ ለአቶ ሃይለማርያም ከፍተኛ ንቀት ያላቸው ሲሆን፣ ከእርሳቸው የሚመጣውን ትእዛዝ አይቀበሉም። አቶ አብዲ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሰላም እንደሆኑ ለማሳየት ሁለቱ ሰዎች ጎን ለጎን ቁጭ ብለው የሚያሳይ ፎርጅድ ፎቶግራፍ አሰርተው በዚሁ ዌብሳይት ላይ እንዲወጣ ካደረጉ በሁዋላ፣ በደረሰባቸው ነቀፋ እንዲነሳ አድርገዋል።
በአቶ አብዲ ጉዳይ በአንድ በኩል የደህንነት ሹሙና አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የመከላከያው ሹም ጄኔራል አብርሃ ተፋጠው እንደሚገኙ የሚገልጸው አብዱላሂ፣ እስካሁን ባለው ሂደት መከላከያ በማሸነፉ እነ አቶ ሃይለማርያም ምንም ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል ብሎአል።
ፕሬዚዳንቱ ወደ አገር ሲመለሱ ችግር አይገጥማቸውም ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ ደግሞ፣ የመከላከያ ባለስልጣናት እጃው ውስጥ እስካሉ ድረስ ምንም እንደማይሆኑ ይናገራል። ነገሮች ገፍተው ከመጡም ውብሳይቱ የእኔ አይደለም ሊሉ እንደሚችል አክሏል።
በመከላከያ አዛዦችና በአቶ አብዲ መካከል ያለው ግንኙነት ከግል ጥቅም ጋር የተሳሳረ መሆኑንም አብዱላሂ ይናገራል ። አቶ አብዲ ከኦብነግ ጋር የሚደረገው ድርድር ስልጣኔን አደጋ ውስጥ ይጥለዋል በሚል ስጋት አይቀበሉትም።
የአካራ ኒውስ ውብሳይት መተዳዳደሪያ ጽሁፍ እንደሚያሳየው ፣ ዌብሳይቱ ስለሶማሊ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ከባለስልጣኖች አንደበት የሚነገረውን እየተቀበለ እንደሚያሰራጭ ያትታል። በዌብሳይቱ ውስጥ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሚያደርጉዋቸው እንቅስቃሴዎችና የአሜሪካ ጉብኝታቸው በፎቶ ተደግፎ ቀርቧል።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ አቶ አብዲ በሚኒሶታ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞቻዋል። በተቃውሞው ላይ የሶማሊ ተወላጆች ኢትዮጵአውያንና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመሆን አቶ አብዱላሂ እናቶችን የሚገድል፣ ጨፍጫፊ፣ ገዳይ የሚሉ የተቃውሞ ድምጾችን አሰምተዋል
የሶማሊክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና በክልሉ የካቢኔ አባሎች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ በጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጽ/ቤት በተካሄደው አስቸኳይ ግምገማ ፣ ፕሬዚዳንቱ ፈጸሟቸው የተባሉ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ቀርበዋል።
ባለፈው ነሃሴ ወር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት በመሩት ግምገማ ላይ ም/ል ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የጠ/ሚኒስትሩ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አለቃ ጸጋየ በርሄ፣የደህንነትምክትልሹሙኢሳያስ ወጊዮርጊስ፣የምስራቅእዝዋናአዛዥጄኔራልአብርሃበቅጽልስማቸውኳታር፣የፌደራልፖሊስወንጀልመከላከልሃላፊ ጄ/ልግርማየመንጁስ፣አቶአዲሱለገሰ፣አቶአብዲመሃመድናየተለያዩየክልሉየካቢኔአባላትእንዲሁምሌሎች 2 የኢህአዴግከፍተኛአመራሮችም በተገኙበት
አቶ አብዲ መገምገማቸውን ኢሳት ዘግቦ ነበር።
አቶአብዲስልጣንከያዙጀምሮእሳቸውበሚመሩትሚሊሺያበብዙመቶዎችየሚቆጠሩሰዎችበተለያዩምክንያቶችመገደላቸውን፣በርካታ ሲቪሎችታስረው
ህክምናሳይገኙበቀላፎ፣በፌርፌርና
በሌሎችምእስርቤቶችእንዲሞቱ ማደረጋቸቸውን፣ ከመንግስት የተመደበውን ግዙፍ በጀት ለአንዳንድ የፌደራል ባለስልጣናት በተለይም ለጄ/ልአብርሃ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ ወቅቶች እንዲሰጣቸው በማድረግና
በተለያዩመንገዶች ከፍተኛ ገንዘብእንዲዘርፍማድረጋቸው፣ የአገርሽማግሌዎችንበመሰብሰብ በአንቀጽ 39 መሰረትየራሳችንንመንግስት ስለምናውጅለዚህታሪካዊክስተትራሳችሁንአዘጋጁ፣ፌደራልመንግስትምበውስጥጉዳያችንጣልቃ
መግባትአይችልምብለውመናገራቸው፣ የልዩ ፖሊስ አባላትና የጎሳ አባላሎቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ እንዲዘርፉ ማሰማራታቸው ፣በክልሉ የሚካሄዱትንትላልቅፕሮጀክቶችያለጫራታበመስጠትሆንብለውለብዝበዛአዘጋጅተዋልየሚሉ የግምገማ ነጥቦች
ቀርበውባቸው ነበር። በግምገማውወቅትጄ ልአብርሃበአቶአብዲላይየቀረበውንግምገማአጥብቀውመቃወማቸው ለአቶ አብዲ የስልጣን እድሜ መራዘም አስተዋጽኦ ማድረጉ በወቅቱ ተዘግቧል።



Tuesday, March 17, 2015

ልዩነታችን ጌጣችን፤ አንድነታችን ህልውናችን ነው

ኢትዮጵያ ስንል ብዙ የተለያዩ ዘውጎች፤ ብዙ የተለያዩ ቋነወቋዎችና ሀይማኖቶች በአንድነት ይዛና አስተሳስራ ብዙ ፈተ ናዎችን በማለፍ ለረጅም ዘመናት ህልውናዋን ጠብቃ የቆየች ሀገር መሆንዋ መታወቂያዋ ሀገር ማለት ነው። እንዳ ሳለ ፈችው ረጅም ዘመናት ሁሉ እንደየዘመኑ በህልውናዋ ላይ ይቃጣ የነበረውን ጥቃት እነዚያ በዘውጎች፤ በቋነወቋዎችና ሀይ ማኖቶች የተንቆጠቆጡት ልጆችዋ በአንድነት በመሰለፍ ብሎም ድል በመምታት ህልውናዋን አስጠብቀው መዝለቃቸው የነጻነት ሀገር የመሆን መለያዋ ምክንያቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው።

ይህ ልዩነታችንን ጌጡ አድርጎ ያስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነት በነፃነት የዘለቀ ህዝብ ከማድረግ አልፎ በአንድ ወቅት የስልጣኔ ምንጭና የአለማችን ሀያል ህዝብ ከመሆን ጫፍ አድርሶን እንደነበር አይዘነጋም። በዚያው ልክ ይህ በልዩነታችን ላይ የተገነባ አንድነታችን ሲላላ ህልውናችን ከገደል አፋፍ ላይ የደረሰበት ዘመንም በታሪካችን ውስጥ መታየቱ አልቀረም። “ዘመነ-መሳፍንት” በመባል የሚታወቀው ጥቁር የታሪካችን ክፍል አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ሌላው ዛሬ የምንገኝበት የወያኔ ዘረኛ ዘመን ነው። ትናንት በዘመነ መሳፍንት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር፤ ዛሬም በወያኔ ዘረኞች ዘመን ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ እንዲገኝ ተደርጓል። በአጭሩ ልዩነታችን ጌጣችን አንድነታችን ደግሞ የህልውናችን ማስጠበቂያ ዋነኛው ቁልፍ መሆኑን መገንዘብ ለማናም አያዳግትም።

ድምጻችን ይሰማ ትግሉን ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ሊያደርግ ነው

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች በመወከል ድምጹ እንዲሰማለት ጠይቆ፣ መለስ የተነፈገው ድምጻችን ይሰማ አመራሮቹን ለማስፈታትና ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ግፊት ለማድረግ እስካሁን ሲከተለው ከነበረው የትግል ስልት አንድ ደረጃ ከፍ ያለ የትግል ስልት ይፋ እንደሚያድርግ አስታውቋል።
ድምጻችን ይሰማ ” መብቴን ካላከበርክ እኔም..” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ህዝብ ሲመረው መብቴ ይከበርልኝ ከሚል ጩኸት መብቴን ካላከበርክ እኔም ወደ ሚል ዛቻ መሄዱ አይቀሬ ነው ብሎአል።
ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ “መብቴን ካላከበርክማ” ወደሚል የትግል ምእራፍ መሸጋገሩንየሚገልጸው ድምጻችን ይሰማ፣ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ስለሚወሰዱት እርምጃዎች መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል።
የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት አሁንም በፍትህ እጦት በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።


Monday, March 16, 2015

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ከሥራቸው ተባረዋል:: 

"ተወይኖብኛል" ይላሉ
"ዩኒቨርሲቲው እኛን harass ከሚያደርግ የተጭበረበር ዶክመንት ይዞ ፕሮፌሰር የሆነውን ሰውዬ (ቆስጠንጢኖስ በርሄ) ወዲያውኑ አታባርርም? ፀሓይ የሞቀው ውሸት እንደሆነ ግልጽ ሆኗል ብዙ ሰው ነው አንጀቱ የራሰው ልንገራችሁ እሱ አሁን ተዋርዶ መባረር ነበረበት"

"አሁንማ ጉድ ፈልቷል እኔ የዲግሪ ተማሪዎችን አቆሜ ነበር፣ ለሁለት ዓመታት:: በተገቢ ሁኔታ ያልተማሩ ልጆች ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ:: ተማሪዎች ሲወድቁ ደግሞ አትጣሏቸው C እና D ስጧቸው ይላሉ:: F ከሰጠህ አስተማሪ አንተ በደንብ ስላላስተማርክ ነው፣ በደንብ አስተምራችው...ሥራ ይበዛብሀል:: ስለዚህ C እና D እየሰጠህ ዝም ብለህ ማሳለፍ ነው:: ስለዚህ ይኼ አንድ ቦታ መቆም አለበት:: የትምህርት ሥርዓቱ ቀውስ ውስጥ ነው::"

"ትምህርት ቀውስ ውስጥ ገብቷል! ዝም ብሎ ቁጥር ...number...እነሱ በፖሊሲ 10ሺህ PHD, 50ሺ MA ይልሀል በ5 ዓመት... ከዚያ ይህን ያህል ተገበርን ይልሀል። እኔማ ተረከቡኝ ብያለሁ የሚረከበኝ አጣሁ:: ይሄ PHD የሚባል ስም... ዶክትሬቴን ውሰዱሉኝና አቶ በሉኝ ብያለሁ:: እባካችሁ ተዘከሩኝ "አቶ ዳኛቸው በሉኝ!"


ኢህአዴግ በመንግሥት በጀት ለካድሬዎችና አባላቱ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎችን የሚያሰለጥነው አካዳሚ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመው የአመራር አካዳሚ በመንግስት በጀት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ዙሮች 2ሺ 500 ያህል ከፍተኛ አመራሮችን፣ ከ30ሺ በላይ መካከለኛ አመራሮችን አሰልጥኗል፡፡

አካዳሚው ያለአንዳች ፈቃድ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ሲሰራ ከቆየ በሃላ በ2006 ዓ.ም በሚኒስትሮች ደንብ ቁጥር 321/2006 ተጠሪነቱ በቀጥታ ለጠ/ሚኒስትሩ በማድረግ መንግሥታዊ ተቋም ሆኖ ተቋቁሟል፡፡

Sunday, March 15, 2015

እንግሊዝ በኢትዮጵያ ያለው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አፈጻጸም ያሰጋኛል አለች

የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚል ተችታለች

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው የ2014 (እ.ኤ.አ.) የሰብዓዊ መብትና የዴሞክራሲ ሪፖርት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ኢትዮጵያ በምትፈጽማቸው ገደቦች ሥጋት እንደገባው አስታወቀ፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚልም ተችቷል፡፡

የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችና ሌሎች አካላት ሕጉ ተጠቅሶ የተከሰሱት የመሰብሰብና ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ለመጠቀም ሙከራ ሲያደርጉ እንደሆነ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

የዘንድሮ ምርጫ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነው.የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ

ባለፈው ታኅሳስ ወር 91ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዓመት ባስቆጠረው ድኅረ ቤተ መንግሥት ሕይወታቸው፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ጀምረዋቸው ስለነበሩ አገራዊ ጉዳዮችና ወቅታዊ አጀንዳዎች ጋር በተያያዘ ከሔኖክ ረታ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

 ሪፖርተር፡- እንደሚታወቀው እርስዎ በአካባቢ ጥበቃና በዱር እንስሳት አያያዝ በግልዎ የሚያደርጉት ጥረት አለ፡፡ ከሰሞኑ አንድ የኬንያ ሚዲያ የኢትዮጵያ አናብስት ቁጥር በአደገኛ ሁኔታ እየተመናመነ መምጣቱንና ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ታሪካዊ ቁርኝት ያለው የአንበሳ ዝርያ ደብዛው ሊጠፋ እንደሚችል ጠቁሞ ነበር፡፡ ምን ተሰማዎት?

Saturday, March 14, 2015

ወይዘሮ አዜብ መስፍን በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ ጀምረዋል::

መውደቂያው የደረሰው ወያኔ እርስ በርሱ መበላላት ጀምሯል: ወሳኝ ወቅት ላይ ነን ፤የደህንነት ሹሙ ጌታቸው ማለት እንደ ወይዘሮ አዜብ አነጋገር “…ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ..” እንደሆነ ሲታወቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወይዘሮ አዜብ በቤተሰቦቻቸው ስም ያቋቋሙት ድርጅት እና ያፈሩት ሃብት እና ንብረት ላይ ክትትል እንዲደረግ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቡድናቸውን ማዘዛቻው ወይዘሮዋ በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ መጀመራቸው
ወዳጆቻቸውን ተገን በማድረግ በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገቡ ከባድ እና ቀላል መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ቀረጥ ስለማይከፈልባችው ጥያቄ በአዜብ መስፍን ላይ ቢያስነሳም ወይዘሮዋ ከተጠየቅን አብረን ነው መጠየቅ ያለብን ሲሉ ከዚህ ቀደም መልስ መስጠታቸው እና ከዘረፋ ጋር ጋር የተያያዘ ጥቄዎች ሲነሳባቸው በጄኔራሎች ካኪ ስር መደበቅ ተግባራቸው መሆኑ ለደህንነት ፈላጭ ቆራጮ እንዳልተዋጠላቸው ታውቋል::

ከዚህ ቀደም በቤተመንግስቱ የውስጥ ሽኩቻ ውስጥ ቂም በቀል እንዳለባቸው የሚነግርላቸው የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው ወይዘሮ አዜብን አጥምዶ የሰው መሳቂያ ለማድረግ ከማሴር አልተቆጠቡን ሲሉ የወይዘሮዋ የቅርብ ሰዎች በምሬት ይናገረሉ:: ወዳጅ መሳይ ተናዳፊ እባብ ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ ብላ አዜብ የምትጠራው ጌታቸው በዘመዶቿ ስም ያፈራችውን ንብረት የመውረስ እና ሸጦ ገንዘቡን በሌላው እንደለመደው ከሃገር የማሻገር እቅድ እንደያዘ የቅርብ ወዳጆቿ አክለው ገልጸዋል:: በደህንነት ሰዉየውና በሴትየዋ መካከል ያለውን ቅራኔ ፈትቶ ጉዳዩን ለማረጋጋት አቶ በረከት ስምኦን እና ጄኔራል ሳሞራ ጥረት ላይ መሆናቸው ታውቋል::

በውጪና በውስጥ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ትልቅ ጫና የበዛበት ወያኔ ከሃገር እና ህዝብ ሃብት በተጨማሪ እርስ በርሱ መበላላት እና መዘራረፍ የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ ዘራፊ ስር አት ለማስወገድ በጋራ እና በአንድነት በመታገል የዜግነት ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን::


Friday, March 13, 2015

እንግሊዝ ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ማቋረጡዋን አስታወቀች

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉምበርግ የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እንግሊዝ በኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመደጎም ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ያቋረጠችው፣ መንግስት መጪውን ምርጫ ተከትሎ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን ማሰሩንና መዋካቡን በመቀጠሉ ነው።
የእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ጸሃፊ ጀስቲን ግሪኒንግ ፣ እንግሊዝ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑዋን ተከትሎ፣ ቀድም ብሎ ይሰጥ የነበረው የማህበራዊ አግልግሎት ድጋፍ እንደተቋረጠ ለእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው አስረድተዋል።

Thursday, March 12, 2015

በህወሓት ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎች ሁሉ ወደ እምቢተኝነት ይደጉ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን ይሰማ ኦርቶዶክሶች”፣ “ድምፃችን ይሰማ መምህራን”፣ “ድምፃችን ይሰማ ተማሪዎች”፣ … ወዘተ። በተለይ ሙስሊም ወገኖቻችን በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያሉ ሲወተውቱ ሦስት ተከታታይ ዓመታት አልፈዋል። ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በማለታቸው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
አቤቱታ የሚሰማ ጆሮ የሌለው አገዛዝ ሲገጥም ምን ይደረጋል? ለአቤቱታ አቅራቢው ያለው ምርጫ ከሁለት አንድ ነው። ወይ አቤቱታን እርግፍ አድርጎ ጥሎ በደልን ተቀብሎ “እህህ !” እያሉ መኖር፤ አሊያም “በቃኝ፣ እንቢ አልገዛም” ማለት፤ ሦስተኛ ምርጫ የለም።

አምስት የደህንነት አባላት ወደ ጨለማ እስር ቤት ተወረወሩ::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አምስት የደህንነት አባላት ወደ ጨለማ እስር ቤት ተወረወሩ::የመከላከያ እና የደህንነት ግምገማዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ::ቀጣዩ ግምገማ ከዛቻና ማስፈራራት ወደ ልመና ሊዞር ነው::ባለፉት ሳምንታት በመከላከያ ሰራዊት በምድር ጦር እና አየር ሃይል እንዲሁም በደህንነት መምሪያ ሲደረጉ የነበሩ ግምገማዎች በስፋት ቀጥለው አባሎቻቸውን እያሰሩ እና እያስፈላሩ በመጭው ሳምንቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::

በረከት ስምኦን ራሳቸውን ከምርጫ ክርክር አገለሉ

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአለማቀፍ ታዛቢዎችና በኢትዮጵያውያን በቂ ትኩረት ያልተሰጠውን የግንቦት 16 ቀን 2007 ምርጫ ክርክር የሚሳተፉለትን መሪዎች ሲያፈላል የነበረው ኢህአዴግ፣ ለመጀመሪያው ዙር የክርክር መድረክ የሚሆኑትን ሰዎች ሲመርጥ፣ አቶ በረከት ራሳቸውን አግልለዋል።
ኢህአዴግ 23 አመራሮችን ለክርክር በእቅድ የያዘ ቢሆንም፣ ከእነዚህ ወስጥ በመጀመሪያው ዙር መጣሪያውን ያለፉት አቶ ሬዲዋን ሁሴን እና አቶ ደሰታ አስፋው ብቻ ናቸው። 21ዱ አመራሮች ቀጥተኛ ተፎካካሪ መሆን አይችሉም ተብለዋል።
በሁለተኛው ዙር ማጣራት አቶ አባይ ፅሃየ ፣ካሳ ተክለብርሃን ፤ ተፈራ ደርበው ፤ሽመልስ ከማል እንዲያልፉ ተደርጓል። ኢህአዴግ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማህደር ሲያጠና ከርሞ ዛሬ በዝግ ለተከራካሪ አመራሮች ገለጻ እያደረገ ነው።
በመጀመሪያው ዙር በእጩነት ቀርበው አይመጥኑም፣ ኢህአዴግን ያዋርዱታል ከተባሉት ውስጥ አባ ዱላ ገመዳ፣ አስቴር ማሞ፣ ዘነቡ ታደሰ፣ ሙፈሪያት ከማል፣ ከበደ ጫኔ፣ ወልዱ ይምሰል፣አህመድ አብተው፣ ተመስገን ጥላሁን፣ አሊ ሲራጅ፣ ታደሰ ሃይሌ፣ ፍሬህይወት አያሌውና ብስራት ጋሻው ይገኙበታል።

ችሎቱን አሻንጉሊት ብለሃል የተባለው አብርሃ ደስታ ተጨማሪ 9 ወር ተፈረደበት * ፍርዱን ሲሰማ ለ3ኛ ጊዜ በማጨብጨብ አሻንጉሊቱን ችሎት “ደፈረ” -

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ለሦስተኛ ጊዜ ችሎት መድፈራቸው ታውቋል፡፡ በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ መጋቢት 3/2007 ዓ.ም ፍ/ቤት የቀረቡት አመራሮቹ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም በነበረው ችሎት ወቅት ችሎት ደፍራችኋል በሚል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽ እያንዳንዳቸው በ7 ወር እስር እንዲቀጡ ሲበየንባቸው ብይኑን በመቃወም ማጨብጨባቸውና ሳይፈቀድላቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በዕለቱም ድርጊታቸው ችሎት መድፈር ነው በሚል ጥፋተኛ ተብለው ነበር፡፡ በዛሬው ውሎው የቅጣት ውሳኔ የሰጠው ችሎቱ ለሦስተኛ ጊዜ በሦስቱ አመራሮች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ዳንኤል ሺበሽን ‹ብይኑን በመቃወም አጨብጭባችኋል› በሚል እያንዳንዳቸውን በ7 ወር እስራት፣ እንዲሁም ከማጨብጨብ በተጨማሪ ችሎቱን ‹አሻንጉሊት› ብሎ ሰድቧል የተባለው አብርሃ ደስታ ደግሞ በ9 ወር እስራት በድጋሜ ተቀጥተዋል፡፡ አመራሮቹ ዛሬም ለሦስተኛ ጊዜ ብይኑ ተሰምቶ እንዳለቀ በተቃውሞ በማጨብጨብ ለሦስተኛ ጊዜ ችሎቱን ‹ደፍረዋል›፡፡ ፍርድ ቤቱም አመራሮቹ አሁንም ጥፋት መፈጸማቸውን ገልጾ፣ ነገር ግን በይቅርታ እንዳለፋቸው በመግለጽ ድርጊታቸውን እንዲያስቡበት አስገንዝቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎ አቃቤ ህግ በ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን ላይ አሻሽሎ እንዳቀረበው የተነገረለትን ክስ ተቀብሏል፡፡ ተከሳሾች መጋቢት 10/2007 ዓ.ም የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡


Wednesday, March 11, 2015

‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

የአውሮፓ ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተወያየ

የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ከህብረቱ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት በተገኙበት ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹ በአምባሳደሮቻቸው እንዲሁም ቀሪዎቹ በምክትል አምባሳደሮቻቸው ተወክለው የተገኙ ሲሆን ተወካዮቹ ወቅታዊ የምርጫ ሂደት እንቅስቃሴና የሰማያዊን የምርጫ እንቅስቃሴ፣ በምርጫው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ የፓርቲው አማራጭ ፖሊሲዎች፣ የድርጅቱን ጥንካሬ፣ የአንድነት አባላት ወደሰማያዊ መምጣታቸው ለትግሉ የሚኖረው ትርጉምና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች በህገ ወጥ መንገድ እንደተሰረዙበት፣ የፓርቲው የቅስቀሳ መልዕክቶቹ ከ6 ጊዜ በላይ በሚዲያ እንዳይተላለፍ መከልከሉን፣ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ፣ እስራትና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው በምርጫ ሂደት ኢህአዴግ አፋኝነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊን መቀላቀላቸው ትግሉን እንደሚያጠናክረው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድነትና መኢአድ ላይ የተፈፀመው ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን እንዲሁም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በኃይል እያጠፋ ‹‹ከእኔ ውጭ አማራጭ የለም›› የሚል አቋሙን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳየት እንደሚፈልግ ለህብረቱ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

‹‹የአውሮፓ ህብረት ችግር የኢትዮጵያን ችግር በአውሮፓውያን ተቋማትና የስነ ልቦና ልክ ማየቱ ነው›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት ‹‹የተቃዋሚዎች አማራጭ ፖሊሲያቸው ምንድን ነው?›› በሚል የሚያነሱትን ተደጋጋሚ ጥያቄ አስታውሰው መደረጀትና መናገር ያልቻለውን የኢትዮጵያን ህዝብ በአውሮፓ ተቋም አይን አይቶ እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን ማንሳቱ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ብዙም እርባና እንደሌለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በእኛ አገር የፖለሲ አማራጭ ለማቅረብ አይቻልም፡፡ ሚዲያው በገዥው ፓርቲ የተያዘና የተቃዋሚዎችን ሀሳብ የማያስተናግድ ዝግ ሆኗል፡፡ እናንተ እንደምትገምቱት የፖሊሲ አማራጭ ለማቅረብ አመች ሁኔታዎች ቢኖሩ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ የተሻለ ምሁርራንና ሀሳብ ስላላቸው ዝርዝር ፖሊሲያቸውን ለማቅረብ አይቸገሩም ነበር፡፡›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ኢህአዴግ ‹‹ተቃዋሚዎች የተበታተኑና የተዳከሙ በመሆናቸው ለቀጠናው ሰላም አማራጩ እኔ ብቻ ነኝ›› ብሎ የአውሮፓ ህብረትን እንደሚያታልል የገለጹት ኢ/ር ይልቃል ‹‹ኢትዮጵያውያን ካላቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ማየት ስላልቻላችሁ ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል፡፡›› ሲሉ የአውሮፓ ህብረትን ወቅሰዋል፡፡


Monday, March 9, 2015

በኢትዮጵያ መንግሥት የሳይበር ጥቃት መፈፀሙ ይፋ ተደረገ

የኢትዮጵያ መንግስት የመረጃ ጠለፋ መፈጸሙን እንደገፋበት ሂዩማን ራይትስ ዎች ተናገረ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ዛሬ ይፋ አንዳደረገው ከሆነ መንግስት ቀስ በቀስ ጋዜጠኞችን ጸጥ ያደርጋል እንዲሁም የዲጂታል ጥቃት ይፈጽማል ሲል ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የመረጃ ስለላ ተቋም

ባለፈው አመት “ዘይ ኖው ኤቭሪቲንግ ዊ ዱ፤የኢንተርኔትና የቴሌኮም ስለላ በኢትዮጵያ” ሲል ቡድኑ ባወጣው ዘገባ የኢትዮጲያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የቴሌኮምና የመረጃ መረብ እያንዳንዱን ሚስጥራቸውን ይበረብራል ማለቱ አይዘነጋም፡፡

ዘንድሮም በተመሳሳይ መንግስት ይህን ድርጊት መፈጸሙን አጠናክሮ እንደቀጠለ የሚናገረው ቡድኑ በውጪ የሚኖሩ ነጻ ጋዜጠኞች ላይ ሳይቀር የሳይበር ጥቃት ይፈጽማል በማለት አትቷል፡፡

መሰረቱን በካናዳ ቶሮንቶ ያደረገ አንድ ገለልተኛ አጥኚ ቡድን ሰሞኑን በአንድ የሚዲያ ተቋም ላይ መንግስት የሳይበር ጥቃት መፈጸሙን ማረጋገጡን የሚገልጸው ሂዩማን ራይትስ ዎች ለኢትዮጵያ መንግስት የመረጃ መረብ መጥለፊያና ጥቃት መፈጸሚያ ምርቶችን የሚሸጡ አለም አቀፍ ኩባኒያዎች ድርጊቱን እንዲያጣሩ፤ድርጊቱን ፈጻሚው መንግስትም በአስቸኳይ ከድርጊቱ እንዲታቀብ አሳስቧል፡፡

ይህን የሂዩማን ራይትስዎች መረጃ ተከትሎ በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ባወጡት ዘገባ የኢትዮጵያን መንግስት አውግዘዋል፡፡

ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት ከአንድ የጣሊያን የደህንነት ተቋም በውጪ የሚኖሩ ጋዜጠኞችን ለመሰለል የሶውትዌር ምርት እንደገዛ በአንድ ገለልተኛ ቡድን ምርመራ መረጋገጡን በመጥቀስ ዘገባውን የሚጀምረው ማዘርቦርድ የተባለው የወሬ ምንጭ ይሁን እንጂ ዘንድሮም በተመሳሳይ መንግስት የሳይበር ጥቃቱን ቀጥሎበታል ሲል ያትታል፡፡ በዚህም ሰለባ ከሆኑት መካከል የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን(ኢሳት) እንዲሁም በውጭ የሚኖሩና በስራ ላይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች እንደሚገኙበት መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

ይህን በሚመለከት ተመሳሳይ ዘገባ ይዞ የወጣው ዋሽንግተን ፖስት በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግስት በውጪ ያሉ ነጻ ጋዜጠኞችን በሽብር ይከሳል አልፎ ተርፎም የሚያሰራጯቸውን የሚዲያ አገልግሎቶች ጃም በማድረግና በሳይበር ጥቃቶች ለማፈን ይሞክራል ማለቱን ድሬ ቲዩብ ዘግቧል፡፡


ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ኢህአዴግ›› የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው በላከው ደብዳቤ ‹‹በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም ግለሰብ ዕጩዎች ሊወዳደሩም ሆነ ሊመረጡም አይችሉም፡፡›› ሲል በኢህአዴግ ስም ዕጩዎች መመዝገባቸውን ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲው አክሎም ‹‹የግንባሩ ዕጩዎች በሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች የየትኛው አባል ፓርቲን መወከላቸው ሳይገለፅ ‹ኢህአዴግ› ብቻ እየተባሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ ዕጩዎች ‹የህወሓት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ኦህዴድ› አባላትና በተጨባጭም የእነዚህ አራት ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች መሆናቸው እየታወቀ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ በአሳሳች ሁኔታ ‹ኢህአዴግ› በሚባል የአንድ ውህድ ፓርቲ ዕጩ መስለው ቀርበዋል›› ብሏል፡፡ ይህም ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ህግን ያልተከተለ፣ ወጥነት የሚጎድለውና ህብረተሰቡንም ግራ የሚያጋባ እንዲሁም ለኢህአዴግ ያደላ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ እንደሚያመለክት ገልጾአል፡፡
‹‹ምርጫውን ያስፈፅማል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ጉልህ ስህተት ሲፈፀም በቸልታ እያለፈ ህገ ወጥነትን እየተባበረ እና እያበረታታ ነው›› ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ኢህአዴግ የሚባል ግለሰብ አባላት ያሉት ፓርቲ ሳይኖር በስሙ የተመዘገቡት ዕጩዎች በአስቸኳይ ከዕጩነታቸው እንዲሰረዙና ጉዳዩም ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ሲል ምርጫ ቦርድን አሳስቧል፡፡
የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች እንወክላቸዋለን በሚሉት አራቱም ክልሎች ዕጩዎችን በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስም ‹‹ህወሓት-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ብአዴን-ኢህአዴግ››፣ ‹‹ኦህዴድ-ኢህአዴግ›› እና ‹‹ደኢህዴን-ኢህአዴግ›› በሚል ያስመዘገቡ ሲሆን አዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች ‹‹ኢህአዴግ›› በሚል እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡


Sunday, March 8, 2015

ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

ክንፉ አሰፋ

አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!”

አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል።

Friday, March 6, 2015

በደልጊ ከተማ ከቤተክርስቲያን ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ የተከለለውን ቦታ 40 የሚሆኑ የምክር ቤት አባላትና ደጋፊዎቻቸው መከፋፈላቸው የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ፣ የካቲት 27 ጧት ላይ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ የከተማው ፖሊስ ጣቢያ ፣ መዘጋጃ ቤት፣ መስተዳድሩና የብአዴን ጽህፈት ቤት መስኮቶችና በሮች ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የመዘጋጃ ቤት ዘበኛም ተደብድበዋል።
በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበትን ተቃውሞ ለማብረድ ፖሊሶች ጥይት ከመተኮሳቸውም በተጨማሪ ሰለፈኞችን በዱላ ደብድበዋል።
ለተቃውሞው መነሻ የሆነው፣ ህዝቡን ወክለው ሲከራከሩ የነበሩት አቶ ተችሎ ካሴና አቶ ፈንታ መኳንንት ተይዘው መታሰራቸው ሲሆን፣ ህዝቡ መሪዎቻችንን ፍቱልን በማለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ፖሊስ ለህዝቡ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ህዝቡ
በጣቢያው ላይ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል
የህዝቡ ተቃውሞ እያየለ መምጣት ያሰጋው ፖሊስ፣ ሁለቱን የህዝብ ወኪሎች ከእስር ቤት በመልቀቅ፣ ችግሩን ለማብረድ ችሎአል። ህዝቡም ወኪሎቹን ተሸክሞ በከተማው በአሸናፊት ስሜት ሲጨፍር ማምሸቱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ከዚህ በሁዋላ የቤተ ክርስቲያኑዋ መሬት ይወሰዳል የሚል እምነት እንደሌላቸው የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የካቢኔ አባላቱ በዘረፋቸው የሚገፉበት ከሆነ ተመሳሳይ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል ብለዋል።


ሶስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጭ የወጣበት ድልድይ የጥራት ችግር አለበት ተባለ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራዉ 108 ሜትር ርዝመት እና አንድ ነጥብ ስድስት ሜትር ስፋት ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ በሃገሪቱ ብቸኛዉ የተንጠልጣይ ድልድይ በመስራት በሚታወቀው ሄልቬታስ ሲዊዝ ኢንተርኮኦፕሬሽን በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በይፋ ተመርቆ ስራ ቢጀምርም፣ በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ባለሙያዎች ድልድዩ የጥራት ችግር እንዳለበት መናገራቸው ነዋሪዎችንና በቦታው ተገኙ አመራሮችን አስደንግጧል፡፡
በአማራ ክልል ገጠር መንገድ ስራዎች ድርጅት የቁጥጥርና ክትትል ኬዝ

በአፋር ወጣቶች ለስለላ እየታፈሱ ነው

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፋር ነጻ አውጭ ድርጅቶች በአካባቢው እያደረሱት ያለው ተጽአኖ ያሰጋው መከላከያ፣ በአፋር የተለያዩ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው። ስማቸው ለደህንነት ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቁት ወላጆች በደርግ ጊዜ የቀረው አፈሳ በክልሉ እንደ አዲስ መጀመሩን ተናግረዋል።

በርካታ ወጣቶች አፈና በመፍራት ጫካ መግባታቸውንም ነዋሪዎች አክለዋል። አርዱፍ፣ አፋር ጋድሌና የአፍዴራ ወጣቶች በቅርቡ ግንባር መፍጠራቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ክፍል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።


የአድዋ ድልን እያከበርን ለዛሬ ነፃነታች ቃል እንግባ!


መቶ አስራ ዘጠነኛውን የአድዋ ድል በዓል እየዘከርን እንገኛለን። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም ቀደምቶቻችን በርካታ የውስጥና የውጭ ችግሮች ነበሩባቸው። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም በመካከላቸው የሀሳብና የጥቅም ልዩነቶች ነበሩ። ያም ሆኖ ግን ቀደምቶቻችን በአገር ነፃነት ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ መግባባት ላይ መድረስ በመቻላቸው በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችና ድርጅት የተጠናከረውን የአውሮፓ ጦር በጥቁር የጦር አዛዦችና ተዋጊዎች መመከት ቻሉ። ከአድዋ በፊት አፍሪቃ በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ አውሮፓዊያን የተሸነፉባቸው ተናጠል አውደ ውጊያዎች ነበሩ፤ ጦርነትን ሲሸነፉ ግን አድዋ የመጀሪያው ነው። በዚህም ምክንያት ነው የአድዋ ድል የአፍሪቃውያን ከዚያም አልፎ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ድል ተደርጎ የሚወሰደው።ዛሬ ግን እኛ ያኔ የነበሩት አያትና ቅድመ አያቶቻችን እደረሱበት የመግባባት ደረጃ ላይ መድረስ ባለመቻላችን አገር በቀሉን ቅኝ ገዢ – ህወሓትን – ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ ማውረድ አቅቶን አገራችንና ሕዝቧን ከባዕድ በባሰ ሁኔታ እያዋረደ በመግዛት ላይ ይገኛል።

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አበል ካልተሰጠን ፍርድ ቤት አንቀርብም አሉ

የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከሳሽ ኣቃቤ እና ህግ በተከሳሽ አቶ ኣስገደ ገ/ሥላሴ መካከል ሲደረግ በነበረው ክርክር ለምስክርነት የተጠሩት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊቀርቡ ባለመቻካቸው በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ቢታዘዝም፤ ባለስልጣናቱ ከለመዱት ምቹ ህይወት አኳያ ማቅረብ ሳይቻል ቀረ።
የህወሀት የደህንነት ሰራተኛው ብስራት አማረ የመሰረተባቸውን ክስ ተከትሎ ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲከራከሩ የቆዩት የቀድሞው የህወሀት ታጋይና የአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ አስገደ ገብረስላሴ ላይ ክሳቸውን እንዲከላከሉ በፍርድ ቤት ብይን መሰጠቱ ይታወቃል።

ተዋቂው ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ የህዝቡን ትግል ተቀላቀለ !

ጋዜጠኛው በኢትዮጵያዊነቱ አያሌ በደሎች እንደ ተፈጸሙበት ያወጋል ! በተለይ ይላል ጋዚጠኛ አለምነህ ዋሴ ፍትህ እኩልነት በሌለባት ሃገሬ ጋዜጠኛ ርዩት ዓለሙ ላይ የተፈፀመው ኢሰባዊ ድርጊት ከሁሉም በላይ ከህሊናው ሊጠፋ የማይችል ዘግናኝና አረምኔያዊ ድርጊት መሆኑን ይገልጻል ። ጋዜጠኛው ልጆቹን ከማሳደግ ባሻገር ሃገሩ ላይ ሲኖር ደስተኛ እንዳ ልነበረ በመጥቀስ ክእንግዲ አለ ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ « ፍትህ እኩልነትና ነጻነት እስኪሰፍን » ሃገር አለኝ ብዬ ፊቴን ወደ ኢትዮጵያ አልዞርም ብሏል ። ጋዜጠኛው ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጀት ገለልተኛ ሆኖ ወገኑን ማገልገል እንዳልቻለና የገዢው ስረአት ወሬ… አቀባይ ሳይሆኑ ገለልተኛ ሆኖ በነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰርቶ መኖር ለህልውና አደገኛ መሆኑን የራሱን ተሞክሮ በመጥቀስ ያብራራል። በስራው ላይ ይደረግበት በነበረ ጫና የማስታወቂያ ስራዎቹ ለአየር እንዳይበቁ በደል እስከመፈጸምና በሙያው በቀን 10 በር ብቻ ተከፍሎት እንዲሰራ የተገደደበት አጋጣሚ እንደነበረ ለኢሳት በሰጠው መረጃ አጋልጦል። ጋዜጠኛው በአሁኑ ሰዓት አስራኤል ውስጥ ስደት ቤቴ ብሎ መኖር የጀመረ ሲሆን ለኢሳት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ ከኢህአ ዴግ መንግስት ባለስልጣናት በኩል ምንም የተባለ ነገር ባይኖረም ጋዜጠኛው ወደ ሶስተኛ ሃገር ካልተሸጋገረ የደህነት ሁኔታው እንደ ሚያሰጋቸው አይሌ ኢትዮጵያውያን ይገልጻሉ። መንግስት ጋዜጠኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተስፋ መቁረጥ የሚሉ እንዚህ ታዛቢዎች ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ከተዋቂው ጋዜጠና ዳሪዎስ ሞዴና ነጋሽ፡መሃመድ ቀጥሎ የጋዜጠኛ አለምንህ ድምጹ በተፈጥሮ የህዝብን ልብ ሰብሮ የመግባት ሃይል ስላለው ምናልባት መንግስት ደልሎ አሊያም በሃይል ወደ ሃገር ሊመልሰው እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። ኢትዮጵያን ሃግሬ ጅዳ በዋዲ


Wednesday, March 4, 2015

አድዋ እና ደደቢት የተቀመጡበት ሰባራ ሚዛን

ወርሃ የካቲት በሃገራችን በርከት ያሉ ወሳኝ ታሪካዊ ሁነቶች የተካሄዱባት ወር ነች፡፡ከሃገራችን አልፎ አፍሪካን፣ ከዛም ገፍቶ የላቲን አሜሪካን ጥቁሮችን ያኮራው፣ በአጠቃላይ በነጭ ቅኝ አገዛዝ ስር ለነበሩ ሁሉ የነፃነት ተስፋ ለመሆን የበቃው የአድዋ ድል የተከወነው በዚች ታሪካዊ ወር በየካቲት ነው፡፡አብረሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ፋሽስቱን ግራዚያኒን ለመግደል ባደረጉት ሙከራ በበቀል የነደደው የፋሽስት ኢጣሊያ አስተዳደር ኢትዮጵያዊ ምሁራንን እያሰሰ፣ ድሆችን በእህል ውሃ እየደለለ ሰብስቦ የከበደች የበቀል ክንዱን ያሳረፈባቸውም በዚሁ በየካቲት ወር ነበር፡፡ በሃገራችን ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያለው የመሬት ላራሹ ጥያቄ የቀረበበትም በየካቲት 18 ነበር፡፡ ‘ብሶት ወልዶን፣ ምሬት አብርሮን አስራ አንድ ሆነን፤ አራት ጠብመንጃ፣አንድ አሮጌ ሽጉጥ እና አንድ ቢለዋ ተማምነን፤ ተጉዘን ተጉዘን ደደቢት በረሃ የደረስነው የካቲት 11 ቀን ነበር’ የሚሉት ህወሃቶችም ‘ደማቅ ታሪክ ፃፍንባት’ ሲሉ ይህችን ቀን ይዘክሯታል፡፡

Tuesday, March 3, 2015

ም/ል ጠ/ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ ቡድኖችን ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡

አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ በማሳየት አቶ ደመቀ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል፡፡

የጊዮርጊስ ጨዋታ ወደ ባህርዳር የተላለፈው-የህውሃት 40ኛ አመት ዝግጅትን ለማካሄድ ሲባል አዲስ አበባን ከሁሉም ትኩረት ከሚስቡ ነገሮች ነጻ በማድረግ ነዋሪው በሙሉ ልቡ የዕለቱን ዝግጅት በቴሌቪዢን መስኮት እንዲመለከት በማሰብ እንደሆነ ከአዲስ አበባ ቡድናቸውን ለመደገፍ የመጡ ተመልካቾች ለዘጋቢያችን ገልጸውላታል። በተሰጠው አስተያየት ዙሪያ የፌደሬሽኑን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5040#sthash.kxqHCXDd.dpuf


አየር ሐይልን ከድቶ በይፋ ግንቦት 7ን የተቀላቀለው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ታናሽ ወንድም ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ መሆኑ ታወቀ

“ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነዋል” በማለት የኢትዮጵያ አየር ሃይልን እና የገዢውን ፓርቲ አካሄድ በመቃወም ግንቦት 7ን መቀላቀላቸው የሚታወሠው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች አደጋ ላይ ይገኛሉ፡፡
ኮተቤ 02 አካባቢ በተለምዶ ቆርቆሮ ሠፈር እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የሚኖሩት የሻለቃ አክሊሉ ቤተሠቦች ሻለቃ አክሊሉ በተለያዩ ምክንያቶች ግንቦት 7ን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በቤተሠቡ ላይ የሚካሄደው ምርመራ እና ክትትል በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በተለይም በታናሽ ወንድሙ ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡
ይህንን ዜና በኢሜይል የላከልኝ ወጣት እንደገለፀው ከሆነ ወጣት ሠይፈ መዘነ ማዕከላዊ እንደሚገኝ ያወቁት ቤተሠቦቹ ወደስፍራው በማቅናት ለመጠየቅ ቢሞክሩም በፖሊሶች መከልከላቸውንና ቤተሠቦቹም እስረኛን መጠየቅ መብታቸው መሆኑን ሲገልፁ ፖሊሶች ሠይፈ አዘነ እስረኛ ሣይሆን አሸባሪ ነው በማለት መልሠዋቸዋል፡፡
ሻለቃ አክሊሉ አዘነ ሴፕቴምበር 2013 ኢሳት ላይ ቀርቦ አየር ሐይል እንደገና ካልተዋቀረ አገርን መከላከል የሚችልበት ደረጃ እንደማይገኝ የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነው እንደሚአገለግሉ፣ አብራሪ የሚባሉት በሚሊሻ ደረጃ መገኘታቸው፣ የዘር መድልዎ እንደሚደረግ፣ የህወሃት ድጋፍ ያላቸው ብቻ የሚስተናገዱበት መሆኑ፣ ከችግሮቹ በግንባር የሚገለጹ ናቸው ሲሉ መግለፃቸው ይታወሳል።
ሻለቃ አክሊሉ ላለፉት 15 ዓመታት ያህል በታማኝነት የኢትዮጵያ ህዝብን ያገለገሉ ሲሆን በአየር ሃይል ውስጥ የሚሰራው የቡድን፣ የዘርና አጠቃላኢ አለው አሰራር ብልሹነት አሳሳቢ በመሆኑ አገር ጥለው በመውጣት ከሶስት ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ግንቦት7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን በወቅቱ ገልፀው ነበር።


Monday, March 2, 2015

ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ
በአበበ ገላው
(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።

የግንቦቱን ምርጫ ለመታዘብ ከመንግስት ግብዣ እንዳልቀረበለት የአውሮፓ ህብረት ገለፀ

የግንቦቱን ምርጫ ለመታዘብ ከመንግስት ግብዣ እንዳልቀረበለት የገለፀው የአውሮፓ ህብረት፣ ባለፉት ሁለት ምርጫዎች በታዛቢዎቼ የቀረቡ ሪፖርቶች በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውም ከታዛቢነት እንድርቅ ገፋፍቶኛል አለ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በ1997 እና 2002 ምርጫዎች የህብረቱን የትዝብት ሪፖርት ሙሉ ለሙሉ ሳይቀበለው መቅረቱ፤ ለዘንድሮ ምርጫ ሌላ የታዛቢ ቡድን የማሠማራትን ጥቅም አጣራጣሪ እንዲሆን አድርጓል ብሏል – የአውሮፓ ህብረት፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ የአውሮፓ ህብረት በታዛቢነት አለመሳተፉ በምርጫው ተአማኒነት ላይ የሚያወጣው ለውጥ የለም ብሏል፡፡
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የአውሮፓ ህብረት በራሱ ምክንያት ምርጫውን እንደማይታዘብ ማሣወቁን ጠቁመው፤ ምርጫውን የአፍሪካ ህብረት፣ የአገር ውስጥ ሲቪል ማህበራትና ተቋማት ይታዘቡታል ብለዋል፡፡
በአና ጐሜዝ የሚመራው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን በ97 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ ክፉኛ በመተቸቱ ከፍተኛ ውዝግብ ከመፈጠሩም በተጨማሪ፣ በ2002 ምርጫም ህብረቱ የምርጫው እለት ሂደቱ መልካም የነበረ መሆኑን ከገለፀ በኋላ፣ በጥቅሉ ምርጫው በአለማቀፍ መመዘኛዎች ሲፈተሽ ግን በርካታ ጉድለቶች አሉበት በማለት ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡


Sunday, March 1, 2015

እንደግብጻውያን ገዳማት እና ሀገራችን እንዳይፈርሱ ዘብ እንቁም (ከ ዘአብርሃም ብሎግ)

በአለም መፋረጃ ወቅት ላይ እንገኛለን። ካልጠፋ ቦታ ለሺ ዘመናት ስነምህዳሩን ጠብቆ ተከብሮ የኖረውን የዋልድባ ገዳምን ማረስ እንዲሁም የዝቋላ ገዳም ላይ እንውጣና ክርስትና ያልሆነ ሌላ እምነት /የእሬቻ በዓልን/ እናክብረበት  ማለት  ፍርጃ እንጂ ምን ይባላል። ከድሮ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ ታቦት ፤መስቀል፤ ወድ የብራና መጽሃፍት ሲሰርቁ ኖረው አሁን ደሞ  የሁለት የተለያዩ ዕምነት ተከታዮችን ለማጣላት ጀመሩ።

በኢትዮጵያ አብያተ ክርስትያናት ላይ ብቻ ሳይሆን  ጥንት ጳጳስ ትልክልን የነበረችው የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የአባ መቃርዮስ ገዳምም እንደዋልድባ ገዳም ካልታረሰ ተብሎ ተፈርዶበታል። ገዳሙ በ360ዓም ኣካባቢ በታላቁ ኣባት ቅዱስ መቃርስ የተመሰረተና ታዋቂዎቹ የቤተክርስቲያን ኣባቶች  እንደ ሙሴ ጸሊም፥ዮሃንስ ሓጺር፥ የ አሌክሳንድሪያው ቅዱስ መቃርስ የመሳሰሉት ኣባቶች  ፈለጋቸውን መከተል የጀመሩበት ነው።።እኚሕ ኣባ መቃርስ ከግብጽ አልፎ ለ ኢትዮጵያ፥ ለግሪክ፥ ለፍልስጤም፥ ለአርመን፥ለእስያውያን፥ለስፔን፥ለጣልያን  ሰዎች ምንኩስናን ያሳዩ  ከአራት ሺህ  በላይ ተከታዮች ያፈሩ  መንፈሳዊ አባት መሆናቸው በሰፊው ተጽፏል።