Thursday, July 31, 2014

አቶ በረከት ስምዖን ከሆስፒታል መውጣታቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያን ሃገሬ ጅዳ በዋዲ

ሰሞኑንን ጅዳ ሳውዲ አረቢያ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩት አቶ በረከት ስሞኦን ሞቱ እይተባለ የሚናፈሰው ዜና ትክለኛ አለመሆኑን የሚገልጹት ምጮች ። የመንግስት ባለስልጣኑ ዛሬ ማምሻውን ከሆስፒታል ወጥተው ሼክ አላሙዲን ወደ አዘጋጁላቸው ሆቴል «ማረፊያ» ማቅናታቸውን አረጋግጠዋል።

እሁድ ለሊት በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በሚስጠር የገቡት እኚሕ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የልባቸውን የደም ቧንቧ ለማስፋት የተደረገው ህክምና ስኬታማ እና ለክፉ ችግር የማይሰጣቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ምንጮች ቢገልጹም የባለስልጣኑ የሰውነት አቋም ከትጎሳቀለው እና ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የጠቆረው ፊታቸው ገጽታ ሰውነታቸው ውስጥ መልካም ነገር እንደሌለ ያመላክት እንደነበር በአካል ያዮቸው የአይን እማኞች አቶ በረከት በቀርብ ቀን ወደ ሃገር ቤት አሊያም ለተሻለ ህክምና ወደ አውሮፓ ለማቅናት እቀድ እንዳላቸው ገልጸዋል። ዛሬ ረፋዱ ላይ አቶ በረከት ከሚያገግሙበት ሆስፒታል ለቀው ከመውጣታቸው ቀደም ብሎ ለጉብኘት ወደ ሆስፒታሉ አቅንተው የነበሩ ምንጮች በአካባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳልነበረ እና ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የሚገመቱ ነጭ ለባሾች ሆስፒታሉ አካባቢ መታየታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ከአቶ በረከት ስሞኦን ጋር የመጡት የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በዝግጀት ላይ መሆናቸውን እነዚሁ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ። የአቶ በረከት ስሞኦን የጤንነት ሁኔታ በተመለከት ከጅዳው የኢትዮጵያ ቆንሳል ጽ/ቤት መረጃ ለማግኘት ያድረኩት ሙከራ ባይሳካም ለዕረፍት ሀገርቤት የሄዱትን ቆንስላ ሸሪፈን ተከተው ወ/ሮ ሙንተሃ ወደተጠቀሰው ሆስፒታል ሰው እየላኩ የኚህን ባለስልጣን የጤነነት ሁኔታ በቀርብ በመከታተል ላይ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ባለስልጣኑ የሚገኙበትን የጤና ሁኔታ ካረፉበት ሁቴል የምናገኘውኝ መረጃ እይተከታተለን ለማቅረብ ይሞከራል::


የተደራጁ ወንበዴዎች ለመፍጠር እየፈለጉ ያሉትን ብዥታ ለማጥራት (ዳንኤል ተፈራ)

ከዳንኤል ተፈራ


ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ እሱም ውህደት ነው፡፡ የአንድነት/መኢአድ ውህደት ወሳኝና መሰረታዊ ድርድሮችን አልፎ የቅድመ ውህደት ፊርማው ከተቀመጠም ከወር በላይ ሆነው፡፡ከፊርማው በኋላ ውህደት አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሮ በአጭር ጊዜ ነገሮችን መልክ ለማስያስ የቻለ ሲሆን ውህደቱም የሁለቱ መስራች የጉባዔ አባላት በተገኙበት ነሐሴ 3 እና 4 ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ታዲያ ከመስራች ጉባዔው አስቀድሞ ሁለቱ ፓርቲዎች በተናጠል ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት የውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም፤ ለውድድር የሚቀርብ እጩ ፕሬዘዳንት መምረጥ፣ አዲስ ስያሜ በመጠቆም እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት ይጠናቀቃል፡፡ በነገራችን ላይ የተናጠሉ ጉባዔ ስራውን የሚጀምረው አዲሱን የጋራ ደንብ በማፅደቅ ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ውህደቱን ተቀበለው የሚባለው ደንብና ፕሮግራሙን ሲያፀድቅ ይሆናል፡፡

የአዲስጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ተጨማሪ የ5 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባት

መኖሪያ ቤቷ በፖሊስ ተበርብሯል

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአንዋር መስጂድ በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የታሰረችው የአዲስጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ሐሙስ ሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም ሜክሲኮ በሚገኘው በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምድብ ችሎት ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር ቀርባለች።
ምርመራውን በማጣራት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ባለፈው ሳምንት የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት ወደአዚዛ መኖሪያ ቤት ተጉዞ ብርበራ ማድረጉ ታውቋል። በዚህ ብርበራ ፖሊስ አዚዛን በጥርጣሬ ከያዘበት ጉዳይ ጋር ተያያዠነት ያለው ማስረጃ እንዳላገኘ ነው ፎቶ ጋዜጠኛዋ የተናገረችው።
ጉዳዩን በማጣራት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ክፍል አዚዛን ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ያቀረባት ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችለው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ግን አምስት ቀን ብቻ በመፍቀድ ለማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አዚዛና ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች እንዲቀርቡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በዕለቱ የተጠርጣሪዎቹን የፍርድ ሂደት ለመከታተል በርካታ ግለሰቦችና ቤተሰቦቻቸው የተገኙ ቢሆንም ችሎቱ ግን በዝግ ተካሂዷል።
ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሰየማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ችሎት አርፍዶ ነበር የተሰየመው።ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ በፍርድ ቤቱ ከመፈቀዱ በቀር አዚዛ በችሎቱ የተጠየቀችው ነገር እንዳልነበር ነው የተናገረችው።
በስፍራው ለስራ ከመገኘቴ በቀር በፖሊስ ሊያሳስረኝ የሚያስችል ምንም የወንጀል ድርጊት አልፈፀምኩም የምትለው ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሃመድ ምንም አይነት ጥፋት ለመፈጸሟ ማስረጃ ባይቀርብባትም ፖሊስ ለቀጣይ 5 ቀናት በእስር ላይ እንድትቆይ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።
አዚዛ እስካሁን በፖሊስ የቀረበባት እና የተጠረጠረችበትን ጥፋት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለመኖሩ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው የጊዜ ቀጠሮ በነጻ ሊያሰናብታት አለያም በዋስ ሊፈታት እንደሚችል ያላትን ተስፋ ለባልደረቦቿ ተናግራለች።

አዚዛ በሚቀጥለው ቀጠሮ ፍርድ ቤት ስትቀርብ የእስር ቆይታዋ 18 ቀናት ይሆናል ማለት ነው።

ሸራተን ሆቴል ብዛት ያላቸውን ሰራተኞቹን አባረረ

በሼህ አላሙዲን ሜድሮክ ኩባንያ ስር የሚገኘው ሸራተን አዲስ ሆቴል አስተዳደር ከሰራተኛ ማህበሩ ጋር ለአመታት የዘለቀ ግጭት ውስጥ መክረሙን የሚያስታውሱት ምንጮች በዛሬው ዕለት አስተዳደሩ የማህበሩን አመራሮች ጨምሮ በስራ ገበታቸው ተገኝተው የነበሩ ብዛት ያላቸውን ሰራተኞች ‹‹ሆቴሉ ከእናንተ ጋር የነበረውን የስራ ኮንትራት አቋርጧል››የሚል ወረቀት በመስጠት ከ15 ዓመታት ያላነሰ ድርጅቱን ያገለገሉ ሰራተኞቹን ማባረሩ ታውቋል፡፡
የስራ ዩኒፎርም ለብሰው ወደ ስራቸው ለመግባት ይዘጋጁ የነበሩት ሰራተኞች ወደ ቢሮ ተጠርተው ወረቀቱን መቀበላቸውን እንዲፈርሙ እየተደረጉና በሆቴሉ የጥበቃ ሰራተኞች ታጅበው ግቢውን እንዲለቁ መደረጋቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡
መረጃውን ተከትሎ ወደ ሆቴሉ አስተዳደር ስልክ ብደውልም ሃላፊ የተሰኙት ሰው ስማቸውንና በሆቴሉ ውስጥ ያላቸውን የስራ ድርሻ ጨምሮ ድንገተኛው የሰራተኛ ስንብት ስለመፈጸሙ ወይም ስላለመፈጸሙ ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑልኝ ቀርተዋል፡፡


የኢትዮጵያ ቴሌኮም ችግር ኔትወርክ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ሲስተሙ ነው ተባለ

‹‹ከቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ችግሮች እየተስተዋሉ ነው›› ኢትዮ ቴሌኮም

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የቻይናው ህዋዌ ኩባንያ ለኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ሥራዎችን እየሠራ ቢሆንም፣ ቀደም ብሎ ይታወቅ ከነበረው የኔትወርክ ችግር በተጨማሪ ሌሎች ሲስተሞችም ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን ተጠቃሚዎች እየገለጹ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ በትግበራ ላይ ካለው የቴሌኮም ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ችግሮች መኖራቸውን አምኖ፣ ቀደም ብሎ ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ማስታወቁን በማስታወስ፣ የተጋነነ ችግር ባለመሆኑ በቅርብ ቀን ሁሉም ነገር እንደሚስተካከል ገልጿል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች እንደገለጹት፣ የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ከአንድ አገር ለመጡት ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ማለትም ዜድቲኢና ሁዋዌ ሲሰጥ ጥሩ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተስፋ ቢያደርጉም፣ አገልግሎቱ ከሳምንታት ያለፈ አልሆነም፡፡ ሁዋዌ የኔትወርክ ችግርን ለመቅረፍ ሥራውን እንደጀመረ በተለይ ‹‹ኖኪያ ኔትወርክ ኤርያ›› በሚባሉት አካባቢዎች ችግሩ ለጊዜው በመፈታቱ ደስታ ተሰምቷቸው እንደነበር የገለጹት ደንበኞች፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊዎች በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰኔ 2006 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የአዲስ አበባ ኔትወርክ ችግር መቶ በመቶ እንደሚቀረፍ ሲገለጽ፣ ደስታቸው እጥፍ ድርብ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

የኃላፊዎቹን ገለጻ በትክክል መስማት አለመስማታቸውን እስከሚጠራጠሩ ድረስ፣ መቶ በመቶ የኔትወርክ ችግር ይቀርፋል በተባለበት ወር ሙሉ በሙሉ ባይሆንም፣ ከፍተኛ የሆነ የኔትወርክ ችግር ተባብሶ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡

‹‹ፈጣን የኔትወርክ አገልግሎት ለማግኘት 3Gን ተጠቀሙ›› የሚለውን የቴሌኮም ማስታወቂያ ተከትለውና በአገልግሎቱ ተማምነው የ‹‹3G›› አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚገልጹት ደንበኞች፣ የሞሉት ገንዘብ ተጠቅመውበት ሳይሆን ስልካቸው ሥራ ላይ ሳይውል ሒሳባቸው በነፃ መወሰዱ ችግራቸውን እንዳባባሰው ይናገራሉ፡፡

የችግሩን ሁኔታ ለማስረዳት በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችና ዋና መሥሪያ ቤት ቢሄዱም፣ እንኳን ችግራቸውን የሚያዳምጣቸው ቀርቶ በአግባቡ የሚያስተናግዳቸው በማጣታቸው አዝነው መመለሳቸውን ደንበኞች ገልጸዋል፡፡ ችግሩ በተለይ በሐምሌ ወር ቀጥሎ መባባሱንና የኔትወርክ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮ ቴሌኮም ለተጠቃሚዎች (ደንበኞች) የለቀቃቸው የገንዘብ መሙያ፣ ማስተላለፊያ፣ ቀሪ ሒሳብ ማወቂያ ሲስተሞችና በአጠቃላይ ደውሎ መገናኘት አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

የቫውቸር ካርድ ገዝተው ለመሙላት ሲታገሉ አልገባ ያላቸው ደንበኞች፣ ባለሱቆች ችግሩን ያመጡት ይመስል ከእነሱ ጋር ግብግብ ላይ መክረማቸውንም አውስተዋል፡፡ በመሆኑም የሚመለከተው የመንግሥት አካል ችግሩን ተገንዝቦና አጣርቶ መፍትሔ የሚመጣበትን መንገድ ቢያመቻች የተሻለ መሆኑንና የኋሊት ከመሄድ እንዲያድናቸው የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጠይቀዋል፡፡

ደንበኞቹ ያነሷቸው ችግሮች በከፊል መፈጠራቸውን ያመነው ኢትዮ ቴሌኮም ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የሚታዩትን አንዳንድ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡

በትግበራ ላይ ካለው የቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ ጋር በተያያዘ፣ አዲሱን ሲስተም ከነባሩ ጋር በማጣጣም የትግበራ ሒደት በኢቪዲኦ፣ ዋን ኤክስ (1X) አገልግሎትና በካርድ መሙላት ዙሪያ የተወሰኑ ችግሮች እየተስተዋሉ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ችግሮቹ የኢቪዲኦና ዋን ኤክስ፣ የሲዲኤምኤ ዳታ አገልግሎት መቆራረጥ፣ ከሽያጭ በኋላ የሚስተናገድ ሲም መቀየር፣ የጠፋ ሲም ማዘጋት፣ የተጓዳኝ አገልግሎቶች ትዕዛዝ በሲስተም ቶሎ ያለማለቅና ሌሎችም ችግሮች መሆናቸውን የጠቀሰው ኢትዮ ቴሌኮም፣ ያልተለዩትን ትዕዛዞች በመለየት በየ24 ሰዓት በደንበኛው አካውንት ላይ በየዕለቱ እየተሞሉ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ችግሮቹን ለመፍታት የቴክኒክ ቡድን አቋቁሞ በመሥራት ላይ መሆኑን የገለጸው ኢትዮ ቴሌኮም፣ ደንበኞች ችግሮቹ መኖራቸውን ተገንዝበው የማስተካከያ ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቋል፡፡


በጋምቤላ በመዥንገርና በደገኞች መካከል ግጭት ተፈጠረ

-17 ሰዎች መገደላቸው የተሰማ ቢሆንም መንግሥት ሕይወት አልጠፋም አለ

በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መዥንገር ዞን የሪ በተሰኘ ቦታ ላይ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተከሰተ ግጭት 17 ሰዎች መገደላቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡

መንግሥት ግን በግጭቱ ጥቂት ሰዎች ቢፈናቀሉም የአንድም ሰው ሕይወት እንዳልጠፋ ገልጿል፡፡

የዓይን እማኞች ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ የዞኑ ቀደምት ነዋሪዎች የሆኑት የመዥንገር ብሔር አባላት በአካባቢው ሠፍረው የሚገኙትን በአብዛኛው የአማራና የትግራይ ተወላጆች የሆኑትንና ‹‹ደገኛ›› ወይም ‹‹ሐበሻ›› በመባል የሚታወቁትን ነዋሪዎች ‹‹ከአካባቢው ይውጡልን›› በማለት ቅሬታ ማቅረባቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለመደ ሆኗል፡፡

ሦስት የኢቴቪ ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሥራቸው ለቀ

በ ፍሬው አበበ (ሰንደቅ ጋዜጣ)በርካታ ጋዜጠኞች በለውጡ ደስተኞች ሆነዋልየኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (የቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት) ሦስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቅርቡ ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የወቅታዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ አሸብር ጌትነት፣ የትምህርታዊ ፕሮግራሞች ክፍል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ተመስገን ገ/ህይወት፣ የመዝናኛ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ፍቅር ይልቃል በወራት ልዩነት ድርጅቱን መልቀቃቸው ታውቋል።የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ከጥር ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ከኃላፊነታቸው ተነስተው በኢቴቪ ከተሾሙ በኋላ የድርጅቱን የአሠራር ሥርዓት ለማስተካከል የወሰዱት ጠንካራ እርምጃዎች በኃላፊዎቹ እንዳልተወደደ ምንጮች ተናግረዋል።በኢቴቪ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የሚደረጉ የውጪ አገር ጉዞዎች በጥቂት ግለሰቦች ሞኖፖሊ ብቻ ተይዞ የቆየ ሲሆን፤ አዲሱ ዳይሬክተር ይህን አሰራር በመሰረዝ የሚመለከታቸው ሪፖርተሮች በየተራ ተመድበው እንዲሰሩበት ማድረጋቸው፣ አንዳንድ ኃላፊዎች የጥቅም ግጭት በሚያስከትል መልኩ ኢቴቪ ውስጥ እየሰሩ በግል ድርጅታቸው አማካይነት ሥራዎችን ለመወዳደር ማመልከታቸውና ይህም ተቀባይነት ማጣቱ፣ እንዲሁም ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍት የነበሩ አሰራሮች እየተዘጉ መምጣታቸው ኃላፊዎቹን ሳያበሳጭ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል።አንድ የድርጅቱ ባልደረባ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገረው፤ አዲሱ ማኔጅመንት ሥር ነቀል ለውጥ እያደረገ መምጣቱ በአብዛኛዎቹ ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ዘንድ ድጋፍ ማግኘቱን ተናግረዋል። አንዳንድ ኃላፊዎች ያለ ችሎታቸው ጭምር ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታ እንደነበርና ይህም በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ይህ ሁኔታ አሁን እንዲስተካከል መደረጉ አስደስቶናል ብለዋል። በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ውስጥ የሚካሄደው ለውጥ በዚሁ ከቀጠለ በቀጣይ ሕዝባዊ ሚዲያ ለመፍጠር የሚያስችል ይሆናል ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝን በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።    ባለፈው ሰኔ ወር አጋማሽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ እንዲያድግ የሚደነግገውን አዋጅ ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል።

Wednesday, July 30, 2014

Ten years old Eyana Mesfin wrote a letter to President Obama regarding Andargachew Tsige.

Dear Mr. Obama,

Hello! I am 10 year old Eyana Mesfin from Centennial, Colorado. I was wondering if you could do something about the crisis in Ethiopia. Andargachew Tsige has been kidnapped during a flight from Dubai to Eritrea. On June 23rd, at a stop in Yemen, they captured him and took him to Ethiopia, his birth country. He is a citizen of Britain, and left Ethiopia in 2005, following protests of the nation’s elections. He is married and has twins, both 7. Andargachew has been captured before and tortured, but he escaped blind in one eye. The Prime Minister of Ethiopia, Hailemariam Desalegn, has labeled his activist group, Ginbot 7, as a terrorist group. They are said to currently be torturing him, which is against human right laws. Millions of Ethiopians are frustrated that nothing is being done. Please help Andargachew, for he is an important figure in Ethiopian hope. Millions of Ethiopians have fled Ethiopia due to poor leadership. His kids don’t even know about his capture, all they think is that he is visiting Ethiopia. Please help Andargachew, I know you’re busy but please, if you can, have Ethiopia free Andargachew Tsige, and rule Ethiopia better. Millions of Ethiopians from Australia to Europe to America, can return to their wonderful, beautiful home.

Thanks,

Eyana Mesfin


የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ (አስቂኙ ክስና አስቂኙ ማስረጃ)

አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነውመቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል:

ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባትየምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰትእድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁንግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸውክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡

በአስሩ ተከሳሾች ላይ የተጠቀሱት የክስ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ አንዱ የሽብር ተግባርን ማቀድ ማሴር ማነሳሳትና መፈጸም ሲሆን(የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ አራት) ሁለተኛው ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል መናድ( የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀጽ 238)የሚሉ ናቸው ፡። ክሱ ላይ በፓርላማ በሽብተኝነት ላይ ከተፈረጁ ድርጅቶች ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል በህቡእ በመደራጀት የሽብርተግባር ላይ መሰማራት እና የመሳሰሉት ክሶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከሶቹ ሲጠቃለሉ

ወጣቶች “በጸረ ሰላም ሃይሎች” ላይ እርምጃ እንዲወስዱብአዴን ጠየቀ

ኢሳት ዜና :-የብአዴን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በከተሞች የሚገኙ አውራጅና ጫኝ፤ሊስትሮ፤ሱቅ በደረቴ፤ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶችን፤ በተለያዩ
አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶችን እና በአደረጃጀት ያልታቀፉ ሌሎች ወጣቶችን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀው ሰነድ ፣ “የጥፋት ፖለቲከኞች እንቅስቃሴ
በመላ የከተማችን ሰላም ወዳድ ወጣቶች የተደራጀና የነቃ ተሳትፎ እንዲከሽፍ ካልተደረገ በመላ ቀልቡ ወደ ልማቱ የገባው ህዝባችን በተለይ ደግሞ ተጠቃሚ እየሆነ የመጣው ወጣቱ
ከልማት ተግባሩ ሊስተጓጎል ይችላል” ሲል አስጠንቅቋል።
በብአዴን የተዘጋጀው ሰነድ ለኢሳት የደረሰ ሲሆን፣ በሰነዱ ላይ የጥፋት ሃይሎች የተባሉት አካላት በስርአቱ ላይ ከባድ ፈተና መደቀናቸውን አትቷል።
ሰነዱ የጥፋት ሃይሎቹ ” የመጀመርያው በአማራ ህዝብ ላይ የተለያየ የጀግንነት ስም እየሰጡ ከሌላው ብሄር ጋር ተቻችለን ተከባብረን በልዩነታችን ውስጥ አንድነትን እንዳንመሰርትና
ከሌሎች ብሄር ወንድሞቻችን ጋር ተቻችለን እንዳንኖር የትምክህትን እና ፀረ-ዲሞክራሲያዊ የሆነ ቅስቀሳቸውን በማራገፍ በተለይም ለዚህ ድብቅ አላማቸው ወጣቶችን መጠቀሚያ
መፈለጋቸውን፣ ይህም በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ጨዋታ ላይ የታየው ምልክት የሚጠቀስ ነው” ብሎአል።
ይጥፋት ሃይሎች ” ከጦር የተመለሱ ታጋዮች ልዩ ድጋፍ አልተደረገላቸውም፣ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ከወጡ ድንጋይ ቀጥቃጭ ይሆናሉ፣ ድንበር ተገፋ፣ ለሱዳን መሬት ተቆርሶ ተሰጠ፣
አማራው በራሱ ብሄር ተወላጆች እተመራ አይደለም፣ የክልሉ አመራር አማራን ተሳደበ” የሚሉ ፕሮፓጋንዳዎችን በመንዛት ላይ ናቸው ሲል ሰነዱ ያትታል።
ሰነዱ ወጣቶች መውሰድ ስላለባቸው እርምጃዎችም ሲዘረዝር፣ የጥፋት ሃይሎች የሚሰሩትን የጥፋት ተግባር በዝርዝር ማጥናት፣ የትግል ስልቶቻቸውን ተከታትሎ በአግባቡ መረዳት፣
ይጥፋት ድርጊታቸውን ሁሉም እንዲያውቀው በርትቶ ማጋለጥ እና ሁሉም የተስተካከለ አቋም ይዞ እንዲታገላቸው መንቀሳቀስ፣ ወደ ህገወጥ ተግባር ሲሄዱም በማስረጃ አስደግፎ ለህግ
እንዲቀርቡ ማድረግ” የሚሉ ነጥቦች ተቀምጠዋል።
ሰነዱ በመጨረሻም “መላው የከተሞች ወጣት የጥፋት ሃይሎችን እና ጸረ-ሰላም፣ ጸረ ዲሞክራሲና ጸረ ልማት ተግባር ከመደበኛ ተግባራችን ጋር በማስተሳስር በቀጣይነት መፋለም
ይጠበቅብናል” ብሎአል።
ብአዴን እመራዋለሁ በሚለው ክልል የህዝቡ ብሶት እየጨመረ ድርጅቱም ህዝቡን ለመምራት በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የብአዴን አባላት ለኢሳት ገልጸዋል።
በከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን እየሰበሰቡ ” ስለ ጥፋት ሃይሎች” በየጊዜው የሚሰብኩ ቢሆንም፣ የክልሉ ወጣት ግን ብአዴንን እንደ ድርጅት እንደማይቆጥረውና አመራሩ
በወጣቱ ምላሽ ተስፋ እንደቆረጡ እንዲሁም ወጣቶችን የሚያሸፍቱ ጸረ ሰላም ሃይሎችን አጋልጡ በማለት በተቃዋሚነት የሚጠረጠሩ ወጣቶችን እየሰቃዩዋቸው ይገኛሉ።


6000 አዳዲስ የደህንነት አባላት ስልጠና እየተሰጣቸው ነው።

ለብአዴን አባላት እድሉ አልተሰጣቸውም።
ምንሊክ ሳልሳዊ
በቀጣዩ ጊዜያት የግንቦት ሰባት የተባለው የተቃዋሚ ቡድን በሃገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ውስጥ መስፋፋት ይፈጥራል ጥቃት ያካሂድብናል በሚል ስጋት መነሾ ጭንቀት ያደረበት የወያኔው ጁንታ ከመቀሌ እና ከደቡብ እንዲሁም የተወሰኑ ከኦሮሚያ ክልል የተወጣጡ 6000 አዳዲስ የደህንነት አባላት በአዋሳ በደብረዘይት እና በአዲስ አበባ ለሶስት ተከፍለው ስልተና እየተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል።የኢሕአዴግ አንዱ ክፍል እንደሆነ ለሚትወቀው የብኣዴን አባላት እና ካድሬዎች በዚህ የደህንነት ስልጠን ላይ እንዲሳተፉ እድሉ አልተሰጣቸውም።

በቀጣይነት ግንቦት ሰባት እና ተባባሪዎቹ የሚወስዱት እርምጃ ስጋት የሆነበት ወያኔ የሚያሰለጥናቸውን የደህንነት አባላቱን በሃገር ውስጥ በሚገኙ የተመዘገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች መዋቅር ውስጥ እና በኢሕአዴግ የወረዳ መዋቅሮች ውስጥ በማቀናጀት እንደሚመድባቸው እና እንዲሁም በጎረቤት አገራት በድንበር ከተሞች እና በዋና ዋና ከተሞች እንደሚመደቡ የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ እና የግንኙነት መረብ በማጥናት መረጃ በመሰብሰብ ሪፖርት እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም በዚህ የደህንነት መዋቅር ስራ ላይ የተመደቡ የወያኔ አባላት ይህን ያህል የሚያረካ ውጤት እና መረጃ ካለማምጣታቸውም በላይ አሁን ከሚመደቡ ጋር በጋራ እንዲሰሩ እንደሚደረግ ታውቋል።

Tuesday, July 29, 2014

California Congressman demands the release of Andargachew Tsige

WASHINGTON – Rep. Dana Rohrabacher on Monday urged Ethiopia’s prime minister to release Andargachew Tsige, a native-born opposition leader with British citizenship who last month was extradicted to the African nation from Yemen under questionable circumstances.

In a letter to Prime Minister Hailemarian Desalegn, the California Republican wrote: “Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other prodemocracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.”

Andargachew was traveling from Dubai to Eritrea on June 23 when, stopping over in Yemen, he was forcibly flown back to Ethiopia, which he fled in 2005 following protests of the nation’s elections. He was granted asylum in Britain, where his wife currently lives. British officials have expressed concerns that his extradition was not properly handled.

The activist was charged with terrorism and sentenced to death in absentia. In his letter to the Ethiopian prime minister, Rohrabacher added concerns from the United States. His letter follows:

July 28, 2014

His Excellency Hailemariam Desalegn

Prime Minister

Federal Democratic Republic of Ethiopia

Office of the Prime Minister

P.O. Box 1031

Addis Ababa, Ethiopia

Dear Mr. Prime Minister,

According to recent news reports, late last month the Ethiopian government arranged for the international kidnapping of opposition leader Andargachew Tsige and his forcible return to your country.

Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other pro-democracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.

All legitimate national governments have a responsibility to respect the human rights of their citizens. The current rulers of Ethiopia only continue to isolate themselves by violating the human rights of Ethiopian citizens, especially democratic political leaders. Mr. Andargachew should be released without delay and allowed to return home.

Sincerely,

Dana Rohrabacher

Chairman

Subcommittee on Europe, Eurasia, and Emerging Threats

House Committee on Foreign Affairs

Source: http://rohrabacher.house.gov/



ከ40 በላይ የሚሆኑ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በወያኔ አለአግባብ የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ በድብዳቤ ጠየቁ

የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ ይሻሻል ብለዋል
ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት የተፈረደባቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል
41 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፕሬስ ነጻነት አቀንቃኞች፣ አለማቀፍና ክልላዊ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትና የሙያ ማህበራት መንግስት በቅርቡ የሽብርተኝነት ክስ የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከትናንት በስቲያ በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን ብሉምበርግ ኒውስ ዘገበ፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ አርቲክል 19 ምስራቅ አፍሪካ፣ ሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ፣ ወርልድ አሊያንስ ፎር ሲቲዝን ፓርቲሲፔሽን፣ ፔን አሜሪካና የመሳሰሉት አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግስት ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን በሽብርተኝነት እየከሰሰ ለእስር መዳረጉን መቀጠሉ ያሳስበናል፣ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ መገታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ሶስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማርያን ሶስት ወራት ለሚሆን ጊዜ ይህ ነው የሚባል ክስ ሳይመሰረትባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ መቆየታቸውንና አንዳንዶቹም በምርመራ ወቅት እንግልት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን የጠቀሰው ደብዳቤው፣ ይህም አግባብ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

ሕወሓት አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ ራሷን በራሷ ያጋለጠችባቸው 4 ቅጥፈቶች

ስንታየሁ ከሚኒሶታ

July 27, 2014

እንደተጠበቀው በሕወሓት መንግስት በሚመራው የኢትዮጵያ ፖሊስ ፕሮግራም ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ተደርጓል። የአቶ አንዳርጋቸው በቲቪ መቅረብ ከዚህ ቀደም በአንዷለም አራጌ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ በደበበ እሸቱ፣ በአቡበከር አህመድ ላይ የተለመደ በመሆኑ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ሆኖም ግን ቪድዮውን ልብ ብሎ ለተመለከተው ወያኔ እንዳሰበው ትርፍ ሳይሆን የበለጠ ኪሳራ እንዳገኘበት ለመረዳት ችያለሁ። ለዚህም ነው ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ የረሳቻቸው 4 ቅጥፈቶች ስል ለዚህ አስተያየቴ ር ዕስ የሰጠሁት።

ሕወሓት ያዘጋጀው የቪድዮ ካሜራ ማንና አቀናባሪው ደንጋጣ እንደሆነ ቪድዮው ያስታውቅበታል። በጣም ተቆራርጦ መቀጣጠሉ ከማስታወቁም በላይ ቢያንስ ከዚህ የተሻለ ኤዲቲንግ ሥራ መሥራት ይችል የነበረ ቢሆንም ይህን ባለማድረጉ ለፕሮፓጋንዳ ሥራ የተዘጋጀውን ቪድዮ ኪሳራ ላይ ጥሎታል። ቪድዮ አቀናባሪው ሆን ብሎ ሕዝብ መቆራረጡን እንዲያውቅ ያደረገ ከሆነ ልናደንቀው የሚገባ ሲሆን፤ ሆኖም ግን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከሆነ ይህ ቪድዮ ቅንብሩ አይመጥንም።

2ኛ. ቪድዮው በተደጋጋሚ የተቀረጸ መሆኑ ያስታውቃል።

ቪድዮውን ልብ ብላችሁ ከተመለከታችሁት በተለያየ ጊዜ የተቀረጸ መሆኑ ያስታውቃል። ይህም የሚፈልጉትን ለማግኘት ብዙ ማይል እንደተጓዙ ያሳያል። ምንም እንኳ ተመሳሳይ ቀን የተቀረጸ ለማስመሰል አንድ ዓይነት ቱታ ቢያስለብሱትም 3 የተለያዩ የውስጥ ቲሸርቶች ይታያሉ። አንዱ ነጭ፣ ሌላኛው ሰማያዊና 3ኛው ቀይ ቲሸርቶች። በሌላ በኩል ቪድዮው ሊያልቅ ሲል የምታዩት ቱታ ደግሞ የተለየ ነው።

3ኛ. ውሃዋ የለችም።

እንግዲህ ወያኔ ሌላው የረሳችው አቶ አንዳርጋቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዳሉ ለስመሰልና ንጹህና የተገዛ ውሃ አጠገባቸው አስቀምጣ ነበር። ቪድዮው ግን በተለያየ ጊዜ የተቀረጸ ለመሆኑ የሚያስታውቀው በሌላኛው የቪድዮ ክፍል ውስጥ ውሃዋ የለችም።

4ኛ. ቶርች የሚደረግ ሰው እንዳለ ይሰማል

ይሄ ትልቁ ወያኔን ራሱን በራሱ ያጋለጠበት ክፍል ነው። ቪድዮው ተጀምሮ ከ1 ደቂቃ በኋላ ያለውን ስትመለከቱት አንዳርጋቸው በሚናገርበት ወቅት ከጀርባው የድብደባና የሲቃ ድምጽ ይሰማል። ይህም ምን ያህን በወያኔ እስር ቤቶች የሚደረጉትን ቶርቸሮች የሚያሳይ ነው። ይህ ለወያኔ ትልቁ ኪሳራ ሊባል የሚችል ደካማው የፕሮፓጋንዳ ቪድዮው ሊባል ይችላል። ራሱን በራሱ ቶርቸር አድራጊ መሆኑን መስክሯልና ይህንን የሚመለከታቸው አካላት ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ማሳየት ይኖርባቸዋል፤ አንዳርጋቸውም እንዲህ ያለው ቶርቸር እንደደረሰበት ማሳያ ሊሆነን ይችላል እላለሁ።



ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።
የደርግ መንደር ምሥረታ የሕዝብ ዓላማ ነበረው፤ የዓላማው መሣሪያ ግን የሕዝብ ሳይሆን ወታደራዊ ጉልበት ነበር፤ በዚህም ምክንያት የሕዝብ ዓላማ ያለው ሥራ የሕዝብን ህልውና በሚፈታተን የጉልበት መንገድ መከተሉ ዓላማው እንዳይሳካ፣ ሕዝብና አገዛዙ ባላንጣዎች ሆኑ፤ ጥሩው ዓላማ በከሸፈ ጉልበተኛነት ሳይሳካ ቀረ፤  በመንደር ምሥረታው ዓላማ ደርግ ክፋት ወይም ቂም ቋጥሮ አልተነሣም፤ ስሕተቱ ከውትድርና ባሕርይ የመጣ

መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ የተለመደውን የተቀነባበረ ፊልም ለህዝብ አቀረበ

ሐምሌ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም አቶ አንዳርጋቸውን በድጋሜ በማቅረብ፣ አቶ አንዳርጋቸው
ከባድ ሚስጢር እንዳወጡ አድርጎ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አንዳርጋቸው በረሃ በነበረበት ወቅት ለአመታት ሲተኛበት የነበረውን ሰሌን ምንጣፍና ይለብሰው የነበረውን ብርድ ልብስ ኢሳት ፎቶውን ያገኘ
ሲሆን፣ በረሃ ላይ የሚገኙ የግንቦት7 ታጋዮች እንደገለጹት ብርድ ልበሱን አንዳርጋቸው ከመቀበሉ በፊት ሌሎች 3 ሰዎች ሲጠቀሙበት ነበር።
አንዳርጋቸው ሲሄድ መኝታውን እራሱ አስሮ እንዳስቀመጠው የሚናገሩት ታጋዮች፣ ታሪክን ጠብቆ ለማስቀረት እንደታሰረ እንደሚቆይ ገልጸዋል።


Monday, July 28, 2014

ኦሮሞ እና እስልምና በ «ሕዳሴ አብዮት» መስመር (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

በወርሃ-ግንቦት ላይ ለዘመናት የተንሰራፋውን ሀገራዊ ደዌ ይፈውሳል ብዬ ተስፋ ስለማደርግበት «የሕዳሴ አብዮት» በሶስት ተከታታይ ክፍሎች ለመዳሰስ መሞከሬ ይታወሳል። በወቅቱ መጪው የ «ሕዳሴ አብዮታችን» መፍትሔ ሊሰጥባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መሀል በዋነኝነት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማሕበረሰብ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የመብት ጥያቄን በተመለከተ በጥቅሉ ጠቃቅሼው አልፌ ነበር። ሆኖም «ሰፋ ብሎ ቢዳሰስ» የሚሉ በተለያየ መንገድ የሚቀርቡ ጎትጓች ድምፆች መበራከታቸው የመነሻ ሃሳቡን ፈታ አድርጌ እንዳቀርብ አስገድዶኛል፤ እንግዲህ ይህ ጭብጥም የዛው ተከታይ መሆኑ ይሰመርልኝ።

የኦሮሞ ጥያቄ፥

Sunday, July 27, 2014

Bereket Simon is critically ill and receiving treatment at Bugshan Hospital in Saudi Arabia

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Bugshan-Hospital-Saudi-Arabia

Bereket Simon, a senior member of the ruling party in Ethiopia and an adviser to Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, has been admitted to Bugshan Hospital in Saudi Arabia. According to Ethiopian Review sources, he is critically ill but in a stable condition. A representative of Bugshan Hospital told Ethiopian Review that Ato Bereket is receiving treatment for coronary heart disease at the cardiology department.


Saturday, July 26, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ የቃል ኪዳን ሰነዱን ይፋ አደረገ። 

-ፓርቲዎች በድርጅታዊ ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱት ጠይቋል

ሰማያዊ ፓርቲ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ በርካታ ምሁራን ተወያይተውበት ብዙ ጥናትና ምርምር አድርገውበታል ያለውንና ‹‹የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ›› በሚል መጠሪያ ያዘጋጀውን ሐምሌ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ይፋ አደረገ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ይፋ ያደረገው የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ዜጎች በጋራ አንድ ሆነው ሊስማሙባቸው የሚችሉ፣ አጠቃላይ በአገራቸው ሁኔታ ላይ የሚግባቡባቸው ጉዳዮችን የያዘ የጋራ ሰነድ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ከፕሮግራም፣ ከፖለቲካ ሐሳብ፣ ከአስተሳሰብና ለወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ ከመስጠት ልዩነት ባሻገር፣ ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር የሚግባቡበት አንድ የጋራ ሰነድ አስፈላጊ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል፡፡ ይህም ሰነድ ፓርቲው ብቃት ባላቸው ምሁራን ተጠንቶና ውይይት ተደርጎበት፣ ሕዝብ ውይይት አድርጎበት አንድ የሚሆንበትና ‹ሕገ መሠረት› (የሕገ መንግሥት ማርቀቂያ መነሻ መሠረት) ሲል የጠራው ሰነድ መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

Friday, July 25, 2014

ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህነንት የበታች ሃላፊዎች በአቶ ኢሳይያስ ጠባቂዎች መገደላቸው ተዘገበ

ምኒልክ ሳልሳዊ

ባለፈው ማክሰኞ ከምሽት ጀምሮ ቦሌ መስመር ወሎ ሰፈር ከአይቤክ ሆቴል ፊትለፊት ገባ ብሎ ከሚገኘው የደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ በተፈጠረ የፖለቲካ አለመግባባት ከአቶ ኢሳያስ ወ/ጊ ጠባቂዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህንነት የበታች ሃላፊዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ታውቋል።

በአማራው ክልል ያሉ እና በህግ በተመዘገቡ ፓርቲዎች ሽፋን የህገወጥ ዲያስፖራ ፓርቲዎችን አላማ የሚያራምዱ የተቃዋሚ አመራሮች ላይ ከምርጫው ቀደም ብሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ለመወያየት የተሰበሰበው የደህንነት ጓድ በስብሰባው ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በወቅቱም ከአዲስ አበባ ከ13 አመት በፊት ተመልምለው ወደ አማራው ክልል የተላኩት በክልሉ ምስጢራዊ የሆኑ የግድያ እና የአፈና እንዲሁም የስለላ መመሪያዎችን በመቀበል ለጽጥታ ሃይሎች በማስተላለፍ ሲያስፈጽሙ እና ሲፈጽሙ የነበሩ እና በደህንነት ኮድ ስማቸው (አለልኝ እና ብቸናው) የተባሉ የደህንነት የበታች ሹሞች እዛው ስብሰባው መሃል በጸጸት እና በብሶት በቁጣ የተሞላ ጠንካራ ጥያቄዎች በማቅረባቸው በተፈጠረ አለመግባባት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረዘይት አየር ሃይል ግቢ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥበአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ የማሰቃያ መርፌዎችን እየተወጉና በኤልክትሪክ ሾክ እየተሰቃዩ መረጃ እንዲያወጡ እየተገደዱ ነው።

መርማሪዎች ከአቶ አንዳርጋቸው የሚፈልጉት መረጃ ከግንቦት7 ጋር በጋራ የሚሰሩ  አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግን አመራሮችን እንዲሁም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ አዛዦችን ስሞች ሲሆን፣ አቶ አንዳርጋቸው ግን እስካሁን ምንም አይነት መረጃ ባለመስጠታቸው ፣ መርማሪዎች ሲበሳጩ መታየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ለወትሮው አንድ መረጃ ሲያገኙ በታላቅ ደስታ የሚፈነጩት መርማሪዎች፣ ምርመራቸውን ጨርሰው ሲወጡ የሚያሳዩት ብስጭት፣ እስካሁን ድረስ የሚፈልጉትን እንዳላገኙ የሚያሳይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ አንዳርጋቸው እንዳስፈላጊነቱ በቀን ሶስት ጊዜ ምርመራ እንደሚካሄድባቸው የሚናገሩት ምንጮች፣ ምርመራውን የሚያካሂዱት የተመረጡ የህወሃት የደህንነት ሰራተኞች መሆናቸውንና በግቢው ለበረራ የሚሰለጥኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ወይም የደህንነት ሰራተኞች ወደ አካባቢው እንደማይሄዱ ገልጸዋል። ምሽት አካባቢ የሚሰማው የጣር ድምጽ የሚረብሻቸው የእለት ተረኛ ጠባቂ መኮንኖች በሁኔታው እያዘኑ አንዳንዶች ስሜታቸውን መቆጣጠር እንደማይችሉ ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

ስለ አቶ አንዳርጋቸው የእለት ውሎ ማወቂያ ብቸኛው ዘዴ የመርማሪዎች ፊት ነው የሚሉት ምንጮች፣ እስካሁን ድረስ ምርመራ በሚያካሂዱ የህወሃት አመራሮች  ዘንድ የደስታ ፊት እንደማይነበብ ገልጸዋል።

የኢህአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታሰሩበትን ቦታ ይፋ ለማድረግ እስካሁን ፈቃደኛ አልሆነም። የእንግሊዝ ባለስልጣናት ለአቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ጥያቄ ቢያቀርቡም ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ከዚህ በተቃራኒ ኢህአዴግ በአቶ አንዳርጋቸው እና በግንቦት7 ላይ ለሚሰራው ድራማ ግብአት ይሆን ዘነድ የተለያዩ ሰዎችን ማሰማራቱን ምንጮች ገልጸዋል። ቀደም ብለው በአገዛዙ ለስለላ ወደ ኤርትራ ተልከው እና ለተወሰኑ ወራት ግንቦት7 ትን ተቀላቅለው በመጨረሻ የኢህአዴግ የስለላ አባላት መሆናቸው ሲታወቅ የጠፉ እንዲሁም ፈንጅ ሊያፈነዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉ እና በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጠቀም እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ያሳየው ቁጣ ያስደነገጣቸው ደህንነቶች ለማንኛውም በሚል በደንበር አካባቢ ጥበቃቸውን እያጠናከሩ ነው። የአቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ግንቦት7ትን የሚቀላቀሉ ሰዎች መጨመራቸውንም ከድርጅቱ የወጣው መረጃ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤልጂየም ብራሰልስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸውን ለመያዝ የሄደበትን እርቀት ከማውገዝ በተጨማሪ የእንግሊዝ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ አጥብቆ እንዲከታተል ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በአውሮፓ ህብረት ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን በከፍተኛ ቁጣ ከማሰማት በተጨማሪ፣ ያዘጋጁትን ደብዳቤ ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናትና ለእንግሊዝ መንግስት ኮንስላ ጽ/ቤት ሃላፊዎች አስረክበዋል።

ኢትዮጵያ በፍርሀት የሞት እና ሽረት ትግል መካከል የምትንጠራወዝ ምስኪን አገር


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ



በሞት ሽረት ትግል ውስጥ የሚገኙት የዞን 9 ትንታግ ወጣት ጦማርያን

የኔ ጥያቄ እውን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሬፐብሊክ መንግስት” ነው ወይስ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቆ የሚገኝ “የፖሊስ መንግስት”? ኢትዮጵያ በሌላ ጠፈር (ህዋ) የምትገኝ አገር ናትን? እነዚህን ጥያቄዎች በጥሞና የማነሳቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ “የፖሊስ ሬፐብሊክ መንግስት” ተብላ ልትጠራ ትችላለች፡፡ በ20ዎቹ አካባቢ የዕድሜ ጣሪያ ላይ የሚገኙ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች በፌስቡክ እና በሌሎች የማህበረሰብ ድረገጾች ያለምንም ፍርሀት በመጻፋቸው እና ሀሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸው ምክንያት ብቻ በገዥው አካል ሽብርተኛ በሚል የሸፍጥ ፍረጃ እና ክስ በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ቤት በመማቀቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል 6 ጦማሪያንን እና 3 ጋዜጠኞችን (የዞን 9 ጦማርያን እየተባሉ የሚጠሩትን) በተለምዶ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው በአስፈሪው የመለስ ዜናዊ የማሰቃያ እስር ቤት ከሚማቅቁት የፖለቲካ እስረኞች የእስር ቤት ቁጥር 8 ቀጥሎ በተሰየመው የማጎሪያ እስር ቤት ለ80 ቀናት ያህል ሲያማቅቅ ከቆየ በኋላ ህገወጥ በሆነ መልኩ ሽብርተኛ የሚል ታፔላ በመለጠፍ መሰረተቢስ የሆነ የሸፍጥ ውንጀላ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

የፖሊስ ሃላፊዎች ጥያቄዎችን አነሱ

ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ሃላፊዎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በሰንዳፋ እና በኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛዎች
ከደህንነት ጋር በተያያዘ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን፣ የሰልጠና ተሳታፊዎች የሚያነሱዋቸውን ጥያቄዎችን አሰልጣኞች መመለስ አለመቻላቸውን በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ ፖሊሶች ለኢሳት ገልጸዋል።
ፖሊሶቹ ” መንግስትበተለይከሙስሊምሃይማኖትተከታዮችየሚነሳውንዲሞክራሲያዊየሆነጥያቄለምንአይመልስም? ለምን በፖሊስተቋምላይየስራጫናእንዲበዛ ይደረጋል?ህዝቡበፖሊስላይያለውጥላቻ
ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣እኛህብረተሰቡን በተገቢውመንገድማገልገልእንፈልጋለንና አስተዳዳራዊ ሁኔታዎች ይለወጡ” የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል። አሰልጣኞቹ የሚቀርቡት ጥያቄዎች ከአቅማቸው በላይ
መሆኑንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የሚመልሱዋቸው እንደሆነ እየገለጹ ነው። በሚሰጠው መልስ ደስተኛ ያልሆኑት ፖሊሶች፣ ትክክለኛውን መልስ የሚሰጠው አካል ይመጣል ብለው ቢጠባበቁም
እስካሁን ድረስ አርኪ መልስ የሚሰጥ ባለስልጣን አላገኙም።

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችን ማሰሩ እና ማዋከቡ ቀጥሏል

በኢየሩሳሌም ተስፋው (አዲስ አበባ)ዛሬ የወይኒ ፍ/ቤት ቀጠሮ ስለሆነ በጠዋት የሰማያዊ ልጆች ከያለንበት ተሰባስበን ሜክሲኮ ወደሚገኘው እንደኛ ደረጃ ፍ/ቤት ሄድን ተሰባስበን ግቢ ውስጥ ቀመን ሳለ እነወይኒን የያዘው መኪና ሲመጣ ባለፈው ያየነውን ሽብር መንዛት ጀመሩ መብታችን አይደል እንዴ መከታተል እንዴት ከግቢ ታስወጡናላችሁ? አልን ከመሃላችን አቤል ኤፍሬምን ና ብለው ወደ ውስጥ አስገቡት እንዴ ለምን ትወስዱታላችሁ ስንል ቆይ አናግሬያቸው መጣሁ ብሎን ገባ የነወይኒ መኪናም ውደውስጥ ገብቶ መውረድ ጀመሩ ወይኒዬ ጭንቅላቷ እና እጇ እንደታሸገ ነው ፊቷ ላይ እሚነበበው ጥንካሬ አሁንም እንዳለ ቢሆንም አካሏ ግን እንደተጎዳ በደንብ ያስታውቃል ከፍተኛ ድብደባ እየደረሰባት እንደሆነ ትናንት ለነ ጌች ነግራቸዋለች እጥፍጥፍ ብላ አንገቷን ደፍታ ስትቀመጥ ሳያት የእውነት ከዚች አገር መፈጠራችንን ነው የጠላሁት ወይኒ እያየችን ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ መልኩ እንባዋ ይፈስ ጀመር ጭንቅላቷን እና እጇን እየነካች የስቃይ ፊት አሳየችኝ እሱንም ፖሊሶቹ እንዳይዋት በመሳቀቅ ነው በዚህ ሁሉ ስቃይ መሃል እጇን እየሳመች እንደምትወደን ደጋግማ ታሳየናለች።ችሎት ገቡ ለሐምሌ 24 እንደተቀጠረ ከዛሬ ጀምሮ ሰው እንዲጠይቀት ፍ/ቤቱ እንዳዘዘ ነገረችን የነሱ መኪና ሲወጣ ወደ ቀጣዩ እስረኛ ጓዳችን ተጠግተን ለመጠየቅ ስንሞክር ሁከት ለመፍጠር ሙከራ አድርጓል ስለዚህ ሶስተኛ ወስደንዋል እዛ ሂዱና ጠይቁ አለን አንድ ጥጋብ አናቱ ላይ የወጣ ፖሊስ እኮ ወንጀሉ ምንድነው? ሁከት መፍጠር ምንም አይነት ሁከት አልፈጠረም መብቱን ነው የጠየቀው ያ ደግሞ ወንጀል ከሆነ ሁላችንም ወንጀለኞች ነን ሁላችንንም እሰሩን አቤል ምንም አይነት ወንጀል አልሰራም ብለን ሊቀ መንበራችን ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ ወደ 30 እምንሆን የሰማያዊ ልጆች ተሰብስበን ገባን።ከዛ በኋላ ምን ብዬ ልንገራችሁ ሁሉም እየተነሳ አፉን ይከፍትብን ጀምር እደፋሃለው እገልሃለው ተው አታስፈራራኝ ይለዋል ፍቅረማርያም ማስፈራራት ነው የገረመህ በድርጊት አሳይሃለው አለው ብርሃኑን ደግሞ ከዚህ በፊት እዛ ታስሮ ሳለ እሚያውቀው አንድ ፖሊስ እንተ ቤቱን ታውቀዋለህ አይደል አሁንም አስገባሃለው አለው በጣም የሚገርመው እንዲህ የሚደነፉት እኮ ተራ ፖሊሶች ናቸው።ምንም አይነት ጥፋት የለብንም መብታችንን ነው የጠየቅነው ስንል መብታችሁን እዚህ አይደለም እምጠይቁት አለን ቆይ ፍ/ቤት መብታችንን ያልጠየቅን የት ነው እምንጠይቀው ታድያ? ሁልሽም እዛ ወስደን ስንቀጠቅጥሸ ጥጋብሽ ይወጣልሻል አለ ተሰብስበን ተቀመጥን እነሱም ይደነፋሉ ይህ ስርዓት ምን አይነት ደረጃ ላይ እንደደርሰ እና የራሱን እድሜ በራሱ አያሳጠረ መሆኑን እያሰብኩ በእልህ ስሜት ተቀምጠናል በተደጋጋሚ ያስፈራሩናል እንድንወጣ ካለበለዚያ እሚመጣው ነገር አስፈሪ መሆኑን ይነግሩናል በቃ እሚመጣውን ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን ውሰዱን አታስፈራሩን በቃ አልን፣ ይልቃልን ጠሩት እና ያዋሩት ጀመር ይህ ፍ/ቤት መሆኑን መቀመጥ እንደማንችል ሰዓት ስለደረሰ የፍ/ቤቱ ግቢ ሊዘጋ መሆኑን እና በሰላም እንድንወጣ ይህ ህገወጥ ድርጊት መሆኑን ብቻ ብዙ ነገር ለፈለፉ ስለአቤል ጉዳይ ሔደን እዛ እንድንጠይቅ ነግረውት መጣ እኛም ወጣን አቤሎን ይዘውት ሄዱ አዎ ተራ በተራ እየለቀሙ ያስገቡናል የሁላችንም ቤት እዛው ነው የጊዜ ጉዳይ ነው።“በሉ እናንተም ሂዱ የኛም ወደዛው ነው ወትሮም መንገደኛ ፊት እና ኋላ ነው” ቀጣይ ተረኛ ደግሞ ማን ይሆን?ላንቺ ነው አገሬ ላንቺ ነውላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነውአዎ ይህ ሁሉ ስቃይ እየደረሰባቸው ያለው አንቺን በማለታቸው ብቻ ነው!

Thursday, July 24, 2014

ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመባት ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ በድጋሜ ተቀጠረች

ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በሙስሊም ኢትዮጵያውያውያን ላይ ያደረሱትን ኢ ሰበአዊ እርምጃ ተከትሎ በአካባቢው ስትንቀሳቀስ ተገንታለች በሚል ሰበብ የተያዘቸው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክርቤትና የሴቶችጉዳይ አባል ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ ለሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሜ ተቀጠራለች፡፡

ወይንሸትጭንቅላቷ አካባቢ የተመታች ሲሆንእጇም በፋሻ እንደታሰረበስፍራው የነበሩ ጓደኞቿ ለኢሳት ገልጸዋል።

ችሎቱን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት ካቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል አቤልኤፍሬም በፖሊሶች መወሰዱ ታውቋል። ችሎቱን ለመከተታል የተገኘችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፖሊሶቹ ችሎቱን ለመከታተል በተገኙት ሰዎች ላይ ይናገሩ የነበሩት ንግግር ” ከፖሊስ የማይጠበቅ” መሆኑን ተናግራለች። ኢህአዴግ እያወሰደ ያለው እርምጃ፣ አገዛዙ የመጨረሻ እድሜው ላይ መገኘቱን እንደሚያሳይም አክላ ገልጻለች

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ የሰጠው መልስ የእንግሊዝ የፓርላማ አባላትን አስገረመ

ኢሳት ዜና

በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ እና የጋራ ብልጽግና መስሪያ ቤት ዋና ጸሃፊ የሆኑት ማርክ ሲሞንድ የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከእንግሊዝ መንግስት የኮንሱላር ምክር የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚጠይቅ ደብዳቤ ለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጽፈዋል። ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሰጠው መልስ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ የተባለ ድርጅት መሪ መሆናቸውን ገልጾ፣ አሸባሪ ለመሆናቸው ማሳያ ይሆን ዘንድ ግንቦት7 በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ በእንግሊዝኛ ተርጉሞ አያይዞ አቅርቧል።

ግንቦት7 አቶ አንዳርጋቸውን ለማስፈታት በኢትዮጵያ ፣ በየመን እና በእንግሊዝ መንግስታት ላይ ኢትዮጵያውያን መውሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች የሚዘረዝር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል።
በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመሄድ ተቃውሞ እንዲያሰሙ፣ ተከታታይ ደብዳቤዎችን እንዲጽፉ የሚጠይቀውን መግለጫ፣ ግንቦት7 አሸባሪ ድርጅት ለመሆኑ
ማሳያ ነው በማለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጻፈው ደብዳቤ የፓርላማ አባላቱንና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን እንዳስገረማቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የአቶ አንዳርጋቸው
ቤተሰቦች ገልጸዋል።

የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉት ሁለቱ የፓርላማ አባላት ጀርሚ ኮርቢን እና ኤምሊ ቶርንቤሪ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሰጠው መልስ ከተገረሙት መካከል ሲሆኑ፣
ባለስልጣኖቹ የእንግሊዝ መንግስት በሂደት ስለሚወስደው እርምጃ እንዲብራራላቸው ደብዳቤ ጽፈዋል። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሃፊ፣ አገራቸው በተከታታይ ስለምትወስደው እርምጃ ዝርዝር
መርሃ ግብር እያዘጋጁ መሆኑን ለፓርላማ አባላቱ ገልጿል።

ኢሳት ባለስልጣኖቹ የተጻጻፉዋቸው ደብዳቤዎች ቅጅ የደረሰው ሲሆን፣ ከደብዳቤዎች ለመረዳት እንደሚቻለው፣ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የሚያቀርበው የሽብርተኝነት ክስ ግንቦት 7 መንግስትን በሃይል አወርዳለሁ ብሎ ማወጁ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ አሁንም የመነጋጋሪያ አጀንዳ እንደሆነ ቀጥሎአል። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ስልኮችን ለኢሳት በመደወል ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን
አክብሮትና መካሄድ ስላለበት ትግል አስተያየቶችን ይሰጣሉ።


ሰውና ልማት (ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፤ ሕይወቱ ክቡር ነው፤ ክቡር ሕይወቱን ለመጠበቅ ብዙ ፍላጎቶቹን ማሟላት አለበት፤ አንዳንዶቹ ፍላጎቶች በየዕለቱ የሚከሰቱና የሚጎተጉቱ ናቸው፤ ስለዚህም ወዲያው ካልተስተናገዱ በጤንነት ላይ መጥፎ ውጤትን ያስከትላሉ፤ምግብና መጠጥ ግዴታዎች ናቸው፤ ልብስና መጠለያም ግዴታዎች ናቸው፤ ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላበት ከገነት ከተባረረ በኋላ በግንባርህ ላብ ብላ ተብሎ ተረግሟል፤ በሰላም በሕግ ጥላ ስር የመተዳደር ፍላጎትም አለ፤ በአለው አቅምና ችሎታ አነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ይጥራል፤ ይህ ቀላል አይደለም፤ ቀላል የማያደርጉት ብዙ ምክንያቶች አሉ።አንደኛ፣ የሰውም፣ የእንስሳም፣ የእጸዋትም ሁሉ መኖሪያና መመገቢያ ምድር አንድ ነች፤ ስለዚህ ውድድሩ ከባድ ነው፤ በዚች ምድር ላይ እየኖሩ፣ ምድር የምታፈራውን እየተመገቡ፣ ውሀዋን እየጠጡ በሰላም መኖር አይቻልም፤ የሰው ልጅ ከቢምቢ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰው ቢምቢ ጋርም መታገል አለበት፣ ከዱር አንበሳ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰው አንበሳ ጋርም ነው።
ሁለተኛ፣ ፍላጎቶች የሥራ ሁሉ ምንጭ ስለሆኑ በጣም ይራባሉ፤ የመራባት አቅማቸው ከሰው ልጅ መራባትና የመፍጠር ችሎታ ጋር የተያያዘ ነው፤ በተጨማሪም ለተመቸው ሁሉ አምሮቶች ፍላጎቶች ይሆናሉ፤ ደሀዎችንና ሀብታሞችን የሚለየው አንዱ ዋና ነገር የፍላጎቶች ብዛት ነው፤ የደሀ ፍላጎቶች ከመሠረታዊ ፍላጎቶች አይርቁም፤ የሀብታሙ ፍላጎቶች ከትልቅ ቤት ወጥተው በትልቅ መኪና አድርገው በአውሮጵላን ሰማይ ይወጣሉ፤ ከዚያም አልፈው ይቧጭራሉ።

የገነት ዘውዴ “ጠባሳ”

ከኢየሩሳሌም አረአያ

እስክንድር አሰፋ ይባላል፤ አሜሪካ ለ22 አመት ከኖረ በኋላ አገር ቤት የገባው በዘመነ ኢህአዴግ ነበር። የት/ሚኒስትሯ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ታናሽ ወንድም ነው። እስክንድር የቅርብ ወዳጄና ብዙ ነገር ያስተማረኝ ሰው ነው። ..ሚያዚያ 1993ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ ይመታሉ። ወቅቱ ሕወሐት ለሁለት የተሰነጠቀበት ጊዜ ነበር። የትምህርት ሚ/ሯ ገነት ዘውዴ ለተማሪዎቹ ህጋዊና ሰላማዊ ጥያቄ በቲቪ የሰጡት ምላሽ የበለጠ ተማሪውን ቁጣ ውስጥ ከተተው።

እንዳውም ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደሚገኘው የገነት ወላጅ እናት መኖሪያ ቤት ተማሪዎቹ ይተማሉ። በሁኔታው የተደናገጠው እስክንድር ከግቢው ሾልኮ በመውጣት ወ/ሮ ገነት ወደሚኖሩበት የገርጂ ቤታቸው ያመራል። በጊዜው ገነት ከጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ታደሰ ጋር ተጋብተው ይኖሩ ነበር።..አመሻሽ ላይ አቶ ተፈራ ዋልዋና የወቅቱ የፖሊስ ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ በወ/ሮ ገነት መኖሪያ ውስጥ ተገኝተዋል። 3ቱ በክብ ሶፋ ዙሪያ ተቀምጠው ይዶልታሉ።

እስክንድር ከአቶ ከበደ (አማቹ) ጋር ፈንጠር ብለው ውስኪ እየጠጡ ነበር። የት/ሚ/ር ገነት ለፖሊስ ኮሚሽነር ወርቅነህ እንዲህ አሉ፥ « በነገው እለት ስለት (ጩቤ) የያዙ ሲቪል ፖሊሶች ተማሪዎቹን ይቀላቀሉ። በምታሰማራቸው ፖሊሶች ላይ አደጋ እንዲያደርሱ ይነገራቸው። ከዛ የሃይል እርምጃው ይቀጥል..» ሲሉ አቶ ተፈራም ሴራውን በመደገፍ ተመሳሳይ የቤት ስራ ለወርቅነህ ነገሩ። እስክንድርና አቶ ከበደ በትዝብት ያዳምጡ ነበር። ..ሌሊቱን እንቅልፍ ያልወሰደው እስክንድር ሲነጋ ለእህቱ ገነት « ምን አይነት እርኩስ ነሽ!?..ንፁህ ተማሪዎች እንዲመቱ ሴራ ትሸርቢያለሽ!?..ለካ ሰው የጠላሽ ያለነገር አይደለም!?..አሁን ኢህአዴግ ገባኝ!..» ሲል ተናግሮ ወጣ። ለ7 አመት እስክንድርና ገነት ሰላምታ ሳይለዋወጡ ዘለቁ።

የገነት የሴራ እስትራቴጂ በማግስቱ ተግባራዊ ሆነ። ተማሪዎች ተደበደቡ፣ ቆሰሉ፣ ሞቱ፣ በጅምላ እስር ቤት ተጋዙ፣ ከአገር ተሰደዱ። ..ገዢውን ፓርቲ ይደግፍ የነበረው እስክንድር ከዛ በኋላ ተጠየፋቸው። ወዳጄ እስክንድር ስለዚህ አሳዛኝ ሴራ ባወራኝ ቁጥር እጅግ በሃዘን ስሜት ተውጦ ነበር።…ይህን እንዳስታውስ ያደረገኝ በትላንትናው እለት በአንዋር መስጊድ የተፈፀመው ተመሳሳይ ሴራና ድራማ ነው። ..በሌላ ጊዜ ስለፈንጂ ድራማዎችና አጥማጆቹ ማንነት እንዲሁም ቅንብር ሴራ ልመለስበት እሞክራለሁ። ..


ከኤርትራ ጋር የታቀደው ጦርነት ሊጀመር ነው!!!

የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ የ ወያኔ መንግስት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊከፍት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ከውስጥ የተላከልኝን መረጃ ማስነበቤ ይታወሳል።

የጦርነቱም ዋና አላማ በኤርትራ ውስጥ ያሉትን የነፃነት ታጋዮችን እንቅስቃሥሤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማምከን የሚል ነው። የዚህ ጦርነት ዋና አላማ በስልጣን ላይ ያለውን የሻብያ መንግስት በመጣል በኢትዮጵያ ውስጥ ሲያዘጋጁቸው የኖሩትን የ ኤርትራ ተቃዋሚወች ወደ ስልጣን በማምጣት በኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ማንኛውም አይነት የትጥቅ ትግል ቦታ ማሳጣት ነው። ለዚህም ይረዳሉ ተብለው በ10 ሺወች የሚሆኑ ኤርትራውያንን በኢትዮጵያ ዪኒቨርስቲወች ውሥጥ ሲያሥተምር ቆይቱል። እነዚህ ተማሪወች ከአካዳሚክ ትምህርት ባሻገር በአመት ሶሦት ጊዜ የ መንግስት አስተዳደር፣ የፓለቲካ እና የደህንነት ትምህርቶችን ሲማሩ ቆይተዋል።

ይህ ጦርነት ግቡን ይምታላቸውም አይምታላቸውም እንደተጠበቀ ሆኖ በቅርብ ጊዜ ጦርነቱ ሊጀመር መሆኑን መረጃወች ይጠቁማሉ።

ይህን የታሪክ አጋጣሚ የኢትጵያ ህዝብ እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል አይታወቅም። በወያኔ ግምት የኢህዴግ ሰራዊት በድል ያጠናቅቃል የሚል እምነት እንዳለው ያመለክታል። ህዝቡ ድጋፍ አደረገም አላደረገም ሰራዊቱ አሁን ባለው አቁም ይህን አደራ በአሸናፊነት እንደሚያጠናቅቅ እምነት እንደተጣለበት ያመለክታል።

የኢህዴግ ሰራዊት ከተቁዋሚ ጎራ ይሠልፍ ይሆን የሚለውንም ሃሳብ አውጥተው አውርደው አስበውበታል። በእነሱ እምነት ይህ ሃሳብ ውሃ የሚቁጥር ሆኖ አላገኙትም።

አይቀሬው ጦርነት ሊጀመር ጫፍ ላይ መሆኑን በ ያዝነው ወር በቀን 18 የአሜሪካ የ አቬሽን ባለስልጣን ያወጣውን የ ሰላማዊ አውሮፕላን በረራ እገዳ አንድ ትልቅ ፍንጭ ነው።

በተጨማሪም በየወረዳው የተጀመረው የውትድርና ምልመላ አንድ ሌላ ተጨማሪ ፍንጭ ነው።

Demeke Yeneayhu


ወያኔ ሰራዊቱን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ሰሜን እያጓጓዘ ነው

የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ የ ወያኔ መንግስት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊከፍት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ከውስጥ የተላከልኝን መረጃ ማስነበቤ ይታወሳል።

የጦርነቱም ዋና አላማ በኤርትራ ውስጥ ያሉትን የነፃነት ታጋዮችን እንቅስቃሥሤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማምከን የሚል ነው። የዚህ ጦርነት ዋና አላማ በስልጣን ላይ ያለውን የሻብያ መንግስት በመጣል በኢትዮጵያ ውስጥ ሲያዘጋጁቸው የኖሩትን የ ኤርትራ ተቃዋሚወች ወደ ስልጣን በማምጣት በኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ማንኛውም አይነት የትጥቅ ትግል ቦታ ማሳጣት ነው። ለዚህም ይረዳሉ ተብለው በ10 ሺወች የሚሆኑ ኤርትራውያንን በኢትዮጵያ ዪኒቨርስቲወች ውሥጥ ሲያሥተምር ቆይቱል። እነዚህ ተማሪወች ከአካዳሚክ ትምህርት ባሻገር በአመት ሶሦት ጊዜ የ መንግስት አስተዳደር፣ የፓለቲካ እና የደህንነት ትምህርቶችን ሲማሩ ቆይተዋል።

ይህ ጦርነት ግቡን ይምታላቸውም አይምታላቸውም እንደተጠበቀ ሆኖ በቅርብ ጊዜ ጦርነቱ ሊጀመር መሆኑን መረጃወች ይጠቁማሉ።

ይህን የታሪክ አጋጣሚ የኢትጵያ ህዝብ እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል አይታወቅም። በወያኔ ግምት የኢህዴግ ሰራዊት በድል ያጠናቅቃል የሚል እምነት እንዳለው ያመለክታል። ህዝቡ ድጋፍ አደረገም አላደረገም ሰራዊቱ አሁን ባለው አቁም ይህን አደራ በአሸናፊነት እንደሚያጠናቅቅ እምነት እንደተጣለበት ያመለክታል።

የኢህዴግ ሰራዊት ከተቁዋሚ ጎራ ይሠልፍ ይሆን የሚለውንም ሃሳብ አውጥተው አውርደው አስበውበታል። በእነሱ እምነት ይህ ሃሳብ ውሃ የሚቁጥር ሆኖ አላገኙትም።

አይቀሬው ጦርነት ሊጀመር ጫፍ ላይ መሆኑን በ ያዝነው ወር በቀን 18 የአሜሪካ የ አቬሽን ባለስልጣን ያወጣውን የ ሰላማዊ አውሮፕላን በረራ እገዳ አንድ ትልቅ ፍንጭ ነው።

በተጨማሪም በየወረዳው የተጀመረው የውትድርና ምልመላ አንድ ሌላ ተጨማሪ ፍንጭ ነው።

Demeke Yeneayhu


ለብሔራዊ አንድነትና ነፃነት – ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል!!!

በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙ የእብደት ተግባራትን ስናጤን ከፊት ለፊት ኢትዮጵያችንን እየጠበቀ ያለው መንታ መንገድ አመላካች ነው። ይህ ከፊት ለፊት የሚጠብቀን መንታ መንገድ አንዱ ወደ ብሔራዊ አንድነት፣ ነፃነትና ብልጽግና ሌላው ወደ እርስ በርስ ትርምስና ውድቀት የሚያመሩ ናቸው። የአንድነት፣ የነፃነትና የብልጽግና መንገድ ለመያዝ መስመራችንን ማስተካከል ያለብን ከአሁኑ ነው።ለመሆኑ ከላይ ያልነውን ለማለት ያስቻሉን በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙት ተግባራት ምንድናቸው?አንደኛ፤ሁለተኛ፤ሦስተኛ፤አራተኛ፤ከላይ የተዘረዘሩት አራት ጉዳዮች በጋራ ሲታዩ የተበታተነ የሚመስለው እና በተለያዩ ስልቶች የሚደረገው ትግል የሚሰባሰብበትና የሚቀናጅበት ወቅት ላይ መደረሱ አመላካቾች ናቸው። ዛሬ የምንገኘው የተለያዩ የትግል ስልቶች እንዲናበቡና እንዲደጋገፉ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ ነው።በተለይም ወያኔ፣ መሸሸጊያ ምሽጉ አድርጎ በሚቆጥረው ትግራይ ውስጥ እየዳበሩ የመጡት የአመጽም አመጽ-የለሽ ትግሎችም አስተዋጽኦ ከፍተኛነት ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲረዳ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ነው። የወያኔ የአፈናና የመጨቆኛ መዋቅሮች የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ዘውጌ ማኅበረሰብ አባላት የሚዘወሩ መሆኑ እውነት ነው። ይህ ማለት ግን ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ወኪል ወይም ጠበቃ ነው ማለት አይደለም። ትግላችን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ጋር መሆኑ እና የትግራይ ሕዝብ የዚህ ትግል አጋር፣ የውጤቱም ተጠቃሚ መሆኑ ማስረገጥ ተገቢ ነው።ከፊት ለፊታችን ካሉት መንታ መንገዶች መካከል የአንድነትን፣ የነፃነትና የብልጽግናን መንገድ ለመምረጥ የትግራይ ሕዝብ በስፋት ትግሉን እንዲቀላቀል ማድረግ ተገቢ ነው። ትግራይ የህወሓት የግል ጓዳ መሆኗ የማብቂያ ጊዜ ማፋጠን ይቻላል። በዲሞክራሲያዊ ትግል ውስጥ ያሉ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ ግንዛቤ ከያዙ ወያኔን ማንሳፈፍ የሚቻልበት እድል በስፋት ተከፍቷል።ስለሆነም፣ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዘረኛውና ፋሽስታዊው ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል አንዱ የትግላችን ስትራቴጂ ሊሆን ይገባል ይላል።ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Monday, July 21, 2014

የዞን 9 ጦማሪያን አባላት “ በወያኔ የስለላ ተቋም ተደርሶበት የተከሰሱበት ማስረጃ” እጃችን ውስጥ ገባ!!

AbbayMedia:  ለጥረታቸው እያመሰገን ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይህንን የኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ እውቀት እንዲጠቀሙበት እንመክራለን ።
ሙሉውን ዝርዝር እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ፡-  https://securityinabox.org/am/howtobooklet
የኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ

 ይህ የኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት ግንኙነት እንዲኖረን ማወቅ የሚያስፈልጉንን መሠረታዊ ነገሮች ለማብራራት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው። መመሪያው በኢንተርኔት ግንኙነት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየትና በማብራራት፣ እነዚህን አደጋዎች ለመቀነስ የሚያስችል በተገቢ መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንድንሰጥ ያስችለናል። ይህን ለማረጋገጥም ስምንት ከደኅንነት (ሴኵሪቲ)፣ ከመረጃ ጥበቃ (ዳታ ፕሮቴክሽን) እና ከጥብቅ ግንኙነት (ኮምዩኒኬሽን ፕራይቬሲ) ጋራ የተያያዙ ሰፋፊ ጥያቄዎችን ይመልሳል።

በእያንዳንዱ ምእራፍ መግቢያ የተነሳውን ርእሰ ጉዳይ ለማብራራት የተፈጠሩ ምናባዊ ክስተቶችና ገጸ ባህርያት ይገኛሉ። እነዚህ ገጸ ባህርያት የተወሰኑ ጉዳዮችን የሚያነሱበት እና የሚዘወተሩ ጥያቄዎችን የሚመልሱባቸው አጫጭር ምልልሶች በየምእራፉ ውስጥ ይገኛሉ። ከየምእራፉ የምንቀስማቸው ትምህርቶች ዝርዝርም በየምእራፉ ይቀርባል። በየምእራፎቹ የሚጋጣሙን በርካታ ቴክኒካዊ ቃላትና ስያሜዎች ትርጉም በመጽሐፉ መጨረሻ በማገናዘቢያ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በማብራሪያው ውስጥ የሚጠቀሱ ሶፍትዌሮችን በተመለከተ “በአጠቃቀም መመሪያ” (Hands-on Guides) ውስጥ ተጨማሪ ማጣቀሻዎች እናገኛለን። በዚህ “የመርጃዎች ስብስብ” (ቱልኪት) ውስጥ የሚገኝ ምእራፍ ወይም መመሪያ ተነጥሎ ለብቻው ሊነበብ ይችላል፤ በወረቀት ለማተምም (ፕሪንት) ሆነ በኤሌክትሮኒክ መልኩ ለሌሎች ለማካፈልም የተመቸ ነው። ሆኖም “የኢንተርኔት ደኅንነት በእጃችን” (Security in-a-box) መመሪያው የሚጠቅሳቸውን በመጽሐፉ እና በሶፍትዌር መመሪያው ውስጥ ተበታትንው የሚገኙትን ሊንኮች (links) እና ማገናዘቢያዎች በሚገባ ብንከተላቸው ከመመሪያው የበለጠ ተጠቃሚ እንሆናለን። የዚህ “እንጎቻ መጽሐፍ” (Booklet) የታተመ ቅጂ ካለን “የአጠቃቀም መመሪያውን” (Hands-on Guides) በምንጠቀምበት ጊዜ ሁሉ ከአጠገባችን ቢኖር መልካም ነው። በእንጎቻ መጽሐፉ ውስጥ ስለአንድ ዘዴ የተጻፈውን ምእራፍ ጨርሰን ሳናነብና ዘዴውን በሚገባ ሳንረዳው የዲጂታል ደኅንነታችን አስተማማኝ መጠበቂያ አድርገን ልንቆጥረው አይገባም።

ባለስልጣኑ ሽመልስ ከማል… ከ5 ሴት 10 ልጅ

አቶ ሽመልስ ከማል በኢትዮጵያ የሽብር ህግ በማዘጋጀት እና አሁን በእስር ላይ የሚገኙትን የሙስሊም ኮሚቴዎች፣ ጋዘጠኞች እና ሰላማዊ ታጋዮችን በህግ ሽፋን በማሳሰር ይታወቃል። አርአያ ተስፋማርያም እንደገለጸው ከሆነ ደግሞ ይህ ከፍተኛ የኢህ አዴግ ባለስልጣን ምግባር የጎደለው ባለጌ ሰው መሆኑን አጋልጧል። እንደአርአያ ጥቆማ ሽመልስ ከማል ከ5 ሴቶች አስር ልጆች ማስወለዱን ወይም መወስለቱን ገልጿል። በቀጥታ ወደ ጥቆማው ሙሉ ቃል ንዲህ ይላል።የኮሚኒኬሽን ሚ/ር ባለስልጣን የሆነው ሽመልስ ከማል ሁለት ልጅ የወለደችለት ሚስቱን በቅርቡ በመፍታት ከቤት እንዳባረራት ታማኝ የቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል። ከኢትዮጵያ ሱማሌና የመን ወላጆች የምትወለደው እንዲሁም ሁለት ልጆች የወለደላት ሽመልስ በሴቶች እህቶቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ተብሏል። ይህቺ ሴት አምስተኛ ሚስቱ ስትሆን ከአምስቱም ሴቶች ሁለት- ሁለት ልጅ ባጠቃላይ 10 ልጅ ሽመልስ ከማል እንደወለደ ማረጋገጥ ተችሏል። አራተኛ የነበረችው ሚስቱ የቅርብ ጓደኛው የሆነው ጋዜጠኛ ተፈሪ መኰንን ታናሽ እህት ስትሆን ሁለት ልጅ ካስወለዳት በኋላ ከቤቱ አውጥቶ ከነልጆችዋ እንደጣላት ታውቋል።
ሽመልስ ከማል ከ5 ሴቶች ለወለዳቸው 10 ልጆች ምንም አይነት የማሳደጊያ እገዛ እንደማያደርግና እንዳውም መብታቸውን እየገፈፈ በግፍ እንደሚያባርራቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። ..ሽመልስ ከማል ከሴት እንዳልተፈጠረ፣ ሴት እህቶች እንደሌሉት ይህን አይነት ጭካኔ የተሞላበት ነውረኛ ድርጊት በተለያዩ እንስቶች ላይ መፈፀሙ ከአሳፋሪነቱ ባሻገር ይህቺ አገር በምን አይነት ጭራቆች እንደምትመራ ፍንትው አድርጐ ያሳያል። ሽመልስ ከማል የሚዋሸው፣ ንፁሃንን የሚወነጅለው፣ የሚቀባጥረው፣ ..ከምንም ተነስቶ አይደለም፤ እንዲህ አይነት ርካሽ ተግባር ባለው ስርአት መፈፀም ስለሚችል ነው።


ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ፦ “መንግስታዊው ‘ጥቁር ሽብር’ የህዝብን የድል ችቦ አያጠፋውም!”

ከቀናት በፊት በእለተ ጁምአ በታላቁ አንዋር መስጂድ በመንግስት ታጣቂዎች የተወሰደው ድንበር የለሽ ጭፍጨፋ የሙስሊሙ ህብረሰተብ ሰላማዊ ትግል በታሪኩ ሌላ መጠምዘዣ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት እንዲሆን የሚያስገድድ ነው፡፡ በዚህ በመንግስት የደህንነት ኃይሎችና በፖሊስ ሀላፊዎች ከቀናት በፊት ታቅዶ በተወሰደ እርምጃ ከ6 ሺ በላይ የመንግስት ቅጥረኛ ሲቪል ለባሾች እንደተሳተፉበት መገለጹ ይታወሳል፡፡ ቅጥረኞቹ የተከበረው የረመዳን ወር የጁምአ ሰላት ከመሰገዱ በፊት በመስጊዱ ውጫዊ ሰሜናዊ አቅጣጫ ግርግር በማስነሳትና ከፖሊሶች ጋር ከሁለቱም አቅጣጫ ድንጋይ በመወራወር የታለመውን ውጤት ለማምጣት ሞክረዋል፡፡ በዚህም በአካባቢው የነበሩትን ጨምሮ በሁሉም አቅጣጫ የነበሩና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የጁምአ ሰላታቸውን እንዳይፈጽሙ እክል ከመሆናቸውም በላይ እጅግ በርካታ ጾመኛ ሙስሊሞች ላይ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል፡፡

Sunday, July 20, 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

ነጻነትን ለመጎናጸፍ ባሩዷን ማሽተት የግድ ነው !!!

ሪያድ ኢብራሂም
የወያኔ የግፍ ስርዓት በህዝብ ትከሻ ላይ ድሩን አድርቶ ፤ የማይጠረግ እስኪመስለን ድረስ ሁለት አስርት አመታቶችን በላያችን ላይ ዘልቋል። በሰላማዊ መንገድ የግፉ ስርዓት ተቋጭቶ ፍትህና እኩልነት በሀገራችን ይሰፍን ዘንድ ብዙ ተሞክሯል። ነገር ግን በወያኔ ስልጣን አልጠግብ ባይነት እና የሰላማዊው መንገድ ክርችም ብሎ በመዘጋቱ ባሩዷን ማሽተት ግድ የሆነበት ጊዜ ላይ ከደረስን ከራርመናል። ትግሉ ከኛ ምን ያህል የአላማ ጽናትን ይፈልጋል? ምን ያህልስ መስዋእትነትን ያስከፍለናል? እንዴትስ ብንታገል ካሰብነው የነጻነት ደጃፍ ባጭሩ ያደርሰናል ብለን ብንጠያየቅ ትክክለኛ ጊዜው አሁን ይመስለኛል።

አብዛኛው ኢትዮጵያዊም በተለይም በወጣትነት የእድሜ ክልል ያለው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣንን ከህወሃት መዳፍ ውጭ አይቶት ስለማያውቅ ፤ ሀገሪቱን እነሱ ብቻ እንዲመሩ መለኮታዊ የሆነ ፈቃድ ያላቸው እስኪመስለው ድረስ ውስጡ አምኖ ተቀብሎት ነበር ለማለት ይቻላል። ዳሩ ቢያምንም አይፈረድበትም ፤ ምክንያቱም እድሜ ሙሉውን በገዢነት የሚያውቀው ወያኔን ብቻ ነውና። ነገር ግን ከጥቂት አመታት ወዲህ ስንመለከት በሀገር ውስጥም ሆነ በባእድ ሀገራት በሚያስደንቅ ሁኔታ የወጣቱን አዲስ የሆነ የትግል መንፈስ በተለያዩ መድረኮች እየታየ ነው። እንደ እኔ ግምት ፤ የትግል መንፈሱን እንዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ካጦዙት አንዱ ስርዐቱ እጅግ ከፋ የሚባልበት ደረጃ ላይ መድረሱና ሌላው የገዥው አምባገነን ቡድን በአፈሙዝ ወደ ስልጣን የመጣ ቡድን በመሆኑ ለሰላማዊ መንገድ ባይተዋርና በር የማይከፍት በመሆኑ ነው።

የኣብራሃ ደስታ ታናሽ እህት ከስራዋ ታገደች

የኣብራሃ ደስታታናሽ እህት ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታገደች። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የሄልዝ ኦፊሰር(HO) ባለሞያ ስት ሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ስትሰራ ነበር።

የወረዳዋ ሃላፊዎች ተክለ የኣብራሃ ደስታ እህት መሆንዋ ያወቁት በቅርብ ግዜ ሲሆን ወድያውኑ የካብኔ ስብሰባ በመጥራት…. “ኣንቺ እንደወንድምሽ ዓረና ነሽ፣ ስለዚ እዚህ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም”. በማለት ማህተምና የቢሮዋ ቁልፍ ቀምተዋታል።

የወረዳዋ ኣስተዳዳሪዎች….. “ላንቺ እንኳን ስራ መሬቱም እሳት ሆኖ ያቃጥልሻል”…. በማለት ከየጠና ፅህፈት ቤት ምክትላ ሃላፊነትዋ፣ ከየኤክስፐርት ስራዋና ከህወሓት ኣባልነትዋ ኣግደዋታል።

ህወሓቶች ልክ በደርግ ገዜና ይደረግ የነበረው በቤታሰብ ደረጃ የማይመለከታቸው ንፁሃን ዜጎች እየደረሱ ማሰቃየት ጀምረዋል። ከዚህ ቀደምም የስየ ኣብራሃ ቤተሰብ በስጋ ዝምድናቸው ብቻ ለእስራትና ለእንግልት ተዳርገው ነበር።

ወኢዘሪት ተክለ ደስታ የህወሓት ኣባል እያለች….. “ወንድምሽ ዓረና ነው። ኣንቺም የወንድምሽ ተከታይ ነሽ”…. በማለት የደረሳት ጥቃት በጭፍኑ የወሰኑት መሆኑ ያስታውቃል።

የህወሓት ሊቀ መንበር ኣቶ ኣባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ የዓረና መስራችና ኣመራር ኣባል ነው።
እስቲ ወንድ የሆነ የህወሓት ኣመራር ኣቶ ኣባይን የ”….ወንድምህ የዓረና ኣባል የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ ተከታይ ስለሆንክ ከትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪነጥ፣ ከህወሓት ሊቀመንበር ነት ህና ከህወሓት ኣባልነጥ ውረድ”….. ይበል።

ህወሓቶች ፓርቲው የቤተሰብ ሃብት ኣድርጎዋት ስላሉ ሌሎች ፓርቲዎችም እንደየነሱ እየመሰላቸው በጅምላ ፍረጃ ተያይዘውታል።

የዓረና ኣባል እህት፣ወንድም ፣ ኣባት፣ እናት፣ ዘመድ፣ ጓደኛ መሆን ዓረና ከማስባሉ ኣልፎ ስራና ሃላፊነት የሚያስቀማ ወንጀል እያደረጉት ነው።

ኣብራሃ ደስታን ማስር፣ ማንገላታት፣ መደብደብ ሳይበቃቸው ወደ ቤተስብ ተሸጋግረዋል። የህወሓት ጉዞ የህዋሊት መራመድ ከጀመረ የቆየ ሲሆን ኣሁንም ቁልቁል እየተምዘገዘግ መሆኑ የሚጦቁም ነው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው….!!!


ምናምንቴዎች በሠለጠኑ ግዜ ህዝብ ያልቀሳል !!!

ኢትዮጵያ ላይ ጥቂት ምናምንቴዎች ሰልጥነው ህዝቡን እያስለቀሱት ነው። ኢትዮጵያዊያን ለብዙ ዘመን በብዙ ሃዘንና እንባ ውስጥ መኖራቸው የታወቀ ነው። የአሁኑ ሃዘን እንዲሁ ተራ ሃዘን፤ ልቅሶውም ተራ ልቅሶ አይደለም። መራር ሮሮ እንጂ። ይህን የህዝብ ሮሮ የሚሰማ መንግስታዊ አካልም የለም። በ“Global terrorist database” ውስጥ የሥም ዝርዝሩ ተመዝግቦ የሚገኘው “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ” ነኝ የሚለው ቡድን መንግስ ነኝ ቢልም የመንግስት መልክና ባህሪይ ሊኖረው አልቻለም። ህወሃት መንግስታዊ አሸባሪ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ለመሆን የሞራልም ሆነ የእውቀት ብቃት ያለው ቡድን አይደለም።

የኢትዮጵያው ጓንታናሞ ቤይ ‹‹ ማዕከላዊ ››

ዳዊት ሰለሞን
ማዕከላዊአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስቆጣ ባለ 70 ገጽ ሪፖርት ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙን ሪፖርት ከሌላው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ በአንድ ተቋም  በማጠንጠኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ማዕከሎች መካከል በአዲስ አበባ ዕምብርት በሚገኘው ማዕከላዊ ተጠርጣሪዎች ግርፋት፣ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ሪፖርቱ አትቷል፡፡አሜሪካ በሁለቱ የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎቿ ላይ በአልቃይዳ የተቀነባበረ ጥቃት ከተሰነዘረባት በኋላ ‹‹ሽብርተኛ›› በማለት የሰየመችውን ቡድን አባላት ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በጆርጅ ቡሽ ፊት አውራሪነት የሽብር ቡድኑ ዋነኛ መጠለያ ያለቻችትን አፍጋኒስታንን ወረረች፡፡ በዘመቻው በቁጥጥር ስር የዋሉ የአልቃይዳ አባላትና ተጠርጣሪዎች በጄኔቭ ስምምነት መሠረት በህግ የመዳኘት መብት እንዳያገኙ ለማድረግ የቡሽ አስተዳደር ከግዛቱ ውጪ በኩባ ድንበር የሚገኘውን ጓንታናሞ ቤይን ከዛሬ አስር አመታት በፊት ከጦር ካምፕነት ወደ ማሰቃያ ማዕከልነት አሸጋገረው፡፡‹‹በሽብርተኝነት›› ተጠርጥረው ወደ ጓንታናሞ ቤይ እንዲገቡ የተደረጉ

Saturday, July 19, 2014

‹‹የአንዳርጋቸው ጽጌን የሞት ቅጣት ሊያፀኑ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ናቸው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

ባለፈው ዓርብ በጽሕፈት ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ቅጣት ሊፀና የሚችለው በፕሬዚዳንቱ ይሁኝታ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ላይ ያላት የመሪነት ሚና እንዳልቀነሰ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸው የአገር ውስጥ የግል ዘርፉን ለማበረታታት እየሠራ እንደሆነና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እያሰረ ያለው በፖለቲካ አቋማቸው የተነሳ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪውን መጠንም ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ከ9፡00 ጀምሮ ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም አንዱ ሪፖርተር የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በድጋሚ የማይታይ ከሆነ የሞት ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆናል ወይ? ሲል የጠየቃቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሞት ፍርድ ተፈጻሚ የሚሆነው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ካፀደቁት በኋላ እንደሆነ አስታውሰው፣ ይኼን ጥያቄ መመለስ የሚችሉት ፕሬዚዳንቱ ብቻ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ቋሚ ሲኖዶስ ለፓትርያርኩ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለመጥራት ታቅዶ ነበር፡፡

ፓትርያርኩ ከአሁኑ መንገዳቸው ካልተጠቆማቸው ፤ ስህተታቸው ካልተነገራቸው ቤተክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ ሊጥሏት ይችላሉ፡፡

አንድ አድርገን ሐምሌ 12 2006 ዓ.ም፡-

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግን የመተርጎምና የማስፈጸም መብት ያለው ቋሚ ሲኖዶስ ፤ ውሳኔዬን አክብረው አላስከበሩኝም ፤ ጠብቀው አላስጠበቁኝም ላላቸው ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡

ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩን ያስጠነቀቀው ፤ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ባካሔደው ሳምንታዊ ስብሰባ ወቅት ነው፡፡ የቤተክህነቱ የፋክት ምንጮች  እንደተናገሩት  የማስጠንቀቂያው መንስኤ ፤ አቡነ ማትያስ ምክራቸውን ለስልጣነ ፕትርክናቸው አይመጥኑም ከተባሉ ግለሰቦችና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ክብርና ነጻነት በመጋፋት ከሚወቀሱ አካላት ጋር ግንባር በመፍጠራቸው ፤ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔንና ልዕልና የሚጻረር ተግባር በየጊዜው በመፈጸማቸውና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላቱን ክፉኛ በማሳሰቡ ነው፡፡

ከፍተኛ ገቢና አገልግሎት አቅም ባላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት የተመሰገኑ አለቆችን ከሓላፊነት በማንሳት በተመለከተ አገልጋዩና ምዕመኑ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ባልሰጡበት ኹኔታ ፤ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጻረር በአቡነ ማትያስ ትእዛዝ የተፈጸሙ ዝውውሮች ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ ሳይወስንና የሚመለከታቸው አካላት ሳያውቁ ልዩ ጸሐፊያቸውን በማንሳት በሌላ መተካታቸውና የመሳሰሉት ጉዳዮች የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ከፓትርያርኩ ጋር በከፍተኛ ደረጃ የተጠየቁባቸው ዐበይት ነጥቦች እንደነበሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ለፓትርያርኩ ጥያቄ ያቀረቡት የቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ ፤ ሳይገባቸውና ደረጃቸውን ሳይጠብቁ ‹ፓትርያርኩን ያማክራሉ› ያሏቸውን ግለሰቦች ስም በመጥቀስ ‹ከማን ጋር ነው የሚሰሩት? ማንን ነው  የሚሰሙት ? ከእኛ ጋር ይሰራሉ ወይስ አይሠሩም ?  › በሚል ጠንክረው እንደጠየቋቸው በምንጮቹ መረጃ ተመልቷል፡፡

አቡነ ማትያስ ስማቸው በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተጠቀሱት ሰዎች ጋር የሚመክሩትና የሚሠሩት ‹አላማዬን ስለሚያስፈጽሙልኝ ነው›› በማለት አቋማቸውን ለመከላከል ቢሞክሩም ‹‹ አገልጋዩና ምዕመኑ የሚዘረፍበትና የሚሰቃይበት ዓላማ ሊኖርዎት አይችልም›› በሚል ጠንካራ ምላሽ እንደተሰጣቸውና በኹኔታውም መደንገጣቸው ተሰምቷል፡፡

‹‹የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ይጎዳል በሚል እንጂ ተመራጩ ነገር ከእሳቸው ጋር(ፓትርያርኩ) ጋር መሥራት ማቆም ነበር፡፡›› ማለታቸውን የተጠቀሰላቸው አንድ የቋሚ ሲኖዶስ አባል ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩ በአጋጣሚው በብጹአን አባቶችና በወዳጆቻቸው ጭምር ቢመከሩም ሊያርሙት ስላፈቀዱትና ከሚገኙበት አሳሳቢ የአሰራር ኹኔታ አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይና ድንገተኛ ጉባኤ ስብሰባ ለመጥራት የሚገደዱበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር ማለታቸው ተነግሯል፡፡

አቡነ ማትያስ በቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ በተጠየቁባቸው ጉዳዮች ስሕተት  መፈጸማቸውን አምነው መቀበላቸውና  ‹‹ከእኛ ጋር ይሰራሉ ወይስ አይሰሩም›› በሚል በቁርጥ ተጠይቀውበታል ለተባለው አዎንታዊ መልስ መስጠታቸው ፤ በቃለ ጉባኤውን የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ ለጊዜው እንደገታው ጠቁመዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልናና የቤተ ክርስቲያኒቱን መብትና ጥቅሞች ከመሰል ተግዳሮቶች የማስጠበቅ ርምጃውን በተተኪ ተለዋጭ አባላቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበትም አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጋፋት ስሕተት መፈጸማቸውን አምነው ከተቀበሏቸው ርምጃዎቻቸው መካከል ፤ ብልሹ አሰራርንና ሙስናን በመዋጋት የአገልጋዩና ምእመኑ ከፍተኛ ተቀባይነት ማትረፋቸው የሚነገርላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደ/ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ዝውውር ዋንኛው ነው ተብሏል፡፡


አቶ አንዳርጋቸው ታፍኖ የተወሰደበት ቦታ እስከአሁን አልታወቀም ነገር ግን በደህንነት ሰዎች በደረሰበት ድብደባ ራሱን በመሳቱ ለህክምና ከአዲስ አበባ ውጪ ይዘውት ወጠዋ

ዛሬ የአዲስ አበባ ምንጫችን ብዙ ቦታዎችን ለማካለል ሞክሬ ነበር ነገር ግን የአንዳርጋቸው ይኖርበታል ተብሎ የሚገመቱ ቦታዎችን ማግኘት እንዳልቻለ ይሁን እንጂ ከደህነነት ሰዎች አንዱ በሆነ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሊኖርም እንደሚችል የግል አስተያየቱን ልኮልናል።

ዘጋቢያችን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በማናገር አቶ አንዳርጋቸው በአሁኑ ሰአት ከሰውነት ክፍሉ ውስጥ አንዱን ሰብረዉት ወይም ቆርጠውት እንደሚሆን  ስቃዩን በማብዛት ነገር ግን  እንዳይሞትባቸው ከአዲስ አበባ ውጪ ለህክምና ይዘውት ወጥተው ይሆናል የሚል በርካታ አስተያየቶች  መሰብሰቡን ዘግቦል።

አዲስ አበባ ላይ ሊያክሙት አይችሉም እንዴ ብለን ላነሳንለት ጥያቄ ሲመልስ፡ ይህን በአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ሊያደርጉት አይችሉም 1ኛ መረጃው ይወጣባቸዋል የራሳቸውን ሆስፒታል እንኮን አዲስ አበባ ላይ አያምኑትም። በወያኔ ውስጥ ውጥረት አለ! ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰውየውን ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ግራ የገባቸው ይመስላል። ስለዚህ እውነትም በአካሉ ላይ ጉዳት ደርሶበት ከሆነ ወደ ማይታወቅበት ስፍራ ወስደው ሊያሳክሙት ይችላሉ የሚለው ገዢ ሃሳብ ያመዝናል።

ይሁን እንጂ አቶ አንዳርጋቸው በሚያደርሱበት ጭካኒያዊ ድብደባ ሂወቱ በድንገት ሊያልፍ የሚችልበት አጋጣሚም ከፍተኛ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ኢቲቪ ድብደባውን በመደበቅ በደረሰበት አደጋ  ሂዎቱ በእስር ቤት አለፈ የሚል ዜና ሊያሰማን ይችላል የሚል ስጋት አለኝ ሲል አያይዞ ስጋቱን ገልጾልናል።

በዚህ አጋጣሚ አቶ አንዳርጋቸውን የታፈነበትን አካባቢ እና ቦታ ለድህረ ገጻችን ከሀገር ውስጥ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃ ለምትሰጡን አባይ ሚዲያ ማበረታቻ እንደሚሰጥ ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡


ወይንሸት ሞላ ክፉኛ ተደብድባ ዝግ ችሎት ቀረበች!

በትላንትናው እለት አንዋር መስጊድ ህዝበ ሙስሊሙ ሲደበደብ ወይንሸት ሞላ በስፍራው ነበረች። አንድ ከዚህ በፊት የሚያውቃት የደህንነት አባል በቀጥታ ወደሷ መጥቶ ይደበድባት ጀመር። በወቅቱ በስፍራው የነበረው በፍቃዱ ጌታቸው ስለሁኔታው እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር።

በወቅቱ የሰማያዊ ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው ወጣት ወይንሸት ሞላ አብራኝ ነበረች፡፡ አንዋር መስጊድ በወንዶች መግቢያ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ ላይ ሆነን ሁነቱን ስንከታተል ከአሁን ቀደም የሚያውቃትና ከህንጻ ላይ ሆኖ ሲቀርጽ የነበር ደህንነት ብቻዋን ነጥሎ እየደበደበ ወሰዳት፡፡  ‹‹ለምን ተወስዳታለህ!›› ብዬ በጠየኩበት ወቅት ከእነዛ ከመንገድ ተለቃቅመው ለድብደባ የተሰማሩት ወጣቶች መካከል አንዱ ሽጉጥ አወጣብኝ፡፡ ለመሳሪያ ልምድ የሌለው በመሆኑ ካርታው እግሩ ስር ወደቀበት፡፡ ወይንሸትን ይዘውም ወደ ውጭ ከነፉ!

እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም (ጽዮን ግርማ)

አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል። እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም. እንደተፈቀደለት፤ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር።

ተገናኝተን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም እንዲህ አለኝ፤ ”ሽብርተኛ አይደለኹም፤ ሀገሬ በማንም እንድትሸበር አልፈልግም አልፈቅድምም እኔ የምፈልገው የሀገሬ ሕዝቦች በነጻነት የሚያስቡባትና የሚንቀሳቀሱባት ሰላማዊ ሀገር እንድትኾን ነው”፤ እስክንድር ”ሽብርተኛ” አይደለምና ከእስሩም በላይ ያንገበገበው ”አሸባሪ” መባሉ ነበር።

እስክንድር ”ጋዜጠኛ” ነው። እስክንድር ሲጽፍ ሀገሪቱ ላወጣችው ሕግ ራሱን አስገዝቶ፣ በሀገሪቱ ሕግ ማዕቀፍ ሥር ራሱን ገድቦ ነው። ይህም ኾኖ ግን ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ አደጋ ሊደርስበት እንደሚችል፣ ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ ሊታሰር እንደሚችል ያውቃል። ግን ደግሞ ቢታሰር በቀጫጭን መስመርም ቢኾን በሀገሪቱ ሕግ ተዳኝቶ ከእስር ሊለቀቅ እንደሚችል ያምን ነበር። በዚህ እምነቱም የመጣበትን ለመቀበል ተዘጋጅቶ ሀገሩ ላይ ቁጭ ብሎ ይጽፋል።

የዛሬ ዕለት፣ በተወሰነ ደረጃ ሰኔ 1 1997 ዓ.ም መሰለኝ (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

የተከበረው የፖሊስ ሙያ ሳይንስ ያገኙትን መደብደብ ነው እንዴ!)

ዛሬ ረፋድ ላይ ከቤቴ ስወጣ፣ የምወደውን የዮጋ ስፖርት ሰርቼ እና አምላኬን አመስግኜ ነበር፡፡ ደስ የሚል ጥሩ ስሜትም ነበረኝ፡፡ ታላቁ አንዋር መስኪድ ከደረስኩ በኋላ የተፈጠረውን አሳዛኝ፣ ሰቅጣጭና ዘግናኝ ሁኔታ ከተመለከትኩኝ በኋላ ግን እስከአሁኗ ደቂቃ ድረስ እጅግ ተከፋሁ፤ ብዙ ነገሮች በአዕምሮዬ ተመላሰለሁ፡፡ ከምንም በላይ የሀገሬ አብዛኛው ህዝብ የተጎሳቀለ ሕይወት እና ይህቺ ሃብታም ሆና በብዙ ችግሮች የሚማቅቁ ዜጎችን የያዘች ሀገሬ አሳዘነችኝ፡፡ ኤልያስ ገብሩ
በጣም ሰላማዊ የሆነ ኃይማኖታዊ ሥርዓት በደቂቃዎች ውስጥ ወዳልታሰበ ብጥብጥ እና ረብሻ ውስጥ ሲገባ በዓይኔ ብሌን ስመለከት እንዴት አልከፋ?! በፖሊስ ፊት የተገኙ ዜጎች በሚያሳቅቅ መልኩ የዱላ በትር ሲያርፍባቸው መመልከት እንዴት አያም?! ፖሊስ ሮጦ የደረሰበትን ሰው አናት አናቱን በዱላ ከመታው በኋላ የምስኪን ወገኖቼ ደም ሲፈስ አይቼ እንዴት የዘወትር ፈገግታዬ እና ሳቄን ላምጣው?

ጨቋኙ እና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በሴቶች እህቶቻችን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ (የአብስራ ዳኛቸው)

         ወያኔ በ97ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ አይን ባወጣ ድርቅና ምርጫውን በማጭበርበር በአሸናፊነት ተወጥቻለሁ ብሎ የንፁሁን ህዝብ ድምፅ በመንጠቅ እና ድምፁ የነጠቀውን ህዝብ ያደረገውን ተቋውሞ በመሳርያ ሀይል በመጠቀም የንፁሁን ህዝብ ደም በማፍሰስ እና አካል በማጉደል በማን አለብኝነት ፖርላማውን ለብቻው በመቆጣጠር ህዝቡን ያለ ፍላጎት በግድ ሲገዛ የማህበረሰቡ አንድ አካል የሆኑ ሴቶች እህቶቻችን በወያኔ የደረሰውን እልቂት በመመልከት ከፖለቲካ ትግላቸው የሚሸሹና የሚያቆሙ መስሎ ተሰምቶት ነበር በአንፃሩ ግን ቡዙ ለአላማቸው ፅኑ የሆኑ ሴት ታጋዮች እንዲፈጠሩ መንገድ ከፍቷል።
        ሴቶች እህቶቻችን ተቋውሞአቸዉን ለመግለፅ እና በአለም ማህረሰብ ላይ ስለ ሀገራቸው ተጨባጭ ሁኔታ ለማሳወቅ ያስገደዳቸው ነገር ጨቋኙ የወያኔ ቡድን የሴቶችን መብት በሀገሪቷ ላይ ተንሰራፍቶ ባለው ስርአት እና በስርአቱ አንቀሳቃሾች እየደረሰባቸው ያለውን ግፍ አይምሮዋቸው ተቀብሎት አምኖ መቀበል ስላቃተው ነው።
        አምባገነኑ የወያኔ ስርአት በሀገሪቱ ላይ ዲሞክራሲን ያለገደብ አስፍኛለው በማለት ሴቶች እህቶቻችን በነፃነት የመናገር ሀሳባቸውን የመግለፅ መብት አላቸው በማለት ሲነገር ይደመጣል ነገር ግን እየተገበረ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው ለዚህም ምስክር የሚሆኑት በአሁኑ ሰአት በወያኔ እስር ቤት ተጥለው ከሚገኙት እንኳን ወጣቷ ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዮት ተጠቃሽ ናት።
        ወያኔ እንደሚናገረው ከሆነ ርዮት የታሰረችበት ዋናው ምክንያት እርሱ ሽብርተኛ ብሎ ከፈረጃቸው ነገር ግን ለሀገር ለህዝብ ነፃነት ከቆሙ ፖርቲዎች ጋር ተባብረሻል በሚል የሀሰት ውንጀላ ነው። ርዮት በጋዜጣ ሙያ ላይ ተሰማርታ እንደምትገኝ ይታወቃል በጋዜጠኝነት ስነምግባር ላይ ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ከህዝብ የሚያገኘው ማንኛውም ሀሳብ እና አቋም ግልፅ በሆነ መንገድ ለሚድያ በማቅረብ የህዝብን ድምፅ ማሰማት ነው ርዮትም የፈፀመችው ይህንኑ ሙያዊ ግዴታዋን ነበር ለዚህም አምባገነኑ የወያኔ ቡድን የሰጠው ምላሽ ቢኖር እርዮትን ወደ እስር ቤት መጣል ነበር።
         በአቋሟ ፅኑ የሆነችው እህታችን ግን እስሩም ሳይበግራት ለህዝብ በላከችው መልእክት ህዝቡ ሰላማዊ ትግሉን ከበፊቱ አጥብቆ መቀጠል እንዳለበት እና በወያኔ ማስፈራሪያ እንዳይበገር አሳስባለች። ከምንም በ ላይ የሚያሳፍረው ወያኔ ርዮት ማሰሩ ሳይሆን ርዮት በሌሎች እስረኞች ላይ በሀሰት እንድትመሰክር እና እሷ ነፃ እንድትወጣ ማባበላቸው ነው በአንፃሩ ደግሞ ርዮት እንደ ወያኔ ባለስልጣናት አይምሮዋን ለሆዳ የሸጠች እንዳልሆነች አሳይታቸዋለች።
        በተመሳሳይ ሁኔታ በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት እና አመራሮች ላይ የደረሰው እስራት እና ጭቆና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ሴቶች ሀሳባቸውን በነፃነት እንዳይገልፁ ምን ያህል እንደሚፈልግ የሚያሳይ ነው። እነዚህ ትግል ናፋቂዎች ድምጻቸውን በአደባባይ ማሰማታቸው ለጨቋኙ የወያኔ ቡድን ያላቸውን ተቋውሞ ለመግለፅ እና ህዝቡንም ከዚህ መራራ ህይወት በሰላማዊ ትግል ታግሎ እንዲላቀቅ ለመጠቆም ነበር። ሆኖም ግን ሴት ወጣቶቹ በፖሊስ ታፍሰው እስር ቤት ለመጣል ደቂቃዎች አልፈጀም በሌላ በኩል ግን ወያኔ እራሱ ሰው ሰላማዊ ትግሉን በነፃነት ያለምንም ፍራቻ ማድረግ ይቻላል እያለ ለብቻው በተቆጣጠረው ሚድያ 30 ግዜ ይለፍፋል። ህዝቡንም በውሸት ከአንገት በላይ እየደለለ ድብቅ ተግባሩን ይፈፅማል።
        ትዋቂዋ የነፃነት ታጋይ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ በነበራት የፖለቲካ አቋም በሀገሯ ላይ በነፃነት መታገል ባለመቻሏ ለእስር መዳረጓ የሚዘነጋ አይደለም። በአንፃሩ ደግሞ ለወያኔ የወገኑ የፓርቲው ደጋፊ የሆኑ ምንም አይነት የትምህርት እውቀት ደረጃ ሳይመዘን አንዳች መስፈርት ሳይቀመጥላቸው የአንድ አካባቢ ሰዎች በመሆናቸው ወይም ከጫካ በመምጣታቸው በስልጣን ላይ ተቀምጠው ለፍተው የተማሩ ሴቶች እህቶቻችንን ዋጋ በማሳጣት በደመ ነፍስ ሀገር ሲያስተዳድሩ ይታያሉ።
        ስለዚህ ይህን ስርአት በመደገፍ ጊዜያዊ ጥቅማችሁ አስጎምጅቷችሁ የህዝቡን ደም የምትመጡ የወያኔ ጭፍሮች ከግዚያዊ ፍርፋሪ ይልቅ የብዙኃኑን የኢትዮጵያ ሴቶችን ድምፅ በማክበር ከሌሎች ሴት ታጋዮች ጋር በመቆም ይህን አምባገነን ቡድን ከመሰረቱ ነቅሎ ለመጣል አብራችሁ መቆም እንዳለባችሁ ልቦናችሁ መገንዘብ አለበት።
             ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ሲስተካከሉ፦
-የሴቶች መብት የሚከበርባት
-ሴቶች በነፃነት ሀሳባቸውን የሚገልፁበት
-ሴቶች ባመኑበት የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ የሚሳተፍበት እና
-ሴቶች በዘር እና በጎሳ ሳይሆን በትክክለኛ የትምህርት ደረጃቸው ህዝብን የሚያገለግሉበት  
  አትዮጵያን መመስረት ይቻላል

                                   ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ በትግራይ ክልል በኩል ምን ያክል ታጣቂዎች እንደተሰለፉ ለማወቅ አልተቻለም።
የመከላከያ ሰራዊት ሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው አይታዩም። አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑንም ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በብአዴንና በህወሃት ታጣቂዎች መካከል የተጀመረው ግጭት እየሰፋ ሂዶ ኢህአዴግን ሊበትነው ይችላል በማለት እየተናገሩ ነው። የዚህን ዜና ዝርዝር እየተከታተልን እናቀርባለን።


Friday, July 18, 2014

በ”ሎሚ” መጽሔት የተጀመረ የፕሬስ አፈና

ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ከመንግስት በተላኩ ኃይሎች የ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ቢሮ ‹‹ያለ ንግድ ፍቃድ›› በሚል ሠበብ ታሸገ፡፡ እነዚህ ከየትኛው ወገን እንደተላኩ ያልታወቁት ኃይሎች በቢሮ ውስጥ የነበሩትን የሂሳብ ሠነዶች ‹‹ይዘን እንሄዳለን፣ አትሄዱም›› በሚል በተፈጠረው እሰጥ አገባ ምክንያት ስልክ ደውለው ቁጥራቸው ከ20 ያላነሱ የታጠቁ የፌደራል ኃይሎችን በመጥራት እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙትን ንብረቶችና ወረቀቶችን ጨምሮ እንዳናወጣ በመከልከልና በማስፈራራት አስቀድመው ታዘው ይዘውት የመጡት ወረቀት “ያልታሰደ ንግድ ፍቃድ” የሚል ቢሆንም፣ ንግድ ፍቃዱ የታደሰበትን ማጋገጫ ሲመለከቱ ደግሞ ፊት ለፊታችን ወረቀቱን በመሠረዝ “ያለ ንግድ ፍቃድ” በሚል ጽፈው አሽገውታል፡፡ በወቅቱ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ለንባብ የምትበቃው ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ወደ ማተሚያ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለች ይህ ችግር መፈጠሩ በሎሚ አባላቶች ላይ ግሬታን ቢፈጥርም፣ በተወሰደው ሕገ-ወጥ እርምጃ ሳንደናገጥ ከምንገባበት አንድ ቀን ዘግይተንም ቢሆን በተከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ማተሚያ ቤት ልናስገባ ችለናል፡፡ በወቅቱም ቢሮአችን እንደሚታሸግ ለምን አስቀድማችሁ በደብዳቤም ሆነ በስልክ አላሳወቃችሁንም ቢባሉም ‹‹የእናንተ ስፔሻል ኬዝ ነው፤ እኛ ከላይ ታዘን ነው›› የሚል ምላሽ ሠጥተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሎሚ መጽሔት አጋር ሆና በሣምንት ሁለቴ ለንባብ የምትበቃው ‹‹አፍሮ ታይምስ›› ጋዜጣም ከወዲሁ ልትዘጋ እንደምትችል አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የዞን 9 አባሎች ያውቁ እንደነበር መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡ ይኸውም እነዚሁ ኃይሎች ከመጀመሪያው ቀን በተለየ ሁኔታ በበነጋታው ተደራጅተው በመምጣት “ሠነዶችን እንፈልጋለን” በሚል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌደራል ኃይሎች የታገዘ የ5 ሠዓታት ፍተሻ (ከብርበራ አይተናነስም) ከአካሄዱ በኋላ በቢሮ ውስጥ የሚገኙትን የሂሳብ ሠነዶች በሙሉ ሰብስበው ወስደዋል፡፡ ሆኖም ግን የምንፈልገው የሂሳብ ሠነዶችን ይበሉ እንጂ፣ በቢሮው ውስጥ የሚገኙትን በተለያዩ ጊዜ የታተሙ የሎሚ መጽሔቶች፣ የአፍሮ ታይምስ ጋዜጦችና በእጅ ጽሁፍ የተተየቡ ወረቀቶችን አንድ በአንድ ሲፈትሹ ተስተውሏል፡፡ ይሄ ሕገ-ወጥ እርምጃ የእኛ የፕሬስ ውጤቶች በሆኑት ሎሚ መጽሔትና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ሆነ ተብሎ ለማጥቃት የታለመ መሆኑን የሚያመለክተው እነዚሁ ያልታወቁት ኃይሎች አስቀድመው ከመምጣታቸው በፊት ‹‹የአፍሮ ታይምስ ቢሮን ለማሸግ እየመጣን ነው›› በማለት የደወሉ ቢሆንም፣ ቢሮ ድረስ መጥተው የነበሩትን ሠነዶች ከወሰዱ በኋላም ከአለቆቻቸው ጋር በስልክ በመነጋገር ሊያሽጉበት ይዘውት መጥተው የነበረውን የማሸጊያ ወረቀት ሳያሽጉበት ተመልሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአንድ ወር በፊት ገዢው መንግስት ነፃውን ፕሬስ ጥላሸት በመቀባትና እርምጃ እንደሚወስድ (ሎሚ መጽሔትን ጨምሮ) በፈበረካቸው የተለያዩ ዶክመንተሪዎቹ ሲዝት የቆየ ሲሆን፣ አሁን አፈናውን በሎሚ መጽሔት ‹‹አሃዱ›› ብሎ ጀምሯል፡፡ ሎሚ መጽሔትም ሆነ አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ እራሱ ገዢው መንግስት ባወጣው የፕሬስ አዋጅ መሠረት ሕግና ደንቡን ተከትለን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ድምጽ በመሆን ተገቢውን መረጃ በወቅቱ እያደረስን ቢሆንም፣ ይህንን ያልወደደው ገዢው መንግስት ነፃ ፕሬሱን ከነአካቴው ለማጥፋት የተለያዩ ወጥመዶችን እያዘጋጀ መሆኑን አንባቢያን እንድታውቁልን እንፈልጋለን፡፡ ውድ አንባቢዎቻችንም ይሄንን ተገንዝባችሁ እስከመጨረሻው ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመቀበል ከጎናችን እንድትቆሙ እናሳስባለን፡፡


የወያኔ ጭካኔ በአንዋር መስጊድ

እነዛ ሰላማዊ ሙስሊም ወጣቶች ያለ ርህራሄ እንደዳጉሳ ሲወቀጡ አየሁ፡፡ ህጻን፣ ሽማግሌ፣ ሴት፣ ርጉዝ ሳይባል በጭካኔ ተደበደቡ፡፡ ታፈሱ! አንዱ ደብድቦ ያሳለፈውን ሌላኛው በተራው ይቀበለዋል፡፡ ተዝለፍልፎ የወደቀ የወደቀበት ላይ ይወቀጣል፡፡ ወጣቶቹ አገር ሰላም ነው ብለው ለመስገጃ የወሰዷቸው መስገጃ ወረቀቶች ደም በደም ሆነዋል፡፡

ፖሊስና ደህንነቶች በድብደባው ቢሳተፉም ያለ ርህራሄ ወጣት አዛውንቱን በቆመጥ የተደባደቡት ከየ ጎዳናው የተለቀሙት ወጣቶች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለመሆናቸው አለባበሳቸው በግልጽ ያሳያል፡፡ ፖሊስ አትደብድቡ እያላቸው እንኳን የሚሰሙ አይደለም፡፡ ሽጉጥ ማቀባበል የማይችሉት ሽጉጥ ተሰጥቷቸው ሲያስፈራሩ ካርታው ሲወርድባቸው ተመልክቻለሁ፡፡

በወቅቱ የሰማያዊ ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው ወጣት ወይንሸት ሞላ አብራኝ ነበረች፡፡ አንዋር መስጊድ በወንዶች መግቢያ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ ላይ ሆነን ሁነቱን ስንከታተል ከአሁን ቀደም የሚያውቃትና ከህንጻ ላይ ሆኖ ሲቀርጽ የነበር ደህንነት ብቻዋን ነጥሎ እየደበደበ ወሰዳት፡፡ ‹‹ለምን ተወስዳታለህ!›› ብዬ በጠበኩበት ወቅት ከእነዛ ከመንገድ ተለቃቅመው ለድብደባ የተሰማሩት ወጣቶች መካከል አንዱ ሽጉጥ አወጣብኝ፡፡ ለመሳሪያ ልምድ የሌለው በመሆኑ ካርታው እግሩ ስር ወደቀበት፡፡ ወይንሸትን ይዘውም ወደ ውጭ ከነፉ!

ወይንሸት ከተያዘች በኋላ የእነዛ አረመኔዎች ዱላ እኛም ላይ አረፈ፡፡ ፖሊሶች ደክሟቸውን ይሁን አዝነው ሲተውን ከየት እንደመጡ የማይታወቁት ወጣቶች ግን እስኪበቃቸው ደብድበውናል፡፡

በድብደባው መሃል አንድ ፖሊስ ክርስቲያን መሆኔን በመግለጽ ከአዛውንቶችና ከህጻናት ጋር ስለቀላቀለኝ እንደነዛ ወጣቶች ተዝለፍልፎ ከመውደቅ ተርፌያለሁ፡፡

እንግዲህ አንድ አገር እስከኖርን ድረስ፣ ጭቆናውም የሁላችን እስከሆነ ድረስ ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ ሊወጣ አይችልምና እኔም እንደወንድሞቼ በአጠና ተደብድቤ ተለቅቄያለሁ፡፡ ግን አልተሰማኝም፡፡ ከእኔው ይልቅ የማይችሉት ዱላ ያረፈባቸው ህጻናትና አዛውንቶች ጣር ልብ ይሰብራል፡፡ ወይንሸት ላይ ያረፈው በትር ያማል!

ጌታቸው ሽፈራው

በየረር ባሬ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከታሰሩት የአገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ አረፉ

ከወራት በፊት በየረር ባሪ ጎሳዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት 19 አገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ በእስር ቤት ውስጥ ማረፋቸው ታውቋል።

የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች አስከሬን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሟቾቹን በራሳቸው ጊዜ በመቅበራቸው የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሞ አስነስተዋል። ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ የክልሉ ፕሬዚዳንት ልዩሚሊሺያዎችን ወደ አካባቢው በመላክ ላይ እያሉ ፣ ከአዲስ አበባ በተላለፈ ትእዛዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ፈጥኖ በመንቀሳቀስ ልዩ ሚሊሺያውን አግቶ አስቁሞታል። ሚሊሺያውም ወደ ጅጅጋ እንዲመለስ መደረጉን ለማወቅ ተችሎአል። ይክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ፣ እርሳቸው የሚያዙት ሚሊሺያ በመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ትእዛዝ ወደ መጣበት እንዲመለሱ መደረጋቸው ያበሳጫቸው ሲሆን፣ እስካሁን ግን ይህ ነው የሚል መልስ አልሰጡም። በክልሉ ፕሬዚዳንትና በተለይም በደህንነት ሚኒስትሩ ጌታቸው አሰፋ መካከል የተፈጠረው ልዩነት እርስ በርስ እስከ መዘላለፍና መካሰስ አድርሷቸዋል። አቶ አብዲ የክልሉን የደህንነት ሃላፊ የህወሃቱን መቶ አለቃ አወጣሃኝን ካሰሩ በሁዋላ ልዩነቱ እየሰፋ ሄዷል። አቶ አብዲም በቅርቡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው ከእንግዲህ
የደህንነት ሃይሎችን እንዳይፈሩዋቸው፣ በክልሉ ያሉት ብቸኛ ሰው እርሳቸው መሆናቸውን መናገራቸውን መዘገባችን ይታወቃል።

የህወሃት ባለስልጣናት አቶ አብዲን ለመተካት ፈተና እንደሆነባቸው እየተነገረ ነው። አቶ አብዲ በክልሉ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ባላቸው ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ይደገፋሉ። ይሁን እንጅ በቅርቡ አልሸባብ ኦጋዴን ውስጥ ገብቶ 33 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን ተከትሎ የመከላከያና የአገር ውስጥ የደህንነት ሃይሉ ፣ ጣታቸውን በአቶ አብዲ ላይ መቀሰር ጀምረዋል።


የዘንድሮ እስር ‹‹ጸበል ቅመሱ›› ሁነብኝ ጃል! (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

(የህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 30 ሳይሻር ተሽሮ ከሆነ መሻሩን ተቃዋሚዎች ይወቁት!)

የምንወዳት ኢትዮጵያ ሀገራችን በተለያዩ ሥርዓታት ውስጥ የተለያዩ የሰዎችን እስር አስተናግዳለች፤ ዛሬም እያስተናገደች ትገኛለች፡፡በ97 ዓ.ም ምርጫውን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮች፣ የግል ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች …ታስረው ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት በኋላ በይቅርታ፣ በነጻ …መፈታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጊዜም በኋላ፣ በተለይ አፋኝ በሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ብዙዎች ታስረዋል፣ እየታሰሩም ይገኛሉ፡፡ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳናበዘንድሮ ዓመት ግን የምናየው እስር የተለየ ሆነብኝ፡፡ የሕገ- መንግሥቱን አንቀ ጽ 30 መሰረት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላቶቻቸው ለሰልፉ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት

የፖለቲከኞቹ እስር እና ያስከተለው ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን ወደኢትዮጵያ ተላልፈው የመሰጠታቸው ጉዳይ በማንሳት “የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሽፋንአድርጎ የሚመጣአሸባሪነትንአይታገስም”ማለታቸውን ዘግቧል።

     የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ በሀገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት መካከል አቶ ሐብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከአንድነት፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ አቶ አብርሃ ደስታ ከአረና ትግራይ (ዘግይቶም ቢሆን ፍ/ቤት ቀርቧል)፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። የጸረ ሽብር ግብረሃይል የግንቦት 7 ልሳን ከሆነው ኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ግንኙነት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በቁጥጥር ስር ማድረጉን በደፈናው በዕለቱ የገለጸ ሲሆን የተያዙት የአንድነት፣ የሰማያዊና የአረና አመራሮች መሆናቸው ሲታይ መግለጫው እነሱን በቀጥታ የሚመለከት ስለመሆኑ የብዙዎች ግምት ሆኗል።

Thursday, July 17, 2014

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።ግፍ መብቃት አለበት። በጥቂት የህወሓት ሹመኖች ትዕዛዝ በኢትዮጵያዊው ወታደር ላይ የሚደርሰው ውርደት ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሓት ሠራዊት አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም። ሠራዊቱ ለራሱ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት ዘብ የመቆም ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት የባንዳ ሠራዊት ሆኖ ሕዝብን በማሰቃየትና ሀገርን በመበደል ተግባር ላይ ተሠማርቶ ማየት አንሻም። ይህንን ለራሱ ክብር ያለው፤ አገሩንና ሕዝቡን የሚወድ የሠራዊቱ አባልም የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም።ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚከተለው ሀገራዊ ጥሪ ለመላው የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ያቀርባል።ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ወይም የፓሊስ ሠራዊት አባል! በጥቂት የህወሓት ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ሆነህ የገዛ ራስህን፣ የቤተሰቦችህን፣ የወገንህን እና የአገርህን ስቃይ ማራዘምህን አቁም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ እንጂ የጥቂት ጎጠኞች ሎሌ ልትሆን አይገባም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታ እንጂ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ስጋት መሆን የለብህም። አንተ የመጪው ትውልድ አርዐያ እንጂ ሕፃናትንና ወጣቶችን ማስፈራሪያ መሆን የለብህም።የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ! ራስህን ተመልከት! ራስህን ታዘብ! ዛሬ ያለህበት ሁኔታ አሳፋሪ ነው። አዛዦችህ አገርን፣ ትውልድንና ታሪክን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው። አንተን ተጠቅመው ነው ይህንን ዓላማቸውን የሚያስፈጽሙት። ይህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆችህ ውርደት ነው። ከወያኔ ባርነት ራስህን ነፃ አውጣና የነፃነት ታጋዮችን ተቀላቀል። ወያኔ መጥፋቱ አይቀርም። ወያኔ የቀድሞውን ጦር እንደበተነው አንተን ለመበተን የሚሻ የለም። አንተ ዛሬ ከወገን ጋር ወገንተኛነትህን ካሳየህ ከአገዛዙ ጋር እጠፋለሁ ብለህ አትስጋ። ለዚህም ነው አንተ ዛሬ በግልም ሆነ በቡድን የምትወስደው እርምጃ የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለን ወገናዊ ጥሪ የምናቀርብልህ።ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ወገናችን!ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን ቁም። ከገራፊዎችና ገዳዮች ጎን ሳይሆን ከነፃነት ታጋዮች ጎን ሁን። ዛሬውኑ ወስን። አሁን የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል ሆኗል። ያሉበትን ታውቃለህ፤ ተቀላቀል። አልያም የጠመንጃህን አፈሙዝ በፋሽስት አለቆችህ ላይ አዙር። ይህንን እርምጃ በመውሰድ ከታሪክ ተወቃሽነት እራስህን በመታደግ ለአገርህና ለወገንህ አለኝታህን አረጋግጥ።ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እህት በ24 ሰአት ከሃገራቸው ተባረሩ።

ለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ

የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።

በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት ጊዜ የጊዜ ገደብ ከተሰጣቸው በሁዋላ ዛሬ ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል። ወ/ሮ ብዙአየሁ የአቶ አንዳርጋቸውን

ቤተሰቦች በመወከል ጉዳዩን ለመከታተል በሚል መሄዳቸውን ከቤተሰቦች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢህአዴግ የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የእግር እሳት እንደሆነበት የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አቶ አንዳርጋቸው የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆናቸውና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የግንቦት7 ዝናም

ከምንጊዘውም በላይ በመጨመሩ የገዢውን ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን እያበሳጨ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አሁንም በተከታታይ ስልኮችን እየደወሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው።

በፐርዝ አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ከእንግሊዝ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለቆንስላው ላቀረቡት ጥያቄ የፐርዝ የእንግሊዝ የቆንስላ ሃላፊ፣

አገራቸው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየተከታተለችው ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል።

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በላኩት ደብዳቤ የአቶ አንዳርጋቸው መታፈን ” ወያኔ ፍጹም አወሪነቱን ያሳየበት እና ዘላአለም የነጻነት ታጋዮችን ለማስፈራራት እና ከትግሎ ሜዳ ለማስውጣት

የተጠቀመበት የትእቤት ስራ ነው። ” መሆኑን ያሳያል ካሉ በሁዋላ፣ የተወሰደው እርምጃ ህዝቡን ለትግል እንደሚያነሳሰው ገልጸዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ማእከላዊ እስር ቤት እንዲታሰሩ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የድርጅቱ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ

አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የምክር ቤት ሰብሳቤ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም አረና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚና ታዋቂ ጸሃፊ መምህር አብርሃ ደስታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣

ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። አንድነት ፓርቲ የተያዙት ሰዎች በ48 ሰአታት ውስጥ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን በመግለጽ ክስ መስርቶ ነበር። ይሁን እንጅ ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል።


ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ ክስ ተመሠረተ

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጦማሪያን፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ

ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሽብርተኝነት ወንጀል በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ለአመፅ ተግባር በህቡዕ መደራጀታቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡

እንደ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ በመደራጀት፣ የአጭርና የቅርብ ጊዜ ግብ በማቀድና በመንደፍ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙት የግንቦት 7 እና የኦነግ ድርጅቶች መመርያና ሐሳብ ሲቀበሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል ስትሠራ መቆየቷን ክሱ ያስረዳል፡፡

የህቡዕ ቡድኑ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ‹‹ሴኩሪቲ ኢን ቦክስ›› የተባለ ሥልጠና እንዲሠለጥንና እንዲደራጅ ስትመራ መቆየቷም በክሱ ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተጠርጣሪ በፍቃዱ ኃይሉ የአገር ውስጥ የሽብር ቡድንን በመምራትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ፣ እንዲሁም ግብ በማስቀመጥና ስትራቴጂ በመንደፍ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተጠርጣሪ ናትናኤል ፈለቀ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የህቡዕ ድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን በሥሩ ላሉት አባላት የሥራ ክፍፍል መመርያ በመስጠት፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር መመርያ ከመቀበሉ በተጨማሪ፣ ለአመፅ ተግባር የሚውል የተላከለትን 48,000 ብር ማከፋፈሉንም ክሱ ያብራራል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ መሥራችና አባል በመሆን የግንቦት 7 እና የኦነግን ስትራቴጂና ዕቅድ በመቀበል በውጭና በአገር ውስጥ ባሉ የቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በውጭና በአገር ውስጥ ሥልጠና በመውሰድ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሰርና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ እንደሚያስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሉና በሚያስገኘው ውጤት ተስማምተው በሕገ መንግሥት ሥርዓት የተቋቋመን መንግሥት በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ በማሰብ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. እስከተያዙበት ዕለት ድረስ በህቡዕ ተደራጅተው፣ የሥራ ክፍፍል በመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን፣ የአመፅ ቡድኖችን በማደራጀት ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በሁከት ለመለወጥ በመሞከር ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡  



በየቀኑ ከልክ በላይ አልኮል የምትጎነጨው ሰመሃል

       የአዜብ መስፍንና የመለስ ዜናዊ ልጅ የሆነችው ሰመሃል መለስ በየቀኑ ከልክ በላይ አልኮል እንደምትጐነጭ የቅርብ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል። የ27 አመት ወጣቷ ሰመሃል አቅሏን እስክትስት ከጠጣች በኋላ እየተነፋረቀች እንደምታለቅስ ታውቋል። ቦሌ በሚገኘውና የቀድሞ ስዩም መስፍን መኖሪያ ቤት ውስጥ ከወላጅ እናትዋ ጋር የምትኖረው ሰመሃል የሚያስለቅሳት ነገር አስገራሚ ሆኖዋል። ሰመሃል በአባትዋ ሞት አሊያም በእናትዋ መታመምና በደረሰባት የፖለቲካ ኪሳራ እንዲሁም ብዙ ባለስልጣናት ስለማይጠይቋቸው “ተበሳጭታ” ይሆን የምታለቅሰው?..የሚሉት ዋናዎቹ ናቸው። ሰመሃል ማወቅ ያለባት ነጥብ አለ። በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖች እስር ቤት በማጐር፣ በመግደልና ቤተሰብ በመበተን፣ በማሰቃየትና ከአገር እንዲሰደዱ እንዲሁም በስደት እንዲያልቁ በማድረግ ወንጀል የፈፀሙት አባትዋ መለስ ዜናዊ እንደነበሩ ልታውቅ ይገባል። የ3 አመቱ ህፃን ናፍቆት አባቱን እስክንድር ነጋን ከጉያው እየደበደቡ ሲወስዱት ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ አንቺ ምናልባት ከአባትሽ ጋር ትሳሳቂ ነበር። የ10 እና 13 አመት ታዳጊ ወጣቶች በምርጫ 97 በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ቀጥታ ትእዛዝ የሰጡት (ያውም በቲቪ ወጥተው) አባትሽ መለስ ዜናዊ ናቸው። የነዛ ሕፃናት ወላጆች ዛሬም ያለቅሳሉ። በ10ሺዎች የሞቱለት የባድመ ጦርነት አስመልክቶ መሬት እንስጥ ያሉት መለስ ዜናዊ ፓርላማ ቀርበው « ቁራሽ መሬት ሄደ ብለን ሃዘን አንቀመጥም፤ ሙሾ አንወርድም» ብለው በጀግኖቹ መስዋእትነት የተሳለቁ ናቸው። የጀግኖቹ እናት ዛሬም ታለቅሳለች። አባትሽ ትተውት የሄዱት የዘርና ጐሳ ፖለቲካ አገሩን እያመሰው ይገኛል። መለስ አስፋፍተውት በሄዱት እስር ቤቶች ዛሬም ዜጐች በጅምላ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ስንቱን ልዘርዝረው!?…እኩል እናልቅስ!?

ከእየሩሳሌም አርአያ


Wednesday, July 16, 2014

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥ አካሄድ መሆኑ ተገለጸ

-‹‹አሁን ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ሕገወጥና አደገኛ ነው›› የተጠርጣሪዎች ጠበቃበሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በክስ ላይ የሚገኙት ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን ስለጨረስኩ መዝገቡ ይዘጋልኝ›› በማለት መዝገቡ እንዲዘጋ ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለና አደገኛ መሆኑን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያንና የሕግ መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሚቀርቡበት ዕለት ነበር፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ ጓደኞቻቸውና የተለያዩ የችሎት ታዳሚዎች በጠዋት ማልደው በፍርድ ቤት ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎቱ አልመጡም፡፡ ከ5፡30 ሰዓት በኋላ ሌሎች ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ተጠርጣሪዎቹና ፖሊስ ችሎት ቆይተው ሲወጡ፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን፣ ደንበኞቻቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸውን ለማጣራት የዕለቱን ተረኛ ዳኛ ለማነጋገር ገቡ፡፡ ጠበቃው ስለደንበኞቻቸው ፍርድ ቤቱን ሲጠይቁ፣ ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን በማሳወቅ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠይቆ መዘጋቱን ሲያስረዳቸው፣ ‹‹እንዴትና በምን ሁኔታ?›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ከመዘጋቱ ውጪ ምንም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡እስረኛ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የምርመራ መዝገቡ ሊዘጋ እንደማይችል የሚናገሩት ጠበቃ አመሐ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸው፣ በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ምንም ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑንም

የጨነገፉ የአፍሪካ መንግስታት የሞራል ዝቅጠት (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ


የጨነገፉ (ዉድቀት የገጠማቸው) መንግስታትን አስመልክቶ በቅርቡ በወጣ መረጃ መሰረት ከአስሩ የመጀመሪያዎቹ ቁንጮ አገሮች ስድስቱ እና ከ25ቱ የመጀመሪያዎቹ ቁንጮ አገሮች 18ቱ በአፍሪካ የሚገኙ አገሮች ናቸው፡፡ የዚህ ትችት ዓላማ የጨነገፉ የአፍሪካ አገሮችን ሬሳ መደብደብ አይደለም፣ ወይም ደግሞ በብዙ የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካን የመንግስት አስተዳደር ውድቀት ትረካ ለማውሳት አይደለም፣ እንደዚሁም ለህዝቦቻቸው መሰረታዊ እና አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ማቅረብ የማይችሉ፣ የህዝቡን ደህንነት ማስከበር የተሳናቸው፣ እጅግ በጣም እየተስፋፋ የመጣውን ሙስና መቆጣጠር ያልቻሉ፣ መንግስታዊ ወንጀለኝነትን የሚያራምዱ፣ እየተስፋፋ የመጣውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ማስቆም የማይችሉ እና ሀብት ባላቸው እና በሌላቸው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የማይችሉ አቅመቢስ ድሁር የአፍሪካ ሽባ መንግስታት ን ለመንቀፍ አይደለም፡፡ስለአፍሪካ የጨነገፉ መንግስታት የሞራል ዝቅጠት ባሰብኩ ቁጥር ስሜቴ ይረበሻል፡፡

ኣቶ ዳኘው ይገዙ የሞት ፍርደኛው የዓረና ኣባል…!

ዓረና-መድረኽ “ዘመቻ ኣብራሃ ደስታ” ብሎ ህዝባዊ ስብሰባ በመኾኒ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ሲያካሂድ የእንዳሞኮኒ ወረዳ ኣስተዳዳሪ የሆነው ኣቶ ሃፍቱ ወላሞ በወረዳ የምትገኝ ታሕታይ ሓያ የምትባል ቀበሌ(ጣብያ) በመሄድ “የዚህ ቀበሌ ዓረና ኣባላት ሞተር ዳኘው ይገዙ ነው ስለዚ በኣከባቢው የዓረና እንቅስቃሴ ለመግታት ዋና መፍተሄ እሱን መግደል ነው።” በማለት ለኣከባቢው ታጣቂዎች ዳኘው ከገድልነው ሌሎቹ ኣባላት ቦታቸው ይይዛሉ በማለት እንዲገድሉት ትእዛዝ ኣስተላልፏል።

ኣቶ ዳኘው ይገዙ የ 65 ዓመት ኣዛውንት ሲሆኑ በጀግነታቸው የወረዳዋ ህዝብ የሚያውቃቸውና ታላቅ ተሰሚነት ያላቸው ናቸው።

ኣቶ ዳኘው የሞት ፍርድ የሰጣቸው ፍርድ ቤት ኣይደለም የወረዳዋ ኣስተዳዳሪ የሆነው ኣቶ ሃፍቱ ወላሞ እንጂ…! ይህ የተናገረው ህዝብ ሰብስቦ በሓምሌ 6 /2006 ዓ/ም ነው።

የዓረና ኣባላት የዓላማቸው ፅናት ሁሉም ዓየነት መስዋእትነት እስከመክፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ኣድርጓቸዋል።

ኣቶ ዳኘው ፍርዳቸው ለመቀበል ዝግጁ ሁነዋል።

የህወሓት መንግስት ግን ወደ ጥፋት መንገድ እየተራመደ ነውና ቆም ብሎ እንዲያስብበት እናሳስባለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!


በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ዓመፅ ተጀመረ…!!!

የሃረማያ ዩኒቨርሲት የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመመረቅያ ፅሑፍ ክፍያ ከዕጥፍ በላይ በመጨመሩ ዓመፅ ኣስነስተዋል።

ተማሪዎቹ ከትናንት በስትያ ሰኞ ሓምሌ 7 /2006 ዓ/ ም ክፍያው 3000ብር እንደሆነ ከዩኒቨርስቲው ሬጅስትራር የተፃፈ ደብዳቤ የተሰጣቸው ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው ሃሳቡ በመቀየር ክፍያው ወደ 8700 ብር ከፍ በማድረግ በቦርድ ለጥፎዋል።

ተማሪዎቹ ተሰባስበው ወደ ዩኒቨርሲቲው ሃላፊዎች የሄዱ ሲሆኑ ክፍያው ከዕጥፍ በላይ እንዲሆን የተደረገበት ወሳኔ ኣግባብነት እንደሌለውና ወደ ቀድመው መጠን ካልተስተካከለ እንደማይመዘገቡ ኣሳውቀዋል።

እንደምጫችን ኣገላለፅ ከሆነ ክፍያው ባንዴ ከእጥፍ በላይ እንዲሆን የትደረገው የመንግስት ሰራተኞች ደምወዝ ጭማሪ ተደርገዋል የሚል እንደሆነ ኣረጋግጠዋ።

የዩኒቨርስቲ ኣስተዳደር በጉዳዩ ኣስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ እንደሆነም ለማወቅ ተችለዋል።

ሃረማያ ዩኒቨርስቲ ልማታዊ መንግስታችን ስግብግብ ዩኒቨርሲት ብሎ ታፔላ እንደሚለጥፍለት ይጠበቃል።

“ስግብግብ ነጋደዎች” ነው…! ያለው በኢቲቪ እየተናገረ የሰማሁት ኣንዱ ቱባ ባለስልጣን።

ዓመፁ በኣግባቡ ይፈታ ይሆን? ወይስ እንደተለመደው መቺ ሃይል ይላካል…?


Tuesday, July 15, 2014

breaking news Andargachew Tsige transferred to a secret location outside Addis Ababa

 TPLF secret police has taken Andargachew Tsige, the kidnapped Ethiopian opposition leader, to a secret location outside Addis Ababa, perhaps the Tigray capital Mekele, according a reliable source in Addis Ababa.

Ethiopian Review's source, who is a disgruntled ANDM member, said that the TPLF leaders kept the abduction and interrogation secret from the other factions of EPRDF because they suspect that ANDM has been infiltrated by Ginbot 7. The paranoid TPLF secret police that is led by Debretsion Gebremichael and Getachew Assefa is currently monitoring the phone, email and SMS of all ANDM senior leaders, including Deputy Prime Minister Demeke Mekonnen.

Ato Andargachew was a founding member of ANDM before he joined the opposition.

“አሸባሪ”ዎቹን ፍለጋ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

 (የሽብር – ዘፍጥረት ፫)    ….በሁለት ተከታታይ ጽሁፎች የሽብርተኝነትን አነሳስ እና የአልሸባብን አፈጣጠር በደምሳሳውም ቢሆን መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ መግባቱ ለምስራቅ አፍሪካው አደገኛ ቡድን መወለድ መንስኤ ስለመሆኑ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች እና ከሞቋዲሾ እስከ ኪስማዩ በደም ከተፃፈው የሠራዊቱ አባላት ገጠመኝ መረዳት ችለናል፤ ይህ ቡድን ዛሬ ከመንግስታዊ ተቋማት ይልቅ ንፁሀን ዜጐችን ዒላማ አድርጎ፣ የቀንዱን አገራት አካባቢ ወደ ሕግ-አልባ የጦር ቀጠናነት መለወጥ የሚያስችለውን ግዙፍ ኃይል አካብቶ አስፈሪ እየሆነ ስለመምጣቱ ማስተዋሉ አዳጋች አይደለም፡፡ ለርዕሰ-ጉዳያችንም መቋጫ የምናደርገው የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ሽብር››ን እንዴት ለፖለቲካዊ ዓላማ እንደሚጠቀምበትና እነማንን በ‹‹አሸባሪ››ነት  ፈርጆ በመወንጀልና በማሳደድ እኩይ ተግባር ላይ መጠመዱን በጨረፍታ መመልከት በመሆኑ ወደዛው እናልፋለን፡፡ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ   የሽብር ድንበር…
የሽብር ድርጊትን ለዓላማቸው ማስፈፀሚያ መምረጣቸውን በይፋ አውጀው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ በአሰቃቂ አደጋዎች በሚመነዘሩ ጥቃቶች ንፁሃንን ለህልፈትና ለከባድ ፍርሃት በመዳረግ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ ጥያቄዎቻቸውን በኃይል ለማስፈፀም መሞከራቸው የተለመደ ነው፤ ለዚህ ይቅር ለማይባለው ጭካኔያቸውም የድል ችቦ ለኩሰው ጮቤ ሲረግጡ በሀዘን ተመልክተናል፤ በቅርቡ በጎረቤታችን ኬኒያ ውስጥ የተፈፀሙትን ዘግናኝ የጅምላ ጥቃቶችና ፍንዳታዎችን ተከትሎ ቡድኑ የሰጣቸው መግለጫዎችም ይህንኑ ያስረግጣሉ፡፡ ከሁሉም በፊት ግን ‹‹የሽብር ድርጊት ምንድር ነው?›› የሚለው ጥያቄ ተፍታቶ መመለስ የሚኖርበት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በዳሰሳችን የምናገኘው ምላሽ ዓለም-አቀፍ ማሕበረሰቡን የሚያቀራርብ ቢሆንም፣

በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል

በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። #Ethiopia  የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ከባድ መሳሪያዎች ተወልውለው በድንበሩ ዙሪያ ተኮልኩለዋል።


የአንዳርጋቸው ጽጌ መያዝ ፡ የግንቦት ሰባት ጥሪ እና የትሕዴን ሰራዊት መመረቅን ትከትሎ በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ሰሜን ምስራቅ ድንበር ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ለሰሜን እዝ ቅርብ የሆኑ የሰራዊቱ ምንጮቻችን በደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።እንዲሁም በአፋር ክልል ውስጥ ክፍተኛ ደህንነቶች በማፍሰስ ሕዝቡን እየሰለሉት መሆኑ ሲታወቅ ከፍተኛ አመጽ በክልሉ እንዳይነሳ ወያኔ መስጋቱ ታውቋል።

ወያኔ ተጠባባቂ ጦሩ ላይ እምነት ስለሌለው የትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ብቻ በተለያዩ ወረዳዎች በመሰብሰብ አስፈላጊውን መመሪያ የሰጠ ሲሆን በሁምራ ክዚህ በፊት ሰልጥነው የሰፈሩ እና መኖሪያቸውን እዛው ያደረጉ የወያኔ ልዩ ተጠባባቂ ጦር አባላት በነፍስ ወከፍ አዳዲስ ላውንቸር ክላሽንኮቭ እና ከበርካታ ጥይቶች ጋር እንደትድላቸው ታውቋል።

እንዲሁም በትግራይ ውስጥ የሰለጠኑ ሚሊሻዎች ከነትጥቃቸው ድንበር አከባቢ ከዚህ ቀደም መሬት ተሰቷቸው የሰፈሩትም ለዚሁ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ተደርገዋል።ታንኮች መድፎች እና ከባባድ መሳሪያዎች ወደ ድንበሩ በመጠጋት አስፈላጊውን አሰሳ እያደረጉ ሲሆን የ24 ሰአት ልዩ ጥንቃቄ የተሞላበት ወታደራዊ የቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ መልክ በጎንደር በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችን መሳሪያ ማስፈታት ሊጀመር መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህም የሚያምለክተው አማራው ከግንቦት ሰባት ጋር ይሸፍታል የሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑ ታውቋል። በዚህ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ይቀርባሉ።

ፍርድ ቤቱ በእነ ሐብታሙ ጉዳይ ትዕዛዝ አስተላለፈ

የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገ መንግስቱና የጸረ ሸብር አዋጁ በሚያዙት መሰረት እጃቸው ከተያዘበት አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባቸውና በቤተሰቦቻችውና በጠበቃቸው መጉብኘት መብታቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ጠበቆቻቸው ያልተሟሉላቸው መብቶች በፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ይከበሩ ዘንድ በዛሬው ዕለት ክስ መስርተው የማዕከላዊ አመራሮች ለቀረበባቸው ክስ በአካል በመገኘት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ሃላፊዎቹ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ሰዎቹን ፍርድ ቤት በ2/11/2006 ዓ.ም ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡የታሳሪዎቹ ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉና አቶ ገበየሁ ደምበኞቻቸውን ማግኘት አለመቻላቸውን ፍርድ ቤት ሲቀርቡም እንዲያውቁ አለመደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ጠበቆቹ ደምበኞቻቸውን ማየት እንዲፈቀድላቸውና በቤተሰቦቻቸውም እንዲጎበኙ እንዲደረግ ትዕዛዝ እንዲሰጥ አቤት ብለዋል፡፡ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ ታሳሪዎቹ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ እንዲደረግና ከጠበቆቻቸው እንዲመካከሩ ይደረግ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ከዚሀ በተጨማሪም በማዕከላዊ እንደሚገኙ የተነገረላቸውን ታሳሪዎች የፊታችን አረብ 4፡00 እንዲቀርቡ ሲል አዟል፡፡የማዕከላዊ ኃላፊም በፍር ቤቱ የተሰጠውን ትዕዛዝ መፈጸሙን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡

አብርሃ ደስታ ተደብድቦ ፍርድ ቤት ቀረበ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በትግራይ እየተካሄዱ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን በመዘገብ ይታወቃል። ለእውነት ሲቆም እንጂ፤ ለህይወቱ ሲሰጋ አይተነው አናውቅም። አብርሃ ደስታ ስራው መምህርነት ሲሆን፤ የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊም ነው። የትግራይ ተወላጅ ሆኖ ስለትግራይ መጥፎ በመዘገቡ የተናደዱበት ይመስላል። ባለፈው ሳምንት ትግራይ ውስጥ ታፍኖ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ ፖሊስ እስር ቤት መምጣቱን ዘግበን ነበር። እዚህ ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ብቻውን መታሰሩ እና በከፍተኛ ሁኔታ መደብደቡ አዲስ የደረሰን ዘገባ ነው።

አብርሃ ደስታ ጠያቂም ሆነ ጠበቃ የለውም። ከድብደባው የተነሳ በጣም መዳከሙ ነው የደረሰን ዘገባ የሚያመለክተው። በፍቃዱ ጌታቸው ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ከሆነ፤ አብርሃ ደስታ እንዳይታይ በማሰብ ለሊት ነበር እስር ቤት ያስገቡት። ይህ ብቻ አይደለም። በሚገርም ወይም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከለሊቱ 6፡30 ለሱ በተሰየመ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ለማወቅ ያልቻልነው ነገር፤ የፍርድ ቤቱ ሂደት፣ የክሱ ጭብጥ እና ይዘት ምን እንደሚመስል ነው። ነገሩን እንደ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ሳይሆን እንደሰው ስናስበው ትክክል አይመስልም። አንድን ሰው አፍኖ አምጥቶ፤ ደብድቦ እና አሰቃይቶ ፍርድ ቤት ማቅረብ የደረስንበትን የፍትህ ዝቅጠት የሚያሳይ ነው።

አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ሲናገር “የትግራይ ህዝብ የህወሃት ደጋፊ አይደለም” ይል ነበር። ለነገሩ የህወሃት ታጋዮች የሞቱት እና የተሰዉት እንደአብርሃ ደስታ ያሉ ሰዎች በግፍ ታፍነው እየተደበደቡ ለፍርድ እንዲቀርቡ ከነበር ያሳዝናል። ህወሃትን እንደግፋለን የሚሉ የትግራይ ተወላጆች ጭምር “የመስዋዕትነት ውጤቱ ይህ ነው?” ብለው እራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው።

የአረና ፓርቲም አንድ አባሉ ታፍኖ እና ታስሮ ሲወሰድ በዝምታ መመልከት የለበትም። የመግለጫ ጋጋታ የታሰሩትን ባያስፈታም፤ አቋምን ማሳወቂያ መንገድ ነውና መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ነው። የይስሙላ ቢሆንም ለሰባዊ መብት ጠባቂ ድርጅትም ቢሆን ማሳወቅ ያስፈልጋል። ከምንም በላይ ግን አንድነት ፓርቲ እንዳደረገው በህገወጥ መንገድ ዜጎችን የሚያስሩትን ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ ያስፈልጋል። ቢሰራም ባይሰራም የህጉን መንገድ ደጋግመን ልንሄድበት ይገባል። ለዛሬው እዚህ ላይ አበቃን።


ሰቆቃን ለማስቆም በጋራ እንነሳ!!! (የግንቦት 7)

ከወያኔ እስር ቤቶች የሚደርሱን መረጃዎች ህሊናን የሚረብሹ ናቸው። የትግራዩ ገዢ ጉጅሌ አባላት በእስር ላይ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጽሙት ሰቆቃ (ቶርቸር) በአስከፊ ሁኔታ ጨምሯል። በጭካኔው «ተወዳዳሪ የለውም» ሲባል በነበረው የደርግ ዘመን እንኳን የማይታወቁ የሰቆቃ ዓይነቶች ዛሬ በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸሙ ነው።

ለማስረጃ ያህል:-
★ ወንዶች የዘር ፍሬዎቻቸውን በመዶሻ ይቀጠቀጣሉ፣
★ ሴቶች ጡቶቻቸውን ይረገጣሉ፤ ክብረ-ነክ ተግባራትም ይፈጸምባቸዋል፣
★ በኤሌክትሪክ በሚሰራ ማሞቂያ የእስረኞችን ጭንቅላት በማጋል እንዲሰቃዩ ይደረጋል፣
★ ከወንበር ጋር አቆራኝቶ ለሳምንት ያህል ማሰር በጣም እየተዘወተረ ያለ የሰቆቃ ዓይነት ሆኗል፣
★ በጠባብ ክፍል ውስጥ ለብቻ ዘግቶ ለወራት ማቆየት የተለመደ ነገር ነው፣
★ ከቆዳ በተሰራ ጅራፍ መግረፍ ድሮም ያለ ቢሆንም አሁን ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ በደርግ ጊዜ የነበሩ ገራፊዎች ከያሉበት እየተፈለጉ እንደገና ለገረፋ ተቀጥረዋል፣
★ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ካራቴና ጁዶ መለማመድ፤ በስለት መቆራረጥ ወጣት የወያኔ «ተተኪዎች» የሚወዱት መዝናኛ ሆኗል፣

እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ አሰቃቂ የሰቆቃ ዓይነቶች የወያኔ እስር ቤቶች መለያ ባህሪያት ናቸው።

የትግራዩ ገዥ ጉጅሌ ሰላዮች ሰቆቃን የሚፈጽሙ ስለመሆኑ በገሃድ አምነው አያውቁም። ሆኖም ግን ሰቆቃን የሚፈጽሙት ተከልለውና ተደብቀው አይደለም። ስንቱ ነው ከተማ ውስጥ በሰው መሃል የተደበደበው? ስንቱ ነው በአደባባይ የተረገጠውና የተዋረደው? በጠራራ ፀሃይ፤ ከተማ ውስጥ፤ ህዝብ መሃል ይህንን የመሰለ ሰቆቃ የፈጸመን እስር ቤት ውስጥ ከዚህ አንድ ሺህ ጊዜ የከፋ ነገር ከመፈጸም ምን ያግደዋል?

በማናቸውም ምክንያት ሰቆቃ መፈጸም እጅግ የተወገዘ እና ምህረት የማያሰጥ ዓለም ዓቀፍ ወንጀል ነው። የደህንነት ስጋትም ሆነ አደጋ ለሰቆቃ በምክንያትነት ሊቀርብ አይችልም። ሰቆቃን ተቀባይነት ያለው የምርመራ ዘዴ የሚያደርግ የወንጀል ዓይነት የለም። «ወንጀል መከላከል» ለሰቆቃ ተቀባይነት የሌለው ምክንያታቸው ቢሆንም እንኳን ወያኔዎች እሱንም በምክንያትነት ማቅረብ አይችሉም። የወያኔ ሰላዮችና ፓሊሶች ሰቆቃን የሚፈጽሙት የሚመረምሩት ብርቱ ወንጀል ስላለ አይደለም። ወያኔዎች በወያኔ ዳኞች ጉዳያቸው ያለቀላቸውና ወያኔያዊ ፍርደገምድል ፍርድ የተሰጣቸው ፍርደኞችንም ጭምር ያሰቃያሉ። ለወያኔ የሰቆቃ እውነተኛ ምክንያቶች ሁለት ናቸው።

የመጀመሪያዉ እና ዋነኛው ምክንያታቸው የዘር ጥላቻ ነው። የወያኔ አረመኔዎች የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑ ግለሰቦችን በደበደቡና ባዋረዱ መጠን አማራንና ኦሮሞን ያዋረዱ ይመስላቸዋል። ለዘመናት በልባቸው ውስጥ የተጠራቀመውን ጥላቻ በግለሰቦች ላይ ይወጡታል። እነዚህ በክፋት የተሞሉ ሰዎች ሲገርፉና ሲደበድቡ የሚሳደቡት፣ የሚራገሙት የተደብዳቢውን ዘር እንጂ ተደብዳቢውን በግል አለመሆኑ የደረሰበት ሁሉ ያውቀዋል።

ሁለተኛው ምክንያት የጉጅሌው አባላትና ተባባሪዎች ሰውን በማሰቃየት የሚደሰቱ እኩያን መሆናቸው ነው። ይህ የስነልቡና ህመም ምንጩ በራስ የመተማመን እጦት ነው። መንፈሰ ደካማ ሰው ውስጡ እየነገረው ያለውን ደካማነት በእጆቹ በሚሰነዝረው ዱላ ማስተባበል ይፈልጋል። የትግራይ ገዢ ጉጅሌ እና ተባባሪዎቹ የሚያደርጉት ይህንኑ ነው። እጃቸው ውስጥ የገቡትን ወገኖቻችንን በማሰቃየት ትንሽነታቸውን ማሸነፍ ይፈልጋሉ።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ ሰቆቃዎችን በማድረስ ላይ ለምትገኙ የትግራይ ገዥ ጉጅሌ አባላት፣ ለቅጥረኞቻቸውና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። ሰቆቃ ፈጽሞ ማምለጥ እንደማይቻል በደርግ ጊዜ የሰቆቃ ቀንደኛ መሪ ከነበረውና በአሜሪካ አገር ተከሶ ዛሬ በናንተው እስር ቤት ከሚገኘው ቀልቤሳ ነጌዎ ትምህርት ውሰዱ። የእናንተም መጨረሻ ከእነሱ የባሰ እንጂ የተሻለ እንደማይሆን ተገንዘቡ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!


Monday, July 14, 2014

“ግንቦት ሰባትን ለማዳከም የተወሰዱ እርምጃዎች ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል” ሲል የፀረ ሺብር ግብረሃይል አስታወቀ፡፡

ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ እና እሁድ በጠቅላይ ሚኒስትር አዳራሽ የጸረ ሽብር ግብረሃይሉና የኢህአዴግ ባለስልጣናት በጋራ የመከሩ ሲሆን፣ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት 3 ሚልየን 400 ሺ ዶላር ወጭ ማድረጉን ገልጿል፡፡ “ኢሳያስ ቢያስፈልገን እርሱን የመያዝ አቅም ላይነን” በማለትራሱን ያሞካሸውግብረሃይሉ ፣ “ኢህአዴግንግስት ንቧን በመያዙየቀጣዩምርጫድልበርላይይገኛል” ሲልበሪፖርቱ አትቷል።
ከሁሉምክልሎችየደህንነትሃይሎችአመራሮችበተካፈሉበትውይይትበቀጣይከግንቦትሰባትሊፈፀምይችላልየተባሉ ስጋቶችም ተነስተዋል። የመከላከያሃይሉልዩትዕዛዝተሰጥቶትየተዘናጋበትንክልልእንዲሸፍንናከፍተኛጥንቃቄእንዲወስድመመሪያእንዲሰጠው ተወስናል፡፡

የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዜና  የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ  ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ  መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ ያሳለፈውን ውሳኔ  ''ጠቃሚ እርምጃ'' በማለት አሞካሽቶታል።
ውሳኔው በተለይ በቅርቡ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገት በኃላ የእንግሊዝ መንግስት  ''የባህር ማዶ የልማት ትብብር ድርጅት'' (UK Department for International Development (DFID) ) ለኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግ የነበረ ከመሆኑ አንፃር የዛሬው ውሳኔ ከፍተኛ መልዕክት ማስተላለፉ አይቀርም።በሌላ በኩል የዛሬው የፍርድቤቱ ውሳኔ ይሄው የልማት ድርጅት (DFID) በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ ይዞታ ጉዳይ አለመመርመሩን ጠቁሞ በእዚሁ አዲሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግበት ማዘዙን ያብራራል።
የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእርምጃውን ፋይዳ ሲያስረዳ  የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ የተናገሩትን በመጥቀስ ነው።እንዲህ ይነበባል -

የሕወኀትን ዕቅዶች እንዴት ማክሸፍ ይቻላል?

ዮፍታሔ፦  ለሕወኀት ቀኑ በፍጥነት እየጨለመ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም እስካሁንም ምንም ዓይነት የማስተካከያ ርምጃም ሆነ የመለሳለስ አቋም ከማሳየት ይልቅ በተለመደው እብሪቱ የመቀጠሉ ምክንያት ሊሠራ የሚችል ዕቅድ አለኝ ብሎ ከማመን ነው። ከሰሞኑ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን አግቶ እስከመውሰድ ድረስ የደፈረበት ድርጊት አገዛዙ የደረሰበትን የፍርኃት ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ ቢሆንም ‘መውጫ ቀዳዳ አለኝ’ ብሎ የሚያስበው አስተሳሰብ ሥር የሰደደ መሆኑን የሚያመለክትም ጭምር ነው። ‘እነዚህን ዕቅዶች ብዙ ሠርቸባቸዋለሁ፣ ዝግጅቶቸን ወደማጠናቀቅ ደርሻለሁ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየኖሩ ከመሥጋት እጅግ የተሻለ ዕቅድ ነው’ ብሎ ያምናል። ይህ ለሌሎችም እንዲተባበሩ ለሚጠየቁት/ ለሚገደዱት ቢያንስ ለሁለቱ ክልሎች (የቤንሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ) እንደምክንያት የሚቀርብ ሐሳብ እንደሚሆን መገመት ይቻላል። ይሁን እንጂ ዕቅዱን ለማክሸፍ የሚቻልባቸው አያሌ መንገዶች አሉ። የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው። ሌሎች ቢጨምሩባቸውና ቢያዳብሯቸው ጥቅሙ ለሀገርና ለወገን ነው።

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና የሌሎችም ፖለቲከኞች መታሰር የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ እንደቀጠለ ነው

የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ህገወጥ በሆነ መልኩ አሳልፈው ከሰጡዋቸው በሁዋላ ኢትዮጵያውያን አሁንም ቁጣቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ” የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ልብን የሚሰብር ቢሆንም፣ ወሳኙ ነገር ማዘን ሳይሆን ለለውጥ ቆርጦ በመነሳት መታገል ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የየመን መንግስት የወሰደውን እርምጃ እንዲሁም የኢህአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን አስሮ ማሰቃየቱን በመቃወም የሚያደርጉትን ተቃውሞ እንደቀጠሉ ነው። በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ችግር በሚታይባት እስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቴላቪቭ ባደረጉት ተቃውሞ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተፈጸመውን ህገወጥ እርምጃ አውግዘዋል። ኢትዮጵያውያኑ እንግሊዝ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ጣልቃ እንድትገባና የሚለቀቅበትን መንገድ እንድትፈልግም ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በሽብርተኝነት ሰበብ ያሰራቸውን በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን ፖለቲከኞች እንዲፈታ አንድነትና መኢአድ በጋራ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ ጠይቀዋል።አንድነት እና መኢአድ ” ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር በአምባገነንነት መስመሩ ለመቀጠል የቆረጠ መሆኑን የሚያረጋገጥ ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ” የሰሞኑ እስር  እንደተለመደው የተቀነባበረ የስርዓቱ ድራማ ከመሆኑም በተጨማሪየ2007ንሀገራቀፍምርጫበተለመደውማሸማቀቅናማወናበድለመውሰድየተጀመረየመጀመሪያርምጃነውብለንምእናምናለን” ብሎአል።

Sunday, July 13, 2014

የአቶ አዳርጋቸዉ መያዝና እንድምታዉ

የአቶ አንዳርጋቸዉ መያዝ በተሰማ-በ16ኛዉ ቀን ባለፈዉ ማክስኞ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቆጣጠረዉ ቴሊቪዥን ጣቢያ ባሠራጨዉ መግለጫ ግን «የአሸባሪ ድርጅት አመራርና በጥብቅ የሚፈለጉ » ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ እና ሌሎች ሰዎች መታሰራቸዉን አረጋግጧል::ጤና ይስጥልኝ እንደምን አመሻችዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚሕ ቀደም ባሸባሪነት ወንጅሎ በሌሉበት ሞት ያስፈረደባቸዉ፤ የግቦት ሰባት የፍትሕ፤ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ሰነዓ-የመን ተይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ መጋዛቸዉ ብዙ እያነጋገረ ነዉ።አቶ አንዳርጋቸዉ የብሪታንያ ዜጋ ናቸዉ።ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያንና የየመን መንግሥታትን እርምጃ አዉግዟል።የብሪታንያ መንግሥት በበኩሉ የየመን መንግሥት አቶ አዳርጋቸዉን ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን የጄኔቫ-ሥምምነትን የጣሰ ብሎታል።በአቶ አንዳርጋቸዉ ላይ ግርፋት ወይም ሌላ በደል እንዳይፈፀምባቸዉ፤ ከኤምባሲና ከሕግ ባለሙያዎች ጋር የመነጋገር መብታቸዉ እንዲጠበቅ ጠይቋል።በተለይ በሌሉበት የተወሰነባቸዉ የሞት ቅጣት እንዳይፀና አሳስቧል።አምንስቲ ኢንተርናሽናል፤ ሑዩማን ራይትስ ዋች እና ሌሎች የተለያዩ የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም አቶ አንዳርጋቸዉ መጋዛቸዉን ተቃዉመዉ፤ «ሰብአዊ ምብት ይጥሳል» የሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸዉን ያሰቃያል ብለዉ እንደሚሰጉ እያስታወቁ ነዉ።Die Gesellschaft für bedrohte Völker(ለተበደለ ሕዝብ ተሟጋች ማሕበር እንደማለት ነዉ) የተሰኝዉ የጀርመን የመብት ተሟጋች ድርጅት ደግሞ አቶ አንዳርጋቸዉን ለማስፈታት የአዉሮጳ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቋል።አዉሮጳ እና ሰሜን አሜሪካ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ በየከተማዉ ባደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ የአቶ አንዳርጋቸዉን መያዝና መጋዝ አዉግዟል።የኢትዮጵያ መንግሥትን ባለሥልጣናትን ሥለ ጉዳዩ ለማነጋገር፤ ቢቻል በዚሕ ዉይይት እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ለተከታታይ ቀናት ሞክረን ነበር-ያገኘናቸዉ እስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።ሌሎቹ ን ልናገኛቸዉ አልቻልንም።የአቶ አንዳርጋቸዉ መያዝ በተሰማ-በ16ኛዉ ቀን ባለፈዉ ማክስኞ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቆጣጠረዉ ቴሊቪዥን ጣቢያ ባሠራጨዉ መግለጫ ግን «የአሸባሪ ድርጅት አመራርና በጥብቅ የሚፈለጉ » ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ እና ሌሎች ሰዎች መታሰራቸዉን አረጋግጧል።በአምደ መረብ የሚፃፈዉ ዉግዘት፤ ክርክርም፤ እንደቀጠለ ነዉ።የእርምጃዉ ሕጋዊ፤ ሠብኣዊና ፖለቲካዊ እድምታ የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።ነጋሽ መሐመድአርያም ተክሌ

የአዲስ አበባ የመሬት ቅርጫ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፦ ዮሐንስ ታደሰ አካ የሚባል ወጣት ስደተኛ የተስፋው ነጸብራቅ የሚል መጽሐፍ እአአ በ2013 በጀርመን አገር አሳትሞአል፤ ሳይፈራ ሀሳቡን የሚገልጽ በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም በታወቀው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያና በቃሊቲም ታስሮ ነበር፤ እሱ እንደሚለው ‹‹በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣን ውስጥ … የመሬት መሀንዲስ›› ተብሎ በ2000 ዓ.ም. ተቀጠረ፤ ከተቀጠረ በኋላ በቦዘኔነት ደመወዝ እየበላ ቆየ፤ ቀይቶ እንደተገነዘበው ‹‹… ለካስ እንኳንስ የእያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ ድርሻ ተለይቶ ሊታወቅ የመሥሪያ ቤቱም ሥራ አይታወቅም፤ መሥሪያ ቤቱም ሥራውን አያውቅም፤ የመሥሪያ ቤቱም ሃላፊዎች መሥሪያ ቤቱን አያውቁትም፤ ጉድ በል አዲስ አበባ! የምናወራው ስለዝነኛው አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነው።›› (ገ. 19)

Saturday, July 12, 2014

‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው? ጽዮን ግርማ

ኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው፡፡ ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።ኢህአዲግ የሥልጣን ወንበሩን ከጨበጠ በኋላ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ በማስተላለፍ በፓርላማ መቀመጫ እንዲያገኙ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተመሰረተ ለማስመሰል ጥረት ቢያደርግም በተለያየ ምክንያት አባሮ መልሶ ለመበታተን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፡

Friday, July 11, 2014

ወያኔ አንዳርጋቸው ያፈነበት እለት የሚረግምበት ቀን ሩቅ አይደለም!

የህወሃት ጉጅሌ እንደማንኛውም አምባገነን ከፊት ከነበሩ አምባገነኖች ቅንጣት ትምህርት አልተማረም። ወያኔዎች በእብሪት የያዙት ስልጣንና ከህዝብ የዘረፉትን ንብረት የሚያጡት እየመሰላቸው በባነኑ ቁጥር የነጻነት አርበኞችን በማፈን በመግደልና በማሰቃየት ፍርሃታቸው የተወገደ ይመስላቸዋል።

ወያኔ የእኛ መሪና የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት አርበኛ በሆነው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያካሄደው አፈና ከአፈናውም በሆላ በሚያደርሱበት አካላዊ ስቃይ ፍርሃታቸው የሚወገድ ወይም ስርአታቸው ከሞት የሚተርፍ መስሏቸው ከሆነ በእጅጉ ተሳስተዋል። አንዳርጋቸው ዛሬ በእጃቸው ሆኖ በነጻነት ይኖር ከነበረበት በበለጠ የሚለበልባቸው የውስጥ እግር እሳት ይሆናል።

አንዳርጋቸው ሰበአዊ ምቾቱንና ለራሱና ለቤተሰቡ መኖርን አቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻነት በህይወቱ ሊጋፈጥ ከቆረጠ ቆይቷል። እኛ የትግል ጓዶቹና ለህዝብ ነጻነት የቆሙ ሃይሎች ሁሉ አንዳርጋቸውን እናውቀዋለን። ወያኔ በአካሉ ላይ የለመደውን ስቃይ ጀምሮበታል፣ ከዚህ የበለጠም ጉዳት እንደሚያደርስበትም እናውቃለን። የአንዳርጋቸውን ታላቅ የነጻነት ሰውነትና ክብረ ህሊናውን፣ በአርበኝነቱ የሚሰማውን የኩራት ስሜቱን ለግፈኞች ያለውን ንቀትና መጸየፍ ሊለውጡ እንደማይችሉ አስረግጠን እናውቃለን።

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብአዊ አያያዝ ያሳሰበው ሰማያዊ ፓርቲ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!!!

ዘረኛውና ፋሽስታዊ ወያኔ፣ የኢትዮጵያዊያንን የትግል መንፈስ ለመስበር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነትና ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል ወኔ ለመስለብ ያቀደበትን የመጀመሪያውን ፕሮፖጋንዳ ለቀቀ። የህግ ልጓም የማያውቀው ፋሽስት በግፍ የያዛቸውን ሰዎችን እይስሙላው ፍርድ ቤት እንኳን ከመቅረባቸው በፊት “ወንጀለኛ” እያለ እንዲህ ዓይነቱ ፕሮፖጋንዳ እንደሚነዛባቸው ተደጋግሞ የታየ በመሆኑ ይህ ፕሮፖጋንዳ የሚጠበቅ ነበር። ሆኖም ግን ፕሮፖጋንዳው ያዘጋጁ ሰዎች ተስፋ ያደረጉትን ውጤት ያመጣ አልሆነም። ወደፊት ደግሞ ሌሎች ሙከራዎች ይደረጉ ይሆናል፤ ውጤታቸው ግን ከዚህኛው የተለየ እንደማይሆን ይገመታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢቲቪ የእውነት ጥፍጣፊ እንኳን እንደማይገኝ ያውቃል።

አቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ ኢትዮጵያውያን  ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል

ኢሳት ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን
ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው።
እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ህዝቡ
ራሱን እያደራጀ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው እያሳሰቡ ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ መንግስት ህዝቡን ለማረጋጋት በሚል አቶ አንዳርጋቸውን በቴሌቪዥን ማሳየቱን ገልጸው፤ ህዝቡ በዚህ ሳይዘናጋ ፣
ባርነትን ከራሱ ለማውረድ ከፈለገ የራሱን እርምጃ መውሰድ መጀመር አለበት ብለዋል።
ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየትና እንዴት እንደሚታገል ፍንጭ ነው ያጣው ካሉ በሁዋላ፣ ስራውን መጀመር አማራጭ የሌለው ነገር ሲሉ አክለዋል።
“አንድ ቀን ቀን ይወጣል ብለን” ስንጠብቅ ከርመናል ያሉት አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ከእንግዲህ የምንጠብቀው ምንም ነገር የለም፣ ሁሉም ደምቷል ብለዋል።
“እኛም ሴቶች ብንሆን ለትግሉ ብዙ የምናግዘው ነገር ይኖራል” ያለችው አንዲት የራያ ቆቦ ነዋሪ፣ ለነጻነት የሚደረገው ትግል ወደፊት መቀጠል እንዳለበት ገልጻለች።
በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫዎችን ማውጣት የቀጠሉ ሲሆን፣ የተቃውሞ ሰልፎችም በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረጉ ነው።
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ህብረት ግንባር ወይም በእንግሊዝኛው አርዱፍ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቁጣውን ገልጿል።
የመን ህገወጥ በሆነ መንገድ አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷን በጽኑ ያወገዘው አርዱፍ፣ የመን በፈጸመቸው ህገወጥ ተግባር ተጠያቂ መሆን አለባት ብሎአል።
አቶ አንዳርጋቸውን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮችን በማሰር የነጻነት ትግሉ እንደማይቋረጥ የገለፀው አርዱፍ ፣ እንዲያውም ትግሉን የበለጠ እንድናጠናክር ያደርገናል ሲል አክሏል።
የአለማቀፍ ማህበረሰቡ፣ የእንግሊዝ መንግስትና  የኢትዮጵያ ሃይሎች በሙሉ ለአቶ አንዳርጋቸው መለቀቅ አበክረው እንዲሰሩ አርዱፍ በመግለጫው ጠይቋል።
በብሪዝበን አውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ጋዜጠኛ ኤልሳ ይመኑ ከስፍራው ዘግባለች።
በፊንላንድየሚገኙኢትዮዽያውያንእናትውልደኢትዮዽያውያን ደግሞ ሄልሲንኪ  በሚገኘው የ እንግሊዝ
ኤምባሲ በመገኘት ያዘጋጁትን ደብዳቤ አስረክበዋል። ኢትዮጵያውያኑ በደብዳቤው የየመን መንግስት የፈፀመውን ታሪካዊና ይቅርታ  የማያሰጥ ተግባር በጽኑ አውግዘው
የየመን መንግሥት አለም አቀፍን ሕግ ጥሶ ለፈፀመው ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ መንገዶች እና  ግዜያት ዋጋ እንደሚያስከፍለው አስታውቀዋል ።
የእንግሊዝ  መንግስትም  አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ ዜጋው  ስለሆኑ ፣ ሰብአዊ   መብታቸው  ስለተገፈፈ እንዲሁም የህወሓት አገዛዝ በቶርቸር እና ሰብአዊ መብት ረገጣ  አለም አቀፍ
ድርጅቶች ባረጋገጡት መሠረት የታወቀ በመሆኑ ባስቸኳይ ተለቀው እንግሊዝ ሀገር ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የእንግሊዝ  መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ባፋጣኝ እንዲሰሩ ጠይቀዋል ።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነን አገዛዝ፣የሰብአዊ መብት ረገጣ ፣ግድያ የሚዲያ አፈና፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አለመከበር የእንግሊዝ መንግሥት ዝም
ብሎ ማየቱን ከቀጠለ ወይንም ጠንካራ አቋም የማይወስድ ከሆነ ለጊዜያዊ ጥቅም ብሎ ዘለቄታዊ
የሆነውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና የእንግሊዝ ብሔራዊ ጥቅም ስለሚጎዳ እንግሊዝ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን የውጭ ጉዳይ ፓሊስ እንደገና ባትክሮት እንድትመረምረው ጠይቀዋል ።

አብርሀ ደስታ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት ቀረበ

ካሳለፍነው ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው በማዕከላዊ በእስር ላይ የሚገኙት ወጣቱ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፣ ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ም/ሀላፊ ወጣቱ መምህርና ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የአረና ፓርቲ አመራር በትላንትው ዕለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ከምሽቱ 12፡16 ላይ የአረና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃ ደስታ ብቻውን በ3 ፌደራል ፖሊሶች ታጅቦ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ማንም ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገባ በፀጥታ ሀይሎችና ሲቪል በለበሱ የደህንነት ሀይሎች በመከልከሉ ምክንያት ስለቀረበበት ክስ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ሊሳካልን አልቻለም፡፡ በወጣቱ ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ ፊት ላይ ይታይ የነበረው ጉስቁልና ከፍተኛ የሀይል እርምጃዎች ሳይወሰድበት እንዳልቀረ አመላካች ነበር፡፡ ይህንን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ የአንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት አልቀረቡም፡፡


Thursday, July 10, 2014

አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊ ነው !!!

ወንድሙን ሲገሉት ፣ ወንድሙን ካልከፋው፣

ሱሬውን አምጡለት፣ ደሙ እንዲገለማው።



በጉን በጉ በላው በድዱ ጎትቶ ፣

ለማን አቤት ይሏል፣ ሰሚስ የት ተገኝቶ።



የሕዝብ ግጥም

አንዳርጋቸው በሁለት ወንጀለኛ መንግሥታት ትብብር ታፈነ፣ ተወሰደ ፣ ታሰረ ፣ ተሰቃየ።
ይህ አሳዛኝና የሚያበሳጭ ዜና ነው። በዚህ ቅጥፈት በሞላበት ዓለም ውስጥ ሕዝባቸውን በየቀኑ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚያፍኑ መንግሥታት ቢተባበሩ ምንም የሚገርም ጉዳይ አይሆንም። አንዱ የሌላውን  እከክ ማከኩ የተለመደ ነው። ይህ የመጀመሪያ ሳይሆን የተደጋገመ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝና የአካባቢው ወንጀለኛ መንግሥታት የተለመደ ወንጀል ነው። ወያኔ ገና ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ እንዲሁም ከዚያ በፊት ጀምሮ ያስራል ፣ ይገድላል ፣ ያሰቃያል።

በዚህ ሰሞን በተፈጸመው ግፍ ውስጥ አንዳንድ የሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የማነበው ሆነ የምሰማው አንድ በጣም መስተካከል ያለበት አስገራሚ ሃሳብ አለ። “አንዳርጋቸው እንግሊዛዊ ስለሆነ የመኖች አስረው ለወያኔ ማስተላለፍ አይችሉም“ የሚል ንግግርም ይሁን ጽሁፍ አንዳንዴ ብቅ ይላል።  እግሊዛዊነቱስ እሺ ኢትዮጵያዊስ ቢሆን? ይችላሉ ማለት ነው? ለማስፈታት በምናደርገው ጥረት ማናቸውንም መንገድ መጠቀም ይገባ ይሆናል። ግን ደግሞ ዓላማችንን አዘናጊ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ጎጂ ሊሆን አይገባም።

እንደ አመራር ከዚህ ስርአት እስር አይደለም ግድያዉንም የምንጠብቀዉ ነዉ፡፡

ተክሌ በቀለ

ስንቱን ወጣት በቅርቡ ገድሎም የለ፡፡ጠላቶቼ ለሚለዉ ብቻ ሳይሆን ከራሱ የሚቃወሙትንና የሚያምኑቱንም ገዳይ ተፈጥሮ እንዳለዉ እድሜ ለእነ አስገደ ገ/ስላሴ አዉቀናል፡፡በቅርቡም ወጣቱ ዮናስ በላይ ያቅሙን አሳይቶናል( በዚህ አጋጣሚ በረታ ዮኒ)፡፡ለወንዙ ልጆችና ለጓዶቹም እንደማይሆን እናዉቃልን፡፡ዓረና እንደፓርቲ ከተቋቋመ ወዲህ ስንቱ ገበሬ በእስር እየተሰቃየ እንዳለ ፓረቲዉ እንደሌሎቹ እየጮኀ ሲሆን ባለጠመኔዉና እስክረቢቶዉ አብረሃ ደስታ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ተጠቂ መሆኑ ነዉ፡፡ሃብታሙ አያሌዉና ዳንኤል ሽበሺ ፍጹም ሰላማዊ ታጋዮች ናቸዉ፤ሌሎችም፡፡እስሩ ቀጥሏል፤ሊቀጥል ይገባል፡፡ይህ ስርአት እስካለ ድረስ ማለቴ ነዉ፡፡ለዉጥ ፈላጊ ከሆነ ለመንም አይቀርለትም፡፡የአንድነትና መኢኣድ(ለግዜዉ ለያይቸ ልጥራቸዉ)፤የመድረክ፤የሰማያዊ፤የትብብርና ሌሎች ፓርቲዎች አመራርና አባላት (እባካችሁ እንወሃድ ወይእንተባበር!) ጠንክረን በመስራት የእስርን ፍርሃት እንደነ አንዷለም፤በቀለ፤ርእዮት፤እስክንድር….እንስበር!! ለመታሰር እንስራ
ልጆቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ይፈሩ፤በዉጭም ያላችሁም ኑና በሰላማዊ ትግል እየታሰርን ይህን ስርኣት እንለዉጥ፤እስክንድር እንዳለዉ ይሁን፤እስርበቱን እንሙላዉ፡፡ሃብታሙ አምነሃለሁ፤ህዉሓት/ኢህኣዴግ ይወድቃል! ለዉድቀት ስለሚሰራ!!!

Wednesday, July 9, 2014

ወያኔዎች- አብደዋል – አቶ ግርማ ሰይፉ በታሰሩ ወጣት ፖለቲከኞች ዙሪያ

የፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል።

«እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ አይቻላቸውም፡፡ እልፍ አህላፍ የነፃነት ሰዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩ የሚታሰሩ ንፁሃን ታሳሪዎች ሳይሆን አሳሪዎ በከፍተኛ የህሊና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን መረዳት አሰቸጋሪ አይደለም፡፡» ሲሉ ነበር አቶ ግርማ በፌስ ቡክ አስተያየታቸውን የሰጡት።«የዚህ ልጅ ነገር ሳያበሳጫቸው አይቀርም፡፡ ሰለማዊ ሰልፍ ላይ በባትሪ አንደሚሰራ ሳያርፍ ያጋልጣቸዋል፡፡ በየሳምንቱ ገበናቸውን በመፅኄት በጋዜጣ ያወጣል፡፡ በዓመት መጨረሻ ደግሞ ትምህርት ተምሮ በክብር በማዕረግ ይመረቃል፡፡ ኢዚህም እዚያም ያገኙታል ሁሉም ጋ ሲያወግዛቸው፤ በቃችሁ ሲላቸው ይሰማሉ፡፡ በቃቸው የሚላቸው ደግሞ እንደበቃቸው ስራቸው ሆኖ ያያቸው እርሱ መሆኑ ያበሳጫቸዋል፡፡ ሌላው በግምት አትችሉም ሲላቸው ሀብታሙ ግን አውቃችሀኋለሁ አትችሉም ይላቸዋል፡፡ በእውነት ነርቫቸውን ነው የነካው፡፡ የሚያጓጓው ግን ምን ብለው 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አሸባሪ እንደሚሉት ነው፡፡ ዛሬ ቄሱን አሸባሪ አሉ የሚለው ዜና አብርሃ ደሰታ ከመቀሌ ሹክ ብሎናል፡፡ ሀብታሙን ቢሉት አይገርምም፡፡ እንሰማለን፡፡ ተረኞች መዘጋጀት ነው፡፡» ብለው የጻፉት አቶ ግርማ የኢሕአዴግን የፖለቲክ ክስረትና የአቶ ሃብታሙን ታታሪነት የገለጹ ሲሆን፣ እርሳቸዉን ጨምሮ ሌሎች በሰላም የሚታገሉ ሁሉ፣ የሰላማዊ ትግል ለሚያስከፍለው እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀርበዋል።የሰላማዊ ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ለሚመስላቸውና በቀላሉ ተስፋ ለሚቆርጡ ወገኖች አቶ ግርማ ሰይፉን ጠንካራ ምክር ለግሰዋል። « ሰላማዊ ታጋዮች መንገላታት እና እስር አሰበውበት የገቡበት ነው፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ያማል ግን ይህን እመም ለመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡ የሀብታሙ አያሌው ባለቤት ባለፈው ሳምንት አባቷን በድንገት በሞት ተነጥቃለች አሁን ደግሞ ባለቤቷ በግፍ ወህኒ ወርዶዋል ኮልታፋ ህፃን ልጅ ይዛ መከራዋን እንደምትገፋ ሀብታሙ ያውቀዋል፡፡ ሊያሞላቅቃቸው ቢፈልግ ግን ከኢህአዴ ደጅ ፍርፋሪ መልቀም የሚከለክለው አልነበረም፡፡ » ሲሉ ነበር በሰላምዊ ትግል ከአምባገነኖች ጋር ትንቅንቅ የየዙ ወገኖችን ጀግንነት ያስረዱት።አቶ ግርማ ሲያጠቃልሉ « ውድ የትግል ጓዶች ከዞን ዘጠኝ ወደ ሌላ ዞን መሸጋገራችሁ ቢያሳዝነንም ፅናታችሁ ያበረታናል፡፡ ፅኑ፡፡ ለካ እነርሱ ይህን የማንበብ መብት የላቸው፡፡ በዞን ዘጠኝ የምትገኙ ሁሉ በርቱ ፅናቱን ይስጣችሁ ማለት የግድ ይላል» በማለት ትግሉን ከማፋፋም ዉጭ ሌላ አማራጭ እንደሌልም ለማሳየት ሞክረዋል።

በየመን መንግስትና በወያኔ ስርአት ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ የተወሰደውን ያፈና በመቃወም ከት.ህ.ዴ.ን. የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ


የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል እየፈፀመ መቆየቱና አሁንም እየቀጠለበት መሆኑ ይታወቃል የወያኔ አምባገነን ስርአት ህዝቡን እየጨፈጨፈና ለነፃነት የቆሙትን ቁርጠኛ ታጋዮች በመግደል፣ የህዝቡን የትግል ማእበል መግታት እንደማይቻል ካለፉት አባቶቹ መማር በተገባው ነበር።  ትናንት በወያኔዎች ቀጥተኛ መሪነት ይካሄድ በነበረውና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ለጭቁኑ ህዝብ ሲሉ በጠላት ስር የወደቁና ባውደ ውጊያ ፊት ለፊት ተዋግተው መስዋእትነት በመክፈላቸው፣ ህዝባዊ ትግሉ በበለጠ እልህና ቆራጥነት ሲቀጥል እንጂ፣ በከፈለው መስዋእትነት ተደናግጦና ተስፋ ቆርጦ ትግሉ ወደ ኋላ ሲመለስና ትርጉም የለሽ ሲሆን አልታየም።   ምክንያቱም ትግል ሲባል ሁሉም አይነት መስዋእትነት ከፍለህ ከአፈናና  ከጭቆና ነፃ በማውጣት ለህዝቡ ፍትህ፤ እኩልነትና ዴሞክራሲ ማስፈን ስለሆነ፣ ይህ በታጋይ እንዳርጋቸው ፅጌ ያጋጠመው ድርጊትም ለዘአለም ህያው ነው።    ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴን/ ይህ በየመን መንግስት በታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የተፈፀመው ታሪካዊ ስህተት በሁሉም የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ላይ የተፈፀመ እንደሆነ በማመን እኩይ ተግባሩን በፅኑ እናወግዘዋለን።    ይህ የታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ለህዝብ ብሎ የከፈለው መስዋእትነት ደግሞ። ያለፉት ጀግኖች አላማቸውን አምነው ለህዝብና ለሃገር ብለው እየከፈሉት የመጡትን ከባድ የመስዋእትነት ዋጋ  በመከተል ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የአንዳርጋቸው ፅጌና የሚሊዮኖች ታጋዮች ዋጋ የከፈሉለት ትግል ወደ ድል ለማብቃት ትግሉ እንዲጠናከርና የአምባገነኑ ስርአት እድሜ እንዲያጥር በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴ.ን / ጥሪውን ያቀርባል።                   ዘለአለማዊ ታሪክ እንጂ ዘለአለማዊ ህይወት የለም!                            


 የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ   

                                                                                                            ሓምሌ 2/2006 ዓ/ም  ድል ለጭቁኖ!!     




  T.P.D.M ዴ.ም.ህ.ት

ሶስቱ አምባገነኖች (እየሩሳሌም አርአያ)

አገሪቱ በሶስት ሰዎች ቁጥጥር ስር እንደወደቀችና አሁን እየተካሄደ ያለው የጅምላ እስርና ድብድባ በነዚህ የሕወሐት ባለስልጣናት ትእዛዝ እየተፈፀመ እንደሚገኝ ታማኝ የቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል። የፌዴራል ደህንነት መሪ ፀጋዬ በርሔ (ሃለቃ)፣ የደህንነት ሃላፊ ጌታቸው አሰፋና ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ሲሆኑ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ታፍነው እንዲወሰዱና በዛሬው እለት አብርሃ ደስታን ጨምሮ ሃብታሙ አያሌውና የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም ሌሎች የተቃዋሚ አመራር አባላቶች የሃይል ጥቃት እየተፈፀመባቸው እስር ቤት እንዲገቡ ማድረጋቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል። አብርሃ ደስታ በፌዴራል ፖሊሶች ተይዞ ሲወሰድ ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመበት ሲሆን በመቀሌ በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሌለና ወዴት እንደተወሰደ እንደማይታወቅ ምንጮች ከስፍራው አረጋግጠዋል። ይህ ሁሉ ጥቃትና የመብት ረገጣ እየተከናወነ ያለው በሶስቱ አምባግነኖች መሆኑን ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም እስር፣ ድብደባና ድራማ በመስራት የስልጣን እድሜን ማራዘም አይቻልም ብለዋል። የኢትዮጵያ ነገር ያበቃው በነሃለቃ ፀጋይ በርሄ (ደናቁርት) መመራት የጀመረች እለት ነው- ሲሉ አክለዋል።


ከልባቸው ደፋር የሆኑ የሀገሬን ልጆች ማየት በመጀመሬ ደስ አለኝ – ኤሊያስ ገብሩ

ፍኖተ ነፃነትየሰሞኑ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ሀዘን፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ እልህ፣ ብሎም የደስታ ስሜትን የቀላቀለ ነበር፡፡ የእሰሩ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸውን ሰምተናል፣ አውቀናል፡፡ የዚህ መሰል አካሄድ ግን መዘዘን የሚስከትል ይመስለኛል፡፡አሁን አሁን ሰዎች እንደጥጃ ከቤታቸው፣ ከየመንገዱ፣ ከሚሰሩባቸው ቦታዎች …እየተወሰዱ መታሰራቸው በሀገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ ክስተት ሆኗል፡፡ ሥልጣን በጨበጡ ኃይሎች ለነገሮች የሚሰጡት ምላሾች የእስር እርምጃ መሆናቸው ከቀጠለ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራቸው ማመዘኑ አይቀሬ ነው፡፡ አይንም ጆሮም ያለው መንግሥት ይስማ!‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለምን ይፈራሉ?›› በማለት ራሴን ደጋግሜ የምጠይቅበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁንም እጠይቅና የራሴን ምላሽ ለራሴ እሰጣለሁ፡፡ የምቀርባቸውን ሰዎች ጠይቄም ምክንያቱን ለመረዳት ጥረት አደርጋለሁ፡፡ ‹‹ፈሪ ለእናቱ›› የሚል መልስ አስተናግጄም አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ግን ‹‹እመኑ እንጂ አትፍሩ›› ነው የሚለን፡፡ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከልባቸው ደፋር የሆኑ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያዊ ወገኖቼን በድፍረት ብቅ ብቅ እያሉ ማየት በመቻሌ ደስ ብሎኛል፡፡አሁን፣ ሕግን አክብሮ በድፍረት መንቀሳቀስ እንጂ ያለተፈጥሯችን መፍራት በብዙ ችግሮች ለተተበተበችው ሀገራችን አይጠቅማትም፡፡ ‹‹ፍትሕ አጥተናል››፣ ‹‹ተርበናል››፣ ‹‹ነጻነት አጥተናል››፣ ‹‹በኑሮ ተማርረናል››፣ … እያሉ የዳር ተመልካች መሆን መፍትሄ አይደለም፡፡ ‹‹ኢትዮጵኖች የጀግና ሕዝቦች ነን›› እንል የለ? ታዲያ ሕግን ተከትለን በተግባር እናሳየዋ!

ታዋቂው የአረና አመራር አብርሃ ደስታ በወያኔ ታጣቂዎች እየተደበደበ ወዳልታወቀ እስር ቤት መወሰዱ ተሰማ

ታዋቂው የአረና አመራር አብርሃ ደስታ በወያኔ ታጣቂዎች እየተደበደበ ወዳልታወቀ እስር ቤት መወሰዱ ተሰማ

የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አባል አብረሃ ደስታ ዛሬ ከሰሃት በዋላ ከሚኖርበት መቀሌ ከተማ በፌደራል ፖሊሶች ወዳልታወቀ ቦት መወሰዱን ምንጮች ጠቆሙ:: አንግዲ ዛሬ በቻ ወደ አራት የተቃዋሚ ኣመራሮች በወንበዴ መንግስት መያዛቸው ነው ። የወያኔ መንግስት እጂግ ወደ ለየለት ውንብድና የገባ ይመስላል ሁኔታው በጣም አሳሳሚ ከመሆኑ የተነሳ ከጣዩን ነገር እጃችንን አጣምረን ከመጠበቅ ይልቅ ወደ ቀጥተኛ ትግል በተባበረ ክንድ መነሳትና የወንበዴ መንግስትን መጣል አለብን።


Tuesday, July 8, 2014

የአንድነት ፓርቲ ወጣት አመራሮችን የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል

ሰበር ዜና/ ፍኖተ ነፃነት

የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ጠዋት ሜክሲኮ አካባቢ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ከተያዘ በኋላ በአሁኑ ሰዓት አየርጤና አካባቢ የሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየተበረበረ እንደሆነ ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡


ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ እንደሚገኙ መግለፃቸውን ኢሳት ዘገበ።

ሰበር ዜና፦ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከቀናት በፊት በየመን የፀጥታ ሀይሎች የተያዙት የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ እንደሚገኙት አዲስ አበባ ለሚገኙት የእንግሊዝ እርዳታ እና ትብብር ሚኒስትሯ ጀስቲን ግሪንግ መግለፃቸውን ኢሳት ዘገበ።


አቶ ሀብታሙ አያሌው ተያዙ፤ እስካሁን ያሉበት ሁኔታም ሆነ ቦታ አልታወቀም

ኢህአዴግ መአስቸኳይ ሀብታሙን ሊለቅ ይገባል፤ አለበለዚይም ሁላችንንም ይሰር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እስራትንና ሞትን እየፈራ መቁሙ ለ23 አመታት በተናጠል ሲሞት፤ በተናጠል ሲታሰር፤ በተናጠል ሲራዝ፣ ሲራብና ሲጠማ፤ በተናጠል ሲጋዝ አንቀላፍቶ የቆየ ቢሆንም አሁንግን በቃ ብሏል፡፡ መሪዎቹን በማሰር ህዝብን ማጎሳቆል፤ መዝረፍ፤ መጨቆንና ማሰደድ ከአሁን በሁዋላ ይበቃል፡፡
አይደለም እስራትና ለሞት ለባርነትም ቀይተነዋል፡፡ ኢህአዴግ ከታሪክ ይማር! ይህ የሀበሾች ምድር ነዉ፡፡ ጀግንነት ባህላችን ነዉ፤ ባርነት አይዋጠንም፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢህአዴግ ከጣሊያን ሊማር ይገባል፡፡ ከባህሪ አባቱ ከሞሶሎኒን ይጠይቀዉ፤ እኛ የሀበሻ ልጆችነን፤ ዉርደት አይዋጥልንም !!!
የፖለቲካ ታጋዮችን በማሰር ትግሉን ማኮላሸት አይቻልም፡፡ ለዚህም የብርቱካን መታሰር ብዙ መጣቶችን ወደ ትግል እንደፋመጣዉ ሁሉ፤ የአንዱአለም መታሰር እነሀብታሙን አምጥቷል፡፡ የብታሙ መታሰር ደግሞ ሺህ ሀብታሙዎችን ያመጣል፡፡
በኛ በኩል ከታሪክ ተምረናል፤ አንድነታችንን አበርትተናል፤ ከዚህ በሁዋላ ኢህአዴግ በልዩነቶቻችን እየገባ እድሜዉን ሊያራዝም አይችልም፡፡ ኢህአዴግም ከታሪክ ይማር እኛ የሀበሻ ልጆች ነን፤ ባርነት ፈፅሞ የማይዋጥልን፤ ጭቆናን አምርረን የምንጠላ፤ በምድር እንደዉሻ ለዘለአለም ከመኖር እንደ አንበሳ አንድቀን በክብር ዉሎ መሞትን እንመርጣለን!!! ምክንያቱም እኛ የሚኒልክ ልጆች ነን!!! እኛ የጣይቱ ልጆች ነን!!! ኢህአዶግ ከታሪክ ይማር!!! ጨዉ ለራስህ ብትል ጣፍጥ፤ አለበለዚያ ድንጋይ ነዉ ብለዉ ይወረዉሩሀል !!! ሀብታሙና የቀደሙት ወንድሞቻችን እነአንዱአለም አራጌ፤ እን እስክንድር ነጋ በአስቸኩዋይ ይፈቱ!!!
ድል የሰፊዉ ህዝብ ነዉ!!!


Monday, July 7, 2014

ቄስ በሽብር ተከሰሱ፥ ህወሓት ሪከርድ ሰበረች!

ቀሲስ ብርሃነ ቆባዕ (ከእግሪሓሪባ) በሽብር ተጠርጥረው (ከነ አደይ አልጋነሽ ጋ) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30, 2006 ዓም በፖሊስ ታሰሩ። ቀሲስ ብርሃነ እያረሱ እያሉ ነው በአራት ፖሊሶችና ስድስት ምልሻዎች ተከበው ከእርሻ ማሳ ታስረው ፖሊስ ጣብያ የገቡ። የነ ቀሺ ብርሃነ ጉዳይ ሽብር የሚል ነው። ህወሓት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አባት በሽብር በመክሰስ ሪከርድ ሰብራለች። ወይስ ቀስን በሽብር የከሰሰች ሌላ ሀገር አለች?

ጉድ ብዪ ሀገሬ ቄሱም፣ ሐጂውም፣ ኡስታዙም አሸባሪ ነው። እናቶችና የሀይማኖት አባቶች አሸባሪ ተሰኝተው የሚታሰሩበት ዘመን ደርሰናል። ካሁን በኋላ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ብቻ አይደሉም በሽብርተኝነት የሚከሰሱ፤ የክርስትና ሀይማኖት አባቶችም አሸባሪዎች እየተባሉ ነው። በህወሓት ዘመን እስላም ክርስትያኑ አሸባሪ ተሰይሟል። አሁን ታድያ በሙስሊሞችና ክርስትያኖች መካከል መተባበር የሚያስፈልግ አይመስላችሁም? በቃ ሁላችን ሀይማኖት፣ ብሄር፣ ጎሳ ምናምን ሳንለይ አምባገነኑ የህወሓት ስርዓት ለመቀየር መተባበር አለብን። ሁላችን የስርዓቱ ሰለባ ነንና።

በሽብር የተከሰሱ የዓረና አባላት ቁጥር 8 ሲደርስ በተለያዩ ቦታዎች የታሰሩ የዓረና አባላት ቁጥር ደግሞ 115 ሆኗል። ቁጥሩ ለሳምንታት ታስረው የሚለቀቁና ደብዛቸው የጠፉ አይጨምርም።

ወይ ሽብር! በቃ ሁላችን አሸባሪዎች ነን።


በሕወሃት አባሎችና እንዲሁም በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራ በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ላይ ያነጣጠረ አንዳርጋቸዋዊ ዘመቻ

ሙሳ ሙሃባ

July 6, 2014

1.በየአገሩ በተለያዩ ሽፋኖች ተሰግስገው ያለት ወንጀለኞች የወያኔ ሹማምንትና ደጋፊዎችን ለፍርድ ማቅረብ፤

2.የወያኔ ኤምባሲዎች ሥራ መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር፤

3.የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችን ከያሉበት (በሰፈር፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በንግድ የተሰማሩ ..) በማደን ማስነወር፣ ማግለል፣ ማዋረድ፤ ከእነሱ ጋር አንዳችም የንግድም ሆነ የሥራ ትብብር አለማድረግ፤ በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳዎችን ማካሄድ። ይህ ኢትዮጵያም ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል።

4.ለሥራ ወይም ለሽርሽር የሚዘዋወሩ ከፍተኛ የወያኔ ባለሥልጣኖችና የጦር መኮንኖችን እየተከታተሉ ማሸማቀቅ፣ ማስነወር፣ መገታተር፤

5.የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በወያኔ መንግሥት የሚመሩ ቢዝነስች ላይ እቀባ ማድረግ፤ በእነሱ ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ። ይህ በኢትዮጵያም በውጭ አገራትም መደረግ ይኖርበታል።

6.በዌስተር ዩኒየን እና በወያኔ ደጋፊዎች በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አለመላክ፤ በየአካባቢው አማራጭ መላኪያ መንገዶችን መፈለግ።

7.ከወያኔ ጋር የሚሠሩ የውጭ አገር ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያላቸውን ሽርክና እንዲያቋርጡ መወትወት፤ አልሰማ ካሉ በቢዝነሳቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ።

8.የምዕራብ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲመረምሩ ማሳሰብ። በወጉ ሳያስተምሩ ለወያኔ ሹማምንቶች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማስጠንቀቅ፤ ተግባሮቻቸውን ለተማሪዎቻቸው ጭምር መንገር (ለምሳሌ University of Greenwich ከ International Leadership Institute ጋር ያለውን ግኑኝነት እንዲሰርዝ፣ እስከዛሬ የሰጣቸውንም የማስትሬት ዲግሪዎች እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ በብዛት በፋክስ መላክ፤ ተመሳሳይ ደብዳቤ Open University እና ከወያኔ ጋር ተሻርከው ለሚሠሩ ዩኒቨርስቲና ኮሌጆች መላክ)

9.ይህ ዘመቻ ለጊዜው በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ የሕዝቡን የነፃነትና የፍትህ ጥረት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች በሆኑ ቱጃሮች የተያዙ ቢዝነሶችም የዘመቻው ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ።



አሜሪካ በወር 10.000 ዶላር የምትከፍለው ነፍሰ ገዳይ

ምንሊክ ሳልሳዊ
ሕወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ አይሁድ ስርአትን የመዘርጋት ምስጢራዊ እቅድ አለው።

በአሁን ወቅት ስብሃት ነጋ የያዘውን ስልጣን የቀድሞው የኢንስቲትዩቱ ፕረዝዳት የነበረው ዶክተር ክንፈ አብርሃ እንደሞተ ወያኔ ዶክተሩን የሚተካ ሰው በማጣቱ በትም ተቸግሮ ስለነበር ቦታውን እንዲይዝ የተፈለገው የትግራይ ተወላጅ ስለነበር አቶ መለስ ዜናዊ በዘር ቆጠራ ሲያጠያይቁ አንድ በሃይለስላሴ ጊዜ ወደ ካናዳ ለትምህርት ሂደው ደርግ ሲመጣ በዛው በጥገኝነት የቀሩ ህይወታቸውን ሙሉ ወርልድ ባንክ የሰሩ እና የተማሩ በጡረታ የሚኖሩ ዲያስፖራ አዛውንት ኢትዮጵያን በዘረኝነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ብቻ የሚያውቛትን ዶክተር የትግራይ ተወላጅ አስጠርቶ ሊሾማቸው አስቦ አልተሳካለም። ለምን ?

እኚህ ካናዳ በጡረት የሚኖሩ አዛውንት በጊዜው የመለስ ዜናዊን ጥሪ ተቀብለው ወደ አዲስ አበባ መጥተው ነበር ። ገና ከአይሮፕላን ወርደው ወደ ኤርፖርቱ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም በሆቴሎች በመንገዶች ላይ የተመለከቱት በዞሩባቸው መስሪያ ቤትች ያሉ ነገሮችን በመታዘብ አስደንጋጭ ገተመኝ ሆኖባቸው ነበር ። ሁሉንም ሲያዩት ከአንድ ብሄር እና ከአንድ ቤተሰብ የተሳስረ ሃገሪቷ የአንድ ሰው ንብረት በሚመስል መልኩ ብሰንሰለት አደጋ ውስጥመሆኗን ሲናገሩ ተደምጠዋል። የአገሪቱ ተቋማት በአንድ ቋንቛ ተገጣጥመው እንደተሰሩ አላቂ ምርቶች አዲስ አበባ በመሰለ ሜትሮ ፖሊቲይን ከትማ ውስት መመልክታቸው እጅግ አስደንግጧቸው ነበር።

እኚህ ለጊዜው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ካናዳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ በጥሪው መሰረት ከመለስ ዜናዊ ጋር በአካል ተገናኝተው በነበረ ጊዜ መለስ ዜናዊ የዶክተር ክንፈን ቦታ እንዲይዙልኝ ፈልጌ ነበር ያስመጣዎት ምክንያትም ይህ ቦታ እንደርሶ ያለ ልምድ ያለው ሰው እንዲይዘው ስለተፈለገ ስለሆነ እርሶን መሾም በ እጅጉ ያስፈልገናል ሲላቸው... ዶክተሩ ነገሩ ስለገባቸው የተጠሩት በ እውቀታቸው ሳይሆን የትግራይ ተወላጅ ብቻ ስለሆነ እንደሆነ ስለተደረዱ የገመቱትም ሆኖ ስለገጠማቸው መለስ ዜናዊን አንድ ጥያቄ ጠየቁት ... ለመሆኑ አገሩን ሁሉ ከላይ እስከ ታች በአንድ ጎሳ አዋቅራችሁ እስከመች መዝለቅ ትችላላችሁ ? በዚህ ዘመን በተለይ ፕራክቲክል ነው? ባላንስ ኦፍ ፓውር / የሃይል ሚዛኑ / ሽፍት ባይደረግ ምን ይውጣቹሃል ? ወዘተ የሚል ጥያቄ አንስተውበት ነበር፡፤

የመለስ መልስ ግን በወቅቱ አጭር ነበር " ይህ ነገር የትም እንደማያደርሰን እንውቀዋለን ።ነገር ግን በተቻለን መጠን ስልጣናችንን ሉዝ (ከማጣታችን) በፊት የትግራይ አይህድ ፈጥረን ማለፍ አለብን ብለን ወስነናል፡፤ ቁርጥ ያለ መልስ ነግሯቸዋል። በጥሪያቸው መሰረት ወደ አዲስ አበባ የመጡት አዛውንት ሃገሪቷ በአደገኛ የጎሳ ቫይርስ ውስጥ መሆኗን ተገንዝበው ከደሙ ንጹህ ነኝ ብለው መልሰውለት ወደ መጡበት ካናዳ ተመልሰዋል።

Amnesty International : ANDARGACHEW TSIGE Was Forcibly Returned To Ethiopia The Same Day

UA: 171/14 Index: AFR 25/003/2014 Ethiopia Date: 4 July 2014

URGENT ACTION ETHIOPIAN ACTIVIST AT RISK OF TORTURE Andargachew Tsige, an Ethiopian political activist in exile, appears to have been arrested in transit in Yemen on 24 June and forcibly returned to Ethiopia. He is at risk of torture and other ill-treatment. Andargachew Tsige is a British national of Ethiopian origin and Secretary-General of Ginbot 7, an outlawed Ethiopian opposition group. He disappeared on 24 June at Sana’a airport in Yemen, while in transit between the United Arab Emirates and Eritrea. Although no official statements have been released by the Yemeni or Ethiopian authorities about his current whereabouts, human rights activists in Yemen told Amnesty International that he was forcibly returned to Ethiopia the same day he landed after being detained at the Sana’a airport.

He is at high risk of torture and other ill-treatment in Ethiopia, where political detainees are frequently tortured in order to extract information and confessions. His incommunicado detention in an unknown location increases this risk.

Ginbot 7 is one of five organisations proscribed as terrorist organisations by the Ethiopian parliament in 2011. In 2012, Andargachew Tsige was prosecuted in absentia on terrorism charges (alongside journalist and prisoner of conscience Eskinder Nega, and others) and sentenced to life imprisonment. Previously, in 2009, he was convicted in absentia on charges related to an aborted coup attempt and was sentenced to death. He was also tried in absentia in the 2005-2007 trial of political opposition members, journalists, activists and others.

In recent years, many Ethiopians wanted by the authorities on the grounds of their political activities have been kidnapped in neighbouring countries and forcibly returned to Ethiopia. This has often involved the collaboration of security forces in those countries. Another of the defendants in the 2012 trial had been kidnapped and forcibly returned from Sudan. All those returned are at risk of arbitrary detention, torture and unfair trial.

Please write immediately in Amharic, English or your own language:  Calling on the authorities to guarantee Andargachew Tsige is not subjected to torture or other forms of ill- treatment;  Calling on the authorities to immediately provide information on the location where he is being held, and to ensure that he has full and immediate access to legal and consular representation and family members;  Calling on the authorities to ensure that Andargachew Tsige is not required to serve any sentence for a conviction in absentia and must be retried on any charges against him in a trial that meets international standards, before a new court and without the possibility of the death penalty.

PLEASE SEND APPEALS BEFORE 8 AUGUST 2014 TO: Minister of Justice Berhanu Hailu Ministry of Justice, PO Box 1370, Addis Ababa, Ethiopia Fax: +251 11 5517755 Salutation: Dear Minister

Minister of Federal Affairs D. Shiferaw Teklemariam Ministry of Federal Affairs P.O.Box 5718 Addis Ababa, Ethiopia Email: shiferawtmm@yahoo.com Salutation: Dear Minister

And copies to: Prime Minister His Excellency Hailemariam Desalegn Office of the Prime Minister, PO Box 1031, Addis Ababa, Ethiopia Fax: +251 11 552030 (keep trying)

Also send copies to diplomatic representatives accredited to your country. Please insert local diplomatic addresses below: Name Address 1 Address 2 Address 3 Fax Fax number Email Email address Salutation Salutation Please check with your section office if sending appeals after the above date.





URGENT ACTION ETHIOPIAN ACTIVIST AT RISK OF TORTURE

ADDITIONAL INFORMATION Andargachew Tsige is a former member of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) party and was Deputy Mayor of Addis Ababa from 1991 to 1994, when he resigned on account of differences with the government.

Based in the UK, he travelled to Ethiopia shortly before the 2005 elections to support the opposition party Coalition for Unity and Democracy (CUD). On 8 June 2005, in the wake of the controversial election results, he was detained in Ethiopia and held at Ziway army camp. He was released on bail in July of that year. Like many detainees, Andargachew was accused of organizing the demonstrations, seeking to subvert the Constitution and other offences, which he denied, but he was not formally charged with any offence. After he was released he returned to the UK, but was subsequently named, tried and convicted in absentia in a major political trial of the leadership of the CUD, journalists, human rights activists and others, on charges including high treason, in 2005-2007. At the time he was the CUD representative in the UK.

After the CUD trial, fellow defendant Berhanu Nega founded the ‘Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy’ from exile in the US, of which Andargachew Tsige became Secretary General. Berhanu Nega was also tried in absentia in the 2009 and 2012 trials.

Name: Andargachew Tsige Gender m/f: M

UA: 171/14 Index: AFR 25/003/2014 Issue Date: 4 July 2014