Saturday, May 31, 2014

ግንቦት 20- የመከራ የስደትና ዘረኝነት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ

ወያኔ ለንግሥና የበቃበትን ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓመተ ምህረት መታሰቢያ በአል ለ23ኛ ጊዜ ለማክበር ሰሞኑን ደፋ ቀና ሲል ሰንብቷል። በኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ህዝብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃንና በተለያዩ የውጪ አገራት የተመደቡ የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በዚሁ የግንቦት 20 በአል አከባበር ሥራ ተጠምደው ከርመዋል። ለኢትዮጵያ አገራችንንና ለህዝቦቿ ባርነትን ለህወሃትና ለግብረ አበሮቹ ደግሞ አልመውት የማያውቁትን ድሎትና ብልጽግናን ያጎናጸፈው ግንቦት 20 በየአመቱ ሲዘከር ልብ ልንላቸው ከሚገቡ በርካታ ትሩፋቶቹ ጥቂቶቹ ማስታወስ ይችላል፦ኢትዮጵያ አገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአብራኳ በተገኙ ከሃዲዎች መዳፍ ውስጥ ወድቃ ሉአላዊነቷና አንድነቷ የተናጋበት ሁኔታ መፈጠሩ፤በዘመናት ጥረት የተቋቋመው ህብረ ብሄር የአገር መከላኪያ ሠራዊታችን ፈርሶ በምትኩ ለጠባብ የዘውግ ጥቅም የተሰባብሰቡ መንደርተኞች ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት ተቋም መመስረቱ፤በከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት አገራችንን ከውጪ ጠላት ተከላክለው ነጻነት ያወረሱን ጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ እየተብጠለጠለ በታሪካችን እንድናፍር መደረጉ፤ዜጎች በብሄር ማንነታቸው ከመንግሥት ሥራና የግል ይዞታ የሚፈናቀሉበት ዘመን መፈጠሩ፤የመንግሥትና የህዝብ ሃብት የነበሩ የንግድና የአገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ወደ ህወሃት የግል ይዞታነት መዛወራቸው፤የዘር የሃይማኖትና የቋንቋ ልዩነት መስፈርት የሆነበት ሥርዓት ተቋቁሞ ዜጎች እርስ በርስ የሚላተሙበት ፤ ለዘመናት በሰላም ከኖርበት ቀያቸው በነቂስ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ደጋግሞ መከሰቱ፤በልማትና እድገት ሥም ሰፋፊ የእርሻ መሬቶቻችን ለህንድ፤ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸቡ የነገው ትውልድ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ውስጥ እንዲወድቅ መንገዶች መመቻቸታቸው፤በሚሊዮን የሚጠጉ ለጋ ወጣቶች ተስፋቸው ተሟጦ ለአሽከርነትና ለግርድና ወደ አረብ አገር የሚፈልሱበት ችግር እየተባባሰ መምጣቱ፤በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ስደትና እንግልት ሰለባ መሆናችን ወዘተሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ተጥሶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአስተሳሰባቸውና በአመለካከታቸው በእስር ቤት እንዲማቅቁ፣ እንዲገደሉና እንዲሰደዱ ተደርገገዋል ።ወያኔ ሰሞኑን ባወጣው “የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ” የግንቦት 20 ድል በሀገራችን ለዘመናት ተንሰራፍቶ የነበረውን የዓፈናና የጭቆና ስርዓት የተወገደበትና በምትኩ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ፅኑ መሰረት የተጣለበት ፣የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች በተለይ ደግሞ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት የማረጋገጥ ቁልፍ ጥያቄ ምላሽ ያገኘበትበመሆኑ ልዩ ቦታና ክብር ይሰጠዋል። የግንቦት 20 ድል ሀገራችን ተደቅኖባት የነበረውን የመበታተን አደጋ በመታደግ የኋልዮሽ ጉዞዋን በአስተማማኝ ሁኔታ በመቀልበስ ድሮ ወደነበረችው የስልጣኔ ማማዋ ለመመለስ የሚያስችል በህዝቦች ይሁንታና መከባበር ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት የተጣለበት የህዳሴአችን ጮራ የፈነጠቀበት የድል ቀን ነው።” ብሏል።ይህንን መግለጫ እንዳነበብን ወይም እንደሰማን የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሰን እንድንጠይቀው ግድ ይለናል።በአገራችን ተንሰራፍቶ የነበረው አፈናና ጭቆና ደጋግመህ እንደምትነግረን ተወግዶአል ለማለት የአንድ ብሄር የበላይነት የሰፈነበት መከላከያ ሠራዊትህ መላው አገሪቱን በመቆጣጠር በአሶሳ፤ በአርሲ፤በሃረር ፤ በኦጋዴን ፤ በጋምቤላ ፤ በአዋሳ፤ በዋካ፤ በአረካ ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ፤ በጎንደር፤ በአዲስ አበባና በሌሎችም በርካታ ቦታዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈጸማቸው ግዲያዎች፤ እስርና እንግልት በምን ቋንቋና መስፈርት ነው በቀድሞ ስራዓቶች ከተፈጸሙት ተሽለው የተገኙት?የደህንነት ሃይሎችህ በዜጎች ላይ የሚወስዱት ዘግናኝ እርምጃዎችና አብዛኛውን ህዝብ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ የከተተው አንድ ለአምስት ጥርነፋህ እንዴት ተደርጎ ነው የሰብአዊና የዲሞክራሲ መብቶች ግንባታ ጽኑ መሠረት የሆነው?ትናንት በበረባሶ ጫማ አዲስ አበባ የዘለቀው ወታደርህና ቤሳ በስቲን ያልነበራቸው መሪዎቹ ዜጎችን ከቄያቸው በማፈናቀል በተቀራመቱት የከተማ ቦታዎች የጦፈ ንግድና በጨበጥከው የመንግሥት ሥልጣን በተመቻቸ ዘረፋ የገነቡት የንግድ ድርጅቶች፤ ህንጻና ከአለም አቀፍ አበዳሪዎች በተገኘ ገንዘብ የተሠሩ መንገዶች እንዴት የዲሞክራሲና የልማት መሠረት ሊሆኑ ይችላሉ ?በምስሌኔዎችህ የምታስተዳድራቸው ብሄር ብሄረሰቦች የእጅ አዙር አገዛዝህን አንፈልግም በስማችን አትነግድብን እያሉህ ከትውልድ መንደርህ ጀምሮ ነፍጥ እያነገቡ እያየህና እየሰማህ ስለየትኛው የብሄር ብሄርሰብ እኩልነትና ነጻነት ነው የምትደሰኩረው?ከውጭ በተገኘ የመሳሪያና የትጥቅ ድጋፍ የሰሜኑን የአገራችንን ክፍል ለማስገንጠል 17 አመት ሙሉ አገራችንን የወጋህ አንተው ሆነህ እያለህ ከየትኛው የአገር መበታተን አደጋ ነው እንደታደከን መላልሰህ እየነገርክ የምትደነቁረን ?የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በማለት የኩራት መሠረታችንን ስታፈርስ ከኖርክና በተለይ አዲሱን ትውልድ ታሪክ አልባ አድርገህ ካበቃህ ቦኋላ በየትኛው ዘመን ወደነበረው የሥልጣኔ ማማ ልትመልሰን ነው ባለ አዲስ ራዕይ የሆንክልን ?” ጆሮ ለባለቤቱ …” እንዲሉ እነዚህ ጥያቄዎች ሲነሱ ወያኔ እንደለመደው ” የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ፤ጸረ ሠላምና ጸረ ልማት ሃይሎች ፤ የብሄር ብሄረሰብ መብት የማይዋጥላቸው የአማራ ትምክህተኞች ፤ የኤርትራ የጥፋት መልዕክተኞች ፤ ሽብርተኞች” የሚሉ አራምባና ቆቦ የሆኑ መልሶችን እንደሚሰጥ መጠራጠር አይቻልም። የወያኔ ታሪክ ሁሌም የክህደት፣ የውሸት፣ የማስመሰል እና የማጭበርበር መሆኑን ሁሉም ህዝብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ነው።ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በየአመቱ የሚያከብረው ግንቦት 20 ደርግ የንጉሰ ነገሥቱን ዘውድ ገርስሶ ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ተገፍቶ ከስልጣን እስከወደቀበት ዕለት ድረስ ያከብረው ከነበረው መስከረም 2 የተለየ ነው ብሎ አያምንም። ወያኔ ደርግን በሃይል ከሥልጣን የገረሰሰበትን ግንቦት 20ን በመስከረም 2 እንደተካው ሁሉ ህዝብ ለነጻነቱ የጀመረው ትግል ተጠናክሮ ወያኔን በሃይል ከሚቆጣጠረው ሥልጣን ሲያሽቀነጥረው የግንቦት 20 በአከባበርም አብሮት እንደሚያከትም ነጋሪ አያሻውም። ህዝብ በዘር በተሰባሰቡ ባንዳዎች መዳፍ ውስጥ የገባበትን ዕለት ፤ብሄራዊ ኩራቱንና ማንነቱን የተነጠቀበት ቀን፤ በገዛ አገሩ የበይ ተመልካች የሆነበትን የወያኔ የድል ቀን መልሶ የሚዘክርበት ምክንያት አይኖረውም። ወያኔ በየአመቱ የሚያከብረው ግንቦት 20ንና የድል ፍሬዎቹን ህዝብ እንደማይጋራው ግንቦት 7 ቀን 1997 ህዝብ በግልጽ ተናግሯል።የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና የትግል አላማ ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ግንቦት 7 ቀን 1997 ያስመዘገበውን ድል መልሶ እንዲቀዳጅ ማድረግ ነው። ስለዚህም ሰላም ፍትህና እኩልነት የተጠማኸው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ በገዛ አገርህ ሠርቶ የመኖር ተስፋህ ተሟጦ ለስደት በባህርና በየብስ ለማምለጥ እያኮበኮብክ ያለህ ወጣት፤ በየስፍራው የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ለማፈን እየተላክ ከገዛ ወገንህ ጋር ደም እየተቃባህ ያለኸው ወታደር፤ የገዥዎችን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም በፖሊሲ ሃይል፤ በደህንነትና ጸጥታ ጥበቃ የተሰማራሃው ወገን ፣ ግንቦት 7 የጀመረው የነጻነት ትግል እናንተንም ጭምር ከአፈናና ከጉስቁልና ነጻ ለማውጣት ስለሆነ ዛሬውኑ ትግሉን ትቀላቀሉ ዘንድ ድርጅትህ ግንቦት 7 ወገናዊ የትግል ጥሪውን ያቀርብልሃል።የግንቦት 20 ድል መቀሌ ውስጥ የአፓርታይድ ሠፈር የገነቡ የሥርዓቱ ቅምጥሎች ፤ አዲስ አበባ ውስጥ የመቀሌ ሠፈር ተብሎ የተሰየመውን ህንጻ ያሳነጹ ሌቦች ፤ በጋምቤላ፤ በአፋር፤ በቤነሻንጉልና ማሃል ኦሮሚያ የእርሻ መሬት እየዘረፉ የተቀራመቱ ህወሃቶችና የጥቅም ተካፋዮች እንጂ የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አለመሆኑን በተግባር ለማሳየት ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የወያኔን የአገዛዝ ሥርዓት ከላያችን ላይ አሽቀንጥረን ለመጣል ከምንጊዜውም በላይ መነሳት ያለብን ጊዜው አሁን ነው።ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

አገሪቱ በሙሉ ወደ ግዙፍ እስር ቤት በተቀየረችበት ሁኔታ  የእኔ መከሰስ አያስደንቅም 

             የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአመራር አባልና የቀድሞው የአማራ ክልል ወጣቶች ሊቀመንበር ዘመነ ካሴን ጨምሮ 10 ወጣቶች በተከሰሱበት የሽብረተኝነት ወንጀል ጥፋተኞች መባላቸውን ተከትሎ፣ ክሱን በሌለበት የሚሰማው አንደኛው ተከሳሽ ዘመነ ካሴ የቀረበበትን ክስ አጣጥሎታል።
አንደኛ ተከሳሽ ዘመነ ካሴ “ኤርትራ ሄዶ የጦር ስልጠና ወስዶ መምጣቱን ፣ መንግስት አሸባሪ ብሎ ከሰየመው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራሮች በተለይም ከጄኔራል ተፈራ ማሞ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር በአካል ተገናኝቶ የሽብር ተልዕኮ መቀበሉን፣ በፌስ ቡክና በተለያዩ የኢንተርኔት ግንኙነቶች ከሌሎች አባላቱ ጋር በመገናኘትና መልዕክት በማስተላለፍ ተጠያቂ ” መሆኑን አቃቢ ህግ በክስ ማመልከቻው ላይ ጠቅሷል።
“ጄኔራል ተፈራ ማሞ በመፈንቅለ መንግስት ተጠርጥረው እስር ቤት ሲወርዱ ከስርአቱ ጋር ነበርኩ” በማለት ክሱን ያጣጣለው ዘመነ ፣ “ጄኔራል ተፈራን እስር ቤት ውስጥ አግኝተኸዋል ከተባልኩም ስርአቱን በሃይል ለማንበርከክ ከሚታገል ድርጅት ጋር ከመቀላቀሌ በፊት ከስርአቱ ጋር እያለሁ ሊያስሩኝ ይችሉ ነበር ” ብሎአል፡
“አገሪቱ በሙሉ ወደ ግዙፍ እስር ቤት በተቀየረችበት ሁኔታ  የእኔ መከሰስ አያስደንቅም ያለው ዘመነ፣ እኛ እየሞከርን ያለውን ከታሰርንበት ካቴና ተንፈራግጠን ራሳችን በማስፈታት ፣ ምናልባት ይህን አስረን ጥለነዋል የሚሉትን ትውልድ ሃይሉን አስተባብሮ ፈርገጥ እንዲልና የራሱን እጣ ፋንታ እንዲወስን” ለማድረግ ብሏል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም በ 9 ኝ ተከሳሾች ላይ፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በማሴር ከጎረቤት አገሮች ስልጠና በመውሰድ፤ የጦር መሳሪያ ግዢን በመፈፀምና የሽብር እቅድ በማውጣት በተለይም በአማራ ክልል በሚገኙ ባለስልጣናት ላይ ግድያ ለመፈፀም የተከላከሉ በይን ሰጥቷል።
ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተከሳሾች ማለትም  ዘመኑ ካሴ፣  አሸናፊ አካሉ፣  ደናሁን ቤዛ፣  ምንዳዬ ጥላሁን እና  አንሙት ይሄይስ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ግንኙነትን በመፍጠር ተልዕኮና ትዕዛዝን በመቀበልና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚረዳቸውን የመሳሪያ ግዢ እንዲከናወን ማድረጋቸውን አቃቢ ህግ ገልጿል።
“በአንፃሩ ደግሞ ከ6ኛ እስከ 9ኛ ድረስ ያሉት ተከሳሾች ደሳለኝ አሰፋ፣  ምክትል ኢንስፔክተር ሙልዩ ማናዬ፣  ጠጋው ካሳና  ይህአለም አካሉ በሽብር እንቅስቃሴው ውስጥ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እርዳታ ሰጥተዋል” የሚለው አቃቢ ህግ፣ ከተከሳሾች መካከል10ኛ ተከሳሽ ሆና ጉዳዩዋን ስትከታተል የቆየችው ሙሉ ሲሳይ በነፃ እንድትሰናበት ተደርጓል።
ኢሳት ዜና

Friday, May 30, 2014

አልሸባብ ባደረሰው ጥቃት 40 ያህል ሰዎች ተገደሉ ተባለ፡፡


አልሸባል ጥቃቱን ያደረሰው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር ላይ በምትገኝ አንድ መንደር ላይ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡
የሶማሊያ የባኮ ክልል አስተዳዳሪ ሙሃመድ አብዱል ታል ለቪኦቬ እንዳሉት ኮሆነ 27 የመንግስት ሚሊሻዎችን እና 12 የአልሸባብ ተዋጊውች ሞተዋል፡፡
አስተዳዳሪው አክለውም የአልሸባብ ጥቃት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ በነበሩ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
አልሸባብ በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም አሁንም የአካባቢው የጸጥታ ችግር መሆኑ በዘገባው ተመልክቷ፡፡


Thursday, May 29, 2014

መንግሥት የፈረመው ስምምነት ጥራት የሌላቸው የቻይና ምርቶች እንዲገቡ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ

‹‹በትራንስፎሜሽኑ  ዘመን የዓለም የንግድ ድርጅትን አንቀላቀልም›› አቶ ከበደ ጫኔ፣ የንግድ ሚኒስትር መንግሥት ከዓመታት በፊት ከቻይና ጋር የተፈራረመው የንግድ ስምምነት የጥራት ደረጃቸው የወረዱ ምርቶች ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ምክንያት መሆኑን የንግድ ሚኒስትሩ ለፓርላማ ገለጹ


ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ ነው

በዛሬው ዕለት ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ በተለይ ቦሌ እየተባለ የሚጠራው ሰፈር የሚገኙ ቤቶች በዛሬው ዕለት እየፈረሰ እንደሚገኝና ህዝብ ይቃወማል በሚል ቡችሌ፣ ሚሊሻ፣ ህዝባዊና ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ይህ ቦሌ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ትናንት ሊፈርስ የነበረ ቢሆንም በግንቦት 20 ምክንያት እንደታለፈ ተገልጾአል፡፡
ደብረ ማርቆስ ውስጥ ቤቶችን ማፍረስ የተጀመረው ግንቦት 18ና 19/2006 ዓ.ም ሲሆን ቀበሌ አራት (4) በተለይም ሞንቃ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር 400 ያህል ቤቶች እንደፈረሱ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ቦሌ የተባለው ሰፈር እንዳይፈርስ በተደረገበት በትናንትናው ቀን ከ23 አመት በላይ ግብር ሲከፈልበት የኖረ የአንድ ግለሰብ ቤት መፍረሱም ታውቋል፡፡ አፍራሽ ግብረሃይሉ የቤቱን ጣራ ካፈረሰ በኋላ ግለሰቡ ለ23 ዓመት ግብር ሲከፍልበት የነበረ መሆኑን በመገለጹ ግድግዳው ብቻ እንደቆመ ወደ አቤቱታ መመራቱን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ደብረ ማርቆስ ውስጥ አብዛኛዎቹ ቤቶች ከ1997 ጀምሮ የተሰሩ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ቤቶች አርሶ አደሮች በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማ በተከለለው መሬታቸው ላይ የሰሯቸው እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ‹‹የአርሶ አደሮቹ መሬቶች ወደ ከተማ ሲከለሉ መንግስት ተለዋጭ ወይንም ካሳ የመስጠት ግዴት የነበረበት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥነት እያፈረሰ እያፈረሰ ይገኛል›› ያሉት አንድ የከተማዋ ነዋሪ እርምጃው ህገ ወጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡



ነዋሪዎች ግንቦት 20 ዳግም በኢትዮጵያ ሲከበር ማየት እንደማይሹ በምሬት ገለጹ

ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው አንዳንድ ዜጎች ” የግንቦት20ን በአል ተገደው እንዲያከብሩ መደረጋቸውን ሲገልጹ” ፣ ሌሎች ደግሞ በአሉ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድር ተከብሮ ማየት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።
ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የግንቦት 20 ድል የመግብ ዋስትናችንን እንድናረጋግጥ እረድቶናል ያሉ ሲሆን፣ አገሪቱ በ1983 ዓም ታመርት ከነበረው 50 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ወደ 250 ሚሊዮን ኩንታል መሸጋገሩዋን ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም ይህን ይበሉ እንጅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም በያዝነው አመት ከ6 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
በአሉ በሚከበርበት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገኙት አቶ ሃይለማርያም ፣ ከግንቦት20 በሁዋላ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሚሊየነሮችና ቢሊየነሮች መፈጠራቸውንም ገልጸዋል። እነዚህ ሚሊየነሮች የየትኛው ብሄር እና የየትኛው ስርዓት ደጋፊ መሆናቸውን አልተናገሩም።
የኢህአዴግ ባለስልጣናት በግንቦት20 በርካታ ድሎች የተመዘገቡበት እንደሆነ ቢገልጹም ዜጎችና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ግን የግንቦት 20ን ድል አጣጥለውታል።
አንዲት እናት ኢህአዴግ በመጪው ምርጫ ካሸነፈና በሚቀጥለው አመት ግንቦት20ን የሚያከብሩ ከሆነ እራሴን አጠፋለሁ ሲሉ ለኢሳት ገልጸዋል። በሀረር ከተማ የሚኖር ሌላ ወጣት ደግሞ ህዝቡ ሳይፈልግ እየተገደደ ሰልፍ እንዲወጣ መደረጉን ተናግሯል።
መንግስት በአሉን ለማክበር ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማፍሰሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
በአዲስ አበባ ብቻ በአንድ ቀበሌ ብቻ ለሻማ ፣ ጧፍ፣ ባንዲራ መስቀያ እንጨት፣ መፈክሮች፣ ለለስላሳ መጠጦችና እሽግ ውሃ ፣ ኩኪስና ቆሎ ፣ለትራንስፖርት እና ለመሳሰሉት ወጪዎች እስከ 5 ሺ ብር የሚደርስ ገንዘብ ሲወጣ፣ በክፈለ ከተማ ደረጃ ለሚደረጉ ስብሰባዎች ደግሞ ለአዳራሽ ኪራይ ከሚወጣው እስከ 15 ሺ ብር ከሚደርስ ገንዘብ ጀምሮ፣ ለኬክ፣ ለውሃ፣ ሻሂና ቡና አቅርቦቶች የሚወጡት ወጪዎች እጅግ ከፍተኛ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
በአገር አቀፍ ደረጃ ለበአሉ ወጪ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚወጣ ግምቶች የሰፈሩ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን በጅጅጋ ለማክበር ካወጣው ወጪ ጋር ሲተያይ የዘንድሮው የግንቦት 20 በአል በብዙ እጥፍ ይበልጣል።


አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ለማግኘት ያሰቡ ግለሰቦች ሁለት ሚሊዮን ብር መዘረፋቸው ተጠቆመ


በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ በሕገወጥ መንገድ የውጭ አገር ገንዘቦችን የሚዘረዝሩ ግለሰቦች፣ አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ለማግኘት የማያውቋቸው ግለሰቦች ዘንድ ሄደው ሁለት ሚሊዮን ብር መዘረፋቸው ተጠቆመ፡፡

በዕለተ ሰንበት እሑድ ግንቦት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. የስልክ ጥሪ የደረሳቸው ግለሰቦች ስለሚያገኙት ሥራና ትርፍ እንጂ ሊገጥማቸው ስለሚችለው ችግር አለማሰባቸውን የገለጹት ምንጮች፣ በደረሳቸው የስልክ ጥሪ ‹‹አንድ መቶ ሺሕ ዶላር አለን›› ያሏቸው ግለሰቦችን ማንነት ሳይሆን፣ የሚገኙበትን ሥፍራ ብቻ መጠየቃቸውን አውስተዋል፡፡

በእጃቸው አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ቀርቶ ምንም ነገር ያልያዙት ግለሰቦች ያሉበትን ቦታና የያዙትን የተሽከርካሪ ዓይነት ሲነግሯቸው፣ ተዘራፊዎቹ ግለሰቦች ሁለት ሚሊዮን ብር ይዘው ለመድረስ ጊዜ እንዳልፈጀባቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ሁለት ሚሊዮን ብር ተሸክመው አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ለመግዛት የሄዱት ግለሰቦች የጠበቃቸው አንድ መቶ ሺሕ ዶላር ሳይሆን መሣሪያና ከፍተኛ ማስፈራሪያ በመሆኑ፣ ምንም ሳያንገራግሩ ሁለት ሚሊዮን ብራቸውን እንዳስረከቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

የደረሰባቸውን ተጨማሪ በደል መግለጽ ያልፈለጉት ተዘራፊዎች፣ የተንቀሳቀሱበት ጉዳይ ሕገወጥ ቢሆንም ገንዘቡ ሁለት ሚሊዮን ብር በመሆኑ ያዋጣናል ወዳሉትና የመጀመሪያው የሕግ ማስከበሪያ ቦታ ወደሆነው ፖሊስ ማምራታቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሆኑትን ሁሉ ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡት ተዘራፊዎቹ፣ የዘራፊዎቹን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲገልጹ በፖሊስ ሲጠየቁ፣ መሣሪያ የያዙና ፈርጣማ አቋም ያላቸው መሆናቸውን  በዝርዝር ማስረዳታቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡

ጉዳዩን ይዞ ሁለት ሚሊዮን ብር ዘርፈው የጠፉትን ግለሰቦች እያፈላለገ ነው የተባለውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም ምላሽ ለማግኘት አልተቻለም፡፡


አቶ መለስ ዜናዊ በአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ ላይ የፈፀሙት አሳፋሪ ወንጀል ሲጋለጥ…(በትረ ያቆብ)


በ በትረ ያቆብ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአፍሪካ ምድር ላይ ሰላምና ብልፅግና እዉን ያደርጋል ተብሎ በአፍሪካ ህብረትና በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋት ታምኖበት የተቋቋመዉ እና “የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ” (African Peer Review Mechanism) የተሰኘዉ ተቋም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የተነሳለትን አላማ እንደሳተ እና ከጥቅም ዉጭ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ፡፡ በተያያዘም በተደራጀ የሙስና ሰንሰለት ተጠልፎ የግለሰቦች ኪስ ማድለቢያ እንደሆነም እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ከዚህ ብዙ አፍሪካዉያንን ካሳዘነ ጉዳይ ጋር በተያያዘም በቀዳሚነት የቀድሞዉ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ፓርቲያቸዉ ህወሐት/ኢህአዴግ አብረዉ እየተወነጀሉ ነዉ፡፡

ይህን አሳፋሪ የአቶ መለስን እና የፓርቲያቸዉን ተግባር በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ መረጃ የደረሰኝ ከሶስት ወር በፊት ሲሆን ፡ መረጃዉን ለጓደኛየ የላከችለት አንዲት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ያካሄደችና ብዙ ዘገባዎችን የሰራች አፍሪካዊ ጋዜጠኛ ነበረች፡፡ የላከችዉም ኢትዮጵያዉያን ሊያዉቁት ይገባል በሚል ነበር፡፡ ባደረግኩት መጠነኛ ጥናት እንደተረዳሁት ጉዳዮ ባልታወቀ ምክንያት ተዳፍኖ እንዲቆይ ህብረቱ ብርቱ ጥረት ያደረገ ሲሆን ፤ ህወሃት/ኢህአዴግም ጉዳዮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀሮ እንዳይደር ብዙ ጥሯል፡፡ ያም ሆኖ ግን ጉዳዩን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች ከዚህ በፊት በአንዳንድ የአፍሪካ ሚዲያዎች አማካኝነት ለህዝብ ይፋ ሊሆኑ ችለዋል፡፡ ነገር ግና እስከ አሁን ግልፅ በሆነ መንገድ መረጃዉ ለህዝብ እንዳልደረሰ ይነገራል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት “የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ” (African Peer Review Mechanism) የተቋቋመዉ በ2003 ዓም ሲሆን ፤ የተቋሙ አላማም የእያንዳንዱን የሕብረቱ አባል ሀገር አጠቃላይ የፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በተመለከተ በገለልተኝነት ጥናት እና ግምገማ ማድረግ እንዲሁም ከዚህ በመነሳት የፖሊሲ አቅጣጫችን ለኃብረቱ በማቀበል ኔፓድ ግቡን እንዲመታ ማድረግ ወይንም የአፍሪካን ሰላም እና ብልፅግና ማረጋገጥ ነዉ፡፡ በተለይም ተቋሙ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ ሙስና እና የሀብት አጠቃቀም ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ ተቋሙ በእነዚህ እስትራቴጅክ የአፍሪካ ሀገራት ችግሮች ላይ መስራትና ለዉጥ ማምጣት ከተቻለ አፍሪካን ካለችበት ኋላ ቀርነትና ድህነት ማዉጣት ይቻላል የሚል እምነት አንግቦ የተነሳ ነዉ፡፡

በግንቦት7 ስም የተከሰሱ ጥፋተኞች ተባሉ


May 28/2014

 ኢሳት ዜና :-የግንቦት7  ህዝባዊ  ሃይል የአመራር አባልና የቀድሞው የአማራ ክልል ወጣቶች ሊቀመንበር ዘመነ ካሴን ጨምሮ 10 ወጣቶች በተከሰሱበት የሽብረተኝነት ወንጀል ጥፋተኞች ተብለዋል።

ሰንደቅ እንደዘገበው አቃቢ ህግ ተከሳሾች ከግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር በህቡዕ ግንኙነት በመፍጠር፤ ኤርትራ ድረስ በመሄድ የጦር ስልጠና በመውሰድና ተልዕኮ ተቀብለው በመምጣት በጦር መሳሪያ የታገዘ የሽብር ወንጀል ሊፈፅሙ ነበር ብሎአል።

የፌዴራሉ  ከፍተኛ  ፍርድ  ቤት  4ኛ  ወንጀል ችሎት ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ተከሳሾች እንዲከላከሉ ሲበይን፣ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ህገ-መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በማሴር ከጎረቤት አገሮች ስልጠና በመውሰድ፤ የጦር መሳሪያ ግዢን በመፈፀምና የሽብር እቅድ በማውጣት በተለይም በአማራ ክልል በሚገኙ ባለስልጣናት ላይ ግድያ ለመፈፀም አሲረው መንቀሳቀሳቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።አንደኛ ተከሳሽ ዘመነ ካሴ “በዐቃቤ ህግ ክስ ስር ከቀረቡበት ክሶች መካከል ኤርትራ ሄዶ የጦር ስልጠና ወስዶ መምጣቱን ፣ መንግስት አሸባሪ ብሎ ከሰየመው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራሮች በተለይም ከጄኔራል ተፈራ ማሞ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር በአካል ተገናኝቶ የሽብር ተልዕኮ መቀበሉን፣  በፌስ ቡክና በተለያዩ የኢንተርኔት ግንኙነቶች ከሌሎች አባላቱ ጋር በመገናኘትና መልዕክት በማስተላለፍ ተጠያቂ ” መሆኑን ገልጿል።

ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተከሳሾች ማለትም  ዘመኑ ካሴ፣  አሸናፊ አካሉ፣  ደናሁን ቤዛ፣  ምንዳዬ ጥላሁን እና  አንሙት ይሄይስ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ግንኙነትን በመፍጠር ተልዕኮና ትዕዛዝን በመቀበልና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚረዳቸውን የመሳሪያ ግዢ እንዲከናወን ማድረጋቸውን አቃቢ ህግ ገልጿል።

“በአንፃሩ ደግሞ ከ6ኛ እስከ 9ኛ ድረስ ያሉት ተከሳሾች ደሳለኝ አሰፋ፣  ምክትል ኢንስፔክተር ሙልዩ ማናዬ፣  ጠጋው ካሳና  ይህአለም አካሉ በሽብር እንቅስቃሴው ውስጥ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እርዳታ ሰጥተዋል” የሚለው አቃቢ ህግ፣ ከተከሳሾች መካከል  10ኛ ተከሳሽ ሆና ጉዳዩዋን ስትከታተል የቆየችው ሙሉ ሲሳይ በነፃ እንድትሰናበት ተደርጓል።
ተከሳሾች  ከመጪው ሰኔ 17 እስከ 20 ቀን 2006 ዓ.ም በተከታታይ የመከላከያ ማስረጃዎቻቸውን በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት እንዲያቀርቡም መታዘዛቸውን ጋዜጣው ዘገባውን አጠቃሏዋል። ዘመነ ካሴ የተከሰሰው በሌለበት ነው::

Wednesday, May 28, 2014

ኃይለማርያም “ኢትዮጵያዊነት ደምቋል” አለ

በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው የግንቦት ሃያ 23ኛ ዓመት በዓል አካል የሆነው የዛሬው ሥነ-ሥርዓት ይበልጥ ደማቅና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚገኙበት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ቀደም ብሎም ገዥው ፓርቲ ወያኔና መንግሥት በሃያ ሦስቱ ዓመታት የሥልጣን ዘመን ተገኙ ያሏቸውን ውጤቶች፣ ተመዘገቡ ያሏቸውን ድሎች ሲገልፁ ነው የሰነበቱት፡፡


40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን? “ኢትዮጵያን በጎሳ ሳጥን ቆልፎ የሚጓዘው ህወሃትና ድግሱ”


ህወሃት በነጻ አውጪ ስም ታግሎ ኢትዮጵያን መግዛት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ነው። ወዳጆቹና መሪዎቹ ባስቀመጡት እቅድ መሰረት ኢትዮጵያን “በመተካካትና በተሃድሶ” ስም ራሱን እያገላበጠ ለመግዛት የቆረጠው ጊዜ በትንሹ 40 ዓመታት እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ባለው የሰረገላው ጉዞ ኢህአዴግ ከ40 – 23 ከመቀነሱ ውጪ አሰበበት ስለመድረሱ መገመት የሚያስችል ምልክት የለም። እንደውም ስጋት እንጂ።ሲጀመር “የገበሬ ተሟጋች” ነኝ በማለት ራሱን የአርሶ አደሩ ወኪል አድርጎ የተነሳው ህወሃት፣ ኢህአዴግ ሆኖ አገር መግዛት ሲጀምር ያስቀደመው የብሄር ብሄረሰቦችን የመብት ጥያቄ እንደ ውዳሴ ጸሎት በመደጋገም ነበር። በዚሁ በጎሳ ላይ ተመስርቶ በቋንቋ የተቆለፈው የአገዛዝ ስልት ሲጀመር ማስጠንቀቂያ የሰጡ፣ ለመታገል የሞከሩ፣ የታገሉ፣ ያስተባበሩ፣ ያደራጁ የህወሃት የ40 ዓመት ጉዞ ጸር ተደርገው ተወሰዱ። ስለ ኢትዮጵያ ጥቅምና ኢትዮጵያዊነት ያሳሰቡ ጠላት ተደርገው ተፈረጁ። በስውር በአፈና፣ በግልጽ ህግ እየተጠቀሰባቸው ከጫወታና ከመኖር ተገለሉ። ብዙዎች እንደሚሉት “የጉዳቱን መጠን ህወሃትና የተጎዱት ቤተሰቦች ይቁጠሩት”!ግንቦት ሃያ “የህዝብ የድል ክቡር ቀን ነው” በሚሉና “የህዝብና የአገር ውድቀት የታወጀበት የክፉ ቀኖች ሁሉ ድምር” ሲሉ በሚሰይሙት መካከል ሰፊ መከራከሪያ አለ። የመንገድ ግንባታ፣ የህንጻ ግንባታ፣ የኮሌጅና የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የግድቦች ግንባታና የአባይ ወንዝ ልማት ወዘተ ጉዳዮች የግንቦት 20 ጣፋጭ ፍሬዎች ስለመሆናቸው “የቀኑ ወዳጆች” ይከራከራሉ። የቀኑ “ባሮችም” ይህንኑ ውዳሴ በማቀንቀን ታማኝነታቸውን ይገልጻሉ። በጥቅም የተደለሉ ሎሌዎች ስለሆኑ ይህንን ድል ለማስጠበቅ በግልጽና በህቡዕ አድርጉ የተባሉትን ያደርጋሉ።በተጠቀሱት የልማት ስራዎች ላይ ተቃውሞ የማያነሱ የቀኑ “ሰለባዎች” ሰላምና መረጋጋት እንዳለ የሚሰብክ አስተዳደር ልማትን ከመስራት ሌላ ተግባር እንደሌለው ይገልጻሉ። አያይዘውም ጣሊያንም በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ በርካታ መንገድና ድልድዮችን መገንባቱን ያጣቅሳሉ። ከሁሉም በላይ ግን ኢህአዴግ በሚገዛት አገርና ሕዝብ ስም የተበደረውን የገንዘብ መጠን “ከተዘረፈው ውጪ” በማለት ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “መንገድ መስራትና ህንጻ ማቆም የመብት ጥያቄን በጥይት ለመመለስና በደም ለመጨማለቅ ዋስትና ሊሆን አይችልም” በማለት ስርዓቱን አጥብቀው ይኮንኑታል።በሌላም ወገን የተሰሩትን ህንጻዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች በማንሳት “የግንቦት 20 ፍሬዎች” ሲሉ ይሰይሟቸዋል። ሲያብራሩም “የነዚህ ሁሉ ሃብቶች መነሻና ባለቤቶች ህወሃትና ህወሃት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ባለሟሎች ናቸው። የህዝብ አይደሉም። ሕዝብም አያምንባቸውም” በማለት ጥርስ ይነክሱባቸዋል። በዝርፊያ ሃብት የሚያግበሰብሰውን ኤፈርት ኢትዮጵያን “ንብረቶችሽን ባደራ ላስቀምጥ” የሚል እስከሚመስል የንግድ ኢምፓየሩን ማስፋቱን አብዝተው ይኮንናሉ።የግንቦት 20፣ የቀኑ ወዳጆች ኤፈርት ላይ የሚቀርበውን ጥያቄ አያስተባብሉትም። ይልቁኑም ድርጅቱ ጓዳና ካዝናው የተለጎመ መሆኑ ያብከነክናቸዋል። አለው የሚባለው ሃብት ሁሉ የትኛው ቋት እንደሚቀበር ስለማይረዱ “የተሸውደናል” ስሜት አላቸው። ለዚህም ይመስላል የህወሃት ወዳጆች “ኤፈርትን ያየህ ወዲህ በለኝ” ሲሉ የሚደመጡት። በግልጽ አነጋገር ኤፈርት ፊት ለፊት ከሚያሳየው ሃብቱ ይልቅ፣ የማይታው ጉዱ ስለሚያመዝን በህወሃት ወዳጆች ሳይቀር አልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) የተደቀነበት ነው።አፈናው፣ ግድያው፣ እስሩ፣ ዝርፊያው፣ ከላይ ከተገለጸው በተቃራኒ አርሶ አደሩ ላይ የሚፈጸመው የመሬት ቅሚያ ሌላው የግንቦት 20 የጨነገፈ ፍሬ ተደርጎ ይወሰዳል የሚሉ አሉ። በተለይም ራሱ ህወሃት ሁሉንም በራሱ ደረጃ ለማሳነስ ሲል ያዋቀረው የቋንቋና ጎሳን ተገን ያደረገ የአገዛዝ ስልት ዛሬ ግንቦት 20ን እድሜውን ወደ ማሳጠር እያደረሱት ነው ሲሉ ያክላሉ። በዚህ አስተሳሰብ ላይ የሚተቹ ሰሞኑን አጠንክረው እንደገለጸት “የግንቦት 20 ወዳጆች ኢትዮጵያዊነት ከውስጣቸው እንዲወልቅ ተደርጎ በተዘጋጀላቸው የትምህርት እቅድ፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ … መሰረት ወደ ጎሳ እየጠበቡ የግንቦት 20 ድል ‘ሰረገላው’ መድረስ የፈለገበት ቦታ ሳደርስ ሃዲዱን ሊያወላልቀው ይችላል”፡፡40 – 23 ዓመት ላይ ያለው ኢህአዴግ ህወሃትን እያጀበና እየሞሸረ ወደ “መንገሻው” ለማድረስ የተሰሩበት የጎሳ ኬሚስትሪ እንደሚከለክላቸው የሚናገሩ ክፍሎች “የግንቦት 20 ድል እየተከበረ 40 ዓመት መዝለቅ ምናልባትም ከተረትም የወረደ ሟርት ነው” ባይ ናቸው። ህወሃት ለጊዜው ብሎ የዘራው የበቀል ዘርና በጎሳ ሳጥን ውስጥ ከቶ ያሳደጋቸው ወዳጆቹና በጊዜ የታሰረ ቦንብ እንደሚሆኑበት ምልክቶቹ ከበቂ በላይ እንደሆኑም ይናገራሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት “ህወሃትን የሚበሉት ራሱ ያመረታቸው ፈንጂዎቹ ናቸው” በመሆኑም የዘንድሮው ግንቦት 20 አንጸባራቂ ጥቅስ “ለመጥበብ ብሎ ህወሃት የወጠነው የጎሳ መዋቅርና አስተምህሮት የህወሃት ፉርጎ የሚሄድበትን ሃዲድ እያወላለቀው ነው” የሚለው ይሆናል – “ጉድጓድ የሚምስ ራሱ ይወቅድበታልና”፡፡

የ“ቀለም” አብዮት ናፍቆት! (ጋዝጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )

May 27, 2014

የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ያበሰረው የጀርመን ግንብ ሊፈርስ ሶስት ዓመታት ብቻ በቀሩበት ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ ቅጥ ካጣ አምባ-ገነንነቱ በተጨማሪ ሀገሪቷን የግል ርስቱ ያደረገው የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርቆስ “ታሪካዊ” የሚባል ታላቅ ስህተትን ፈፀመ፤ ጠንካራ ተፎካካሪው ሊሆን እንደሚችል ቅድመ-ግምት ተሰጥቶት የነበረውን የተቃዋሚው ቡድን መሪ ካስገደለ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እንዲካሄድ የፈቀደውን ምርጫ በአሳፋሪ መንገድ አጭበረበረ፡፡ ይህን ጊዜ የሕዝቡን ትዕግስት አልባነት የተረዱና መነሻቸው ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን የሆኑ ቁጡ ወጣቶች የማኒላ ጎዳናዎችን አጥለቀለቁ፡፡ ለሶስት ቀናት (ከየካቲት 22-25) በቆየው ሕዝባዊ ንቅናቄም ጡንቸኛውን ማርቆስ ከመንበሩ ፈነቀሉት፡፡

አመፀኞቹ ፊሊፒናውያን በሀገሬው ባህልና የቆየ እምነት መሰረት እንቅስቃሴው ሰላማዊ መሆኑን ለመግለፅ ሲሉ በማኒላ አውራ መንገዶች ታንክ ጠምደው ተቃውሞውን ለማክሸፍ ለተሰለፉት የሀገሪቱ ወታደሮች ቢጫ አበባ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ አመፁ “ቢጫ አብዮት” የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡ ይህ ሁነትም ጥቂት ዓመታት ዘግይተው በምስራቅ አውሮፓ ለተቀጣጠሉ አብዮቶች በቀለም መሰየም መነሻ መሆን መቻሉን በጉዳዩ ዙሪያ የተዘጋጁ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ፡፡ በ1990ዎቹ አጋማሽ በዚህ ክፍለ-አህጉር የተደረጉት ህዝባዊ አመፆች፣ የተለያዩ ቀለማትን እንደየሀገራቱ ባሕልና ወግ በትእምርትነት መጠቀም መጀመራቸውም የሚያስረግጠው ይህንኑ እውነታ ነው፡፡

በአናቱም የኢራኑ የ2002ቱ “አረንጓዴ” አብዮት፣ የተቃውሞ መሪው ሆስኒ ሞሳቪ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተጠቀመበት ቀለም በመሆኑ ሲመረጥ፤ የቅርቡ የግብፅ አብዮትም በጥንታዊቷ የፈርኦን ምድር ልማድ፡- ትንሳኤን፣ ህይወትንና ፀሐይን በተምሳሌትነት በያዘው “ሎተስ” በተባለ አበባ እንዲሰየም በአብዮተኞቹ ተመርጧል (የድህረ-ሙባረክ ግብፅን ወደጥንት ታላቅነቷ የመመለስ ግብን ይተረጎማል በሚል)፡፡ ቀድሞ በግራ-ዘመሞች (ኮሙኒዝምን ለመመስረት) ይመራ የነበረው ጠብ-መንጃ ቅልቅሉ አብዮት ምዕራፍ ከተዘጋ በኋላ፣ በእንዲህ ያለ ፍፁም ሰላማዊ መንገድ የሚካሄዱ ንቅናቄዎች “የቀለም አብዮት” በሚል ስያሜ መጠራት መጀመራቸው ይታወቃል፡፡

የቀለም አብዮቶቹ በረከቶች

በምስራቅ አውሮፓ በአድቃቂው የማሕበረ-ሱታፌ (ሶሻሊስት) ሥርዓት ማግስት ብቅ ያሉት መሪዎች ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን በመገንባት ሽግግሩን መምራት ባለመቻላቸው እና ነፃ ማሕበረሰብ ለመፍጠር የተነቃቃውን ልሂቅ ህልሞች በኃይል በማጨንገፋቸው የቀለም አብዮቶቹ መቀስቀስ ብቸኛው የታሪክ ምርጫ ሆኗል፡፡ በመጨረሻዎቹ የኮሙኒዝም መንኮታኮት ዋዜማ እና በዚህ ክፍለ-ዘመን መባቻ ላይ ግዙፎቹን ሥርዓታት ያፈራረሱ ማሕበረሰባዊ መነቃቃቶች (ሰላማዊ አብዮቶች) ከኮሙኒዝም ወደ ዲሞክራሲዊ አስተዳደር መሸጋገርን ዋነኛ ዓላማ ከማድረጋቸው በተጨማሪ፣ ባተገባበር የጋራ መለዮ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ለሳምንታት ወይ ለወራት ድንኳን ዘርግቶ በአደባባይ በመቀመጥ፤ አሊያም ለተከታታይ ቀናት ሰላማዊ ሰልፎችንና የሥራ ማቆም አድማዎችን በመምታት መንግስታዊ ተቋማትን ማሽመድመድ… ከሞላ ጎደል መገለጫዎቻቸው ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የምርጫ መጭበርበርን ተከትለው የሚቀሰቀሱ መሆናቸውም ያመሳስላቸዋል፡፡ ለዚህም ከፊሊፒንሱ ‹‹ቢጫ›› እስከ ጆርጂያ ‹‹ፅጌረዳ››፤ ከካዛጊስታኑ ‹‹ሮዝ›› እስከ ዩክሬን ‹‹ብርቱካንማ›› አብዮቶች ድረስ የተመለከትናቸው የአደባባይ ተቃውሞዎች በድህረ-ምርጫ ወቅቶች መቀስቀሳቸው ማሳያ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንቅናቄዎቹ በሙሉ የተመሩት በሲቪል ድርጅቶች አሊያም በወጣቶች ስብስብ መሆኑ ሌላው የሚያመሳስላቸው ባህሪይ ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ያየናቸው የቀለም አብዮቶች በዋናነት በመንገዱ ነፍስ-አባት ጄን ሻርፕ ‹ቅዱስ መፃህፍት› የተቃኙ ሲሆኑ፤ በተለይም የአንሳንሱኪን ረዥም እስር ላመጣው ለ1985ቱ የበርማ እንቅስቃሴ የጻፈው ‹‹ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ›› የተሰኘ ስራው ለታህሪር ወጣቶች ጭምር በመመሪያነት ማገልገሉ ይታወሳል፡፡ የዚህ የ86 ዓመት አዛውንት ጸሐፊ ዋነኛ ጭብጥ ‹‹ገዢዎች የሚሰነብቱት ህዝብ እስከፈቀደ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ዜጎች የመገዛት ፈቃዳቸው ቀስ በቀስ እየቀነሰ ከሄደ አም-ባገነኖቹ መውደቃቸው አይቀርም፡፡ ይህንንም ለማድረግ እነርሱ የሚያሸንፉበትን የብረት ትግል ከመምረጥ ይልቅ፣ ሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ብቸኛው መንገድ ነው›› የሚል መሆኑ ለተቀባይነቱ አስተዋፅኦ ያደረገለት ይመስለኛል፡፡

በሌላ በኩል የቺኮዝሎቫኪያው የ‹‹ቬልቬት›› (ጀንትል) እና የዩጎዝላቪያው ‹‹ቡልዶዘር›› አብዮቶች በስኬታማነት ለመጠቀስ የሚበቁ ናቸው፡፡ በህዳር ወር 1981 ዓ.ም የተከበረውን አለም አቀፍ የተማሪዎች ቀን አስመልክቶ ፕራግ ከተማ በተሰባሰቡት ተማሪዎች ላይ ፖሊስ የወሰደው የኃይል ጭፍለቃ ያስቆጣቸው ግማሽ ሚሊየን ዜጎች ወደ ከተማይቱ አደባባይ በመትመም ያካሄዱት ‹‹የፕራግ ፀደይ›› የተሰኘ ሕዝባዊ ዓመፅ፣ በቀናት ውስጥ ነበር ኮሙኒስት ስርዓቱን ያንኮታኮተው፡፡ በርግጥ ለዚህ ዓመፅ መነሳሳት፣ አብዮቱን እንዲመራ ከቤቱ የተጠራው ቫክላቭ ሆቬልና ጓዶች አቋቁመውት የነበረው ‹‹ቻርተር 77›› የተባለው የመብት ተሟጋች ሲቪክ ማሕበር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ብዙዎቹ አባላቱም ሀገሪቱ ቼክና ስሎቫክ ተብላ ለሁለት ከተከፈለች በኋላም በፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደነበራቸው ይታወሳል፡፡ ሌላኛው ‹‹አትፓር›› በተሰኘ የወጣቶች ንቅናቄ ተመርቶ አምባ-ገነኑን ስሎዶቫን ሚሎሶቪችን መመንገል የቻለው የ‹‹ቡልዶዘር›› አብዮት ተብሎ የሚጠራው ሕዝባዊ አመፅም፣ በሰላማዊነቱና በመልካም ምሳሌነቱ ከቀለም አብዮቶቹ ጋር አብሮ ይዘከራል፡፡

የ‹‹ቀለም›› አብዮቶች እና እኛ

በምስራቅ አውሮፓ ሀገራት የቀለም አብዮቶች የተካሄዱበት አውድ፣ እንደኛይቷ ኢትዮጵያ የሽግግር ማሕበረሰቦች መሆናቸውን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ተመሳስሎ መኖሩን መካድ አይቻልም፡፡ በተለይም ከአረብ አገራት ይልቅ ከእነዚህኞቹ ጋር የሚያስተሳስረው ከአርባና ሃምሳ ዓመታት በፊት የዲሞክራሲ ጥያቄ በኢትዮጵያም ተነስቶ የነበረ መሆኑ (መቼም በአረቦች ምድር ከአምስትና አስር ዓመት ቀደም ብሎ እንዲህ አይነቱ ጥያቄ የሚታሰብ እንዳልነበረ ልብ ይሏል)፣ ሀገራችንም ሆነች ምስራቆቹ በሕብረ-ሱታፌ ሥርዓት ማለፋቸው፣ በፖለቲካ የነቃ ማሕበረሰብ መኖሩ (በቅርቡ በዩክሬን የተመለከትነው አብዮት ዋነኛ መነሾ መንግስት ከአውሮፓ ሕብረት ይልቅ ወደሩሲያ ማዘንበሉን በመቃወም እንደሆነ ይታወቃል)… የመሳሰሉት ተያያዥ ጭብጦች እነርሱ ያለፉበትን መንገድ መርምረን ከጥንካሬያቸውም ሆነ ከድክመታቸው መማር እንድንችል ዕድል ይፈጥራል ብሎ መደምደሙ ማጋነን አይሆንም፡፡

የሆነው ሆኖ ስለመጪው አብዮት እንዲህ አብዝተን እንድንጨነቅ የሚያስገድደን የተጠቀሱት ሀገራትን ሕዝብ፣ ለተቃውሞ አደባባይ ያወጧቸው ገፊ-ምክንያቶች እጅግ በከፋ መልኩ በዚህችም በእኛይቱ ሀገር ሞልተው የመትረፍረፋቸው እውነታ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ሁለቱ አብዮቶች (የየካቲቱ እና የ83ቱ) ያልመለሷቸው በርካታ መሠረታዊ ጥያቄዎች ከመኖራቸው በተጨማሪ፣ ኢህአዴግ ያነበረው ሥርዓት የዲሞክራሲ ጭፍለቃው ገደብ ማጣት እና የተሳሳተ ፖሊሲው ያስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት ወደዚህ ጠርዝ የሚገፋ ተጨባጭ ሀቅ ነው፡፡

በርግጥ የየካቲት 66ቱም ሆነ የግንቦት ሃያው አብዮቶች ከአውዳሚ ውጤቶቻቸው ጋር የተመጣጠነ ባይሆንም፣ የራሳቸው የሆነ በጎ አበርክቶ እንዳላቸው አይካድም፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በምሳሌነት የሚጠቀሰው፣ ቀዳሚው ከባሕላዊ እና ኋላቀር ንጉሳዊ አገዛዝ ወደ ወታደራዊ የተደረገ ለውጥ ቢሆንም፣ የዘመናዊውን ስነ-መንግስታዊ ኑባሬ የመፍጠር ሙከራው አዎንታዊ ተብሎ በታሪክ መመዝገቡ ሲሆን፤ ዳግማዊው አብዮት ደግሞ በተሻለ ሁኔታ የፓርቲ ፖለቲካን እና ሀሳብን የመግለፅ መሰል ጅማሮዎችን ቢያንስ በአዋጅ ደረጃ መደንገጉ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ለዚህች አነስተኛ ውጤት አሰቃቂ የእርስ በእርስ ዕልቂትን የመሰለ ለትውልድ ክፍተት የዳረገ ውድ ዋጋ መከፈሉ መቼም ቢሆን የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ዛሬ አብዝሃው ሕዝብም አብዮትን በራሱ መተላለቅን የሚያስከትል መዓት አድርጎ ለመውሰድ የተገደደው ከዚህ ካሳለፈው ጥቁር ታሪክ ጠበሳ ሳቢያ ነው፡፡ ግና፣ በእጅጉ ተናፋቂው ዘመነኛው የቀለም አብዮት ቀርቶ በእነ ማርክስ አስተምህሮ የሚበየነውም ቢሆን እንኳ፣ ከሥርዓታዊ ለውጥ አምጪነቱ ባሻገር ጭቆና ላደነዘዘው ማሕበረሰብ ንቃተ-ህሊና ወሳኝ መሆኑ እና በሀገር ጉዳይ ላይ ምን አገባኝ የሚል ሕዝብን ወደ ጠንካራ የፖለቲካ ተሳታፊነት ማድረሱን ፈፅሞ መካድ አይቻልም፡፡ የየካቲቱ አብዮት እንደ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ አገላለፅ በደስታና በተስፋ ተጀምሮ፤ በሰቆቃና በፀፀት ቢደመደምም ከ66-68 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ፈጥሮት የነበረው የአደባባይ ውይይትና የማሕበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ለዚህ ጭብጥ ሁነኛ ማሳያ መሆን ይችላል፡፡
በኢህአዴጓ ኢትዮጵያ የአብዮትን አስፈላጊነት ጠቅሶ አስተያየት መስጠቱ የሥርዓቱ አገልጋዮችን ብቻ ሳይሆን፣ ለውጥ ፈላጊውንም ሲያስበረግገው (አልፎ አልፎም እንደ ጥፋት መልእክተኛ ቆጥሮ እስከማውገዝ ሲያደርሰው) መስተዋሉ የተለመደ ሆኗል፡፡ ይህ ግን ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በምስራቅ አውሮፓም ሆነ በሰሜን አፍሪካ አገራት የተከሰቱት የዘመኑ አብዮቶች መነሻቸው አማራጭ ማጣት እንጂ፤ እብሪት በገፋቸው አሊያም የሥልጣን ጥማት ባክለፈለፋቸው ቀስቃሾች የተካሄዱ አለመሆናቸውን ራሳቸው የንቅናቄው ሰለባዎችም የሚክዱት እንዳልሆነ በግላጭ ይታወቃል፡፡ የሩሲያ አብዮት መሪ ቪላድሚር ኤሊች ሌኒን የትኛውም አገዛዝ እንደቀድሞ በጭፍለቃ መቀጠል አለመቻሉ በአንድ በኩል፤ ተጨቋኞች ለተቃውሞ ማጉረምረማቸው በሌላ በኩል በተመሳሳይ ወቅት መከሰትን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ሲል ይጠራዋል፡፡ በዚህ ንዑስ ርዕስም በኢትዮጵያ ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› መኖሩን በማስረጃ አስደግፌ ለማተት እሞክራለሁ፡፡

‹‹አብዮታዊ ሁኔታ››

በኢትዮጵያ ምድር ሕዝባዊ አብዮት አይቀሬ እንዲሆን ያስገደደው ዋነኛ ምክንያት ሁሉም የለውጥ መንገዶች እንዳያፈናፍኑ ተደርገው በመዘጋታቸው እንጂ፤ ኢህአዴግ እንደሚወነጅለው ዘግናኙን የቀይ እና ነጭ ሽብር ታሪክ የመድገም ፍላጎት የተጠናወተው ፖለቲከኛ አሊያም ተሟጋች ባራገበው የኑፋቄ ቅስቀሳ አለመሆኑ ከማንም የተሰወረ አይመስለኝም፡፡ በርግጥ ይህ የአብዮታዊ ግንባሩ ክስ፣ በሌሎች መሰል ጉዳዮች በተከሰተባቸው ሀገራት እንደታየው የአመፅን ነባራዊ ማህበረ-ፖለቲካዊ መነሻ ከመቀበል ይልቅ፣ በውጭ ኃይሎች ላይ ማሳበብን መምረጥ የተለመደ ከመሆኑ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ለአብነትም በቅርቡ ለእስር የተዳረጉትን ሶስት ጋዜጠኞች እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን ክስ ማየቱ በቂ ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው የምስራቅ-አውሮፓ ሀገራትም ላጋጠማቸው ሕዝባዊ አብዮት፣ በዋናነት አሜሪካንና የባለሀብቷን ጆርጅ ሶሮ ፋውንዴሽን የተባለ ተቋም በመወንጀል ይታወቃሉ፡፡ ይህንን መሰሉ አብዮት ያሰጋው ኢህአዴግም የእነርሱን እርምጃ (ተቋሙን እስከመዝጋት መሄዳቸውን) በመኮረጅ፣ ከጥቂት ዓመት በፊት ካወጣቸው አዋጆች አንዱ መያዶችን አዳክሞ (ከአስር በመቶ የበለጠ የውጭ እርዳታን እንዳይቀበሉ በመከልከል) በቁም የሚገድል እንደሆነ አይዘነጋም፡፡ በጊዜው ግንባሩ ካቀረባቸው መከራከሪያዎች ይልቅ፣ አቶ መለስ ለ‹‹Famine and foreigners in Ethiopia›› ፀሐፊ ፒተር ጊል፤ በምዕራባውያን ሀገራትና ተቋማት ድጋፍ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሰሩትን መያዶች ‹‹የኒዮ ሊበራሊዝም እግረኛ ወታደሮችና ተለዋጭ ተቃዋሚዎች›› ሲል መኮነኑ፣ የአዋጁን መግፍኤ አስረግጦ ይናገራል፡፡ ግና፣ ‹‹ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ…›› እንዲሉ፤ ኢህአዴግ አለቅጥ አግንኖ ሀገር-ምድሩን በደም የሚያጨቀይ ‹‹ጭራቅ›› አስመስሎ ፍርሃት ለማንበር እየሞከረበት ያለው ‹‹የቀለም አብዮት›› (colour revolution) የራሱ ንድፈ-ሃሳብ የሌለው፣ ሠይፍ የማያማዝዝ፣ ፍፁም ሰላማዊ መሆኑ ከቶም ቢሆን ሊጠፋው አይችልም፡፡

የሆነው ሆኖ አገዛዙ ‹መሰል አብዮት በዚህች አገር እንዳይቀሰቀ›ስ በሚል ስጋት እንቅልፍ አጥቶ ሲባንን የሚያድረው እና የለውጥ መንገዶችን በጠቅላላ ለመዝጋት ሌት ተቀን የሚዳክረው፣ የአረቡ ‹‹ፀደይ›› አብዮት የጨቋኞቹን የሰሜን አፍሪካ መሪዎች መንበር በጥቂት ቀናት ውስጥ መገልበጡ የፈጠረበት ድንጋጤ ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ በወቅቱ ነፍሱን ይማረውና መለስ ዜናዊ በአደባባይ ‹‹ህዝቡ ያምፃል ብለን ሳንተኛ አናድርም›› ሲል ለማስተባበል ቢሞክርም፤ በጥቂት ወራት ውስጥ ብቻ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተሟጋቾችን (አክቲቪስቶችን)… በዚሁ ጉዳይ ወንጅሎ እስር ቤት መክተቱ የንግግሩን አራምባ ቆቦነት ያስረገጠ እርምጃ ነበር፡፡ በተጨማሪም የፓርቲው የግል ፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ልሳን እንዲሆን በተገደደው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ብቻ በተለያዩ ሀገራት የተካሄዱ አብዮቶች አሉታዊ ጎን ላይ ያተኮሩ ዘገባዊ (ዶክመንተሪ) ፊልሞች እና ‹‹የሕትመት ዳሰሳ›› በተሰኘ ፕሮግራሙ እየደጋገመ በማቅረብ አታክቶናል፤ ለወደፊቱም ይበልጥ እስኪያንገሸግሸን ድረስ ገና ያታክተናል፡፡ በእነዚህ ፊልሞች እና ዝግጅቶች የ‹‹አረቡ ፀደይ››ንም ሆነ ‹‹የቀለም አብዮትን›› ደም አፋሳሽነት እየተደነቃቀፉ ሊያስፈራሩን ከሞከሩ ዙምቢ ‹‹ተንታኞች›› አንስቶ፤ በስነ-ምግባር ጉድለት እስከተባረሩ ጋዜጠኞች ድረስ ተሳታፊ ቢሆኑም፣ ተጨባጩን የሀገራችንን እውነታ የሚያስረግጥ አንዳች ሊያሳምን የሚችል ፍሬ ያለው ነገር ሲናገሩ አልተደመጡም፤ በስማ በለው የሰሜን አፍሪካውያንን ለውጥ መሻት እና የዩክሬንን ሕዝብ ‹‹ፍሪደም ሃውስ››ን ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ደርበው ከመርገም ያለፈ፡፡ በግልባጩ የአገዛዙን ‹‹ሚሊየነር ገበሬዎችን አፈራሁ››፣ ‹‹የምርጫ ሥርዓት ገነባሁ››፣ ‹‹በተከታታይ 11 በመቶ ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት አስገኘሁ››፣ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦችን መብት እስከ መገንጠል አስከበርኩ››፣ ‹‹ቀለበት መንገድ ሰራሁ››፣ ‹‹አባይን ልገድብ ነው››… ጂኒ ቁልቋል የሚለው ርካሽ ፕሮፓጋንዳ መልሰው መላልሰው በማስተጋባት የለውጥ መንፈሱን ለማጠልሸት የሄዱበት ርቀት መልሶ ራሳቸውን ለትዝብትና ሀፍረት የዳረገ ይመስለኛል፡፡

ያም ተባለ ይህ ሶስተኛው አብዮት አይቀሬ የሚሆንበት ምክንያት በሁለት ተከፍሎ የሚታይ ሲሆን፤ ይኸውም አማራጭ መንገዶች መዘጋት እና ሕዝባዊ ቁጣ ቀስቃሽ ኩነቶች በተመሳሳይ ወቅት መከሰት የሚል ነው፡፡ እነዚህን ሁለት አንጓ ጉዳዮችም በአዲስ መስመር ነጣጥለን፣ ተንትነን እንያቸው፡፡

የመጀመሪያው ‹‹መንገዶች መዘጋት›› ተብሎ የተገለፀው የዜጎችን በምርጫ ፖለቲካ እምነት ማጣት፣ የተቋማት ነፃነት መጨፍለቅ፣ የሕግ-የበላይነት መሻርን ጨምሮ በጥቅሉ በሕገ-መንግስቱ የተደነገገው የሥርዓት መቀየሪያ መንገድ መብት መገርሰስን ይወክላል፡፡ ይህ ኩነትም በዛሬዋ ኢትዮጵያ ለመከሰቱ አብይ ማስረጃ ሆኖ የሚጠቀሰው፣ በቀደሙት አራት ምርጫዎች ገዥው-ፓርቲ በማጭበርበር እና ኃይል በመጠቀም አሸናፊነቱን ማወጁ ነው፡፡

በሁለተኛነት ‹‹ቁጣ ቀስቀሽ ኩነቶች›› በሚል የጠቀስኩት ደግሞ ከሞላ ጎደል በሚከተሉት ችግሮች ይገለጣል፡- ስርዓቱ ከእነአስከፊው አምባ-ገነን ባህሪው ከሁለት አስርታት በላይ በስልጣን መቆየቱ የፈጠረው መሰላቸት፣ ስልታዊ የመብት ጭፍለቃ መረብ መዘርጋት፣ የመናገርና የመደራጀት ዲሞክራሲያዊ መብት በ‹‹ሕግ›› ስም ማፈን፣ የዋጋ ንረትና የስራ አጥ ቁጥር አለቅጥ ማሻቀብ (በተለይም ከትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡት ወጣቶች ስራ-አጥ ለመሆናቸው ተጠያቂው ገዢው ፓርቲ መሆኑ)፣ ይሄ ሁሉ ተደማምሮ ደግሞ በአገሪቱ አስከፊ ድህነት ማስፈኑ፣ የፍትህ እጦት፣ የፕሬስ አፈናው እንደ ‹‹ፍትህ››፣ ‹‹ፍኖተ ነፃነት››፣ ‹‹ልዕልና››፣ ‹‹ሰለፊያ›› ጋዜጦች፤ እንዲሁም ‹‹አዲስ ታይምስ›› እና ‹‹የሙስሊሞች ጉዳይ›› ያሉ መጽሔቶችን በኃይል ወደመዝጋት ከመሻገር አልፎ ተርፎ ማህበራዊ ድረ-ገፆች፣ የአሜሪካ እና የጀርመን ድምፅ የሬዲዮ ስርጭት፣ አልጀዚራ እና ኢሳትን የመሳሰሉ ሚዲያዎችን ‹‹አመፅ ቀስቃሽ›› በሚል ውንጀላ ለማፈን በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የድሀ ሕዝብ ሃብት ማባከኑ፣ የደሞዝ ማሻሻያ አለመደረጉ፣ በተለያዩ ከተሞች የታየው የዜጎች ከርስት መፈናቀል፣ የመሬት ቅርምት፣ እያቆጠቆጠ የነበረው የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት በ2002ቱ ምርጫ በአውራ ፓርቲ መተካቱ፣ የሲቪክና ሙያ ማህበራት ከተፅእኖ ነፃ መሆን አለመቻል፣ የሀገሪቱ ጭቁን ወታደር ኑሮ ከእጅ ወደአፍ መሆን፣ የአርሶ አደሩም ሆነ የከተሜው ሕይወት አለመለወጥ፣ የብሔር ጥያቄ ክሸፈት ከእርስ በእርስ ፍጥጫ ተሻግሮ በተለያዩ ክልሎች የዘውጉ ቋንቋ ተናጋሪ ያልሆኑ ዜጎች መፈናቀል ማስከተሉ፣ የኢኮኖሚ እድገት አለመታየቱ፣ በሰላማዊ መንገድ ፍትሃዊ ጥያቄዎቻቸውን ባቀረቡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ በአርሲ፣ በወሎ፣ በአዲስ አበባና በመሳሰሉት አካባቢዎች በፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመው ሞት እና የጅምላ እስር፣ ማሕበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ እየተሞከረ ያለው ሴራ፣ የፌዴራሊዝሙ አወቃቀር የፈጠረው ችግር፣ ከፖለቲካው መገልል እና መሰል የአገዛዙ ጭካኔ ባሕርያት ስርየታቸው በሕዝባዊ አብዮት ብቻ ይሆን ዘንድ ማስገደዱን ከቶስ ቢሆን ማን ይስተዋል?!

በአናቱም የሁሉም የሥልጣን እርከን ጠቅላይ የነበረው አቶ መለስ ማለፍን ተከትሎ የተፈጠረው የመዋቅር ክፍተት ሕዝባዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ከዕዝ ውጪ ማድረጉ እና ቀድሞ በግንባሩ ውስጥ ተጨፍልቀው የነበሩ ጥያቄዎችም ሆኑ የተለያዩ ቅሬታዎች አቧራቸውን አራግፈው ጠረጴዛው ላይ መቀመጣቸው ገፊ-ምክንያት ተደርገው ይጠቀሳሉ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ የግንባሩ መሪዎች በደፈናው አብዮትን ከሽብር ድርጊት ጋር ቀላቅለው ከማውገዛቸው በተጨማሪ፣ የየካቲቱ አብዮትን ጠልፎ ሥልጣን የተቆናጠጠውን የመንግስቱ ኃይለማርያምን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለዘመን ተጋሪዎቼ በዘጋቢ ፊልም ስም እያሳዩ አንድም ፍርሃት ለመፍጠር መሞከር፤ ሁለትም ‹‹እኛ ነን ከዚህ በላኤ-ሰብ ሥርዓት ነፃ ያወጣንህና ሃምሳ ዓመት ሰጥ-ለጥ ብለህ ተገዛ›፤ ሶስትም የቀለም አብዮትን ጭራና ቀንድ አብቅለውበት ሽብር በመንዛት ላይ ያነጣጠረ ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ ቁማር በመቆመር መጠመዳቸው ከአብዮት ያነሰ አማራጭ እንዳይኖር አድርጓል፡፡ በርግጥ የዴሞክራሲያዊ መብቶች እና የሕግ የበላይነት በተከበረባቸው ሀገራት የቱንም ያህል የጠነከሩ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ቢነሱ፣ ብዙውን ጊዜ ከአብዮት ይልቅ በምርጫ ፖለቲካ ብይን ሲሰጥባቸው የመታየቱ አጋጣሚ መዘንጋት የለበትም፡፡

የሆነው ሆኖ የድህረ-መለሱ ኢህአዴግ የፖለቲካ ማሻሻያ ከማድረግ፤ በመከላከያ ሠራዊቱ፣ በፌደራል ፖሊስ እና በደህንነት ሰራተኞቹ ደፍጣጭነት መተማመንን መርጦ፣ ‹ነገም ዝምታው እንዳረበበ፣ አደባባዩም የፀጥታ ዳዋ እንደወረሰው፣ የእኛም መንበረ-ስልጣን እንደተረጋጋ መሽቶ ይነጋል› በሚል ተምኔታዊ ተስፋ በመወሰዱ፣ ታሪክ ራሷ በተቃራኒው ቆማ የሶስተኛው አብዮት ሰለባ እንዲሆን መበየኗን ለመስበክ ነብይ መሆንን አይጠይቅም (በነገራችን ላይ በሶስተኛው አብዮት ለበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች መወሳሰብና አለመግባባቶች መግፍኤ የሆኑት ‹‹አሻጥራዊ የፖለቲካ ባሕል፣ የብሔር፣ የመሬት ጥያቄ እና መሰል ጭብጦች የማያዳግም ምላሽ እንዲያገኙ ቅድመ-ዝግጅት ካልተደረገ ለአራተኛ አብዮትም መነሾ ሊሆኑ መቻላቸውን ማሳሰቡ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ)

የህዳሴ አብዮት

ከላይ የሰፈረው ሀተታ ሁላችንንም የሚያስማማ ይሆናል በሚል መተማመን በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት (ምናልባትም በቀጣዩ አዲስ ዓመት መጀመሪያ) ሀገሬን በተቀደሰ መንፈስ ለመዋጀት የግድ መቀስቀስ ያለበት ሕዝባዊ ንቅናቄ ‹‹የህዳሴው አብዮት›› የሚል ስያሜ ቢኖረው፣ በግሌ ለቅብሉነቱም ሆነ አንድምታውን በቀላሉ ለማብራራት የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ …ያም ሆነ ይህ በሚቀጥለው ሳምንት ከህዳሴው አብዮት አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመነሻ ሃሳብ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡


Tuesday, May 27, 2014

በትግራይ ክልል አንድ ባለስልጣን በጥይት ተገደለ | Zehabesha Amharic

በትግራይ ክልል አንድ ባለስልጣን በጥይት ተገደለ | Zehabesha Amharic

በማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ረቂቅ የፓትርያርኩና የምልዓተ ጉባኤው ልዩነት ተካሯል፤ ለመሥራት ተቸግሬአለኹ ያሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከፓትርያርኩ ረዳት ሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል


ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከጨለማው ቡድንና ፖለቲከኞች ጋራ የመከሩበትን የራሳቸው ያልኾነ የተልእኮ ሐሳብና አጀንዳ የተቃወሟቸውን የምልዓተ ጉባኤውን አባላት ‹‹በገንዘብ የተገዛችኹ›› እያሉ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና በአማሳኞች መሠረተ ቢስ ክሥና ውንጀላ በመዝለፍ ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍረዋል፡፡አቡነ ማትያስ ለአጥኚ ኮሚቴው የላኩት ባለ24 አናቅጽ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች ሳይቀነሱና ውይይት ሳይደረግባቸው በደንቡ ካልተካተቱና ረቂቁ በሌላ ኮሚቴ ዳግመኛ ካልታየ በሚል አጀንዳውን በራሳቸው አቋም ብቻ ለመቋጨት ያደረጉት ሙከራ፣ በፍጹም አንድነት በቆሙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተቃውሞ ውድቅ በመደረጉ በመተዳደርያ ደንቡ ማሻሻያ ላይ የሚደረገው የምልዓተ ጉባኤው ውይይት ይቀጥላል፡፡ከድንጋጌዎችና ግዴታዎቹ መመሪያ ውስጥ፡- የማኅበሩ ፈቃድ በየዓመቱ እንዲታደስ፤ ማኅበሩ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዳይሰበሰብና ቢሮ እንዳይከፍት፤ የሠራተኞቹ ቅጥርና ምደባ በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲካሔድ፤ አባላቱ በግልም በቡድንም በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሥራ፣ በቀኖናዊ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌና በሰንበት ት/ቤቶች ጉዳይ እንዳይገቡ፤ የማኅበሩ አባላት በግል ለሚሠሩት ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና የሀገርን ሰላም የሚፃረር ድርጊት›› ማኅበሩ ሓላፊነት እንዲወስድ የሚሉት ይገኙበታል፡፡የአጥኚ ኮሚቴው አብላጫ አባላት፣ የፓትርያርኩን የድንጋጌዎችና ግዴታዎች መመሪያ ‹‹ከቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔና የደንብ ማሻሻያ አቅጣጫ ጋራ የማይሔድ›› በሚል ያልተቀበሉት ሲኾን ማኅበሩ በበኩሉ በተለይ በፈቃድ ዕድሳት ረገድ የተነሣው ሐሳብ ‹‹በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ በጸደቀ መተዳደርያ ደንብ የሚመራውን የማኅበሩን አገልግሎት ለማስቆም የሚደረግ አካሔድ ነው፤›› ብሏል፡‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የመሥራት አቅሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም እየሠራ ባለው ሥራ ኹሉ አብያተ ክርስቲያናትን፣ አድባራትንና ገዳማትን በስፋት እየጠቀመ ያለ፣ በምሁራን የታቀፈ ኹለንተናዊ ዝግጅት ያለው ማኅበር ስለኾነና ብዙ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ የሚገኝ በመኾኑ ራሱን የቻለ ድርጅታዊ መዋቅር ሊዘጋጅለት እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡›› /የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጥኚ ኮሚቴውን ባቋቋመበት የግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤው ያሳለፈው ውሳኔ/‹‹ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና እያደገ በመሔድ ላይ ለሚገኘው የማኅበሩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የሚመጥንና ለወደፊቱም ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅም የላቀና የተሻለ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው ራሱን የቻለ መዋቅራዊ አደረጃጀት ሊዘጋጅለትና የማኅበሩን አገልግሎቶችና የወደፊት ኹኔታዎች ያገናዘበ መተዳደርያ ደንብ ሊቀረፅለት ይገባል፡፡›› /የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የምልዓተ ጉባኤ ውሳኔው ለአጥኚ ኮሚቴው የሰጠው የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ አቅጣጫ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሓላፊነታቸው በአርኣያነት የሚጠቀስ ጥረት ባደረጉበት የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ሳቢያ ከፓትርያርኩ ጋራ ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደገቡና አብረው ለመሥራት እንደሚቸገሩ በምልዓተ ጉባኤው መካከል ቆመው የተናገሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ‹‹አባቶቼ፣ አሰናብቱኝ›› ሲሉ ቅዱስ ሲኖዶሱን ጠይቀዋል፤ ምልዓተ ጉባኤው እንደሚነጋገርበት ይጠበቃል፡፡ፓትርያርኩ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መልቀቂያ ያቀረቡበትን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የረዳት ሊቀ ጳጳስ ምደባ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ለመከፋፈል እየተጠቀሙበት እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡

የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ በቅርቡ ባረፉት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ቦታ÷ ምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከት÷ ተዛውረዋል፤ በምትካቸው የአኵስም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትና የመንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት መመደባቸው ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ኢሰብአዊ ወንጀል


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬእ.ኤ.አ ሜይ 2/2014 ቢቢሲ/BBC እንደዘገበው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል የጸጥታ ኃይሎች ከመናገሻ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ላይ ቢያንስ 47 የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ረሽነዋል፡፡ ስብዕናው በውሸት እና በሀሰት ውንጀላ የበከተው ገዥ አካል ይህንን እልቂት እንደተለመደው ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ “ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች በቆሰቆሱት እና በአስተባበሩት አመጽ“ ምክንያት የሚል የሀሰት ፍረጃ በመስጠት በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችንን ቁጥር ለማሳነስ ጥረት አድርጓል፡፡ ይህ በወጣት ተማሪዎች እና ህጻናት ላይ የተፈጸመው የማንአለብኝነት የእብደት አሰቃቂ እልቂት በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘንድ ሰፊ ሽፋን አልተሰጠውም፡፡ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጅማ እና በሌሎች ከተሞች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙት ንጹሀን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ እና ድብደባ ይቁም“ የሚል መግለጫ በማውጣት እኩይ ድርጊቱን አውግዟል፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በኦሮሚያ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ህብረተሰብ አቀፍ ገጠራማ እና ከተማ ቀመስ አካባቢዎችን ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የወሰን ክልል የሚያካትተው እና የኦሮሞ አርሶ አደሮችን እንዲሁም ሌሎች ኗሪዎችን የሚያፈናቅለው የአዲስ አበባ የተቀናጀ መሪ የልማት ዕቅድ ሀሳብ ተዘጋጅቶ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተማሪዎች የተቃውሞ አመጽ ገነፈለ“ ብሏል፡፡ በማስከተልም ሂዩማን ራይትስ ዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙት ተማሪዎች ላይ የገዥው አካል የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ያሉትን የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጠይቋል፡፡በዚህ መረን በለቀቀ ዕኩይ ድርጊት የተሰማኝን ሀዘን በቃላት ለመግለጽ ተስኖኛል ምክንያቱም ልብን ሰብሮ የሚገባው ይህ የአሰቃቂ እልቂት ሀዘን ልሸከመው ከምችለው ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛልና፡፡ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት እና የነገይቱ ኢትዮጵያ ተረካቢ የሆኑት እምቦቀቅላ ተማሪዎች ገና በወጣትነት ለጋ እድሚያቸው ኃላፊነት በማይሰማው መንግስት ነኝ ባይ የወሮበላ ቡድን ስብስብ በጥይት ውርጅብኝ በመጨፍጨፋቸው ታላቅ ሀዘን ተሰምቶኛል፣ እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስሜቴን እየቆጠቆጠኝ ይገኛል፡፡ ተማሪዎቹ የሚሰማቸውን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ህገመንግስታዊ ያልተገደበ መብት ነበራቸው፡፡ ያንን መብት በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው ምክንያት ብቻ የጥይት በረዶ ተርከፍክፎባቸዋል፡፡ እናም ሁላችንም ልናዝንላቸው ይገባል፡፡

የመደብ ወይስ የብሄር ጭቆና?!


እንዲህ ተጠይቋል

“ባለፉ ስርዓታት የነበረ የማሕበረ ፖለቲካ መዋቅር የመደብ የትግል (ጭቆና) መሰረት ያደረገ ነበር ወይስ ብሄር?”

ባለፉ ስርዓታት ጭቆና ነበረ (አሁንም አለ)። በኢትዮጵያ ታሪክ በህዝብ የተመረጠ ህዝብን ለማገለግል የተነሳ መንግስት አልነበረም (የለም)። ስለዚህ ጭቆና አለ። ጭቆናው ምን መሰረት ያደረገ ነው? ብሄር ወይስ መደብ? በኔ እምነት ጭቆናው ከሁለቱም ዉጭ ነው። በኢትዮጵያ የመደብ ጭቆና አልነበረም (የለም)፤ የብሄር ጭቆናም አልነበረም (የለም)። የነበረው (አሁንም ያለው) ጭቆና የኤሊት (Elite) ጭቆና ነው።

እስካሁን ድረስ የመደብ ፖለቲካ የለንም። የመደብ ፖለቲካ ከሌለ የመደብ ጭቆናም የለም። የብሄር ጭቆናም አልነበረም፣ የለም፣ ሊኖርም አይችልም። የመደብ ጭቆና ግን ለወደፊቱ ሊኖር ይችላል።

ያለፉ የኢትዮጵያ ገዥዎች ስልጣን ለመያዝ እንዲሁም በስልጣን ለመቆየት ሲሉ በህዝቦች ላይ በደል አድርሰዋል። በደል ሲያደርሱ ብሄር ወይ መደብ መሰረት አድርገው አይደለም። መደብ ጭራሽኑም አልነበረም፣ የለም። ብሄር ነበር፤ ግን ጭቆናው ብሄር መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስልጣን መሰረት ያደረገ ነበር፣ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ Class Based Or Nation Based Struggle ሳይሆን Elite vs People Based Power Struggle ነው።

ገዥዎች ስልጣን መያዝና እስከ ህልፈታቸው በስልጣን መቆየት ይፈልጋሉ። ለስልጣናቸው ሲሉ ታድያ ይደግፈናል የሚሉትን የሕብረተሰብ ክፍል ይጠቅማሉ፤ ለስልጣን አደጋ ነው በሚሉት ህዝብ ወይ ግለሰብ ደግሞ ጉዳት ያደርሳሉ፤ ስልጣናቸውን ለማጠናከር። ግን በፖለቲካ አንድን የሕብረተሰብ ክፍል መጥቀም አይቻልም፣ ይከብዳልና። ስለዚህ በሕብረተሰቡ ስም የተወሰኑ ግለሰቦች እንዲጠቀሙ ይደረጋል። ግለሰቦቹ ሲጠቀሙ የመጡበትን ሕብረተሰብ እንደተጠቀመ ተድርጎ ይታሰባል: ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሲባል። ህብረተሰቡ በስልጣን ላይ ያለ ስርዓት “የኛነት” ስሜት ያሳድራል። ለዚህም ፕሮፓጋንዳ ይሰራል። ምክንያቱም የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ነው መጥቀም የሚቻለው። ለስልጣን የሚረዳው ግን አብዛኝው ህዝብ ነው። ተጠቃሚ ግለሰቦች ታማኝ የስርዓቱ አገልጋዮች ይሆናሉ። በነሱ ታማኝነት ስርዓቱ ዕድሜው ያራዝማል።

ለስልጣን አደጋ የሚሆን ግለሰብ ወይ ማሕበረሰብ ደግሞ የጥቃት ዒላማ ይሆናል። የስልጣን ዒላማ የሚሆነው በመደቡ አልነበረም (በመደቡ ዒላማ ሊደረግ ይችላል ግን መደብ አልነበረም)። በብሄሩም አልነበረም። በግዜው ካልተመቱ የስልጣን ስጋት ይሆናሉ የተባሉትን ግለሰቦች ወይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይጠቃሉ፤ ብሄራቸው ምን ይሁን ምን። ግን በኢትዮጵያ ታሪክ አንዳንድ ብሄሮች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለምን? በብሄራቸው ምክንያት? አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ አይደሉም፤ ስጋት ይሆናሉ ስለተባሉ ብቻ ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጎዳትም የመጠቀምም መስፈርት ብሄር ወይ መደብ አይደለም፤ የፖለቲካ ታማኝነት (Political Patrimonial-ism) ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልምድ መሰረት የፖለቲካ ታማኝነት የሚገናኘው ከብሄር ጋር ነው። ሙሉ በሙሉ ባይባልም አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች የበለጠ ይተማመናሉ (ምክንያቱም ፖለቲካችን መርህ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስሜት መሰረት ያደረገ ነው። በስሜት መነዳት ደግሞ አለመሰልጠን ነው)። አማርኛ ተናጋሪ ስልጣን ከያዘ አማርኛ የሚናገረውን (ሌላ ቋንቋ ከሚናገር) የበለጠ ያምናል። ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞን የበለጠ ያምናል። ትግርኛ ተናጋሪ ትግራዋይን የበለጠ ያምናል። በዚህ መሰረት አማራኛ ተናጋሪ ስልጣን ሲይዝ አማራዎችን ያስቀድማል (ለስልጣኑ ሲል)። ሌሎች ደግሞ ቅሬታ ያድርባቸዋል። ከዛ ለስርዓቱ ታማኝ አይሆኑም። ታማኝ ካልሆኑ በጠላትነት ይፈረጃሉ። በጠላትነት ሲፈረጁ ተጎጂ ይሆናሉ። እነዚህ የስርዓቱ ተጠቃሚ የሚደረጉ ታማኞች ግለሰቦች ናቸው። ብሄር ሙሉ ተጠቃሚ ማድረግ አይቻልምና። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሙሉ ወይ የሀገር ህዝብ በሙሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ተጠቃሚዎች ታማኝ ግለሰቦች ናቸው። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሊሆኑ ይችላሉ። አንድን ብሄር ሌላኛው ብሄር እየበደለ ነው ይባላል። በዳዮቹ ግን ኤሊቶች (elites) ናቸው። ይህን ነገር ጉዳዩ የብሄር ጭቆና ያስመስለዋል። የብሄር ጭቆና ሊኖር ግን አይችልም።

ስለዚህ ባለፉ ስርዓታት (አሁንም ጭምር) በህዝቦች የሚደርስ በደል አለ። ይህንን በደል ብሄሮች የሚፈጥሩት አይደለም። ያለው በደል በብሄሮች ላይ የተፈፀመ የelites በደል ነው። ኦሮሞዎች የተበደሉ ኦሮሞ ስለሆኑ አልነበረም። ለተመሰረተው ስርዓት ተቀብለው አሜን ብለን እንዲገዙ ለማድረግ የተቃጣ ጥቃት ነው የተፈፀመባቸው። ስለዚህ ጥቃቱ ስልጣን መሰረት ያደረገ ነው። ዒላማው የፖለቲካ ታማኝነትን መሰረት ያደረገ ነው።

አማርኛ ተናጋሪ ንጉሶች ታማኝ ባልሆነ ማንም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ። ለዚህም ነው በሁሉም ህዝቦች (አማራን ጨምሮ) በደል የደረሰው። ትግርኛ ተናጋሪ ገዥዎች ታማኝ ባልሆነ ማንኛውም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ፤ ለስልጣን ሲሉ። ምሳሌ ህወሓት የትግራይ ልጆች በሆኑ እነ ስየ አብርሃ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አስገደ ገብረስላሴና ሌሎች ታጋዮች ላይ መጥፎ እርምጃ የወሰደው እነኚህ ሰዎች ትግርኛ ተናጋሪ ስላልነበሩ አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ ስላልሆኑ እንጂ።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ምድር የደረሰውን እንዲሁም እየደረሰ ያለው ጭቆና ብሄር ወይ መደብ መሰረት ያደረገ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነት መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያውያን ጭቆና የብሄር ወይ የመደብ ሳይሆን የፖለቲካ ነው።

It is so!!!


Monday, May 26, 2014

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ

 May26/2014

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ትላንት ሌሊት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ ።
በአደጋው በተወሰኑ ተማሪዎች ላይም መጠነኛ የአካል ጉዳት ደረሷል ።
የዩኒቨርሰቲው  ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ሽብሩ ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፤ አደጋው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ፤ መንስኤው ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም ።
እሳቱን በአካባቢው ህብረተሰብና በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪ ኤጀንሲ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችላል ያሉት ዶክተር አድማሱ ፤ አደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም ዓይነት ጎዳት አለማድረሱን ተናግረዋል።
በቃጠሎው ወቅት ከህንጻው ለመውጣት በሚያደረጉት ግፊያ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች ከግድግዳ ጋር በመጋጨትና በመውደቅ ቆስለዋል።
ተማሪዎቹም በአካባቢው በሚገኝው አጣጥ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአባቶች ስንብት ከጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ


ከ97ቱ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የ2002ቱ ምርጫ የቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል፤ ከመቼውም በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን ያጠበበው ገዢው ግንባር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን የምረጡኝ ክርክር እንደ 97ቱ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍም ሆነ በአዳራሹ ታዳሚዎችና ታዛቢዎች እንዲገኙ አልፈቀደም፤ በዚህ ክርክር ላይ ኢህአዴግ እንደተለመደው ለመጀመሪያ ጊዜ ካቀረባቸው ጥቂት አፈ-ቀላጤዎቹ መካከል የተመልካችን ትኩረት በመሳብ ጎልማሳው የወራቤ ፍሬ ሬድዋን ሁሴንን የሚተካከል አልነበረም፡፡ ሬድዋን ዕድሉን ካገኘ እንደ ‹‹ጓድ›› መንግስቱ ኃ/ማሪያም ለሰዓታት ሳያቋርጥ ቃላቶችን እንደ መትረየስ አከታትሎ ማንጣጣት ጎልቶ የሚታወቅበት ባህሪው ነው፤ ‹ከሎጂክ› ይልቅ የተዋቡ አረፍተ ነገሮችን መደርደር ይቀናዋል፤ በየመሀሉም የመድረክ ተወካዮችን ‹‹ራዕይና የጠራ ፖሊሲ የሌላቸው››በማለት ይዘልፋል፤ መልሶ ደግሞ ‹ፀረ-ኢትዮጵያዊና ፀረ-ሰላም ናቸው›› ሲል ይኮንናል፡፡ በየሰከንዱ በአስደንጋጭ እና በአደገኛ(Inflammatory) የቃላት ሰይፍ ይመትራቸዋል፡፡ ይህ ‹‹ታጋይ››ነቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በጉምቱ የድርጅቱ ሰዎች ዘንድ ሞገስን አስገኝቶለታል፡፡ ይሁንና ከዕለታት በአንዱ ቀን በዛው አድናቆት በተቸረበት የክርክር መድረክ፣ እንደልማዱ ቃላት ስንጠቃው ላይ ተጠምዶ የነገር ጦሩን ሲያወናጭፍ ድንገት አዳልጦት ታላቅ ‹‹ስህተት›› ፈፀመ፡፡Temesgen Desalegn “Fact” Ethiopian Amharic newspaper editor

የሬድዋን ‹‹ስህተት›› ድርጅቱ-ኢህአዴግ አፄ ምኒሊክን፣ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የሚያብጠለጥልበትን የታሪክ ንባብ ገልብጦ መተንተኑ ነበር፡፡ እንደሚታወቀው ግንባሩ ንጉሡ ዐድዋ ላይ ጣሊያንን ድባቅ ከመቱት በኋላ እግር እግሩን ተከትለው እያሳደዱ መረብን በመሻገር፣ ከምድረ-ኤርትራም ጠራርገው ለማስወጣት አለመሞከራቸው፤ በአካባቢው ተወላጆች ዘንድ ለተፈጠረው የተገንጣይነት ስሜት ገፊ-ምክንያት አድርጎ መስበክ የጀመረው ከበረሃው ዘመን አንስቶ ነው፡፡ ይሁንና ከተማ ውስጥ በአቋራጭ የተቀላቀላቸው አዲሱ ‹‹ካህን›› ሬድዋን ሁሴን ፕሮፓጋንዳው እንደ በረኸኞቹ ‹‹ካህናት›› ከደም-አጥንቱ ጋር በደንብ አልተዋህደምና ምኒሊክ ከአድዋ ድል በኋላ ጦርነቱን እስከ መረብ-ምላሽ ድረስ ልግፋው ብለው ወደፊት ቢቀጥሉ ኖሮ ለአሰቃቂ ሽንፈት ከመዳረጋቸውም በላይ፣ በሺዎች መስዋዕትነት የተገኘውን ድልም አሳልፈው በመስጠት ትርጉም አልባ ያደርጉት እንደነበረ በመሞገት፣ ስለወቅቱ የንጉሡ ውሳኔ ትክክልነት ኢህአዴግን ወክሎ በተገኘበት መድረክ ላይ በይፋ መሰከረ፡፡ ይህ ከድርጅቱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹ቅዱስ መጽሐፍ› የሚጣረስና አለቆቹንም ያስከፋ ‹‹ስህተት››፣ በቀሪዎቹ የክርክር መድረኮች ላይ እንዳይሳተፍ እግድ አስጣለበት፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምተሃታዊ ማጭበርበር ተፈጽሞብናል ያሉ ደንበኞች ቅሬታ አሰሙ


በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከሚተዳደሩ ባንኮች ውስጥ አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ብቻ ከ45 የሚበልጡ ቅርጫፎች እንዳሉት ይታወቃል። ባንኩ ለደነበኞቹ በሚሰጠው የተቀላጠፈ አገልግሎት ከግዜ ወደግዜ አቅሙን እያጎለበት በሃገር ውስጥ ብቻ ከ205 በላይ የሆኑ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን በመክፈት ከ8000 በላይ በሆኑ ሰራተኞች በመታገዝ የአገልግሎት አድማሱን እስከ ጅቡቲ ድረስ ተደራሽ ለማድረግ ቢጠረም በተለያዩ ግዜያት በሚፈራረቁበት አሰታዳሪዎቹ ተቋሙ ቀደም ብሎ የነበረውን ስም እና ዝና ይዞ መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች ባንኩ ከደንበኞቹ ቆጥሮ የተረከበውን ጥሬ ገንዘብ በእምነት መስጠት እንደተሳነው ይናገራሉ ። በተለይ 1000 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቀማጭ ገንዘቦችን ባንኩ ለደንበኞቹ ሲያስረከብ በባንኩ ማህተም የታሸጉ ባለ መቶ ኖት ብሮች ላይ የሁለት መቶ እና ከዛ በላይ ጉድለት የሚታይባቸው መሆኑን የባንኩ ተገልጋይ
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ በመረጃ አስደግፈው ይገልጻሉ።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተለያዩ ጉዳዩች ከፍተኛ አሃዝ ያለው ገንዘብ በየቀኑ ውጪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ከ2 እስከ 5000 በር እንደሚጎድልባቸው የሚናገሩ ምንጮች ከተጠቀሱት የባንኩ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከደንበኞች ኪስ እንደሚመዘበር ይናገራሉ ። ባንኩ በስህተት ትርፍ ገንዘብ እንደማይሰጥ የሚናገሩ ቅሬታ አሰሚዎች ጉድለቱ የተለመደ ነው ከማለት ውጭ በባንኩ ፀያፍ ተግባር አቤት ለሚሉት አካል አጥተው በዚህ መንግስታዊ ተቋም ስም በዜጎች ላይ በጠራራ ፀሃይ እይተፈጸመ ባለው ማጭበርበር ማዘናቸውን ይገልጻሉ ። ሰሞኑንን በቅሎ ቤት አካባቢ የሚገኝ ንግድ ባንክ በአደራ ያስቀመጡትን 25 0000 ብር ወጪ ለማድረግ ወደ ቅርጫፍ መ/ቤት ጎራ እንዳሉ የሚናገሩ አንድ እማወራ የባንኩ ሰራተኞች በማህተም አሽገው ለእማኝነት ሁለት የታሸጉ ርብጣ ብሮችን ቆጥረው እንዳስረከቦቸው ጠቅሰው እቤት ደርሰው በተቀሩት ባለመቶ ኖት ብሮች ላይ ቆጠራ ሲያደርጉ 600 በር ጉድለት ማሳየቱን ገልጸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምተሃታዊ ማጭበርበር እንደተፈጸመባቸው የምስክርነት ቃላቸውን ስጥተዋል።

ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የመሰከሩ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተፈጸመባቸው።


ምንሊክ ሳልሳዊ

የአወሊያ ትምህርት ቤት ኮሌጅና ሀይ ስኩል መምህራኖች ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን ከአመፅ ጋር በማያያዝ ለኮሚቴዎቹ በመሰከሩ መምህራኖች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ ።
FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ]
ከኑሮው ውድነት ጋር ተያይዞ የሚከፈላቸው ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ የሆነባቸው የአወሊያ ትምህርት ቤት መምህራን ግንቦት 4\2006 በአወሊያ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሰባሰብ የአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር እስከዛሬ በሰሩት ስራና ውጤት ፍትሃዊ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው መጠየቀቸው የሚታወስ ነው ፡፡
መምህራኖቹ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ይህን ጥያቄ በሰላማ መንገድ ሲጠይቁ ትምህርት ቤቱ ከቻለጥያቄያቸውን ሰምቶ ምላሽ እንዲሰጣቸው ካልሆነ ደግሞ መጪው የትምህርት ዘመን ከመድረሱ በፊት የተሻለ ነው የሚሉትን አማራጭ ለመወሰን እንዲያመቻቸው ፈጣን ምላሽ መጠየቃቸው እየታወቀ የመንግስት ደህንንቶችና የፀጥታ ሰዎች ግን ሂደቱን የመምህራን አመፅ አስመስለው በማቅረብ አንዳንድ መምህራንን እያሸማቀቁና እያስፈራሩ መሆኑን ምንጮች ለፍትህ ሬዲዮ ገልፀዋል ፡፡ከ 5 እስከ 30 አመታት ባገለገልንበት ተቋም እየተከፈለን ያለው ደመወዝ በቂ ባለመሆኑ አስተዳደሩ ማሻሻያ ያድርግልን የሚል ጥያቄ ከማንሳታቸው በቀር አንድም ማስፈራሪያ እንዳልሰነዘሩ በወቅቱ ተሰብስበው በነበረ ጊዜ የያዙት ቃለ ጉባኤ አስርጂ እንደሆነ የፍትህ ሬዲዮ ምንጮች ጠቁመዋል ፡፡ በቅርቡ በፍርድ ቤት ተገኝተው ለኮሚቴዎቻችን የመከላከያ ምስክር የነበሩ መምህራኖችን ታርጌት ያደረገ የሚመስለው ይህ ማስፈራሪያ ሆን ተብሎ በመንግስት የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ተገልፇል ፡፡ ይህን የመምህራኖች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ አስተዳደሩ ፍትሃዊና ሰላማዊ መሆኑን ቢያምንበትም አንዳንድ የመንግስት ሃላፊዎች ግን የትምህርት ቤቱን አስተዳደር መምህራኖቹ እንደረበሹ አስመሰለው ክስ እንዲያቀርቡ በመጎትጎት በስብሰባው ላይ የተሳተፉትንና ለኮሚቴቻችን መከላከያ ምስክርነት የቀረቡትን መምህራኖች ለማሸማቀቅ እየተሞከረ ለመሆኑ ለአስተዳደሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለፍትህ ሬዲዮ አጋልጠዋል ፡፡

BREAKING NEWS Sebhat Nega wants to return to TPLF Executive Politburo


Removed from the politburo of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) in 2010, Sebhat Nega still holds hopes of once again heading the party he helped to found.
Despite his advancing years and his ousting from the top of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF, mainstay of the coalition ruling Ethiopia) and from EFFORT (the holding company for TPLF companies), Sebhat Nega is keen to go beyond his current post of executive director of the pro-government Ethiopian International Institute for Peace and Development (EIIPD). An old hand in the TPLF who has long been in dispute with Azeb Mesfin, the widow of the late Prime Minister Meles Zenawi, he is still making his presence felt behind the political scenes.

While on a tour of the Tigray Regional State in early May to sound out the local TPLF leaders, managers and activists, Sebhat Nega hit the headlines when he agreed with those present at a meeting denouncing corruption, nepotism and iniquity of the TPLF regime. He then immediately toned down his criticisms, stating “we must join together to solve these problems”.Interviewed about the TPLF’s record on the German radio station Deutsche Welle in the Amharic language a few days ago, Sebhat Nega defended the party’s policies over the 23 years it has been in power since 1991. He justified sidelining the pan-Ethiopian organisations in the Transitional Conference of the time. Nevertheless, he then stated he was prepared to launch a campaign himself to reconcile with these political groups.

የመጨረሻዉ ካርድ



ኢትዮጵያ ዉስጥ ማንም ኃይል በምርጫ ሥልጣን ያዝኩ ብሎ አፉን ሞልቶ ለመናገር ኦሮሚያና አማራ ክልል ዉስጥ ምርጫዉን ጉልህ በሆነ ብልጫ ማሸነፍ አለበት፤ ወይም አማራና ኦሮሚያ ዉስጥ ተሸንፎ ፓርላማ ዉስጥ አብዛኛዉን ወንበር ተቆጣጥሮ መንግስት መመስረት አይቻልም። ወያኔ ዛሬ ያንን የእንቅልፋሞች ፓርላማዉ ተቆጣጥሮ መንግስት ነኝ ብሎ የሚፏልለዉ ሁለቱን የአገራችንን ግዙፍ ብሄረሰቦች ለያይቶና አንዱ ሌላዉን በጥርጣሬ አይን እንዲመለከት አድርጎ ነዉ እንጂ ወያኔ በየቀኑ የሚያስራቸዉ፤ የሚደበድባቸዉ፤የሚያሳድዳቸዉና የሚገድላቸዉ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች በፍላጎታቸዉ መርጠዉታማ አይደለም። ወያኔ ዛሬ ከሚታይበት የፖለቲካ ኪሳራና ህዝባዊ መተፋት አንጻር እንደቀድሞዉ ኦሮሞንና አማራን በመከፋፈልና በመለያየት ብቻ ስልጣን ላይ መቆየት እንደማይችል ስለተረዳ እነዚህ ሁለት የአገራችን ግዙፍ ብሄረሰቦች እርስ በርሳቸዉ ተጋጭተዉ እንዲተላለቁ የሚቻለዉን ሁሉ እያደረገ ነዉ። ወይም ቀለል ባለ አማርኛ ወያኔ ከጫካ ይዞት የመጣዉን የመጨረሻ ካርድ መዝዞ አገራችንን በቀላሉ ወደ ማትወጣዉ የዘርና የጎሳ ግጭት ዉስጥ ለመክተት ቁጭ ብድግ እያለ ነዉ።ወያኔ የመሬት ባለቤትነትን ጉዳይ ህገ መንግስቱ ዉስጥ ሸንቁሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የግል ንብረት የሚሆነዉ በእኔ መቃብር ላይ ነዉ ያለዉ አለምክንያት አይደለም። ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የህዝብና የመንግስት ነዉ ይበል እንጂ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ትክክለኛዉ የመሬት ባለቤት ህዝብም መንግስትም ሳይሆን ህወሀት ወይም ወያኔ ነዉ። ይህንን ወያኔ የሚባል የዘረኞች ስብስብ ባስቸኳይ ጠራርገን በገዛ አፉ እንደተናገረዉ በወያኔ መቃብር ላይ የአገራችንን የተዛባና ጎታች የመሬት ይዞታ በፍጥነት ካልቀየርን ሁላችንም የወያኔ ገባር መሆናችን የማይቀር ነዉ:። ዛሬ ወደድንም ጠላን አገራችን ዉስጥ ልክ እንደፊዉዳሉ ዘመን መሬት እንደ ስጦታ ለዘመድና ለቤተዘመድ የሚሰጥ ደሃዉንና ሀብታሙን የሚለይ የመጨቆኛ መሳሪያ ነዉ። መሬት መብት መርገጫ ነዉ፤ መሬት አፍ ማስዘግያ ነዉ፤ መሬት ማማለያ መሳሪያ ነዉ፤ መሬት የማይወዱትናን የኛ አይደለም የሚሉትን ማግለያና መድረሻ ማሳጫ ነዉ። ባጠቃላይ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የወያኔ ቂም በቀል መወጫ አይነተኛ መሳሪያ ነዉ። ወያኔ እኔን አይደግፈኝም ከሚለዉ ከማንም ሰዉ መሬት ቀምቶ ላሰኘዉ ሰዉ መስጠት ይችላል። ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ብዙ መጓዝ አያስፈልግም፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ አዳዲሶቹን የከተማ ቦታና ሰፋፊ የእርሻ መሬት ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ መመልከቱ ይበቃል።በቅርቡ አምቦ ዉስጥ በግፍ የተጨፈጨፉት የኦሮሞ ተማሪዎች እንደዚህ አይነቱን አግላይ የሆነ የወያኔ የመሬት ፖሊሲ የተቃወሙ ተማሪዎች ናቸዉ። ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በልማት ስም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የኦሮሞ ገበሬዎችን እያፈናቀለ መሬቱን ለራሱ ወገኖች መስጠቱን በመቃወም አምቦ፤ ጅማ፤ ወለጋ፤ አዳማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ወያኔንና ደጋፊዎቹን ክፉኛ ያስደነገጠ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ያደረጉትና ምትክ የሌለዉን ህይወታቸዉን የገበሩት ይህ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ የወያኔ የመሬት ፖሊሲ ስለገባቸዉ ነዉ።

ሒዩማን ራይትስ ዎች በዛሬው ዕለት ያወጣው ሪፖርት ለሥራ ፍለጋ ወደ አረብ ሀገራት በሚሄዱ የኢትዮጵያና የአካባቢዋ ሀገራት ዜጎች ላይ በየመን የሚፈጸመውን ዘግናኝ ማሰቃየትና ግድያ ይዘረዝራል፡፡



ባለ 82 ገጹ ሪፖርት በብዛት ከኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት በየመን አቋርጠው የሚሄዱ ዜጎች ላይ በማሰቃያ ካምፖች የሚደርስባቸውን አሰቃቂ ድብደባና ግድያ ቁልጥ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በጀልባ የመን የሚገቡትን እየያዙ በካምፖቹ ውስጥ የሚያጉሩት የወንጀለኛ ቡድኖች ስደተኞቹን በማሰቃየትና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ይህን ያህል ብር ካላመጣችሁ እንገድላቸዋለን በሚል ማስፈራሪያ ብር እንደሚቀበሏቸው ይዘረዝራል ሪፖርቱ፡፡

በዚህ መልኩ ከአንድ ተያዥ ከ200 እስከ 1 300 ዶላር ድረስ ወንጀለኞቹ እንደሚቀበሉ ተገልጿል፡፡ አሰቃቂ ድብደባ፣ ጆሮ ማቃጠል፣ ጥፍር መንቀል፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች እጅግ ሰቅጣጭ ማሰቃያዎች እንደሚፈጸሙ የሚጠቅሰው ሪፖርቱ የወንጀለኞቹ ቡድን ከሀገሪቱ ፖሊስና የጸጥታ ኃይል ጋር ያለውን መመሳጠርም ይጠቅሳል፡፡

ሒዩማን ራይትስ ዎች በዛሬው ዕለት ያወጣው ሪፖርት ለሥራ ፍለጋ ወደ አረብ ሀገራት በሚሄዱ የኢትዮጵያና የአካባቢዋ ሀገራት ዜጎች ላይ በየመን የሚፈጸመውን ዘግናኝ ማሰቃየትና ግድያ ይዘረዝራል፡፡ ባለ 82 ገጹ ሪፖርት በብዛት ከኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት በየመን አቋርጠው የሚሄዱ ዜጎች ላይ በማሰቃያ ካምፖች የሚደርስባቸውን አሰቃቂ ድብደባና ግድያ ቁልጥ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በጀልባ የመን የሚገቡትን እየያዙ በካምፖቹ ውስጥ የሚያጉሩት የወንጀለኛ ቡድኖች ስደተኞቹን በማሰቃየትና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ይህን ያህል ብር ካላመጣችሁ እንገድላቸዋለን በሚል ማስፈራሪያ ብር እንደሚቀበሏቸው ይዘረዝራል ሪፖርቱ፡፡

በዚህ መልኩ ከአንድ ተያዥ ከ200 እስከ 1 300 ዶላር ድረስ ወንጀለኞቹ እንደሚቀበሉ ተገልጿል፡፡ አሰቃቂ ድብደባ፣ ጆሮ ማቃጠል፣ ጥፍር መንቀል፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች እጅግ ሰቅጣጭ ማሰቃያዎች እንደሚፈጸሙ የሚጠቅሰው ሪፖርቱ የወንጀለኞቹ ቡድን ከሀገሪቱ ፖሊስና የጸጥታ ኃይል ጋር ያለውን መመሳጠርም ይጠቅሳል፡፡


Sunday, May 25, 2014

ከአያት መገናኛ የተነጠፈው የባቡር ሐዲድ እየተቀየረ ነው


በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር መስመር ዝርጋታ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በሚገኘው የአያት መገናኛ መስመር ላይ የተነጠፈው ሐዲድ፣ ከመሥፈርቱ ውጪ በመሆኑ ምክንያት በሌላ ሐዲድ በመቀየር ላይ ነው፡፡

ከሳምንት በፊት የተጀመረው ቀደም ሲል የተዘረጋውን ሐዲድ የመቀየር ሥራ በአሁኑ ወቅት ከአያት ወደ ሲኤምሲ አካባቢ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የሆነውን ቻይና ሬልዌይ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ የሆነውን ስዌድሮድ የተባለ የስዊድን ኩባንያ ሪፖርተር ለማነጋገር ቢሞክርም፣ በኮንትራት ስምምነቱ መሠረት ለሚዲያ መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የመጀመሪያውን ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ ሲጀምር፣ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ በተቀመጡት መሥፈርቶች መሠረት እንዲሠራ ተነግሮት ነበር ብለዋል::

ፖሊስ አቶ አስራት አብርሃን አስሮ “ያሉበትን አላውቅም” አለ


የራት ፓርቲዎች መድረክ የሆነው መድረክ ትናንት በአዲስ አበባ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብለው የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ከተማ በፖሊስ መታሰራቸውን የሰሙት የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሐብታይ ገብረ ሩፋኤልናበቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለው ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ እስረኞቹን ሊጠይቁ በሄዱበት በወረዳው ከታሰሩ በኋላፖሊስ አቶ ሐብታይን ሲለቅ አቶ አስራትን በወረዳው አሳድሯቸው ነበር፡፡

ዛሬ ማለዳ አቶ አስራትንና የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ ወደ ቡራዩ ያመሩት የአቶ አስራት ባለቤትና የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ አስራት በፖሊስ ጣብያው አለመታሰራቸው ተነግሯቸዋል፡፡አቶ ሐብታይ በስፍራው በመገኘት
‹‹አስራት ከእኔ ጋር ታስሮ ነበር››ቢሉም የኦሮሚያ ፖሊስ ‹‹የምትሉትን ሰው እኔ አላሰርኩትም››የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በቡራዩ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጣብያዎች በመኖራቸው አስራትን ፍለጋ ወደ ፖሊስ ጣብያዎቹ ያመሩት የአንድነት አመራሮች ተመሳሳይ ምላሽተሰጥቷቸዋል፡፡አብርሃ ደስታ በበኩሉ የአቶ አስራትን መታሰር በማስመልከት የሚከተለውን በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል::

ፖለቲከኛ አስራት አብርሃም በደህንነት ሰዎች ከቡራዩ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ ተወሰደ። ምንም ወንጀል ሳይሰራ በቡራዩ ከተማ ለሰለማዊ ሰልፍ ሲቀሰቅሱ የታሰሩ የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ በመሄዱ ምክንያት ታፍኖ ከተወሰደ የሕገወጥ ዓማፂ ቡድን አባል ቢሆን ኑሮስ ምን ያደርጉት ነበር? ደሞ ሰለማዊ ሰዎችን እያፈኑ ከደርግ እንሻላለን ይሉናል! ደርግ ኮ እያፈነ የገደለን ሕገወጥ ዓማፂ ቡድን (ህወሓት) ስለነበረ ነው። በደርግ ግዜ ህወሓት ዓማፂ ሕገወጥ ቡድን ነበር። የህወሓት አባል የሆነ ወይ ህወሓትን የተባበረ ሁሉ እርምጃ ሲወሰድበት ደርግን እንቃወመው ነበር። አሁን ደግሞ ሰለማዊ ሕጋዊ ታጋዮችን እየታፈኑ የሚወሰዱበት ግዜ ላይ ደረስን! አሁን እንደ ህወሓት ያለ ሕገወጥ ድርጅት (ዓማፂ ቡድን) ቢኖር ኑሮስ ምን ያደርጉን ነበር? ወይ ግንቦት 20!

በጣሊያን ራሳቸውን እንዳጠፉ የተነገረላቸው ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት አሟሟት መንስኤ በውል አልታወቀም


ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጭ ከጧቱ 1 ሰአት ተኩል ላይ ወደ ቢሮአቸው በመግባት ራሳቸውን ከ2ኛ ፎቅ ወርውረው የገደሉት የ62 አመቱ ዲፕሎማት አቶ ፍሰሃ ተስፉ ስለ አሟሟታቸው መንስኤ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።

ክሮናካ ዲ ሮማ የተባለው የጣሊያን ጋዜጣ ዛሬ ይዞት በወጣው ሰፊ ዘገባ ዲፕሎማቱ ከመሞታቸው ከሁለት ቀናት በፊት ከስራ ተነስተው ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ተነግሮዋቸው እንደነበር አንዳንድ ጓደኞቻቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ግን ዲፕሎማቱ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ስለመታዘዙ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ጋዜጣው እንደዘገበው ዲፐሎማቱ  ራሱን ያጥፋ ወይም ሌላ ሰው ይግደለው እንደማይታወቅ ገልጾ፣ ራሱን ካጠፋ ግን አንድ መልእክት ለማስተላለፍ አስቦ ያደረገው ሊሆን እንደሚችል የፖሊስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

በዲፕሎማቱ ቢሮ ውስጥ ምንም  አይነት ማስታወሻ አለመገኘቱን፣ የተዘበራረቀ ነገር አለመኖሩንም የገለጸው ጋዜጣው፣ የረጅም ጊዜ ዝግጅት የተደረገበት ነበር ብሎ ለመናገር እንደማይቻልም አትቷል።

ፖሊስ ኢምባሲውን በመዝጋት ካለፉት 2 ቀናት ጀምሮ ምርመራ በሰራተኞች ላይ እያደረገ ይገኛል።

ዲፕሎማቱን ያገኙት የኢምባሲው ሰራተኞች ሲሆኑ ከሞተ ከአንድ ሰአት በሁዋላ አምቡላንስ በቦታው ቢደርስም  የዲፕሎማቱን ህይወት ለማትረፍ እንዳልተቻለ ታውቋል።

አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ ራሱን አጥፍቷል ብለው እንደማያምኑ እየተናገሩ ነው።

አቶ ፍስሃ ወደ ኢጣሊያ ከመዛወራቸው በፊት በአውሮፓ ህብረት ዴስክ ኦፊሰር ሆነው ከሰሩ በሁዋላ፣ የአለማቀፍ ተቋማት ጊዜያዊ ዳይሬክተር እንዲሁም የዲያስፖራ ክፍል ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ሰርተዋል።

አቶ ፍስሃ የህወሃት አባል መሆናቸውን አንዳንድ ወገኖች ይገልጻሉ።


በኮልፌ ቤቱ የፈረሰበት አባወራ በጅብ ሲበላ አንዲት ወላድ በድንጋጤ ህይወቷ አለፈ


‹‹ቪዛ ይሰጠንና ወደ ሱማሌያ ቢሆንም እንሂድ›› ቤታቸው የፈረሰባቸው

በኮልፌ ቀራኒዮ አለም ባንክ አካባቢ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በማድረግ ቤቶችን ሰርታችኋል የተባሉ ዜጎች ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በሀይል ፈርሶ ንብረታቸው መወረሱን አመለከቱ፡፡ ከ15.000 የሚልቁ ነዋሪዎች በሚገኙበት አለም ባንክ አካባቢ ሰዎቹ አነስተኛ መጠለያ ያረፉባቸውን ቤቶች ከገበሬዎች ላይ በመግዛት መኖር ከጀመሩ አመታት መቆጠሩን ያስረዳሉ፡፡ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ልከውና ወደ ስራ በተሰማሩበት ቅጽበት ከጸጥታ ሰራተኞች ጋር አካባቢውን የወረሩት አፍራሽ ግብረ ሃይሎች መኖሪያ ቤቶቹን ማፍረሳቸውን በሀዘን ተውጠው ገልጸዋል፡፡ ቤቶቹ በድንገት መፍረሳቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊሶች ክፉኛ መደብደባቸውንና መወሰዳቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል፡፡ቤቷ ሲፈርስ የደነገጠች እመጫት ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ ቤቱ በመፍረሱ መሄጃ ያጣ አባወራ ላስቲክ ዘርግቶ በተኛበት ጅብ ጎትቶት ወስዶት በልቶታል፡፡በጅብ የተበላው አባወራ ስርዓተ ቀብርም ዛሬ መፈጸሙ ታውቋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ ለጎዳና እንደተዳረጉ የሚናገሩ ሰዎች‹‹ኢትዮጵያዊነታችን ተሰርዟል፣ቪዛ ይሰጠንና ሌላው ቢቀር ወደ ሶማሊያ እንድንሄድ ይደረግ ›› ብለዋል፡፡


የአሜሪካ የሸፍጥ ዲፕሎማሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና”



የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና ነውን”?

የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ የሆኑት ጆን ኬሪ ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ፕሬዚዳንት ባሽር አላሳድን “አሸባሪ” ወንጀለኛ ናቸው ብለው ከፈረጁ በኋላ የአላሳድ የቀጣዩ ዓመት የምርጫ ዕቅድም “አስቂኝ የመድረክ ትወና” ነው ብለው ተችተው ነበር፡፡ ኬሪ በመቀጠልም እንዲህ በማለት ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “አሳድ ከአሸባሪ ኃይሎች ጋር ህብረትን ፈጥረዋል፣ አሸባሪዎችንም እያቀረቡ እና እየረዱ ነው፣ እናም በእራሳቸው ህዝብ ላይ አሸባሪነትን በመፈጸም ዕኩይ ተግባራት ላይ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡“ እንዲሁም ኬሪ የሚከተለውን ነገር አጽንኦ በመስጠት ተናግረዋል፣ “የአሳድ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዕቅዶች ለታዕይታ የተዘጋጁ አስቂኝ የመድረክ ትወናዎች ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ለመተግበር የሚደረጉ ምርጫዎችም በህዝብ ላይ የሚካሄዱ ዘለፋዎች ናቸው፣ እንደዚህ ዓይነቶቹ ዕኩይ የምርጫ ዕቅዶች በሶሪያ እና በዓለም ህዝቦች ዴሞክራሲ ላይ የሚቃጡ ሸፍጦች ናቸው፣“ ብለው ነበር፡፡

አሳድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሶሪያን ህዝብ አሳር ፍዳውን በማሳየት ላይ የሚገኙ እና በዘመኑ የሰውን ልጅ ከሚያሰቃዩ አምስት የመጀመሪያዎቹ ወሮበላ ወንጀለኞች ምድብ ውስጥ እንደሚካተቱ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2007 በተደረገው ምርጫ ባሽር 97.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለሰባት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ በዚያን ጊዜ የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት ማኮርማክ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “በሶሪያ ያለው ገዥ አካል ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንደልብ በህዝቡ ውስጥ ተንቀሳቅሰው ሀሳባቸውን በመግለጽ መመረጥ እንዳይችሉ ለማድረግ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ ባለው ማስፈራራት እና በሰላማዊ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ላይ የሚያራምዱት ግፍ የተሞላበት ጭቆና ላይ የቀረበው ዘገባ ዩናይትድ ስቴትስን ያሳስባታል፡፡ የሶሪያ ህዝብ ተማዕኒነት ያለው ግልጽ እና በህዝቡ ሙሉ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ድባብን በመፍጠር ፍትሀዊ ምርጫ የማድረግ እና የሚወክሉትን ዕጩዎች መምረጥ እንዳይችል ባሽር አላሳድ መብቱን ቀምተውታል“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ ስለአሳድ “አስቂኝ የምርጫዎች ትወና መድረክ” ማውሳት አዲስ ነገር አይደለም፡፡

እ.ኤ.አ ማርች 2011 የቀድሞ የየአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሂላሪ ክሊንተን ደም ለተጠሙት ባሽር አላሳድ (በሺዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ ሰላማዊ ህዝቦችን ካለፈው ኦክቶበር ጀምሮ ቢያንስ 14 ጊዜ በኬሚካላዊ መሳሪያ ለጨፈጨፉት) መልካም ስብዕና ጥብቅና ቆመው ተስተውለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ለየት ያለ መሪ አለ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ወደ ሶሪያ በመሄድ ጉብኝት አድርገው የተመለሱት በርካታ የሁለቱም ፓርቲዎች (ዴሞክራቶች እና ሬፐብሊካኖች) የኮንግረስ አባላት አላሳድ የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ በመሆናቸው ላይ እምነት እንዳላቸው ገልጸው ነበር “ ብለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ ጊዜ ተቀይሮ ከሶስት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አሳድ “የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ” መሆናቸው ቀርቶ ወደለየለት “አሸባሪነት” እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተዋናይነት ተቀይረው ተገኙ፡፡ እንደ ሂላሪ አባባል የት ይደርስ የተባለ ወይፈን አጎንብሶ ሲጠባ ተገኘ መሆኑ ነውን?

በአውሮፕላን ጎማ ስር ተደብቆ 5 ሰአት በአየር ላይ የተጓዘው ተአምረኛ ወጣት እናት ያለችው ኢትዮጵያ ነው


ከአድማስ ራድዮ የተገኘ

ባለፈው ሰሞን ከካሊፎርኒያ ተነስቶ ሃዋይ ድረስ በአውሮፕላን ጎማ በመንጠላጠል የተጓዘው ወጣት ህይወት መትረፍ ተአምር መሰኘቱን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ የ 16 ዓመት ወጣት ሶማልያዊ መሆኑ ሰሞኑን ሲዘገብ፣ እናቱ ደግሞ ያለችው ኢትዮጵያ መሆኑ አብሮ ተነስቷል።
ሶማሌያዊዋ እናት ምርጊቱ ከጭቃ በተሰራ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ተቀምጣለች። ግድግዳው ከመሳሳቱ የተነሳ ነፋስ እንዳያስገባ በአሮጌ አንሶላ ተሸፍኗል። ያለችው ሸደር በተሰኘ የስደተኞች መጠለያ ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። እንግዲህ የካሊፎርኒያው የ 16 ዓመት ወጣት ሶማሌያዊ አውሮፕላን ላይ የተንጠለጠለው እዚህች ስደተኛ እናቱ ጋር ኢትዮጵያ ለመምጣት በመፈለጉ ነበር።

ዩባ መሃመድ የተባለችው ይህችው እናት፣ እሷን ናፍቆ አውሮፕላን ላይ ተንጠለጠለ የተባለው ይህን ልጇን ላለፉት 8 ዓመታት አላየችውም። ጸጉሯን የሸፈነችበትን ነጭና ጥቁር ሂጃብ እያሻሸች፣ ያህያ አብዲ ስለተባለው ይኸው ወጣት ልጇ ስትናገር በእምባ ጭምር ነው። ለ 5 ሰአት ተኩል በአውሮፕላን ጎማ ተንጠልጥሎ ከአገር አገር ሄደ መባልን ስትሰማ እንደተንቀጠቀጠች ትናገራለች።

ወጣቱ ያህያ አብዲ ካሊፎርኒያ ሊያሳድጉት በወሰዱት ቤተሰቦች ዘንድ ደስተኛ አልነበረም። ደስተኛ ያልሆነው በነሱ አያያዝ ሳይሆን፣ እናቱን እጅግ በመናፈቁ ነበር። እናም ናፍቆቱ ሲብስበት ባለፈው ኤፕሪል 20 ቀን ፣ ከቤቱ በመውጣት ሳንሆዜ ከተማ ባለው አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አጥር ጥሶ ገባ። እናም በልጅነት ሃሳቡ ፣ ወደ እናቱ ሊወስደው የሚችለው አውሮፕላን ነውና ፣ ያገኘው አውሮፕላን ጎማ ላይ ተንጠላጠለ። አውሮፕላኑ ደግሞ እንዳጋጣሚ ወደ ሃዋይ የሚሄድ ነበረ።

Saturday, May 24, 2014

እግዚአብሄር የኢትዮጵያውያንን ጸሎት ለምን አልሰማም አለ? (ኪሩቤል በቀለ)

እንደምታውቁት እምነት አልባ የሆነውና በዲያብሎስ ሓይል ተደግፎ ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ያለው ሕወሃት በዚህ እኩይ ተግባሩ 23ተኛ ዓመቱን እያገባደደ ነው:: ሕወሃትን በመሰለ አረመኔ መዳፍ ሥር የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረግጦ መከራውን ሲገፋ አምላክ ለምን ዝም አለ?

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና ምእመናን ከሃያ ዓመት በላይ  አምላካችን ኢትዮጵያን እንዲታደጋት በጸሎት ተማጽነናል:: ግን እግዚሃብሔር አልሰማንም:: ለምን?

ለቡዙዎች ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ነው:: አንዳንዶቹ እግዚአብሄር ስለመኖሩም ሳይጠራጠሩ አይቀሩም:: ጥቂቶች ደግሞ እግዚአብሄር ፊቱን አዙሮብናል ይላሉ:: ምክንያቱን ግን ማወቅ ተስኖአቸዋል:: እግዚአብሔር ለምን ጸሎታችንን አይሰማም የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ዘንድ የጊዜአችን አንገብጋቢ ርዕስ ነው::


መልሱ ከባድ ይመስላል:: ግን የእግዚአብሄርን ቃል ላነበበና የህይወቱ መመሪያ ላደረገ ክርስቲያን መልሱ ቀላል ነው:: በኢሳይያስ 58: 1-9 የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ በቂ ነው:: አምላክ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር ነው::

 ድምፅ :: እንደመለከት ድምጻችሁን አርጋችሁ እንደአመጹብኝ :: ለያዕቆብም ዝርያዎች ስለሃጢአታቸው :: እኔን የእኔን የአምላካቸውን መንገድ  የሚሹ ሀቀኛውን መንገድ  ትዕዛዝ ያከበሩ ለማስመሰል ሽር ፍትህን ከእኔ :: ወደ እኔም ለመቅረብ የሚፈልጉ ጾመናል ግን ጾማችንን አላየህም ራሳችንንም ዝቅ አርገናል ግን አምላክ  የፈለጋችሁትን እርስ በርሳችሁም :: :: እንደዚህ ጸሎታችን ይሰማል ብላችሁ እንደዚህ ዓይነቱን አንገታችሁን ደፍታችሁ እየዋሻችሁና ያሻችሁን እያረጋችሁ ነው ? እንዲህ ዓይነት ጾም ነው በጌታ ፊት ተቀባይነት  የምመርጠው ጾም የክፋትን ሰንሰለት የሚበጥስና የጭቆናን ቀንበር ? እኔ የምመርጠው ጾም የተራበውን የሚያበላ ማደሪያ የሌለውን ቤት የተራቆተውንም የሚያለብስ  እነዚህን ብትፈጽሙ ግን  አሳያችኋለሁምህረቴም በቶሎ ይደርስ እኔ የምመርጠውን ጾም ብታደርጉ ሃቅንና ፍትህን የናንተ ደጀን ሆኖ ከኋላ ከእዚህ በኋላ እግዚአብሄርን እርዳን ብላችሁ ብትማጸኑት አለሁ :: ጸሎታችሁንም ::“እግዚአብሄር ጸሎታችንን ለምን እንድማይሰማ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው በቂ መልስ ነው::

ይህ አሳዛኝ ሁኔታ በእስራኤላውያን ላይም ተከስቷል:: ናቡከደነጾር የሚባለው የባቢሎን ንጉሥ እስራኤልን ወርሮ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ማካሄዱ ሳያንሰው በእሱ ስም እንዲያመልኩ አስገድዷቸው ነበር:: ለጊዜውም ቢሆን አምላክ ዝም ብሎ ተመልክቶ ነበር::በኋላ ግን እግዚአብሄር ናቡከደነጾርን ሕሊናውን እንዲስት አርጎ እንደ አውሬ በዱር ወድቆ ሳር እንዲበላ አደረገው:: አምላክ የእስራኤላውያንን ምልጃና ጸሎት ተቀብሎ እንባቸውን አበሰ:: ይህም የሆነው እስራኤላውያን ወደ ልባቸው ተመልሰው አምላካቸውን በቅንነት ማምለክ ሲጀምሩ ነው::

ልባችን ንጹህ እስከአልሆነ ድረስና ወደ ቤተክርስቲያን እየተመላለስን ብቻ ወይም እንደአብዛኞቹ ቀሳውስትና መነኮሳት አምላክን እናገልግላለን እያልን በማስመሰል በእግዚአብሄር ቃል የምንነግድ ከሆነ እግዚሃብሄር በፍጹም ጸሎታችንን አይሰማም:: በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራ ምን እንደሚካሄድ ተመልከቱ :: አንዱ አንዱን ሲያማ፤ይባስ ብሎ ዓለም ፍርድ ቤት ሲከስ፤ ሲያወግዝ ፤በቤተክርስቲያን ገንዘብ አዲስ አበባ ውስጥ ቤት ሲሰራ፤ዲያቆን ሲደበድብ፤ ከቤተ ክህነት ዲያቆንና ቄስ ሲያባርር  ነው የምንመለከተው::

በፍትወተ ሥጋና ከልክ ባለፈ ፍቅረ ንዋይ ተቃጥለን አምላክን ወደ ጎን ትተነዋል:: እግዚአብሄርን መፍራት ረስተናል:: ግብረ ሰዶም በጠራራ ፀሃይ እንደ ሰደድ እሳት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲስፋፋ ዝም ብለን እንመለከታለን:: ቤተሰባችን፤ ቤተክርስቲያናችንና አገራችን በማያቋርጥ ሁኔታ ላለፉት 40 ዓመታት እየታመሱ  ነው::በረብሻና በእርስ በርስ ጦርነት ያልተጠመደ ቤተሰብ ወይም ቤተክርስቲያን ወይም የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር ከቶ አይገኝም::ለገንዘብና ለሥልጣን የሚደረገው አሳፋሪ ግብግብ ሳያንስ፤ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሰው ሚስት ሲዳፈሩ የተያዙ መነኮሳት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::

በቅርቡ በኦክላንድ ካሊፎርኒያ ውስጥ የተከሰተው አጸያፊና ዘግናኝ ድርጊት በቂ ማስረጃ ነው:: አንድ መነኩሴ የሰው ሚስት ሲያባልግ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ተባረረ:: የሚገርመው ከዚህ ተግባሩ በፊት በዚሁ መነኩሴ መሪነት ቤተክርስቲያኑንን በጥብጦ ለሁለት ክፍሎ ነው የራሱን ቤተክርስቲያን የክፈተው:: በጣም አሳዛኝ የሆነው ነገር ደግሞ ከተባረረ በኋላ የተፈጸመው ነገር ነው:: መነኩሴው ሥራ ፈት ሁኖ ግን ለጥቂት ጊዜ ታክሲ ሲነዳ ከከረመ በኋላ ኢትዮጵያ ይገባል:: ለትንሽ ጊዜ ድምጹ ከጠፋ በኋላ ድንገት አሜሪካ ከተፍ ይላል:: ምነው ሲባል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሲኖዶስ ሹመት ሰጥቶ ነው የሕወሃት ደጋፊ ቤተክርስቲያኖችን እንዲያገለግል ወደ አሜሪካ እንደገና የላከው ተባለና ቁጭ:: እንዲህ ዓይነት የድፍረት ሃጢያት ውስጥ ነው ቤተክርስቲያንም ምዕመናንም የምንመላለሰው! እንዴት ብሎ ነው አምላክ ጸሎታችንን የሚሰማው:: አይሰማም:: ብንጾምም ጾማችን የረሃብ ዓድማ፤ ስግደታችንም ጅምናስቲክ  ሆኖ ነው የሚቀየረው::

እግዚአብሄር መስዋዕትነትን ከማቅረብ ይልቅ ከልባችን አምነነው ትእዛዙን ብናከብር ነው ጸሎታችንን የሚሰማው:: የዕለት ተለት ሕይወታችን በክፋት: በውሸት: በጸብ: በማጭበርበር: በሃሜት: በክስ: በተንኮል: በእብሪትና በሌሎችም ሓጢያቶች እስከተሞላ ድረስ አምላክ ጸሎታችንን አይሰማም:: እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን ብንመመላለስ መስዋታችንን ብናቀርብና እንዲሁም አሥራታችንን ብንሰጥ ግን ከሰኞ እስክ ቅዳሜ ቃሉን ሳናከብር በዓመፅ ብንኖር አምላክ ጸሎታችንን በፍጹም አይሰማም::ስለዚህ በመጀመሪያ ማስመሰሉን አቁመን ልባችንን ወደ አምላክ መልሰን በቃሉ መኖር መጀመር አለብን:: ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ንስሓ ለመግባት አለም አቀፍ ኑዛዜ (International Confession)ማካሄድ ይኖርባታል:: ይህ ሲሆን ብቻ ነው እግዚሃብሄር ጸሎታችንን ሰምቶ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የሚታደገው:: ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ወደ ቀደመ ክብራቸው የሚመለሱት ይህንን ስናደርግ ብቻ ነው::

አምላክ ለኑዛዜና ለንስሃ ያብቃን!

ከመከራና ከስደት አውጥቶ ፍጹም ሰላማችንንና አገራችንን እንዲመልስልን አምላካችንን በንጹህ ልብና በቃሉ በመኖር እንማጸነው::ያኔ አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል::


በሃረር በአንድ ለአምስት ያልተደራጁ የእርዳታ አጎበር እንደማያገኙ ተነገራቸው

ኢሳት ዜና :-የሃረር ወኪላችን እንደዘገበው ለወባ መከላከያ በሚል ከውጭ በእርዳታ ስም የተገኘውን አጎበር የመንግስት ባለስልጣናት በአንድ ለአምስት እና በአንድ ለሰላሳ ላልተደራጁት አንሰጥም በመላታቸው ፣ መደራጀት ያልቻሉ ነዋሪዎች አጎበር ሳያገኙ ቀርተዋል።

በነጻ የሚታደለው ይህ አጎበር ከክረምቱ መግቢያ ጋር ተያይዞ የአካባቢው ህዝብ ራሱን ከወባ እንዲከላከል ተብሎ የሚሰጥ ነው። ከአለማቀፉ የወባና ኤድስ ፈንድ በነጻ እንደተገኘ በሚገለጸው እርዳታ ፣ ገዢው ፓርቲ ዜጎች የድርጀቱ አባል ካልሆኑ አጎበር አይሰጣችሁም ማለቱ ተገቢ አለመሆኑን አጎበር እንዳያገኙ የተከለከሉ ሰዎችን አነጋግሮ ዘጋቢያችን ሪፖርቱን አጠቃሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በቅርቡ የንግድ ድርጅቶቻቸው ለተቃጠለባቸው ሰዎች በሚሰጠው እርዳታ ላይ አድልዎ በመታየቱ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው።

ዜጋን ከዜጋ የመለየቱ ተግባር ተገቢ አይደለም የሚሉት ነጋዴዎች፣ የመንግስት ሹሞች ሆን ብለው በከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አላስፈላጊ አለመተማመን እንደፈጠርና እንዲጋጩ ለማድረግ መሆኑን ነጋዴዎች ገልጸዋል።

ከ1 ሺ በላይ ነጋዴዎች አሁንም ምንም አይነት መፍትሄ ያልተሰጣቸው ሲሆን፣ ስራ ለመጀመር ባለመቻላቸው ቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ ወድቀዋል።



በራችንን ከፍተን የወያኔን ሌብነት ማቆም አንችልም!


የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ስልጣናቸውን በህዝብ ፈቃድ ላይ እንዳልቆመ አሳምረው ያውቃሉ። ነጻ የህዝብ ምርጫ ቢኖር ምን እንደሚሆኑ የዛሬ ዘጠኝ አመት በአይናቸው አይተዋል፣ በጀሮቸው ሰምተዋል። ከዚያ ተመክሮ ተነስተው ዳግም የህዝብ ፈቃድ ላለመጠየቅ ምለዋል። ቅዱሱን የዴሞክራሲና የፍቅር መንገድ ሳይሆን ሳይጣናዊውን የከፋፍሎና አናክሶ የመግዛትን መንገድ ዋና ምርጫቸው አደርገው ከወሰዱ ሰንብተዋል። የፍትህና የዴሞክራሲ ሂደት በኢትዮጵያ እነሱ እስካሉ ድረስ እንዳይነሳ አድረገው ቀብረውታል። በራሳቸውና ጥቅማቸው ላይ ኮሽታ በመጣባቸው ቁጥር ችግሩ በምስኪኑና የነሱ ሰለባ በሆነው ህዝብ ውስጥ መካከል እንደተፈጠረ ግጭት ለማስመሰል እና ለማድረግ የማያደርጉት ነገር የለም።ወያኔ ሰሞኑን በመላው የኦሮሞ ተወላጆች የመጣበትን ተቃውሞ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ጠብ ለማድረግ ያላደረገው ነገር የለም። መሰረታዊ የሆነውን የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ የባህርዳር እና በሌሎች የሀገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች ደግፈው ሂወታቸውን ያጡለትን የጋራ የወገንን ጥያቄ ለመቀልበስና፣ የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ጠብ ለማድረግ ያላደረገው ጥረት የለም።መሰረታዊ የሆነውን የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ በጥይት ብቻ ሊመልሰው እንደማይችል የተረዳው ወያኔ፤ በግርግሩ ውስጥ አማሮችና ኦሮሞዎች ደም እንዲቃቡና እንዲጋጩ አድርጎ ገላጋይ ለመምሰል የሚያደርገው ሙከራ ባይሳካለትም ይህን ተንኮል በህዝቡ ውስጥ የመትከል አባዜ ስራውን በስፋት ተያይዞታል። ሰሞኑን በመላው ኦሮምያ ካድሬ በማሰማራትና ገላጋይ በመምሰል ዋናውን የወያኔ መሬት ዝርፊያ ይቁም የሚለውን ጥያቄ በማለባበስና በማፈን ዘዴ ላይ ይገኛል።ወያኔ ይህን ስልት የመረጠው ወያኔን የምንቃወም የነጻነትና የዴሞክራሲ አንድነት ሃይሎች የትብብር ደረጃ ያለበትን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት ነው።

በፒያሳ ወርቅ ቤቶች ኮርኒስ ውስጥ ለ3 ቀን ያሸመቀው ወጣት ተያዘ

 ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፒያሳ እምብርት ላይ በሚገኘው ዝነኛው ላሊበላ ወርቅ ቤት ውስጥ ለብዙዎች ትንግርት የሆነ ነገር ተከስቷል፡፡ ያውም በጠራራ ፀሃይ፡፡ ላሊበላ ወርቅ ቤት፤ በአካባቢው ከሚገኙ ሌሎች ወርቅ ቤቶች ለየት የሚያደርገው ለምሳ ከ7-9 ሰዓት መዘጋቱ ነው የሚሉት የወርቅ ቤቱ ባለቤት አቶ ኢዛና ካሣዬ፤ የዚያን ዕለት ግን ገበያ በመብዛቱ ለምሳ ሳይዘጋ እንደቀረ ይናገራሉ፡፡
የላሊበላ ወርቅ ቤት ትንግርት የተጀመረው ከጎኑ በሚገኘው ኢየሩሳሌም ወርቅ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ኮርኒስ ውስጥ የመንደፋደፍ ድምፅ እንደሰሙ የሚናገሩት የኢየሩሳሌም ወርቅ ቤት ሰራተኞች፤ ለጊዜው ቢደናገሩም “እርግብ ነው” በሚል ተስማምተው ወደ ስራቸው መግባታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ሆኖም ድምፁ እየጨመረ በመምጣቱ ጥርጣሬ ይገባቸውና አንደኛው ሰራተኛ ክፍት በሆነው ኮርኒስ በኩል ባትሪ አብርቶ ተጠግቶ ይመለከታል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ


ያለ በቂ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ከአራት ሳምንት በፌት ከተያዙት ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በተጨማሪ በአንድ ጦማሪ አባል መኖሪያ ቤት ላይ ፖሊስ ለ7 ሰአት የቆየ ብርበራ አካሄደ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በዞን ዘጠኝ ጦማሪና መስራች ሶልያና ሽመልስ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፖሊስ ብርበራ ያካሄደ ሲሆን የጸረ-ሽብር ሕጉ ይፈቅድልናል የሚል ምክንያት ሰጥተው ያለ ፍርድ ቤት የብረበራ ማዘዣ ከካሜራ ቀራጭ ጋር የተገኙት ሰባት ፖሊሶች በጦማሪዋ ክፍል እና ሌሎች አስፈላጊ ነው ባሉዋቸው ክፍሎች ሲያካሂዱ ነበረውን ብርበራ ጨርሰው ይጠቅመናል ያሉትን የዶ/ር መረራ ጉዲና የመጨረሻ መጽሀፍ እና ሌሎች ወረቀቶች ወስደው ቤት ውስጥ የነበሩትን የጦማሪዋን ወላጅ እናት አስፈርመው ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ቤቱን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሰው በመምጣት ተጨማሪ ፍተሻ በዋናው መኖሪያ ቤት መካሄድ እንፈልጋለን ብለው ሁለተኛ ዙር ብርበራ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ እናካሂዳከን በሚል ሰበብ ትንሹ ክፍል ውስጥ የጦማሪዋን እናት እነዲወጡ በማግለል ከማቀዝቀዛውን አንቀሳቅሰው አፍታም ሳይቆዩ 19 ገጽ የግንቦት ሰባት ፕሮግራም አግኝቻለሁ ሲል አንዱ ፈታሽ ተናግሯል።

የሶማሊ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ወሬዎች እየተናፈሱ ነው


ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን አለመቆማቸውንና እንዲህ አይነት አሉባልታ እየተነዛ ያለው የሁለቱን ብሄር ህዝቦች ለማጋጨት መሆኑን እየተናገሩ ነው።
የተማሪዎች ወላጆች በሚነዛው ወሬ መደናገጣቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበረውና  የስዊድንን የአንቲገን ሽልማት አሸናፊ የሆነው አብዱላሂ ሁሴን ወሬው እንዲህ አይነቱ አሉባልታ በስፋት የሚሰራጨው የሁለቱን አካባቢዎች ተወላጆችን ለማጋጨት ነው ብሎአል።
ኦህዴድ /ህወሃት የተለያዩ ብሄረሰቦችን ተወላጆች ለማጋጨት እንቅስቃሴ መጀመሩን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን ማቅረባችን ይታወሳል

የኢትዮጵያመንግሥት የጋዜጣናመጽሔት አከፋፋዮችን ያለንግድፈቃድ በመሥራት እናታክስ ባለመክፈል ወንጀል ለመክሰስ እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰማ፡፡



ኢሳት ዜና:የጋዜጣና መጽሔት አከፋፋዮች በተለይ መንግሥትን የሚደግፉ ጋዜጣና መጽሔቶችን ሆንብለው ከገበያ ያስወጣሉ በሚል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጠናከረ ትችት ከመንግሥት ባለሰልጣናት በመቅረብ ላይ ሲሆን በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮምኒኬሽንጽ/ቤት እያካሄደ ያለውን ጥናት ማጠናቀቁ ታውቋል።

ምንጮችእንደገለጹትየጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችንበሕገወጥነጋዴነትከመክሰስጎንለጎንእነሱሲሰሩ የነበሩትን ሥራ በአነስተኛና ጥቃቅን ነጋዴዎች በማስተላለፍ መንግስት በአከፋፋዮች አማካይነት ይደርሳል ያለውን አፈና ለማስቀረት እንደሚቻል ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ይህ የመንግሥት ሃሳብ ገናከውጥኑ ተቃውሞ እየቀረበበት የሚገኝ ሲሆን፣ በተለይ የሕትመት ስርጭቱን በተዘዋዋሪ መንገድ መንግስትለመቆጣጠር ማሰቡ መንግስት የፈለገውን ሲያሰራጭ፣ያልፈለገውን እንዲያፍን ዕድል ይሰጠዋል።

በአሁኑ ወቅት በገዢው ፓርቲ ልሳን በሆነው ራዲዮ ፋና ከአከፋፋዮች ጋር በተያያዘ ከጋዜጠኞች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን በተለይ የብሮድካስት ባለስልጣን የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ ብዙዎቹ አከፋፋዮች ሕገወጦች መሆናቸውን በመጥቀስ መንግስት እርምጃ ለመውሰድ እያጠና መሆኑን በግልጽ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ፕሮግራም ላይ አከፋፋዮቹ ከውጪገ ንዘብ እየተቀበሉ የተወሰኑ የፕሬስ ውጤቶችን ያፍናሉ የሚሉ ውንጀላዎችም ተደምጠዋል፡፡ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ገዢው ፓርቲ አይደግፉኝም የሚላቸውን ጋዜጦች በተለያዩ ወንጀሎች እየከሰሰ ከገበያ ሊያወጣቸው እየሞከረ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።


በአዲስ አበባ ከሚፈርሱ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሰብአዊ  ቀውስ እየተከሰተ ነው  


ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ በቀጠለው የቤት ፈረሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በድንገት ቤቶቻቸው እየፈረሱባቸው ንብረቶቻቸውን እየተዘረፉ ሜዳ ላይ እየወደቁ ሲሆን፣ ትናንት ሌሊት በድንኳን ተጠልለው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል የ4 ልጆች አባት የሆኑ ግለሰብ በጅብ ተበልተው ዛሬ ከፊል አካላቸው በፖሊሶች መነሳቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ፖሊሶች መረጃው እንዳይወጣ አካባቢውን ተቆጣጥረው ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲያደርጉ የዋሉ ሲሆን፣ ቀሪው አስከሬን ከተነሳ በሁዋላ ደግሞ በማይክራፎን እየዞሩ በላስቲክ ድንኳን የተጠጉትን ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያዘዙዋቸው ነው። ብዙዎቹ ልጆቻቸውን የት እንደሚያስጠጉዋቸው ጨንቋቸው ለኢሳት በመደውል የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል
የሟቹን ግልሰብ ስም ለማግኘት ጥረት ብናደርግም እስካሁን አልተሰካላንም።ፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናድርግም አልተሰካላንም።
ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት በጻፉት የጋራ ደብዳቤ ደግሞ ፣ እንደ አዲስ ሰሞኑን የሚፈርሱ ቤቶች በዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተስፋ በተደረገ ፈንድ ለሚገነባው የኦሎምፒክ መንደር ፕሮጀክት ቦታ ለማዘጋጀት ሲባል በመሆኑ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የህዝቡን ስቃይ አይቶ፣ ድጋፉን እንዲያዘገይ ጠይቀዋል።
ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው “የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 2 ሚሊዩን የኢትዮጵያ ብር እንደሚሰጣቸው” ገልጸዋል።

Friday, May 23, 2014

የአረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል



አረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል – ፍኖተ ነጻነት አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በመግጨት አደጋ አድርሰውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዳራሹ ውስጥ ተዘግቶብን ዙሪያውን ተከበናል ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ ተጨማሪ ኃይል ጠይቋል ሲሉ የአረና አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ ወላይታ ከተማ በተደራጁ ሰዎች ዝርፊያና ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡


Thursday, May 22, 2014

የግንቦት 7 ሳምንታዊ ርዕሰ አንቀጽ




ዝክር ለግንቦት 7 1997 እና ለግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም.

ዘንድሮ፣ የታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን 1997 አገር ዓቀፍ ምርጫ ዘጠነኛ ዓመት እና ንቅናቄዓችን የተመሠረተበት ስድስተኛ ዓመት የምንዘክረው ከመችውም በላይ አገራችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሁና ነው። ወያኔ የማይገዛትን አገር እንዳትኖር ለማድረግ እማትወጣው አረንቋ ውስጥ ከመክተት የማይመለስ ኃይል መሆኑን ዛሬ በአምቦ፣ በጉደር፣ በጊምቢ እና መሰል ቦታዎች በተግባር እያስመሰከረ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፍላጎቱን የመግለጽ አንፃራዊ ነፃነት አግኝቶ የነበረበት የግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ምርጫን ስናስብ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ መመዘናችን አይቀርም። ያኔ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ እጁ መዳፍ ቀርባ ትታየው የነበረችው ድል እስከዛሬ አልጨበጣትም። ትግሉ ግን ቀጥሏል። የዛሬው ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከያኔው በበለጠ ከታሪክና ከራስዋ ጋር የታረቀች አገር የመመሥረትን ርዕይ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት መስጠትን የሚጠይቅ ሆኗል።
ወያኔ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለአለፉት አርባ ዓመታት ሲያብላላው የቆየው፤ በመንግሥት ሥልጣን በቆየባቸው ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ በፓሊሲ ደረጃ ሲያስፈጽመው የቆየውን የዘር ፓለቲካ አስከፊ ውጤት አሁን እየታየ ነው። ይህ የዘር ፓለቲካ ራሱ ወያኔን ያጠፋዋል። ችግሩ ግን የዘር ፓለቲካ ወያኔን ነጥሎ አያጠፋም፤ ከወያኔ ጋር አገራችንንም ሊያጠፋ ይችላል። ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ጉዳይ ደግሞ የዘር ፓለቲካ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። በጎረቤት አገራት ውስጥ ያየነውን ዓይነት የእርስ በርስ እልቂት ወደ አገራችን ለማምጣት ህወሓትና ኦህዴድ ተግተው እየሠሩ ነው። ሌሎች የወያኔ ተቀጥላ ድርጅቶችም የዚህ ትልቅ የጥፋት ፕሮጀክት አካል ናቸው።
የግንቦት 7 1997ቱ ብሩህ ተስፋ በፋሺስቱ ወያኔ የግፍ አፈና ሲጨልም፤ ያ ተስፋ እንዲያንሠራራ በግንቦት 7 2000 ዓ.ም. የተቋቋመው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ የኢትዮጵያን ተስፋ ለማጨለም ከተነሱ ኃይሎች በተፃራሪ በመቆም የሕዝብና የአገር አለኝታነቱ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
በዚህም ምክንያት፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የሆንን ሁሉ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ይኖርብናል። በግራም ይሁን በቀኝ ያለ ጽንፈኝነት አገራችን አይጠቅምም፤ የምንመኛትን ኢትዮጵያ አያመጣልንም። ሕዝባችንና አገራችንን ከዚህ አረንቋ ማውጣት የሚቻለው የአንድነትና የእኩልነት ፓለቲካን አሸናፊ ማድረግ ስንችል ነው።
በአሁኑ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ለሀገራችን የሚጠቅማትና ትክክለኛ ነው ብለን የምናምነው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚታገል፤ የተለያዩ የኅብረሰተሰብ ክፍሎች በመሰላቸው መንገድ ለመደራጀት መብታቸው እውቅና የሚሰጥ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ማኅበረሰቦች በሙሉ በእኩልነት የሚስተናገዱበት ሥርዓትን የሚያልም፤ መሰማማት፣ መቻቻል እና ከዚያም አልፎ መተጋገዝ ያለበት የኢኮኖሚና የፓለቲካ ሥርዓት እንዲኖር የሚታገል፤ የእምነቶች እኩልነትን የሚያከብር፤ በታሪክ ውስጥ የተፈፀሙ በደሎችን መርምሮ ማኅበራዊ እርቅ ለመፍጠር ፍላጎት ያለው ፓለቲካ ነው።
ይህ ዓይነቱ የአንድነትና የእኩልነት ፓለቲካ በአሸናፊነት እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል ብሎ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል። ይህ ለሁላችንም የሚበጀው ፓለቲካ አሸናፊ ለማድረግ የሚከተሉትን መፈፀም ይጠበቅብናል።
በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የሚደርስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፍጹም የማንታገስ መሆኑን ማመንና በተግባሮቻችንም ይህንኑ መግለጽ፤
ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር መውጫው መንገድ ወያኔን ማስወገድና በምትኩ የዜጎችን እኩልነት የሚያረጋግጥ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያስታርቅና የሚያስተሳስር መንግሥት መመሥረት መሆኑን ማመንና በተግባሮቻችን ማሳየት፤
የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላቶች ወያኔ እና ተቀጥላዎቹ፣ በተለይም ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ መሆናቸውን በማመን ትኩረታችንን ነቀሎ ወደሌላ ከሚወስዱ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች መቆጠብ፤
በብሔር ከተደራጁ ኃይሎች ጋር በሚለያዩን ነገሮች ላይ ሳይሆን በሚያስተባብሩን ጉዳዮች ላይ በማተኮር የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ አጀንዳ ማክሸፍ፤
በስሜትከተሞሉ የአጭር ጊዜ እይታዎች ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ አስተሳሰቦችና ተግባራት መቆጠብ፤ እና
አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ደህንነት፣ለፍትህና ለነፃነት በግንባር ቀደምትነት መቆም፤
የግንቦት 7 ንቅናቄ አባላትና ደጋፊዎች ከላይ የተዘረዘሩትን ለመፈጸም የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ያለንን ዝግጁነት እየገለጽን፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔና ግብር አበሮቹ ከፊቱ የደቀኑበትን ከፍተኛ አደጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተባብሮ እንዲያስወግድ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።
አስቸጋሪ ወቅት ላይ የምንገኝ ቢሆንም እንኳን በርትተን ከታገልን የተረጋጋች፣ ዲሞክራሲያዊ ሉዓላዊ አገር – ኢትዮጵያ – ይኖረናል። ለዚህ ውጤት በርትተን እንታገል።
ክብር የግንቦት 7 1997 ሀገራዊ ተስፋን እውን ለማድረግ ለወደቁ ሰማዕታት!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!


“ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ” (ከጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ)

ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር።እንግዶቹ አልመው የሚተኩሱ፣ አስበው የሚገድሉ አልመሰሉኝ አሉ። የሚያስቡበትና የሚያልሙበት ሕሊና የሌላቸው ፍጥረታት አድርጌ ላያቸው አልደፈርሁም። ባይሆን ሁሉም ጠላታችሁ ነውና አንዲት ጥይት ጮኸች ወይም አንድ ሰው ትንሽ ድምፅ አሰማ “በለው” በሚል መዘውር የተዘወሩ “መዘውራን” በመሆን በሳሩም በቅጠሉም ኤኬ47ቱን ማንጣጣት ያዙ። ያን ጊዜ በአእምሮዬ ጥግ በምትገኘው የማስታወሻ ሰሌዳዬ ላይ “ይኽ ቀን ገሐነም ባዶውን ያደረበት ዕለት ነው” ብዬ መዘገብሁ። እነዚህ ሰዎች እንደ መሪዎቻቸው በጥላቻ የተጠመቁ ከሆኑ መመለሻው ይቸግረናል። ከቶ ከየት ተነሥተን የት እንደርስ ይሆን? የማልረሳው ማስታወሻዬ ነው።
የጥንቱ ጋዜጠኛ ግዮን ሐጐስ ጄኔራል መንግስቱ ንዋይ ተከሰው ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ሪፖርተር ሆኖ ተመድቦ ነበር። ያን ጊዜ እኔ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበርሁ። መሬቱ ይቅለለውና ግዮን ሐጐስ ስለ ጄኔራል መንግስቱ ሲያወራኝ “በንግግራቸው መሐል ኰራ ብለውና ችሎቱን እየቃኙ ዓይናቸውን- አራት ማዕዘን እየወረወሩ- “ የተናቀ ከተማ በአህያ ይወረራል” ይሉ ነበር። ( በነገራችሽን ላይ ጄኔራል መንግስቱ አንድ ዓይናቸው ጠፍቶ ነበር። በወንድማቸው በአቶ ገርማሜ ንዋይ በተተኰሰባቸው ጥይት)የአህያን ሠራዊት ወግ – በቁሙና በእርቃኑ -እንደገና የሰማሁት ከባድመ ጦርነት በኋላ – ከባድመ ጦርነት ጋር ሲዘገብ ነው። የጦርነቱን ዳፋ- ድልና ሽንፈት – ውጤትና ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ ያካተተ አንድ ጥናት እንደሚለው በራስ ስዩም የፈረስ ስም በምትጠራዋ “በይርጋ ጉብታ” ትራያንግል- በባድመ በተደረገው ጦርነት በፊተኛው ረድፍ ተሰልፈው የቀዳሚ- ሰማዕትነትን ሙያ የተወጡ 36ሺህ ኢትዮጵያውያን አህዮች ናቸው። ግፍ የተፈፀመባቸው እንስሳት ይባሉ?..ከጥናቱ እንደ ተረዳሁት ከአርባ ሺህ በላይ የሚሆኑ የሰሜን- ምዕራብ ኢትዮጵያ ገበሬዎች የኢሳይያስ ሠራዊት እንደ ድንች በዚያ አካባቢ የቀበራቸውን ፈንጂዎች እንዲያመክኑ ተደረገ። በአጭሩ አህያውም “ሰውም”- በወያኔ ትርጉም አማራ ሰው ከተባለ- በፈንጂ ማሳ ላይ እየተንደባለሉ አለቁ። አንድ ቀን ነፃነት ከተመለሰ ለዚያ ሁሉ ሕዝብ ውሎ ይደረግ ይሆናል። ለአህዮቻችንም ጭምር!

የሶማሊ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ወሬዎች እየተናፈሱ ነው

አባይ ሚዲያ፦
በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን አለመቆማቸውንና እንዲህ አይነት አሉባልታ እየተነዛ ያለው የሁለቱን ብሄር ህዝቦች ለማጋጨት መሆኑን እየተናገሩ ነው።

የተማሪዎች ወላጆች በሚነዛው ወሬ መደናገጣቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበረውና  የስዊድንን የአንቲገን ሽልማት አሸናፊ የሆነው አብዱላሂ ሁሴን ወሬው እንዲህ አይነቱ አሉባልታ በስፋት የሚሰራጨው የሁለቱን አካባቢዎች ተወላጆችን ለማጋጨት ነው ብሎአል።

ኦህዴድ /ህወሃት የተለያዩ ብሄረሰቦችን ተወላጆች ለማጋጨት እንቅስቃሴ መጀመሩን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን ማቅረባችን ይታወሳል።


(አባይ ሚዲያ)፡ የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ሲል ኤርትራውያን ስደተኞችን መስታጠቅ ሊጀምር ነው።



የኢትዮጵያ መንግስት በጎረቤት ኤርትራ በኩል እየጠነከረ የመጣውን የኢትዮጵያውያን የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ ለመግታት ያስችለው ዘንድ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን በማሰባሰብ የአስመራን መንግስት በሃይል በመገልበጥ ዴሞክራሲ በኤርትራ መፈንጠቅ አለበት የሚል አዲስ ዘዴ መጀመሩን ከአካባቢው ለመረዳት ችለናል።

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ወጣት ኤርትራዊ ሲገልጽ፡- አካባቢው የእርስ በርስ የጦርነት ቀጠና መሆኑ ለወያኔ የትኩረት አቅጣጫን በኤርትራኖች የእርስ በርስ ጦርነት በመለወጥ በአካባቢው እየጠነከረ የመጣበትን ሃይል ወደ ህዝቡ እንዳይዳረስ ለማድረግ ለራሱ ጥቅም የጀመረው ሴራ እንጂ ለእኛ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች አስቦ በኤርትራ ዴሞክራሲ ይፈጠር በሚል ትላንት በድንገት ወደ ትግሉ ግቡ ሊለን አይችልም ሲል መረጃውን ሰጥቶናል።

በትላንታናው እለት የኤርትራውያን ስደተኞች 23ኛ የነጻነት አመታቸውን በሚያከብሩበት የስደተኞች መጠለያ የወያኔ ባለስልጣኖች ተገኝተው ስደተኞችን ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገብተው እንዲታገሉና የኢሳያስን መንግስት እንዲገለብጡ በጥብቅ ያሳሰቡ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህን ተከትሎም ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች “ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ትጥቅ አንስተው ለመታገል ተቃዋሚ ሃይሎችን ሊቀላቀሉ ነው” የሚል ዜና መላኩን ሱዳን ትሪቢውት የተባለው ድህረ ገጽ አስፍሮታል።

በአለፈው ሳምንት የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል 4ኛ ዙር በርካታ የነጻነት ታጋይ ወታደሮችን ማስመረቁን መዘገባችን ይታወሳል።


Wednesday, May 21, 2014

ታሣሪዎቹ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች “ተደበደብን” አሉ

ፖሊስ “አመፅ በመቀስቀስ ጠርጥሬአቸዋለሁ” ብሎ ከሦስት ሣምንታት በፊት ከያዛቸው ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች (ብሎገሮች) መካከል አንዳንዶቹ “ድብደባና ሌላም ሌላም ሥቃይ ደርሶብናል” ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡

ፖሊስ በበኩሉ ምርመራውን በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ለማጠናቀቅ ሃያ ስምንት ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፡፡

ጠበቆች ጥያቄውን ቢቃወሙም ፍርድ ቤቱ ግን ከፖሊስ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ የጊዜ ቀጠሮውን አፅድቋል፡፡

አማራውን በሁለንተናዊ መልኩ አዳክሞ መግዛት ወይም ማጥፋት፦

በጌታቸው ፏፏቴ፦

ራስ ስሁል(ራስ ስዑል) ሚካኤል መቀመጫውን በጐንደሩ ቤተ-መንግሥት በማድረግ በሥሩ ንጉሶችን በማንገስ ከላይ ሆኖ የሚቆጣጠራት በመሳፍንቶች የምትመራና አንድ ማዕከላዊ የሆነ ግዛቷ ለተወሰነ ጊዜ ተዳክሞ የነበረች ኢትዮጵያችን ይገዛ ነበር። በኋላ በመይሳው ካሣ(አፄ ቴዎድሮስ) የተገነባ ማዕከላዊ መንግሥት ተመስርቶ እነሆ እኛ እስካለንበት ዘመን ደርሷል። የኛው ሞራልና ኢትዮጵያዊነት ወኔ ደግሞ የት እንደሚያደርሰን እናየዋለን።ወደ ራስ ስሁል ልመለስና ራስ ስሁል ሚካኤል ጨካኝና ተንኮለኛ መሆናቸውን የሚያሳይ አንዱን ንጉሥ ከምግብ ጋር መርዝ በመጨመር አንደኛውን ንጉሥ በሻሽ አሳንቀው መግደላቸውን የሚገልጽ አንድ ጹሑፍ አንብቤ ስለነበር የህወሃት ድርጅታዊ ፕሮግራም ከዚህ የተቀዳ ይሆን ? በማለት አንዳንድ የቀደምት ጸሓፍትን መመልከት እንዳለብኝ የግድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ራስ እየተባሉ ንጉሶችን ይገዙ የነበሩት ራስ ስሁል ሚካኤልና ዛሬ ህወሃት ብዙ የክልል ንጉሶችን አንግሶ የክልል ንጉሶችን እየገዛ ሕዝባችን በጭቆና መዳፍ ሥር ወድቆ መተናፈሻ ተነፍጎት ሳይ ይህን ችግር ቶሎ ነቅለን ካልጣልን እስከ ወዲያኛው ትውልዳችን መክኖ እንደሚቀር ግልጽ ማሳያ መስሎ ይታየኛል።የዘመኑ የክልል ገዥዎች ወይም መሪዎች ከህወሃት መንገድ ትንሽ ሲያፈነግጡ ምን እንደሚከተላቸው ግልጽ ሲሆን ውክልናቸው ወይም ታማኝነታቸው ላሉበት ክልልና ህዝብ ሳይሆን ለህወሃት ብቻ እንደሆነ ማሳመኛ የሚያስፈልገው አይመስለኝም።በቅርብ ወራት የሞተውን የኦሮሞ ክልል ፕሬዘዳንት ዓለማየሁ አቶምሳን ህመም ምንጭ ምን እንደሆነ በተለያየ መንገድ ያፈተለኩት ወሬዎች እንደሚነግሩን ህወሃት የራስ ስሁልን ታሪክ እንደደገመ ነው።የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ከህወሃት የተቀሰረበትን ጣት ለማስነሳት ተገንጥየ ወደ ሶማሌ ሄጀ እቀላቀላለሁ ብሎ ለጊዜው ቢያስፈራራም ነገ የሚገጥመውን በጋራ የምናየው ይሆናል። እንግዲህ ይህን ያህል ካልኩ አቅሙና ጊዜው እንዲሁም መረጃው ያላችሁ ይህን መነሻ በማድረግ ጠንከር ያለ ጹሑፍ ታስነብቡን ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።
ህወሃት የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም ማናቸውንም አይነት ጸረ ህወሃት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማፈን ያለ የሌለ አቅሙን አሟጦ እየተጠቀመ መሆኑን በግልጽ የምናውቀው ቢሆንም እንደ ድርጅት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን በፕሮግራሙ ቀርጾ የያዘው ትልቁ ዓላማው ግን አማራውን አዳክሞ መግዛት ወይም ማጥፋት እንደሆነ ይታወቃል። ከነዚህም ዋና ዋናዎቹ :-

Monday, May 19, 2014

‹‹የፓትርያርኩን ሥልጣን ሊገድብ የሚችል የሕግ ረቂቅ ለውይይት ቀረበ


ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚያስተላልፉት በብሔራዊ ቋንቋ ብቻ ይኾናል

       የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ፓትርያርኩን የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ በሚገልጽና የፓትርያርኩን ሓላፊነትና ተጠያቂነት በጉልሕ የሚያሳዩ አንቀጾችን ባካተተ የሕግ ረቂቅ ላይ እየተወያየ እንደኾነ ተገለጸ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በ1991 ዓ.ም. ያወጣችውን ሕግ ከሌሎች ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማጣጣም፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዕድገትና ነባራዊ ኹኔታዎች ጋራ በማገናዘብ ያሻሽላል የተባለው የሕግ ረቂቁ ለውይይት የቀረበው፣ ባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጎች ኹሉ የበላይ ነው የተባለው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁ÷ ርእሰ አበውና ለካህናቷና ለምእመናንዋ ኹሉ መንፈሳዊ አባት ለኾኑት ለፓትርያርኩ እንደራሴ እንደሚሾም በአንቀጽ 24 ላይ ማስፈሩ ተመልክቷል፡፡ እንደራሴው ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን የተጣለበትን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ ለማከናወን እንዲችል የሚያግዝ›› መኾኑ በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ተገልጧል፡ ፡

እንደራሴው የሚመደበው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ብቻ በሚሳተፉበት ምርጫ ሲኾን፣ ለምርጫው ሦስት ዕጩዎች በፓትርያርኩና በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ጥቆማ እንደሚለዩ ተጠቅሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖናና ትውፊት የማስጠበቅ እንዲሁም ያለአድልዎ የማስተዳደር ሓላፊነት ላለበት ለፓትርያርኩ በእንደራሴነት የሚመረጠው ሊቀ ጳጳስ ማሟላት የሚገባው መመዘኛ በሕጉ መመልከቱ የተጠቆመ ሲኾን መመዘኛው ለእንደራሴው ከ50 – 60 ዓመት የዕድሜ ገደብ ሲያስቀመጥ፣ የአስተዳደር ችሎታና የመንፈሳዊ አመራር ልምድን፣ መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት አጣምሮ መያዝን እንደሚጠይቅም ታውቋል፡፡ ‹‹ግለሰባዊ የሥልጣን ፈላጊነት ስሜት የሚገንበት፣ የፓትርያርኩን ሥልጣን የሚጋፋና መካሠስን የሚያበረታታ ነው›› በሚል አንቀጹን የተቃወሙ የቤተ ክህነት ሓላፊዎች፣ ምደባው አስፈላጊ ኾኖ ከተገኘም እንደራሴው በፓትርያርኩ ጥቆማ ብቻ መመረጥ እንዳለበት የቃሉ ትርጉም እንደሚያስገደድ በመጥቀስ ይከራከራሉ፡፡

የአህጉረ ስብከት የሥራ ሓላፊዎች በአንጻሩ፣ የእንደራሴው ምደባ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ብልሹ አሠራር እንዲታረም የአደረጃጀትና የአሠራርለውጥ ጥናት በማድረግ ላይ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አመራር መጠናከር የራሱ አስተዋፅኦ አለው በሚል እንደሚደግፉት ተናግረዋል፡፡ እንደራሴው ፓትርያርኩን ከማገዝ ውጭ ‹‹ለቅዱስ ፓትርያርኩ ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ የሚጋራው የተለየ ሓላፊነት አይኖረውም፤›› በሚል በረቂቁ የሰፈረውን አንቀጽ በመጥቀስ ምደባው ፓትርያርኩን የመጋፋት ሚና እንደሌለውም ገልጸዋል፡፡ ተጠያቂነትን በተመለከተም ፓትርያርኩን ብቻ ሳይኾን ኹሉንም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪ ከማድረግ፣ በአስተዳደር በደልና በአመራር ጉድለት የካህናቱንና የምእመናኑን አመኔታና ተቀባይነት ማጣትን ጨምሮ ከሀብትና ንብረት ባለቤትነት ጋራ የተያያዙ ዝርዝር የተጠያቂነት አንቀጾች በረቂቁ በመካተታቸው በፓትርያርኩ አልያም በወቅታዊ እይታ ላይ ብቻ የታጠረ ረቂቅ እንዳልኾነ ያስረዳሉ፡፡

ጉዳዩ በዋናነት የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ አመራር ከማጠናከር አንጻር ሊታይ ይገባል የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች፣ ምልዓተ ጉባኤው የሕግ ማሻሻያ ረቂቁን በጥልቀት በማዳበር የቅዱስ ሲኖዶሱ ሉዓላዊ ሥልጣን በማንም የማይገሠስበት መሣርያ አድርጎ እንደሚያጸድቀው እንጠብቃለን ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ፓትርያርኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ በዓላት ላይ እንዳስፈላጊነቱ እየተገኘ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚሰጠው እንዲሁም በብዙኃን መገናኛ መንፈሳዊ መልእክት የሚያስተላልፈው በአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ብቻ እንደሚኾን በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ላይ መስፈሩ ተጠቅሷል፡፡


ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ? (ተመስገን ደሳለኝ)



ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡

አርባ አራት ዓመት ወደኋላ…

 በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ እንቅስቃሴ መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962 ዓ.ም በአራት ገፅ
ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ
በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-

“…ማንንም ሰው የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃ የቱ ነው ብላችሁ
ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ባሕል የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ ብሔራዊ ልብሳችሁ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የአማራ
ወይም የትግሬ ይላችኋል፡፡”

 ይህ ሀቲት በወቅቱ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ቁጣ ከመቀስቀሱም በላይ ዋለልኝን በ‹ፀረ-አማራና ትግሬነት› አስፈርጆ
ለውግዘት ዳርጎት ነበር፡፡ እራሱም ቢሆን በአንድ የዩንቨርስቲው መድረክ ላይ የተሰነዘረበት ከባድ ተቃውሞ በፈጠረበት
ብስጭት ‹‹እኔም አማራ ነኝ፤ ያውም ከአማራ ሳይንት-ቦረና›› ማለቱ ይታወሳል (ቦረና በተለምዶ አማራ መጥቶበታል
የሚባለው አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡ ግና፣ ዋናው ጥያቄ የእርሱ አማራ መሆን ያለመሆን አይደለም፤ እዚህ ድምዳሜ ላይ
የደረሰበት ምክንያት ከተጨባጩ እውነታ ጋ ምን ያህል ይዛመዳል? የሚል ነው፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ ከዚህ ጽሑፍ በፊት
ብሔር ተኮር ጎዳዮችን አንስቶ ካለማወቁም በዘለለ፣ ሌሎች ሲያነሱ ፅንፈኛ ተቃዋሚ ስለነበረ ነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ ኢብሳ
ጉተማ (ኋላ ላይ የኦነግ መስራችና አመራር የሆነው) ‹‹ኢትዮጵያዊ ማነው?›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ግጥም እጅግ ተናድዶ
‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ግጥም ታቀርባለህ? ዘረኛ ነህ፤ ኢትዮጵያውያንን የመከፋፍል ዓላማ ነው ያለህ?›› በማለት
እስከመቃወም መድረሱ የክርክሩ አንዱ ጭብጥ ነው፡፡

 ታዲያ ዋለልኝ መኮንን ድንገት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ከምን የተነሳ ይሆን? በርግጥ ለዚህ ድንገቴ የአቋም ለውጥ ሶስት
መላ-ምቶች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹በአፄው ሥርዓት ላይ አሴረዋል› ተብለው ከተከሰሱትና ‹ኦሮሞ እየተጨቆነ
ነው› የሚል እምነት ከነበራቸው ጄነራል ታደሰ ብሩ ጋር በታሰረበት ወቅት፣ በጄነራሉ ስብከት አመለካከቱ ተቀይሮ ሊሆን
ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹መገንጠልን መደገፍ በመጨረሻ የማትገነጠል ሀገር እንድትኖር ያደርጋል››
በማለት ከተከራከረበት ከራሱ አቋም ጋር የሚያያዝ ነው፤ ሶስተኛው ‹የሻዕቢያ (ኤርትራውያን ተማሪዎች) አሊያም የአሜሪካኑ
የስለላ ተቋም (ሲ.አይ.ኤ) መጠቀሚያ ሆኖ ነው› የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከዋለልኝ ጀርባ ‹ስውር እጅ›ን ለመፈለግ
ያስገደደው በጊዜው ብዙሁ ተማሪ ለሀገሪቱ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ‹የንጉሣዊው አስተዳደር ኋላቀርነት እና ስግብግበነት ነው› ብሎ
ከማመኑም ባለፈ፣ ከፌዴራላዊ ይልቅ የቻይና ኮሙኒስታዊ ሥርዓት አድናቂ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የተማሪውን
እንቅስቃሴ በመምራት በዘመኑ ከዋለልኝ የላቀ ተሰሚነት የነበረው ጥላሁን ግዛው ‹‹ጎሰኝነትን›› በአደባባይ አጥብቆ ይቃወም
እንደነበረ፣ በ1968 እ.ኤ.አ የታተመው ‹‹Struggle›› ቅፅ 3፣ ቁጥር 1 መጽሔት ጋር ያደረገውን ቃለ-መጠይቅ መጥቀስ
ይቻላል፡-

‹‹በመጀመሪያ ደረጃ በጎሰኝነትና በሶሻሊዝም መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ጎሠኝነት በተወሰነ አካባቢ ብቻ
የሚቀርና አካባቢ ቀመስ ነው፡፡ ሶሻሊዝም ግን ዓለም ዓቀፋዊ ነው፡፡ …እንደ ዩንቨርስቲ ተማሪነታችንና እንደ እጩ
ምሁርነታችን የሕብረተሰባችንን አቋም ከመደብ አንፃር መተንተን እንጂ በጎሣ መከፋፈል አይገባም›› ማለቱ ይታወሳልና፡፡

የህወሓት-ውልደት



 ዋለልኝ መኮንንን ‹‹የብሔር ጭቆና›› ትንተናን መሰረት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የፋኖ ድርጅቶች መመስረታቸው
አይካድም፡፡ ከእነዚህም መንግስታዊውን ሥልጣን ለመጨበጥ የበቃው ህወሓት አንዱ ነው፡፡

 የአማራና ትግሬ ጨቋኝነትን የሚያውጀው ጽሑፍ በተሰራጨ በአምስተኛው ዓመት የትግርኛ ተናጋሪውን ብሔራዊ ጭቆና
ለማስረገጥ ጽሑፉን እንደ ሰነድ ማስረጃ ቆጥረው ‹‹ትግራይን ነፃ እናወጣለን!›› ያሉ ፋኖዎች ነፍጥ አንግበው በረሃ
ቢወርዱም፣ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት አካባቢ ‹‹እንታገልለታለን›› በሚሉት ዘውግ ተወላጆች ሳይቀር መናፍቅ
ተደርገው መወገዛቸው ይታወሳል፡፡ ደራሲና ገጣሚ አስማማው ኃይሉም ‹‹ኢህአሠ›› በተባለው መጽሐፉ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹በ1969 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ በእምባ ሰገንይቲ ወረዳ ነበለት አካባቢ ሽምዕጭ ተብሎ በሚጠራው መንደር
የህወሓትና የኢሕአሠ አባላት ሕዝብን ለመቀስቀስ ተገኝተው ነበር፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የድርጅታቸውን ዓላማ
ካስረዱ በኋላ ያካባቢው አዛውንት ማሳረጊያውን ንግግር አደረጉ፡፡ አዛውንቱ መሔድ የሚሳናቸው ስለነበሩ ሰዎች
ደግፈው ወደ በቅሏቸው እንዲያወጧቸው ከጠየቁ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ፡፡ ወደ ህወሓት አባላት
እጃቸውን ዘርግተው ‹እናንተ ከሆዳችን የወጣችሁ ልጆቻችን ናችሁ›፤ ወደ ኢሕአሠ አባላትም ፊታቸውን አዙረው
‹እናንተ ደግሞ ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት መጥታችሁ ለእኛ ስትሉ ነው የምትታገሉት፡፡ የሆነው ሆኖ እኛ የትግራይ
ሰዎች ሆነን ስንቀር ኢትዮጵያ ከማን ጋር ልትቀር ነው? ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዊ ከሚል ጋር ነው የምንወግነው›
ሲሉ ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡›› (ገፅ 235)

 ህወሓት በትግራይም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን አገዛዛዊ ጭቆና፣ የብሔር አስመስሎ እስከ መገንጠል
ቢንደረደርም፣ የገጠመው ተቃውሞ ፕሮግራሙን ለመከለስ አስገድዶታል፡፡ ዘግይቶ ላገኘው ድጋፍም ቢሆን ከዘውግ ተኮሩ
ተረት-ተረት ይልቅ አምባ-ገነናዊው የደርግ አስተዳደር የወለደው ሽብርና ጭፍጨፋ የተሻለ ጠቅሞታል፡፡ ለዚህም በዛሬይቷ
ትግራይ ከሶስት ያላነሱ ፀረ-ህወሓት ድርጅቶች መኖራቸው ማሳያ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

 በሌላ በኩል ከህወሓት ምስረታ አንድና ሁለት ዓመት አስቀድሞ ወደ አደባባይ የመጡት ኢህአፓና መኢሶን የትግል
አጀንዳቸው የመደብ ቅራኔ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ይህ ግን በወቅቱ ከህወሓትም በከረረ መልኩ ‹‹የብሔር ጥያቄ በመገንጠል
ብቻ ነው የሚፈታው›› የሚል እምነት ተከታዩ ኦነግን ህልውና አያስክድም፡፡ እዚህ ጋ የምንመለከተው ሌላኛው ግራ አጋቢ
ጉዳይ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ሠልፍ (በ1957 ዓ.ም) አስተባብሮ
የሕግ-መወሰኛው ምክር ቤት ድረስ የመራው ባሮ ቱምሳም (በአብዮቱ ሰሞን የኢጭአት የአመራር አባል ነበር) ሆነ፤ የመኢሶኑ
ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ኃይሌ ፊዳን የመሳሰሉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቆች፣ ከኦነግ በተቃራኒው ከብሔር ይልቅ
የመደብ ጥያቄ አቀንቃኝ የነበሩ መሆኑን ነው፡፡ በነገራችን ላይ በግሌ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ብያኔ እነዋለልኝ የለጠጡትንና
ያጎኑትን ያህል እንኳ ባይሆንም እንደገና መከለስ እንደሚያስፈልገው አምናለሁ፡፡

 የሆነው ሆኖ ህወሓት መንግስታዊውን ሥልጣን በጨበጠ ማግስት ‹የሰነበተውን የብሔር ቅራኔ በማያዳግም ሁኔታ የሚፈታ›
ሲል ያንቆለጳጰሰውን ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ቢተገብርም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን የመግታት አቅም
እንደሌለው ለማረጋገጥ የአንድ እጅ ጣቶች ያህል ዓመታት እንኳን አልፈጀም፡፡ በደቡብ በጉጂ እና ጌዲዮ፣ በጉጂ እና ቡርጂ፤
በጋምቤላ በአኝዋክ እና ኑዌር፤ በቤንሻንጉል በጉምዝ እና በርታ መካከል የተከሰቱት የይገባኛል ግጭቶች በማሳያነት ይጠቀሳል፡፡

 የፌዴራሊዝሙ ቀዳዳዎች

 ዘውግ ተኮር ፌዴራሊዝሙ፣ ገና ከጠዋቱ ለከፋ ዕልቂት ሊዳርግ እንደሚችል በማስታወስ ይሰሙ የነበሩ የተራዘሙ
ጩኸቶችን ችላ ብሎ ዛሬ ላይ ቢደርስም፤ ለፕሮፓጋንዳ በሸነቆራቸው ቀዳዳዎች እየገባ ያለው ከባድ ንፋስ ከራሱ አልፎ
ሀገሪቷንም ከበታኝ አደጋ ፊት አቁሟታል፡፡ ለዚህም አገዛዙ የፈጠራ ትርክቱን ለማስረፅ የሄደበት የኑፋቄ መንገድ የአንበሳውን
 ድርሻ ይወስዳል፡፡ በፓርቲው ካድሬዎች በኩል በየዕለቱ የሚዘራው የጥላቻ ፖለቲካ፣ ሐውልት ማነፅ፣ ከፋፍሎ ማቆም እና
መሰል ስልቱ በተጨማሪ ሜጋ በሚያሳትማቸው መጻሕፍት እልቂት ጠሪ ዘውግ ተኮር ቅስቀሳዎችን እስከማሰራጨት መድረሱን
ተመልክተናል፡፡

ለአብነትም የሚከተለውን ግጥም ልጥቀስ፡-

“ነፍጠኞች እቤታቸው በክብር ይጎለታሉ፣
 እኛን በኃይል አስገድደው ያሰራሉ፣
 ቁጥቋጦ እንደምትመነጥረው መንጥራቸው
 ወደመጡበት ወደ ሸዋ አባራቸው፡፡” (“ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ቅፅ 3፤ ገፅ 145)

 ግና ‹‹ሸዋ›› ሱዳን ወይም ግብፅ አይደለምና ዛሬ ከጉራፈርዳ እስከ ደንቢዶሎና ጊምቢ ለተተገበረው የማባረር ዘመቻ ዋነኛው ተጠያቂ የሥርዓቱ ኤጲስ ቆጶሳት መሆናቸውን ግጥሙ ያስረግጣል፡፡ በግልባጩ እነዚህ ሰዎች በ97ቱ ምርጫ ዋዜማ፣ ሚያዚያ 30 ቀን መስቀል አደባባይ ቅንጅት በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ አቶ በድሩ አደም ‹‹ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን›› ማለታቸውን፣ ወደ ዘውግ ጥላቻ ከመቀየራቸውም በላይ፣ የቅንጅቱን አመራሮች ለቅመው ካሰሩ በኋላ የሰውየውን ንግግር ‹‹የዘር ማጥፋት ሙከራ!›› ሲሉ ለመሰረቱባቸው ክስ በማስረጃነት ማቅረባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ በዚያው ሰሞን አቦይ ስብሃት ነጋም የብአዴን ጓዶቻቸውን ‹‹እኛ ወደመቀሌ ስንባረር፤ እናንተን መንዝ ላይ አራግፈን ነው የምንሄደው!!›› አሉ መባሉም ጉዳዩ በራስ ላይ ሲደርስ ምን ያህል አሳማሚ እና ለበቀል እንደሚያነሳሳ ሁነኛ ጥቁምታ ቢሰጥም፣ ገዥዎቻችን ትምህርት ሊወስዱበት አለመቻላቸው ያስቆጫል፡፡ እንዲያውም ከምርጫ 97 በኋላ በዩንቨርስቲዎች ግቢ የሚነሱ ተቃውሞዎች ዘውግ-ተኮር ወደመሆን ነበር የተሸጋገሩት፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዩንቨርስቲዎች በተናጠል (በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን) ስር ማደራጀት የጀመረው ከዚሁ ምርጫ በኋላ እንደነበረ አይዘነጋም፤ ለእንዲህ አይነቱ የፓርቲው ተልዕኮ ደግሞ እንደ ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ አይነት የገዥው-ፓርቲ መንፈስ የሰረፀበት ‹‹ምሁር›› ጠቀሜታን ለመረዳት አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ያለበትን ሁኔታ መቃኘቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ሁለት አስርታት የህወሓት አባልና ደጋፊ ተማሪዎች የግቢውን መንፈስ አይመረምሩም (አይሰልሉም) ነበር እያልኩ አይደለም፤ በግላጭ የጓደኞቻቸውን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ሪፖርት ያደርጉ ነበርና፡፡ በአናቱም የዘውግ ተኮር ፖለቲካው መተግበር በጀመረበት ወቅት ወደ ትምህርት ቤት የተላኩ ልጆች፣ ዛሬ ለዩንቨርስቲ መብቃታቸው፣ አጀንዳው በቅፅበት ሊፈፀም የመቻሉን እውነታ በኦሮሚያ ሰሞኑን የተመለከትነው ቀውስ በቂ ማሳያ ይሆናል፡፡
 የተጭበረበረው አጀንዳ

 ‹የብሔር ጥያቄ ዋነኛው የቅራኔ ቅርፅ ነው› የሚለው ህወሓት ይህን ጥያቄ መፍታት ሥርዓታዊ ግብ እንደሆነ እስኪሰለቸን
ቢደሰኩርም፤ አጀንዳውን ከማጭበርበሪያነት የዘለለ ዋጋ አልሰጠውም፡፡ እናም ታሪክ ቢያንስ በዚህ በኩል በበጎ
እንደማያስታውሰው ለመናገርም ብዙ ማስረገጫዎችን መጥቀስ አይገድም፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን እየናጣት ያለው፤ ጥያቄያችን
አልተመለሰም› የሚሉ ብሔርተኛ ቡድኖች መበርከት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በስያሜ ደረጃ እንኳን (መሬት ላይ ያላቸውን
ጉልበት ትተን) ከአስራ አንድ የማያንሱ ተገንጣይ ንቅናቄዎች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ የእነዚህን ከኦጋዴን እስከ ጋምቤላ፤
ከቤንሻንጉል እስከ አፋር ድረስ ያሉ አማፅያን እንቅስቃሴን የጥቂት ልሂቃን ቅብጠት አድርጎ መውሰድ ርትዕ አይሆንም (ስለምን
ቢሉ ደርግም ህወሓትን የሚያስበው እንዲያ ነበርና)፡፡ እናም ከትልቁ ኦሮሞ ጥያቄ መጠለፍ ጀምሮ፤ እነዚህ ጉዳዮች አስቀድሞ
ግንባሩ የብሔር ጥያቄን ለሥልጣን መወጣጫ ብቻ ለመጠቀም ማስላቱን ይጠቁሙናል፡፡

 ሌላኛው ጭብጥ አሁንም ድረስ ማንነት ተኮር ጥያቄዎች አለመቆማቸው ነው፡፡ ከቅማንት እስከ ወለኔ እና ቁጫ ድረስ ያሉት
‹‹ማንነታችን ታውቆ ዞን ይሰጠን›› ጩኸቶች ማቆሚያቸው የቱ ጋ እንደሆነ ራሱ ኢህአዴግም የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡
በግልባጩ ለእነዚህ ሶስት የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄ በቅርቡ የሠጠው ምላሽ ጭፍለቃ መሆኑን ስናስተውል፤ ‹ተነሳሁለት›
ከሚለው የብሔር ጭቆናን ማጥፋት አኳያ የሚነግረን ሀቅ ሥርዓቱ የሄደበትን ቁልቁለት ብቻ ነው፡፡

በሶስተኛነት ከዚሁ ጋር አያይዘን ልናነሳው የምንችለው ርዕሰ ጉዳይ የመገንጠል መብት ነው፡፡ ከዋለልኝ እስከ ጥላሁን ታከለ እና
ቱሞቱ ሌንጮ (ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ) ድረስ የነበሩ የዘመኑ ትውልድ መንፈስ ተርጓሚዎች መገንጠልን ሕብረ-ሱታፌ
(ሶሻሊስታዊ) ሥርዓት ለመገንባት መዳረሻ መንገድ አድርገው ቢያቀርቡትም፤ ጥራዝ ነጠቆቹ ህወሓቶች ሕገ-መንግስቱ ውስጥ
ቀርቅረውታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ‹‹መገንጠልን ለመከላከል ነው›› ቢሉም፤ ከፌደራሊዝሙ አወቃቀር አኳያ
‹የማይተገበር መብት› ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በዋናነት ሁለት ነጥቦች ይነሳሉ፤ ‹እንደ ስታሊኒስቷ ሩሲያ
 ሁሉ መብቱ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቢካተትም፣ የማዕከላዊ መንግስቱ ሥልጣን ፍፁማዊ መሆን እንዳይተገበር ያደርገዋል›
የሚለው የመጀመሪያው ነጥብ ነው፡፡ ሁለተኛው የመብት አፈፃፀሙ ራሱ በተለያዩ አስገዳጅ ተዋረዳዊ ትግበራዎች መጠላለፉ
ነው፡፡ በተለይም ሁለትና ከዚያ በላይ ዘውጎችን ያቀፉ ክልሎች የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሱ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው
ለመረዳት የክልሎቹን አወቃቀር መመልከቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ነጥቦች ስንነሳ የመገንጠል ግብ ያላቸው
እንቅስቃሴዎች በትጥቅ ትግል አገዛዙን ካላስወገዱት በቀር በሕገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ሊተገበሩ
አለመቻላቸውን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ሁነትም ሥርዓቱ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያነበረው ከፋፍሎ ለመግዛት እንጂ፤
እስክንደነቁር በጩኸት ስለሚነግረን ‹‹ጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች›› መብት ደንታ ኖሮት እንዳልሆነ ያስረግጥልናል ብዬ
አስባለሁ፡፡



 በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ኃይለስላሴ ቀጥሎ ረዘም ላለ ዓመታት ሀገሪቱን የመምራት ዕድል ያገኘው ኢህአዴግ
የተሻለች ሀገር የመገንባት በርካታ ዕድሎችን አምክኗል፡፡ ወደሥልጣን በመጣ ማግስት ዘውገኝነትን የመንግስታዊ መዋቅሩ
ብቸኛ ገፅ ሲያደርገው፣ ከብዙ ጫፎች ከተነሳበት ከባባድ ተቃውሞዎች መሀል፡- ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝሙ ማሕበረ-ባሕላዊ
መሰረቱ በጣም የተሳሳተ መሆኑን እና የዘውግ ማንነትን ብቸኛው የክልሎች ድንበር አሰማመር መነሻ ማድረግ ለእርስ በእርስ
የዜጎች ትንቅንቅ ያጋልጣል የሚሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ ሥርዓቱ ይህን ጆሮ ሰጥቶ ከማዳመጥ ይልቅ ቢያፈገፍግም፣ ያሳለፍናቸው
ሃያ ሶስት ዓመታት በሞቶችና በመከራዎች የተፃፉ ኩነቶችን አሳይተውናል፡፡ ‹‹ባለሥልጣን›› እና ‹‹ሥልጣን የለሽ›› (ባለቤትና
መጤ) በሚል ጨዋታ፣ በየክልሎቹ የሚገኙ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከክልሉ የሥራ ቋንቋ ውጪ በመናገራቸው ብቻ፣ አንዳችም
ተቋማዊ ውክልና እንዳያገኙ ማድረጉ፣ ከየአካባቢዎቹ በግፍ ለተፈናቀሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው መነሻ ሆኗል፡፡
አዲሱን የአዲስ አበባ የማስፋፊያ ዕቅድ ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞም ሌላ ቅርፅ ወደመያዝ መሻገሩ አንዱ
ሰሞነኛ ማሳያ ነው፡፡ በምዕራብ ወለጋ ለረዥም ጊዜ ኑሯቸውን መስርተው የነበሩት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አካባቢውን
ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸው የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየክልሎቹ ዘውጎች ‹‹መጤ›› ያሏቸውን
ማባረር ላለመጀመራቸው እርግጠኛ መሆን የምንችልበት ምንም አይነት ዋስትና የለንም፡፡ እናሳ! ይህ አይነቱ ክልልን
ከ‹‹መጤ›› ዘውግ የማንፃት ሂደት ማቆሚያው የቱ ጋ እንደሆነ ማን ሊገምት ይቻለዋል? ዘግናኝ ደም መፋሰስስ ሳያስከትል
ይህንን ክፉ ድርጊት መሻገር የምንችለው እንዴት ነው?

 እንግዲህ ይህ ሁሉ የፍርሰት መርዶ እየተሰማ ያለው፣ የሥርዓቱ ሰዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ለዚህ ከፍታ የበቁበትን ሃያ
ሶስተኛ የድል ዓመት በፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በሚሉበት ዋዜማ ላይ ቆመን ቢሆንም ‹‹ጊዜው ከቶም ቢዘገይ አልረፈደም››
እንዲሉ፤ ተገፍቶ ገደል ጠርዝ የተንጠለጠለውን የኢትዮጵያን ህልውና በደለደለ መሰረት አፅንተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር
አንዳች እርምጃ መውሰዱ ብቸኛ አማራጭ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህ ዘመን ለጣለው ትውልዳዊ የማንነት ዕዳ ክንውን
ቀዳሚው ተግባር ኢህአዴግን ‹‹በቃህ!›› ብሎ ማስቆም እንደሆነም መቀበል የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ግና፣ ይህ ሳይሆን
በወታደራዊ ጡንቻ ካሳለፍናቸው ዓመታት ጥቂቱን እንኳ እንዲሰነብት ከፈቀድንለት፣ የደም ባሕር ሲያጥለቀልቀን ቆመን
ለመመልከት ተስማምተናል ማለት ነው፡፡

ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
May 18, 2014


የወያኔን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማፋጠን ኅብረታችን ይጠንክር!!!



ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በግፍ ሕይወታቸው ባጡ ዜጎች መርዶ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እና ቁጭት ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይመኛል። ህወሓት እና አጋፋሪው ኦህዴድ በነዙት ሽብር ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ፣ የተደበደባችሁ እና ለእስር የተዳረጋችሁ ወገኖቻችንም ህመማችሁም እስራችሁም የሁላችንም ነው። መላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ከእናንተ ጋር ተገድሏል፣ ቆስሏል፣ ተደብድቧል፣ ተግዟል፣ ታስሯል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ግንቦት 7 ደጋግሞ ያስገነዝባል።በህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ ያልተበደለ የኢትዮጵያ ክፍል የለም። የወያኔ አጋፋሪ የሆነው አህዴድ የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ሕፃናትንና አዛውንትን ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ፣ ሌላው አጋፋሪ ብአዴን ደግሞ በጎንደርና አካባቢው ተመሳሳይ ጭፍጨፋዎችን አካሂዷል። ወያኔ ከፋሺስት ኢጣልያ ወርሶ ለሃያ ዓመታት በትጋት ያራመደው “የከፋፍለህ ግዛ” ፓሊሲ ምርት እነሆ ዛሬ በዓይኖቻችን እያየን ነው። ፋሽስት ጣልያን ጀምሮት የነበረውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ስትራቴጄ ለማጠናቀቅ ህወሓት በጥድፊያ ላይ ነው። ይህን እኩይ ዓላማ ማስቆም የሁላችን ኃላፊነት ነው።

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ሕ.አ.ግ/ የተሰጠ መግለጫ


በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጅምላ ግድያ በጥብቅ እናወግዛለን

ወታደራዊ ጡንቻውን እና የስለላ መረቡን መከታ በማድረግ የስልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ቆርጦ የተነሳው የወያኔው የማፊያ ቡድን፣ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያነጣጠረውን የጥፋት ኢላማ እና የቀሰረውን ጣት ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ብልሹው ስርዓት በፈጠረው የፍትሕ ጉድለት እና የአስተዳደር በደሎች የተነሳ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና አመጾች መቀስቀሳቸው የግድ ነው። በማስተር ፕላን ሽፋን የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን ለመጨፍለቅና የአርሶ አደሮችን ህልውና የሚፈታተነውን የወያኔን የጥፋት ፖሊሲ በመቃወም የምዕራብ ሸዋ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ ቢወጡም የተማሪዎቹ የፍትሕ ጥያቄ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ወከባ፣ እስራት እና ግድያ በተማሪዎች ላይ ተፈጽሟል።

ሰብዓዊነት ፍጹም ያልፈጠረበት ይህ ነፍሰ ገዳይ ቡድን በእብሪትና በማን አለብኝነት የንጹሃን ተማሪዎችን ደም በከንቱ ማፍሰሱ ሳይበቃ ይባስ ብሎ የተማሪዎችን ፍትሐዊ ጥያቄ ወደ ተቃዋሚ ሀይሎች ማሳበቡ ሥርዓቱ በሕዝብ ላይ ምን ያህል ንቀት እንዳለው በገሀድ ያሳያል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በኢንቨስትመንትና በማስተር ፕላን ሽፋን ዜጎችን ማፈናቀል፣ ማዋከብ እና ጅምላ ግድያን መፈጸም አሳፋሪ ወንጀል መሆኑን እየገለፀ በተማሪዎች ላይ የተወሰደውን የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ ያወግዛል።

ይኸው እብሪተኛ ቡድን በሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን በደልና ሰቆቃ አጠናክሮ ቀጥሏል። የጎንደር፣ የአፋር፣ የጋምቤላና የኦጋዴን አርሶ አደር ወገኖቻችን ከእርሻ መሬታቸው ተፈናቅለው አውላላ ሜዳ ላይ ተጥለዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል። አሸባሪው የወያኔ ቡድን የምርጫ ድራማ በተቃረበ ቁጥር እና ለተዘፈቀበት ውስጣዊ ቀውስና ውጥረት፣ ዜጎችን ማሸበር እና ማስፈራራት እንዲሁም ብቀላና ግድያን መፈጸም ወያኔ እንደ ማስታገሻ መድሀኒት እንደሚጠቀምበት ለማናችንም ቢሆን የተሰወረ ሚስጥር አይደለም። በመሆኑም ኢትዮጵያንና ዜጎቿን ከወያኔው የስጋት ቀጠና ለማውጣትም ሆነ በሀገሪቱ ምድር ስርዓቱ የቀበረውን የዘረኝነት ፈንጅ ማምከን ዛሬ ወቅቱ የጠየቀው ሀቅ ነው። ስለሆነም ወያኔ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያነጣጠረውን የጥፋት ኢላማ ለማክሸፍ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሞራላዊና ህሊናዊ ግዴታ የሚጠበቅ በመሆኑ መላ ኢትዮጵያዊ በተጀመረው ሕዝባዊ ተጋድሎ የበኩሉን አስተዋጾ ያደርግ ዘንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወገናዊና ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል።

የህዝብ ወገናዊነቱን እና ጥቃት መላሽነቱን በድርጊት እያስመሰከረ የመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በነፍሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ለጠላትም ለወገንም ያስገነዝባል።

                          አንድነት ኃይል ነው!!!

                                                  የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር


Sunday, May 18, 2014

አኖሌ…..የባህር ዳር ነውር….አምቦ እና ግምቢ


ኢትዮጵያችን አደጋ ላይ ነች። የአደጋዋ ምንጭ ህወሃት እና ህወሃት ነው። ህወሃቶች በአገራችን ላይ የመዘዙት የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። ከበቀል ስሜታቸው ጋር መቶ ዓመት የመንገስ ምኞት አላቸው። ምኞታቸውንም እውን ለማድረግ የንፁሃን ደም ለህወሃቶች መስዋዕት ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል። እስከ ዛሬ ብዙ ኦሮሞዎችና አማሮች መሥዋዕት ሁነዋል። የመስዋዕቱ ምንጭ እንዳይደርቅ አሩሲ ላይ አኖሌ ቁሟል።እርሱን ተከትሎ ባህር ዳር “አማራና ኦሮሞ” ኳስ እንዲጫወቱ ሁኖ ነውር የሆኑ ስድቦች እየተነቀሱ ወጥተው በኢቲቭ እንዲተላለፍ ተደረገ። ይሄን ተከትሎ የመሬት ቅርምቱ ተከሰተ። አምቦና ግምቢ ላይ በህወሃት-ኦህዴድ ፊታውራሪነት የንፁሃን ደም በከንቱ ፈሰሶ ህወሃት የለመደውን ምሱን አገኘ።

ህወሃት የአኖሌ ሃውልት እንዲሰራ ሲፈቅድ የሚታየው በዚህ ሃውልት ምክንያት አብረው የኖሩ ህዝቦች ደም ተቃብተው በጠላትነት ሲቆሙ ነው።የአኖሌ ሃውልት በህወሃት-ኦህዴድ እጅ ሁኖ የሚሰብከው አብሮነትን ሳይሆን ልዩነትን ነው። ፍቅርን ሳይሆን ጥላቻን ነው። የአኖሌን ሃውልት የሚመስል ሌላ ሰማይ ጠቀስ ኃውልት በመቀሌ ከተማ ለትውልድ የሚተላለፍ ቂምን እየሰበከ ቁሟል። ስሙንም “የሰማዕታት” ሃውልት ብለው ይጠሩታል። ከአሩሲው አኖሌም ሆነ ከመቀሌው ሠማዕታት ሃውልት ትውልዱ የሚያተርፈው ቂም እና በቀል ነው። እነዚህ ሁለት ኃውልቶች ሠላምን አይሰብኩም፤ አብሮ መኖርን አያስተምሩም። ሃውሎቶቹን ያየ ግማሹ ቂም ይቋጥራል፤ ገሚሱ ይገረማል፤ ሌላውም የአገሪቱን መፃኢ ሁኔታ እያሰበ ይተክዛል። ህወሃቶች እጅግ ብዙ አሰቃቂ፤ አስገራሚ እና አሳዛኝ ነውሮችን በዚያች አገር ላይ መፈፀማቸው የታወቀ ነው።

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ



የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።

በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።




ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ


የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

ትኩረት በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ላይ ይሁን!!!


ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች። በአንድ በኩል ህወሓት እና አገልጋይ ድርጅቶቹ በተለይም ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ የተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለመሸፈን የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ ለመጫር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎችና ጥቃቶች እንዲኖሩ በካድሬዎቻቸውና በቅጥረኞች አማካይነት እየጣሩ ነው። በዚህ እኩይ ተግባር ውስጥ ባለማወቅ በስሜት ብቻ የሚነዱ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ ወገኖችም እየተሳተፉበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በዘውግም ይሁን በአገር ደረጃ የተደራጁ የፓለቲካ ድርጅቶች መሪዎች የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና ግብረአበሮቹ ስለመሆናቸው የጠራ አቋም

Saturday, May 17, 2014

የዛሬው የጋዜጠኞቹ እና የዞን 9 ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ – “ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ተደብድቤያለሁ”

አዲስ ጉዳይ መጽሔት ዘገባ ከአዲስ አበባ
"የሥነ ልቦና ጫና ደርሦብኛል"
ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዬርጊስ



ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006 በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት 3 ጋዜጠኞች እና 3 ብሎገሮች ነበሩ፡፡ ፖሊስየተጠርጣሪዎቹን ጉዳዩ ከወንጀል ወደ ሽብር በማሻሻሉ እና ምርመራዬን አላጠናቀቀኩም በማለቱ የ28 ቀን ተጨማሪ የምርመራጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ሦስት ሰዓት ይሰማል የተባለው ችሎት 4፡30 አካባቢ የተጀመረ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር118721 የተከሰሱት ሦስት ተጠርጣሪዎች ኤዶም ካሣዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያ ቀርበዋል፡፡

በዛሬው ችሎት ከእየአንዳንዱ ታሳሪ ሦስት የቤተሰብአባላት ወደ ችሎት ገብተው እንዲታደሙ ተፈቅዶነበር፡፡ ፖሊስ ክሱን ከወንጀል ወደ ሽብር ከፍ አድርጎቀርቧል፡፡ ምርመራዬን ስላላጠናቀቅኩ የተጨማሪ የ28ቀናት ጊዜ ይሰጠኝ ብሎም ለችሎቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

Friday, May 16, 2014

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ ዛሬ በድብቅ ሊፈረም ነው!



የኢትዮ ሱዳን ዳር ድንበር በግልፅ የተከለለ እንዳልሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚጠቀሙት መሬት የኢትዮጵያ እንደሆነ ሲወሰድ ሱዳናውያን የሚገለገሉበትም የሱዳን ነው ተብሎ ይታሰባል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያን አርሶአደሮችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ለሱዳን ማስረከቡ ይታወቃል። ብዙ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ተፈናቅለዋል፣ የተወሰኑ ተለዋጭ መሬት ሲሰጣቸው ምንም ያላገኙም አሉ።

ድንበሩ ብዙ ዉዝግብና ተቃውሞ ያለው ሲሆን የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳኖች ጋር በመተባበር በድብቅ ለመከለል ተስማምቷል። እንዲህ ነው የተደረገው፥ በድንበሩ አከባቢ የሚገኙ ኗሪዎች (የኢትዮጵያና የሱዳን) ድንበራቸውን አይተው ክለላውን ይፈፅማሉ፣ ይፈራረማሉ። ለሱዳን የተሰጠው መሬት ታውቋል። ሁሉም ነገር በኢህአዴግና የሱዳን መንግስት አልቋል። አሁን "የሀገር ሽማግሌዎች" እንዲፈርሙ እየተደረገ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች እንዲፈርሙ የተፈለገበት ምክንያት የድንበር ክለላ የተከናወነው በኗሪዎች ነው እንዲባል ነው። ለሌላ ግዜም ምስክር ሁነው እንዲቀርቡ ነው።

በዚህ መሰረት በድንበሩ አከባቢ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች ማይካድራና በረከት የተወሰኑ ሰዎች በካድሬዎች ተመርጠው "ኮሚቴ" ተሰኝተው ዛሬ ግንቦት 8, 2006 ዓም እንዲፈርሙ ወደ ሱዳን ድንበር ተጉዘዋል። እነዚህ ኮሚቴ ተብለው የተመረጡ ሰዎች ስለ ድንበሩ ይሁን አከባቢው እውቀት የሌላቸው፣ የአከባቢው ኗሪዎች ሳይሆኑ በቅርብ ግዜ ባከባቢው መሬት የተሰጣቸው ሰፈርተኞች ናቸው። ዕድሜየቸውም ከአርባ በታች ነው፣ ትምህርት የላቸውም፣ የድንበሩ ታሪክ አያውቁም፣ መሬት ስለተሰጣቸውና በካድሬዎች ስለታዘዙ ብቻ ሊፈርሙ የሚችሉ ናቸው። ስለዚህ የሀገር ሽማግሌዎች ሊባሉ አይችሉም። ምክንያቱም ሰፈርተኞች እንጂ ኗሪዎች አይደሉም፣ ወጣቶች ናቸው (ድንበሩ ላያውቁት ይችላሉ)፣ ትምህርት የላቸውም (የድንበር ጉዳይ ምን ያህል ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ ላይረዱ ይችላሉ) ወዘተ። ዛሬ እንዲፈርሙ የተወሰዱት በድብቅ መሆኑ ነው።

የድንበር ጉዳይና ሌሎች የሑመራ አከባቢ ኗሪዎች በማየሉ ተቃውሞ እየተቀሰቀሰ በመሆኑ ባከባቢው ተገኝቶ መረጃ ማሰባሰብ አስቸጋሪ እየሆነ ነው። የመንግስት አካላት ኗሪዎች ለሌሎች አካላት መረጃ እንዳይሰጡ እያስፈራሩ ነው። መረጃ መሰብሰብም አይፈቀድም። በዚሁ አጋጣሚ ግርማይ ወልደግዮርግስ የተባለ የድምፂ ወያነ ሬድዮ ጋዜጠኛ ባስተዳዳሪዎች ከቀረቡለት አራት ካድሬዎች ዉጭ ሌሎች ኗሪዎችን በማነጋገሩ ምክንያት ባለስልጣናት ፖሊስ ጠርተው አስረውታል። የድምፂ ወያነ ሬድዮ ጋዜጠኛ ህዝብን ሳንፈቅድልህ አገጋግረሃል ተብሎ ነው የታሰረው።

በሑመራ አከባቢ ብዙ ተደራራቢ ችግሮች አሉ። ሕገወጥ የመሬት ሽንሸና እየተደረገ ነው። ኗሪዎችን ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ስርዓቱ ያገለግላሉ ለተባሉ ሰዎች መሬት እየተሰጠ ይገኛል። ለምሳሌ አቶ ካሕሳይ ገብረሚካኤል የተባሉ ያከባቢው ኗሪ መሬታቸው ተወስዶ ለሌላ የህወሓት ካድሬ ዉሽማ ተሰጥቷል። ፍትሐዊ ያልሆነ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

በድንበሩ ጉዳይ በድብቅ እየተፈረመ ያለው ነገር ተቀባይነት የለውም። ለሱዳን የሚሰጥ መሬት መኖር የለበትም። ተግባሩ ሕገወጥ ነው። ኢህ አዴግም ለተግባሩ ይጠየቃል።

አብርሃ ደስታ

የመደብ ወይስ የብሄር ጭቆና?!



አብርሃ ደስታ እንደዘገው፦

እንዲህ ተጠይቋል????

"ባለፉ ስርዓታት የነበረ የማሕበረ ፖለቲካ መዋቅር የመደብ የትግል (ጭቆና) መሰረት ያደረገ ነበር ወይስ ብሄር?"

ባለፉ ስርዓታት ጭቆና ነበረ (አሁንም አለ)። በኢትዮጵያ ታሪክ በህዝብ የተመረጠ ህዝብን ለማገለግል የተነሳ መንግስት አልነበረም (የለም)። ስለዚህ ጭቆና አለ። ጭቆናው ምን መሰረት ያደረገ ነው? ብሄር ወይስ መደብ? በኔ እምነት ጭቆናው ከሁለቱም ዉጭ ነው። በኢትዮጵያ የመደብ ጭቆና አልነበረም (የለም)፤ የብሄር ጭቆናም አልነበረም (የለም)። የነበረው (አሁንም ያለው) ጭቆና የኤሊት (Elite) ጭቆና ነው።

እስካሁን ድረስ የመደብ ፖለቲካ የለንም። የመደብ ፖለቲካ ከሌለ የመደብ ጭቆናም የለም። የብሄር ጭቆናም አልነበረም፣ የለም፣ ሊኖርም አይችልም። የመደብ ጭቆና ግን ለወደፊቱ ሊኖር ይችላል።

ያለፉ የኢትዮጵያ ገዥዎች ስልጣን ለመያዝ እንዲሁም በስልጣን ለመቆየት ሲሉ በህዝቦች ላይ በደል አድርሰዋል። በደል ሲያደርሱ ብሄር ወይ መደብ መሰረት አድርገው አይደለም። መደብ ጭራሽኑም አልነበረም፣ የለም። ብሄር ነበር፤ ግን ጭቆናው ብሄር መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስልጣን መሰረት ያደረገ ነበር፣ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ Class Based Or Nation Based Struggle ሳይሆን Elite vs People Based Power Struggle ነው።

ገዥዎች ስልጣን መያዝና እስከ ህልፈታቸው በስልጣን መቆየት ይፈልጋሉ። ለስልጣናቸው ሲሉ ታድያ ይደግፈናል የሚሉትን የሕብረተሰብ ክፍል ይጠቅማሉ፤ ለስልጣን አደጋ ነው በሚሉት ህዝብ ወይ ግለሰብ ደግሞ ጉዳት ያደርሳሉ፤ ስልጣናቸውን ለማጠናከር። ግን በፖለቲካ አንድን የሕብረተሰብ ክፍል መጥቀም አይቻልም፣ ይከብዳልና። ስለዚህ በሕብረተሰቡ ስም የተወሰኑ ግለሰቦች እንዲጠቀሙ ይደረጋል። ግለሰቦቹ ሲጠቀሙ የመጡበትን ሕብረተሰብ እንደተጠቀመ ተድርጎ ይታሰባል: ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሲባል። ህብረተሰቡ በስልጣን ላይ ያለ ስርዓት "የኛነት" ስሜት ያሳድራል። ለዚህም ፕሮፓጋንዳ ይሰራል። ምክንያቱም የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ነው መጥቀም የሚቻለው። ለስልጣን የሚረዳው ግን አብዛኝው ህዝብ ነው። ተጠቃሚ ግለሰቦች ታማኝ የስርዓቱ አገልጋዮች ይሆናሉ። በነሱ ታማኝነት ስርዓቱ ዕድሜው ያራዝማል።

ለስልጣን አደጋ የሚሆን ግለሰብ ወይ ማሕበረሰብ ደግሞ የጥቃት ዒላማ ይሆናል። የስልጣን ዒላማ የሚሆነው በመደቡ አልነበረም (በመደቡ ዒላማ ሊደረግ ይችላል ግን መደብ አልነበረም)። በብሄሩም አልነበረም። በግዜው ካልተመቱ የስልጣን ስጋት ይሆናሉ የተባሉትን ግለሰቦች ወይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይጠቃሉ፤ ብሄራቸው ምን ይሁን ምን። ግን በኢትዮጵያ ታሪክ አንዳንድ ብሄሮች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለምን? በብሄራቸው ምክንያት? አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ አይደሉም፤ ስጋት ይሆናሉ ስለተባሉ ብቻ ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጎዳትም የመጠቀምም መስፈርት ብሄር ወይ መደብ አይደለም፤ የፖለቲካ ታማኝነት (Political Patrimonial-ism) ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልምድ መሰረት የፖለቲካ ታማኝነት የሚገናኘው ከብሄር ጋር ነው። ሙሉ በሙሉ ባይባልም አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች የበለጠ ይተማመናሉ (ምክንያቱም ፖለቲካችን መርህ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስሜት መሰረት ያደረገ ነው። በስሜት መነዳት ደግሞ አለመሰልጠን ነው)። አማርኛ ተናጋሪ ስልጣን ከያዘ አማርኛ የሚናገረውን (ሌላ ቋንቋ ከሚናገር) የበለጠ ያምናል። ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞን የበለጠ ያምናል። ትግርኛ ተናጋሪ ትግራዋይን የበለጠ ያምናል። በዚህ መሰረት አማራኛ ተናጋሪ ስልጣን ሲይዝ አማራዎችን ያስቀድማል (ለስልጣኑ ሲል)። ሌሎች ደግሞ ቅሬታ ያድርባቸዋል። ከዛ ለስርዓቱ ታማኝ አይሆኑም። ታማኝ ካልሆኑ በጠላትነት ይፈረጃሉ። በጠላትነት ሲፈረጁ ተጎጂ ይሆናሉ። እነዚህ የስርዓቱ ተጠቃሚ የሚደረጉ ታማኞች ግለሰቦች ናቸው። ብሄር ሙሉ ተጠቃሚ ማድረግ አይቻልምና። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሙሉ ወይ የሀገር ህዝብ በሙሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ተጠቃሚዎች ታማኝ ግለሰቦች ናቸው። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሊሆኑ ይችላሉ። አንድን ብሄር ሌላኛው ብሄር እየበደለ ነው ይባላል። በዳዮቹ ግን ኤሊቶች (elites) ናቸው። ይህን ነገር ጉዳዩ የብሄር ጭቆና ያስመስለዋል። የብሄር ጭቆና ሊኖር ግን አይችልም።

ስለዚህ ባለፉ ስርዓታት (አሁንም ጭምር) በህዝቦች የሚደርስ በደል አለ። ይህንን በደል ብሄሮች የሚፈጥሩት አይደለም። ያለው በደል በብሄሮች ላይ የተፈፀመ የelites በደል ነው። ኦሮሞዎች የተበደሉ ኦሮሞ ስለሆኑ አልነበረም። ለተመሰረተው ስርዓት ተቀብለው አሜን ብለን እንዲገዙ ለማድረግ የተቃጣ ጥቃት ነው የተፈፀመባቸው። ስለዚህ ጥቃቱ ስልጣን መሰረት ያደረገ ነው። ዒላማው የፖለቲካ ታማኝነትን መሰረት ያደረገ ነው።

አማርኛ ተናጋሪ ንጉሶች ታማኝ ባልሆነ ማንም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ። ለዚህም ነው በሁሉም ህዝቦች (አማራን ጨምሮ) በደል የደረሰው። ትግርኛ ተናጋሪ ገዥዎች ታማኝ ባልሆነ ማንኛውም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ፤ ለስልጣን ሲሉ። ምሳሌ ህወሓት የትግራይ ልጆች በሆኑ እነ ስየ አብርሃ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አስገደ ገብረስላሴና ሌሎች ታጋዮች ላይ መጥፎ እርምጃ የወሰደው እነኚህ ሰዎች ትግርኛ ተናጋሪ ስላልነበሩ አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ ስላልሆኑ እንጂ።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ምድር የደረሰውን እንዲሁም እየደረሰ ያለው ጭቆና ብሄር ወይ መደብ መሰረት ያደረገ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነት መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያውያን ጭቆና የብሄር ወይ የመደብ ሳይሆን የፖለቲካ ነው።

የአሶሳው ግድያ የታቀደ ስለመሆኑ ተረጋገጠ


አብርሃ ደስታ እንደዘገበው፦ ባለፈው ሳምንት 9 የትግራይ ተወላጆች በቤኑሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ታርደው መገደላቸው ይታወሳል። አንድ ሌላ የታክሲ ሹፌርን በጥይት ተገድሏል (ከትግራይ)። በአንድ የዕጣን ድርጅት ይሰሩ የነበሩ ሦስት የአማራና ኦሮምያ ክልል ተወላጆችን ተገድለዋል። ትናንት ሐሙስ ግንቦት 7ም አንድ መኪና በታጣቂዎች ተይዞ በእሳት ጋይቷል። በተሳፋሪዎቹ የደረሰ ጉዳት በትክክል ባይታወቅም አንዲት ተሳፋሪ ግን ቆስላ ተገኝታለች።

በ9ኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግድያ ለማጣራት በመኮርኩት መሰረት ግድያው ሆን ተብሎ ታቅዶ የፈፀመ ስለ መሆኑ አረጋግጫለሁ። ሙሉ መረጃ ያላቸው አሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዳረጋገጥሉኝ ከሆነ ዓማፂ ቡድኑ የትግራይ ሰዎችን አርዶ ለመግደል ማቀዱ ይታወቅ ነበር። የወረዳው አስተዳዳሪ ይህን መረጃ ከግድያው በፊት ደርሶታል። ባከባቢው የሚገኘው የመከላከልያ ሰራዊት አዛዥም ግድያ እንደሚፈፀም ተነግሮታል። ባጠቃላይ መንግስት ግድያው በተመለከተ ሙሉ ቅድመ መረጃ ነበረው። መንግስት መረጃ እያለው ግድያው መከላከል አለመቻሉ ኗሪዎችን አሳዝኗል። በአሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መንግስት ተገቢውን ፀጥታ የማስከበር ተግባር አለመፈፀሙ አስገርሟቸዋል። መንግስት ለስልጣኑ እንጂ ለህዝብ ደህንነት እንደማይተጋም አስረግጠዋል። አሁንም አሶሳ አከባቢ የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ስጋት ዉስጥ ናቸው።

መንግስት በትግራይ ልጆች ላይ ግድያ እንደሚፈፀም እያወቀ ለምን መከላከል እንዳልቻለ ለህዝብ መግለፅ ይኖርበታል። የሰለማዊ ሰዎች ደህንነት መጠበቅ ባለመቻሉም ይቅርታ ይጠይቅ፣ ተገቢውም ካሳ ይክፈል።

ዝክር ለግንቦት 7 1997 እና ለግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፍላጎቱን የመግለጽ አንፃራዊ ነፃነት አግኝቶ የነበረበት የግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ምርጫን ስናስብ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ መመዘናችን አይቀርም። ያኔ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ እጁ መዳፍ ቀርባ ትታየው የነበረችው ድል እስከዛሬ አልጨበጣትም። ትግሉ ግን ቀጥሏል። የዛሬው ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከያኔው በበለጠ ከታሪክና ከራስዋ ጋር የታረቀች አገር የመመሥረትን ርዕይ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት መስጠትን የሚጠይቅ ሆኗል።ወያኔ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለአለፉት አርባ ዓመታት ሲያብላላው የቆየው፤ በመንግሥት ሥልጣን በቆየባቸው ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ በፓሊሲ ደረጃ ሲያስፈጽመው የቆየውን የዘር ፓለቲካ አስከፊ ውጤት አሁን እየታየ ነው። ይህ የዘር ፓለቲካ ራሱ ወያኔን ያጠፋዋል። ችግሩ ግን የዘር ፓለቲካ ወያኔን ነጥሎ አያጠፋም፤ ከወያኔ ጋር አገራችንንም ሊያጠፋ ይችላል። ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ጉዳይ ደግሞ የዘር ፓለቲካ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። በጎረቤት አገራት ውስጥ ያየነውን ዓይነት የእርስ በርስ እልቂት ወደ አገራችን ለማምጣት ህወሓትና ኦህዴድ ተግተው እየሠሩ ነው። ሌሎች የወያኔ ተቀጥላ ድርጅቶችም የዚህ ትልቅ የጥፋት ፕሮጀክት አካል ናቸው።የግንቦት 7 1997ቱ ብሩህ ተስፋ በፋሺስቱ ወያኔ የግፍ አፈና ሲጨልም፤ ያ ተስፋ እንዲያንሠራራ በግንቦት 7 2000 ዓ.ም. የተቋቋመው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ የኢትዮጵያን ተስፋ ለማጨለም ከተነሱ ኃይሎች በተፃራሪ በመቆም የሕዝብና የአገር አለኝታነቱ ማረጋገጥ ይኖርበታል።በዚህም ምክንያት፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የሆንን ሁሉ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ይኖርብናል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፒቴን አስመራ ላይ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀለ፤ * መንግስት አላስተባበለም



ዘ-ሐበሻ እንደዘገበው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባላት ገዢውን የኢሕአዴግን መንግስት በመክዳት ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚያደርጉትን ስደትቀጥለዋል። የኤርትራ ሚዲያዎች የመንግስታቸውን ቃል አቀባይ በመጥቀስ እንዳስነበቡት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሚግ 23 አብራሪየሆነው ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስ ስርዓቱን ጥሎ አስመራ ገብቷል።

Thursday, May 15, 2014

9 የትግራይ ተወላጆች በአሶሳ ተገደሉ

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው፦
ባለፈው ሳምንት የጉልበት ሥራ ለመስራት በአንድ ኮንትራክተር ተቀጥረው ወደ አባይ ግድብ በደህንነት መኪና ሲጓዙ ከነበሩ 28 የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ ዘጠኙ ታርደው ሲገደሉ የተወሰኑም ቆስለዋል። ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ አንድ የትግራይ ተወላጅ በተመሳሳይ ተገድሎ ተገኝቷል። ቀጥሎም በአንድ ድርጅት ሲሰሩ የነበሩ ሦስት ሰራተኞች መገደላቸው ተሰምቷል። ገዳዮቹ ከኢህአዴግ ጋር የተጣላ የአንድ ዓማፂ ቡድን አባላት ናቸው። ባከባቢው የፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ ሰራዊት አባላት ቢገኙም ወንጀሉ መከላከል እንዳልቻሉ ታውቋል። ሁኔታው ለማረጋጋት ሲሉ አቶ ፀጋይ በርሀና አቶ አዲሱ ለገሰ ወዳከባቢው ቢጓዙም የተለመደ ፖለቲካ ከመስበክ የዘለለ ነገር አላደረጉም። መንግስት ፀጥታን ማስከበር ይገባዋል። ደግሞ ሰለማዊ የቀን ሰራተኞች በደህንነት መኪና መጫን ተገቢ አይደለም። በደረሰ ጉዳት ጥልቅ ሐዘን ይሰማናል።
ወላዲት ትግራይ መዓዝ ይኾን ሓዘንኪ ዘብቅዕ?፦


በአዲስ አበባ ካርታ ዙሪያ የተቃወሙ ሃሳብ ያቀረቡ የኦህዴድ አባላት እየታደኑ ነው



ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የህወሃት አጀንዳ ነው በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩትን የኦህዴድ አባላት ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመሩን  ከኦህዴድ ምንጮች የደረሱን ዜና አመለከተ።
ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉት እነዚህ አባላት እንደተናገሩት፣ ድርጅቱ አዲሱን የአዲስ አበባ ፕላን በተመለከተ አባላቱ እንዲወያዩበት ቢያስደርግም፣ በውይይቱ ወቅት የተቃውሞ ሃሳባቸውን ሲያሰሙ የነበሩትን ሰዎች ማሰር ተጀምሯል። በርኴታ የድርጅቱአባሎች ደግሞ  ከእስራት ለመሸሽ  መደበቃቸው ታውቋል።
ኦህዴድ የህወሃት ደጋፊና የህወሃት ተቃዋሚ በሚል ከሁለት መከፈሉን ተከትሎ የህወሃት ደጋፊው ወገን ደጋፊ ያልሆነውን ወገን እያሳደደው መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚደረገው ጥረት ፣ የህወሃት ደጋፊ በሆኑ የኦህዴድ አባላት ተጠናክሮ ቀጥሎአል።
ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳበትን ተቃውሞ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌለውን የብሄር አጀንዳ በማንሳት ብሄሮች እርስ በርስ እንዲጣሉ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አባሎቹ ተናግረዋል።
በዩኒቨርስቲዎች ሆን ተብሎ አሉባልታ የሚነዙ ካድሬዎች መሰማራታቸውን እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በቡድን የተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶችንበሌሊት ወደ ሌሎች ብሄር ተወላጆች ቤት በመላክ ግጭት እንዲያነሱ በኳድሬዉች ግፊት እየተደረገመሆኑን እነዚህ ወገኖች አክለው ገልጸዋል።
በምስራቅ እና በምእራብ ወለጋ ኦህዴድ ያደራጃቸው ወጣቶች የሰዎችን ቤቶች እየመረጡ በሌሊት  ከመደብደብ ጀምሮ እስከ ማቃጠል መድረሳቸውን እንዲሁም ንብረቶችን እየዘረፉ እንደሚገኙ የሚናገሩት አባሎቹ፣ ህዝቡ በትእግስትና በተለመደው የመከባበር ባህሉ ይህን ችግር እንዲያልፈው አሳስበዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ከመቶ በላይ ተማሪዎች ሲለቀቁ፣ 40 ተማሪዎች ግን አመጹን ከቅስቅሳችሁዋል በሚል በእስር ላይ እንዲቆዩና ምርምራ እንዲደረግባቸው ፖሊስ መወሰኑ ታውቋል።
በተመሳሳይ ዜና ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡትን ተማሪዎች አስጠግተው የነበሩ ቤተክርስቲያኖች፣ ተማሪዎቹን እንዲያስወጡ _ክልሉን በሚመራው የምስራቅ እዝ  ወታደራዊ አዛዦች ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ማንነታቸውን ያልገለጹ የምስራቅ እዝ ባለስልጣናት ቤተከርስቲያኑዋ በአስቸኳይ ተማሪዎችን እንድታስወጣ ትእዛዝ ከሰጡ በሁዋላ ተማሪዎቹንሸራ በለበሱ መኪኖች ተጭነው መውሰዳቸውን ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተሉ ወገኖች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ሰኞ እለት ትምህርት ቢጀመርም በግቢው የሚገኙ ተማሪዎች ቁጥር አሁንም እጅግ አነስተኛ ነው።
በኦሮምያ ክልል ያለውን የጸጥታ ችግር በተመለከተ የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ

ኢሳት ዜና :-መንግስት በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ጓደኞቻቸው እንዲፈቱላቸው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ የነበሩ የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ወደ ግቢው ዘልቀው በገቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሲደበደቡ መዋላቸውን ተማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች  ለኢሳት ተናግረዋል።
የግቢው ተማሪዎች ጥያቄያቸውን  ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማቅረብ ላይ ሳሉ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ውስጥ ሰብረው በመግባትና የጪስ ቦንብ በመወርወር ተማሪውን በሰደፍና በዱላ መደብደባቸውን ተማሪዎች ገልጸዋል።
ተማሪው እንደሚለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ታፍሰው ደዴሳ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ወደሚገኝ እስር ቤት መጋዛቸውን ገልጿል።
በወለጋ የሁሉም አካባቢ ተማሪዎች በአንድነት ድምጻቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን አክሎ ገልጿል
በሌላ ዜና ደግሞ ከአዳማ ዩኒቨርስቲ 5 ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
የደህንነት ሃይሎች ወደ ግቢ በመግባት ከ20 በላይ ተማሪዎችን ይዘው የወሰዱ ቢሆንም፣ 5 ተማሪዎችን አስቀርተው ሌሎችን መልቀቃቸው ታውቋል። ከ20 በላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በሌላ ዜና ደግሞ በጊምቢ እና በምእራብ ወለጋ የሚኖሩ ከሌሎች አካባቢ የመጡ ሰዎች መረጋጋት መጀመራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል
የኢህአዴግ መንግስት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ የትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ የተለያዩ አሉባልታዎችን የሚነዙ ካድሬዎችን ማሰማራቱን ኢሳት በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያመንግስትየፕሬዚዳንትሳልቫኪርንንግግርለማስተባበልሞከረ





 ኢሳት ዜና :-የደቡብሱዳንፕሬዝደንትሳልቫኪርባለፈውአርብ  አዲስአበባውስጥከተቀናቃኛቸውዶ/ርሪክማቻርጋርየሰላምስምምነቱንየፈረሙትጠቅላይሚኒስትርኃይለማርያም “አስርሃለሁ” ብለውስላስፈራሩኝነውሲሉየተናገሩት “ለቀልድነው” ሲልየኢትዮጵያመንግስትመግለጹን ሰንደቅ ዘግቧል።
ሳልቫኪርከተቀናቃኛቸውዶርሪክማቻርጋርየሰላምስምምነትፈርመውወደሀገራቸውእንደተመለሱጁባየአየርማረፊያተሰብስበውለሚጠብቋቸውሰዎችበሰጡትመግለጫየኢትዮጵያውጠቅላይሚኒስትርኃይለማርያምደሳለኝእሳቸውንምሆነተቀናቃኛቸውንየሰላምስምምነቱንሳይፈርሙከአዲስአበባንቅንቅእንደማይሉእንዳስጠነቀቋቸውተናግረው ነበር።
አቶሀይለማርያምዶ/ርማቻርንባናገሩበትዕለትጠዋትእሳቸውንም፦ “ይሄንንስምምነትካልፈረምክአስርሃለሁ” እንዳሏቸውየጠቀሱትሳልቫኪር፤ እሳቸውምበምላሻቸው “በዚህችጥሩሀገርእኔንካሰርከኝእርግጠኛነኝጥሩምግብይቀርብልኛል።ስለዚህወደጁባመመለስአያስፈልገኝም።በነፃምትመግበኛለህ” ብለውመመለሳቸውንነውየገለጹት።
ይህየሳልቫኪርመግለጫብዙዎችንያስገረመሲሆን፤የኬንያውንደይሊኔሽንንጨምርበበርካታሚዲያዎችሽፋንአግኝቷል።ነገሩማነጋገሩንበቀጠለበትበአሁኑወቅትሰንደቅሳምንታዊጋዜጣስለጉዳዩጥያቄያቀረበላቸውየጠቅላይሚኒስትርሀይለማርያምደሳለኝቃልአቀባይአቶጌታቸውረዳ፤<< ፕሬዝዳንቱይሄንንቃልየተናገሩትየሰላምስምምነቱንበማስፈራራትናበጫናመፈረማቸውንለማመልከትሳይሆንለቀልድሲሉ  ነው>> በማለት ምላሽሰጥተዋል።
<<የፕሬዝዳንቱአነጋገርየሰላምስምምነቱንአስፈላጊነትበተመለከተያላቸውንቁርጠኝነትለመግለፅእንጂንግግራቸውስምምነቱንበግዴታየተፈፀመለማስመሰልአይደለም፤ሆኖምሚዲያዎችግንሁኔታውንአሉታዊበሆነመንገድማራገባቸውየተለመደነው፤ኢትዮጵያሁለቱንተቀናቃኝወገኖችየሰላምንአቅጣጫእንዲከተሉጥረቷንትቀጥላለች።የእነሱሰላምየእኛምሰላምመሆኑንበመረዳትበተሟላመልኩተሳትፎአችንንእንቀጥላለን>> ሲሉምአቶጌታቸውአክለዋል።
ፕሬዚዳንትሳልቫኪር እስካሁን ድረስ “ለቀልድስልየተናገርኩትነው>> በማለት ማስተባበያ አልሰጡም።