Wednesday, January 25, 2017

በኩዌት አንድ ኢትዮጵያዊትን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ አገር ዜጎች በስቅላት ተቀጡ

ኢሳት (ጥር 17 ፥ 2009)
የኩዌትት መንግስት አንድ ኢትዮጵያዊትን ጨምሮ ሰባት የተለያዩ ሃገራት ዜጎችን ዛሬ ረቡዕ በስቅላት የሞት ቅጣት መፈጸሙን የሃገሪቱ ዜና አገልግሎት ኩና ዘገበ።
ከአንድ ኢትዮጵያዊት በተጨማሪ ሁለት የኩዌት፣ ሁለት የግብፅ፣ አንድ የባንግላዴሽ፣ እና አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ እንዲሁም ሰዎችን በማገት ድርጊት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ድርጊቱ ሊፈጸምባቸው መቻሉን የኩዌት መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

በደቡብ ክልል በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሻራ በሚባለው አካባቢ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ አርሶአደሮች ከተማውን ለማስፋት በሚል ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ በመደረጉ ለችግር ተጋልጠዋል

ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሻራ በሚባለው አካባቢ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ አርሶአደሮች ከተማውን ለማስፋት በሚል ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ በመደረጉ፣ ብዙዎች አካባቢውን ጥለው ሲሰደዱ ሌሎች ደግሞ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተዳርገዋል። ለከተማው መስፋፋት በሚል አርሶአደሮች ከፍያ ሳያገኙ መሬታቸውን እንዲለቁ መደረጉን በመቃወም አቤቱታ ቢያሰሙም “ መሬት

ከጎንደር ወደ መቀሌ እቃ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ወለቃ በምትባለዋ መለስተኛ መንደር ላይ ሲደርስ በቦንብ በመመታቱ መኪናውም ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዞ ወድሟል።

ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ረቡዕ ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ ከጎንደር ወደ መቀሌ እቃ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማው በ10 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ወለቃ በምትባለዋ መለስተኛ መንደር ላይ ሲደርስ በቦንብ በመመታቱ መኪናው እስከነጭነቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዞ ወድሟል። ምንጮች እንደገለጹት ተሽከርካሪው ሌሊት ጎንደር ላይ እቃዎችን በመጫን ወደ መቀሌ ጉዞ በማድረግ ላይ ነበር። አስቀድሞ መረጃ የደረሳቸው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ተዘጋጅተው ሲጠብቁ እንደነበርና እነዚህ ሃይሎች ጥቃቱን እንደፈጸሙት የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ እንደተፈጸመ የእሳት አደጋ መኪና የደረሰ ቢሆንም፣ ቃጠሎውን መቆጣጠር ሳይችል ቀርቷል። የአጋዚ ወታደሮች አካባቢውን በመቆጣጠራቸው መኪናውን ምን እንደጫነ ለማወቅ ሳይችሉ መቅረታቸውንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Tuesday, January 24, 2017

የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ ካለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ በኦሮምያ 1200 ሲገደሉ፣ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታስረዋል

ጥር ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ ካለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ በኦሮምያ 1200 ወጣቶች፣ እናቶችና አባቶች ሲገደሉ፣ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታስረዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የድርቅ አደጋ የከፋ እንደሆነ የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ

ኢሳት(ጥር 16 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ዳግም የተከሰተው የድርቅ አደጋ በ120 ወረዳዎች ውስጥ የከፋ እየሆነ መምጣቱን የአለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) ይፋ አደረገ።
ካላፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በአራት ክልሎች የተከሰተው ይኸው የድርቅ አደጋ ሃገሪቱ በምግብ ምርት ራስን ለመቻል እያደረገች ባለው ጥረት ላይ ስጋት አሳድሮ እንደሚገኝ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የድርቅ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

Tuesday, January 17, 2017

ድርቅ በተከሰተባቸው ክልሎች 24 ሺ አካባቢ የሚደርሱ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ

(ጥር 9 ፥ 2009)
አዲስ የድርቅ አደጋ በተከሰቱባቸው አራት ክልሎች ወደ 24 ሺ አካባቢ የሚደርሱ ቤተሰቦች በድርቁ ሳቢያ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ።
ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በአፋር ኦሮሚያ፣ ደቡብና የሶማሊ ክልሎች ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።
ይህንኑ የድርቅ አደጋ መባባስ ተከትሎ 23ሺ 764 ቤተሰቦች ከመኖሪ8ያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለአስቸኳይ የምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ዕርዳታዎች መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርቁን አስመልክቶ ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል።
በአራቱ ክልሎች በመዛመት ላይ ባለው የድርቅ አደጋ 5.6 ሚሊዮን ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ሲሆን፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ርብርብ ካላደረገ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል።
የድርቁ ሁኔታ መባባስን ተከትሎ በደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ዞኖች ቆዳን በሚያሳክክ ወረርሽን እየተጠቁ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች ባለፈው ሳምንት የደረሰውን የቦምብ አደጋ ተከትሎ ውጥረት መንገሱ ተገለጸ

(ጥር 9 ፥ 2009)
ሰሞኑን በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች የደረሰን የቦምብ አደጋ ተከትሎ በሁለቱ ከተሞች ውጥረት መንገሱን የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ገለጸ።
የጥምቀት በአል አከባበርን አስመልክቶ በሁለቱ ከተሞች ተጨማሪ ጥቃት ሊደርስ ይችላል ሲል ፖሊስ ማሳሰቢያ መስጠቱንም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎቹ ባሰራጨው የጉዞ ጥንቃቄ መረጃ አመልክቷል።
ይሁንና ፖሊስ ሊደርስ ይቻላል ስላለው ተጨማሪ ጥቃት የሰጠው ዝርዝር መረጃ የሌለ ሲሆን፣ በሁለቱ ከተሞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ የሚከበረውን የጥምቀት በአል አስመልክቶ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሃይል መሰማራቱ ታውቋል።
የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ዜጎቹ ወደ አካባቢው በሚደረጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ ዕርምጃን እንዲወስዱ የሰጠው ማሳሰቢያም ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቀጥል በመግለጫው አስፍሯል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በሁለቱ ከተሞች በሚገኙ ሆቴሎች የቦምብ አደጋ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፣ በጎንደር ኢንታሶል ሆቴል በደረሰው ፍንዳታ የአንድ ሰው ህይወት አልፎ 18 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ፖሊስ ገልጿል።

በድርቅ ለተጎዱ 5 ሚሊዮን 600 ሺ ኢትዮጵያውያን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚሆን 948 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ያስፈልጋል

 የኢህአዴግ መንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ባደረጉት ሪፖርት በድርቅ ለተጎዱ 5 ሚሊዮን 600 ሺ ኢትዮጵያውያን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚሆን 948 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ያስፈልጋል። አብዛኛው ገንዘብ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ዜጎች የሚውል ነው። ከዚህ ውስጥ የኢህአዴግ መንግስት 47 ሚሊዮን ዶላር ለመነሻ እንደሚለግስ አስታውቋል። ቀሪው ወጪ በአለማቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ይሸፈን አይሸፈን አልታወቀም። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አምና ተከስቶ የነበረውን ድርቅ 75 በመቶ በራሳችን አቅም ተቋቁመነዋል በሚል መግለጫ መስጠታቸው ይታወቃል። ይሁን እንጅ አሁን በቀረበው እቅድ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ወጪ እንዴት እንደሚሸፈን አልተገለጸም። በሌላ በኩል በደቡብ ኦሞ ዞን በተከሰተው ድርቅ በታህሳስ ወር በሃመርና በናኩሌ ወረዳዎች ብቻ 6 ሺህ የቀንድ ከብት አልቀዋል። ይህን ተከትሎ የ2 ሚሊዮን ብር የመኖ ሣር ወደ ዞኑ ለማጓጓዝ ሙከራ እየተደረገ ቢሆንም፣ ውሃ በሌለበት ሁኔታ ሙከራው እንስሳቱን ከእልቂት እንደማይታደግ ከዞኑ ወደ ወረዳዎች የተንቀሳቀሰው የግብርና ባለሙያዎች ቡድን አሳውቋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የደቡብ ኦሞና ሰሜን ኦሞ ድንበር/ወሰን የሆነውና ላለፉት 25 ዓመታት 5 ሺ 490 ሄክታር መሬት በመስኖ ሲያለማ የነበረው የ‹ወይጦ› ወንዝ በመድረቁ በወንዙ ዳርቻና ከወንዙ መስኖ የእንስሳት ፈጥኖ-ደራሽ ሳሮችን/መኖ ለማምረት የተጀመረው ሙከራም በወይጦ ወንዝ መድረቅ መቋረጡን ባለሙያዎች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኢሳት የሰሜን ጎንደር ወኪል እንደዘገበው፣ ከዚህ በፊት የጥምቀትን በአል ለማክበር ይደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በዚህ አመት አልተደረጉም

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የሰሜን ጎንደር ወኪል እንደዘገበው፣ ከዚህ በፊት የጥምቀትን በአል ለማክበር ይደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በዚህ አመት አልተደረጉም። የሃይማኖት አባቶች የሆኑት የአቡነ አብርሃ እና አባ ቀለመወርቅ መታሰር እንዲሁም በዞኑ የሚፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ የሃይማኖት አባቶች በአሉን በተቀዛቀዘ ስሜት ለማክበር እንዲወስኑ አድርጓቸዋል። የወረዳው ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት ህዝቡ ቢያምንበትም ባያምንበትም በአሉ እንዲከበር የሚል ትእዝዛ ለሃይማኖት አባቶች ሰጥተዋል። በወገራ ወረዳ አምባጊዮርጊስ ከተማ ደግሞ ታቦቱ ቤ/ክርስቲያኑን ዞሮ እንዲገባ እንጂ በፊት የሚደረገው ስነስርዓት እንዳይከናወን ወስነዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገረ ስብከቱ ሃላፊ አቡነ ኤልሳዕ በአቡነ ቀለምወርቅ እና በበአሉ አከባበር ዙሪያ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ለማግኘት ቢፈልጉም፣ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

አገዛዙ ወደ ሶማሊያና ሱዳን በሰላም አስከባሪ ስም በሚልካቸው ወታደሮች ላይ የማእረግ ማጭበርበር እየፈጸመ ገንዘብ እንደሚያገኝ የአጋዚ የህግ ክፍል ኤክስፐርት አስታውቋል

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገዛዙ ወደ ሶማሊያና ሱዳን በሰላም አስከባሪ ስም በሚልካቸው ወታደሮች ላይ የማእረግ ማጭበርበር እየፈጸመ ገንዘብ እንደሚያገኝ የአጋዚ የህግ ክፍል ኤክስፐርት አስታውቋል። የአጋዚ ኮማንዶ እና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ የህግ ሰነድ እና ዝግጅት ኤክስፐርት የነበረው ሃምሳ አለቃ ወደ ሶማሊያ ሰላም አስከባሪ አባል ሆኖ ሲሄድ ሻለቃ ተብሎ የተሰየመው ሃምሳ አለቃ ኃ/ሚካኤል በእውቀቱ ጋሻዬ በአጋዚ ውስጥ ያለውን የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ዘረኝነት፣ ሙስና፣ ብልሹ አሰራር እና ጭካኔ በመቃወም ክፍለጦሩን መክዳቱን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቆይታ አረጋግጧል። ሃምሳ አለቃ ኃ/ሚካኤል በተለይም ሰላም ለማስከበር በሚል በተባበሩት መንግስታት እንዲሁም በአፍሪካ ኅብረት ወይም አሚሶም በሶማሊያ ሴክተር ሶስት በባይደዋ ከመጋቢት ወር 2007 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ ወር 2008 ዓ.ም በቆየበት ወቅት የህወሃት ወታደራዊ አዛዦች በሰራዊቱ ላይ የፈፀሙት ወንጀል እጅግ ዘግናኝ እንደነበር አስታውቋል። በገለጻውም በተለይ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም ባይደዋ በሚገኘው ከቡራካባ 27 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኘው ጁባ በተባለ ስፍራ በኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል ቸልተኝነት እና ዕውቀት ማነስ 42 የአጋዚ አባላት በፈንጂ እና በሌሎች መሳሪያዎች ተገለው አስከሬናቸው በየቦታው ወድቆ ያየበት ሁኔታ በቁጭት እንደሚያስታውሰው አውስቷል። ያለምንም ወታደራዊ ጥናት እና ክትትል ባልተደረገበት ተጠያቂ የሆነው ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል በሃላፊነት ሳይጠየቅ ለተሻለ እድገት የታጨበት መንገድ በሰራዊቱ እልቂት ባሳየው ንቀት እና ትእቢት የተቆጡ ወታደሮች አግተውት በምልጃ መትረፉን ይናገራል። አያይዞም የህወሃት አባል የሆኑት የክፍሉ አዛዦች ለገንዘብ ያላቸው ፍቅር እና ስግብግብነት ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ እንዴት እንዳዋረዱ እራሱን በምስክርነት ያስቀምጣል

Tuesday, January 10, 2017

በጎንደር ቀበሌ 18 በሚገኘው ኢንታሶል ሆቴል ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል

ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማምሻውን በደረሰን ዜና መሰረት በጎንደር ቀበሌ 18 በሚገኘው ኢንታሶል ሆቴል ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል። በሆቴሉ ውስጥ ፋሲል የእግር ኳስ ቡድን የባንክን ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ የሚዝናኑ ወጣቶች ነበሩ። ከ5 በላይ በጽኑ የቆሰሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለማውቅ የተቻለ ሲሆን፣ ወታደሮችና ፖሊሶች አካባቢውን በመክበባቸው በትክክል የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። ዛሬ ማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2009 ዓም ጠዋት ላይ ደግሞ አቶ ባረኮ በሚባል ቦታ ላይ ማንነታቸው አልተወቁ ሃይሎች አንድ የፌደራል ገድለው የጦር መሳሪያውን ይዘው ተሰውረዋል። ትናንት ዋርካ በሚባለው አካባቢም እንዲሁ መጠነኛ የቦንብ ፍንዳታ ተከስቶ ነበር። ፍንዳታውን ማን እንዳደረሰው የታወቀ ነገር የለም። በቅርቡ በባህርዳር ከተማ በአንድ ሆቴል ላይ ተመሳሳይ ፍንዳታ መድረሱ ይታወቃል።

Monday, January 9, 2017

ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተማ በተደረገው የከፍተኛ የጦር አዛዦች ስብሰባ ላይ በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ውሳኔዎችን አሳልፏል

ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተማ በተደረገው የከፍተኛ የጦር አዛዦች ስብሰባ ላይ በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ውሳኔዎችን አሳልፏል። የምእራብ እዝ ማሰልጠኛ ሰሜን ጎንደር በሚገኘው ሰራባ በሚባለው ቦታ ላይ እንዲሆን የመጨረሻ ውሳኔ በደቡብ ምስራቅ እዝ በ13ኛ እና 32ኛ ክፍለ ጦሮች ስር የሚገኙ ሁለት ሬጀመንት ጦር ወደ ሰሜን ጎንደር በማምጣት፣ ሰሜን ጎንደርን ሙሉ ለሙሉ የወታደራዊ ቀጠና አድርጎ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ መደምሰስ የሚል ውሳኔም አሳልፏል። እንዲሁም በጭልጋ የሚቋቋመውን አንድ አዲስ ክፍለ ጦር በፍጥነት አደራጅቶ ወደ እንስቃሴ እንዲገባ የማድረግ ስራን ተቀላጥፎ ይቀጥል ብሎአል።

በኦሮምያ በተለይም በአዳማ ፣ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፣ በአማራ ክልል ደግሞ በጎንደር እና አዊ ዞኖች በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል።

ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሳምንቱ መጨረሻ በኦሮምያ በተለይም በአዳማ ፣ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፣ በአማራ ክልል ደግሞ በጎንደር እና አዊ ዞኖች በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። 10 ሺ ወጣቶች ከእስር መፈታታቸውን ባስታወቀ ሁለት ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አዲስ የተጀመረው የእስር ዜና በነዋሪዎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። በአማራ ክልል በተለይ ከወራት በፊት ተደርጎ በነበረው ህዝባዊ አመጽ ላይ በህወሃት ደጋፊዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል የተጠረጠሩ ወጣቶች እየተፈለጉ የታሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ክትትል እየተደረገባቸው ነው። የህወሃት ካድሬዎች በክልሉ በብዛት በመሰማራትና ለአንዳንድ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ በመስጠት እንዲሁም ሹመት ይሰጣችሁዋል በሚል ፣ ጸረ ህወሃት አቋም ያላቸውን ወጣቶች እንዲጠቁሙ እያግባቡ ነው። በአዳማ፣ ጉጂና ቦረና ዞንም እንዲሁ አፈሳው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያመጡ ጫና እየተደረገባቸው ነው። እንደ አዲስ ነውጥ ሊያነሱ ይችላሉ የተባሉ ወጣቶችን በተናጠል እየለዩ ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከስራ ገበታቸው እና ከትምህርት ቤቶች አፍነው በመውሰድ ማሰሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን ምንጮቻችን ገልፀዋል። ከኢሬቻ የጅምላ ግድያ በኋላ አብዛኛኛው ሟቾች እና ቁስለኞች የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ተከትሎ የህወሃት ኢህአዴግን አገዛዝ የሚያወግዙ ወጣቶች በተለያዩ መንገዶች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው። ከቀድሞው በተለየ ሁኔታ በአካባቢው ነዋሪዎች ተቀባይነት ያጣው ገዥው ህወሃት ኢህአዴግ በክልሉ ውስጥ አፈናውን ካጠናከረባቸው አካባቢዎች ውስጥ የምስራቅ ሸዋ ዞን በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በምስራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ፀጉራቸውን በመላጨት ክብር በሚነካ ሁኔታ ”አይደገምም” የሚል ቲሸርት በማልበስ የተወሰኑ ወጣቶች ከእስር የተለቀቁ ቢሆንም፣ አሁንም በታንከኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ፣ በፖሊስ ጣቢያዎች እና በተለያዩ ስውር ስፍራዎች ብዙ ወጣቶች በደኅንነቶች ታፍነው በጅምላ ታስረው ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው

ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ የባህረ-ሰላጤ ሃገራት ገንዘባቸውን በኢትዮጵያ እንዲያስቀምጡ በመደረግ ላይ መሆኑን መንግስት ሰኞ ይፋ አደረገ።

ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ የባህረ-ሰላጤ ሃገራት ገንዘባቸውን በኢትዮጵያ እንዲያስቀምጡ በመደረግ ላይ መሆኑን መንግስት ሰኞ ይፋ አደረገ። በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ለሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት አመታት የውጭ ምንዛሪ ግኝቷ የቀነሰው የምትልካቸው የግብርና ምርቶች መጠን ጨምሮ ባለበት ወቅት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ለሚተላለፉ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊሰጥ የነበረውን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ አገደ

ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ለሚተላለፉ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ሊሰጥ የነበረውን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ አገደ። የሃገሪቱ አለም አቀፍ የልማት ትብብር ባለፈው ወር “የእኛ” የሚል መጠሪያ ላላቸው ቡድኖች የ5.2 ሚሊዮን ፓውንድ (ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ) ድጋፍ ለማድረግ ውሳኔን አስተላልፎ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል። ይሁንና፣ ድርጅቱ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት እንዲሁም የመገናኛ ተቋማት ገንዘቡ ከታለመለት አላማ ውጭ ሊውል ይችላል ሲሉ ተቃውሞን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ተቃውሞውንም ተከትሎ የሃገሪቱ አለም አቀፍ የልማት ትብብር ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የነበረው ድጋፍ እንዲያዝና በቀረቡ ቅሬታዎች ዙሪያ ምርመራ እንዲካሄድበት ትዕዛዝ አስተላልፎ እንደነበር ይታወሳል።

በኢትዮጵያ አዲስ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ

ኢሳት (ጥር 1 ፥ 2009) በኢትዮጵያ አዲስ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የምግብ እና ውሃን እጥረት እንዲሁም የመማሪያ ቦታና የትምህርት ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲርቁ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ መሆኑን ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በአፋር፣ ሶማሊ፣ ኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ 5.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከወራት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ለነዚሁ ተረጂዎች በተያዘው የፈረንጆች 2017 አም ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 9.2 ሚሊዮን ሰዎች የውሃና የንፅህና ድጋፍን እንደሚሹ ለመረዳት ተችሏል። በዚሁ የድርቅ አደጋ ከ300 ሺ የሚበልጡ ህጻናት የከፋ የምግብ እጥረት ይደርስባቸዋል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን፣ ህጻናቱን ለመታደግ ልዩ

Tuesday, January 3, 2017

በባህርዳር ወህኒ ቤት 4 ሰዎች ሲገደሉ ሌላ አንድ ነጋዴ ደግሞ ኮማንድ ፖስት ነን ባሉ ታጣቂዎች ተገደለ

አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ በረሃ ሲወርዱ ከተያዙት 6 ሰዎች መካከል 4ቱ መገደላቸውን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
በአዲስ ቅዳም ወረዳ በሚገኘው መሰናዶ ትምህርት ቤት ያስተምር የነበረው መምህር አሸናፊ ሸዋረጋው፣ 7 ሆነው ወደ በረሃ በመጓዝ ላይ እያሉ፣ ከመካከላቸው አንዱ የደህንነት አባል በመሆን ጠቁሞ ካስያዛቸው በሁዋላ፣ በባህርዳር እስር ቤት ለወራት ታስረው ቆይተዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ዛሬም ግጭት እንደነበር ተገለጸ

አሊ አመር በሚባለው አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን የቤንሻንጉል ነጻነት ንቅናቄ መሪ አቶ አብዱል አላዲህ ገልጸዋል።
የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ወደ አካባቢው በብዛት የተጓዙት ወታደሮች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸማቸውን እንዲሁም በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ሃላፊው ገልጸዋል።
በገዢው ፓርቲ ወታደሮች እና በእነሱ ታጋዮች መካከል የሚደረገው ውጊያ ለሳምንታት መቆዩቱን የሚናገሩት መሪው ፣ በርካታ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች መገደላቸውንም ይገልጻሉ።

የስኳርና የዘይት ዋጋ ጨመረ

በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱን የስኳር እና የዘይት ዋጋ ጭማሪ ተደርጎባል።
ገዢው ፓርቲ በሞኖፖል በሚያከፍለው ዘይት ላይ በሊትር 2 ብር ጭማሪ ያደረገ ሲሆን፣ አንድ ሊትር ዘይት በ23 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በተመሳሳይ መንገድ በሚከፋፈለው ስኳር ላይም እንዲሁ የ2 ብር ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ አንድ ኪሎ ስኳር በ23 ብር ተመን እየተሸጠ ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የነዳጅ እና የፍጆታ እቃዎች መጨመር፣ በአገሪቱ ከሚታየው የዶላር እጥረት ጋር ሊያያዝ ይችላል ሲል በዘገባው አመልክቷል።

ሁለት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 19 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተፈረደባቸው

የከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የሬዲዮ ቢላል ጋዜጠኞችን ዳርሰማ ሶሪ እና ካሊድ መሁሃመድን ጨምሮ በተለያዩ 19 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የእስር ውሳኔ አሳልፏል።
ዳርሰማ ከህመሙ ጋር በተያያዘ 4 አመታት ከአምስት ወራት ሲፈረድበት፣ ካሊድ ደግሞ 5 አመታት ከስድስት ወራት ተፈርዶበታል።