Tuesday, February 23, 2016

የድርቅ አደጋው በቀጣዩ ወር ወደረሃብ ሊቀየር ይችላል ተባለ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2008)
መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ኬር ኢንተርናሽናል  ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ወደረሃብ ደረጃ ለመቀየር አንድ ደረጃ ብቻ እንደቀረው ማክሰኞ ይፋ አድርጓል።
በቅርቡ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የጎበኙት የድርጅቱ ሃላፊዎች አሁን ያለው የሃገሪቱ ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ በደረጃ አራት ላይ መቀመጡንና ወደረሃብና (ደረጃ አምስት) ለመድረስ ከጫፍ መቃረቡን አስረድተዋል።
የድርጅቱ ዋና ሃላፊ የሆኑት ሎሪ ሊ ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ አፋጣኝ ምላሽን ካላገኘ በቀጣዩ ወር አስከፊ ጉዳት ሊከሰት እንደሚችል አሳስበዋል።
ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የእርዳታ ጉድለትም ከ10 ሚሊዮን በሚበልጡ ተረጂዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን አሳድሮ እንደሚገኝ ሃላፊው አክለው ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment