Friday, July 31, 2015

ወያኔዎች የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለምን ያስጨንቃቸዋል?


ባለፉት 24 ዓመታት ወያኔዎች በሃገር ውስጥ (በሰላማዊ መንገድ) ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ድርጅቶች እና ፖለቲከኞች ከማዳከም አልፈው በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት ተጽኖ መፍጠር እንዳይችሉ አድርገዋቸዋል።Andargachew Tsige is Ethiopian
አብዛኛዎቹ ፖለቲከኞች የወያኔ አፈና ሲበረታ ከማምረር ይልቅ ፖለቲካውን እርግፍ አድርገው ይተውታል ወይንም ደግሞ ስደት ይወጡና ቀደም ሲል የተሰደደውን የኢትዮጵያ ስደተኛ ተቀላቅለው እንደ አብዛኛው ስደተኛ ቤተሰቦቻቸውን እና እራሳቸውን በኢኮኖሚ የማሻሻል ተግባር ላይ አተኩረው ይቀራሉ። ይህ እየተለመደ የመጣ አካሄድ ወያኔዎቹን ተመችቷቸው ኖረዋል፣ እነ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የጨዋታውን ህግ እስከቀየሩት ድረስ።
በርግጥም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጓዶቹ ወደ ፖለቲካው ሜዳ ያመጡት አዲስ የጫወታ ህግ ሰርቷል!
ወያኔ አዲሱን የጨዋታ ህግ ከጅምሩ አልወደደውም፣ ከሚቆጣጠረው ግዛት ውጪ የሚደረጉ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ኋይት ሃውስ ፊት ለፊት ሻማ ከማብራት ያለፉ እንዳይሆኑ ምኞቱ ነበር። ይህ አልሆነም።

ሁሉም በያለበት የነፃነት ትግሉን ይቀላቀል!!!


def-thumbእኛ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ የሰውነት መብታችን ተገፎ የዜግነት ነፃነታችን ተረግጦና ተዋርደን የምንገኝበት ጊዜ ቢኖር ዛሬ ነው፡፡ የጅምላ ግድያ፤ የጅምላ እስርና የጅምላ ስደት እንደ ዘመነ ወያኔ የታየበት ዘመን የለም፡፡ ህፃናት በረሀብ ከሚማሩበት ክፍል ውስጥ የሚወድቁበት ፤ ወንድ ልጅ በደህንነት ሀይሎች ታፍኖ የሚደፈርበት፤ ሴት ልጅ በገመድ የታሰረ የባልዋነወ ብልት መንገድ ለመንገድ እንድትጎትት የተደረገበት ዘመን ቢኖር ያሳለፍነው የወያኔ ዘመናት ብቻ ነው፡፡ ባጠቃላይ የሰው ልጅ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ መከራና ሰቆቃ እንድንሸከም የተገደድንበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡
በአንፃሩም ስለ ለፃነት ስለ ፍትህና እኩልነት ሲሉ የተሰዉ ዋጋም የከፈሉ፤ አሁንም እየከፈሉ የሚገኙ ጥቂት አይደ ሉ ም፡፡ ከነዚህም አንዱ አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ለነፃነት ለፍትህና ለ ዲሞክራሲ የሚደረገው ተጋድሎ ውሎ አድሮ ዛሬ ከዋናውና ወሳኝ ከሆነው ምእራፍ ላይ መድረሱ ደግሞ የሁላችንንም ተስ ፋ ያለመለመና የተደፋው አንገታችን ቀና ያደረገ መሆኑና በተቃራኒው የወያኔን ካንፕ ያሸበረ መሆኑ በገሀድ እየታየ የሚገኝ እውነት ነው፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች በጎርፉ እየተጥለቀለቁ ነው

ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎች የሌላቸው እስኪመስል ድረስ እግረኞች ብቻ ሳይሆኑ አሽከርካሪዎችም ጭምር መንገድ ለማቋረጥ ሲሳናቸው ተስተውሏል። በርካታ የአዲስ አበባ መንገዶች ከዓመት እስከ ዓመት ተመሳሳይ ችግሮች ቢስተዋልባቸውም መንገድ ትራንስፓርት የፍሳሽ ማስወገጃዎችን በመስራትና የተበላሹትን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አልቻለም። የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ቢያሰሙም ችግራቸውን ሰምቶ መፍትሔ የሚሰጣቸው አካል ግን እስከ አሁን ድረስ ባለማግኘታቸው፣ በዝናብ ወቅት ከፍተኛ የሆነ ችግሮች እንዳሉባቸው በገሃድ መታየት መጀመሩን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከ40 በላይ የሚሆኑ የአየር ኃይል አባላት ስርዓቱን ከዱ!

በህወሓት አገዛዝ ስር የሚገኘው አየር ኃይል ከዚህቀደም የተንሰራፋው ዘረኝነት፣ ገደብ የሌለው ዘረፋ እና አስተዳደራዊ ግፍና በደል ያንገሸገሻቸው በርካታ አባላቱ ተዋጊ ጀቶችን እና ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን እየያዙ በተደጋጋሚ መክዳታቸው ይታወቃል፡፡ በአየር ኃይሉ ውስጥ የአባላት ኩብለላ ከምድር ኃይሉ በከፋ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ ከ40 በላይ የሚሆኑ ሞያተኛ አባላቱ ባንድ ጊዜ ከየምድቦቻቸው ተሰውረዋል፡፡
ስርዓቱን ከከዱት 40 ሞያተኛ የሆኑ የአየር ኃይሉ አባላት ውስጥ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች፣ የኮማንድ ፖስት እና የጠቅላይ መምሪያው ሰራተኞች ይገኙበታል፡፡ ቴክኒሻኖች ቁጥራቸው 15 ሲሆን ምድቦቻቸው ትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ስኳድሮን፣ ሱ 27 ስኳድሮን እና አንቶኖቭ 12 ነበሩ፡፡
ከአየር ኃይል በየጊዜው ከሚከዱት ሞያተኞች ውስጥ የኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን አዛዥ ሻለቃ አክሊሉ መዘነን ጨምሮ አብዛኞቹ ወደ በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡

Wednesday, July 29, 2015

የአይን ምስክርነት !!! (ከ24ኛ ክ/ጦር ባልደረባ)

        "አልሸባብ ማለት ተፈጥሮ ጋር ተዋህዶና ተመሳስሎ ጥቃት የሚሰነዝር ሲሆን፣ የመገርመው ነገር የእነሱን ተዋጊዎች መሬት ሁሉ ትደብቃቸዋለች። በጭራሽ አይታዩም። ……… ከእለታት ባነዱ ቀን ወደሶማሊያ ስንዘምት ከአዛዦች የተነገረን ድስኩር አልሸባብ ማለት በቅጡ እንኳ ባልተጠገነ መሳሪያ የሚዋጋ፣ የጥቂት ፈሪዎች ጥርቅም በመሆኑ እኛ ካለን ዘመናዊ መሳሪያ እና የሰራዊት ብዛት አንፃር ጠንካራ የስነ ልቦና ብርታት እንድንገነባ ነበር። ……… በጉዟችን ላይ መንገድ የማፅዳት ስራው በዶዘርና በግሬደር ታጅቦ ፈንጂ አምካኞች ቦታው መፅዳቱን መስክረው ጉዞ ጀመርን ነገር ግን ደቂቃዎችን እንደተጓዝን የፊተኛው ኦራል በፈንጂ እንዳልነበረ ሆነ። ብዙም ሳይቆይ ከየት እንደሚተኮስ 'ማናየው ጥይት ሰራዊቱን አመድ አደረገው። የዚያን እለት አቧራው ሲጨስ በወኔ እየፎከሩ ከምሽግ የሚወጡ በርካታ የቤኒሻንጉል ልጆች እንዳልነበሩ ሆኑ። በድናቸውን አይናችን እያየ በመኪና ይጎትቱት ነበር። … …… አንዳንዴ አልሸባብን ማግኘት ሲያቅተን በንዴት ደባቂ ሊሆኑ ይችላሉ ያልናቸውን ሁሉ ገድለን የአልሸባብ ወታደር እንደገደልን ሪፓርት እናደርግ ነበር። አለቆቻችን በተጠገነ መሳሪያ የሚዋጋ ነው ያሉት አልሸባብ ድባቅ ከመታን በኃላ እንኳ ድስኩራቸው አሁንም ስለአልሸባብ የተጠገነ ማሳሪያ መያዝና ድክመት ነው። በዚህም ከፍተኛ አለመግባባትና ቅራኔ ተፈጥሯል።

ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው! ፕ/ሮ መስፍን ወልደ ማርያም

ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና መገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤ ዛሬ የአሜሪካኑ ፕሬዚደንት ያደረገው ንግግር ከፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ እስከፖሊሶች፣ መርማሪዎችና አዛዦቻቸው፣ እስከጦር ኃይሉና አዛዦቻቸው፣ አስከዓቃብያነ ሕግና ዳኞች፣ እስከወህኒ ቤት ጠባቂዎችና አዛዦች በየሥልጣን ተዋረዱ ላይ ሆነው የኢትዮጵያውያንን የሰውነትና የዜግነት እኩልነት አፈራርሰው በጎሣ መሠረት ላይ ሊበታትኑት የሚሞክሩትን በኃይለኛ ቃላት ከመሬት በታች ከቶአቸዋል፤ ማሰብና ማስተዋል የጎደለው፣ ከአፍንጫ የራቀ አመለካከት የሌለበት፣ አገርን የሚያጠፋ፣ ከሰውነት ጎዳና የሚያወጣ የድንቁርና መንገድ መሆኑን ገልጧል፡፡

የበረከት በህይወት መኖር እያጠራጠረ ነው! መሞቱን የሚናገሩም ኣሉ


ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በድብቅ ገብተው የልብ በሽታ ህክምና የተደረገላቸው የመንግስት ከፍተኛ ሹም በህይወት መኖራቸውን እንደ ሚጠራጠሩ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ምስጢራዊ ምንጮች አረጋገጡ፡፤ በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ለህክምና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ሃገር ከተመለሱ ወዲህ የጤንነታቸው ሁኔታ እንብዛም ባለመስተካከሉ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ወደ ሳውዲ አረቢያ « ብግሻን» ሪፈራል ሆስፒታል ማቅናታቸው የታወሳል ፡፤ አቶ በረከት ስሞኦን ከብስጭት ከተለያዩ የአልኮል መጠጦችና ከአይምሮ አደንዛዥ እጽ እንዲርቁ ተመክረው ጤንነታቸው አሰተማማኝ ደረጃ እስኪ ደርስ የዶክተሮች ቅርብ ክትትልእንደሚያሻው ተነግሯቸው በቀጠሮ ቢሸኙም የቀጠሮ ግዜያቸውን አክብረው ዶክተሮቻቸው ጋር መቀረብ አለመቻላቸውን የሚገልጹ የሆስፒታሉ ምንጮች ባለስልጣኑ በህይወት መኖራቸውን ይጠራጠራሉ።
ጅዳ « ብግሻን» ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና የተደረገላቸው የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ሹም የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ አስይቶ እንዳል ነበር ሙያዊ ትንታኔ የሚሰጡ ምስጢራዊ የሆስፒታሉ ምንጮች በሽታው የልብ እንደ መሆኑ መጠን ባልታሰበ ግዜ ባለስልጣኑን ለሞት ሊዳርጋቸው እንደሚችል ከአቶ በረከት ጋር ለመጣ አስታማሚ ገልጸው እንደ ነበር ያስታውሳሉ። በዚህም መስረት አቶ በረከት ስሞዖን ለሶስተኛ ግዜ ልባቸውን መታየት እንዳለባቸው ተነግሮቸው ቢሰናበቱም በቀጠሮ ቀን ተገኝተው ህክምናቸውን መከታተል ባለመቻላቸው በጤናቸው ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳየው የምርመራ ውጤት በረከት ሌላ ሃገር ለህክምና ሄዶ ካልሆነ በቀር አሁን ባሉበት ሁኔታ የልብ በሽታው ለአደጋ ሊዳርጋቸው እንደሚችል በመጥቀስ ባለስልጣኑ በህይወት የሉም የሚለውን ጥርጣሬ ያጠናክራሉ ። በአቶ በረከት ስሞን ጤንነት ዙሪያ ከጅዳ «ብግሻን» ሆስፒታል ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን ።

በኦባማ ጉብኝት ኢሕአዴጎች ለሁለት ተከፍለዋል – “የምርጫው 100% ውጤት የዓለም መሳቂያ አድርጎናል” የሚሉ ካድሬዎች በዝተዋል

የኢትዮጵያ መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጣ ነው በማለት እጅጉን አስቀይሞን የነበረው ኦባማ ዛሬ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ልዩ ሆኖ ቀረበ።

የኢትዮጵያ መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጣ ነው በማለት እጅጉን አስቀይሞን የነበረው ኦባማ ዛሬ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ልዩ ሆኖ ቀረበ።
ኦባማ “ዴሞክራሲ ማለት ፎርማል ምርጫ ማለት ብቻ አይደለም” ሲል አዳራሹ በአንድ እግሩ ቆመ ጭብጨባው ቀለጠ ፉጨቱ አስተጋባ ሁሉም በዚህች ሰበብ ምርጫ እያጭበረበሩ እዴሜ ያራዝሙ ስለነበር እውቅና ያገኙ መሰላቸው የኦባማ ንግግር ግን ባላሰቡት መንገድ ነበር የቀጠለው “ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው የሚታሰሩ ከሆነ ፣ ወይም መንግስት ሲቪል ሶሳይቲ ላይ በሚወስደው ጥብቅ እርምጃ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎች ዛቻ የሚደርስባቸው ከሆነ ያኔ ዴሞክራሲ ስሙ ብቻ ይኖራችኋል ነገር ግን ቁም ነገሩ እና በጣም አስፈላጊ የሆነው ፍሬ ነገር አይኖረውም” በማለት ኩም ሲያደርጋቸው እየደበራቸውም ቢሆን ጭብጨባውን አምበጫረቁት።
እኔ አምናለው ሀገራት የሰጡትን የነፃነት ሙሉ ተስፋ ከፍፃሜ ማድረስ አይችሉም የህዝባቸውን ሙሉ መብት እስካልጠበቁ ድረስ በማለት የህዝብ መብት መከበር እንዳለበት በአንክሮ አሳሰበ።
እኔ አይገባኝም ሰዎች ስልጣን ላይ ረጅም ጊዜ መቆየት ለምን እንደሚፈልጉ በተለይ ብዙ ገንዘብ ካገኙ በኃላ። የአፍሪካ መሪዎች ህገ-መንግስታቸውን ማክበር አለባቸው ፣ የስልጣን ዘመናቸው ሲያልቅ ከስልጣን መውረድ አለባቸው ስልጣን ለማራዘም ሲባል ህገ-መንግስቱን የሚቀያይሩ ከሆነ አለመረጋጋትን ይፈጥራል በማለት የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ለሶስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደራቸውን ተከትሎ የተነሳውን ረብሻ በመጥቀስ ማንም ሰው እድሜ ልኩን ፕሬዝዳንት ሆኖ መኖር አይችልም አለ።
እኔ ፕሬዝዳንት መሆኔ ለእኔ ልዩ መብት ነው ከዚህ የተሻለ ኢንተረስቲንግ ስራ አላገኝም ነገር ግን ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን አይችልም ፕሬዝዳንቱም ጭምር ስለዚህ ስለዚህ ለሶስተኛ ጊዜ እንድወዳደር ህጉ ስለማይፈቅድልኝ ስልጣኔን አስረክባለው። እኔ ብቻ ለሀገሬ እማስብ እና መስራት የምችል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው በማለት የአፍሪካ መሪዎችን እስከ አፍንጫቸው ነግሯቸው ወረደ።

Tuesday, July 28, 2015

ፕ/ት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችንና የሰብአዊ መብት ተማጋቾችን ማሰሯን በአደባባይ ነቀፉ

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በስልጣን ላይ ያለውን ገዢ ፓርቲ ” በዲሞክራሲያዊ ምርጫ” የተመረጠ ነው ብለው መናገራቸውን ተከትሎ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ተቃውሟቸውን ባሰሙ ማግስት፣ ይህንን ንግግራቸውን የሚቃረን ንግግር በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተገኝተው አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ ስለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በመጀመሪያው ቀን የተናገሩትን ላለመድገም ጥንቃቄ ያደረጉ ሲሆን፣ ምርጫውን በተመለከተ ያነሱት ብቸኛ ጠንካራ ጎን ያለ ብጥብጥ ተጠናቋል የሚለውን ነው።

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እንቅስቃሴ መገደቧን የምትቀጥል ከሆነ የህዝቦቿን እምቅ ሃይል መጠቀም አትችልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ባለፈው ምርጫ ተቃዋሚዎች በነጻነት የምርጫ ቅስቀሳ እንዳያደርጉ ገደብ ተጥሎባቸው እንደነበር ጠቅሰዋል። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም አገሪቱ ብዙ እንደሚቀራት ማመናቸው ጥሩ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ኦባማ ፣ የጉብኝታቸው አላማም በጓደኝነት ቀርቦ አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
በአዳራሹ ውስጥ በተሰባሰቡ አፍሪካውያን ጭብጨባ የሚቋረጠው ንግግራቸው በአብዛኛው በአፍሪካ መሪዎች ላይ አነጣጥሯል። ከአፍሪካ በዲሞክራሲ ግንባታ የተመሰገኑት ቦትስዋና፣ ቤኒን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴራሊዮንና ናይጀሪያ ሲሆኑ፣ በተቃራኒው በምሳሌነት የተጠቀሱት ደግሞ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ቡሩንዲ ናቸው።
በብዙ የአፍሪካ አገሮች የዜጎች ነጻነት ይገፈፋል የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ “ዲሞክራሲ በየወቅቱ የሚደረግ የተለመደ ምርጫ አይደለም ብለዋል። “ጋዜጠኞችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እስር ቤት ውስጥ አስቀምጠህ ዲሞክራሲ አስፍኛለሁ ብትል፣ ዲሞክራሲያው የስም እንጅ የተግባር አይደለም” ያሉት ኦባማ፣ “ለጸጥታ ብለን ነጻነትን የምንሰዋ ከሆነ፣ ከሁለቱም ሳንሆን እንቀራለን” በማለት በጸረሽብር ትግል ስም የሚደረገውን የመብት ገፈፋ ነቅፈዋል።
“የአፍሪካ መሪዎች፣ በተለይም ገንዘብ ካገኙ በሁዋላ ስልጣን ለምን እንደማይለቁ አይገባኝም” የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ መሪዎቹ የጻፉትን ህገመንግስት እንደማያከብሩ፣ የጨዋታ ህጉን ጨዋታው መሃል ላይ እንደሚቀይሩት” በማንሳት በሰፊው ተችተዋል። “የስልጣን ገደብ ሊኖር ይገባል፣ ማንም የእድሜ ልክ መሪ ሊሆን አይገባም” የሚሉት ባራክ ኦባማ፣ እኔ ከሌለሁ አገር ይፈርሳል የሚሉ መሪዎች፣ አገራቸውን አለመገንባታቸውን ሊያውቁት ይገባል ብለዋል።

አርበኞች ግንቦት 7 የቴፒ ወጣቶች ላሳዩት ተግባራዊ መነሳሳት አድናቆት እና ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለውን ክብር እየገለፀ


በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል።
ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር አንድነት ግድ ያለን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው በርካታ ቁም ነገሮች ያሉ ቢሆንም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።
1. “ጥቂቶች ነን፤ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለው ተስፋ ቆርጠው በደልን ለመቀበል አልመረጡም፤
2. ዓላማቸው ትልቅና ሀገራዊ ቢሆንም እርጃዎቻቸው አካባቢ ተኮር አድርገዋል፤
3. የሚወስዷቸው እርምጃዎች በአቅማቸው መጠን እንዲሆኑ በማድረግ በራሳቸው ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ማድረግ ችለዋል፤
4. እንደሁኔታው በፍጥነት መሰባሰብና መበታተን የሚችል ቀልጣፋስብስብ ማደራደት ችለዋል፤ እና
5. በከፍተኛ ሥነሥርዓት በመታነጽ ከቴፒ ሕዝብ ጋር ያላቸውን ትስስር አጠናክረዋል።

Monday, July 27, 2015

ኢትዮጵያና ኬንያ ሶማሊያን ለመቀራመት መስማማታቸውን ዊኪሊክስ አጋለጠ

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዊክሊክስ ባወጣው መረጃ ላይ የኢትዮያና የኬንያ ገዢዎች ሶማሊያን ለአራት ቦታ በመክፈል ለመቀራመት በሚስጥር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስነብቧል።

ሶማሊያ ለም እና በማዕድን የበለጸገ ምድር ባለቤት በመሆንዋ የብዙ ሀገራትን ፍላጎትን ትስባለች።ዊክሊክስ ጅቡቲ ከሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ መረጃውን እንዳገኘው ገልጿል።በአሁኑ ወቅት ብዙ አገራት በሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ፤የተወሰኑት በግፊት እንዲወጡ ተደርገዋል ብሎአል።
ሶማሊያ ለአራት ክልል ትከፈላለች ሁለቱን ኢትዮጵያ ስትወስድ ቀሪውን ሁለቱ ደግሞ ወደ ኬንያ ይጠቃለላሉ። ሁለቱም አገራት 300 ሺህ ስኩዌር ካሬ ሜትር መሬትና ተጨማሪ አምስት ሚልዮን ሕዝብ ይደርሳቸዋል ይላል ዊክሊክስ በመረጃው።
ኢትዮጵያና ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈቃጅነት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሽዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በሶማሊያ አሰማርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ግን ሁለቱ አገራት በቀጠናው ድብቅ አጀንዳ እንዳላቸውና ኬንያ ወጣት ሶማሊያዊያንን በኪሲማዩ እያስታጠቀችና ስልጠናም እየሰጠች መሆኗንና ታጣቂዎችንም እንደምታግዝ ገልፆ ኢጣሊያም የኬንያንና የኢትዮጵያን ዓላማ እንደምትደግፈው ጨምሮ ገልፅዋል።
ሶማሊያን ለመቀራመት መስማማታቸውን ዊክሊክስ መግለፁን በመቃወም ወይም በማስተባበል ሁለቱም አገራት ምንም ዓይነት ማስተባበያ አልሰጡም ሲል ዊክሊክስ ዘግቧል።

ፕ/ት ኦባማ «ኤርትራ ያለ ተቃዋሚ ድርጅትን በአሸባሪነት ለመፈረጅ» የሚያስችል በቂ መረጃ የለንም አሉ፤

ኢሳት ዜና ፦ የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ ይህን የተናገሩት ” በአሜሪካና በኤርትራ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመወጋት የምታደርገውን ጥረት እያደናቀፉ በመሆኑ የእርስዎ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት ለመርዳት ምን ያክል ዝግጁ ነው ተብሎ ከኢቢሲ ጋዜጠኛ ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ጋዜጠኛው የድርጅቱን ስም በግልጽ ከመግለጽ ቢቆጠብም፣ ፕ/ት ኦባማ የሰጡት መልስ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ምክትል ሃላፊ ዌዲ ሸርማን አርበኞች ግንቦት7ትን በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ያቀረቡትን ጥያቄ፣ ለፕ/ት ኦባማም ማቅረባቸውን የሚያመለክት ነው። ፕ/ት ኦባማ በመልሳቸው «ፖሊሲያችን መንግስትን በሃይል ከስልጣን ማውረድን አይደግፍም፣ ይህ ፖሊሲያችን በዲሞክራሲያዊ ሁኔታ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስትንም ያካትታል» ካሉ በኋላ፣ «በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩብኝ ነው በማለት የሚፈርጃቸው ድርጅቶች እንዳሉ እናውቃለን፣ ይሁን እንጅ በመንግስት ላይ ተቃውሞ ቢያሰሙም የሽብር ዝንባሌ እንደሌላቸው የእኛ የመረጃና የደህንነት መረጃዎች ያሳዩናአል» በማለት በኢህአዴግ መንግስት በኩል የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ተናግረዋል። «ይህንን በመገምገም በኩል ግልጽ የሆነ መስፈርት አለን ያሉት ኦባማ፣ ለወደፊቱ እነዚህ ድርጅቶች የሽብር ጥቃት ይፈጽማሉ አይፈጽሙም የሚለውን ለወደፊቱ የምናየው ይሆናል ብለዋል።

የወያኔ ታጣቂዎች በታህታይ አድያቦ ወረዳ እርስ በራሳቸው ተዋጉ

በታህታይ አድያቦ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ የገዢው የኢህአዴግ ስርዓት ወታደሮች እርሰ በራሳቸው እየተገዳደሉ እንደሚገኙ ተገለፀ። በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞንታህታይ አድያቦ ወረዳ ተሰማርተው የሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት በመካከላቸው አንድነትና ፍቅር እንደሌላቸው የገለፀው መረጃው በተለይ ደግሞ በአባላትና በአዛዦች መሃል በተከሰተው ያለመስማማት ምክንያት ወታደር ታዘዘ ደበበ የተባለ ግለሰብ መቶ አለቃ አስራት ባዩና አምሳ አለቃ ካሳ አለሙ የተባሉን በጥይት ገድሎ ለራሱም ህይወቱን እንዳጠፋ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።

በተመሳሳይ- በአዲ ሃገራይ አካባቢ የሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አንድ ወታደር 3ት ኮነሬሎችን ከነ አጃቢዎቻቸው ገድሎ ራሱን ህይወቱን እንዳጠፋ ባላፈው የዜና ዘገባችን መግለፃችን ይታወሳል።
ምንጭ – ትህዴን

ኢ/ር ይልቃል መንግስት ለፕሬዝደንት ኦባማ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ አስታወቁ

• ‹‹ኦባማ ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው››

• ‹‹ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ››
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ቤተ መንግስት ውስጥ ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የሚያደረገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ ለነገረ ኢትየጵያ ገልጸዋል፡፡ የራት ግብዣው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጥሪ የተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ‹‹ አሸባሪ አድርጎ የሚቆጥረን ኢህአዴግ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ለማስመሰልና ዕውቅና ለማግኘት ያደረገው በመሆኑ አልገኝም›› ብለዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል አክለውም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆና እና ስቃይ ውስጥ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› ብለዋል፡፡

የሱዛን ሳቅ! ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፍ ምን ያስቃል?


ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱዛን ራይስ ወደኬኒያ እና ኢትዮጵያ ስለሚደረገው ጉብኝት መግለጫና ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሸ ሰጥተው ነበር፡፡
የጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር በማስረዳት ንግግር የጀመሩት ራይስ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢህአዴ ሹማምንትና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች እንዲሁም ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስረድተዋል፡፡
ከጠያቂ ጋዜጠኞች መካከል ተራው የደረሰው አይዛክ አምባሳደር ራይስን ስለ ጉዞው የጸጽታና ደኅንነት ጉዳይ ከጠየቀ በኋላ ከዚህ በፊት ሌላኛዋ ጋዜጠኛ (ክሪስቲ) ያነሳችውን ሃሳብ በማጠናከር “ፕሬዚዳንት (ኦባማ) የኢትዮጵያና የኬኒያ መሪዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ አድርገው ይቆጥሯቸዋል?” በማለት ጠየቀ፡፡

የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት ባደረጉት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ብዛት ያላቸውን የኢህአዴግ ሰራዊት ደመሰሱ


arbegnoch g7 በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ-ሰገን በተባለው አካባቢ የሚገኙትን የኢህአዴግ የሰራዊት አባላት በግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰባቸው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ምክንያት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ተገለፀ።
ባለፈው ቀናት በሑመራ አካባቢ ማይ ሰገን በተባለው ቦታ ላይ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ ባደረሱት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን የገለጸው መረጃው በውጊያው ከተገደሉት ታጣቂ አመራሮችም።….
ኮማንደር ወልደሚካኤል ገብረእዝጊአብሄር የሃይል አዛዥ የነበረ፤ ካሕሳይ ነጋሽ በባዕኸር የሚልሻ አዛዥ የነበረ፤ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው የሻምበል ማእርግ ያለው በ24 ክፍለጦር የሓይል አዛዥ የሆነውና ሌሎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
እነዚህ የስርዓቱ ታጣቂዎች- በአካባቢው ሰላማዊ ህዝብ የተለያዩ ግፍ ሲፈፅሙ የቆዩ በመሆናቸው የተነሳ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በላያቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን የተገኘው መረጃው አስረድቷል።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፥

justice

ከተከሳሾቹ መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አመራር፥ አቶ አግባው ሰጠኝ ‹‹የታሰርኩት የመተማ መሬት ለሱዳን መሸጡን በመናገሬ ነው፡፡
ትናንትም መሬቱ መሸጡን ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ወደፊትም እናገራለሁ፡፡ የተከሰስኩት በመሬቱ ጉዳይ ነው እንጅ አሁን የተከሰስኩበትን ወንጀል ፈጽሜ አይደለም፡፡›› ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡

Saturday, July 25, 2015

ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ


“በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን”
ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ቢሰጥ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው በንግግር (በወሬ) ደረጃ A በተግባር ግን D እንደሚሰጧቸው ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ምዕራባውያን ዕንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስረዱ፡፡
በአሜሪካ ድምጽ የStraight Talk Africa አዘጋጅ ሻካ ሳሊ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን የአፍሪካ ጉብኝት በተመለከተ ከሁለት ቀናት በፊት ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሦስት አፍሪካውያንን ተጋብዘው ነበር፡፡ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሴራሊዮኑ ፕሮፌሰር አብዱል ካሪም ባንጉራ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ስብስብ ኃላፊ ጋናዊው ኒ አኩቴ እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር ኢትዮጵያዊው ኦባንግ ሜቶ ነበሩ፡፡
በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ለፕሬዚዳንቱ ምን ውጤት ትሰጣላችሁ በማለት ሻካ ላቀረበው ጥያቄ ዶ/ር አብዱል D እሰጣቸዋለሁ፡፡ ይህም በተለይ ከአፍሪካ ጋር ስላለላቸው ግንኙነትና እንዴት የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ውጤት አልባ እንደሆነ በመመልከት ነው ብለዋል፡፡ ይህንን ያሉበትም ምክንያት በርካታ ሰዎችን በመጠየቅ ባደረጉት ጥናትና ምርምር እንደሆነ ሆኖም አሜሪካ ከኩባ ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙነት በማለዘብደረጃ የተጫወቱ ሚና ከዚህ የወረደ ነጥብ እንዳያገኙ እንደረዳቸው ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ርዕዮት አለሙ

riyot Alemu

የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝ እንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡ በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣ ሲፒጄ፣ ፔን ኢንተርናሽናል፣ ዶሀ ፍሪደም ሴንተር፣ አርቲክል 19ንና ሌሎች ያልጠቀስኳችሁ በርካታ አለምአቀፍ ድርጅቶች ለጉዳዬ የሰጣችሁት ትኩረት በኢትዮጵያ ያለውን አምባገነን ስርዓት በማጋለጥ በኩል ትልቁን ድርሻ ተጫውቷልና ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡

Friday, July 24, 2015

ፕ/ት ኦባማ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ለኢትዮጵያ መሪዎች ያነሳሉ ብለው እንደሚጠብቁ የሂውማን ራይትስ ወች ባለስልጣን ገለጹ

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት የፕሬዚዳንቱ አንድ አጀንዳ ይሆናል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። ፕ/ት ኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት አልነበረባቸውም የሚለው አስተያየት ዋናው ጉዳይ አለመሆኑን የገለጹት ሌፍኮው፣ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ የሚለው ጥያቄ ዋናው ጉዳይ መሆን እንደሚገባውና የጉብኝታቸው ውጤት ፣ በሁዋላ ላይ የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚፈጽማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በጦር ወንጀል እንዲሁም በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች የሚያስጠይቀው መሆኑን የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሯ፣ ፕሬዚዳንቱ ሰራዊቱ ተጠያቂነት እንዲኖረው ጫና እንዲያደርጉ ድርጅታቸው ከሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጋር በመሆኑን መጠየቁንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያና በኬንያ በሚያደርጉት ጉብኝት ስለተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መብት መልዕክት እንደሚያስተላልፉ አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሳወቁት ፤ በአፍሪካ ጉብኝታቸውና በሌሎች ጉዳይች ዙሪያ ከቢቢሲው ጆን ሶፔል ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። ኦባማ በተመሳሳይ ጾታ ተጓዳኞች ዙሪያ እየተፈጸመው ያለው መገለል በሚቀርበትና መብታቸው በሚከበርበት ዙሪያ ለአፍሪካ መሪዎች መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል። “እየሄዱ ያሉት በፓርላማዋ አንድም የተቃዋሚ ተወካይ ወደሌለባት ኢትዮጵያ እኮ ነው” በማለት ጆን ሶፔል ሲያነሳባቸው፤ “አዎ፤እሱን አውቃለሁ” በማለት ምላሽ መስጠት የጀመሩት ፕሬዚዳንቱ፤ በጉዟቸው የሰብዓዊ መብቶች በሚጠበቁበትና ለሲቪል ማህበረሰቡ እንቅስቃሴ በሮች በሚከፈቱበት ዙሪያ እንደሚነጋገሩና ይህም የተሻለ ሁኔታ እንዲፈጠር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በበርማ ያደረጉትን ጉብኝት ምሳሌ በመጥቀስ አብራርተዋል። ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው በ አካባቢው ደህንነትና በአፍሪካ እያደገ በመጣው የቻይና ኢንቨስትመንት ዙሪያም ከህብረቱ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ ጠቁመዋል።

ጥቃት አድርሶ በኛ ላይ ሊያላክክ ስለሆነ ሕዝብ ሆይ ተጠንቀቅ”

አርበኞች ግንቦት 7 ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ “ሕወሓት እራሱ የሽብር * እያንዳንዱ ዜጋ የህወሓትን እኩይ ሴራ ተገንዝቦ ራሱን፣ ቤተሰቡንና አካባቢውን ከጥቃት እንዲጠብቅ

* ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል
* በህወሓት የተደገሰልንን የሽብር ጥቃት ማምከን ይኖርብናል

ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል። እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ህወሓት ስልጣን ከመያዙ በፊትም በኋላም ሲያደርገው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ህወሓት እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብዓዊና ዘግናኝ ተግባር ለመፈፀም የሚያስችሉ እኩይ ስለልቦና እና ልምድ አለው።
ginbot 7
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በቅርቡ የጀመረው የነፃነት ትግል የፈጠረበት መደናገጥ ለመሸፈንና ንቅናቄውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ለማስወገዝ ያግዘኛል ብሎ ያመነበት ይህን ዘግናኝ ሴራ ከሳምንት በፊት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁቱን አጠናቆ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የነፃ ሚዲያ አባላት ደርሰውበት ለሕዝብ ይፋ በማድረጋቸው እንዲዘገይ ተደርጎ ነበር። አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ ሴራው ከበፊቱ በባሰ እና ይበልጥ አውዳሚ በሆነ መጠን ተግባራዊ ለማድረግ የህወሓት “ስውር” መንግሥት ወስኗል። በዚህም ምክንያት ይህ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ዝዋይ እስር ቤት

ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም

temeprison

ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤–
1. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሰዎች በመሆናቸው ሰብአዊ ደኅንነታቸውና ክብራቸው ሁልጊዜም እንዲጠበቅላቸው ያስፈልጋል፡፡
2. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሁሉ ከመሰቃየትና ከመጉላላት በጸዳ አያያዝ እንዲጠበቁ ይደነግጋል፤
3. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ አንድ እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ ከሚኖሩበት በጣም ርቆ አይታሰርም፤
4. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ የታመመ እስረኛ ሙሉ ህክምናና አስፈላጊውን መድኃኒት ሁሉ ማግኘት አለበት፤
5. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች በአእምሮና በመንፈስ የሚያድጉበት ትምህርትን የማግኘት፣ መጻሕፍትን የማግኘት መብቶች አሏቸው፤
6. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ በእምነቱ መሠረት አምልኮቱን የመፈጸምና የሃይማኖቱን መጻሕፍት የማንበብ መብት አለው፤

አቶ በፍቃዱ አበበ የመከላከያ ምስክሮችን አሰማ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ተከሶ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው በአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ዋና ፀኃፊ አቶ በፍቃዱ አበበ በትናንትናው ዕለት ሀምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡

ከአምስቱ የመከላከያ ምስክሮች መካከል አራቱ ፣ የአርባ ምንጭ ፖሊስና ደህንነቶች በፍቃዱ አበበ ላይ በሀሰት ከመሰከሩ የተሻለ ጥቅም እንደሚሰጣቸው ቃል ገብተውላቸው እንደነበር ገልጸው መስክረዋል፡፡
ከዓመት በፊት አንድነት ፓርቲ በአርባ ምንጭ ከተማ ያደርገው በነበረው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተሳትፈሃል ተብሎ ከድንጋይ ማንጠፍ ማኅበር የተሰናበተ አንድ ወጣት ‹‹በፍቃዱ አበበ ለግንቦት ሰባት እየመለመለ ይልካል፡፡እኔንም መልምሎኛል ብለህ ከመሰከርክ ወደ ስራህ እንመልስሃለን›› እንዳሉትና እሱም ፈቃደኛ ባለመሆኑ በሀሰት ሳይመሰክር መቅረቱን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ሌላ ወጣት በፍቃዱ ላይ ምስክር ሆኖ ከቀረበ የሚፈልገውን እንዲሚያደርጉለት ቃል ተገብቶለት እንደነበር ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ይህ ወጣት የአቃቤ ህግ ምስክር ሆኖ ልደታ ፍርድ ቤት ድረስ መጥቶ የነበር ቢሆንም በፍቃዱን እንደማያውቀውና በሀሰት መስክር መባሉን እንደሚገልጽ ለአቃቤ ህጉ በመናገሩ ሳይመሰክር እንዲመለስ መደረጉን አስረድቷል፡፡
አቶ በፍቃዱ ተጨማሪ ምስክሮችን ለማሰማት እንዲሁም የአቃቤ ህግ ምስክር ሆኖ በሀሰት መስክሮብኛል ያለው ግለሰብ ለአርባ ምንጭ ፖሊስና ለልደታ ፍርድ ቤት የሰጠው ቃል እንዲቀርብለት በመጠየቁ ተጨማሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለማቅረብ ለነሀሴ 21 ቀን 2007 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡አቶ በፍቃዱ አበበ በመከላከያ ምስክርነት የጠራቸው ግለሰቦች እንደታሰሩበትና ለምስክርነት የመጡትም ሲጉላሉበት እንደሰነበቱ መግለጹ ይታወቃል፡፡
በተጨማሪም ፕ/ት ባራክ ኦባማ ሲመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሳችሁ መሆኑን ደርሰንበታል በሚል የታሰሩት አቶ መርከቡ ኃይሌና አቶ አበበ ቁምላቸው ለሀምሌ 20 ቀን 207 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ዛሬ ሀምሌ 16 ቀን 2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት በዝግ ችሎት የቀረበው አቶ መርከቡ ኃይሌ ለውሳኔ ለሀምሌ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡
በቄራ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ አበበ ቁምላቸው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበት ለሀምሌ 20 ቀን ተቀጥሯል፡፡አቶ አበበ የጊዜ ቀጠሮ ሲሰጥበት ይህ ለሶስተኛ ጊዜው ሲሆን ደህንነቶች ‹‹ከሌሎች አባላቶች ጋር በመሰባሰብ ሁከት ለመፍጠር እየሰራችሁ ነው›› በሚል ምርመራ እንደሚያደርጉበትና ድብደባም እንደሚፈጽሙበት ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ ሀምሌ 11 ቀን 2007 ዓ.ም ባልታወቀ ምክንያት የታሰረው የቀድሞ አንድነት አባል አቶ ፍቃዱ በቀለ ካሳንቺስ የሚገኘው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምድር ቤት ውስጥ ብቻውን ታስሮ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከእስር ዜና ሳንወጣ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዘመዶቹ ውጪ እንዳይጎበኝና የሕክምና ዕርዳታ እንዳያገኝ ተከልክሏል።

በባህርዳር የቀድሞ የሰራዊት አባላት ያደረጉት ተቃውሞ በሃይል ተበተነ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው መንግስት ዘመን በውትድርና ሙያ አገራቸውን ያገለገሉ እንዲሁም በኢህአዴግ ዘመን በተመሳሳይ ሙያ ያገለገሉ እና ያለ ስራ ወይም ያለጡረታ የተሰናበቱ ወታደሮች፣ በአገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት መቋቋም አልቻልንም፣ መንግሰት ስራ ይሰጠን ወይም ደሞዝ ይክፈለን በሚል የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመነሳት ወደ መስተዳድሩ ጽ/ቤት በማምራት ላይ የነበሩ ወታደሮች ፣ መስተዳድሩ አካባቢ ሳይደርሱ በፌደራል ፖሊስ እንዲበተኑ ተደርጓል። በፖሊሶችና በቀድሞ ወታደሮች መካከል መጠነኛ የሆነ ግጭት ቢነሳም፣ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ሰልፉ ተበትኗል።
ወታደሮቹ ለሱዳን የተሰጠው መሬት ህገወጥ ነው በማለት ሲያወግዙም ተሰምተዋል። በአገራቸው የመስሪ

Thursday, July 23, 2015

ህወሓት በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ተኩኖ ህወሓትን ማዳከም አርበኝነት ነው!

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ለኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አባላት የሚከተለው መልዕክት ማስተላለፍ ይሻል።

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው የሚያፈናቅሉ፣ መኖሪያ ቤቱን የሚያስፈርሱ መሆናቸው እናንተም እየተሳተፋችሁበት ያለ ሥራ ነውና የምታውቁት ነው። “አጋር ድርጅቶች” የሚል ስያሜ የተሰጣችው አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ እና ኢሶዴፓ “አጋር” ሳይሆን የህወሓት ጀሌዎች መሆናቸው እናንተም እኛም የምናውቀው ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ የተባሉ አድርባይ ድርጅቶች ባይኖሩ ኖሮ ህወሓት ለ24 ዓመታት ኢትዮጵያዊያን እየገደለና እያሰረ፤ እየዘረፈ በውሸት ምርጫና በውሸት ዲሞክራሲ ስም ፍጹም የሆነ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ አምባገነናዊ ሥርዓት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሰፍን ባልቻለም ነበር። ህወሓት በኢትዮጵያዊያን አናት ላይ እንዲፈነጭ እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ድርጅቶች አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው።

Wednesday, July 22, 2015

ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 29/2007 ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጠ

64002-images

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበር ቢሆንም ይገኙበታል ለሚባሉት ማረሚያ ቤቶች በተለይም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚላከው ማዘዣ ዘግይቶ በመላኩ እንዳልደረሰለት ገልጾ ለዛሬ ሀምሌ 15/2007 ለምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም አቶ አንዳርጋቸው ዛሬም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለምን እንዳላቀረበ የተጠየቀው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ማዘዣው እንደደረሰው ገልጾ ነገር ግን ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ መፃፍ ሲገባው ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተብሎ በመፃፉ አቶ አንዳርጋቸውን ማቅረብ እንዳልቻለ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ ተፅፎ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 29/2007 ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት 10 ግለሰቦች መካከል ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል የሚል ክስ የቀረበባቸውና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲመሰክሩላቸው የጠሩት አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ማንዴላ ጥላሁን፣ አቶ አንሙት የኔዋስና አቶ አሰፋ ደሳለኝ ናቸው፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ


በእነ ዘላለም ወርቃገኘው የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው ተከሳሾቹ ሀምሌ 1/2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት 7/2006 ዓ.ም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተገኘ የተባለ መረጃ ከአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ማስረጃ ዝርዝርነት እንዲወጣ፣ ተከሳሾቹ ለፖሊስ መረጃ የሰጡበት መንገድና ፖሊስ የሰነድ ማስረጃዎችን የያዘበትን መንገድም አቃቤ ህግ ህጋዊ መሆኑን ስላላረጋገጠ በደንበኞቼ ላይ በማስረጃነት እንዳይያዝ ሲሉ መቀወወሚያ አቅርበው ነበር፡፡
ከተከሳሾቹ መካከል በዛሬው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹መቃወሚያው የቀረበው ከተከሳሾች እጅ ተገኙ የተባሉት ማስረጃዎች በህጋዊ መንገድ የተገኙ ስለመሆናቸው አቃቤ ህግ በማስረጃ ስላላረጋገጠ ነው›› ሲል ፍርድ ቤቱ መቃወሚያውን እንዲቀበለው ጠይቋል፡፡ ሆኖም ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መቃወሚያውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በነፃ ይሰናበቱ ወይንም ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ለብይን ለነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም 9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ ከጥብቅና በመታገዳቸው ምክንያት ሰባቱም ተከሳሾች በዛሬው ችሎት ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡ በዚህ መዝገብ ተከሰው አቶ ተማም መቃወሚያ ካቀረቡላቸው መካከል አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሽ ይገኙበታል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔውን የሱር ኮንስትራክሽንን ንብረት ማውደሙን ገለጸ ፣ጦርነቱ በጎንደር አካባቢ ልዩ ወረዳዎች ቀጥሏል

Ginbot7_arebegnochi1

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ጋዜጣዊ መግለጫ:- የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግና የነፃነት ፋኖዎች በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ ጉያ ውስጥ ሆነው በወልቃይት የጀመሩትን ወታደራዊ ጥቃት አሁንም አጠናክረው በመቀጠል የህወሓትን አገዛዝ እያሽመደመዱት ነው፡፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለውን በቁሙ ደርቆ የበሰበሰ ዛፍ ከስሩ ገዝግዞ ለመቁረጥ የተጀመረው ትግል ሰሞኑን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከወታደራዊ ጥቅምና ደህንነት አንፃር ስማቸውን ለመግለፅ በማይቻልባቸው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ላይ በሚንቀሳቀሰው የህወሓት ፀረ-ሽምቅና ሚሊሻ ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ደምስሰውታል፡፡ በአዘዞ እና ጠዳ ከተሞች መካከል ከሚገኘው መገጭ ወንዝ አጠገብ በግንባታ ስራ ላይ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን የድንጋይ መፍጫ ማሽነሪዎች እና ሌሎችን የግንባታ ቁሳቁሶች በአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ስራውን አቁሞ እንዲሸሽ ተገዷል፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን የህወሓቶች የግል ንብረት የሆነው ኤፈርት በስሩ ካሉት ከ60 በላይ የንግድ ኩባንያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሱር ኮንስትራክሽን ውድመት በደረሰበት አካባቢ የግንባታ ስራውን በብቸኝነት የያዘው እንደተለመደው ያልምንም ጨረታ ነው፡፡ በተያያዘ ዜና ከዚያው ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚኖር አቶ ጎሸ ሽባባው የተባለ ገበሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ስንቅ አቀብለሃል በሚል በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውሎ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡ አቶ ጎሸ ሽባባው አሁን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት እስር ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡ በላይ አርማጭሆ አንገረባ ቀበሌ የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እና የህወሓት ጸረ-ሽምቅ ኃይል ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ጦርነት አድርገዋል፡፡ ጦርነቱም የተካሄደው ሀምሌ 11 2007 ዓ.ም ሲሆን በአካባቢው ለአሰሳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የህወሓት ፀረ-ሽምቅ ኃይል በውስጥ አርበኞች የተከፈተበትን ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መቋቋም ስላልቻለ አንድ ሰዓት ከፈጀ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ በርካታ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ የሱዳን መከላከያ ኃይል የኢትዮጵያን ወሰን ጥሶ ገብቶ ከሆር ሁመር ገበሬዎች ጋር መታኮሱ ታውቋል፡፡ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 2 ገበሬዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን መከላከያ ኃይል ድንበር ሰብሮ ገብቶ በገበሬው ህዝብ ላይ የጦር ጥቃት ሲያደርስ እየተመለከተ እንዳላየ በዝምታ አልፎታል፡፡

ከስር ቤት የተላከ ደብዳቤ ምንጭ ናትናኤል መኮንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ

ለእናት ሀገር ሲባል፣ ማን ይፈራል….!

በሰላማዊ ትግል ጓዶቻችን የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና፣ መልካም ህልም አላሚዎቹ የዞን 9 ጦማርያን ያለምንም ወንጀል በስርዓቱ ወደር የለሽ ፍራቻ ምክንያት ብቻ ከንጹህ ህሊናቸውና ከመልካም ስራቸው ጋር ወደ ማጎሪያ ቤት በተወረወሩ ጊዜ፣
‹‹በሉ እናንተ ሂዱ የእኛም ወደዚያው ነው፣
ድሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው›› ብለን ነበር፡፡

ይህን ብለን ሳናበቃ ግን በዚህ ሁኔታ የሀገራችን እጣ ፋንታ ምንድነው? የሚል ጥያቄ በውስጣችን ይመላለስ የነበርን የዛሬዎቹ አባሪ ተከሳሾች የሆንን ወጣቶች መደበኛ ያልሆነ ውይይት ጀመርን፡፡ በዚህ ውይይታችንም አምባገነኑን የወያኔ አገዛዝ ሊያስወግደው ቀርቶ ሊያሳምመው እንኳን በማይችል ጉንተላ መሳይ ትግል ውስጥ ሆነን ለሀገራችን

Tuesday, July 21, 2015

የደቡብ ምስራቅ እዝ በርካታ ወታደሮችን አሰረ:

Minilik Salsawi 


– በጄኔራል አብርሃ የሚመራው የደቡብ ምስራቅ እዝ ካለፈው እሮብ ጀምሮ ቀጥራቸው 180 የሚጠጉ ወታደሮቹን ከስሩ ካሉት ክፍሎች ሰብስቦ ማሰሩን የወታደራዊ ደህንነት ምንጮች ገልጸዋል::ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ እንዳሉት በከፍተና የስለላ መረብ ስር የወደቁት የእዙ ወታደሮች የሃገሪቱን ጉዳይ እና በግል የሚደርስባቸውን ጉዳይ እርስ በእርስ ይወያያሉ የራዲዮ ፕሮግራሞችን ይከታተላሉ የከትማ ወሬ ይዘው ይመጣሉ ወዘተ የተባሉ ወታደሮች ተጣርቶ ተለቅመው በጅጅጋ ወታደራዊ ማጎሪያ ወህኒ ቤት መታሰራቸው ታውቋል::

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

ሐምሌ ፲፫ (አስራሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል” በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል አባላት ለፕሮፌሰሩ በጋራ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የገለጸው ሻለቃ አክሊሉ፣ ከአባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

Sunday, July 19, 2015

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ



ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.
ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው ዕለት ሀምሌ 12 2007 ዓ.ም ኤርትራ ገብቷል፡፡

ዶ/ር ብርሃኑ ኤርትራ በገባ በጥቂት ሰዓታት ልዩት የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፖለቲካ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ወደሚገኝበት ቦታ በማምራት ከህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አርበኛ ታጋዮች ጋር ምሳ በልቷል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አርበኛ ታጋዮች ባስተላለፈው መልዕክት "ከሁሉም ነገር ዓላማ ያስተሳሰረው ስለሚልቅ፤ ለእኔ ለአገሩ ህይወቱን መሰዋዕት ለማድረግ ከተዘጋጀ ሰው የሚበልጥ ምንም ነገር በምድር ላይ ባለመኖሩ ወደ እናንተ መጥቻለሁ፡፡ የመጣሁትም እናንተን ለማስተማር ሳይሆን ከእናንተ ለመማር ነው... ለነፃነታችን አብረን እንሞታለን..." በማለት ተናግሯል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 አመራርና የምክር ቤት አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ እና ሌሎች በርካታ የድርጅቱ አባላት ከዶ/ር ብርሃኑ ቀደም ብለው ኤርትራ ገብተው ውለው አድረዋል፡፡ ሌሎች አመራሮችና አባላት በቅርቡ እንደሚገቡም ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፤- የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት

Friday, July 17, 2015

በጋሞ ጎፋ ዞና ኢህአዴግ ባለስልጣናት በእርስ በርስ ሽኩቻ እየታመሱ ነው

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ችግሩ የተፈጠረው በጋሞና በጎፋ ተወላጅ ባለስልጣኖች መካካል ነው። የዞኑን፣ የክልሉንና የፌደራል ስልጣኑን የተቆጣጠሩት የጎፋ ተወላጅ ባለስልጣኖች፣ ጋሞዎችን ሰድበዋል ፣ የጋሞ ተወላጅ ባለስልጣናትን በንቀት ያያሉ በሚል እርስ በርስ በጀመሩት ቁርሾ፣ የመንግስት ስራ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ የእርስ በርስ ሽኩቻውን ወደ ህዝብ በመውሰድ የጋሞ ባለስልጣናት የጋሞ ተወላጆችን አሰባስበው ለነገ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ ይዘዋል። የጋሞ ባለስልጣናት ደጋፊዎቻቸውን ከገጠር ማስመጣታቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ ተስፋየ ቤልጂጌ፣ ጥላሁን ከበደና ሌሎች የክልልና ዞን ባለስልጣናት እንዲወርዱላቸው ይጠይቃሉ። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዘመናት ተቻችለው የኖሩትን ሁለቱን ህዝቦች በሚከፋፍለው ሴራ ውስጥ እጃቸው አለበት በሚል፣ ተቃውሞው በእርሳቸውም ላይ እንደሚካሄድ ምንጮች ገልጸዋል። የአካባቢው የኢህአዴግ ሹሞች እርስ በርስ የሚካሂዱት ሽኩቻ መጠኑን አስፍቶ ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዳያመራ ስጋት መፈጠሩን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ቅዳሜ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ እውቅና ያግኝ አያግኝ የታወቀ ነገር የለም።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጦር ነጋሪት ጆሮ እንዳትሰጥ አንድ ምሁር መከሩ

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ኤንድ ኢንተርናሽናል ስተዲስ የተባለው ተቋም " ከአሜሪካ ጉዞ በፊት የአሜሪካ ፖሊሲ በኬንያና በኢትዮጵያ" በሚል ርእስ ባዘጋጀው ፓናል ውይይት ላይ የተገኙት በጆርጅ ማሶን ዩኒቨርስቲ የግጭት አስወጋጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ቴሬንስ ሊዮንስ እንደተናገሩት ኢህአዴግ በቅርቡ በኤርትራ ላይ ጦርነት ለማወጅ የሰጠውን መግለጫ አሜሪካ እንደማትደግፈውና እንደማትተባበር በግልጽ ማስታወቅ እንደሚገባት መክረዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት ኢህአዴግን "አምባገነኑ ጓደኛችን" በማለት እንደሚገልጹት የተናገሩት ፕሮፌሰሩ፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በ3 ምሰሶዎች ላይ አረፉ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሚመሰገን የኢኮኖሚ እድገት ብታገኝም፣ ፕሬዚዳንት ኦባማንም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያን ለሚጎበኙት የምመክራቸው ታች ወርደው የህዝቡን ኑሮ እንዲያዩ ነው ብለዋል። ሽብረተኝነትን በመዋጋትም በኩል በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የተለያዩ ፍላጎቶች ስላሉ አሜሪካ ጥቅሙዋን በትክክል መግለጽ እንደሚገባትና እነዚህ ግንኙነቶች የአሜሪካን ዘላቂ ጥቅም ያረጋግጣሉ ወይ የሚለውን መመለስ እንደሚገባ ተናግረዋል። ሰብአዊ መብትን በተመለከተ ኢህአዴግ 100 በመቶ አሸንፌያለሁ ማለቱ፣ በራሱ አገዛዙ ምን ያክል ጠንካራ አምባገነን መሆኑን ያሳያል ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ የአሜሪካንና የኢህአዴግን ግንኙነት ከግብጽና ከፓኪስታን አምባገነን መንግስታት ጋር ካለው ግንኙነት ጋር አመሳስለውታል። ኢትዮጵያ ሲቪል ሶሳይቲውን በሙሉ ሽባ የሚያደርግ ህግ ማውጣቱንም አክለዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ላይ ተጽኖ ለማድረግ ያላቸው ጉልበት አነስተኛ መሆኑን እንደሚገልጹ የገለጹት ምሁሩ፣ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በራሱ ትልቅ ጉልበት መሆኑን ገልጸዋል። ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች እንዲፈቱ፣ የሲቪክ ተቋማት ህግ እንዲሁም የጸረ ሽብር ህጉ እንዲለወጥ ወይም እንዲሻሻል ፕ/ት ኦባማ ተጽኖ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ አካባቢውን ታረጋጋለች የሚለው አስተሳሰብ ጥያቄ ውስጥ መግባት እንዳለበት ያመለከቱት ፕሮፌሰሩ፣ ኢትዮጵያ በሶማሊያና ኤርትራ የምትሰራውን የማተራመስ እንቅስቃሴ በማንሳት አሜሪካ የወደፊት ጥቅሟን በማሰብ ጉዳዩን እንደገና ማየት አለባት ብለዋል። ሰሞኑን የኢህአዴግ መንግስት ያወጣው በእብሪት የተሞላ የጦርነት ነጋሪት አደገኛ መሆኑን የገለጹት ፕ/ሩ ፣ ፕሬዚዳንት ኦባማ በዚህ ጉዳይ ላይ ከእናንተ ጋር አንተባበርም በማለት ለኢህአዴግ ባለስልጣናት በግልጽ ሊናገሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የኤርትራን ድንበር ዘልቆ መግባት ከፍተኛ ቀውስ ያስከትላል ሲሉ ፕ/ት ቴሬንስ አስጠንቀዋል :: ሌሎች ፓናሊስቶች በኢትዮፕያና በኬንያ ስላለው ሰብአዊ መብት ጥሰት ፣ ፕ/ት ኦባማ መከተል ስለሚገባቸው ፖሊሲ አስተያየት ሰጥተዋል። በውይይቱ ላይ ከኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕና ከሂውማን ራይትስ ወች የተወከሉ ተናጋሪዎች ሲቀርቡ፣ በኬንያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ማርክ ቤላሚም ተገኝተዋል፡፡

ኢህአዴግ ያሰባሰበው የህዝብ ድምጽ ” አስፈሪ” ነው ተባለ

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ 2007ትን መቶ በመቶ በሆነ ድምጽ አሸንፊያለሁ ብሎ ያወጀው ኢህአዴግ፣ ከምርጫው በሁዋላ ያሰባሰበው የህዝብ አስተያየት ለፓርቲውም ሆነ ለአገሪቱ ህልውና አስፈሪ መልእክት የያዘ ነው ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ሪፖርቱ በመጪው ነሃሴ በሚካሄደው የግንባሩ ጉባኤ ላይ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ህዝቡ በአስተዳዳር፣ በፍትህ፣ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች፣ በውሃና በመብራት እጦት እየተሰቃየ መሆኑን ተጠናክሮ በቀረበው ሪፖርት ላኢ ገልጿል። ከሁሉም በላይ ሙስናና ዘረኝነት አገሪቱን ወደ አስከፊ ጎዳና እየወሰዱዋት መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፣ በተለይም በኦሮምያና አማራ ክልሎች የተሰባሰበው መረጃ ግንባሩም ማስደንገጡን ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ዘጋቢያችን ገልጿል።
ኢህአዴግ በትምህርት እና በጤና ረገድ የተሻለ ስራ ሰርቷል ብሎ ህዝብ እንደሚያምን የሚያሳየው ሪፖርት፣ በሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያ ህዝቡ አሉታዊ መልስ መስጠቱንና በስርአቱ መማረሩን አመላክቷል።
ሁለተኛውን የ5 አመት እቅድ ተንተርሶ በተዘጋጁ የህዝብ መድረኮች ላይ የተሰጡት አስተያየቶች ፣ በድብቅ ከተሰበሰቡት መረጃዎች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሆነው መገኘታቸውንም የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ግንባሩ የህዝብ አስተያየቱን ተቀብሎ መሰረታዊ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ ያደርጋል ተብሎ እንደማይጠበቅ አስተያየቱን አስፍሯል።

ታማኝ በየነ የኢሳት ቦርድ ሊቀመንበር ሆነ፥ ኢሳት ሙሉ የ24 ሰአት ዝግጅቱን ጀመረ፥

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዢው መንግስት ከፍተኛ አፈና የሚደርስበት የኢሳት የቴሌቪዝን ስርጭት ከሳምንታት ሙከራ በሁዋላ ዛሬ ሙሉ ስርጭቱን በ ኤም 44 ሳተላይት ጀምሯል።
አዲሱ ሳተላይት ጠንካራ ሲግናል ያለው ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በሙከራው ወቅት ስርጭቱን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የኩባንያው ኢንጂነሮች ገልጸዋል።
ተመልካቾች አልፎ አልፎ የድምጽ ወይም የምስል መዛባት ቢያጋጥማቸው ስርጭቱን ለማፈን ከሚደረግ ሙከራ የመጣ መሆኑን እንዲያውቁት ኢንጂነሮች መክረዋል።

ዛሬ የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ቢሮ ከቁጥጥሩ ዉጭ የሆነ ከበድ ያለ ዉጊያ እንደገጠምና በመጥቀስ የድጋፍ ጥሪ ቢጠይቅም ከመከላከያ ሰራዊት ዘመቻ መምሪያ ክፍል መልስ አጥቷል።

ሰበር የተጋድሎ ዜና!
***************
*ዛሬ የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ቢሮ ከቁጥጥሩ ዉጭ የሆነ ከበድ ያለ ዉጊያ እንደገጠምና በመጥቀስ የድጋፍ ጥሪ ቢጠይቅም ከመከላከያ ሰራዊት ዘመቻ መምሪያ ክፍል መልስ አጥቷል። የጎንደርና የትግራይን ጠረፍ የዘለለዉ ጦርነት ተጧጡፎ ቀጥሏል።
*ሰሜን ጎንደርና ትግራይ ያልተጠበቁ ስፍራዎች በጦርነት እየታመሱ ሲሆን አርማጭሆና ወልቃይት ጠገዴ ለወያኔ የሚቀመስ አልሆነም። አዎ የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮች መከላከል አቅቷቸዉ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ሐአሎች እንዲያግዟቸዉ ከበላይ ወታደራዊ አስተዳደር ቢታዘዙም የተፈለገዉን ያህል መከላከል አልተቻለም። አርበኞች ግንቦት 7 ሽምቅ ዉጊያዉን በብቃት እየተወጣ በሚገኝበት በትናንትናዉና በዛሬዉ እለት ከራሱም ወታደሮቹ እየተስዉ ይገኛሉ።
ወያኔ ኦባማ መጥቶ እስኪሄድ የጦር ሜዳ ሽንፈቱን ለመደበቅ ሲል ብቻ ቁስለኛ ወታደሮችን ወደ ከተማ ወስዶ ህክምና አስጠት መስጠት ባለመፈለጉ ወታደራ አቅራቢያ ካምፖች ዉስት ጊዜያዊ የህክምና ጥላዎችን ዘርግቶ ቁስለኞችን እያጉላላ ይገኛል።
ድል ለነጻነት ሀይሎች!

Thursday, July 16, 2015

ኢሳት ሙሉ የ24 ሰአት ዝግጅቱን ጀመረ

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዢው መንግስት ከፍተኛ አፈና የሚደርስበት የኢሳት የቴሌቪዝን ስርጭት ከሳምንታት ሙከራ በሁዋላ ዛሬ ሙሉ ስርችቱን በ ኤም 44 ሳተላይት ጀምሯል።

አዲሱ ሳተላይት ጠንካራ ሲግናል ያለው ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በሙከራው ወቅት ስርጭቱን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የኩባንያው ኢንጂነሮች ገልጸዋል። ተመልካቾች አልፎ አልፎ የድምጽ ወይም የምስል መዛባት ቢያጋጥማቸው ስርጭቱን ለማፈን ከሚደረግ ሙከራ የመጣ መሆኑን እንዲያውቁት ኢንጂነሮች መክረዋል።
ኢሳት በዚህ ሳተላይት ለርጅም ጊዜ የሚያቆየውን ስምምነት ፈርሟል። ሌሎች ተጨማሪ ሳተላይቶችን ለመከራየት በድርድር ላይ ሲሆን፣ እንደተሳካለት ለህዝብ ያስታውቃል፡፡
ገዢው ፓርቲ ኢሳትን ለማፈንና የኢሳት ጋዜጠኞችን ኮምፒዩተሮች ለመሰለለል ብዙ ሚሊዮኖችን እያወጣ ሲሆን፣ ለአንድ አመት ብቻ 1 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ሀኪንግ ቲም ለተባለ ድርጅት መክፈሉ ሰሞኑን የአለም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። ስለላውን ተከትሎ አንድ አሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የከፈተው ክስ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ተከሳሹ ለኢሳት ተናግሯል።
ለደህንነት ሲባል ስሙ እንዳይገለጽ የተፈለገው ከሳሽ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሰሞኑ ችሎት ላይ አለመገኘታቸውን ይሁን እንጅ በጠበቆቻቸው አማካኝነት መልስ መስጠታቸውን ገልጿል። ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው የቀጠሩዋቸው ጠበቆች ጠንካራና ታዋቂ ቢሆንም፣ በከሳሽ በኩል የቀረቡት የህግ ባለሙያዎች ለእውነት የቆሙ በመሆናቸው ያሸንፋሉ ብሎ እንደሚገምት ገልጿል። ፍርድ ቤቱ የኢህአዴግን መንግስት ጥፋተኛ ብሎ ከወሰነ ውሳኔው በአለም ላይ ስለላን በተመለከተ አዲስ የህግ አካሄድ እንደሚፈጥር ገልጿል። ውሳኔው በአሜሪካ የስለላ ድርጅት ላይ ሳይቀር ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥቷል።

የመሳሪያ ትግሉን የህዝብ ብሶት የወለደው ነው ሲሉ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናገሩ

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲያችሁ አባሎች የትጥቅ ትግልን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በመርህ ደረጃ ኢህአዴግን ብሶት ከወለደው ሰው ጠመንጃ የማያነሳው ለምን ድነው ሲሉ ጠይቀዋል። ሰው መኖር ካልቻለ ምን አማራጭ አለ ሲሉ የጠየቁት ኢ/ር ይልቃል ሰው መቀመጫ መሄጃ ሲያጣ ቢሀድ ምን ይገርማል፣ አትሂድስ ለምን ይባላል? ብለዋል። እንዴውም ወጣቱ ባይሄድ ነው የሚገርመኝ ያሉት ኢ/ር ይል

ባህር ዳር ከተማ የሰዎችን ህይወት የነጠቀ ግጭት ተነሳ ተኩሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው

በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሜትሮሎጂ ጀርባ በተለምዶ ዝንጀሮ ወንዝ በሚባለው አካባቢ የከተማው አስተዳደር የመኖሪያ ቤቶችን በግሬደር ማፍረሱን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪዎችና በታጣቂዎች መካከል  በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ከሶስት በላት ሰዎች መሞታቸውን የአይን ምስክሮችን ጠቅሰው ዘግበዋል፡፡  ከስፍራው እየደረሰን የሚገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ግጭቱ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ተኩሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ 


የግል አየር መንገዶች ከበራራ በፊት ለመከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ስራቸውን እንዳስተጓጎለ ገለጹ

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ በመለስተኛ የግል የአውሮፕላን የበረራ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ባቀረቡት አቤቱታ፣ የስራ ዘርፉ ከቢሮክራሲ ጋር በተያያዘ ለኪሳራ እየዳረጋቸው መሆኑን ሳያንስ፣ ከበረራው 24 ሰአታት በፊት ለመከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉ መታዘዛቸው ስራቸውን አስቸጋሪ አድርጎታል።

አንዳንድ ባለሀብቶች በተለይ ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚደረገው በረራ ፈታኝ እንደሆነባቸው ገልጸዋል። አስቸኳይና ድንገተኛ በረራ የሚጠይቁ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ሲመጡ፣ አፋጣኝ አገልግሎት መስጠት አልቻልንም ያሉ ሲሆን፣ የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ” ሪፖርት የሚያደርጉት ላራሳቸው ደህንንነት ሲባል ነው የሚል መልስ ሰጠዋል። “በሰሜን አካባቢ የሚደረገው በረራ የደህንነት ስጋት ስላለበት፣ ማንኛውም አብራሪ በረራ ከማካሄዱ ከ24 ሰአታት በፊት ለመከላከያ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙ ተገቢ ነው ” የሚል መከራከሪያ በባለስልጣናቱ በኩል ቀርቧል።

ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር በአካል ተገናኝታችኋል›› የሚል ክስ የመሰረተባቸው ተከሳሾቹ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የሚገኙ በመሆናቸው መከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ይታዘዝልን›› የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
የፌደራል አቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ አይችሉም ብሎ

ሰራዊቱ የትጥቅ ትግሉን እየተቀላቀለ እንደሆነ ተገለፀ

ኢሳት ዜና (ሐምሌ 07 2007)በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተንሰራፍቶ ያለውን አፈናና የአንድ ብሄር የበላይነት በመሸሽ በርካታ ወታደሮች የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ መሆናቸውን በሽግግር መንግስት ወቅት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የነበሩት አቶ መሀመድ ሀሰን ለኢሳት አስታወቁ።
ሰሞኑን ወደ ኤርትራ በመጓዝ በዚያ የሚገኘውን የትጥቅ ትግል መመልከት እንደቻሉ የተናገሩት የቀድሞው ዲፕሎማት፣ በቆይታቸው ከሰራዊቱ ጋር የተሰደዱ በርካታ ወታደሮችን እንዳነጋገሩ ገልጸዋል።
እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1994 አ.ም ስራቸውን በገዛ ፍቃዳችው እንዳቋረጡ የተናገሩት አቶ መሀመድ ሀሰን፣ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦር የተባለ ሰራዊት እንዳሌላትና ሁኔታው የአፓርታይድ ጦር ሊያስብለው እንደሚችል አስረድተዋል።
በጦሩ ውስጥ ሀገራዊ ስሜት የለም ማለት ይቻላል የሚሉት አቶ መሀመድ የአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ በኦፊሰርነትና በተለያዩ ሀላፊነት ቦታዎች ተመድበው እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ነዋሪነታቸውን በቤልጂየም ያደረጉትና የቤልጂየም የሰራተኛው ፓርቲ አባልና አመራር የቀድሞው የኢትዮጵያ ዲፕሎማት መሀመድ ሀሰን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በአሁኑ ወቅት በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን መረዳት እንደሚችሉ በቃለ ምልልሳቸው አመልክተዋል።
ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተጀመረው ጥቃትም በመንግስት ላይ አለመረጋጋትን ሊያመጣ እንደሚችልም ገልጸዋል።
በስልጣን ላይ ያለው ገዢው መንግስት የከፋፍለህ ግዛን ስርአት ዘርግቶ እንደሚገኝ ያስታወቁት መሀመድ ሐሰን በአማራ፤ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብለዋል።