Wednesday, February 24, 2016

የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ጉብኝቱን መቼ እንደሚያካሂዱ ባይገለጽም፣ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት የስደተኞች ጉዳይ ዋና አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በጉብኝታቸው በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ አንስተው ከኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ይነጋገሩ አይነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን በማካሄድ ጫና መፍጠር ከቻሉ፣ ጠ/ሚኒስትሩ ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጡ ይችላሉ ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።

No comments:

Post a Comment