Monday, February 1, 2016

የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት በኢትዮጵያ ተጨማሪ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች መኖራቸውን አስታወቀ

ከሰላሳ ዓመት በኋላ የተከሰተውን ዘግናኝ የርሃብ አደጋ ተቋቁሞ የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ይቻል ዘንድ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት USAID የ100 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ልገሳ አደረገ። ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 10.5 ሚልዮን ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውን አመልክቶ ይህ አሃዝ በቅርቡ እንደሚያሻቅብ ስጋቱን ጠቁሟል።
የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት USAID ሃላፊ የሆኑት ጋይሌ ስሚዝ የሁኔታውን አሳሳቢነት ሲገልጹ ''አስከፊው እርሃብ ያስከተለው ቀውስ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል የኢትዮጵያ ሕዝብ የእኛ እርዳታ በአፋጣኝ ያስፈልገዋል''
በተጭማሪም አሉ ጋይሌ ስሚዝ ''በአፋጣኝ ተጨማሪ ግብአቶ...ችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ገበሬዎቹን ወደ አምራችነት እንዲመለሱ በማድረግ ከዚህ ቀውስ እንዲወጡ ማስቻል አለብን!'' በማለት ለረድኤት ድርጅቶችና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፕሬዝዳንት ባንኪ ሙን በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ በተከሰተውን ድርቅ ሳቢያ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት አስከፊ የምግብ ጥረት ስለሚከሰት ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት የእርዳታ እጃቸውን በአፋጣኝ እንዲዘረጉ ተማጽኖዋቸውን አቅርበዋል።
ባንኪሙን አክለውም ''አፋጣኝ ልገሳ በማድረግ የብዙዎችን ሕይወት በማዳን ቀውሱን መከላከል አለብን!'' ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበትን አስጊና አስፈሪ የርሃብ አደጋ ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎችን በጎበኙበት ወቅት የተባበሩት መንግስታትና ዓለም አቀፍ ለጋሾች በጋራ 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማለትም ከሃያ ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment