Wednesday, August 15, 2018

ለሱዳን ተላልፈው የተሰጡ የኢትዮጵያ መሬቶች በአቶ አባይ ጸሀዬ ፊርማ የተፈጸሙ መሆናቸው ተጋለጠ። ይህንን የሚያሳየውና የአቶ አባይ ጸሀዬ ስምምነት የተገለጸበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል።

No automatic alt text available.(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) ስምምነቱን የተፈራረሙት አቶ ደመቀ መኮንን እንደሆኑ ተደርጎ ለዓመታት ሲገለጽ የነበረው ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነም የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ አስታውቋል።
አቶ አባይ ጸሃዬ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ የተፈራረሙት ሰነድ ላይ መሬቶቹ በአስቸኳይ ለሱዳን ተላልፈው እንዲሰጡ የሚል ትዕዛዝ እንዳለበትም መረዳት ተችሏል።
በኢትዮጵያ ድንበር ጉዳዮች ኮሚቴ የተገኘው ሰነድ እንደሚያመለክተው በአቶ ደመቀ መኮንን ፊርማ የተፈጸመ ነው የተባለው ስምምነት ትክክለኛ እንዳልሆነ ተረጋግጧል።
ሰነዱን የፈረሙት የህወሀት አመራርና በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩት አቶ አባይ ጸሀዬ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
8 አንቀጾች ባሉት ሰነድ ላይ እንደተመለከተው በኢትዮጵያ ይዞታ ስር የሚገኙ ሶስት የእርሻ መሬቶች በአስቸኳይ ለሱዳን እንዲሰጡ አቶ አባይ ጸሀዬ በፊርማቸው ተስማምተዋል።

1600 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የሁለቱ ሀገራት ደንበር በተመለከተ የኢትዮጵያን ጥቅም ያልሰጠበቀ ስምምነት በህወሀት አገዛዝ በኩል መደረጉን በመግለጽ ተቃውሞ ሲቀርብ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን አገዛዙ የሚቀርቡትን ተቃውሞዎች መሰረተ ቢስ በሚል ሲያጣጥል ቆይቷል።
በሰነዱ ላይ እንደተመለከተው ግን ህወሀት ከኢትዮጵያ ህዝብ ደብቆ የተወሰኑ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱን ነው ለማወቅ የተቻለው።
የኢትዮጵያ መሬቶችን ለሱዳን ተላልፈው ከመሰጠታቸው ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ የነበሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው።
በሰነዱ ላይ ስምምነቱን የተፈራረሙት አቶ ደመቀ መኮንን አለመሆናቸው ተረጋግጧል።
በህወሀቱ አቶ አባይ ጸሀዬ ፊርማ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የተላለፉበት ስምምነት የተፈጸመው እንደ አውሮፓውያን አኦጣጠር በሚያዚያ 11/2005 መሆኑ ተመልክቷል።
በሱዳን በኩል ስምምነቱን የተፈራረሙት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዱራሂም ሞሀመድ ሁሴን ናቸው።
ይህ ስምምነት በይፋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለተገልጸ ሲሆን የሱዳን ባለስልጣናት ስነዱን በመያዝ የይገባኝናል ጥያቄአቸውን በሃይል ጭምር እያነሱ ለበረካታ የኢትዮጵያ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ግድያ እንግልት ያበቁ ግጭቶችን መፍጠራቸው የሚታወስ ነው።
አቶ አባይ ጸሀዬ በፊርማቸው ስላስረከቧቸው የኢትዮጵያ መሬቶች በተመለከተ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሜቴ መግለጫ በማውጣት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቋል።

No comments:

Post a Comment