Thursday, December 31, 2015

የኣባይ ግድብ ኣደጋ እንደሚደርስበት ባለሙያዎች ገለጹ

ግድቡ የተሰራበት ቦታ ከፍተኛ ሙቀት ስላለበት ግድቡ በግንባታ ሂደትላይ እያለ ውሃ መያዝ ካልጀመረ ያለምንም ሞያውያን ማማከር ወያኔዎች ለጥቅማቸው ሲሉ ብቻ ለግብጽ መንግስት ግድቡ ውሃ እንዳይዝ መፈረማቸው እዛው ግድቡ ላይ የተሰማሩት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን የፕሮጀክቱ ሃላፊ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ይህንን ኣረጋግጧል። በካድሬዎች ግን ማስፈራርያ እንደደረሰበትና ምንም ኣስተያየት እንዳይሰጥ ከውሉ ጋር ለማወቅ ተችሏል ምናልባት ይህንን ለማስተባበል በቅርቡ እንዲዋሽ ሊገደድም ይችላል። ወያኔው ግን ከህዝብ ለማምለጥ “ግንባታው ኣይቋረጥም” እያለ ነው ዋናው ቁም ነገር ግን ግንባታው ሳይሆጅ በጥቂርም ቢሆን ውሃ ካልያዘ የሚፈለገውም እርጥበት ካላገኘ እስከመሰንጠቅና መደርመስ ኣደጋ እንደሚደርስና ይህንንም ሆን ብለው ግብጾች በቂ ልምድ ስላላቸው እጃቸውን ይዘው ከተወሰነ ጉቦ ለወያኔ በማሳቀፍ እንደፈጸሙት እየተገለጸ ነው።
……61 ሺህ ሂወት የገበርንበት ባድሜ ለኤርትራ ሲበየን ህዝብ እንዳያምጽ ኣስቀድመው በውጭ ጉዳይ ኣማካኝነት ስዩም መስፍን ባድሜ ብቻ ሳይሆን ሌላም ያልጠየቅነውን ለኛ ተሰቷል ሚለውን መግለጫ እንደሰጡ ኣይዘነጋም።

የአገራችን መሬት ሲቆረስ ፣ ህዝባችን ሲጐዳ እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም! — ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር

ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር የቀረበ ወቅታዊ ጥሪ

እኛ የቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት ዓባላት ለአለፉት 25 ዓመታት በውድ የሃገራችን ሕዝብ ላይ ወያኔ/ህውሃት መራሹ ቡድን የፈፀመውና እየፈፀመ ያለውን ግፍ ፣ በደልና ሰቆቃ እንዲቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል መሆን እንዳለበት እናምናለን ። ይሁን እንጅ የሕዝባችንን ሰቆቃና መከራ፣ ስደትና ዕልቂት ከምንም ባለመቁጠር ይባስ ብለው የሃገሪቷን ልዑላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው ለመስጠት ሽር ጉድ በማለት ላይ ይገኛሉ

በኦሮምያ ተቃውሞው መቀጠሉን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች የተቃዋሚ መሪዎችን መሪዎችን ማዋከብ ቀጥለዋል

በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሳምንታት ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎአል። በተለይ በምእራብ ሃረርጌዋ መቻራ ከተማ ህዝብ ነቅሎ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ በሆድሮ ጉድሩ ደግሞ የተማሪዎችን ሰላማዊ ተቃውሞ ሌላ አቅጣጫ ለመስጠት በአካባቢው የተሰማሩት ወታደሮች በትምህርት ቤት ላይ ቦንብ ወርውረው አንድ ተማሪ መግደላቸውን የአሮሞ ፌደራሊስ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ ገብሩ ገብረማርያም ለኢሳት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን መታሰር አስመልክቶ የአሜሪካ ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤት መግለጫ አወጣ

የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በሰጡት መግለጫ በዚህ ዓመት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መሰረታዊ መብት ጥበቃ መገለጫ የነበረው የበርካታ ጦማሪያን ከእስር መለቀቅን ጨምሮ ፤ በኢትዮጵያ የታዩ መሻሻሎችን የምንደገፍ ቢሆንም፤ በቅርቡ የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞች ጉዳይ በጥልቅ አሳስቦናል ብለዋል፡፡

Tuesday, December 29, 2015

በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ለመሬት ዝርፊያ ከፍተኛ አመራሮችን ተጠያቂ አደረጉ

ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚገኙት ከፍተኛ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችና የስራ ሂደት መሪዎች ለኢሳት እንደተናገሩት ‹‹ በእኛ ዘመን መሬት በየትኛውም አቅጣጫ በሙሰኞች እጅ መውደቁ ቁጭት ፈጥሮብናል፡፡ ››ይላሉ ፡፡ ትልቁን ሚና የሚጫወቱት የስርአቱ አመራሮች ናቸው ሲሉ ይወቅሳሉ።
ከአደርባይነት የተላቀቀ አመራር ማግኘት ከፍተኛ የወቅቱ ችግር መሆኑን የሚናገሩት የስራ ሃላፊዎች በተለይ መሬት በከተሞች ላይ ትልቅና ፈታኝ በሆነ መንገድ በግለሰቦች እጅ እየተጠቃለለ መሆኑን ይገልጻሉ፡
‹‹በፈጻሚው አካልም መሬትን በተገቢ መንገድ ለማስተላለፍ የሚታዩ ውስንነቶች አሉ ›› የሚሉት የስራ ኃላፊ ባለሙያዎች ከባለሃብቱ ጋር በመደራደር ካለ አግባብ ለመጠቃቀምና የድሃውን ህብረተሰብ ንብረት ለመንጠቅ የሚሰራ ስራ እንዳለ ይናገራሉ፡፡ የፍትህ አካሉ ከደላሎችና ከሙሰኛ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር በመንግስት ክርክሮች ላይ ሁልጊዜም መሸነፍ እንደሚታይ የሚገለጹት ኃላፊው ይህም የስርዓቱ መሰረታዊ ችግር እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና የባህርዳሩ ሆምላንድ ሆቴል በአካባቢው የነበሩትን 62 አባዎራዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው በማፈናቀል በከተማዋ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የ20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ መቀበሉ ነዋሪውን እያነጋገረ ነው፡፡
በሆቴል ንግድ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ባለሃብቶች በተለየ ሁኔታ ያለ በቂ ምክንያት ሰፊ መሬት የተሰጣቸው የሆቴሉ ባለቤት ፣ ለገዢው መንግስት ካላቸው ቀረቤታ አንጻር ልዩ ልዩ ስብሰባዎችንና ግብዣዎችን ያለ ጨረታ እንዲሰጣቸው መደረጉ አግባብ እንዳልሆነ በዘርፉ ተወዳዳሪ የሆኑ ባለ ሆቴሎች ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡
በባህርዳር ከተማ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ነዋሪ 150 ካሬ ሜትር ቦታ በማጣት የመኖሪያ ቤት ችግር ላይ ባለበት ሁኔታ በከተማዋ ማዕከላዊ ቦታና ወደ አየር መንገድ በሚወስደው ሰፊ አስፓልት ዳርቻ የሚገኘው ይህ ሆቴል ፣ በሆቴል ማስፋፊያ ስም ቢሰጠውም በቦታው ላይ የሚገነቡት የሆቴሉ ተጨማሪ ህንጻዎች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ከሁለት ፎቅ ያልበለጡ ተራ ግንባታዎች መሆናቸውን ፕላኑን የተመለከቱ የክልሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
ከባህርዳር ዜና ሳንወጣ በከተማው የሚገኘው አባይ ድልድይ በተወሰነ ደረጃ የመስመጥ አደጋ በማጋጠሙ መኪኖች እስከ ግማሽ ሰዓት ድረስ ተራ እየጠበቁ ለማለፍ ተገደዋል፡፡ የግድቡ መበላሸት ያሳሰባቸው ነዋሪዎች ከአምና ጀምሮ ተደጋጋሚ አቤቱታዎችን ለኢሳት ሲልኩ ቆይተዋል።

ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ በኪሳራ ምክንያት ከንግድ ባንክ መዋሃዱን ሰራተኞች ተናገሩ

ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባንኩ ሰራተኞች እንደገለጹት ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እንዲዋሃድ የተደረገው ከጀርባው ያለውን የዘረፋ ወንጀል ሽፋን ለመስጠት ነው።ሰራተኞቹ በዘረፋው ወንጀል የበላይ የመንግስት አካላት እንዳሉበት ይገልጻሉ።
ባንኩ በ2008 ዓም 12 ሚሊዮን ብር መክሰሩን የሚገልጹት ሰራተኞች ለኪሳራው ምክንያት ናቸው ያሉዋቸውን በርካታ የሙስና ወንጀሎች ዘርዝረው አቅርበዋል።
ባንኩ አገልግሎትን እንዲያቀላጥፍ በሚል ቲ 24 የተባለ Core Banking software ቢገዛም ፣ ለግዢው የወጣው ወጪ ግን በአገሪቱ የሚገኙ ሌሎች የግል ባንኮች ካወጡት በሶስት እጅ ይልቃል። አብዛኞቹ የግል ባንኮች 80 ሚሊዮን ብር አውጥተው ሶፍትዌሩን የገዙ ሲሆን፣ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ግን ለተመሳሳይ ምርት 300 ሚሊዮን ወጪ አድርጓል። ባንኩ በድንገት ከንግድ ባንክ ጋር እንዲዋሃድ መደረጉ ንግድ ባንክም ተመሳሳይ ሶፍትዌር ያለው በመሆኑ ለዚሁ ግዢ ተብሎ የወጣው 300 ሚሊዮን ብር ዋጋ አልባ የሚያደርገው ነው ሲሉ ሰራተኞች ይገልጻሉ።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወጣቶቸ እያደኑ ማሰራቸውን ቀጥለዋል

ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ እንደገና ባገረሸበት ማግስት አመጹን ደግፈዋል በሚል በክልሎች እና በአዲስ አበባ የተለያዩ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። በአንቦና ወለጋ ዩኒቨርስቲዎች በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያው የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍ ከሚታወቁት መካከል ደግሞ የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ዮናታን ተስፋየ በደህንነት ሃይሎች ታፍኖ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስዶ ታስሯል።
ዮናታን ባለፈው ግንቦት ተደርጎ በነበረው ምርጫ ሰማያዊውን በመወከል ባደረገው የምርጫ ክርክር ብዙዎች ድጋፋቸውን ሰጥተውት ነበር። ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋውና ፍቅረማርያም አስማማው ሰላማዊ ትግል ታጋዮችን ከማስበላት በስተቀር ለውጥ አያመጣም በሚል ሰማያዊ ፓርቲን ከለቀቁ በሁዋላ አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ሲሄዱ መንገድ ላይ መያዛቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ጓደኛቸው ዮናታን ተስፋየ ግን በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት ይቻላል በሚል በፓርቲው ውስጥ ታቅፎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ወጣት ዮናታን፣ የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ማንሳታቸው ተከትሎ በሚሰጣቸው አስተያየቶች ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የተለያዩ ማስፈራሪያዎች ሲደርሱት ቆይቷል።
ከወጣት ዮናታን በፊት በማህበራዊ ሚዲያዎች የጎላ ተሳትፎ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ተይዞ ታስሯል።
መንግስት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ የኦፌኮ አመራር የሆኑትን እነ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ከ5 ሺ በላይ የኦሮሞ ወጣቶችን አስሯል። ከ124 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ በጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል።

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮናታን_ተስፋዬ‬ ተሰወረ

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የማህበራዊ ገፅ ንቁ ተሳታፊ የሆነው ዮናታን_ተስፋዬ‬ትላንት ጠዋት ለስራ ወደ ሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እንደወጣ ወላጅ እናቱ የተናገሩ ሲሆን አክለውም ከትምህርት ቤቱ ለማጣራት እንደሞከሩና ጠዋት ወደ ስራ ገብቶ እንደነበር እንደነገሩዋቸውና መቼ እንደወጣ እንዳላወቁ እንደነገሩዋቸው አሳውቀዋል የዮናታን የእጅ ስልክ ሲደወልለት የሚጠራ ሲሆን ነገር ግን አይነሳም የፌስ ቡክ አካውንቱም ከ18፡00 ሰዓታት በፊት ከኦንላይን እንደወጣ ያሳያል እስካሁንም ወደ ቤቱ አልተመለሰም የት እንዳለ ቤተሰቦቹም ሆኑ ጋደኞቹ አፈላልገውት ማግኘት አልቻሉም። በአንድ አሳቻ ቦታ ለሻይ እረፍት ሲወጣ ወይም ከሚያስተምርበት ቦታ የህወሀት ቅልብ ወንበዴዎች አፍነውት ነው ተብሎ ይገመታል።

በጋራ ከማልቀስ፣ በጋራ መታገል

 በአበበ ገላው
ከ66ቱ አብዮት ወሳኝ ትምህርት መቅሰም አለብን። የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች መሬት ላራሹ እና ዳቦ ለተራበው ነበሩ። የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት አልባ አድርጎ ሲያስገብር የነበረው ፊውዳላዊ ስርአት የተንኮታኮተው እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመነሳታቸው ብቻ አልነበረም። ኢትዮጵያውያን ሁሉ በገዥዎችና በተገዢው ጭቁን ህዝብ ያለውን የመደብ ትግል ተረድተው ከዳር እስከዳር በአንድነት መነቃነቅ በመቻላቸው ነበር።
በርግጥ ያለመታደል ሆኖ ያ ህዝባዊ አብዮት በወታደራዊ ሃይል ተቀልብሶ ሌላ አስከፊ አንባገነናዊ ስርአት ተተካ።ከዛ ዘመን በከፋ መልኩ ዛሬ የኢዮጵያን ህዝብ ከመሬቱና ከቀዬው እያፈናቀለ በረሃብ የቀፈደደውን የህዝብ ደም እየመጠጠ በዘር ከፋፍሎ እየቀጠቀጠና እየገደለ የሚገዛ ዘረኛ የውስጥ... ቅኝ ገዢ አስተሳሰብ ያለው የጥቂቶች ዘውጋዊ ስርአት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል እየፈጸመ ህዝብን በመግዛት ላይ ይገኛል።
ስለዚህም ነው የስርአቱ ሰለባ ሁሉ ልዩነቱን አቻችሎ በዘር ቆጠራ ላይ የተመሰረተውን የህወሃቶች ስርወ መንግስት ከስር መሰረቱ ለመጣል በጋራ መነሳትና መታገል የሚገባው። ሰሞኑን በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ አመጽም በድጋሚ ሊያስተምረን የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ ህወሃቶች የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም የማይፈጽሙት ወንጀል የለም። የህዝብ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ህዝብ በአሸባሪነት ፈረጆ ጦርነት ማወጅ የስርአቱን ቀቢጽ ተስፋነት በግልጽ አጉልቶ ያሳየ እውነታ ነው።
የህወሃቶች ስርወ መንግስት በስልጣን ላይ እስካለ ድርስ የየትኛው ህዝብ የመብትና የፍትህ፣ የእኩልነትና የነጻነት፣ የመሬትና የዳቦ ጥያቄ ፈጽሞ ሊመለስ እንደማይችል ግልጽ ነው። በመሆኑም በየአቅጣጫውና በየክልሉ የሚደረገውን ትግል ከፍ አድርጎ ብሄራዊ ንቅናቄ መጀመር የግዜው አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ከውጭም ከውስጥም በህብረት ለመታገል ሁላችንም ልዩነቶቻችንን አቻችለን በቅን ልቦና እንነሳ።
በተለይ ደግሞ አክቲቪስቶችና የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎች ለሚቀርቡላችሁ የጋራ የትግል ጥሪ ፈጣንና አወንታዊ መልስ እድትሰጡ በጭቁ ህዝባችን ስም እማጸናለሁ።
አንድነት ሃይል ነው!

Monday, December 28, 2015

በኮርያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት በመቃወምና እንዲሁም በኦሮምያ የደረሰውን ጭፈጨፋ በማውገዝ በኮርያ ሲዖል ከተማ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ፈት ለፊት የታቃዉሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሱዳን ኢምባሲ በማምራት የኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ ለመስጠት ያሰበዉ መሬት የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተቃወሙ በመሆኑ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ለወደፊቱ ለሚፈጠረው ዘላቂ ሰላም እና ጥሩ ጉርብትና ሲል ከመንግስት ጋር ምንም አይነት ድርድር እንዳያደርግ ጠይቀዋል። ከኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ የተዘጋጀዉን ደብዳቤም እንዲሁ ለኢምባሲዉ ልከዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ኢምባሲ በመሄድ መንግስት መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱን እንዲሁም በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግድያ፣ ድብደባ እና እስራት በጽኑ አውግዘዋል። የህዉሐት አገዛዝ በአገሪቷ ላይ እያካሔደ ያለዉን እርስ በርስ የማጋጨት ሥራ እንዲያቆምም ጠይቀዋል።

ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ማሰር መቀጠሉ እያሳሰበው እንደመጣ አሳወቀ።

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እለተ ዐርብ በጸጥታ ኃይሎች ከመንገድ ላይ ተይዞ የታሰረ ሲሆን፣የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ሚርካናም በደኅንነት ኃይሎች ተይዞ ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ ጂፒጄ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔት እየከፋ መምጣቱንና በአፍሪካ ውስጥ ካሉ አገራት ጋዜጠኞችን በማሰር የኢትዮጵያ መንግስት ከቀዳሚዎቹ ተርታ መቀመጡን ሲፒጄ በሪፖርቱ አስታውቋል።
የነገረ ኢትዮጵያው ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን በርካታ ጽሁፎችን በድፍረት በመጻፍ እንዲሁም በእስር ቤት የሚንገላቱ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ ተከታትሎ በመዘገብ ይታወቃል።
ከገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው እንደነበርና የታሰረውም ከስራው ጋር በተያያዘ መሆኑን ጋዜጠኛ ጌታቸው ለፍርድ ቤት ገልጿል።ሌሎች የሰማያዊ አባላትም ከጋዜጠኛ ጌታቸው ጋር አብረው ተይዘው ታስረዋል

የካራቶሪው ባለቤት መሬቴን ትነኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናትን አስጠነቀቁ

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋምቤላ 300 ሺ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ለማልማት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው የካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ከሪፖርትር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የጋምቤላ ክልል መንግስት በግድ ሳይፈልጉ በፈለጉት ዋጋ ከፍለው 300 ሺ ሄክታር መሬት እንደሰጧቸው ተናግረዋል። እኔ የጠየቁት 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ያሉት ባለሃብቱ፣ እነሱ ግን 300 ሺ ሄክታር ካልወሰድ ብለው ሰጡኝ ብለዋል።
መሬታቸውን ማንም እንደማይነጥቃቸው የተናገሩት ባለሀብቱ “መሬቴን ንኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ። ይሄ ማስጠንቀቂያ ነው። የእስካሁኑ የሚበቃ መሰለኝ። ራሴን መከላከል አያስፈልግኝም። ባለስልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት ውጤቱን ያገኙታል ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
“የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደሚሰጡኝ ይልቁንም እኔ በማምንበት ዋጋ እንድከፍል፣ ከዚያ ያነሰ መሬት ግን እንደማይሰጡኝ አስታወቁ፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፡፡” ተቀበልኩ የሚሉት ባለሃብቱ፣ በመካከለኛ ደረጃ ያሉ ባለስልጣናት ፖለቲካውን ተገን አድርገው ሊያሰሩኝ አልቻሉም ብለዋል።
ሼክ ሙሃመድ አላሙዲንንም በኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን የቻሉ መንግስት ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበርን ለማካለል የተጀመረ ስራ እንደሌለ የኮምኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች ደጋግመው እንዲሰሩ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጽ/ቤት አሳሰበ፡፡

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት ለኮምኒኬሽን ባለሙያዎችና ለጋዜጠኞች ባሰራጨው የመንግስት የሳምንቱ አቋም መግለጫ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ የተጀመረ ስራ እንደሌለ እንዲናገሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።
“መንግስት ሁሉም የኢትዮጵያ ድንበሮችን የማካለል ስራ ጠቃሚ መሆኑን ይረዳል”ያለው ፣ የአቋም መግለጫው፣ ሆኖም የኢትዮ-ሱዳንን ድንበር ለማካለል አሁን ምንም የተደረገ ስምምነት የለም።» በማለት በሱዳን ሚዲያዎች በተደጋጋሚ እየተዘገበ ያለውን ጉዳይ ለማስተባበል ሞክሯል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ለኢህአዴግ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር የኢትዮ ሱዳን ድንበር አካላይ የጋራ ኮምሽን ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አምነዋል። አያይዘውም በድንበሩ አካባቢ የሚኖሩ «ሽፍቶች» ያሉዋቸው ኢትዮጵያዊን ወደ ሱዳን ገብተው ግድያ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሃይለማርያም የኢትዮጵያ ባለሀብቶችና አንዳንድ አርሶአደሮች ሱዳን ክልል ውስጥ ገብተው መሬት እያረሱ መሆኑን መናገራቸው፣ ጠ/ሚኒስትርነታቸው ለኢትዮጵያ ነው ወይስ ለሱዳን የሚል ጥያቄ አስነስቶባቸው ሰንብቷል።

መንግስት በሃይል ሊያዳፍነው የሞከረው ተቃውሞ እንደገና አገረሸ

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ መንግስት አጋዚ የሚባለውን ጦሩን በማሰማራት ሊጨፈልቀው ያሰበው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደገና አገርሽቶ በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል። በወለጋ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በርካታ ተማሪዎች ተደብድበው ታስረዋል። ተማሪዎቹ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ወደ ጫካዎችና አጎራባች ከተሞች ቢያመልጡም ወታደሮቹ እግር በእግር እየተከታተሉ በመደብደብ አስረዋቸዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ወታደሮቹ ከትናንት በስቲያ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ገብተው በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ያደረሱ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችም ተይዘው ታስረዋል።
ዛሬ ደግሞ በሰሜን ሸዋ ኤጄሬ ከተማ ተማሪዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ተማሪዎች ተጎድተዋል።
መንግስት የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ ባደረገው ሙከራ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ሊግ 122 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ድርጅቱ የሟቾቹን ስም ፣ የትውልድ ቀንና ቦታ በዝርዝር አቅርቧል።
ህዝባዊውን ጥያቄ በሃይል ለመጨፍለቅ ከፍተኛ ሰራዊቱን ያሰማራው መንግስት፣ በተጨማሪም ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ ታዋቂ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ይዞ አስሯል። 4 አመታት እስር ቤት ቆይተው በድጋሜ የተፈቱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በድጋሜ ሲታሰሩ፣ ምክትል ዋና ጸሃፊው አቶ ደጀኔ ጣፋም እንዲሁ ታስረዋል።

Sunday, December 27, 2015

ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ነው

ambo
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰማ::
ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት መደፈራቸውን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል::
ፖሊሶች ሴት ተማሪዎችን መድፈራቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:

CPJ: Ethiopia arrests second journalist in a week, summons Zone 9 bloggers

The Committee to Protect Journalists calls on authorities in Ethiopia to release the editor-in-chief ofNegere Ethiopia online newspaper, Getachew Shiferaw, who was arrested on Friday, according to news reports.

Friday, December 25, 2015

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ይመለከታል! December 25, 2015



def-thumb
የንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት የትግል ጥሪ በ11ኛው ሰዓት ላይ እንደምንገኝ ገልጸዋል ። የ 11ኛው ሰዓት መልዕክት፣ አንደኛ፣ ወደ 12ኛው ሰዓት ወይም ወደ ፍጻሜው እየተቃረብን መሆኑን የሚነገረን ነው። የ11ኛው ሰዓት የትግል ጥሪ የአንድን የትግል ምዕራፍ ለመዝጋት እና አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሪው ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት ከአሁኑ ማሰብ መጀመር እንዳለብን የሚያነቃን ደወል ነው። 11ኛው ሰዓት ላይ ቆመን ከ12ኛው ሰዓት በሁዋላ ስለሚፈጠረው ነገር መጨነቅ ካልቻልንና በጊዜ ቤታችንን ካላሰናዳን ፣ ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ሊገጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶች በጊዜና ብቃት ባለው መልኩ ለመፍታት መቸገራችን አይቀርም ። አንድ በእድሜ የገፋ ሰው 11ኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ከህይወቱ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚኖረው ህይወት ማሰላሰሉ ተፈጥሯዊ ነው። የ11ኛው ሰዓት ጥሪም የአንድን አገዛዝ እርጅናና ፍጻሜ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ በቦታው የሚወለደውን አዲስ ስርዓት ምንነትም የሚያሳይ ነው።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የመሰጠቱን ጉዳይ ዳግም አረጋገጡ።

 
ንግግራቸው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አስመስሏቸዋል።
''በታሪካችን ያላየነው ረሃብ ላይ ነን'' አቶ ኃይለ ማርያም

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ታህሳስ 15/2008 ዓም በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ በተለይ በኦሮምያ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የድንበር ጉዳይ ላይ  የተለመደ አወዛጋቢ እና የበለጠ አወሳሳቢ ንግግሮችን ተናግረዋል።

በኦሮምያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ችግሩን፣መነሻውን እና መፍትሄውን የጠቆሙበት አገላለፅ የእራሳቸውን እና የመንግስታቸውን መፍትሄ ቢስነት በአደባባይ በድጋሚ ያጋለጠ ነው።ችግሩ ገበሬው መረጃ አለማግኘቱ ነው ማለታቸው እና በውጭ ኃይሎች ቅስቀሳ ነው የሚለው እርስ በርሱ የተቃረነ አነጋገር በእራሱ ለእራሳቸውም በአግባቡ የገባቸው አይመስልም።ችግሩን መንግስት ስለ ፕላኑ አለመንገሩ ነው ያሉት እና አሁን መንግስታቸው እያናገረ ያለው በጥይት መሆኑን ለሚያስተውለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግራቸው በሕዝቡ ላይ ከመዘባበት ያለፈ አንዳች የሚሰጠው ፋይዳ የለም።በመፍትሄነት ያስቀመጡትም ምንም አዲስ ነገር የሌለው እና አሁንም መልሰን እንነግረዋለን የሚለው አባባል ንግግሩ በጥይት እንደሆነ አመላካች ነው።ሕዝብ የሚባለው እና የሚደረገው ስላልገባው ነው የሚለው አባባል በእራሱ ለሕዝብ ያለን የንቀት ደረጃ አመላካች ነው።በሰላማዊ ሰልፍ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ እየሰቀሉ ድምፃቸውን ያሰሙ ታዳጊዎችን በጥይት አረር ከመቱ (እንደ አቶ ኃይለማርያም አነጋገር 'ካናገሩ') በኃላ አሁንም እናናግራለን እያሉ መዘባበት በእራሱ ህዝብን የአላዋቂነት ጥግ ነው።

Neamin Zeleke announces he will no longer work as managing director of ESAT due to other responsibilities

(ESAT News) — Mr. Neamin Zeleke announced today that he would no more work as managing director of the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT) effective from January 1, 2016, due to what he said was burdens from other commitments and to make room for other responsibilities.
Mr. Neamin Zeleke Patriotic Ginbot 7The Board of Directors of ESAT is in the meantime looking for a full-time managing director who would oversee the day-to-day activities of ESAT.
Mr. Neamin has been instrumental in establishing ESAT studio located in Washington DC five years ago and served as its manager till 2013. Since 2013, Mr. Neamin has served as the managing director of ESAT’S three studios: London, Amsterdam and Washington DC.
Mr. Neamin however promised he would continue to help ESAT in other capacities.

Thursday, December 24, 2015

ታንዛኒያ በሕገ-ወጥ ስደተኞች መጨናነቋን አሳወቀች

ታኀሳስ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና ቪዛ ሳይዙ ድንበር ተሻግረው ወደ ታንዛኒያ የሚገቡ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ቁጥር እያደር መጨሩንና ሁኔታው ከአገሪቱ አቅም በላይ መሆኑን የታንዛኒያው የአገር ውስጥ ሚንስቴር ቻርለስ ኪታዋንጋ አስታወቁ።
አብዛሃኞቹ ስደተኞች የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች ሲሆኑ የኢትዮጵያ፣ሶማሊያና ኤርትራ ዜጎች ቅድሚያውን ይወስዳሉ። በቅርቡ 42 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዳሬሰላም ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ሲገቡ መያዛቸውን ተከትሎ ሚኒስቴሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ከ10 ሽህ በላይ ሕገወጥ ስደተኞች በታንዛኒያ ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ በመግባታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
ታንዛኒያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚሻገሩ ስደተኞች መሸጋገሪያ መዳረሻ ናት። የሰብዓዊ መብት ተማጓቾች የታንዛኒያ መንግስት ለስደተኞች ሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ ባለ ሁለት አሃዝ እድገት እንዳስመዘገበች ገዢው መንግስት በመገኛኛ ብዙሃን ሌት ከቀን ቢለፍፍም ኢትዮጵያዊያን ግን የማትተካ ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ መፍለሳቸውን አላቋረጡም።

የዞን 9 ጦማሪያን በአቃቤሕግ ይግባኝ ተጠየቀባቸው

ታኀሳስ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በነሶልያና መዝገብ ከሽብር ነፃ የተባሉት አምስት ተከሳሾች ላይ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል በሚል ለታኅሣሥ 20 ቀን 2008 እንዲቀርቡ ተብለዋል።
መጥሪያው የደረሰው የበፍቃዱ ኃይሉ ሰነድ እንደሚያሳየው ይግባኝ የተባለባቸው በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ እና በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሀኔ እንዲሁም አቤል ዋበላ ናቸው። በፍቃዱ ኃይሉ የተቀየረለትን ‘አመጽ የማነሳሳት’ የወንጀል አንቀጽ ለመከላከል ለጥር 30, 2008 መቀጠሩ ይታወሳል።

ኢሳት ስርጭቱን ለማስጀመር በሂደት ላይ መሆኑን የስራ አመራር ክፍል አስታወቀ

ታኀሳስ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስና በዲፐሎማሲ ዘመቻ የኢሳትን የሳተላይት ስርጭት ለማፈን ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ከቆየ በሁዋላ፣ በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ስርጭቱ እንደገና ለቀናት እንዲቋረጥ አድርጓል። ስርጭቱ መቋረጡን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን የደረሱን ሲሆን፣ ኢሳት ወደ አየር ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ስራ አመራር ክፍል ገልጿል።
ኢሳት በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አየር እንደሚመለስ የገለጸው ድርጅቱ፣ ህዝቡ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ አሁንም በትእግስት ከኢሳት የሚሰጠውን መረጃ እንዲጠባበቅና የተለመደውን የድጋፍ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።

መንግስት ታዋቂ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን እየያዘ በማስር ላይ ነው

ታኀሳስ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት ወጣቶችን በየአካባቢው እያፈሰ ከማሰሩም በላይ የተቃዋሚ መሪዎችን ሲያስፈራራ ከቆየ በሁዋላ መሪዎችን ይዞ ማሰር ጀምሯል።
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ም/ል ሊ/መንበር አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ዋና ጸሃፊ የሆኑት የህግ ባለሙያውና ከ10 አመት በፊት በተደረገው ምርጫ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ደጀኔ ጣፋ ገለታ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ታስረዋል።
ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በመንግስት ላይ በሚያደርሱት ጠንካራ ትችት ይታወቃሉ። በተመሳሳይ ዜና በጅማ ሂምና ዩኒቨርስቲ የሚማሩ 13 የኦሮሞ ተወላጆች ተማሪዎችን ለተቃውሞ ቀስቅሰዋል በሚል እየተፈለጉ ነው። የዩኒቨርስቲው የጥበቃና ደህንነት የስራ ሂደት ቢሮ ባወጣው ማስታወቂያ ገመችስ ታከለ፣ አሸናፊ ሌንጂሳ፣ አለማየሁ ገመቹ፣ መብራቱ ጅሬኛ፣ መሃመድ ሸምሲዲን፣ አብዲሳ በንቲ፣ ፋጂ ሙላት፣ አብደላ ተስሳ፣ ዘነበች ጌታቸው ፣በሻቱ ቃናአ፣ ቢራ ነጋሽ ደመቀ እንዲሁም አሰፋ ፋና ታህሳስ 14 በዩኒቨርስቲው ተገኝተው የዲሲፒሊን ኮሚቴው የሚሰጠውን ውሳኔ እንደከታተሉ ተጠርተዋል። በኦሮምያ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ 85 ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ታስረዋል።

አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የኦፌኮ መሪዎች ታሰሩ

ኢሳት (ታህሳስ 14 ፣ 2008)
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ኦፌኮ ከፍተኛ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ከሰዓታት በፊት በመንግስት ሃይሎች ታሰሩ። 21 ደህንነቶችና ታጣቂዎች አዳማ የሚገኘውን የአቶ በቀለ ገርባ መኖሪያ ቤት ለ 5 ሰዓታት ያህል ሲበረብሩና ሲፈትሹ እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።
ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ለአምስት ሰዓታት ከተካሄደው ፍተሻና ብርበራ በኋላ፣ 12 ሰዓት ላይ አቶ በቀለ ገርባ በመኪና ወደአዲስ አበባ ተወስደዋል ተብሏል።
የኦፌኮ ም/ፕሬዚደንት አቶ በቀለ ገርባ፣ የአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ዞኖችን የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በመቃወም ፓርቲያቸው በሚያደርገው እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ ከሚያደርጉ መሪዎች አንዱ እንደሆኑ ይታወቃል።
አቶ በቀለ ገርባ ቀደም ሲልም ለ4 ዓመታት ወህኒ ውስጥ መቆየታቸው ይታወሳል። በፖለቲካ ምክንያት ከነሃሴ 2003 ጀምሮ በወህኒ ቤት የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ፣ ከእስር የተለቀቁት በቅርቡ በመጋቢት 2007 ዓም እንደነበር ይታወሳል።

ወያኔ ድብቅ ፍላጎቱን ለማሳካት የህዝብ ደም እስከመቼ እንዳፈሰሰ ይቀጥላል??? (የአብስራ ዳኛቸዉ)


  ሃገራችን ኢትዮጵያ ክብሯ ተነፍጎ የህዝቦቿ መብት እና ጥያቄ ተረግጦ ያለፍላጎቷ በብሄር እና በጎሳ ተከፋፍላ በጥቂት እራስ ወዳዶች በተያዘ ስልጣን እንዳሻቸው እያደረጉ የሀገር ፍቅር እና ንፁህ አእምሮ የሌላቸውን በሆዳቸው በመደለል የራሳቸው አሽከር በማድረግ ለእውነት እና ለህዝብ እኩልነት የቆሙትን ደግሞ በፈለጉት መንገድ በማስወገድ የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት ለማሳካት የህዝብ ደም በማፍሰስ እድሜያቸውን ለማራዘም ከበፊቱ የበለጠ ቀጥለዋል።

Wednesday, December 23, 2015

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ህዝቡ ትግሉን አፋፍሞ ለመቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታወቀ ።

በደቡብ ኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ፣ ቡሌ ሆራ፣ ደሬ ፣ ያቤሎ ፣ ዱግደዳዋ ፣ ተልተሌ ፣ አሬሮና በሌሎችም ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚገኙ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ገበሬዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ትግሉ የሚፈልገውን አስፈላጊውን መሰዋዕትነት በመክፈል እስከ መጨረሻው ለመጓዝ መቁረጣቸውንና እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ገለፁ ።

ሰበር ዜና ህወዓት በጎንደር ህዝብ ላይ የጅምላ ግድያ ለመፈፀም የትግራይ ተዋጊ ሚሊሻወችን እና አጋዚወችን ማሰለፉ ተሰማ።

ላለፉት ሳምንታት የተለያዮ የሁለቱ ክልሎች ባለስልጣናት እና የህወዓት ትግራይ የሚመራው የፌደራል ባለስልጣናት የወልቃይት ህዝብ እየሰበሰበ ሲያናግር ቢቆይም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እኛ አማራ እንጂ ትግራውያን አይደለንም በሚል ሰጣ ገባ ባለስልጣናት ያደረጉት ስብሰባወች ሁሉ ውጤት አልባ ሆነዋል። በዚህ ምክንያት የትግራይ መስተዳደር የወልቃይት ጠገዴ መሬት የትግራይ መሬት ነው በሚል ለአንዴ እና መጨረሻ ያለውን እልባት ለመስጠት የጦርነት ዘመቻ ማወጁን መረጃወች አመልክተዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ መላው የአማርውን ህዝብ ከጎናችን ሁኑ ሲሉ በተወካዮቻችው ለሰሜን ሸዋ፣ ወሎ ፣ጎንደር እና ጎጃም ህዝቦች በርካታ ወረቀቶችን በመበተን ጥሪ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ አስጠነቀቁ

“እናንተም ሆናችሁ ህወሓት የአገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበር ስላልቻላችሁ፣ ህዝቡንም መምራት ስለተሳናችሁ ስልጣናችሁን ልቀቁ አርበኞች ግንቦት 7 ይምራን…” በማለት ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በአንድነት ጠይቋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ለሱዳን ተቆርሳ የምትሰጥ አንድ ጋት መሬት እንኳን ብትኖር ህዝቡ ከውስጥም ከውጭም በአንድነት ለመዋጋት ቆርጦ እንደተነሳና ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ ማስጠንቀቂያ ጭምር አስተላልፏል፡፡

Monday, December 21, 2015

መድረሻ ያጡት 4500 ቅጥረኛ ወያኔዎች በአማራው ሀይል ተከበቡ

ተደጋግሞ እደተዘገበው ወያኔ በቅማንት ስም ጎንደርን ለመረከብ ሴራ ሲያሴር ከርሞ ብጥብጥ ፈጥሮ ነበር፡፡ ወዲያው በወያኔው ቅጥረኛ ሰራዊት ላይ አማራው “በሉ እንግዲህ ቋራ ላይ እንክተት” ብሎ ልክ አባቶቹና እናቶቹ በጥንት ዘመን ያደርጉ እንደነበረው ታጥቆ ተሰባስቦ ወደሽንፋ ሄደ፡፡ ወደቋራ ከዘመተው አማራም የደባርቅ፤ የበለሳ፤ የደብረታቦር፤ የጎጃም፤ የጎንደር አማራ ይገኝበታል፡፡ በመኪና እየተጫነ ሆ ብሎ ሽንፋ ገባ፡፡ በማሩ ቀመስ ደምቢያ በኩል ያለው አማራ ደግሞ ሆ ብሎ ወደዛው ወደሽንፋ ዘመቻ ሲያደርግ መንገድ ላይ ታቦት ከቤተ ክርስቲያን ወጥቶ በስንት ልመና ተመለሰ፡፡

ሰበር ዜና በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቀሰቀሰ

በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቆስቁሶ ነገር ግን የመጨረሻ የማጥቃት እርምጃ ለመዉሰድ ታግደናል እየተደበደብን ነዉ፤፤
ይላል የወያኔ መንግስት የሰሜኑ እና የምስራቁ እዝ።

ሰበር ዜና የሱዳኑ ፕርዝዳንት ኦመር ሃሰን አልበሸር በአሁኑ ሰአት አዲሰ አበባ ይገኛሉ


የሱዳኑ ልኡካን ቡድን የደንበሩን ጉዳይ ለመጨረሰ እና ለመፈራረም ዛሪ ሌልት 9፡00አዲሰ አበበ ባገብተዋል
ባልፉት ስምሳምንታት በጭንቅ የነበረው በሁሉም አቅጣጫ ህዝባዊ አመጹ ያስፈራው ወያኔ ከአመጹ ጀርባ አቀጣጣይ ናቸው
ያላቸውን እንደ ቢቢን ኢሳት ቲቭን ማፈኑ ይታወቃል ህዝባዌ

የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጠየቁ

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ የወሰደውን እርምጃ በጽኑ አውግዘዋል። የኦሮሞ ህዝብ በአጋንንት ተመስሎ ተሰድቧልና ተሳዳቢው ባለስልጣን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል።

መንግስት ለሞቱት ዜጎች ሃላፊነቱን እንዲወስድና ለህዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አሳስበዋል።በአዲስ አበባ የሚገነቡት ፎቆች የማን ናቸው? ሲሉም ጠይቀዋል።አርጅተናል አልቻልንም ስልጣናችንን እናስረክብ ያሉ አመራሮችም አሉ።

የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት በየአካባቢው እየዞሩ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፖሊሶች እየዞሩ የስርጭት መቀበያ ዲሾችን ከማስወረዳቸው በተጨማሪ ባለስልጣኖችና ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩና በስብሰባ ቦታዎች ሳይቀር ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት አስጠንቅቀዋል።

ሰሞኑን ኢሳት በናይል ሳት የሚለቀው ስርጭቱ ከገዢው ፓርቲ በተደረገው አፈና የተቋረጠበት ቢሆንም በዩቴል ሳት 70 ቢ፣ በ75 ዲግሪ ላይ አሁንም ስርጭቱን እንደቀጠለ ነው።

Sunday, December 20, 2015

75 killed in Ethiopia protests: HRW

east 75 people have been killed during weeks of protests in Ethiopia which have seen soldiers and police firing on demonstrators, Human Rights Watch said on Saturday.

“Police and military forces have fired on demonstrations, killing at least 75 protesters and wounding many others, according to activists,” HRW said in a statement.
There was no immediate response from Addis Ababa, but it has previously put the toll at five dead.

Saturday, December 19, 2015

የጎንደር አማራ በሶስት ግንባር ከጠላቶቹ ጋርበጀግንነት እየተፋለመ ነው:

gonder
1 _ በምእራብ በኩል መሬት ቆርሶ ሊወስድ ከተዘጋጀ ከሱዳን ጦር ሰራዊት ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ነው ።
2 _ በሰሜን ግንባር አባይ ወልዱ እያስታጠቀ ከሚያስገባው የትግሬ ታጣቂ ጋር እየተፋለመ ነው ።
3 _ ሶስተኛው ግንባር መሬት ቆርሶ ለመስጠት ከወሰነው የወያኔ ሰራዊት ጋር “መሬቴን የምትሰጠው ሬሳየን ተራምደህ እንጅ እስትንፋሴ እያለ የነፋሲለደስንና የመይሳውን መሬት ንክች አታደርጋትም ” እያለ እየተፋለመ ነው ።
*** ይህ በእንድህ እያለ የሱዳን መንግስት ” ከ 50 በላይ ዜጎቼ መሬቱ የኛ ነው በሚሉ ኢትዮጵያውያን ታጣቂወች ታፍነው ተወስደውብኛል ። ዜጎቼን ለማስለቀቅ የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር እየሰራ ነው የሚል አስገራሚ መግለጫ እውጥቷል ።
በሌላ በኩል የወልቃይት ማህበረሰብም “በትግራውያን የማንነት ዘረፋ ስለተፈፀመብን ወደ ትክክለኛው ማንነታችን አማራነታችን ለመመለስ በምናደርገው ፍልሚያ የአማራ ህዝብ ሊረዳን ይገባል ” እያለ ነው ።
እኛም ከዚህ ለነፃነቱ ለማንነቱ እና ለሀገሩ እየታገለ ካለው ህዝብ ጎን ልንሰለፍና አጋርነታችንን ልናሳየው ይገባል ።

Friday, December 18, 2015

የህወሓት የደንነት ቢሮ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን አስጠነቀቀ፡

የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር ወስኖአል። የውሳኔውን ቅጅ ከ አንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ጋር በአቶ ካሳ ተክለብርሀን በኩል ለጠቅላይ ሚንስትሩ ልኳል።

የአቶ ሀይለማርያም አስተዳደር አመፁን ለመቆጣጠር መመሪያ ከአሜሪካ መንግስት መቀበሉን በአስቸኳይ አቁሞ የተነሳውን መጠነ ሰፊ አመፅ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የሚያስችል የኦፕሪሽን መርሀ ግብር አውጥቶ ለፊደራል ፓሊስና መከላከያ ማስረከብና ለተግባራዊነቱም ካልተንቀሳቀሰ ሙሉ ሰላም የማስከበሩን ስራ መከላከያ ይረከባል ይላል። በአጭሩ መፈንቅለ መንግስት ይደረጋል ማለት እንደሆነ ምንጮቸ አረጋግጠዋለል።

መንግስት በልማት ስም እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የአየር ላይ ካርታ እያስነሳ ነው

ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህንነት ምንጮቻችን እንደገለጹት መንግስት እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጠሎአል። 99 በመቶ የሚሆነው ቦታ በአንድ ብሄር ተወላጆች የተያዘው የብሄራዊ ደህንነት መስሪያ ቤት ኢንሳ፣ ተላልፎ የሚሰጠውን መሬት የአየር ላይ ፎቶግራፍ እያነሳ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

የደህንነት ኤጀንሲው ፎቶ የማስነሳቱን ስራ የሚሰራው ትልቅ ለሆነ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚል ሰበብ ሲሆን፣ ዋናው አላማው ግን መሬቱን ለማካለል የሚሰጠውን ቦታ ለመወሰን መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ተቃውሞ እንዳይነሳ ለማድረግ የህዝቡን አጀንዳ በተለያዩ መንገዶች ለማስቀየር ተደጋጋሚ ሙከራዎች ማድረጉንም አክለው ገልጸዋል። የአየር ላይ ቅኝቱና ፎቶ የማንሳቱ ስራ እንደተጠናቀቀ ድንበር የመከለሉ ስራ ይከናወናል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደብድበው ታሰሩ

ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ምሽት የፌደራል ፖሊስ አባላት 6 ኪሎ ግቢ በመግባት 2 ተማሪዎችን ማሰራቸውን ተከትሎ የታሰሩት ተማሪዎች እንዲፈቱ በሰልፍ የጠየቁ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደብድበዋል።

Thursday, December 17, 2015

ከታጋይ አረበኛ ተስፋሁን‬ የንፁሃን አንገት በከንቱ እየተቀላ ዝምታ የለም::

ተነስ ተነስተዋል ጀግኖች አዋሳ አዲስ አበባ ጎጃም ባሌ አርባምንጭ ወሎ   ህዝብ ራሱን ከሞት የመከላከል ተፈጥሮዊ መብት አለዉ።በግልፅና በስዉር ጦረነት የታወጀበት ህዝብ አፀፋዊ

እርምጃ በገዳዮች ላይ መዉሰድ አለበት።ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ህዝብ ላይ ቃታ የሚስበዉን የወያኔ ማፍያ ቡድን ባገኘነዉ ነገር
ሁሉ እርምጃ እንዉሰድበት። በቅርብ ርቀት በቀላሉ በጠርሙስ ነዳጅ ሞልቷ በመወርወር ራሳችን እንከላከል። ገዳዮች ነፍስ
አላቸዉ:: በፍራት ይርዳሉ። ይበረከካሉ! በመጨረሻም እጅ ይሰጣሉ! ይቀጣጠል ይንደድ በታሪክ ህዝብ ተሸንፎ አያዉቅም።
እንደ ሰደድ እሳት በፍጥነት ይዳረስ። በአራቱም አቅጣጫ ፀረ ወያኔ ትግሉ ይቀጥል:: አለን ከጎናችሁ ነን ።የንፁሃን አንገት
በከንቱ እየተቀላ ዝምታ የለም:: አሁን ነዉ የአገሬ ሰዉ ጀምረናቸዋለን እንጨርሳቸዋለን ማለት:: በቃ የዘረኞችን እድሜ
ከዚሕ ላይ ያብቃ! በለዉ !በቃ በለዉ አገሬ
አገር አድን ንቅናቄ's photo.

ምእራብ ሸዋ ሚታ ሮቢ ከተማ ከባድ ተቃዉሞ ተጀምሯል:: ከ11 ሽህ በላይ ገበሬ ከሚናሬ ወደ ሽኖ ከተማ እየተመመ ነዉ::

ምእራብ ሸዋ ሚታ ሮቢ ከተማ ከባድ ተቃዉሞ ተጀምሯል::

ከ11 ሽህ በላይ ገበሬ ከሚናሬ ወደ ሽኖ ከተማ እየተመመ ነዉ::
ወያኔ አንድም እርምጃ ቢወስድ ምላሹ የከፋና በቂም የታጀበ ይሆናል:: በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ያቀረበን መግደል ማቁሰል የከፋ ዉጤት አለዉ::
በወለጋም በርካታ ቦታወች ተቃዉሞዉ የመለስ ዜናዊይን ምስል የኦህዴድን አርማ እየለቀሙ በማጋየት የቀጠለ ሲሆን ወሳኝ ወሳኝ መንገዶችም በመዘጋት ላይ ናቸዉ::
አዲስ አበባ በኦሮሞ ተወላጆች መኖሪያ ቤት ፍተሻ ተጀምሯል:: ወያኔ ያቄመዉ ሰዉ ቤት ፈንጅና ጦር መሳሪያ አስቀምጦ ድራማ ሊሰራ አስቧል::
በህዝብ ባስ በሰላም ባስ ህዝቡ መሄድ አደገኛና የወያኔ ቀጢይ ድራማ ሰለባ መሆን ነዉ:: ቤተክርስትያን መስጊድ ገበያ ሲኒማ ቤት ወዘተ… ህዝብ የሚሰበሰብባቸዉ አካባቢ ህዝቡ ጥንቃቄ ያድርግ:: ወያኒ አሸባሪ ፀረ ሰላም አፈነዳዉ ብሎ ህዝብን ንብረትን ለማዉደም አስቧል::
ጎንደር ፍጥጫዉ ቀጥሏል:: ከተማዋ እስከ መተማ አገሪቱ ተወጥራለች:: ባህርዳርና የጎጃም ከተሞች ሊወልዱ ምጥ ላይ ናቸዉ::
አርበኞች ግንቦት ሰባት ወያኔን ቁም ስቅሉን በማሳየትና የህዝብን ደም በመመለስና ተቃዉሞወችን በማቀናጀት የወያኔን ሴራ በማጋለጥ ተጠምዷል::

ከአራዳ ፍርድ ቤት እስረኞች አመለጡ | አካባቢው በተኩስ ተናወጠ

(ዘ-ሐበሻ) ከጥቂቅ ደቂቃዎች በፊት ለዘ-ሐበሻ በደረሰው ዜና መሠረት በአራዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ነውጥ ነበር:: የዚህ የተኩስ መነሻ ከልደታ ፍርድ ቤት እስረኞች ስላመለጡ ነው ተብሏል::
የአይን እማኞች እንደሚገልጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም እስረኞች ያመለጡ ሲሆን አክባቢው ተረብሾ ይገኛል::
የአይን እማኞች እንደሚገልጹት እስረኞች አምልጠዋል በሚል ከሃያ በላይ የጥይት ድምጾችን ሰምተዋል:: በተለይም በዛሬው ዕለት በዚሁ ፍርድ ቤት መምህር ግርማ ቀጠሮ ስለነበራቸው በርካታ ሕዝብ በአካባቢው ይገኝ እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸው ተኩሱ በተሰማበት ወቅት ፖሊስ ዛሬ በዳኛ አለመኖር ወደ ነገ ቀጠሯቸው የተሻገረው መምህር ግርማን በአስቸኳይ ይዞ ወደ ማረፊያ ቤት ይዟቸው ሄዷል::

Wednesday, December 16, 2015

በኦሮምያ ዛሬም ተቃውሞው ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ከባድ ማስጠንቀቂያ በሰጠ ማግስት በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች መንግስትን የሚቃወሙ ህዝባዊ አመጾች ተካሂደዋል። ህዝባዊ አመጾቹ በሃረርጌ አሰቦት፣ በምእራብ ወለጋ ባቡ ገምበሌና ነጆ፣ በሆድሮጉድሩ በጋጨቲ እንዲሁም በአሰላ የተካሄዱ ሲሆን፣ በቡራዩ ፣ አምቦና አወዳይ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰማርተው ቅኝት እያደረጉና የሚጠረጥሩት ወጣት እየያዙ እያሰሩ ነው።

ታህሳስ 5 በአወዳይ የነበረውን ተቃውሞ በማስመልከት ዘጋቢያችን ከቦታው ያጠነከረው ዘገባ እንደሚያመለክተው፣የጫት እና ሌሎች ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ይዘው የመጡ አርሶደአሮች በወታደሮች ተደብድበው ታስረዋል። ህዝቡ በተቃውሞው ወቅት ተይዘው በአወዳይ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ እስረኞች እንዲፈቱ ያደረገ ሲሆን፣ ከእስር ቤት ጠባቂ በተተኮሰ ጥይት ሶስት እስረኞች ቆስለዋል።ህዝቡ ቁስለኞችን ይዞ ወደ አብዲ በሽር መካከለኛ ክሊኒክ ሲወስዱዋቸው፣የክሊኒኩ ባለቤት ከመንግስት የሚደርሰውን ጥቃት በመፍራት አላክምም በማለታቸው የክሊኒካቸው መስታውት በተበሳጩ ወጣቶች ተሰብሯል። ግለሰቡ ለህብረት ባንክ ያከራዩት ፎቅ መስታውትም የተሰበረ ሲሆን፣ ባለሀብቱም ግንባራቸው በድንጋይ ተፈንክተዋል።
ህዝቡ መንግስትን ከመቃወም ውጭ እርስ በርስ የነበረው መከባበር አስገራሚ እንደነበር ዘጋቢያችን አክሎ ገልጿል።
በኦሮሚያ ከተሞች እየተቀጣጠለ ያለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአዲስአበባም ሊቀጥል ይችላል በሚል ስጋት የጸጥታ ቁጥጥሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠብቋል፡፡ ወረዳዎችም ሕዝቡን እየሰበሰቡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲመካከሩም ከአ/አ አስተዳደር ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡
በአዲስአበባ ጎዳናዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ዱላ እና ክላሽ የያዙ ፖሊሶች በብዛት የተሰማሩ ሲሆን በከተማዋ የሚገኙ ዓለምአቀፍና አህጉራዊ ደርጅቶች ጥበቃቸው ተጠናክሮአል፡፡ በብዙ የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ ጫማ የሚጠርጉ ሊስትሮወች ሳይቀሩ አንዳች የተለየ እንቅስቃሴ ሲያዩ ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዋል፡፡
ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የኦሮሚያን ተቃውሞ በጠመንጃ ሃይል ለመቆጣጠር ባለፈው አንድ ሳምንት ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ተቃውሞን ከመቆጣጠር ይልቅ በተቃራኒው እየተባባሰ መምጣቱ የአገዛዙን መሪዎች አስደንግጦአል፡፡
የመብራት እና ኢንትርኔት መስመር መቆራረጥ እጅግ ተባብሶ ቀጥሎአል።ከአዲስአበባ በተለያዩ ወረዳዎች አመራሮች በስብሰባ የተወጠሩ ሲሆን ሕዝቡንም በየአዳራሹ እየሰበሰቡ እንዲያወያዩ በታዘዙት መሰረት ስራቸውን ማከናወን ጀምረዋል፡፡
መንግስት ተቃውሞው ወደ ህዝባዊ አመጽ መሸጋጋሩን አስታውቋል።

አርበኞች ግንቦት7 ከመንግስት ወታደሮች ጋር ተከታታይ ውጊያ እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የንቅናቄው ከፍተኛ የአመራር አባል የሆነው እንደገለጸው የንቅናቄው ሰራዊት ዋልድባ አካባቢ የነበረውን ወታደራዊ ቀለበት በመስበር በአድርቃይ ላይ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ29 በላይ ወታደሮችን ገድሏል። ጦርነቱ አሁንም ቀጥሎአል። በግንባር የተሰለፉ 6 አብሪዎች ወይም በቅኝት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ አባሎቻቸው ከፍተኛ ውጊያ አድርገው ጥይታቸው ማለቁን ተከትሎ በወያኔ እጅ ወድቀዋል ሲል ታጋይ ዘመነ አክሎ ገልጿል። ከተከዜ ወደ መሃል አገር እየገሰገስን መሆኑን መንግስት ራሱ የለቀቀው መረጃ ያመለክታል የሚለው ታጋይ ዘመነ፣ መተማ አካባቢ በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች አሁንም ድረስ ትግል በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ታጋይ ዘመነ መተማ ዘባጭ ውሃ አካባቢ ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ከ9 እስከ 10 ሰአት በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ባደረሱት ጥቃት 19 የልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውንና 20 ቁስለኞች ሸዲ ሆስፒታል ገብተው በመታከም ላይ መሆናቸውም ገልጿል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩትን ህዝባዊ ተቃውሞች የአርበኞች ግንቦት7 ንቅናቄ ሙሉ ድጋፉን እየሰጠ መሆኑን ታጋይ ዘመነ አክሎ ገልጿል ፡፡ መንግስት 5 የአርበኞች ግንቦት7 አባላትን አድርቃይ ላይ መማረኩን መግለጹና ጦርነት መካሄዱን ማመኑ ይታወቃል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በመከላከያ ምስክርነት እንደማያቀርበው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አሳወቀ

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርበው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ18 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በመሆኑና ከአሁን ቀደም ምስክር ሆኖ ከማረሚያ ቤቱ ወጥቶ መስክሮ ስለማያውቅ ለምስክርነት ለማቅረብ እንቸገራለን የሚል ደብዳቤ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ለልደታ ፍርድ ቤት መላኩን ተከትሎ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለምስክርነት ሳይቀርብ ቀርቷል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአንድ አመት በፊት ከ6 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ተኩል ለ30 ደቂቃዎች ሲጠየቅ የነበረውን ሕገ መንግስታዊ መብቱ በመጣስ ወሕኒ ቤቱ በአሁኑ ሰዓት እንዳይጠየቅ ከማድረጉም በተጨማሪ በተደጋጋሚ የታሰረበትን ክፍል በመፈተሽ መፅሃፍ ቅዱስ ሳይቀር እንዳያነብ መከልከሉን ነገረ – ኢትዮጵያ አክሎ ዘግቧል።

Tuesday, December 15, 2015

ገዢው ፓርቲ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ ዛሬ ማክሰኞ ብቻ ከ11 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በገዢው ፓርቲ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 በላይ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል።

በሰሜን ጎንደር የመንግስት ሹመኞች የለኮሱት ግጭት ደም አፋሳሽ ሆነ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሆን ብለው በቀሰቀሱት ግጭት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እየተፈናቀሉ ነው።

ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት ጥቃቱን የሚፈጽሙት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው የመንግስት ሚሊሺያዎችና አስተዳዳሪዎች ናቸው። አንድ ባሏ ፊቷ ላይ የተገደለባት ሴት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በመንግስት አቀናባሪነት መፈጸሙን ገልጻለች።

ርእዮት አለሙ ጋዜጠኛና መምህር ርእዮት አለሙ ከአረበኞች ግንቦት 7 ተቀላቀለች።

ርእዮት አለሙ
ጋዜጠኛና መምህር ርእዮት አለሙ ከአረበኞች ግንቦት 7 ተቀላቀለች።
ርእዮት አለሙ በቃል ምልልስ እንደተናገረችው
ዳግም እስር ቤት አልመለስም ዙሬ ቃሊቲ አልገባም ብላለች ።
ርእዮት እንዳለችው መንግስትን የማይደግፉ ጋዜጣዎች ተዘግተዋል።
ጋዜጠኛ የእውነት ከፃፍ ቦታው እስር ቤት ነው ሌላው ይቅርና በፌስ ቡክ መፃፍ ራሱ እስር ቤት እያስገባ ነው።
ስለዚህ የአረበኞች ግንቦት 7 ጋር ተቀላቅያለሁ በማለት አስታውቃለች

Conflict between Amharas and Qimants worsens in Gondar

Several people were feared dead in a conflicted that was believed to be intentionally instigated by the TPLF regime’s operatives between the Qimant and Amhara ethnic groups.

Unconfirmed reports say more than 50 people were killed so far in Gondar in the ensuing conflict. Yet, ESAT’s endeavor to confirm casualties from North Gondar Police Headquarters was unsuccessful.
Reliable sources told ESAT that the government has armed some members from both sides leading to a full scale conflict between the two people.
“The conflict has widened its scope; there is a fight in Negade Bahir, Chonchiq, Bhona, and Gubbay,” sources told ESAT.
On Sunday, the government forces burnt homes and crops of farmers. Later, the farmers pursued and battled them, according to ESAT’s sources. The government militia are said to be plotting similar action in Armachiho, sources said.
Gondar has become a battle field in many fronts. The TPLF regime has given a huge tracts of land to Sudan, which in return agreed not to host Ethiopian opposition guerrilla fighters. Most of the Northern and North Eastern part of Gondar was also ceded to Tigray in the last 24 Years. Currently, a fight is underway between the Amhara and Qimants, who were given arms by the regime. ESAT’s reliable sources say the TPLF has provided weaponry and strategic support for some Qimants to wage war against the Amharas, whom the regime perceives as its enemy. The TPLF has also opened an office for Qimants in Mekelle, ESAT’s sources said.

Monday, December 14, 2015

በኦሮምያ የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱን እየሰፋ ነው

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ላለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም መቀጠሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ለመከላከል መከላከያ ሰራዊቱን ሳይቀር አሰማርቶ በወሰደው እርምጃ ከ45 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል። በመላ ኦሮምያ በሚገኙ ከተሞች የፀጥታ ሃይሎች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ።የመንግስት ባለስልጣናት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባራዊ አይደረግም በማለት ህዝቡን ለማሳመን ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካለቸውም። በየቀኑ እየጨመረ የመጣው ተቃውሞ ያሳሳበው መንግስት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው ሲሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ክስ እያቀረቡ ነው። ከወሊሶ 100 ኪሜትር ርቅት ላይ በምትገኘው አመያ ወረዳ ገጠር ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ከአካባቢው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ አባላት ነዋሪዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ ሲቀሰቅሱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በሰሜን ጎንደር የተነሳው ግጭት እንዳልበረደ ነዋሪዎች ተናግሩ

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ እንዳስነሳው በሚነገረው ግጭት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በአማራና ቅማንት ህዝብ መካከል ለዘመናት የቆየውን አንድነትና ዝምድና በማፍረስ አካባቢውን ወደ ግጭት ለመቀየር ገዢው ፓርቲ አስታጥቆ ያሰማራቸው ሚሊሺያዎች ግድያ እየፈጸሙ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። እንዲህ አይነት ድርጊት ተፈጽሞ አያውቅም የሚሉት ነዋሪዎች ግጭቱ እየተስፋፋ የተለያዩ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን እያካተተ መምጣቱን ገልጸዋል። ነጋዴ ባህር፣ ጮንጭቅ፣ ብሆና፣ ጉባይ በተባሉት አካባቢዎች አሁንም ድረስ ግጭት አለ። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ከ50 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ቢገልጹም፣ ኢሳት የተጠቀሰውን አሃዝ ከሰሜን ጎንደር ፖሊስ ጽ/ቤት ለማረጋገጥ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም።

ትናንት ምሽት ጭልጋ ጮንጭንቅ በሚባለው አካባቢ የመንግስት ታጣቂዎች መኖሪያ ቤቶችንና የስብል ክምር አቃጥለው ሲሮጡ፣ ገበሬዎች ተከታትለው በታጣቂዎቹ ላይ ተኩስ ከፍተዋል። ግጭቱ ይህን ዜና እሳካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልበረደም። በአርማጭሆም ልዩ ሃይሎች ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ልዩ ሃይሎች ከትክል ድንጋይ ትምህርት ቤት ጀርባ ባለ ተራራ ላይ መትረጊስ ጠምደው በመታየታቸው ተማሪዎች አንማርም ብለው ትምህርት ቤቱን ለቀው ወጥተዋል። ሽንፋ ላይ ደግሞ ታጣቂዎቹ ሰዎችን ከቤት እያስወጡ ንብረታቸውን ዘርፈዋል።

በሃዋሳ እና ሻሸመኔ መግቢያ አካባቢ ቦንብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በአንዋር መስጊድ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ ፣ ዛሬም በአዋሳና ሻሸመኔ ድንበር አካባቢ ተመሳሳይ ፍንዳታ ተከስቶ 2 ሰዎች ተገድለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ ጥቃቱ በኦሮምያና ደቡብ ክልሎች መካከል መካሄዱ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ለማጋጨት ሊሆን ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በአ/አ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ ፡፡

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ማደያዎች ነዳጅ በሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ተጨናንቀው ውለዋል።

እንዲህ አይነቱ ክስተት አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ቢሆንም፣የዛሬው ከሌሎቹ ጊዜያት የሚለየው በበርካታ ማደያዎች ነዳጅ ባለመኖሩ ነው፡፡ የችግሩ ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም አንዳንድ ምንጮች በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ከተከሰተው
የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ነዳጅ መግባት ባለመቻሉ ነው ብለዋል።

ወያኔዎች ነገሩ ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖባቸዋል።

ላለፉት በርካታ አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየከረረ ነው፤ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል እያልን ስንጎተጉትና ስንጽፍ ነበር። ህዝብ ይሄንን መንግስት በጣም እንደሚጠላ፤ ሕዝብ ጨዋ ስለሆነ ታግሶ እንጂ የመረረው እለታ ጉድ እንደሚፈላ ስንናገርና ስናስጠነቅቅ ነበር። ሰዎቹ አልሰሙንም። ጭራሽ 100% አሸነፍን ብለው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት በገሃድ አሳዩ።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ጠረፍ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል።

45 ሱዳናውያን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ተወሰዱብኝ ስትል ጸረ ሰላም ያለቻቸውን በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ዓውግዛለች፥ በተጨማሪም ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጠርፍ ተሻግረው ሸፈቱ ሲል እሄው የሱዳን አረብኛ ጋዜጣ ዘግቧል።

በወገኔ ላይ አልተኩስም ያሉ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እያቃጠሉ ሕዝቡን እየተቀላቀሉት ነው ተባለ

በኦሮሚያ እና በ150 የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣን ለማብረድ መንግስት ወታደሮቹን አሰማርቶ ትናንት ብቻ በም ዕራብ ሸዋ እና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ 25 ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ከሃገር ቤት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ሕዝቤ አልተኩስም ያሉ ሕወሓት የሚያዘው መከላከያ ሚ/ር ወታደሮች በየቦታው ዩኒፎርማቸውን በአደባባይ በማቃጠል ሕዝቡን እየተቀላቀሉ ነው::

ሕዝብን ከመጨፍጨፍ እየዘመተ ያለው ጦር –

በነሶሞራ የሚመራው እዝ፣ ህዝብን ለመጨረስና በሃይል አንገትን ለማስደፋት ሁለት ዲቪዝን ጦር ወደ ምራብ ሸዋና ወለጎ እየወሰደ ነው። ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ አገዛዙ ሊወስደው የሚችለው የመጨረሻ ተግባር ነው። ጎንደር ላይ ከሰፈረው ጦር በተጨማሪ ወደ ኦሮሚያ እየተሰማራ ያለው ሲደመርበት በሌሎች ከተሞች የሚኖረው ጦር በጣም የተመናመነ ነው።

በመሆኑም በአዲስ አበባ. በጎጃም፣ በወለኦ፣ በሰሜን ሸዋ፣ እና በደቡብ ክልል ሕዝቡ ለነጻነትና ለመብት ድምጹን ማሰማት ቢጀመር ይሄ ስርዓትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመገርሰስ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።
በመሆኑም ሌላው ማሀበረሰብ ድምጹን ያሰማ ዘንድና በኦሮሚያና በጎንደር ለመብታቸው ከቆሙ እየተገደሉ ካሉ ወገኖቻችን ጎን እንዲቆም ያስፈልጋል።
እስከአሁን በጎንደር ከ150 በላይ ዜጎንች የተገደሉ ሲሆን በኦሮሚያ የዛሬን ቀን ሳይጨመር ከሰባ በላይ ሕይወታቸው አልፏል።

ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ መስመር የሚወስደው መንገድ ቡራዩ ላይ በሕዝብ እንደተዘጋ ነው::

በዛሬው እለት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የሚቃወመው የቡራዩ ከተማ ጠዋት የጀመረው የሕዝብ ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል::የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ሕዝቡ ላይ እየተኮሱ ነው:: የመንግስት መስሪያ ቤቶች ትምህርት ቤቶች እና መደብሮች የተዘጉ ሲሆን እስካሁን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 3 ሰዎች በወያኔ ተገድለዋል::እንዲሁም – በጂማዓርጆ ወለጋ – በጫንጮ – በዴሳ – ሜታሮቢ- ጊንጪ – ነጆ- ሚናሌ- እላ ጎሮ – ሜታ- ነቀምት – ደምቢዶሎ ቀለሜ- ጊንዶ -አስጎሪ -ደንዲ -ቱሉ ቦጃ -ጫሊያ- አቺማ ጆሪ -ጊዳ -ዋራ ጂሩ – ሆሮ ጉዱሩ ተቃውሞው ተፋፍሞ ቀጥሏል::በጀልዱ ጎጆ ከተማ ሰባት ሰዎች ከአግኣዚ ጦር በተተኮሰ ጥይት ቆስለዋል::

Sunday, December 13, 2015

ቋራ ዛሬም በተኩስ ስትናጥ አደረች:: የጎንደር ግጭት የደም ጎርፍ ፈጠረ::

ቋራ ዛሬም በተኩስ ስትናጥ አደረች:: የጎንደር ግጭት የደም ጎርፍ ፈጠረ:: በህወሃት የተጠነሰሰዉ ሴራ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ አካባቢዉን ሙሉ በሙሉ የጦር አዉድማ አድርጎታል:: በነፍስ ገብያ ያሉ ቁጥር 4 እና ቁጥር 3 የሰፈራ ጣቢያ ያሉ ህፃናት እና ሴቶች ህይወት ተቀጥፎል:: የተረፊት በቋራ ገበሬዎች ጥበቃ እየተደረገላቸዉ ነዉ:: በአካባቢዉ ገነዉ የነበሩ እና የህወሃትንስዉር ሴራ ሲያስፈጥሙ የነበሩ የህወሃት ባለሃብቶች እሳቱእያቃጠላቸዉ ነዉ::

አርበኞች ግንቦት 7 በህወሓት ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን ገለጸ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በህወሓት አገዛዝ የጦር ኃይል ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ!!

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ተደጋጋሚ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የህወሓትን መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡

Saturday, December 12, 2015

የመተማ መንገድ ተዘጋ

በሰሜን ጎንደር መተማና የሱዳን ቦርደር ጋላባት መንንገድ ሙሉ ለሙሉ እንደተዘጋ ከስፋራው የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል። ከሱዳን ፖርት ወደብ ነዳጅን ጨመሮ ወደ ኢትዮጵያ በተለይም ለጎንደርና ለትግራይ የሚገባው በመተማ በኩል እንደሆነ ይታወቃል።
በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ፣ በአርማጭሆ በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች እንደሚከሰቱ ይታወቃል። በተለይም በወልቃይት ጠገዴ የሚኖረው ሕዝብ “ወደ ትግራይ ክልል የተቀላቀልነው በኃይል ነው። እኛ ጎደሬዎች ነን” በሚል ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው።

በሰሜን ጎንደር መተማ ላይ እየሆነ ያለው ይህ ነው። በአጋዚ ዘረኛ ጦር የተገደሉ አማሮች!!!

በተጨማሪም ለጉልበት ስራ በመተማ በኩል ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጲያዊያን ወጣቶች በጥይት ተጨፈጨፉ!!

ለማሽላ ቆረጣ በአንድ ሱዳናዊ ባለሃብት አማካኝነት ወደ ሱዳን ከገቡ የጉልበት ሰራተኞች መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጲያዊያን ወጣቶች በሱዳን መከላከያ ሰራዊት በጂምላ መጨፍጨፋቸውን የአርበኞች ግንቦት ፯ ድምፅ የራዲዮ ዜና ምንጮች ገለጹ፡

በድርቁ ሳቢያ በሞያሌ ከተማ የአተት ወረርሽኝ ተቀስቅሷል

ከድርቁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያና የኬንያ አዋሳኝ ከተማ በሆነችው ሞያሌ ከተማ፣ የአተት ወረርሽኝ ተከስቶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ወደ 90 ገደማ የሚሆኑ በበሽታው ተይዘው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡
በከተማው በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ተይዘው በጤና ተቋማት የታከሙት 91 ያህል ሲሆኑ 71 ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ 18 ደግሞ እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ ህክምና ሲወስዱ ነበር ተብሏል፡፡

በድርቅ የተጎዱና የተረጂዎች ብዛት 18 ሚሊዮን ደርሷል ተባለ

በድርቅ ሳቢያ ለረሃብ የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን ከአስር ሚሊዮን በላይ እንደሆነ በመጥቀስ በይፋ የእርዳታ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ የተረጂዎች ጠቅላላ ቁጥር 18 ሚሊዮን እንደደረሰ ተገለፀ፡፡
የድርቁ አደጋ ከባድ መሆኑን በመግለጽ ለቀረበው የእርዳታ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት የእንግሊዝ የውጭ ተራድኦ ሚኒስትር፤ በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ድጋፍ የሚያገኙት 7.9 ሚሊዮን ሰዎችን ጨምሮ የተረጂዎቹ ቁጥር 18 ሚሊዮን ሆኗል ብለዋል፡፡
በድርቁ ተጎጂ የሆኑ ዜጎች በጥር ወር ወደ 10.2 ሚሊዮን እንደሚያሻቅብ መንግስት ይፋ ያደረገ ሲሆን ለመጀመሪያው ዙር እርዳታ 516 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡ መንግስት ለለጋሽ ሀገራትና ተቋማት የእርዳታ ጥሪ በይፋ አቅርቧል፡፡
ለምግብ ግዢ ብቻ 1.1 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው የጠቀሰው መንግስት፤ አጠቃላይ የድርቁን ችግር ለመቋቋም ከ1.4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡
በትግራይ የድርቁ ተጎጂዎች 1.2 ሚሊዮን፣ በአማራ ክልል 2.3 ሚሊዮን፣ በአፋር 409,200፣ በኦሮሚያ 3.8 ሚሊዮን፣ በደቡብ ክልል 668,900፣ በሱማሌ 1.5 ሚሊዮን፣ በድሬደዋና በሐረሪ በድምሩ ከ80 ሺህ በላይ፣ በጋምቤላ 37 ሺህ 450 እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 83,476 መሆናቸውን የመንግሥት ሪፖርት አመልክቷል፡፡
ለድርቁ የውጭ ሀገራት ለጋሽ ድርጅቶችና ተቋማት ድጋፍ እንዲቸሩት በትናንትናው እለት መንግስት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከ50 በላይ ለሚሆኑ ዲፕሎማቶችና አለማቀፍ ለጋሽ ተቋማት ስለድርቁ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
ከድርቁ ጋር በተያያዘ ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት አስቸኳይ አልሚ ምግብ ይፈልጋሉ ያለው መንግሥት፤ 3.6 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ ድርቅ አምጪ በሆኑ የተለያዩ በሽታዎች ሊጠቁ እንደሚችል ሪፖርት አድርጓል፡፡  ድርቁ በአጠቃላይ 429 ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን 286 ሺህ 400 ሰዎችን ሊያፈናቅል ይችላል ተብሏል፡፡

በምዕራብ ሸዋ የተለያዩ መንደሮች ከ100, 000 ሕዝብ በላይ ለተቃውሞ አደባባይ ወጣ

በምዕራብ ሸዋ በጊንዶ ከተማና በአካባቢዋ የሚገኙ መንደሮች በአጠቃላይ ከ100 ሺህ ህዝብ በላይ ወጥቶ ስርዓቱን በመቃወም ላይ ይገኛል:: ዛሬ ዴሴምበር 12, 2015 የተደረገውን ተቃውሞ ትላልቅ እናት እና አባቶች ሳይቀሩ ተቀላቅለውታል:: በጊንዶ ከተማ የተለያዩ ቃጠሎች በየአደባባዩ እየታዩ ሲሆን የአጋዚ ጦር አካባቢውን በሁለት አቅጣጫ እንደከበበው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል:: ቀጣይ ፎቶዎች ይናገራሉ:: ከዚህ ቀደም በነበረው የዘ-ሐበሻ ዜና በጅማ ከተማ የተፈጠረው ተቃውሞ አሁንም እንዳልበረደ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ:: በባሌ ደንበል ታውን የተነሳው ተቃውሞም እንደቀጠለ ነው:: 

የአርበኞች ግንቦት 7 የመጀመሪያ ምክርቤት ስብሰባ መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከህዳር 26 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓም ድረስ ሰራዊቱ በሚገኝበት የትግል ቦታ የመጀመሪያውን የምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ በስኬት አጠናቋል::

ይህ ስብሰባ የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። የፓርቲ መሪዎች የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ በቀለ ነጋ በፖሊሶች ታይዘው ተወሰዱ::

ምኒሊክ ሳልሳዊ #Ethiopia #Oromoprotests is Underway in Welega University – በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።በአምቦ ገበያው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተቀየረ::በቀበሌ 6 አምቦ ለቅዳሜ ገበያ የወጣ ሕዝብ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማ ነው::

Friday, December 11, 2015

በኦሮምያ የሚካሄደው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው።

ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ አርሲ ዞን ከሻሸመኔ በ60 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ አዳባ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው በጥይት መመታቱ ታውቃል። የቀበሌ ጽህፈት ቤቱ እና የወረዳው የፍርድ ቤት መዝገብ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ ወድሟል።

ተመሳሳይ ተቃውሞ በነቀምትም በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ወደ አምቦ የሚወስደው መንገድ በመዝጋት ተሽከርካሪዎች እንዳይተላለፉ አድርገዋል።

በአንዋር መስኪድ ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች ቆሰሉ

ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በታላቁ አንዋር መስጊድ የሶላት ጸሎት በማድረስ ላይ በነበሩ ሙስሊም ዜጎች ላይ በደረሰ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች ተጎድተው ወደ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ተወስደዋል። አደጋውን ማን እንዳደረሰው የታወቀ ነገር የለም።ፖሊሶች በአካባቢው ተገኝተው ሲያጸዱ መታየታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በተነሳው ግጭት ከ10 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ እንደቀሰቀሰው በሚነገረው ግጭት ከትናንት ጀምሮ ከ10 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ የጎንደር መተማ መንገድ በመዘጋት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል።

የመንግስት ካድሬዎች በቅማንትና አማራ መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ሰሞኑን ካድሬዎቹ መሳሪያ ታጥቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸው ነበር። ምንም እንኳ ህገመንግስቱ የጦር መሳሪያ ታጥቆ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል የሚደነግግ ቢሆንም፣ ካድሬዎች ሆን ብለው መሳሪያ እየታጠቁ ትንኮሳ ማድረጋቸው፣ ለግጭቱ መነሳት ምክንያት ሆኗል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
የገዢው ፓርቲ የጸጥታ አስከባሪዎች ግጭቱን ከቀሰቀሱ በሁዋላ ከዳር ሆነው መመልከታቸው የአካባቢውን ነዋሪዎች አሳዝኗል።