Monday, February 1, 2016

በቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች ቤታችንን አናስፈርስም በማለት ተቃውሞ አሰሙ

በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ ቡታጅራ የወረዳው ባለስልጣናትና ፖሊሶች ቤት ለማፍረስ በመሄዱበት ወቅት ህዝቡ አታፈርሱም በማለት ተቃውሞውን በማሰማት፣ ባለስልጣኖቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል። ህዝቡ "ኢህአዴግ ሌባ፣ መሬታችን አይሸጥም፣ መሬት አይገኝም፣ መሬት የህዝብ ነው" የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።
ታህሳስ ወር መጨረሻ ላይም እንዲሁ ህዝቡ ቤታችንን አታፈረሱም በማለት የፖሊሶችን መሰሪያ በመቀማት ወደ መጡበት መልሷቸዋል።
የወረዳው ፖሊሶች ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዳቸውም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment