Tuesday, September 30, 2014

ሰበር ዜና መምህራንን ከስራ ቦታችው ማፍናቅል ትጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ
ከሰሞኑ በተካሄደው ስልጠና እናተያያዥ ጉዳዮች ከመምህራን ጋር መስማማት ያልቻልው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎቸ በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ የተለያዩ ወጣት መምህራንን ስልጠናው በተሳካ ምክንያት እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቸ ውስጥ ድብቅ አጀንዳ ይዛቹህ ስትንቅሳቅሱ ተገኝታቹሀል በሚል ምክንያት የተነሳ ህወሀት መራሹ መንግስት የሚከተሉትን መምህራን ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ያለፍላጎታችው ተነስተው ወደ ገጠራማ ስፍራዎች እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባገኘው መረጃ መሰረት በግዴታ ዝውውር የተሰጣቸው መምህራን የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. መ/ር ይማም ሐሰን
2. መ/ር ሙለታ ዲንቃ
3. መ/ር ኤርሚያስ ተገኝ
4. መ/ር ሐይለ አምላክ ይገዙ
5. መ/ር ደምስ ግዛቸው
6. መ/ር አንዳርጋቸው ምህረቴ
7. መ/ር አንተነህ ንጉሱ
8. መ/ር ይስሀቅ ጉደታ
9. መ/ር መላኩ አበበ
10. መ/ር ዮሐንስ ካሳሁን
11. መ/ር ዳዊት የሺጥላ
12. መ/ር ዘሪሁን አላምረው ሲሆኑ ከትላንትናው እለት ማለትም 19/01/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ያለፍቃዳቸው መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በተመሳሳይ መንገድ በርካታ መምህራን ከስራ የመባረር እና ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መመደባቸው ይታወሳል


በህወሃት “የትግራይ ኩራት ተነክቷል” ባዮች አይለዋል“ሃይለማርያም በቀጣዩ ምርጫ ሊታቀቡ ይችላሉ”

የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን “ከኋላ” አስከትለው ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያካሄዱት የፊት ለፊት ንግግር ያስደሰታቸውና ያስኮረፋቸው ክፍሎች አሉ። “በህወሃት መንደር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የመወከል ባለጊዜው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ምልክትና ተምሳሌት ነው” የሚሉት ወገኖች ቀደም ሲል ሲሰማ የነበረውን “የትግሬ ኩራት ተነክቷል” ስሜት በገሃድ ሲያንጸባርቁ ታይቷል።

አስገድደው ከሚመሩት ህዝብ ይልቅ ለውጪው ዓለም በመስገድና በማጎብደድ ወደር እንደሌላቸው የሚነገርረላቸው አቶ መለስ ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ያገኙትን ዕድል አላገኙም። ከታላቋ አሜሪካ መሪ ጋር በግል የፊት ለፊት ወግ አላደረጉም። በተለያዩ መድረኮች ላይ በጅምላ ተገኝተው ከመጨባበጥና ውስን ቃላቶችን ሲለዋወጡ ከመታየቱ ውጪ ያላገኙትን ይህንን ዕድል አቶ ሃይለማርያም ማግኘታቸው ቅር ያሰኛቸው ክፍሎች “መለስ ከመሬት በታች ሆነው የዲፕሎማሲውን ስራ ሰርተው መድረኩን እንዳመቻቹ አስመስለው በተለያዩ መንገዶች መግለጻቸው የዚሁ የኩራታችን ተነካ ስሜት ነጸብራቅ ነው” የሚሉ ወገኖች አሉ።

ስብሰባው በኋይት ሃውስ እልፍኝ ወይም በተባበሩት መንግስታት ሳሎን ውስጥ አልነበረም የተካሄደው። ዓለምአቀፉ ሒልተን በሚያስተዳድረው የኒውዮርኩ ዋልዶርፍ አስቶሪያ ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ የአሜሪካ “ባንዲራ” እና የኢህአዴግ አርማ እንዲሰቀል ተደርጎ ንግግሩ መደረጉን ያወሱ ክፍሎች፣ ፕሬዚዳንት ኦባማ ምርጫ እየተቃረበ መሆኑንን ጠቁመው “የሲቪል ማኅበረሰቡ እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለበት መታየት አለበት” በማለት ያነሱት ሃሳብ ከስብሰባው በላይ ሚዛን አንስቷል። ኢህአዴግ የመያዶች ህግ በሚል በማተም የዘጋውን የሲቪል ማኅበረሰቡን ተሳትፎ አስመልክቶ ኦባማ ማንሳታቸው ውሎ አድሮ የሚመነዘሩ ጉዳዮችን እንደሚያስነሳ አመላክቷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም በፌስቡካቸው የለጠፉት የዚሁ የሆቴል ክፍል ስብሰባ በርካታ አስተያየት ተሰንዝሮበታል። “ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አንተ መሆን አለብህ” ከሚሉት የስጋና የደም አስተያየት ጀምሮ የዚሁ የፊት ለፊት ንግግር የቀድሞው “ባለ ራዕይ” መሪ “ራዕይ” ፍሬ አጎምርቶ የመታየቱ ብስራት ተደርጎ ተወስዷል፤ ታምኗል። ክብሩና ታሪኩም ለመለስ መቃብርና አጽም ህይወት ማላበሻ የአበባ ጉንጉን በረከት ሆኖላቸዋል።

የመለስ ሞት ዱብዳ የሆነበት ህወሃት፣ ከዱብዳው ማግስት ጀምሮ መርዶውን ሚስጥር ያደረገው የርዕሰ መንበሩ ወንበር ለይስሙላም ቢሆን እንዳይወሰድ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ እንደሆነ በወቅቱ ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው። የመለስን የጥድፊያ ሞት “የግፍ ዋጋ፣ የአምላክ ቅጣት” በማለት ጮቤ የረገጡ ቢኖሩም፣ በህወሃት መንደር ግን ዜናው መሬት የተደረመሰ ያህል ስሜታቸውን ያራደ፣ ከሞት ጋር እልህ የተጋቡ የሚመስሉ፣ በዚሁ እሳቤ መለስ ቢሞቱም ያሉ ለማስመሰል የተደረገውና እየተደረገ ያለው ግብ ግብ “አምልኮ መለስ” ማስረጃ እንደሆነ ብዙዎች ተችተዋል።

ከዩኒቨርሲቲ የዲንነት በርጩማቸው ጀምሮ የሚያውቋቸው ሃይለማርያምን “የቆረጣ አካሄድን የተካነ” ሲሉ ይገልጹዋቸዋል። የሲዳማን ብሄረሰብ ለማስደሰት ከክልል ፕሬዚዳንትነታቸው ተነስተው አቶ መለስ ኢህአዴግ ቢሮ የተዛወሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም፣ በብሄር ውክልና ማመጣጠን ሰበብ ምክትል ጠ/ሚ ከመባላቸው ሌላ መለስ ቢሮ ለመጠጋት የሳቸው ሚና የለበትም። እንዳው አጋጣሚ ነው በሚል የሚከራከሩ ሃይለማርያም በኦባማ አስተዳደር ጫና ወንበሩን እንዲይዙ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ህወሃቶች ውሳኔው “የትግሬዎችን ኩራት የነካ” መሆኑንን በመግለጻቸው በተደጋጋሚ መመከራቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ይገልጻሉ።

ለጎልጉል ቅርብ የሆኑ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሰሞኑን እንደጠቆሙት ህወሃቶች “በኩራታችን ተወሰደ” ስሜት ሃይለማርያም ደሳለኝን በቀጣዩ ምርጫ በራሳቸው ሰው ለመተካት እየሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል። በተለያዩ ሚዲያዎች ቴድሮስ አድሃኖም ቀጣዩ ጠ/ሚ/ር ይሆናሉ ስለመባሉ ለተጠየቁት “ቴድሮስ የግራውን መስመር የማያውቁ በመሆናቸው አምባገነን፣ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ሊሆኑ አይችሉም፤ መስፈርቱን አያሟሉም በሚል ፈተናውን ሊያልፉ የማይችሉ ተደርገው ስለመወሰዳቸው መረጃው አለኝ” ብለዋል።

“የህወሃት የስለላው ማሽን” የሚባሉትና በፈላጭ ቆራጭነቱ አግባብ ግንባር ቀደም እንደሆኑ የሚነገርላቸው “ዶ/ር” ደብረጽዮን ሌላው እጩ ናቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ ጎልጉል ስማቸውን ጠቅሶ ለጠ/ሚኒስትርነት ህወሃት ወደ ግንባር እያቀረባቸው መሆኑንን መግለጹ አይዘነጋም። የመረጃችን ምንጭ የሆኑት እኚሁ ዲፕሎማት፣ “ዶ/ር” ደብረጽዮን አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ በመሆን መስፈርቱን የሚያሟሉ ቢሆኑም ዓለምአቀፍ እውቅና የሌላቸውና ለዚያ የሚበቁ እንደማይሆኑ በራሳቸው በህወሃት ሰዎች መታመኑን ጠቁመዋል።

14ቱ የሰማያዊ አመራሮችና አባላት ለጥቅምት 3 ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በቁጥጥር ስር ውለው በየካ ፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት ጣቢያ ውስጥ ደንብ ተላልፋችኋል በሚል በቀበና ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው 14 የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም የቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ወይስ አይከላከሉ በሚል ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ተስጥቷል፡፡

አቃቢ ህግ 14ቱ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ጣቢያ እያሉ ‹ፍትህ የለም›፣ ‹ዴሞክራሲ የለም›፣…በማለት ጮክ ብለው ድምጻቸውን በማሰማት የጣቢያውን ደንብ እንደተላለፉ በክሱ ላይ ተመልከቷል፡፡

በሌላ በኩል በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋን ጨምሮ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ሀሙስ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ፡፡ በቀጣዩ ቀን መስከረም 23 ቀን ደግሞ የሰማያዊ አርባ ምንጭ አመራሮች በተመሳሳይ ችሎት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ /EPPFG/ የጀርመንን መንግስትን ጨምሮ ለአለም ታላላቅ መንግስታትና ድርጅቶች ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ባለ 6 ገጽ ደብዳቤውን አቀረበ

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ የጀርመንን መንግስትን ጨምሮ ለአለም ታላላቅ መንግስታትና ድርጅቶች ባለ 6 ገጽ ደብዳቤውን አቀረበ::

ድርጅቱ በደብዳቤው የወያኔን የ 23 አመት የግፍና የጭካኔ አገዛዝ አንድ በአንድ ጠቅሶ ያቀረበ ሲሆን ይህም መቀጠል እንደሌለበት ያመነው  የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ጠንክሮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ዘግቧል:: ሃገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት በማዕድን ሃብትዋ እና በስው ሃይል ትልቅ ብትሆንም በአስተዳደር ችግር ግን በአለም ከመጨረሻዎቹ ሃገሮች ተርታ ተመድባ መቀመጥዋ ለዚህ ትግል እንዳነሳሳውም ገልጾዋል::

ደብዳቤውንም :-

ለጀርመን መንግስት

Sunday, September 28, 2014

እንኳን ለልማታዊው የደመራ አከባበር አደረሳቹ!

ከባህር ማዶ ነኝና ዛሬ የመስቀል በዓል እንደመሆኑ የአገር ቤት የደመራን በዓል በቀጥታ ለመከታተል እያቅለሽለሸኝም ቢሆን የወያኔን የቀጥታ ስርጭት መከታተል ጀመርኩ። ብዙም ሳልቆይ ግን ከወትሮው በተለየ አለባበስ ሁኔታ ለበዓሉ ድምቀት ከሚሰጡት ወትሮ ከምናውቃቸው የስንበት ትምህርትቤት መዘምራን በተጨማሪ የሃኪም ፣የኢንጅነር፣ የገበሬ፣ የተማሪ፣ የአስተማሪ፣የወዛደር... ምን የቀረ አለ?... ልብስ የለበሱ በርካታ ሰዎች በመዘምራኑ ተከበው ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመለከትኩ። መልዕክቱ ወዲያው ገባኝ። እንደገባኝም አልቀረ ካድሬው ጋዜጠኛ የኢትዮጲያ ቤተክርስቲያን ልማቱን ትደግፋለች፣ የሚደረጉትን ልማቶችን ትባርካለች፣ የመነኮሳት ልብስ ተላብሰው የሚታዩትም ስለልማቱ ሲጸልዩና ሲባርኩ ነው እያለ ሲደሰኩር... ሐይማኖታዊው የመስቀል ስርዓት መሆኑ ቀርቶ በደንበኛው የወያኔ እጅ የተቦካና የተጋገረ ልማታዊ የደመራ በዓል ስለሆነ ከዛ በላይ ማየት አላስፈለገኝም። ውስጤ ባዶ ሲሆን ተሰማኝ።

አማራና ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አከርካሪውን እንሰብራለን ሲሉን፣ አይ አማራም አደለሁ እምነትም በልብ ስለሆነ አይጠፋም ብዬ ዝም አልኩ። አማራም እየታደነ ከነህይወቱ ወደገደል ተጨመረ፣ተገደለ፣ከቀየው ተፈናቀለ፣ ዘሩም አንዲመክን ተደረገ። አድባራትም ተቃጠሉ፣መነኮሳትም ተዋረዱ፣ ቤተክርስቲያንም ተሰደደች። በመቀጠል ኦሮሞው ላይ ዞሩ። የኦሮሞ ግንባር ሲፋቅ ኦነግ ነው እያሉ ገደሉት፣ አገር ጥሎ እንዲጠፋ አደረጉት፣ እስር ቤቶችን በኦሮሞ ልጆች ሞሉት። ኦሮሞ አይደለሁምና ዝም አልኩ። ማነው ባለሳምንት ብለው ደግሞ ሙስሊሙ ላይ ዞሩ። የተሻለና ዘመናዊ የሆነ እምነት አመጣንልህ ተቀበል፤ ካልተቀበልክ ደግሞ እየተባለ በየመንገዱ ደበደቡት፣ እንደውሻ አሳደዱት፣ ሽብርተኛ ብለው አሰሩት። ሙስሊም አደለሁምና ምን አገባኝ አልኩ። ማን ቀረ ከቶ፧ የጋምቤላና የሱማሌው ጭፍጨፋ፣ የአፋሩ፣ የደቡቡ ሁሉም በየተራ ተወረደበት። ከፋፍለውና ነጣጥለው መቱን፣ እርስ በርስ አባሉን፣አዳከሙን።

አንድ የቀረችኝ የማንነቴ መለያ የሆንችው እምነቴና እምነቴን የማሳይበት ባሕላዊ እሴት ብትኖረኝ እሷንም ዛሬ ተነጠኩ። ሲጀመር የጋራ የሆነውን የማንነት ታሪክ አበላሹት፣ ታሪክ አልባ አደረጉን። በመቀጠል ህዝብን ከህዝብ በማነሳሳት አለመተማመንን አብቅለው አንድነታችንን በማኮላሸት ነጣጥለው መቱን። ከዛ አቅም እንደሌለን ሲያውቁ አገሩን ለባዕዳን ቸረቸሩት። በገዛ አገራችን የበይ ተመልካች ሆነን ቁጭ አልን።

ከንግዲህ ምን ቀረኝ ? አገሬን፣ እምነቴንና ታሪኬን አጣሁ ማለት ነው። እንግዲህ እኔ ማነኝ ? የሚጣልለትን እየበላ የሚኖር እንስሳ ወይስ ከወደኩበት አቧራዬን አራግፌ በመነሳት እንደኔው ከተረገጠው ጋር ዘር ሃይማኖት ሳልል እጅ ለእጅ ተይይዤ ማንነቴን መመለስ፤ በተባበረ ክንድ የወያኔን ስርዓት አሽቀንጥሮ በመጣል በጋራ፣ በእኩልነትና በመቻቻል መርህ ኢትዮጲያችንን ከፍ በማድረግ ተከብረን መኖር ? ለመሆኑ ለመኖርና ላለመኖር ምርጫ ያስፈልገዋል እንዴ ?
ዋ... ኢትዮጲያዬ!
መጽሐፈ ሄኖክ፣ መስከረም ፩፮፣ ፪ሺ፯

ጋዜጠኛ ውብሸት መንግስት ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ መሆኑን ተናገረ

ነገረ ኢትዮጵያ

በሽብር ስም ጥፋተኛ ተብሎ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሰሞኑን መንግስት ከሀገር የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደሀገራቸው ቢመለሱ እንደማይከሳቸው በማስታወቅ፣ ለዚህም ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ መሆኑን በእስር ቤት ተገኝቶ ጋዜጠኛውን ለጎበኘው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡

አምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ መከሰሳቸውን ተከትሎ ሀገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች በሚሰሩበት ተቋማት ላይ የቀረበው ክስ የማይመለከታቸው በመሆኑ ወደሀገራቸው ተመልሰው በሙያቸው ሰርተው መኖር እንደሚችሉ፣ ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ዋስትና እንደሚሰጥ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እውነቱ ብላታ ማስታወቃቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ‹‹ጋዜጠኞች አልተከሰሱም፤ ወደፊትም አይከሰሱምም›› ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ‹‹የመንግስትን ዋስትና መተማመን አይቻልም፤ የስርዓቱን ባህርይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፤ ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ ነው፡፡ በግሌ የሙያ አጋሮቼ ሀገር ቤት ሆነው የሚወዱትን ሙያ ቢሰሩ ደስ እሰኛለሁ፡፡ ሆኖም ግን ይህን መንግስት ማመን ከባድ ነው›› ብሏል፡፡

በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ለእስር የተዳረጉት ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር በተያያዘ መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል ያለው ጋዜጠኛ ውብሸት፣ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ዋስትና አግኝተናል ብለው ቢመለሱ እንኳ የሙያ አጋሮቻቸው በእስር ለምን ይማቅቃሉ ብለው መጠየቅ እንደሚኖርባቸው አስተያየቱን ገልጹዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ የተሰደዱትን ዋስትና እሰጣለሁ ሲል አንድ ቁማር መጫወት ፈልጎ ነው፡፡ ይህም የተሰደዱትን አልከሰስሁም በማለት እናንተ ወንጀል አልሰራችሁም፤ በተለያዩ እስር ቤቶች ያሰርኳቸው ግን ወንጀል ስለፈጸሙ ነው የሚለውን ማስረገጥ በመፈለግ ነው፡፡ እኛ ወንጀል ሰርተን አይደለም የታሰርነው፡፡ ርዕዮት ዓለሙ ህክምና እንኳ እያገኘች አይደለም፡፡ ታዲያ መንግስት ዋስትና እሰጣለሁ ሲል ይህን ሁሉ ግፍ ይዘነጉታል ብሎ ነው እንዴ?›› ሲል ጠይቋል፡፡

እንዲሁ እንደ ቀላል ነገር ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ዋስትና እሰጣለሁ ማለት ሌላ በተግባር እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አይደብቅም ያለው ጋዜጠኛ ውብሸት፣ መንግስት ተራ ጨዋታውን ትቶ ወደልቦናው እንዲመለስ ጠይቋል፡፡ ‹‹ስርዓቱን 23 ዓመት አውቀነዋል፡፡ መታለል አይኖርብንም›› ብሏል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከቃሊቲ፡፡


የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን ተቃወሙ

ለስልጠናው 2,345,000 ብር ይወጣል
ለተማሪዎች፣ ለነዋሪዎች፣ ለመምህራንና ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሰጥ የቆየውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን በነገው ዕለት እንዲጀምሩ የተነገሩት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን መቃወማቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ነገ መስከረም 19/2007 ዓ.ም በሚጀምረው ስልጠና 4100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሳተፉ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆነ ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ይህንም ተከትሎ ሰራተኞቹ ‹‹ስልጠናው የዕረፍት ጊዜያችን የሚሻማ ነው›› በሚል መቃወማቸውን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው ለ11 ቀን የሚቆይ ሲሆን ለአበል 50 ብር እንዲሁም ለባነርና ለሌሎች ቁሳቁሶች 90 ሺህ ብር በአጠቃላይ 2,345,000 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሽህ) ብር የሚወጣበት በመሆኑ ጊዜና ገንዘብ ከማባከን ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም ሲሉ ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


የቅዳሜ ውሎ በቃሊቲ

‹‹ እስረኞች መብት አላቸው፡፡ አንዳንድ እስረኞች ግን ከሌሎቹ የተለየ መብት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ምንም መብት የላቸውም››

ዛሬ ወደቃሊቲ አቅንተን ነበር፡፡ የእነ አቶ በቀለ ገርባ፣ የአዛውንቱ ሲሳይ ብርሌ፣ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ምክር፣ ትንታኔና ተስፋ አንዳች ጥንካሬ ይሰጣል፡፡ የእነዚህ ታሳዎች ጥንካሬ ቃሊቲ እስር ቤት መሆኑን ሁሉ ያስረሳል፡፡

መጀመሪያ እነ በቀለ ገርባን ጠይቀን ነው ወደ ጋዜጠኛው ያቀናነው፡፡ ውብሸትን ለመጠየቅ ስናቀና የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል የነበረው ገብረወሃድ እስረኞች ከሚጠየቁበት ውጭ አንድ ጥግ ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር ሰብሰብ ብሎ አየነው፡፡ እስረኞች ወደሚጠየቁበት ስናመራ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዳይሬክተር የነበረው መላኩ ፋንታና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለመጠየቂያነት የተከለለው ቦታ ላይ ጎን ለጎን ቆመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እያወሩ ደረስን፡፡

ከውብሸት ጋር ለተወሰኑ ደቂቃዎች ካወራን በኋላ ይበቃል ተባለ፡፡ ገና ወደ ውብሸት ስንመጣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የነበሩት መላኩ ፋንታ አሁንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እያወሩ ነው፡፡ ገብረ ወሃድም እንደዛው፡፡ እንግዲህ በእስረኞች መካከል የሚፈቀደው የሰዓት ገደብም ይለያያል ማለት ነው፡፡ ለ‹‹አሸባሪ›› ጋዜጠኛ 10ና 20 ደቂቃ፣ ለ‹‹ኪራይ ሰብሳቢ›› ባለስልጣን ደግሞ የፈለገውን ያህል ጊዜ ይሰጣል፡፡

ያቆሰለኝ ግን ይህ አይደለም፡፡ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከእናትና አባቷ ውጭ በማንም አትጠየቅም፡፡ እህቷ እስከዳርና እጮኛዋ ጋዜጠኛ ስለሽ ሀጎስ ርዕዮትን መጠየቅ ይቅርና ወደ ግቢው እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ ውብሸትን ጠይቀን ስንወጣ ለመረዳት እንደቻልኩት እስረኞች ከሚጠየቁበት ውጭ አንድ ጥግ ይዞ ከቤተሰቦቹ ጋር ሰብሰብ ብሎ (ወንበርና ጠባብ ጠረጴዛ ነገር ቀርቦላቸዋል) በዓል እያከበረ የነበረውን ገብረወሃድ ብቻ አልነበረም፡፡ በእጮኛዋና በእህቷ እንዳትጠየቅ ከተደረገችው ርዕዮት ዓለሙ ጋር ታስራ የምትገኘው የገብረ ወሃድ ባለቤት ኮሎኔል ኃይማኖት ከባለቤቷና ከቤተሰቦቿ ጋር ሆና በዓል እንድታከብር ተፈቅዶላታል፡፡

የእኔ ጥያቄ ለምን እነ ገብረወሃድ ተፈቀደላቸው አይደለም፡፡ ነገር ግን ርዕዮት በእጮኛዋና በእህቷ እንዳትጠየቅ በተደረገችበት ወቅት እነ ገብረወሃድና ከርዕዮት ጋር ታስራ የምትገኘው ባለቤቱ ያለ ምንም የሰዓት ገደብ እንዲያውም እስረኞች ከሚጠየቁበት ክልል ውጭ በዓል እንዲያከብሩ መደረጉ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ‹‹እስረኞች መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ እስረኞች ከሌሎቹ የተለየ መብት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ምንም መብት የላቸውም›› የሚል ያልተጻፈ ህግ እንዳለ ያሳያል፡፡ ህግ በእንሰሳዊ ስልት ለሌቦች አድልታ ስለ እውነት ለቆመችው፣ በብዕሯ ለህዝብ ለማሳወቅ ለጣረችው ወጣት ፊቷን ስታዞር አበቃላት፡፡ ይህ ርዕዮት ላይ ሆኗል፡፡ በቃሊቲ፣ በኢትዮጵያ ፍትህ እንዲህ አብቅቶላታል፡፡


የውጭ ምንዛሬው ዘረፋ በወያኔ ባለስልጣናት እና አጋሮቻቸው ተጧጡፎ ቀጥሏል።

ካለምንም ዋስትና በስልክ ትእዛዝ ብቻ ባለስልጣናት በርካታ ዶላሮችን ከባንክ ይወስዳሉ።

– በድንበር አከባቢ የሚገኙ የውጪ ምንዛሬዎች ወያኔዎች ለግል ጥቅማቸው ይከፋፈሉታል።…
– የውጪ ምንዛሬው ዘረፋ ከብሄራዊ ባንክ ጀምሮ እስከ ድንበር ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎች
ድረስ በሙስና መረብ የተያያዘ የባለስልጣናት ስውር እጆች የተደባለቁበት ነው::
– “የሃገሪቱ ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች በባዶ ካዝናዎች ተተክተዋል።” የብሄራዊ ባንክ ባለሙያዎች

ከባንኮች አከባቢ የሚወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት በላኪነት ስራ ላይ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት የገዢው መደብ ባለስልጣናት እና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጥቅም ትሥሥር ላይ የተለጠፉ አቆርቋዥ ነጋዴዎች ንግድን ሽፋን በማድረግ ሃገሪቷን በማራቆት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ::አንዳንድ ባለስልጣናት ደሞ እንደ ቻይና ህንድ እና ቱርክ ከመሳሰሉ ከውጪ አገር ዜጎች ጋር የውስጥ ሽርክና በመፍጠር በጥቅም ትሥሥር ከመሬት ጀምሮ እስከ ማንኛውም ማተሪያሎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገቡ በኢንቨስትመንት ስም ከሚመሰረተው ድርጅት ጋር የማይገናኙ ውድ እቃዎች ሳይቀሩ ገብተው ሃገሪቷ ማግኘት የሚገባትን እንዳታገኝ ባለስልጣናት ጋሬጣ ሆነዋል::

እንደባንክ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ የወያኔ ባለስልጣናት ቤተሰቦች እና ዘመድ አዝማዶች በላኪነት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን ገንዘብን ምንም አይነት ዋስትና ሳያሲዙ በአነስተኛ ወለድ እየወሰዱ የማይከፍሉ እና ሰነድ የሚያስጠፉ እንዲሁም ያለምንም ቀረጥ እና ታክስ ወደ ውጭ ሃገር ምርቶችን በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የኢሲያ ሃገራት ባንኮች ይዶሉታል:: የባለስልጣናት ቀጭን የስልክ ትእዛዝ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላሮች ኢሮዎች እና ፓውንዶች ከባንክ ይወሰዳሉ።

ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬን ለመሸጥ እና ለመግዛት ዋጋ ቢወስንም የግል ባንኮች ግን የውጭ ምንዛሬ መግዣ ዋጋን ወደጎን በመተው ከወያኔ የላኪ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሬ በመሸጫ ዋጋ እንዲሸምቱ ሲደረግ በዝምታ ታልፈዋል:: አንዳንድ ላኪዎች ከመንግስት ባንኮች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሬ በተዘዋዋሪ ለግል ባንኮች ሲቸበችቡ እየታየ በዝምታ እየታለፈ ነው::በመተማ በሞያሌ በመልካ ጀብዱ በኩምሩክ በሁመራ በሃርትሼክ ወዘተ በኢትዮጵያ ዙሪያ ገባ የድንበር ከተሞች ላይ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩት በአብዛኛው የወያኔ አባላት እና የአከባቢ ባለስልጣናት ካድረዎች ከሚወጡ የሃገር ውስጥ ምርቶች የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት ታውቋል::ይህም ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ከብሄራዊ ባንክ ጀምሮ እስከ ድንበር ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎች ድረስ በሙስና መረብ የተያያዘ የባለስልጣናት ስውር እጆች የተደባለቁበት ነው::

መሰረታዊ ለሆኑ የገቢ እቃዎች የጠፋው የውጭ ምንዛሬ በባለስልጣናት ሲዘረፍ ለሃገሪቱ የፖለቲካ ፍጆታ የመከላከያ እና የደህንነት መዋቅሮች ሲመደብ ማየት በህዝብ ጉሮሮ ላይ ቆሞ ስልጣንን በማስረዘም ሃገርን እየገደሉ መሆኑ በአደባባይ እያየነው ያለነው ሃቅ ነው:;የብሄራዊ ባንክ ከጊዜው የገዢ መደቦች ጋር በማበር የሃገርን ሀለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች አሳልፎ እየሰጠ ከባንክ አሰራር ውጭ ከፖለቲካው ጋር ግንኙነት ያሌላቸው አስመጪ ነጋዴዎች ማግኘት ያለባቸውን የውጭ ምንዛሬ ባለማግኘታቸው በሰላሳ እና አርባ ፐርሰንት ጭማሪ ምንዛሬዎችን በመግዛት ጋሬጣ የተፈጠረባቸው ሲሆን ይህ ሁሉ የገዢው መደብ አባላት የፈጠሩት የውጭ ምንዛሬ ዘረፋ በሃገሪቷ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲሰራፋ አድርጎታል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1774#sthash.zll5ZJRg.rZ7oMqKW.dpuf

Friday, September 26, 2014

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር እስማኤል አሊሴሮ እና የባህል ሚኒስትሩ በወታደራዊ ካምፕ አደሩ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሆኑት አቶ አሚን አብዱልካድርና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እስማኤል አሊስሮ በኤሊ ዳአር ወረዳ በማዳ ከተማ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ አደሩ።

ትናንት ማታ 10:00 ሰዓት ሲሆን በቡሬ ወደ ማንዳ የገቡት እኚህ ባለስልጣን ህዝብ እንዳያያቸው ተደበቀው እና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ታጅበው ማለፋቸውን ምንጮችን ዘግበውልናል። እነዚህ ባለስልጣናት ወደዚህ የመጡበት ጉዳይ በውል ባይታወቅም ወደ ኤሊ ዳዓር ወረዳ የመጣነው የዓለም የባህልና የቱሪዝም ቀንን ለማክበር ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

ከፈደራል የመጡ አንድንድ የመከለኪያ መኮነኖችም አብረዋቸው እንደነበሩም ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓት በዛ አካባቢ የኔትዎርክ አገልግሎት ተቆርጠው ይገኛል።

በሌላ ዜና የአፋር ክልል መሪዎች በየቀኑ የኢሳት ዜና እንደሚከታተሉ አንድ ስሙን ሊነግረኝ ያልፈለገ ባለስልጣን ነግሮናል። በአሁኑ ጊዜ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገሮች ታማኝ መረጃዎች ለህዝብ እያቀረበ ያለው የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን በየቀኑ በየቤታቸው የሚከታተሉት ታማኝ መረጃ ለማግኘት መሆኑን ከእነዚህ ባለስልጣናት መረዳት ተችሏል። እንደያውም አቶ እስማዒል አሊ ሴሮን ጨምሮ ብዙዎቻቸው ዜና በሰሙት ቁጠር «እውነታቸው ነው» እያሉ ለኢሳቶች ምስክር እንደሚሆኑ ታማኝ ምንጮችን ነግረውናል። በተለይ በኦጋዴን ህዝብ ላይ የተፈፀመው ጨፍጨፋና የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት የነበሩት ኡሞድ ኡባንግ ሰላደረጉት ቃለ ምልልስ አቶ እስማእል በስሜት በመሆን «የሰማሁት ሁሉም እውነት ነው» በማለት እንደመሰከሩ ሰምተናል። አብዛኛው የአፋር ክልል መሪዎች የሚችሉት የአፋርኛ እና አማርኛ ቋንቋ ብቻ ሰለሆነ ኢሳትን ለመከታተል ኢሳት የሚገኝበትን ሳተላይት በገንዘብ እንዳሰሩ ምንጮቻን ገልፀዋል።


ጄ/ል አበባው ታደሰ መከላከያን ለቀቁ!!

ኢሳት ዜና :- 98 በመቶ የሚሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ፣ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል ሰአረ መኮንን ጋር በመነጋገር ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በመከላከያ ውስጥ የሚታየውን ሙስና አልተቆጣጠሩም በሚል ሊገመግሙዋቸው ነበር የሚል ሪፖርት ቀርቦባቸው ከሃላፊነት ዝቅ እንዲሉ መደረጉን ኢሳት ከ9 ወራት በፊት ” የመተካካቱ ተውኔት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ” በሚል ርእስ ባቀረበው የምርመራ ዘገባ ገልጿል።

በጊዜው እንደተዘገበው ጄ/ል ሳሞራ የኑስን የሚተካው ኢታማዦር ሹም ከህወሃት እጅ እንዳይወጣ ለማድረግ ተፎካካሪ ሆነው ይቀርባሉ ተብሎ የተገመቱትን ጄ/ል አበባውን ጠልፎ ለመጣል ሁለቱ ጄኔራሎች የቤት ስራውን ወስደው ሲሰሩ ቆይተዋል ጄ/ል አበባው ግሳጼ ደርሶባቸው ከሃላፊነት እንዲለቁ ሲደርግ የህወሃቶቹ ጄ/ል ሰአረ መኮንንና ጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው ከፍተኛ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
በአንጻሩ ጄ/ል አበባው ከሃላፊነት ተቀንሰው ያለፉትን 9 ወራት ንብረቶቻቸውን በመሸጥ ውጭ የሚወጡበትን አጋጣሚ ሲያፈላልጉ ከርመዋል። ጄ/ል አበባው በባህርዳር ከተማ የሚገኘውን አልዋቅ ሆቴልና ሌሎች ድርጅቶቻቸውን ለሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ከሸጡ በሁዋላ ከአገር ለመውጣት ቢያስቡም መከልከላቸውንና የቁም እስረኛ መሆናቸውን ምንጮች ገልጻል።
የጄ/ል አበባው የቁም እስረኛ መሆን በብአዴንና በህወሃት የመከላከያ የሰራዊት አባላት መካከል ያለውን ሽኩቻ ሊያባብሰው ይችላል የሚሉት ምንጮች፣ አንዳንድ ምልክቶች መታየታቸውን ተከትሎ በመካከለኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ የአማራተወላጅ መኮንኖች ለይ ጥበቃ እና ክትትሉ ጨምሯል። የብአዴን አባል የሆኑ መኮንኖች በሰራዊቱ ውስጥ የሚታየውን የህወሃት ፍጹም የባላይነት በተደጋጋሚ ይቃወማሉ።


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በቋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ።

ማጥቃቱም በወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ በኦጋዴን ለተፈጸመው ጅምላ ግድያ ወታደራዊ ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።
ሕዝብን ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እያሰረ፣ እያንገላታ፣ እያሳደደና እየገደለ የሚገኘውን የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረደ በአርበኝነት ትግል እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ ጊዜያት በወያኔ ላይ በሚያካሂዳቸው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻዎች ለተጨቆነው ሕዝብ ብሶት አፀፋዊ ምላሽ በመስጠት ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።
ሰሞኑን ወያኔ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄዱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአፀፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሰረት መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ/ም በቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ ደለጎ በተባለው አካባቢ በወያኔ ፀረ-ሽምቅ ኃይሎችና በፌደራል ፖሊሶች ላይ ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ወስዷል። በዚህም የማጥቃት እርምጃ አስራ ሶስት (13) የወያኔ ታጣቂ ኃይሎች ሙት፣ ዘጠኙ (9) ደግሞ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን የእጅ ቦምቦች፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ከነመስል ጥይቶቻቸውና ትጥቆቻቸው ጋር ተማርኳል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በወገኖቻችን ላይ ወያኔ ለሚፈጸመው ጅምላ ግድያ፣ እስራትና መፈናቀል የሚሰጠውን ወታደራዊ የአፀፋ ምላሾች አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ተልዕኮ መሳካትና አምባገነናዊውን የወያኔ አገዛዝ ለመጣል ለሚደረገው ትግል ድጋፍ በመስጠት የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያደርግ ግንባሩ ጥሪውን ያስተላልፋል።


Thursday, September 25, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መስከረም 23 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች መስከረም 23/2007 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 አራዳ ችሎት እንደሚቀርቡ የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ እንዲሁም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጅነር ጌታሁን አርባምንጭ ውስጥ ወር ከ15 ቀን ያህል ታስረው የነበር ሲሆን ወደ ማዕከላዊ ከተዛወሩ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ታሳሪዎቹ በቤተሰብ፣ በኃይማኖት አባትና በጠበቃ እንዳይጠየቁ የተከለከሉ ሲሆን የምክትል ሊቀመንበሩ አቶ በፈቃዱ ባለቤትና አባት እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል


የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ በአቶ በረከት ማስጠንቀቂያ ተጠናቀቀ

ነገረ ኢትዮጵያ

• ‹‹ የተባላችሁትን መስራት አለባችሁ፣ ግዴታችሁም ነው›› አቶ በረከት

• ‹‹በቀጭን ትዕዛዝ ነው የምንሰራው፣ የተጻፈ ህግ አይሰራም›› ዳኞች

አቶ በረከት

ከሁለት ሳምንት በፊት በአቶ በረከት ስምኦን የተከፈተውና 15 ቀን የፈጀው ባህርዳር ላይ የተደረገው የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ ትናንት መስከረም 14/2007 ዓ.ም በአቶ በረከት ስምኦን ማስጠንቀቂያ መጠናቀቁን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ስብሰባውን የዘጉት አቶ በረከት ስምኦን ‹‹ፖሊስ፣ አቀቤ ህግና ዳኛ ከአስፈጻሚው (ከካቢኔው) ጋር ተስማምቶና እጅና ጓንት ሆኖ መስራ አለበት፡፡ ይህ ነው ልማታዊ የፍትህ ስርዓት፡፡›› ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በተቃራኒው ተሰብሳቢዎቹ ‹‹ከአስፈጻሚው አካል ጋር እጅና ጓንት ሆናችሁ ስሩ ማለት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲኖር መፍቀድ ነው፣ ሊሰበስበን ይገባ የነበረው የካቢኔ አካል ሳይሆን የራሳችን ተቋም የሆነው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፣ ስልጠናው በራሱ የዳኝነት ስርዓቱን፣ ተቋሙንና ግለሰባዊ መብታችንን የጣሰ ነው፡፡›› ሲሉ ቅሬታቸውን እንደገለጹ ታውቋል፡፡ በአንጻሩ አቶ በረከት ‹‹አሜሪካን ጨምሮ በየትኛውም አገር የፍትህ ስርዓት አስፈጻሚ አካሉ ጣልቃ ይገባል፣ ይህ የምታነሱት ሀሳብ አደናቃፊ ሀሳብ ነው፣ የተባላችሁትን መስራት አለባችሁ፣ ግዴታችሁም ነው›› ማለታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የተገኙት ዳኞችም ‹‹በቀጭን ትዕዛዝ ነው የምንሰራው፣ አድር የተባለውን ማድረግ ነው፣ የተጻፈው ህግ አይሰራም›› በሚል የወረደላቸውን ትዕዛዝ እንደሚያስፈጽሙ ጠቁመዋል፡፡ በስብሰባው የተገኙት ሰብሳቢ ዳኛ (የተቋም ባለቤት)ና የስራ ሂደት አስተባባሪ በስብሰባው ላልተገኙት ባልደረቦቻቸው ከእነ አቶ በረከት በወረደላቸውን ትዕዛዝ መሰረት ‹‹አቅጣጫ ይሰጣሉ››ም ተብሏል፡፡


ስልጠና የሚያስፈልገው ላልሰለጠነው የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ነው!

አምባገነኖች በውድም በግድም ህዝብ ስብሰባ ጠርተው ህዝቡ ፊት በቆሙ ቁጥር ሌት ከቀን የሚያባንናቸውን የተመረረ ህዝብ የነጻነት አመጽ የሚያስቀሩ ይመስላቸዋል። የህዝብ ሃብትና ጊዜ በከንቱ እንዳሻቸው እያባከኑ፣ ነጋ ጠባ ስብሰባ፣ ግምገማ፣ “ስልጠና” ወዘተ የሚጠሩት ህዝብ የነሱን ፍላጎትና ውሳኔ የኔ ነው ብሎ የሚቀበላቸው፣ የሚሰማቸው እና ፍርሃታቸውን ያቀለላቸው እየመሰላቸው ነው።

የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ሰሞኑን ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ሰራተኞችንና መላውን ለፍቶ አዳሪ ተሰብሰብና እናሰልጥንህ የሚሉት በአገዛዛቸው የተንገፈገፈው ህዝብ ምሬቱ ወደ አመጽ እንዳይገነፍል ያደረጉ እየመሰላቸው ነው። ዲሞክራሲንና የህዝብ ወሳኝነትና ልእልናን በተቀበሉ ሀገሮች እንደወያኔና ቀደም ብሎ እንደነበረው የደርግ ስርአት የመንግስት ስብሰባ የማይዘወተረው ለዚህ ነው። የህዝቡን ፍርድ በስብሰባ እና በስልጠና እንደማያቆሙት ስለሚያውቁ ህዝብን ስለሚያከብሩ ነው።

ሰሞኑን በመላ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ወያኔዎች ‘ስልጠና’ ብለው የሚጠሩት፣ በይዘቱ አያቶቻችንን ድሮ ላውጫጪኝ ይጠቀሙበት የነበረውን አፈርሳታ የመሰለ የመደናቆሪያ ስብሰባ አላማው ግልጽ ነው።

አላማው ህዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ቢቻል ለማደንዘዝ ካልተቻለም ለማስፈራራት ነው። ግፍን፣ ፍትህ ጥፋትን ልማት፣ ጭካኔን፣ ርህራሄ ለማስመሰል አፈጮሌ ነኝ ያለ ካድሬ ሁሉ የምላስ ጂምናስቲክ የሚሰራበት ጉባኤ ነው። ከተሰብሳቢው ህዝብ ከረር ያለ ጥያቄ በመጣ ቁጥር መላ ቅጡ የሚጠፋቸውም ለዚህ ነው። እነሱ የተዘጋጁት የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ አይደለማ! የህዝቡን ጥያቄ እንደማይመልሱማ ያውቁታል።

ነገሩ መልከ ጥፉን በስም ይደገፉ ሆነና ይህንን ቧልት ‘ስልጠና’ ብለው ይጠሩታል። እነዚህ ራሳቸው መሰረታዊ ስልጣኔ የሌላቸው አሰልጣኞች መምህራኑን ስለትምህርት ጉዳይ ሊያሰለጥኗቸው ሲንጠራሩ አይፍሩም። ባለሙያውን ሁሉ በሙያው ካላ ሰለጠንህ ብለው ግዳጅ ስብሰባ ያጉሩታል። ይህ የወያኔ ተግባር እውቀትና ስልጣን ከተምታታባቸው የወያኔ ጉጅሌዎች ስለመጣ ብዙ ላያስገርም ይችል ይሆናል። እንደ ህዝብና እንደ ዜግነታችን ግን በያንዳንዳችን ላይ እየደረሰ ያለ ውርደት ነው። ወያኔ ካላዋረደንና ሰበአዊ ክብራችን ካላሳነሰ የሚገዛን አልመሰለውም።

ግንቦት 7 ውስጥ ያለን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ይህ ዘርፈ ብዙ ውርደት እንዲቆም ነው የምንታገለው። የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ዘመን ይህን በመሰለ ውርደት ውስጥ ሊኖር የሚገባው ህዝብ አይደለም ብለን እናምናለን። የማያቋርጠው ጥሪያችን ዛሬም ተመሳሳይ ነው። ፈልገናቸው ሳይሆን በሃይል ራሳቸውን የጫኑብንን የወያኔ ጉጅሌዎች ከጫንቃችን ላይ እናራግፋቸው።

በአንድነት እንነሳ! በያለንበት ለዚህ ውርደት እምቢ እንበል። ውርደታችን እምቢ ያልን ቀን ይቆማል። ያን እለት ጨለማው ይገፈፋል። የነጻነታችንና የክብራችን ጎህ ይቀዳል።

በያለንበት እምቢ እንበል! ስለተገፋንና ስለተዋረድን ማመፅ መብታችን ነው። የቻልክ ተቀላቀለን። ያልተመቸህ በያለህበት በራስህ አነሳሽነት ራስህን አደራጅ። የነጻነታችን ቀን ቅርብ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በቋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ።

ማጥቃቱም በወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ በኦጋዴን ለተፈጸመው ጅምላ ግድያ ወታደራዊ ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።
ሕዝብን ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እያሰረ፣ እያንገላታ፣ እያሳደደና እየገደለ የሚገኘውን የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረደ በአርበኝነት ትግል እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ ጊዜያት በወያኔ ላይ በሚያካሂዳቸው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻዎች ለተጨቆነው ሕዝብ ብሶት አፀፋዊ ምላሽ በመስጠት ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።
ሰሞኑን ወያኔ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄዱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአፀፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን በዚህም መሰረት መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ/ም በቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ ደለጎ በተባለው አካባቢ በወያኔ ፀረ-ሽምቅ ኃይሎችና በፌደራል ፖሊሶች ላይ ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ወስዷል። በዚህም የማጥቃት እርምጃ አስራ ሶስት (13) የወያኔ ታጣቂ ኃይሎች ሙት፣ ዘጠኙ (9) ደግሞ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን የእጅ ቦምቦች፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ከነመስል ጥይቶቻቸውና ትጥቆቻቸው ጋር ተማርኳል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በወገኖቻችን ላይ ወያኔ ለሚፈጸመው ጅምላ ግድያ፣ እስራትና መፈናቀል የሚሰጠውን ወታደራዊ የአፀፋ ምላሾች አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ተልዕኮ መሳካትና አምባገነናዊውን የወያኔ አገዛዝ ለመጣል ለሚደረገው ትግል ድጋፍ በመስጠት የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያደርግ ግንባሩ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ስዊድን የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ኢሳያስ አፈወርቂ ጉዳዩ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው አሉ
ስዊድንና ኤርትራ በዲፕሎማቲክ የእሰጣ እገባ ውስጥ ከገቡ በርከት ያሉ ጊዜያት የተቆጠሩ ሲሆን በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ባልተገባ ተግባር ተገኝተዋል በሚል የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ስዊድንን በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ የስዊድን መንግስት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ እጅ አለበት ብለዋል። በስዊድን የወጣውን አዲስ ሕግ ተከትሎ የስዊድን መንግስት በኤርትራ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ላይ በዚያው በስዊድን ክስ መመስረቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሻክሯል።

የኤርትራ መንግስት ዋነኛ የውጪ ምንዛሪ ገቢ በተለያዩ ሀገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ላይ የጣለው ሁለት በመቶ የገቢ ታክስ ሲሆን በድርጊት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን በኢምባሲያቸው ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። በስዊድን የሚገኙ ኤርትራውያንም ኢምባሲያቸው የሚጠበቅባቸውን የታክስ መጠን ካልከፈሉ የተለያዩ የዜግነትና የጉዞ ዶክመንቶችን ከመከልከል ባለፈ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በማያዣነት ተጠቅሞ እስከማስፈራራት ደርሷል በሚል ለስዊድን መንግስት ክስ ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል። የኤርትራ መንግስት በስዊድን በሚገኙ ኤርትራውያን እና የስዊድን ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የተደራጀ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን የተቃውሞ አደራጅ ግለሰቦችን ለይቶ ለመከታተል በስዊድን የሚገኘውን ኤምባሲውን እና ዲፕሎማቶችን ይጠቀማል በሚልም ጭምር ነው የስዊድን ባለስልጣት የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ለማባረር በምክንያትነት ያስቀመጡት።

የኤርትራ መንግስት በየሀገሩ በሚገኙ ኤምባሲዎቹ አማካኝነት ከኤርትራ ዲያስፖራዎች በታክስ መልኩ በሚሰበሰበው ሁለት በመቶ ገቢ ሽብርተኞችና በፋይናንስ እያገዘ ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካኝነት ማዕቀብ ከተጣለበት ዓመታት ተቆጥረዋል። ሆኖም ከማዕቀቡ በኋላ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት በተለያየ ሀገራት ኤምባሲዎች በኩል ታክሱን ለመሰብሰብ የሚያደርገው ሙከራ በየሀገራቱ መንግስታት ተቃውሞ እያስነሳበት ነው። ከዚህ ቀድም በተመሳሳይ መልኩ ካናዳና ኤርትራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የካናዳ መንግስት በቶሮንቶ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓታት ውስጥ እስከማባረር ደርሷል።

የስዊድን እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው ብለውታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የኤርትራ መንግስት ሁለት በመቶ ታክሱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በሽብርተኝነት ለማተራመስ ይጠቀምበታል በሚል ማዕቀቡ እንዲጣልበት ሰፊ የዲፕሎማሲ ሚናን መጫወታቸውን በምስራቅ አፍሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ጂስካ አፍሪካ ኦንላይን ዘግቧል። (ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)


ለህወሃት የማስጠንቀቂያ ደወል!



ይህንን ደብዳቤ የምጽፍላችሁ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን በተውጣጣው የማኅበራዊ ፍትሕ እንቅስቃሴ ከሚመራው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ስም ቢሆንም በተለይ ግን ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች እንደመሆናችን እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ አባል የላኩላችሁ ደብዳቤ መሆኑን እንድታውቁልኝ እወዳለሁ። በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አለመግባባት ሲከሰት ሁኔታውን ማብረድና ወደ መልካም ማምጣት የቤተሰቡ አባላትና ስለቤተሰቡ በጥልቀት የሚያስቡ ሽማግሌዎች ዋንኛ ተግባር ነው። ታዲያ እኛም አንድ አገርና አንድ ተስፋ በፊታችን ያለ እንደመሆኑ በመካከላችን ያለውን ችግርና ግጭት በእውነትና በታማኝነት ልንነጋገር ይገባል ብዬ ከማመን ነው ይህንን የምጽፍላችሁ።የዚህ ደብዳቤ ዋና ዓላማ የህወሃትን ሊቀመንበር፣ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የትግራይ ተወላጅ ወንድምና እህቶቻችንን በሙሉ፤ ስለ እያንዳንዳችን ጣት እንድንጠቋቆም ሳይሆን እርስበርሳችን መነጋገር እንችል ዘንድ ለመጋበዝ ነው። ይህም ንግግርና ውይይት ከፍ ብሎ ወደ ብሔራዊ ዕርቅ እንዲያመራ ለማድረግ ነው። ከዚህ አንጻር ይህንን ደብዳቤ በምጽፍበት ጊዜ ህወሃትን ከትግራይ ሕዝብ በመለየት ለማስቀመጥ ያደረኩትን ሙከራዎች በሙሉ ልብ እንድትሏቸው እሻለሁ። የዚህ ደብዳቤ አግባብ በሥልጣን ላይ ላሉቱና ላጋዦቻቸው ነው እንጂ ብዙውን ጊዜ አለአግባብ ከህወሃት ጋር አብረው የሚወቀጡት የትግራይ ወገኖችን ደርቤ እየተናገርኩ አለመሆኑን እንድታስተውሉልኝ ይሁን።ይህንን ደብዳቤ የምጽፍላችሁ በጥላቻ በመነሳሳት ሳይሆን በፍቅርና መልካምን ሁሉ በማሰብ እንደሆነ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም የህወሃት ዘረኛ ፖሊሲ ከህዝቡ ጋር ተቆራኝቶ በአገራችን በቂ ምሬትና ጥላቻ በትግራይ ወንድሞችና እህቶቻችን ላይ እንዲኖር በማድረጉ እኔ በዚያ ላይ ሌላ ጥላቻ የመጨመር ምንም ፍላጎት የለኝም። እንዲያውም ከአምስት ዓመት በፊት የአደባባይ ምስጢር የሆነውን እውነታ በማፍረጥረጥ በህወሃት እየተገበረ ያለው የዘር መድሎና አፓርታይድ ሥርዓት እያደረሰ ያለውን በግልጽ አስረድቼ ነበር። የዚያን ጊዜ የጻፍኩት ደብዳቤ እዚህ ላይ ይገኛል። (http://

“ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅም” ኣለች።

የትግራይዋ ህወሓት ማለቴ በሰማእታት ሓወልት ፅሕፈት ቤትዋ ያደረገችው ህወሓት( ኣዲስ ኣበባ የህወሓት ኣንጃ ሰላለች ነው) “ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅም” ኣለች።

ይህ ኑዛዜ የተሰማው በኣገር ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና የሚሉት(ተቃዋሚና ያለፉት ስርዓቶች የሚሰድቡበት መድረክ ስለመሰለ ነው) በትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት(ደጀን ቢሮ) የሚሰሩ ሰራቶኞች በፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው።

በዚህ መድረክ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎችና ሃሳቦች እጅጉን ጠንካሮችና የህወሓት ተራ ኣባላትና ጥቂት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ፍፁም ታላቅ ልዩነት መነሩ የሚያሳዩ ናቸው።

በዚህ መድረክ “…ኣብራሃ ደስታ ህገ መንግስት የስጠው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን በኣግባቡ በመጠቀሙ ለምን በሽብር ኣምካኝታቹ ኣሰራቹት?…” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ነው የመቐለዋ ህወሓት ኣብራሃን እንዳላሰረችና” የማሳሰርያው ምክንያትም ኣላውቅም” ብላ የካደችው።

ስብሰባው እየመሩት የነበሩት የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ “..ስለ ኣብራሃ ደስታ መታፈንና መታሰር በፌስቡክ ስሰማ በቀጥታ ወደ ህወሓት ቢሮ ሂጀ ኣነጋጋርኳቸው። ከህወሓት ፅህፈት ቤት ያገኘሁት መልስ ምንም የሚያውቁት እንደሌለና ህወሓት እንዳላሳሰረው ረግረውኛል..” ሲሉ በስብሰባው ገልፀዋል።

ኣብራሃ ደስታን የመቐለዋ ህወሓት ካላሳሰርችው ሌላዋ ተጠያቂ የኣዲስ ኣበባዋ የህወሓት ኣንጃ ናት ማለት ነው።

ከፍተኛ ቁጣ የተላበሰው የፕላኔት ሆቴል ተስብሳቢ ህዝብ ለህወሓት መሪዎች ኣስፈሪ ነበር።

ኣገሪትዋ እየበጠበጥዋት ያሉት መላ የህወሓት ኣባላት ሳይሆኑ የተወሰኑና ጥቂት ሰዎች መሆናቸው በግልፅ በመላ ትግራይ ያሉ ስብሰባዎች የተነሱ ሃሳቦች ቁልጭ ኣድረገው እያሳዩ ናቸው።

ሌላው ከፍተኛ የመወያያ ኣጀንዳ በዓረና ኣባላት እየደረሰ ያለው ዓፈና፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ኣማራጭ ሃሳብ ወደ ህዝቡ እንዳይቀርብ ማደናቀፍ የኣዲስ ኣበባዋ ኣንጃ ሳትሆን የመቐለዋ ኣንጃ ስራ መሆኑ በግልፅ ተነግራቸዋል።

እጅጉን ያስደስታል ህዝቡ ነፃነት ፈልጓል፣ ዲሞክራሲን ናፍቆታል፣ መልካም ኣስተዳደርን ቋምጣል። ለዚህ ማሳያ በዓረና የሚደረገው የማፍረስ፣ እንዳይንቀሳቀስ የመከልከል ተግባር ውጉዝ ከመኣርዮስ እያለው ይገኛል።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።


የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የፖለቲካ ስልጠናውን ተቀላቀሉ…

ኢሳት ዜና ፦ መንግስት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የትምህርት መመሪያን ለማጥመቅ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በግዳጅ እንዲወስዱ እየተደረጉ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎቹ የፖለቲካ ስልጠና እንዳለ አስቀድመው በመስማታቸው፣ ከስልጠናውን የቀሩ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ የወረዳ ሹሞች መምህራን ተማሪዎችን እንዲያመጡ የተለያዩ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ እያግባቡ ነው።

አንድ መምህር ለኢሳት እንደገለጹት፣ ከተማሪዎች በፊት የተደረገው የመምህራን ስልጠና ያለውጤት ከተበተነ በኋላ፣ ተማሪዎች ስለሰላም እና ስለትምህርት ስርአት ስልጠና ይወስዳሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ስልጠናውን ለመውሰድ በአካል የተገኙት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ሆኖ መገኘቱንተናግረዋል። መስከረም 5 ይጀመራል የተባለው ትምህርት በፖለቲካ ስልጠናው የተነሳ እስከ አሁን አለመጀመሩን የተናገሩት መምህሩ በዚህ ሁኔታ በሚቀጥለው ሳምንት መደበኛው ትምህርት ይጀመራል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል።

በከፍተኛ ምሬት ውስጥ የሚገኙ መምህራን ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑም አክለው ገልጸዋል ነገረ ኢትዮጵያ ዛሬ በሳራጨው ዘገባ ተማሪዎች ‹‹ እኛ እድሜያችን ከ18 ዓመት በታች ነው አንመርጥም፣ ለምን ትጨቀጭቁናላችሁ፣ ኢህአዴግ አይመረጥም››የሚሉ አስተያየቶች በመስጠታቸው ፖሊስ «እየረበሻችሁ ነው» በሚል እያስፈራራቸው መሆኑን ገልጿል። የፌደራል ጉዳዩች እና የትምህርት ሚኒስቴር ባወጡት የጋራ ዕቅድ መሰረት ማንኛውም የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነባሩ ተማሪ ከመግባቱ በፊት ከመስከረም 16 ቀን ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ስልጠና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቆ ተማሪዎች ጥሪ እየተደረገላቸው ነው።


ከቤተመንግስት ዘርፎ የወሰደው የጃንሆይ ወርቅ ከአገር እንዲወጣ በመለስ ዜናዊ ድጋፍ እንደነበረ አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋለጠ።

ብስራት አማረ ከቤተመንግስት ዘርፎ የወሰደው የጃንሆይ ወርቅ ከአገር ያወጣው አቶ መለስ ዜናዊ በተሳፈሩበት አውሮፕላን እንደነበረ አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋለጠ። በአሜሪካ ኦሀይ ግዛት የሚኖረው የቀድሞ የሕወሐት አባልና የደህንነት ሹም ብስራት አማረ ከቤተመንግስት ከዘረፈው የጃንሆይ ወርቅ ጋር በተያያዘ እንዲታሰር መደረጉን ያስታወሰው ምንጩ ይህን ውሳኔ ያስተላለፉት ጥቂት የፓርቲው አመራሮች መሆናቸውን ጠቁሟል። ብስራት በሆለታ እስር ቤት እንዲታሰር ቢደረግም ወርቁን ግን አሳልፎ እንዳልሰጠና ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ከእስር ተፈቶ ወደ አሜሪካ ማምራቱን ያመለከተው ምንጩ በሚሊዮን የሚገመት ዶላር የሚያወጣው ታሪካዊ ወርቅ አቶ መለስ ዜናዊ በተሳፈሩበት አውሮፕላን ተጭኖ አሜሪካ መግባቱንና ብስራት አማረ እንደተረከበ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቀው ምንጭ አጋልጧል። ብስራት አማረ በዚህ ወርቅ እራሱንና ቤተሰቡን ሚሊየነር ያደረገ ከመሆኑም ባሻገር የደህንነት አባል የነበረው ታናሽ ወንድሙ ጠስሚ (ቅቤ ማለት ነው ትርጉሙ) በአገር ውስጥ ከፍተኛ ንግድ ከሚያንቀሳቅሱ ሃብታሞች አንዱ መሆን እንደቻለ ሲታወቅ ብስራት በአሜሪካ ለምትኖር አንዲት ኢትዮጵያዊ እንድትሸጥለት የሰጣትን 1ኪሎ ወርቅ ወስዳ እንደካደችው ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል። ባለፈው አመት ከቦሌ አየር ማረፊያ እንዲመለስ የተደረገው ብስራት ለቪ.ኦ.ኤ ሲናገር « መለስ በመሞቱ እንዲህ አይነት ችግር ተፈጠረብኝ» ማለቱ ይታወሳል። ሕወሐት በረሃ እያለ የፈፀማቸው ግድያዎችና አሰቃቂ ግፎች በዋነኛነት ይመራና ይፈፅም የነበረው ብስራት አማረ ሲሆን በተለይ ወረኢ በተባለ ቦታ በነበረው ባዶ 6 የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ የኢህአፓ አመራር አባላት የነበሩት እነፀጋዬ ገ/መድህንና ሌሎቹ በብስራት እንደተጨፈጨፉ ከመረጋገጡ ባሻገር ይህን የሚያውቁ የፓርቲው ሰዎች በወንጀለኛው ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ መሆናቸውን በመጥቀስ መረጃውን ከዚህ ቀደም ይፋ እንደተደረገ ይታወሳል። ሆኖም ወንጀለኛውን ለመፋረድ የሞከረ አካል የለም።

እየሩሳሌም አርአያ


Tuesday, September 23, 2014

በቂሊንጦ ግንቦት 7 ነው ተብሎ የታሰረው ወጣት 10 ጥፍሮቹን ነቅለው ብልቱ ላይ የላስቲክ ውሃ አንጠልጥለው እንዳሰቃዩት ተጋለጠ

(ዘ-ሐበሻ) የግንቦት 7 አባል ነው ተብሎ የታሰረው አበበ ካሴ የተባለ ወጣት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሕወሓት/ኢሕአዴግ ካድሬ ወታደሮች ከፍተኛ የሆነ ግፍ እየተፈጸመበት መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያደረሱ ወገኖች አስታወቁ።

“ዛሬ ከወደ ቂሊንጦ የደረሰኝ መረጃ እጅግ የሚዘገንና እንቅልፍ የሚነሳ ነው” በሚል መረጃውን ያቀበለን ውስጥ አዋቂ አበበ ካሴ ግንቦት 7 ነው በሚል የታሰረ ሲሆን መቀጣጫ እናደርግሃለን፤ ምስጢር አውጣ እያሉ በሚዘገንን መልኩ የ10 ጣቶቹን ጥፍሮች እንደነቃቀሉት አስታውቋል። እንደ መረጃ ምንጩ ገለጻ ከሆነ ብልቱ ላይ የታሸገ የላስቲክ ውሃ (ሃይላንድ) በማንጠልጠል ሲያሰቃዩት የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከብልቱ ፈሳሽ መውጣት መጀምሩም ተገልጿል። እንደመረጃ ምንጩ ገለጻ ከሆነ አበበ በብልቱ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ሕመም ህክምና እንዲደረግለት ቢጠይቅም “ሕክምና ማግኘት አይደለም ገና እንግድልሃለን” ብለው ከልክለውታል።

አበበ በአሁኑ ወቅት የእስረኛ መለያ መታወቂያውን መቀማቱን ያጋለጠው የመረጃ ምንጫችን የሚፈጸምበት ግፍ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱን እና እየተፈጸመበት ያለው የጭካኔ ተግባርም በምን ዓይነት ቋንቋ መግለጽ እንሚቻል ከባድ እንደሆነ ገልጾልናል።


የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች – ከተመስገን ደሳለኝ

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ
ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል
አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር
ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ለጥቆ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞው
የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በኤምባሲው ግቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁት የዕራት ግብዣ ላይ (ግንቦት 19/2001
ዓ.ም) ድንገት ተገናኝተን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤ ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው፣ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ግንቦት 7 እና እነጀነራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ዕለት እንደ አፄ ኃይለሥላሴ የክብር ዘብ፣ ከሽመልስ
ከማል ጋር በረከት ስምዖንን ግራና ቀኝ አጅቦ በተገኘበት ወቅት ነው፡፡ በተቀረ በመንግስት ሥልጣን ሲገለጥ ብዙም
አላስተዋልኩም፡፡ ከዚህ ይልቅም ኢህአዴግነቱን ለማሳየት የሞከረበትን አንድ ገጠመኝ አስታውሳለሁ፤ ይኸውም “የፍትሕ”
ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው እና አሁን በስደት ሀገር የሚገኘው ባልደረባዬ ማስተዋል ብርሃኑን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባለው
ቢሮው ድረስ በመጥራት ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ከሰነዘረበት በኋላ፣ ዛሬ የቀድሞ ጓዶቹ ሥራዬ ብለው እንደቀጠሉበት አይነት
በጋዜጣው ላይ የሀሰት ውንጀላ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ከኃላፊነቱ ራሱን እንዲያገል አስጠንቅቆት እንደነበር ከራሱ ከባልደረባዬ
ማስተዋል አንደበት ሰምቻለሁ፡የሆነው ሆኖ አቶ ኤርሚያስ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፉ በተመላኪው ሰው አመራር “ሁሉን
አዋቂነት” ላይ የቆመው መን

በጋምቤላ ግጭት የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው

ሸፍተው የነበሩ የዞኑ የፖሊስ ልዩ ሃይል አዛዥና የሚሊሽያ አባላት እጃቸውን ሰጡ

በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጎደሬ ወረዳ፣ በመዠንገር ዞን በተቀሰቀሰውና አሁንም ድረስ በአንዳንድ ቦታዎች በቀጠለው ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ የክልሉ ባለስልጣናት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡ በአዲስ አመት ዋዜማ የተቀሰቀሰውና ከ40 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት መነሻ ከመሬት ባለቤትነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ለአዲስ አድማስ የገለፁት ምንጮች፤ “ደገኞች መሬታችንን ይልቀቁ” የሚሉ የአካባቢው ተወላጆችና አንዳንድ የክልሉ ባለስልጣናት በመንግስት ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የሰፈራ ፕሮግራም ተገን በማድረግ ነባር ይዞታ ያላቸውን ነዋሪዎች በማፈናቀላቸው ግጭቱ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው ተወላጆችና ከሌሎች አካባቢዎች በመጡ ነዋሪዎች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየና በየጊዜው የሚያገረሽ ግጭት እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን፣ በቅርቡ የተከሰተው ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል የፌደራል መንግስት በደረሰው መረጃ መሰረት፣ በአፈ ጉባኤ ካሳ ተክለብርሀን የተመራ ቡድን ከክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር በአካባቢው የማረጋጋት ስራ ቢሰራም፣ በዞኑ ያሉ አንዳንድ የፖሊስና የሚሊሺያ አባላት “መሬታችንን ይልቀቁ” የሚለው ሃሳብ እንዲሰርፅ በማድረጋቸው ግጭቱ እንደተፈጠረ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡

ግጭቱ ከተፈጠረ በኋላም የዞኑን የፖሊስ ልዩ ሀይል አዛዥ ጨምሮ የፖሊስና የሚሊሽያ አባላት ሸፍተው ጫካ መግባታቸውን የተናገሩት ምንጮች፤ በአሁኑ ወቅት አዛዡና ሌሎች ጥቂት አባላት እጃቸውን ለመንግስት ሃይሎች እንደሰጡ ገልፀዋል፡፡ በአካባቢው የተከሰተው ግጭት ሁነኛ መፍትሔ ካልተበጀለት፣ በአቅራቢያ ወደሚገኙ ሌሎች አካባቢዎች ሊዛመት ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩን ያመለከቱት ምንጮቹ፤ ከወራት በፊት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ሰዎች ዲማ ተብሎ በሚጠራው የክልሉ አካባቢ አስር ሰላማዊ ዜጎችን ገድለው መሰወራቸውን ገልፀዋል፡፡ በአካባቢው የተከሰተው ግጭት ከክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር በላይ በመሆኑ፣ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሃይል ጣልቃ ገብቶ የማረጋጋት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ኢሕአዴግ ጋዜጠኞችን እና ፀሃፍያንን በገሃድ ማሳደድ ጀምሯል።

በኢትዬ ምህዳር ጋዜጣ እና በጃኖ መፅሄት በሚፅፋቸው ፁሁፎች በመላ ሀገሪቱ ሀገር ወዳድ እና ፀረ ኢህአዴግ አቃሙን ያሳየው ወጣቱ ሰለሞን መንግስ (ሶል ዘባህርዳር) በኢህአዴግ ካድሪዎች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገበት እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ቀድሞ ይሰራበት ከነበረው ባህርዳር ዩንበርስቲ ስራ ለቆ ወደ ወረታ እና አለምበር ከተማ አምርቶ የነበረው ሰለሞን ከባድ የሆነ የካድሪዎች ክትትል ህይወቱን እንዳመሰቃቀለው ለማወቅ ተችላል። የጥረት ኢንበስትመንት ባለስልጣን የሆነው ታላቅ ወንድሙ አቶ ታደለ መንግስት ከካድሬዎች ጎን ሆኖ ወንድሙ እንዲሰቃይ እያደረገ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የፎገራ ወረዳ ካቢኔዎች እንዴት አድርገው ሊያስሩት እንደሚገባ እየመከሩ እንዳሉ ታውቃል። የሰባዊ መብት ጥሰት ማድረሳቸውን ያጋለጠባቸው በአለምበር ከተማ የሚገኙ አድማ በታኝ ፖሊሶች መስከረም 4ቀን በምሽት ሊደበድቡት ሲሉ ሰለሞን ሮጦ ማምለጡን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። የኢህአዴግን አንባገነናዊ ስርአት በመቃወሙ በ2002 አም ምርጫ በወረዳው ባለስልጣናት ተደብድቦ የነበረ ሲሆን በህዝብ ቁጣ ከእስር መፈታቱ አይዘነጋም።


Sunday, September 21, 2014

ሕዝቡና ተማሪው በአገር ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር መግባባት አልቻልንም በማለት ስልጠናው እንዲቋረጥ ጠየቀ።

ምንሊክ ሳልሳዊ


- ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።

- የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።

- ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

- በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።

- ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።

- በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።

በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአዲስ አበባ የኢሕአዲግ ጽ/ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደጠቆሙት እስከዛሬ በተሰጡ ስልጠናዎች የተሰብሰቡ ሪፖርቶች እንደሚይመለክቱት ሕዝቡም ይሁን ተማሪው በተጻራሪነት እንደቆሙ እና በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እና ማንጓጠጥ ያሳዩ መሆኑን የጠቆመ ሲሆን ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም ብሏል።

በጎንደር ዩንቨርስቲ ለየት የሚያደርግው ተማሪው ብሶቱን በከፍተኛ ቁጣ መግለጹ ነው።

በጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪው በዩንቨርስቲው ትምህርት ላይየና በመምህራን ጉዳይ ከፍተና ቁጣ በማሰማት ላይ ሲሆን ዩንቨርስቲው በመልካም አስተዳደር እጦት እና በሙስና እየታመሰ መሆኑን ተነግሯል በአንድ ምት ጊዜ ውጽት ብቻ 3 ፕሮፌሰሮች 3 ዶክተሮች 14 ሁለተኛ ዲግሬ ያላቸው ምሁራን ልምድ ያላቸው መምህርን ጎንደር ዩንቨርስቲን ለቀዋል።ለዚህ ምክንያቱ ደሞ የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንገሻ አምባገነንነት እና ፈላጭ ቆራጭነት መሆኑን ተማሪዎቹ አስምረውበታል።

የዩንቨርስቲው አመራር እና ቦርዱ አምባገነን ናቸው ያሉት ተማሪዎች በሙስና እና በወገንተኝነት የተዘፈቁ ስለሆኑ በዩንቨርስቲው ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ምሁራን እንዲለቁ ምክንያት ህነዋል።በ2007 ይነሳሉ ተብለው የነበሩት እና በጣም አስቸጋሪ ባህሪ እንዳላቸው የሚነግርላቸው የዩንቨርስቲው ፕረዚደንት ፕሮ.መንገሻ በኢሕ አዴግ ብባለስታን ድ/ር ስንታየው ትእዛዝ እንዲቀጥሉ መደረጉን ተማሪውን አስቆጥቷል።

ህዝቡና ተማሪው ዛሬ በጠዋቱ እነዚህን ሲናገሩ አርፍደዋል።

1 ኢሕአዲግ የሃምሳ አመት እቅድ አውጥቷል መጀመሪያ ደረጃ የ50 አመት እቅድ በማን ማንዴት ነው የሚያውጣው ሃምሳ አመት ከህዝብ ፍቃድ ውጪ የመግዛት እቅድ ኢሕአዴግ አለው ማለት ነው ይህንን አንቀበልም ሃገሪቷን ሌላ አደጋ ውስጥ ለመክተት ካልሆነ በቀር ማንም መንግስት እንዲህ አያቅድም።

2 ኒኦሌቤራሊዝምን እና ሶሻሊዝምን እየጠላችሁ ልማታዊ ዲሞክራሲ ትሉናላችሁ ከየትኛው የትናው እንደሚሻል እንኳን ግንዛቤ የላችሁም በውቀት ያልጠገባ አመራር እና አባል ታቅፋችሁ ሃገር እንዲት እንደምትመሩ በፍጹም አቅቷቹሃል እና አስቡበት

3 የትምህርት ጥራት አውርዶ የዩንቨርስቲዎችን ቁጥር ማብዛቱ፡ተቀሜታው ምንድነው ? በጎንደር ዩንቨርስቲ ዋና ነጥብ የሆነው በዩንቨርስቲው ውስጥ ያለው ትምህርትን የመግደል አምባገነናዊ አስተዳደር በስፋት ተነስቶ እንደነበር ሰልጣኖች ጠቁመዋል።

4. የከተሞችን እድገት በተመለከተ አንጻራዊነት አይታይም የይስሙላ ልማት ፕሮፓጋንዳ እንጂ እድገት የለም መንግስት ባወጣው ህግ በጤናው መስክ ፋርማሲዎች ቫት አያስከፍሉም ይባላል በተዘዋዋሪ ግን የቫት ማሽን አስገብተው እያስከፈሉ ነው ይህ የመንግስትን በዝባዥነት ያሳያል ።ብነጻ ገበያ ሰበብ መንግስት እጁን በገብያ ውስጥ እየከተተ የህዝቡን ንሮ እያደፈረሰ ነው ።ጎን ለጎን የጉምሩክ ቀረጥ የሚጠየቀው ከ እቃው በላይ ነው ይህ ደሞ የከብያውን ትራንዛክሽን እየጎዳው ነው የሚሰራው ለህገር ነው ወይንስ ለዘረፋ ህዝቡ ተማሯል መፍትሄ እንጅ ስልጠና አንፈልግም።

5 መንግስት ሙስኛ ባለስልጣናት ተንሰራፍተዋል እያለ ነው ራሳችሁ ያመናችሁበትን እርምጃ ክመውሰድ ይልቅ እናንተ እርምጃ የምትወስዱባችው ከኢህአዲግ ፖለቲካ ጋር ሲኳረፉ ነው ይህ አግባብ አይደለም ሁሉም ስው በህግ ፊት እኩል መሆኑ ማረጋገጥ የተሳነው መንግስት እንዴት ስልጠና ይሰጣል።

በኦሮሚያ ክልል በመቱ ዞን የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ታሰሩ

ፍኖተ ነፃነት
የአንድነት ፓርቲ የመቱ ዞን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ታመነ መንገሻ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መስከረም 3 ቀን 2007 ዓ.ም በመቱ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ከአካባቢው የደረሰን ዜና ያመለክታል፡፡ አቶ ታመነ መንገሻ የታሰሩት አማራ ይቀውጣ ብለሃል በሚል ሰበብ እንደሆነና ይህን ተናገሩ በተባለበት ወቅት ታመው አልጋ ላይ እንደነበሩ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ፖሊስ በሳቸው ላይ እንዲመሰክር ፖሊስ ጣቢያ ለምስክርነት የቀረበው ግለሰብ እሳቸው ሲናገሩ የሰማሁት ዓላማችን መለያየት ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት እንዲቀጥል ነው ብለው በማለታቸው መስካሪውም እንዲታሰሩ ተደርገው በዋስ ተለቀዋል፡፡አቶ ታመነ መንገሻ ጳጉሜ 4 ቀን ታስረው እንደነበረና ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በዋስ ቢለቀቁም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ካድሬዎች ለምን ተለቀቁ መታሰር አለባቸው በማለታቸው በድጋሚ እንደታሰሩ እስካሁንም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በተያያዘም በመቱ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያም የታሰሩ 15 እና ከ 15 ዓመት በታች የሚገኙ በርካታ ወጣቶች እንደሚገኙና የታሰሩበት ምክንያትም የተቃዋሚ ፓርቲ አባልና ደጋፊ ናችሁ በሚል እንደሆነ ከአካቢው ምንጮቻችን ያደረሱን ዜና ያመለክታል፡፡

Saturday, September 20, 2014

UN experts urge Ethiopia to stop using anti-terrorism legislation to curb human rights

GENEVA, Switzerland, September 18, 2014/African Press Organization (APO)/ -- A group of United Nations human rights experts* today urged the Government of Ethiopia to stop misusing anti-terrorism legislation to curb freedoms of expression and association in the country, amid reports that people continue to be detained arbitrarily.

The experts' call comes on the eve of the consideration by Ethiopia of a series of recommendations made earlier this year by members of the Human Rights Council in a process known as the Universal Periodic Review and which applies equally to all 193 UN Members States. These recommendations are aimed at improving the protection and promotion of human rights in the country, including in the context of counter-terrorism measures.

“Two years after we first raised the alarm, we are still receiving numerous reports on how the anti-terrorism law is being used to target journalists, bloggers, human rights defenders and opposition politicians in Ethiopia,” the experts said. “Torture and inhuman treatment in detention are gross violations of fundamental human rights.”

“Confronting terrorism is important, but it has to be done in adherence to international human rights to be effective,” the independent experts stressed. “Anti-terrorism provisions need to be clearly defined in Ethiopian criminal law, and they must not be abused.”

The experts have repeatedly highlighted issues such as unfair trials, with defendants often having no access to a lawyer. “The right to a fair trial, the right to freedom of opinion and expression, and the right to freedom of association continue to be violated by the application of the anti-terrorism law,” they warned.

“We call upon the Government of Ethiopia to free all persons detained arbitrarily under the pretext of countering terrorism,” the experts said. “Let journalists, human rights defenders, political opponents and religious leaders carry out their legitimate work without fear of intimidation and incarceration.”

The human rights experts reiterated their call on the Ethiopian authorities to respect individuals' fundamental rights and to apply anti-terrorism legislation cautiously and in accordance with Ethiopia's international human rights obligations.

“We also urge the Government of Ethiopia to respond positively to the outstanding request to visit by the Special Rapporteurs on freedom of peaceful assembly and association, on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment and on the situation of human rights defenders,” they concluded.


ከዚህ በላይ የት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናል

ኢሳት ዜና :-ከዚህ በላይ የት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናልም በማለት በመንግስት አሰራር ማዘናቸውንም ተናገረዋል፡፡

የቋራ ከተማ ነዋሪዎች ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት የጠየቋቸው የመልካም አስተዳደር ፣የመንገድ ፣የመብራት እና ስልክ ችግሮች ይፈታሉ በማለት አመራሮቹ ቃል ቢገቡም በዚህ አመት በተደለደለው የበጀት ቀመር ተጨማሪ በጀት ሳይያዝ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የወረዳዋ አመራሮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

የነጋዴ ማህበር አመራር የሆኑት አቶ ገብረ ህይዎት ተሻገር የክልሉ አመራሮች በተገኙበት ያቀረቡት የነጋዴው አቤቱታ ከንግድና ኢንዱስትሪ ጋር ያለው መናበብ ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ገልጸው ባልሸጡበት ዋጋ በሚጠየቁት ግብር የተነሳ ነጋዴው ‘ይህ መንግስት ገደለን ‘በማለት የሚያማርር መሆኑን ፊት ለፊት በመናገራቸው ያተረፉት ከስብሰባው በኋላ በዞን አመራሮች ወከባ እንጅ ምንምአይነት የግብር መሻሻል ለነጋዴው ማህበረሰብ እንዳልተደረገ በምሬት ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በድንበር አካባቢ ያለው የወቅቱን ሁኔታ በመግለጽ ለርእሰ መስተዳደሩ ያቀረቡት ኢንቨስተሮችና የአካባቢ ነዋሪዎች ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ባላት አዋሳኝ መሬት ዙሪያ የሱዳን ዜጎችና ወታደሮች ዘልቀው በመግባት መኪና መዝረፍ፣ዜጎችን መግደል እና በእሳት ማቃጠል በተደጋጋሚ ቢታይም በክልሉ መንግስት የተወሰደ ርምጃ ባለመኖሩ መቸገራቸውን ከወራት በፊት ቢገልጹም አሁንም ይኼው የጎረቤት ሃገር ጥቃት በመቀጠሉ ከአካባቢው በመሸሽ ለመኖር መገደዳቸውን በእርሻስራ የተሰማሩ ባለሃብትች ገልጸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ቦታ ያለ ጠረፍ ላይ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊቱ ከተማ ላይ መሆኑ ሰራዊቱ ድንበርን ከማስከበር ይልቅ በየመጠጥ ቤቱ በመንቀሳቀስ የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውክ እንደሚውል መታዘባቸውን ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶቹ አክለውም በውች ሃገር ያሉ ዘመናዊ ትራክተሮችና ማሽኖችን ገዝተው በማስገባት እንዳይጠቀሙ በመታገድ ለስርአቱ አቀንቃኝ የሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተሰቦች የሚያስመጧቸውን ማሽኖች በከፍተኛ የዋጋ ልዩነት እንዲገዙ መገደዳቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ በመገኘት ለርእሰ መስተዳድሩ ቅሬታቸውን ካቀረቡት የቋራከተማ ነዋሪዎች መካከል የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካይ እንደተናገሩት ለሁሉም የእምነት ተቋማትና መንግስታዊ ድርጅቶች የቦታ ትክ ተሰጥቶ ቋሚ ቦታቸው ተከብሮ ባለበት ሁኔታ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የአምልኮ ቦታ እስካሁን አለመከበሩ አግባብ እንዳልሆነ በምሬት ገልጸዋል፡፡ በጥንት ዘመን ‘አሞራ አገሩ ዋርካ-የእስላም ሃገሩ መካ’ የባል ነበር፡፡ አሁንም ይህ አስተሳሰብ በኛ ላይ እየጠንጸባረቀ ነው፡፡እኛ የተፈጠርነው ኢትዮጵያ ስለሆነ እንደ ኢትዮጵያዊ ልንታይ ይገባል፡፡ ሲሉ ተደምጠዋል ፡፡

ቅሬታ አቅራቢው አክለውም ኢህአዴግ በተለያዩ ቦታዎች የሚሰሩ ስራዎችን በአግባቡ ባለማወቁ ከሃላፊዎች የሚሰጠውን የውሸት ሪፖርት በማመኑ ኢህአዴግ እና ህዝቡ እየተራራቁ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ የየተወከደበትን ቀን እየተራገመ ነው የሚሉት ቅሬታ አቅራቢበዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚንጓዝ ከሆነ ለሃገሪቱ የመበታተን ዕጣያሰጋታል በማልት በድፍረት ተናግረዋል ፡፡የተሸሙ ባለስልጣናት ሃላፊነትን በአግባቡ ከመስራት ይልቅ ስልጣናቸውን ለግልመጠቀሚያ እያደረጉ መሆኑንበአይናችን እያየን ነው በማለት ምሬታቸውን ሲገልጹ ተሰምተዋል ፡፡ ተወካዩ ይህን ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘታቸው እንዳሳዘናቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል ፡፡

በውይይቱ እንዲገኙ የታሰቡት የተወሰኑ የስርአቱ ደጋፊዎች ብቻ እንዲሆኑ ቢታሰብም ነዋሪችን ችግራችን እንገልጻለን በማለት በግድ በመግባታቸው አመራሮች ያላሰቡት ፈተና እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል ፡፡

ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክልሉ የተለያዩ የሰሜን ጎንደር ጠረፍ ከተማዎች በመዘዋወር የህብረተሰቡን ችግር ለማድመጥ በሚል ቢንቀሳቀሱም የተጠየቁትን ችግሮች ለመፍታት ሳይሆን ሕብረተሰቡ የተለያዩ ጸረ መንግስት ታጣቂ ቡድኖችን በውስጡ በማቀፍ ችግር እንዳይፈጥር እና ልዩ ልዩ ተስፋ በመስጠት መጭውን ምርጫ ያለስጋት ለማሸነፍ ሆን ብሎ በታቀደ መልኩ የምርጫው ዓመት በተቃረበ ቁጥር ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ የተለመዱ የቃል ማባበያዎች እና ማደናገሪያ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ርእሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ በዞሩባቸው ከተሞች ተመሳሳይ ተቃውሞች እንዳጋጠማቸው ታውቋል ፡፡

- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1680#sthash.qkascY35.dpuf

CPJ- ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል

CPJ-የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ሳምንት በለቀቀው ሪፖርት በአለፉት አስር አመታት ለስደት የሚዳረጉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛ ነው ብሏል።  የኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች መሰደድ CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰዎስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል በተደጋጋሚ ተነግሯል።ዛሬም እንደግመዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚደርስባቸዉን ጫና ሽሽት ሐገር ጥለዉ የሚሰደዱት የነፃ ወይም የግል ጋዜጠኞች ቁጥር እያሻቀበ ነዉ።CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰዎስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል።በመሆኑም አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ከሚወስደው አፈና፣ የማተሚያ ቤትና ሌሎችም ችግሮች ተዳምረው የስደተኛ ጋዜጠኞች ቁጥር ከዚህም እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል፡፡ በቅርብ የተሰደዱት ጋዜጠኞች የደህንነት ሁኔታ አንጻር ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም፡፡ እስካሁን አገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር

አገራችሁ የጋዜጠኞች እስር ቤት ነው መባል አያስከብርም

ለሁለት አስርት ዓመታት በተቃውሞ የፖለቲካ ጎራ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ በተለያዩ ጊዜያት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እየመሰረቱ መርተዋል፡፡ ከስድስት ዓመታት ወዲህ መድረክን የተቀላቀሉት ፕሮፌሰሩ፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከፖለቲካው ንፍቀ ክበብ ጠፍተው ከርመዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤጥ እቁባይ፤ ፕሮፌሰሩ የት ጠፍተው እንደከረሙ፣ ስለተቃዋሚ ፓርቲዎችና ኢህአዴግ ወቅታዊ እንቅስቃሴ፣ ስለመጪው ምርጫና ሌሎች ተያያዥ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ አነጋግራቸዋለች፡፡ የፕሮፌሰር በየነ፤ የት እንደጠፉ በመመለስ ይጀምራሉ፡-

ትንሹንም ትልቁንም ማሰር ለምን እንዳስፈለገ እኔ አላውቅም
አገራችሁ የጋዜጠኞች እስር ቤት ነው መባል አያስከብርም
መንግስትን እንወያይ ብለን ከጠየቅን ዓመት ሆኖናል

ሁለት አመት የተባለው በዝቷል፡፡ ለአንድ ዓመት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ “ሳባቲካል ሊቭ” (ለጥናትና ምርምር እረፍት መውሰድ ማለት ነው) ወስጄ አሜሪካን አገር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሳስተምርና ምርምር ሳደርግ ቆይቼ ነው የተመለስኩት፡፡ ያ ማለት ግን ከፖለቲካው እንቅስቃሴ ውጪ ሆኛለሁ ማለት አይደለም፡፡ ውጪም ሆኜ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እገናኝ ነበር፡፡ ምናልባት ደጋግሜ አገር ውስጥ በሚታተሙ የግል ጋዜጦች ላይ አለመታየቴ ይሆናል እንጂ የያዝነውን አጀንዳ ለማራመድ የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅደው ደረጃ እየተንቀሳቀስኩ ነኝ፡፡

በእርግጥ እዩኝ እዩኝ የሚል አካሄድ የለኝም፡፡ ድሮውንም በተቃውሞ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የገባሁት በድንገት ወይም በግርግር አልነበረም፡፡ ኢህአዴግን ስለምጠላም አይደለም፡፡ የመርህ ልዩነት ስላለኝ ነው፡፡ እኔ በሌለሁ ጊዜ ታዲያ ትግሉን ሌሎች ያራምዱታል፡፡ የፖለቲካ እንቅስቃሴውን እየተከታተሉ የቆዩኝ ታጋዮች አሉ፡፡ በተረፈ ይሄው አለሁ፤ መጥቻለሁ፡፡

Friday, September 19, 2014

የቀድሞው “የአብዮት አድናቂ” ኑዛዜ (“Confession of the Ex-Revo” )

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

ርዕሱን  አላስታውሰውም ‘ንጂ እ.ኤ.አ በ2011 Arab Uprising በመባል የሚታወሰውን አብዮትተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን ፌስቡከኞችም (በተለይ ዲያስፖራ የሚገኙ) ግንቦት 20 ላይ (ልክ በኢሕአዴግ የ20ኛ አገዛዝ ዕድሜ)   “Anger day” በሚል በፌስቡክ አብዮትመጥራታቸውን ተቃውሜ አንዲት ጽሑፍ ጽፌ ነበር፡፡ በዓመቱ ደግሞ ‹‹ አብዮት ወረት ነው›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ አብዮት ለማስነሳት ፍላጎት ያላቸው በርካቶች እንዳሉ ገልጬ ነገር ግን ይጎድላቸዋል የሚባሉትንነገሮች ዘርዝሬ ጽፌ ነበር፡፡ በነዚህ ሁለት ጽሑፎች ላይ፣ ላዩን አብዮትን የተቃወምኩ ቢመስልም እውነታው ግን ጽሑፎቹ በተጻፉበትወቅት ሕዝቡም፣ ተቃዋሚ ልሂቃኑም፣ ሁኔታዎቹም ለአብዮት ዝግጁ አይደሉም የሚል ዝንባሌ ማሳየቱ ነበር፡፡ከሌላ ዓመት በኋላደግሞ ‹‹ስለለውጥ›› በሚል ርዕስ ተከታታይ ጽሑፎችን በ‹‹ዞን 9›› ላይ በግል ተነሳሽነት ማስፈር ጀምሬ ነበር፡፡ ጽሑፉን የጀመርኩት ‹‹ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በምርጫ ይለቃል?›› በሚል ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹አይለቅም›› የምልባቸውን ምክንያቶች ካስቀመጥኩ በኋላ የለውጥ አማራጭ የምላቸውን (አብዮት፣ሰላማዊ አለመታዘዝ /civil disobedience/ የመሳሰሉትን) በየዘርፉ እየቀነጫጨብኩ ለማሳየት ነበር ዓላማዬ ከዚያም ‹‹የለውጥ ፍርሃት››፣ ‹‹የሥርዓት ለውጥ እና ሃይማኖት››

ባለፈው አመት በርካታ የመካላከያ ሰራዊት አባላት መልቀቃቸውን ወታደሮች ገልጹ

ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጳጉሜ ወር የመከላከያ ሰራዊትን ጥለው የጠፉ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ በጠጠናቀቀው አመት በርካታ ወታደሮች እየለቀቁ የተቃዋሚድርጀቶችን ከመልቀቅ ባሻገር ወደ ማሃል አገር እየሄዱ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው።የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ትወስዳለህ ተብሎ ያለፍለጎቱ መከላከያን የተቀላቀለና ባለፈው ሳምንት መስሪያ ቤቱን በመልቀቅ የግል ኑሮውን ለመምራት የፈለገ ወታደር  እርሱ በነበረበት የሁመራ እና በአድሜአካካቢዎች በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ግፍ ሲፈጸም ማያቱን ተናግሯል። ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት አለ የሚለው ወታደሩ፣ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው መከፋፈልና የሞራል ድቀት ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል።ኢሳት ከመከላከያ ሰራዊት የሚለቁ የሰራዊቱን አባላት በተደጋጋሚ እያነጋገረ ማቅረቡ ይታወቃል

በህወሓት አገዛዝ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የጅምላ ግድያ በጽኑ እናወግዛለን!!!

የአገራችን የኢትዮጵያን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ኃይል የተቆጣጠረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እሥራትና ግድያ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያጋልጡ ማስረጃዎች በየጊዜው ከራሱ ከአገዛዙ እየሾለኩ በመውጣት ላይ ናቸው።መስከረም 5 ቀን 2007 ዓም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን በምስል ተደግፎ የቀረበው በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከነዚህ ማስረጃዎች አንዱ ነው ።የወያኔን አገዛዝ ይቃወማሉ የተባሉና በኦጋዴን ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ጋር ንኪኪ አላቸው የተባሉ እነዚያ የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ የሆኑ ምስኪን ዜጎች አስከሬን መሬት ለመሬት እየተጎተተ አንድ ቦታ እንዲከማች ሲደረግ፤ አስከሬኑን ለመሰብሰብ ከታዘዙት የአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ የገዛ ወንድሙ አስከሬን ከሚጎተተው መሃል እንደነበረ መስማት ህሊናን የሚሰቀጥጥና የወያኔ የጭካኔ እርምጃ አቻ የሌለው ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው።በደርግ ዘመን ቤተሰብ የተገደለበትን ሰው አስከሬን ለማግኘት የጥይት ዋጋ ለመክፈል ይገደድ ነበር በማለት ሥርዓቱን በነጋ በጠባ የሚወነጅል አገዛዝ ከሚወነጅላቸው ሥርዓት በባሰ በኦጋዴን የገደለውን ንጹህ ዜጋ አስከሬን የገዛ ወንድሙ መሬት ለመሬት እንዲጎትተው አድርጓል። በዚህም ህወሓት በሰብዓዊነት ላይ ከቀደምቶቹ ሁሉ የከፋ የሚሰቀጥጥ ወንጀል ፈጽሟል። ቀደም ሲል በበደኖ፤ በአርሲ፤ በአርባ ጉጉ፤ በሃዋሳ ፤ በጋምቤላ እና ድህረ ምርጫ 97 በአዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ነዋሪዎች ላይ በወያኔ ልዩ ትዕዛዝ ተመሳሳይ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ተካሂደዋል። ይህ ሁሉ ወንጀል እየተፈጸመብን አስከዛሬ ወያኔን በጫንቃችን ተሸክመን ለመኖር የተገደድነው እነዚሁ ጥቂት ዘረኞች ሕዝባችንን በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈላቸው አንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ሲጠቃ ሌላው በዝምታ የሚመለከትበት ሁኔታ በመፈጠሩ ነው።ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ይህንን አረመኔያዊ እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል። ጊዜው ሲደርስ የዚህ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም ወያኔ ሕዝባችንን አቅም ለማሳጣት ላለፉት 23 አመታት በኅብረተሰባችን መካከል የገነባውን የጥርጣሬና የጥላቻ ግንብ በመናድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በኦጋዴንና በሌሎች የአገራችን ክፍሎች ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃና እልቂት ለማስቆም እንዲችሉ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል።ኦጋዴን ውስጥ ለፈሰሰው የንጽሃን ደምና በሰብዓዊነት ላይ እየተፈጸመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ሥልጣንን በኃይል የሙጥኝ በማለት በአገርና በሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ጥቂት የህወሃት አመራር መሆኑ አያጠያይቅም። ይህንን ወንጀለኛ ቡድን ለፍርድ ለማቅረብ ንቅናቄዓችን ግንቦት 7 የሚያደርገውን ሁለገብ ትግል ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የቆመ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀል በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ቀርቦለታል።ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Thursday, September 18, 2014

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ቃሊቲ ተዛወረ

ውብሸት ቃሊቲ በፊት ለፊት በር በኩል ዋይታ ቤት በሚባለው በኩል ይገኛል፡፡ ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን ሊጠይቀው የፈቀደ ሁሉ መጠየቅ ይችላል›› ብላለች፡፡

ውብሸት ወደ ቃሊቲ የተዛወረበት ምክንያት የቤተሰብ ጉዳይ ስላለበት መሆኑን የጠቀሰችው ወ/ሮ ብርሃኔ ባለቤቷ ቃሊቲ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ መሆኑን ገልጻለች፡፡ ‹‹እስከ መቼ ቃሊቲ እንደሚቆይ ባላውቅም መስከረም 29 ቀጠሮ ስላለው እስከዚያው በዚሁ እንደሚቆይ እገምታለሁ›› ብላለች፡፡
ጋዜጠኛ ውብሸት የአንድ ልጅ አባት ሲሆን ቀደም ሲል ዝዋይ እስር ቤት እያለ ልጁን ለማየት ፈተና እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹አሁን ለጊዜውም ቢሆን ልጃችንን ይዠ ስለምጠይቀው ልጁን ቶሎ ቶሎ ማየት ችሏል›› ስትል ወ/ሮ ብርሃኔ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግራለች፡፡
የውብሸት ልጅ ፍትህ ውብሸት ይባላል፡፡ ይህ ህጻን ‹‹እኔም ሳድግ እንደ አባቴ እታሰራለሁ?›› ሲል መጠየቁ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በእስር ቤት ሆኖ የጻፈው ‹‹የነጻነት ድምጾች›› መጽሐፍ ለንባብ መብቃቱን ባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃኔ ገልጻለች፡፡


በሽብርተኝነት የተከሰሱት አርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ተወሰዱ

ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው ለግንቦት7 የአርባ ምንጭና አካባቢው ወጣቶችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ለሳምንታት በአርባ ምንጭ እስር ቤት ታስረው የቆዩት የፓርቲው የአርባ ማንጭ ምክትል ሰብሳቢ በፍቃዱ አበበ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢንጂነር ጌታሁን  ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጸዋል።ኢንጂነር ጌታሁን በየነ ቀደም ብሎ ተፈትቶ የነበረ ቢሆንም፣ በድጋሜ በሌሎች ላይ ትመሰክራለህ ተብሎ በድጋሜ መያዙን አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።መንግስት የወሰደው እርምጃ ሰማያዊ ፓርቲን ለማዳከም መሆኑንም ሃላፊው አክለዋል

ህወኃት በወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የዘር ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው

የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ተከዜን ተሻግሮ እስካሁን በሃይል የወሰዳቸው የጎንደር ወልቃይትና ፀገዴ ቦታወች ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ፀለምት፡ እና ከፀገዴ ከነበሩት ጠቅላላ 39 ቀበሌወች ውስጥ 25ቱን ቀበሌወች ወደ ትግራይ ወስዶ አንድ ወረዳ የመሰረተ ሲሆን ወደ አማራ ክልል ከፀገዴ የቀረው 14 ቀበሌ ብቻ ነው። አካባቢው በለምነቱ የታወቀና ድንግል መሬት ያለበት ሰፊ አካባቢ ሲሆን በብዛት የሚመረቱት የአዝርዕት አይነቶች ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ ሩዝ፣ስኩኣር አገዳ፣ ፍራፍሬና አትክልት በስፋት ይመረታሉ። በዚሁ በወልቃይት ፀገዴ አካባቢ የሚገኙና ወደ ትግራይ የተወሰዱ ትላልቅ ከተሞች ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ማይፀብሬ፡ ዳንሻ፣ ማክሰኞ ገበያ/ ንጉስ ከተማ/ና ዲቪዥን የተባሉ ከተሞች ተወስደዋል።የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ይህንኑ የመስፋፋት ስስቱን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት አንገረብ ወንዝን በመጠቅለል የፀገዴ ቀሪ ቀበለወችን እና የታች አርማችሆ ለም መሬትን ለመውሰድ እየተዘጋጀ እንደሆነ ያካባቢው ጭብጦች ያስረዳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይትና የፀገዴ ህዝብ አሁንም በጉልበት የተነጠቀውን የጥንት የጠዋቱን መሬት ለማስመለስና መብቱን ለማስከበር ሰፊ ኣንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ለትግሉም መላው የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም የአማራ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ እያቀረበ ነው።
ይህንን የተረዳው የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅትም የሚያጋጥመውን የህዝብ ተቀዋውሞ ለመጨፍለቅና ያሰባቸውን ተጨማሪ መሬቶች ለመውሰድ ባካባቢው የተለያየ የፀጥታ ሃይሎችን እያደራጀና እያዘጋጀ ነው።

ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶችም
1ኛ. 120 የትግሬ ተወላጆች በልዩ ሁኔታ ተመልምለው በሁመራ ከተማ ለሁለት ወር ያክል ልዩ ስልጠና በሚስጥር ተሰጥቷቸው ስልጠናቸውንም ነሃሴ 7/ 2006 ዓ/ ም አጠናቀዋል ። የነዚህ ልዩ ሰልጣኞች ተልዕኮ በወልቃይት ፀገዴ ውስጥ ትግሬ አይደለንም አማራ ነን የሚሉትን እና መሬታችን ይመለስ የሚል ጥያቄ የሚያነሱትን እየለዩ እንዲደበደቡ እንዲገርፉ እንዲያስሩና እንዲገድሉ የተዘጋጁ ናቸው ቁኣሚ ደመወዝና ቀለብም የሚሰፈርላቸው ሲሆን የሚመሩትም በህወሃት ከፍተኛ መሪወች እንደሆነ ታውቁኣል።።
2ኛ, የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት በወረራ የያዛቸውን የጎንደር ወልቃይት ፀገዴን መሬት አስተማማኝ በማድረግ የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግ ይረዳው ዘንደ በፀለምት ዲቪዝን ከተማ 1500 የሆኑ የትግሬ ተወላጆች ከተለያዩ የፀጥታ ተቁአሞች በማውጣጣት በዚሁ ከተማ አደራጅቶና አዘጋጅቶ ለማንኛውም የአካባቢው ስራ ዝግጁ አድርጎ አስቀምጧቸዋል። ኣነዚህ አባላት አብዛኛወቹ የቀድሞ የህወኃት አባላት የነበሩ ሲሆኑ ከመከላከያ፣ ደህንነት፣ ፖሊስና ከትግራይ ፈጥኖ ደራሽ/ ልዩ ሃይል/ ከሚባሉት የፀጥታ መዋቅሮች ተውጣጥተው የተደራጁና በተጠንቀቅ ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ናቸው።
3ኛ, ይህንኑ እንቅስቃሴ ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ የትግራይ ልዩ ሃይልም ማዕከሉን ማይካድራና ዳንሻ አድርጎ እንዲቀመጥና ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን ተደርጉኣል። በተጨማሪም ተከዜን ተሻግሮ የሰፈረው የትግራይ ተወላጅ በሙሉ የጦር መሳሪያ እንዲታተቅ ተደርጉኣል።

ይህ በእንዲህ ኣንዳለ በተለይም በፀገዴ ወረዳ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ግደይ አዛናው የተባለውና የዚሁ አስተዳዳሪ አባት የሆኑት የምድረ-ገበታ ቀበሌ አስተዳዳሪና የወያኔ ተቀጣሪ ካድሬ አቶ አዛናው ገብርየ በትውልዳቸው የደባርቅ ተወላጅና አማራ ቢሆኑም በጥቅም በመገዛት አማራነታቸውን የከዱና የፀገዴ ህዝብ አማራ አይደለህም አማርኛ እንዳትትናገር እያሉ በስብሰባ ሁሉ የሚቀሰቅሱና ፀገዴን ለመሸጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ካሉት ባንዳወች ግንባር ቀደሞቹ በመሆናቸው በአካባቢው ህዝብ ጥርስ ውስጥ መግባታቸው ታውቁል።

ሌላ በደረሰን መረጃ መሰረት ደግሞ አቶ ካሳሁን ሲሳይ የተባለ በፀገዴ ወረዳ ምድረ-ገበታ ቀበሌ ይኖር የነበረ ሰው በ1982 ዓ/ም ህወኃት በማናለብኝነት የወልቃይት ፀገዴን መሬት በሃይል ሲወስድ ከተቀዋወሙ ሰወች አንዱ ስለነበር፣ በወቅቱ የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰውየውን ይዘው ገርፈውና አስረው ሽሬ በመውሰድ ለ 20 አመት ያክል ካሰሩት በሁኣላ በሃምሌ 2006 የፈቱት ሲሆን ሰውየው ከስር ተመልሶ ወደ ቀየው ሲመጣ ይህ ያንተ አገር ስላልሆነ እዚህ መኖር አትችልም ተብሎ ከተወለደበት፣ እትብቱ ከተቀበረበትና ካደገበት ቦታ በአሳዛኝ ሁኔታ እንዲባረር ተወስኖበት እንዲሰደድ ተደረጉኣል።


የጊፍት ሪል ስቴት ባለቤት ታሰሩ

የጊፍት ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ዋና ሥራአስኪያጅ አቶ ገብረየሱስ ኢተጋ በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የሊዝ ቦርድ ከተፈቀደላቸው መሬት በላይ ይዘው በመገኘታቸው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አቶ ገብረየሱስ በቀድሞ ወረዳ 28 ልዩ ስሙ የካ አባጣፎ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ከተረከቡት መሬት በተጨማሪ ከ30ሺ ካሬሜትር በላይ ይዘው በመገኘታቸውና እንዲያስረክቡም በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ከትላንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በቁጥጥር ሥር ውለው ትላንት ፍ/ቤት መቅረባቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።ምንጮቻችን እንዳመለከቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሊዝ ቦርድ ለጊፍት ሪል ስቴት በቀድሞ ወረዳ 28 የካ ለገጣፎ አካባቢ የሚገኝ 13 ሄክታር መሬት ቦታ 21 ባለ 3 ፎቅ ኮንዶሚኒየም፣ 81 ቪላ ቤቶች፣ በመጀመሪያ ፌዝ ለመገንባት፣ 20 ኮንዶሚኒየም ሕንጻ እና 130 ቪላ ቤቶች መዝናኛ ሱቆችና ቢዝነስ ሴንተር ያለው ግንባታ በሁለተኛው ፌዝ ለመሥራት በሪል ስቴት መመሪያው መሠረት የሊዝ ዋጋውን ከፍሎ ይህንን ጉዳይ በቀድሞ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ የሚመራው አስተዳደር ጥቆማ ቀርቦለት የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በቃለ ጉባዔ ቁጥር 18/2004 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ጊፍት ሪል ስቴት በሕገወጥ መንገድ የወሰደውን መሬት እንዲመልስ ወስኖ ክፍለ ከተማውም በእጁ የሚገኘውንም ካርታ እንዲያመክን ማዘዙን ምንጮቻችን አስታውሰዋል።ሊዝ ቦርድ ቃለጉባዔ ቁጥር 4/97 በቀን 2/2/1997 እንዲወስዱ ተወስኗል። ሆኖም ጊፍት ሪል ስቴት የውል ማሻሻያ አድርገናል በማለት የመሬት መጠኑን አሳድጎ በሕገወጥ መንገድ ትርፍ መሬት መያዙን አስተዳደሩ አረጋግጧል።

የኢህአዴግ ም/ቤት “የአመራሩ ሚስጥሮች ተላልፈው የተሰጡበትና በአደገኛ እጅ የወደቁበት ሁኔታ ተከስቷል” አለ

ኢሳት ዜና :-ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በአንድወር ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአመራሩ ሚስጢሮችተላልፈው የተሰጡበትና በአደገኛ ሃይሎች እጅ የወደቁበት ሁኔታ መከሰቱን ፣ አፋጣኝ እርምጃካልተወሰደ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተወስቷል።3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ትናንት ሲጠናቀቅ ብአዴንና ደኢህዴን በከፍተኛ ድክመት ውስጥእንደሚገኙና ከዚህ ድክመታቸው በአስቸኳይ እንዲወጡ እርምጃ እንዲወስዱ ማሳሰቢያተሰጥቷል።በዝግ በተደረገው ስብሰባ የምርጫ 2007 ፈተናን ለመወጣት ብአዴንና ደኢህዴንበክልሎቻቸው የደረሰባቸውን የህዝብ ጥላቻ አጥፍተው ወደ ላቀ የምርጫ አሸናፊነትየሚያደርሳቸውን ምክረ-ሃሳብ ተቀብለው ተለያይተዋል።ምክርቤቱበግምገማውባለፉትዓመታትበሀገሪቱየፖለቲካልኢኮኖሚ  ከፍተኛለውጥለማምጣትቢቻልም፣  በአማራ  እናደቡብክልሎችበተመሩየህዝብመድረኮችህዝቡ ስቃዩን፣ ችግሩንናፈተናውን እንዲሁም ለፓርቲው ያለውን ጥላቻ በግልጽ መናገሩ ግንባሩን ብዥታ ውስጥ ከቶታል።የኢህአዴግምክርቤትየኪራይሰብሳቢነትፖለቲካልኢኮኖሚንበልማታዊፖለቲካልኢኮኖሚበመቀየርሂደትውስጥየታዩድክመቶች በሚል ርእስ ባደረገው ግምገማ ላይ የቢንሻንጉል፤ሐረሬ፤ሶማሌ፣ጋምቤላናአፋርክልሎችከድጋፍመውጣትአልቻሉም ብሎአል፡፡ባለፉት 13 ዓመታትየተከናወኑልማታዊናዴሞክራሲያዊተግባራትንተከትሎየልማታዊፖለቲካልኢኮኖሚ ደረጃበደረጃለውጥቢኖረውምከሚፈለገውፍጥነትአኳያብዙእንደሚቀረው ገልጿል፡፡በየደረጃውየሚገኘውአመራርበተለይምከፍተኛአመራሩየነበረውንሚናምክርቤቱበዝርዝርመመልከትመጀመሩንና በዚህምአመራሩእራሱሚስጥሩተላልፈውየተሰጡበትበአደገኛእጅየወደቀበት ሁኔታመታየቱን፣ አፋጣኝእርምጃካልተወሰደአደጋውየከፋ ሊሆን እንደሚችልበግምገማው ላይ ተነስቷል።ሁሉምክልሎችበአጭርጊዜየምርጫዳሰሳእየሰሩእንዲልኩመመሪያ ተላልፎላቸዋል።

Wednesday, September 17, 2014

የበረከት ጤና – ከኢየሩሳሌም አረአያ

አቶ በረከት ስሞኦን በሳኡዲ አረቢያ የልብ ቀዶ ህክምና እንዳደረጉ ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ። በደቡብ አፍሪካ ከአመታት በፊት (ፔስ ሜከር) የተባለ የልብ ምትን የሚያስተካከል በረከት እንደተገጠመላቸው ያስታወሱት ምንጮቹ ይህ በመበላሸቱ ምክንያት የበረከት ህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ወድቆ እንደነበረና በቅርቡ አልሙዲ ሳኡዲ ወስደው ይህ እንዲስተካከል በማደረጋቸው የበረከት ጤና ሊመለስ መቻሉን ምንጮቹ አስረድተዋል። በረከት ከጤናቸው ባሻገር በፖለቲካው መድረክ በነስብሃትና ደብረፂዮን በደረሰባቸው መገፋት እንደሚበሳጩ ምንጮቹ አመልክተዋል። በረከት ስሞኦን ለባለሃብቶች በቢሊዮን የሚገመት ብድር በመፍቀድ በከፍተኛ ሙስና ከተነከሩ ባለስልጣናት አንዱ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ ለአልሙዲና ለሳሙኤል የፈቀዷቸው ብድሮች በቂ ማስረጃ ናቸው ብለዋል። በረከትን ውጭ እየወሰዱ የሚያሳክሙት ደግሞ አልሙዲ ናቸው። በረከት ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ ተካፍለዋል።


ኢትዮ ቴሌኮም ሙስሊም ሰራተኞችን አስተዳደሮችን የሚያሸማቅቅ ህገ ደንብ አወጣ።

የኢትዮ ቴሌኮም ስራተኞችና አስተዳደሮች ፂማቸውን እንዳያሳድጉ ተከለከለ!

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ከወርሃ ሃምሌ 2003 ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ,ውስጥ ከነበረው አህባሽን በግዳጅ ከመጫን ሂደት ጀምሮ ህዝበ ሙስሊሙ በራሱ ተቋም ላይ የመረጣቸውን የመሳጅድ ኮሜቴዎችና ኢማሞችን በግዳጅ ከቦታቸው ላይ በማንሳት፣ የአህባሽን ሥልጠና አልወሰዳችሁም ተብለን ወደእስር ማጓዝ፣ ኢስላማዊ እውቀት መቅሰሚያዎች የሆኑትም መድረሳዎችንና የሂፍዝ ማዕከላትን መዝጋት፣ የዩኒቭርስቲ ተማሪ ወንድሞችን ፂማቹን ካልቆረጣችሁ፤ ሱሪያችሁን ካላሥረዘማችሁ አትማሩም በማለት ማሸማቀቅ እንዲሁም ሶላተችሁን አትስገዱ ማለት፣ሴት እህቶቻችን ኒቃብ ሂጃብ ጅልባብ እንዳይለብሱ መከልከል(የባህር ዳር ዩኒቭርስቲ ተማሪዎች ሶላትና ሂጃብ ተከልክለው በገፍ ማባረራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው) ፣ ሙስሥሊም ባለሥልጣናትን ከቦታቸው ማንሳት ወይንም ተፅዕኖ በማይፈጥሩበት ቦታ ካለ ፍላጎታቸው ማስሥቀመጥ፣ በትልልቅ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ,ሙሥሊም ወንድሞች ሱና እንዳይተገብሩ ማሸማቀቅና መከልከል፣ ሰላማዊ መብት ጠያቂዎችን በገፍ ማሰርና መግደል(የሃምሌ 11ዱ ጥቁር ሽብር የመንግሥትን አምባገነንነት በግልፅ ያየንበት ነው) እንዲሁም የመሳሰሉትን ይህ ነው የማይባል አስከፊ እኩይ ተግባራትን ካለአንዳች ርህራሄና እዝነት ከአንድ ሃገርን ይመራል ከሚባል መንግስት የማይጠበቅ የግፍ መዐት እንዳወረደብን ይታወቃል።

የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ * በእስር ቤት ከቅዳሜ ጀምሮ እህል አልመቀሰም

በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘውና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ አደረገ፡፡ የሸዋስ ማክሰኞ ጱግሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከጠበቃው ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ መገናኘት ባለመቻሉና ዘመድ አዝናድ እንዲሁም የኃይማኖት አባት እንዳይጎበኘው በመከልከሉ ነው፡፡

የሽዋስ አሰፋ በባለቤቱ ብቻ ከሳምንት አንድ ቀን እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ሲሆን የርሃብ አድማ ባደረገባቸው ቀናት ባለቤቱ ምግብ ስታስገባ ለየሸዋስ ምግቡ እንደደረሰው ተደርጎ ባዶ ሳህን ሲደርሳት ቆይቷል፡፡ ባለቤቱ የበዓል ቀን ልትጎበኘው በሄደችበት ወቅት ‹‹ወጥቷል›› ተብላ የተመለሰች ሲሆን በማግስቱ ልጆቹን ይዛ ልትጠይቅ ስትሄድም ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው!›› በሚል እንዳታገኘው በመደረጓ ለ15 ቀናት ሳትጠይቀው ቆይታለች፡፡

Tuesday, September 16, 2014

“ከአሁን በኋላ ትግላችን ወደ ኋላ ሊመለስ አይገባም”የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ

ክቡራት እና ክቡራን የሙያ ባልደረቦቻችን መምህራን ሰላሙ ይብዛላችሁ:: የእናንተው የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ የእኛን የመምህራንን ድምጽ ለማሰማት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል:: እስካሁን ባደረገው ትግል በርካታ ማስፈራሪያ እና ዛቻ በሰልጣን ላይ ካለው መንግስት ቢደርስብንም ትግሉን ስንጀምር ጉዟችን ረጅም እንደሆነ በማወቃችን በየጊዜው የሚደርሱብንን በድሎች ተሸክመን እዚህ ደርሰናል ሆኖም የህወሀት የደህንነት ሀይሎች በኮሚቴው ላይ እያደረሱት ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት አካሄዳችንን እንድንቃኝ አስገድዶናል::
ከአሁን በኋላ ትግላችን ወደ ኋላ ሊመለስ አይገባም ትግላችን ከመከላከል ወደ ማጥቃት ሊሻገር ይገባዋል::
በዚህም መሰረት ከነገ ማለትም ከመስከረም 5,2007 አ.ም ጀምሮ በአዲስ መንገድ ለመንቀሳቀስ ጊዜያዊው ኮሚቴ የተለያዩ የትግል ስልቶችን ቀይሶ የሙያ ባልደረቦቻችንን ለማንቀሳቀስ እቅድ ነድፎ ወደ ስራ መግባቱን ይገልጻል::
በዚህም መሰረት ከነገው ከመስከረም 5 ጀምሮ የሚካሄዱ የተቃውሞ አካሄዶች:-
1. ከማንኛውም የኢህአዴግ አባል መምህር ጋር ያለንን ግኑኝነት ማቋረጥ::
የኢህአዴግ አባላት እንደሆኑ የምናውቃቸውን ግለሰቦች እየመረጥን ከማንኛውም ማህበራዊ ግኑኝነቶች ማግለል ማለትም ሰላምታ አለመለዋወጥ: በተሰበሰብንበት አካባቢ አባላቶቹ መጥተው ሲቀላቀሉ መበተን ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን የማግለያ መነገዶች በመጠቀም ከህዝቡ እንዲገለሉ እና ብቻቸውን እንዲቀሩ ማስቻል::
2. ነገ በሚጀመረው የመምህራን ስልጠና ላይ ተቃውሟችንን ለማሰማት ስበሰባው ላይ በተደጋጋሚ ሰበብ እየፈጠሩ መውጣት: ስብሰባውን መከታተል አቁመን መጽሀፍት እና ጋዜጣ ማንበብ እንዲሁም በስብሰባው ላይ ምንም አስተያየትም ሆነ ድጋፍ ከመስጠት መቆጥብ ይኖርብናል::
ማሳሳቢያ ይህንን ስናደርግ የኢህአዴግ ቅጥረኞች እየነጠሉ እንዳያጠቁን ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅብን ሲሆን ይህንን መረጃ ለቀሪው ባልደረቦቻችን ሼር በማድረግ ሁሉም የትግሉ አካል እንዲሆን የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ ::
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


እነ አባዱላ ፓስፖርታቸውን ተቀምተዋል- ኦህዴድና ብአዴን ይጠይቃሉ፤ ህወሓት ይመልሳል

ነገረ ኢትዮጵያ

ከአመታት በፊት የገዥው ፓርቲ አባል ሳይሆን በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይሰራ ነበር፡፡ 1997 ዓ.ም በኋላ ግን በዚህ አቋሙ አልቀጠለም፡፡ ‹‹አንዴ ቅንጅት ሌላ ጊዜ ደግሞ ኦነግ እያሉ ስም ሲለጥፉብኝ ‹ከዚህ ሁሉ!› ብየ ኦህዴድን ተቀላቀልኩ›› ይላል ካድሬው ለነገረ ኢትዮጵያ፡፡ ከዚህ በኋላ ባሉት ጊዜያት ደመወዝና እድገት በእጥፍ ተጨምሮለታል፡፡ የትምህርት እድል ተሰጥቶታል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ኦህዴድም ሆነ ኢህአዴግ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል በቅርብ ርቀት ተገኝቶ ተከታትሏል፡፡

ካድሬው እንደሚለው ከእነ አባዱላና መሰል ፖለቲከኞች ውጭ የኦህዴድ ካድሬዎች በፓርቲያቸው እምነት የላቸውም፣ በህወሓት በደል በእጅጉ ተማርረዋል፡፡ የ‹‹ብአዴኖችም ከእኛ የሚለይ ነገር የለውም፡፡ ተመሳሳይ ነው፡፡›› ይላል ካድሬው፡፡

በበርካታ ጉዳዮች ‹‹ፓርቲዬ›› ከሚለው ኢህአዴግ እንደሚለይ ቢገልጽም በአንድ ጉዳይ ግን ይስማማማል፡፡ ‹‹ጥያቄ የሚያቀርብ ካድሬ አንድም ኦነግ አሊያም የድሮው ቅንጅት አካል የነበረ ፓርቲ ወይንም ትምክተኛ ተብሎ ስም ይሰጠዋል፡፡ ኦነግ ወይንም ‹‹ቅንጅትነት/ትምክተኝነት›› ጥያቄ ማንሳት ከሆነ የኦህዴድ ካድሬዎች ሲገለጡ ኦነጎች ናቸው፡፡ ብአዴኖቹ ደግሞ እንደዛው ቅንጅት/ትምክተኛ ናቸው ማለት ነው››፡፡ በዚህ ጉዳይ ካድሬው የድሮው ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹ኦህዴድ ሲገለጥ ኦነግ ነው!›› በሚለው ይስማማል፡፡

ካድሬው ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጸው በተለይ የብአዴንና የኦህዴድ ካድሬዎች በህወሓት ጫና ከመቼውም በላይ ተማርረዋል፡፡ ‹‹አዛዡም ናዛዡም ህወሓት ነው፡፡ ትጠይቃለህ፡፡ ስም ይሰጥሃል፡፡›› የሚለው የኦህዴድ ካድሬ፤ የኦህዴድና የብአዴን ካድሬዎችም ሆነ ባለስልጣናት ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ እንደሌላቸው ከተሞክሮው ይመሰክራል፡፡ ‹‹ብአዴንና ኦህዴድ ይጠይቃሉ፡፡ ህወሓት ይመልሳል፡፡ የብአዴንና የኦህዴድ ባለስልጣናት ካድሬዎቹ የሚጠይቋቸውን ጥያቄዎች እንኳን በራሳቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ ህወሓት ብአዴንም፣ ኦህዴድም፣ ኢህአዴግም ሆኖ ሁሉም የሚጠይቀውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ እንዲያው እድል ተሰጥቷቸው የሁለቱ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች ቢመልሱ እንኳ የህወሓት ተራ ካድሬም ቢሆን የሆነ ነገር ያስተካክላል፡፡ ኦህዴድና ብአዴን ብቁ አለመሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርገው ነው፡፡››

ካድሬውን ‹‹ኢህአዴግን ምን የሚያሰጋው ይመስልሃል?›› በሚል ከነገረ ኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄም የመጀመሪያው ያደረገው ፓርቲው ውስጥ ያለውን ክፍፍል ነው፡፡ ‹‹አብዛኛው የኢህአዴግ ካድሬ እንደ እኔ ፓርቲው ያደርስብኛል ካለው አደጋ ለመዳን አሊያም ለገንዘብ የተቀላቀለ ነው፡፡ አያምንበትም፡፡ ሁሉም ቀን ነው የሚጠብቀው፡፡ ወደ ህዝብ ሲቀርቡ በመካከላቸው ችግር እንደሌለ ያስመስላሉ እንጅ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች በመካከላቸው ከፍተኛ ቅራኔ አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ የኦህዴድ ካድሬዎችን አስቆጥቷል፡፡ እስካሁን ይመለስላቸው አይመለስላቸው ባላውቅም በወቅቱ እነ አባዱላ ፓስፖርታቸውን እንደተቀሙ ሰምቻለሁ፡፡ ይህ አንድ ቀን የሚፈነዳ ይመስለኛል፡፡››

ሌላው ይላል ካድሬው ‹‹ህዝብ በፓርቲው እምነት እንደሌለው ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ህዝብ ገንፍሎ የሚወጣ ይመስለኛል፡፡ በእርግጥ አሁን ህዝቡ ዝምታን መርጧል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ህዝብን ለማሳመን ወይንም ለማስተማር በሄድኩበት አጋጣሚ ከዝምታው በስተጀርባ ህዝብ ለፓርቲው ጥላቻ እንዳለው ለማየት ችያለሁ፡፡ በቅርቡ በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና የተሰጣቸው ተማሪዎች ሰነዱን አቃጥለው ስለ ነጻነት ዘምረዋል፣ ፓርቲው አብጠልጥለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲደማመር አንድ ቀን ህዝብ ገንፍሎ የሚወጣ ይመስለኛል››


አባተ ኪሾና የጭቃ ፖለቲካ( አርአያ ተስፋማሪያም)

ቦታው ወህኒ ቤት ነው፤ የቀድሞ ደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ፣ ስዬ አብርሃ፣ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያትና ታምራት ላይኔ በእስር እያሉ ያወጋሉ። አባተ ኪሾ እንዲህ አሉ፥ « መለስ ዜናዊ የተናገረኝን መቼም አልረሳውም፤.. እንዲህ ነበር ያለኝ፤ “አባተ አንተና የአዲስ አበባ ቆሻሻ ማፍሰሻ ቱቦ አንድ ናችሁ። የተቀበለውን ሳያስተላልፍ ውጦ የሚያስቀር፤…አንተም ለሕዝብ እንድትናገር የነገርንህን ውጠህ የምታስቀር (የማታስተላልፍ) የዚህ ከተማ ቱቦ አይነትህ ነህ።…አባተ ኪሾም ሆነ ሌሎቻችሁ የውሸት እያለቀሳችሁም ቢሆን ካድሬና ህዝቡን ማሳመን አለባችሁ!”..ማለታቸውን አንደኛው እስረኛ ነግረውኝ ነበር።…አሰፋ ጫቦ ደግሞ በስብሰባ ላይ ስድብ ስለበዛ « እባክህ አቶ መለስ ስድቡን አስቁም?» በማለት በግል ሲጠይቋቸው « ዝም በል..ፊዳል» ብለዋቸዋል መለስ። “አቃጣሪ” ማለታቸው ነው።..መስከረም 2000ዓ.ም ፓርላማው ሲከፈት ስለ ሱማሊያ ጦርነት ከክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጥያቄ የቀረበላቸው መለስ ዜናዊ « የሱማሊያን ጦርነት በኮንደም አልተዋጋነውም» ብለው አረፉት። በዛው አመት « ወራዳ ..እደግመዋለሁ ወራዳ…» እያሉ ብዙ ተናገሩ። መለስ «ትምክህተኛ፣ ጠባብ፣ ጐጠኛ፣ ጦርነት ናፋቂ..» የሚሉ ቃላቶች ከአፋቸው አይጠፉም። « እስከአንገታችን በስብሰናል፣ ገምተናል..» ብለዋል። በምርጫ 97 « ጣት እንቆርጣለን» ሲሉ በቲቪ መስኮት የዛቱት መለስ ዜናዊ ለፈፀሙት የጅምላ ግድያ በአጣሪነት ለተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ ዳኛ ወ/ሚካኤል መሸሻ ሲናገሩ « ይህን ሪፖርት ብታቀርብ በቦዘኔ መንገድ ላይ አስገድልሃለሁ» እንዳሏቸው አጋልጠው ነበር። ክቡር ደ/ች ዶ/ር ዘውዴ ገ/ስላሴ (ነፍሳቸውን ይማር) መለስና ስብሃት ሲያናግሯቸው « አንተ በአንድነት አስታከህ የፊውዳል ስርአት ለመመለስ የምትፈልግ የፊውዳል ርዝራዥ ነህ፤.» ብለዋቸው እንደነበረ በሃዘን አጫውተውኛል። መለስ ዜናዊ ለገዛ የትግል ጓደኞቻቸው አልተመለሱም፤ የመጀመሪያዋን የሴት ታጋይ አረጋሽ አዳነ ስቅስቅ ብላ እስክታለቅስ ተናግረዋታል፤ እንዲሁም በ2002 የካቲት ወር መቀሌ አደባባይ በትግርኛ ቋንቋ ንግግር ያደረጉት መለስ ዜናዊ በፖለቲካ የተለይዋቸውን (አረና ፓርቲ) ሲሳደቡ « ባህር ውስጥ ሽንትህን ብትሸና ለውጥ አያመጣም። እነዚህ ሰገራ (ፍታን) ናቸው። ጭቃ (ኩርሲ ) ናቸው…» በማለት እንደተናገሩ የሚታወስና የአቶ ገብሩ አስራት መፅሐፍ ጭምር ቃል በቃል የሚገልፀው ነው። ይህ ነው የመለስ “ራዕይ”!?.. “ ከአፀያፊ የስድብ ጐተራ” በጥቂቱ የተቀነጨበ። አፀያፊ!!


በ 2007 ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ

ኢሳት ዜና :-በ2007ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድምፁን እንዳይሰጥ ለማፈን በሚያስችል ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ሚሊሽያ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ሰሞኑን ለታማኝ አመራሮች በሰጡት ድርጅታዊ መግለጫ ላይ በያዝነው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ የተለያየ ፅንፍ በመያዝ ገዢው ፓርቲ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ችግሮችን በማስወገድ ሙሉ በሙሉ አሸናፊ ለማድረግ የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
አቶ መኳንንት ባለፈው ዓመት ለዚሁ ልዩ ተልዕኮ ከ360 በላይ ለሆኑ የሚሊሽያ አመራሮችና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ፤ በወረዳ ደረጃ ላሉ የሚሊሺያ አባላትም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሁለት ዙር ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ከ3 ሺህ 600 በላይ በሆኑ ቀበሌዎች ላሉ የሚሊሽያ አባላትም ልዩ ተልዕኮውን እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ የሚያግዝ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ምክትል ሃላፊው ለታማኝ የስርአቱ ደጋፊዎች ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ያሉ የሚሊሽያ አባላት ከህዝቡ የተወጣጡ እና የገዢው መንግስት ደጋፊዎች መሆናቸው ስለሚታመን ጠዋትና ማታ ከህብረተሰቡ ጋር በመገናኘት በየቀበሌው ካሉ ልዩ ልዩ የወጣት፣ የሴቶች እና የአርሶ አደሩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የመራጩን ህዝብ አመለካከት የመቀየር ስራ እንዲሰራ መታዘዙን፣ ይህ አሰራር ህዝቡ ታማኝነቱንና ድምጹን ለገዢው ፓርቲ የሚሰጥ መሆኑን የማረጋገጥ ሂደቱን ሊያሳካ ይችላል ተብሎ
እንደታመነበት ለታማኞች ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የተሰጡትን ስልጠናዎች ለማካሄድ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ ቢሆንም፣ ከዚህ ወጪ ውስጥ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ህብረተሰቡ እንዲሸፍን መደረጉን፣ ገንዘብ በእጁ የሌለው ድሃው ህብረተሰብ ሳይቀር በግ ፣ ፍየል ፣ ዶሮና እህል እንዲያዋጣ በማድረግ ለሚሊሺያው ስልጠና መሰጠቱን ባለስልጣኑ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ተመላሽ ከሆኑ ወታደሮች ውስጥ የተሻለ የድርጅት ፍቅር ያላቸውን በመለየት ወደ ሚሊሽያው የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሆነ በዚሁ ዝግ ውይይት ተናግረው ፣ ወታደሮቹ በየገጠር ቀበሌው ሲሰማሩ ልዩ ልዩ ጥቅሞችን ከአርሶአደሩ ሊያገኙ የሚችሉበትን አሰራር ለመዘርጋት ግፊት የማድረግ ሃሳብ ወደ አመራሩ ዘንድ እንደወረደም አስረድተዋል፡፡ አቶ መኳንንት የግልና የመንግስት ተቋማት ጥበቃዎችና ሚሊሺያው ከላይ እስከታች የአመለካከት ችግር ያለባቸው በመሆኑ እና ተልዕኮ የሚሰጣቸው ከጸረ ሰላም ሃይሎች በመሆኑ ለአካባቢው ልማት ጠንቅ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ተከታትለው አንዳንድ ርምጃዎችን ለመውሰድ በአመራሩ መካከል መግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በዳንግላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ አንዳንድ አመራሮችና የሚሊሺያ አባላት ሚሊሺያው ከገዢው መንግስት ጥቅም ይልቅ የህብረተሰቡን ጥቅም በማስቀደም ከታሪክ ተወቃሽነት ነጻ እንሆናለን ብለዋል። የድምጽ መረጃውን ለላኩልን የሚሊሺያ አባላት ምስጋናችንን እንገልጻለን።


(ድብቅ ስትራቴጂ) የህወሓት ሥርዓት የአፋር ህዝብን መሬት የትግራይ ነው አለ

በአኩ ኢብን አፋር )(በአኩ ኢብን አፋር )በሰሜናዊው የአፋር ክልል የሚገኙ የአፋር ክልል ወረዳዎች ዳሉልን ጨምሮ «የትግራይ መሬት ነው!» በማለት አፋቸው ሞልተው የሚናገሩ የህዋሓት መሪዎች ይደመጣሉ!! እሱም አብዓላ፣ ደሉል፤ ኮናባ፣ ባራህሌ፣ የትግራይ መሬት ነው ከሚባሉ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። በኮናባ ወረዳ ከሁለት ሳምንታት በፊት በትግራይ ነዋሪዎችና በአፋር ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ አንድ የአፋር ወጣት ሲሞት 3 ደግሞ መቁሰላቸው ዘግበን ነበር። ችግሩ በሁለት ነዋሪዎች መካከል የሚፈጠር ግጭት አይደለም! የህዋሓት መንግስት የአፋር መሬትን ለመቀራመት የሚያደርገው ሆን ተብለው የሚደረጉ ትንኮሳዎች መሆናቸው ግልፅ ነው! «የኮናባ ወረዳ እና የአፅቢ ወረዳ የድምበር ወዝግብ የቆየ ቢሆንም የዛሬው በመንግስት ሆን ተብሎ የተፈጠረ በመሆኑ አሳስቦናል።» ይላሉ የኮናባ ነዋሪዎች።

የህዋሓት መንግስት ባለስልጣናት «መሬቱ የእኛ ነው እስከ ዳሉል የትግራይ መሬት ነው ብትፈልጉም ባትፈልጉም መንግስት እርምጃ ይወስዳል» ብለው ይናገራሉ። የአፋር የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች በነገሩ በመገረም «በመሬታችን እየሞተን ነው! ገና አሁንም እንሞታለን!» በማለት ባለፈው ሳምንት በውቅሮ የተደረገው ስብሰባ ያለ ምንም መፍተሄ ተበትኗል! በስብሰባው የትግራይ ክልልን ወከለው የተገኙት የውቅሮው የዞን አስተዳደር የዞኑ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የአፅቢ ወረዳ መስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ በአፋር በኩልም እንደዛው። ለእነርሱ ታማኝ የሆኑት የዞን 2 የመንግስት ባለስልጣናትና በርካታ የአገር ሽማግለዎች ተገኝተዋል!! በዚህ ስብሰባ በባለፈው ውግያ የንፁሃን ሰዎችን ህይወት ያጠፉትን ሰዎች የአፅቢ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች ለህግ እንዲያቀርቡ በአፋር ሽማግሌዎች የተጠየቁ ቢሆንም ሰሚ አላገኙም!! «ካሁን በኋላ» ይላሉ የኮናባ ወጣቶች «ካሁን በኋላ ሁላችን በተጠንቀቅ እንቆማለን እንሞታለን!»ከመንግስት የምንጠብቀው ፍትህ የለም!!

የወያኔ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሲዎች ተሽመድምዷል።ትግሉም ወሳኝ ምእራፍ ላይ መሆኑ ተረጋግጧል

ወገን የሞተውን ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የቀብር ስነ ስርአቱን የምንፈጽምበት ወቅት ላይ ነን ።
– ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::
– ወያኔ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ በተገኘው የትግል ስልት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻችንን እነወጣ።ወያኔ እየመራው የሚገኘው ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ሃገርን ረመጥ ላይ እየከተታት ሲሆን የወያኔ ሳቦታጅ ጥቂት ሰዎች በሃገር ሀብት በህዝብ ላይ እንዲፈነጩ አድርጓቸዋል::በሃገሪቱ ማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከበፊቱ በተለየ እና በባሰ ሁኔታ ተንኮታኩተው አፈር መልበሳቸው በይፋ ታውቋል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል::በአላማ ሳይሆን በጊዜያዊ የመኖር ሂደት ላይ የተመሰረተው የካድሬዎቹ ሩጫ ድካምን በመፍጠሩ ሁሉም በያለበት ቆም ብሎ እያሰበ ሲሆን አሳቡም የገፈፍኩትን ገፍፌ ሃገርን ድባቅ መትቼ ልሽሽ ሆኗል::ገበናን ገበና ይገፈዋል እንደሚባለው የወያኔ ጁንታ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚያዊ ገበና በገበና ተጋልጧል:: የማይሰማ ነገር የለም እና እኛም ሰማን አነበብን አየንም እነሆ ታዝበን ዝም አላልንም ገበናዎቹ ገበናውን ሲገልቡት አብረን አልሳቅንም ሀገር ነውና ገበናዎቹን ተመርኩዘን

በአይሳኢታ፣ በዱብቲ፣ በአዋሽ፣ በአሚ ባራ፣ በገዋኔ፣ በአፍዴራ፣ በዶቢና ሚሌ የሚገኙ አፋሮች መሬታቸውን ተቀምተው በርሃብ እየተቆሉ ነው

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘሐበሻ እንደዘገበው

የደርግ ስርዓት ወድቆ የኢህአዴግ መንግስት ሲመጣ ብዙ የአፋር መሬት ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለስ ተደርጓል። በሰሜናዊው የአፋር ክልል በዳሉል ወረዳ ይተዳደሩ የነበሩ ብዙ የአፋር ህዝቦች በግዴታ በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲተዳደሩ ተደርገዋል!
ለምሳሌ፦ ያህል፥ ታላክ፣ ጎደለ፣ ሰሄሎ እና ሰውነ ሲሆን ከዚህ በላይ ስማቸው በተጠቀሱት ቦታዎች ከኢህአዴግ ሰርዓት በፊት ከአጼዎች ዘመን ጀምሮ የአፋር መሬት እንደነበረ ይታወቃል። ታላክ እና ጎደለ እሰከ ሰሄሎ በደጅ አዝማች አህመድ ሲተዳደሩ ሰውነ ደግሞ በኦና ማሕሙድ ይተዳደር ነበር።


በዚህ አካባቢ የሚተዳደሩ የአፋር ህዝቦች እስካሁን ድረስ በቋንቋቸው የመማር ማስተማር እንዲሁም ባህላቸውን የማሳደግ የሰብዓዊ መብት ያላገኙ ሲሆን በሚኖሩበት የትግራይ ክልል እንኳን የአፋር ብሄረሰብ አይባሉም ኢህአዴግ ይኸው ቆምኩላችሁ መብታችሁን አስከበርኩላችሁ እያለ የአፋር ህዝብ ግን ገና ጭቆና ላይ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ወገኖቻችንና ለዴሞክራሲም ሆነ ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ የመብት ታጋዬች ሊያውቁልን ይገባል! ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ደርግን ለመዋጋት ወደ ጫካ ሲገቡ ይሄ የአፋር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ የቅርብ ጎረቤት ስለነበር ምግባቸውን አብስለው ለተጋዬች ከማቅረብ ጀምሮ ከጎናቸው የቆመ ህዝብ ቢሆንም ዛሬም ከጭቆና ልወጡ አልቻሉም።

ወድ የተከበረችሁ ወገኖቼ ሆይ ይሄን ስናገር ግን የቀረው የአፋር ህዝብ መብት ተክሮለታል ማለት አይደለም! በክልላችን በወያኔ ያልተወረረ የአፋር መሬት የለም። በአይሳኢታ፣ በዱብቲ፣ በአዋሽ ፣በአሚ ባራ፣ በገዋኔ ፣በአፍዴራ ፣በዶቢና ሚሌ የሚገኙ አፋሮች በአሁኑ ጊዜ ከመሬታቸው ተፈናቅለው በረሀብ እየተሰቃዩም ይገኛሉ።

የተንዳሆ የስኳር ፋብሪካ የተጀመረው በ2001 ዓ.ም ቢሆንም እሰከ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከስኳር ችግር አልወጣም። ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት የህወሃት ባለ ስልጣናት ሲሆኑ አብዛኛቸው ከመከላኪያ ሰራዊት በጡረታ የወጡ መኮነኖች ናቸው! የአፋር ክልል መንግስትም ቢሆን ለስራቸው የሚሰጠውን ባጀት ወደ ውጭ ሀገር እየላኩ ማስቀመጥ ብቻ ነው!! ሌላው ቀርቶ በአፋር ክልል በሰላም ሲኖሩ የነበሩ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን በግዳጅ ከአፋር ክልል እያስወጡ ይገኛሉ። በዚህ አመት ብቻ ከ400 ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች በሰፈራ ፕሮግራም ወደ አፋር ክልል ገብተዋል!!

በመጨረሻም:- የአፋር ህዝብ ከኢትዮጵያ ነፃነት ታጋዮች ጋር ለሚደረገው ትግል ከዳር እስከ ዳር ዝግጁ መሆኑን በአፋር ወጣቶች ስም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። የአፋር ህዝብ ይህ የአንባገነን ስርዓት አብቅቶ የነፃነት ፀሃይ የምትወጣበት ቀን በጉጉት የሚጠብቅ ጭቁን ህዝብ ነው!

ነፃነት ለኢትዮጵያ


ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት

እንደምን አመሻችሁ!

በዚህች መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቤተሰቦቹና ከወዳጆቹ ጋር ሆኖ አዲሱን አመት ለመቀበል በሚዘጋጅባት ምሽት በግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም እንኳን ለአዲሱ አመት በሠላም አደረሳችሁ ስል ከፍተኛ ክብርና ትልቅ ደስታ ይሰማኛል። መቼም በባህላችን ለሠላም ያለን ቦታ ከፍተኛ ስለሆነ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር እንኳን በሠላም አደረሳችሁ እንባባላለን እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሠላም ከጠፋ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል።

ዉድ የአገሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ-

እኛን ለመሰለ ከሁለት አስርተ አመታት በላይ በዘረኛ አምባገነኖች ለተረገጠ ሕዝብ የአዲስ አመት ዋዜማ አሮጌዉን አመት ሸኝተን አዲሱን የምንቀበልበት የሆታና የጭፈራ ምሽት ሆኖ ማለፍ የሚገባዉ አይመስለኝም። ይልቁንም በዚህ አሮጌዉን 2006ትን ተሰናብተን አዲሱን 2007ትን በምንቀበልበት ምሽት ባሳለፍነዉ የትግል አመት የገጠሙንን ችግሮችና መሰናክሎች መርምረንና ከድክመታችን ተምረን በ2007 ዓም ለምናደርገዉ ወሳኝ ትግል እራሳችንን ማዘጋጀት ያለብን ይመስለኛል።

Monday, September 15, 2014

ሽመልስ ከማል የሚመራው የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስልጠና በጩኸት ተበተነ።

ምንሊክሳልሳዊ‬
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ (ቂሊንጦ-አቃቂ) ውስጥ ይሰጣል የተባለው ስልጠና በተማሪው ጉርምርምታ እና ተቃውሞ የተበተነ ሲሆን ስልጠናውን እየሰጠ የሚገኘው ሽመልስ ከማል ብከፍተና ድንጋጤ እና መረበሽ ውስጥ እንደነበር ታውቋል። ትማሪው ከተቃውሞ በተጨማሪ ሽመልስ ሲለፈልፍ የሚሰማው ባለመኖሩ እና ፌስቡክ በመጠቀም ፡የጆሮ ማዳመጫ በማድረግ ሙዚቃ እየስማ ሊለው ደሞ መስማት ደብሮት እያንቀላፋ የስልጠናውን ወንበር ገጥሞ ሲተኛ ተስተውሏል።‪ተማሪው እረፍት እንፈልጋለን ወሬ ሰለችን በማለት ቢጮህም ሽምመስ ከማል ዲስኩሩን ቢቀጥልም ተማሪው ተቃውሞውን ስብሰባውን በመርገጥ ወጥቶ ገልጿል። ይህን ተከትሎ ከሰአት በኋላ በየግሩፓችሁ እንድትገኙ ሲል ዩንቨርስቲው ማሳሰቢያ ሰቷል። ተማሪዎቹ ከየክፍለከተማቸው ጥሪ ተደርጎላቸው ትላንትና ወደ ዩንቨርስቲው ግቢ ይተስባሰቡ ሲሆን ከገቡ በኋላ መውጣት አይቻልም ተብሎ ግቢውን በመዘጋጋት ተማሪው በግድ ዩንቨርስቲው ውስት እንዲያድር እና ለዛሬው ስልጠና እንዲገባ ቢደረግን ስልጠናው ሳይሳካ ተበትኗል።ትላንትና ማታ ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን ከግቢው መውትታ የሚቻለው በመጭው ቅዳሜ ከሰአት በኋላ መሆኑ ተነግሯል።የካፌው ምግብን በተመለከተ ደረጃውን ያልተበቀ እና ለጤንነት አስጊ ነው ያሉት ተማሪዎቹ በጥዋት ስልጠና ግቡ ቢባሉም እየተነጫነጩ 2 ሰአት ግቡ የተባሉ 3 ፡10 ገብተዋል፡ ወደ ስልጠናው እንደገቡም ለአንድ ሰአት ያህል ሳይቀጥል ሽመልስ ከማል ምናገር ሲጅምር ጩሀት ስለተጀመረ እና ስልጠናውን አንፈልግም የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች በመስማታቸው ረግጠው ለመውጣት ተማሪዎቹ ሲሞክሩ በአስተባባሪዎች በሩ በመዘጋቱ ሁኔታው ስላላማራቸው በሩን በመክፈት ከሰአት ብህውላ በቡድን ስልጠናው እንዲሰጥ በማለት አደራሹ ተዘግቷል።

Sunday, September 14, 2014

Ginbot 7 discards ER Report as “false and fabricated” 

Ethiomedia SEATTLE – A report published by Ethiopian Review that implicates Eritrea in the abduction of Andargachew Tsege is absolutely “false and fabricated,” a top Ginbot 7 leader told Ethiomedia by phone on Tuesday.

Neamin Zeleke, executive committee member of Ginbot 7, dismissed Ethiopian Review’s Report line by line, regretting why the ER editor in the first place never asked anyone of Ginbot 7′s leaders for their views in what the editor called an investigative report.

“Whatever said in that report is pure fiction,” a resentful Neamin Zeleke said, wondering if ER had an “ax to grind by publishing a fictitious story.

Asked whether Dr Berhanu Nega and Andargachew Tsege had that much polarized differences on Eritrea as reported by ER, Neamin said, “Absolutely no! Elias Kifle could have talked to anyone of us but he didn’t. Instead, he wrote a fiction out of his own fantasy, which regrettably hurts the struggle we all of us try to promote and bring about the reign of democrayc and justice in Ethiopia.”

Neamin also regretted that ER’s fiction appeared on Ethiomedia, which he described as ‘credible news source.’

In an emailed message, Neamin wrote:

“Despite differences on some issues, as a responsible media, we have expectation from Ethiomedia to counter-check the veracity of ER’s ludicrous fiction before reprinting it on its site. ER is interested in concocting fabricated stories instead of reporting the truth and presenting the actual facts. In this case about G7, its leadership, Andargachew , and the circumstances of his abduction from Yemen, who did what and the chronology of the events before and after his abduction by the Woayne Mafia.”

On the side of Ethiomedia, we are trying to reach out to Elias Kifle, editor and publisher of Ethiopian Review, and seek his responses to some outstanding questions related to the story that Ginbot 7 has labeled as ‘false.’

የወያኔ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሲዎች ተሽመድምዷል።ትግሉም ወሳኝ ምእራፍ ላይ መሆኑ ተረጋግጧል

- ወገን የሞተውን ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የቀብር ስነ ስርአቱን የምንፈጽምበት ወቅት ላይ ነን ።
– ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::
– ወያኔ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ በተገኘው የትግል ስልት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻችንን እነወጣ።

ወያኔ እየመራው የሚገኘው ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ሃገርን ረመጥ ላይ እየከተታት ሲሆን የወያኔ ሳቦታጅ ጥቂት ሰዎች በሃገር ሀብት በህዝብ ላይ እንዲፈነጩ አድርጓቸዋል::በሃገሪቱ ማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከበፊቱ በተለየ እና በባሰ ሁኔታ ተንኮታኩተው አፈር መልበሳቸው በይፋ ታውቋል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል::በአላማ ሳይሆን በጊዜያዊ የመኖር ሂደት ላይ የተመሰረተው የካድሬዎቹ ሩጫ ድካምን በመፍጠሩ ሁሉም በያለበት ቆም ብሎ እያሰበ ሲሆን አሳቡም የገፈፍኩትን ገፍፌ ሃገርን ድባቅ መትቼ ልሽሽ ሆኗል::

Saturday, September 13, 2014

ሰበር ዜና፡ ታጋይ ዘመነ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አመራር ከአባይ ሚደያ ጋር አጭር ቆይታ አደረገ

አባይ ሚዲያ ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የፖለቲካ ሃላፊ ከሆነው ታጋይ ዘመነ ካሴ ጋር የስልክ ውይይት አደረገ። ታጋይ ዘመነ ለአባይ ሚዲያ ሲናገሩ አቶ ኤልያስ ጋዜጠኛ ስለመሆኑም እና እንዴት እና በምን ሂሳብ ወደ ትግል አለም እንደገባም እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ወጣቱ ታጋይ ዘመነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት አዲሱ አመት የሰላም እና የድል ዘመን እንዲሆን በመመኘት እና ወንድማችን ታጋይ አንዳርጋቸውን የከፈለውን መሰዋእትነት ከንቱ እንዳይሆን ህዝባዊ ሃይሉ እና ከሌሎች የነጻነት ሃይሎች ጋር እየተደረገ ያለው ሂደት መፋጠኑን በዚህ አመት የምናወራበት ሳይሆን ወደ ትጋበር ተሸጋግረን ወያኔን የምናበረክክበት ዘመን እንደሚሆን አትጠራጠሩ ሲል መልእክቱን አስተላልፉል።

አባይ ሚዲያ ሰሞኑን ስለ ታጋይ ዘመነ እና ግንቦት 7 በኢትዮጵያን ሪቪው ባለቤት አቶ ኤልያስ ክፍሌ እያደረገ ያለውን ግንቦት 7ን የማጥላላት ዘመቻን አስመልክቶ  ላቀረብንለት ጥያቄ ሲመልስ፡-

በመጀመሪያ እንደዚህ አይነት ለወረደ እና ትግልን ለመጉዳት ሲል ቀን ከሌት በሚሰራ ግለሰብ የሚለውን መመለስ ለእኔ ራሱ ተገቢ አይደለም። እኛ ያለነው ተግባራዊ ትግል ላይ ነው እንጂ ምኞት ላይ አይደለም። እናም እኔ ራሴን ዝቅ አድርጌ በተራ ጉዳዮች መግባት አልፈልግም የኢትዮጵያ ህዝብ ከእኛ ብዙ ይጠብቃል። እውነተኛ ታጋይ፣ እውነተኛ ጋዜጠኛ፣ እውነተኛ ሰራተኛ ሀገራችን ካጣች እኮ ቆዪ፤ ስለዚህ ኤልያስም ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉን ለመጉዳት ከሚሰሩ ተኩላዎች መጠንቀቅ እና እነሱ የሚመሩትን የግል ዌብሳይት የመረጃ ምንጭ አድርጎ አለመውሰድና አለማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ለደቂቃም ቢሆን ያዘናጋናል አሁን አንተ ስትደውልም ስራ ትቼ ነው የማናግረው። ብዙ እና በርካታ ስራዎች አሉብን አጣዳፊ የሆኑ።

አባይሚዲያ፡ ሙሉውን ቃለምልልስ ከኢሳት የማክሰኞ ዝግጅት በኋላ ይዞ የሚቀርብ መሆኑን ለአንባቢዎቹ ይገልጻል።


በጋምቤላ የተነሳውን ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል

የመዠንገር ብሄረሰብ ተወላጆች ጎደሬና ሜጫ በሚባሉት አካባቢዎች እንደ አዲስ በጀመሩት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስካሁን አስከሬኖች እንዳልተነሱ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከጋምቤላ ብሄረሰብ ውጭ ያሉ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች በሙሉ ይወጡበሚል የተጀመረው ግጭት ፣ ደም አፋሳሽ ሆኖ ከመቀጠሉ ባሻጋር፣ በትናንትናው እላት ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱሰዎች ተፈናቅለው ቴፒ ከተማ መግባታቸው ታውቋል።ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ዋነኛው የግጭት መንስኤ በጡረታ የተገለሉ የህወሃት የጦር መኮንኖች የአካባቢውን መሬት በርካሽ ዋጋ በመግዛት ነዋሪዎችን ማፈናቀላቸውና አካባቢውን እየተቆጣጠሩ መምጣታቸው መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።የመዠንገር ጎሳ አባላት ብሄር ሳይለዩ በማንኛውም ሰው ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ሲሆን፣ ካለፉት ሁለት ወራትጀምሮ በርካቶች ተገድለው በሺ የሚቆጠሩት ዜጎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።የክልሉ የጸጥታ ሹም መያዛቸውና የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦኬሎ አኳይ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ተይዘው ለኢህአዴግ መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸው ለአሁኑ ግጭት ማገርሸት ምክንያት መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።ግጭቱን ለመቆጣጠር ወደ ስፍራው ያመራው የፌደራል ፖሊስ ሰራዊትም ከአካባቢው ታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮች ገልጸዋል።ግጭቱ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎአል።በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።ኢሳት በትናንትና የዜና እወጃው ከ9 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሶ ነበር። ይሁን እንጅ የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰው አሃዝ በላይ ነው።

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ ተዛወሩ

በሽብርተኝነት ተከሰው አርባምንጭ ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞ ጎፋ ዞን አመራሮች ከነበሩበት የአርባ ምንጭ እስር ቤት አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ወንጀል ምርመራ መዘዋወራቸው ታወቀ፡፡

ከዞኑ አመራሮች መካከል የአርባ ምንጭ ምክትል ሰብሰቢ አቶ በፍቃዱ አበበ እና ደርጅት ጉዳይ ኃላፊው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ጱግሜ 5 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ የተዘዋወሩ ሲሆን ቀሪዎቹ አሁንም አርባምንጭ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ፡፡

ወደ ማዕከላዊ የተዘዋዋሩትን የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ አመራሮች ምግብና ልብስ ከማቀበል ውጭ መጠየቅ እንደማይቻል የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


Friday, September 12, 2014

ቪኦኤ አማርኛ፣ ከድጡ ወደ ማጡ? – በአበበ ገላው 

የዛሬ ወር ገደማ የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር ሙሉ በሙሉ ሃሰት የሆነ ዘገባ በአሜሪካን ሬድዎ አማካኝነት አሰራጨ። የዘገባው አላማ በካሊፎርኒያ የሚገኘው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ሽልማት መልሶ መንጠቁንና ዝግጅቱ መሰረዙን በማስመልከት የቀረበው ዘገባ ሃሰት ነው ብሎ ለማስተባበል እና እኔን፣ አለማቀፉን የኢትዮጵያዊያን መብት የጋራ ህብረት እንዲሁም ኢሳትን በሃሰተኝነት ለመወንጀል የታለመ ነበር።አበበ ገላውይሁንና ለእርምጃው ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዩኒቨርሲቲው እንዲመረምርና ሽልማቱን መልሶ እንዲያጤን ስለተደረገ መሆኑ በግልጽ የተነገረ እውነታ ነበር። ዩኒቨርሲቲውም ለክብሩ ስነ ስርአት መሰረዝ የሰጠው ዋነኛ ምክንያት ይሄው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ መሆኑን በይፋ ደጋግሞ ገልጿል።
አልተሳካም እንጂ ሄኖክ በተለይ በእኔ ላይ ያነጣጠረ በተንኮል የተሞላ ጎጂና የተዛባ ዘገባ ሲያቀርብ ይሄኛው ሶስተኛው ነው። በግንቦት 10, 2004 (May 18, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተቃውሞ ድሞጽ ሳሰማ ሄኖክ በአይኑ ያየው በጆሮው የሰማው ሃቅ ቢሆንም ድምጼን ሳንሱር አርጎ ዘገባውን አዛብቶ ለስርጭት አበቃው። በዚህም ምክንያት ቪኦኤ ከአድማጮቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለቀረበበት በሳምንቱ ዘጋባውን እንደገና በሌላ ሰው አስተካክሎ ተቆርጦ የቀረውን ድምጼን አስገብቶ ሌላ ዘገባ ለማስተላለፍ ሞከረ። ይሄን በጋዜጠኝነት ስም የተሰራ እርካሽ የፖለቲካ ቁማር ታዝበን አለፍነው።ከዛም ግኡሽ አበራ የሚባል አንድ የቦስተን ነዋሪ በእኔ ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም ሲዶልት ገና ከጥንስሱ በFBI ተደርሶበት ምርመራ እንደተደረገበት ተዘገበ። በዚህ ላይ ወያኔ የተቀናጀ ስራ በመስራት፣ አንዳንድ ድህረ ገጾችን፣ ፓልቶኮችን እና ቪኦኤን በመጠቀም እኔ ግኡሽ አበራን ልክ በሃሰት የወነጀልኩት ለማስመሰል ሌላ ያልተሳካ ጥረት ተደረገ። እንደተለመደው ሄኖክ አሳፋሪ የካድሬ ስራውን በመቀጠል ከፍተኛ መዛባት ለመፍጠር ሞከረ። ትንሽ ብዥታ ቢፈጥሩም ያሰቡትን ያህል ግን አልተሳካም። ፈጽሞ ያላናገረውን የFBI ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደለመደው ድምጽ ሳያስገባ “የጥቅሱ መጀመሪያ፣ የጥቅሱ መጨረሻ” በማለት አድማጭን ግራ የሚያጋባ ዘገባ ለቀቀ። እኔ እንደ ጋዜጠኛ ባይሆንም እንደ ጉዳዩ ባለቤት ከቦስተን FBI ቃል አቀባይ ግሬግ ኮምኮዊች ጋር ያደረኩት ንግግር የድምጽ መረጃ እስካሁን በእጄ ላይ አለ። በተጨማሪም እንደነ ግኡሽ ስራ ቦታው ድረስ ሄደው የFBI መርማሪዎች ካፋጠጡት ግን በሴራው አለመሳተፉ ከተረጋገጠው ቤዛ ጥላሁን ያገኘሁት ዝርዝር መረጃ ጭምር በእጄ ይገኛል።ዘፋኝና የግኡሽ ደባል የነበረችው አበራሽ የማነ በግዜው የቤዛ ወዳጅ የነበረች ሲሆን አሁን ትዳር መስርተዋል። በወቅቱ ለአበራሽ የማነ መርማሪዎቹ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ውንጀላ ማንም ባያቀርብባትም ፓልቶክ ላይ ብቅ ብላ በሃሰት አበበ ገላው ወነጀለኝ እንድትል ተደረገ። እነ አውራምባ ታምስም ወገንተኛ የሆነና የሚያስተዛዝብ ስራ ሰሩ። ይህንንም በወቅቱ ታዝበን አለፍነው።

FBI በዋነኛነት ትኩረት ያደረገው ግኡሽ ላይ ነበር። ለዚህም ምክንያት ደግሞ እንዳወሩት በፌስቡክ ስለተሳደበ ወይንም ስለዛተ ሳይሆን በግድያ ወንጀል ዱለታ ሊያስጠይቅ የሚችል መረጃ መርማሪዎች እጅ በመግባቱ ነበር። በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ መብት የመርማሪዎቹ ሲሆን የዘገባው እውነታ ግን ከላይ የተጠቀሰው ነው።በግልጽ አፍቃሪ ወያኔ የሆነው ሄኖክ ሰማእግዜር ግን ጥቅስ ብሎ ያነበበውን ብዥታ የሚፈጥርና ከዋናው ጭብጥ ውጭ የሆነና አዛብቶ ያቀረበውን ሃተታ በተውሶ የወሰደው ከሶስተኛ ወገን፣ እንደውም እንደሰማሁት ከሆነ፣ ከትግሪኛ ዝግጅት ክፍል ነበር። ይሁንና ጥረቱ እውነቱን አልቀየረውም። ግኡሽ አበራ እኔን በስም ማጥፋት በፍርድ ቤት እንደሚከስ ወያኔዎች ደጋግመው ከመናገር አልፈው ከፍትኛ ገንዘብ ቢያዋጡም እስካሁን የተሰማ ክስ የለም።እኔ በወቅቱ ወንጀል ሲዶልት የተደረሰበት ሰው ማንንም በስም ማጥፋት መክሰስ አይቻለውም ያልኩት እውነትን በመተማመን ነበር። አሁንም ፍርድ ቤቶች ክፍት ስለሆኑ ግኡሽ ብቻ ሳይሆን የውሸት ዘገባ በማሰራጨት እጅ ከፍንጅ በመያዝ አደባባይ ያወጣሁት ሄኖክ ሰማእግዜር (እስከ እረዳቶቹ) ዶሴውን ጠርዞ ፍርድ ቤት መሄድ ይችላል። ይሁንና ውሸት ታጥቆ አየር ላይ መውጣትም ይሁን የውሸት ዶሴ ጠርዞ ፍርድ ቤት መሮጥ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ።የአሁኑ ይባስ እንዲሉ ሄኖክ አቶ ሃይለማሪያም አሜሪካ ሳይደርሱ ላስቸኳይ ስራ ተመለሱ፣ ያልደወሉትን ስልክ ደውለው ክብሩ ይቅርብኝ አሉ፣ እኔ ያልጻፍኩትን ደብዳቤ እያነበበና እያጠቀሰ፣ ያልተናገርኩትን ተናገረ፣ ያልዘገብኩትን ዘገበ እያለ ፈጽሞ ያላናገራቸውን ቃል አቀባይ ያላሉትን አሉ እያለ፣ አደባባይ ወጣ። በሁዋላ ስናጠያይቅ እንደውም የተረዳነው አሳፋሪው የቪኦኤ የሃሰት ዘገባ የተሰራው በቡድን ለሶስት መሆኑን ነው።ታዲያ ምነው ይሄ ሁሉ የቪኦኤ ሰራዊት አንዲት ቅንጣቢ መረጃ ማውጣት ተሰናው? ከሁሉ የሚገርመው ደግሙ ውሸታችን “ቢቢጂ” የተባለ ቦርድ አጸደቀልን ብለው አይናቸውን በጨው አጥበው አደባባይ መውጣታቸው ነው። በእውነቱ በጣም ያሳዝናል። ቢቢጂም ቢሆን በመረጃ የተደገፈ ማስተባበያ ይዞ እስካልመጣ ድረስ አድማጭም አክባሪም በቀላሉ ማግኘት ይችላል ብዬ አላምንም። የተራዳሁት አንድ ጉዳይ ቪኦኤ ውስጡን ለቄስ ነው። ማንንም የመውደድም ይሁን የመጥላት ግላዊ መብታቸውን ብናከብርም ውሸት ታጥቀው አየር ላይ ከወጡ ግን ችላ ሳንል ደግመን በእውነት ሚሳኤል አናወርዳቸዋለን።እኛ ለህዝባችን ነጻነትና መብት ከመከራከርና ከመታገል አንቆጠብም። ለዚህም ደግሞ ከማንም ፍቃድ አንጠይቅም። አንዳንድ የቪኦኤ አማርኛ ክፍል ባልደረቦች የእነ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ክብር ተነካ ብለው እኛን ለማጥቃት መነሳታቸው ባያስገርምም ያሳዝናል። በከንቱ ይደክማሉ እንጂ አቶ ሃይለማርያምም ሆኑ አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በዙ ተቀጣሪዎች አሏቸው። ሁለቱም ወገኖች ቪኦኤን በቃል አቀባይነትይሁን በጥብቅና አለመቅጠራቸውን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

እንኳን በሜድያ ስራ የተሰማራ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ይቅርና ማንም እንደሚያውቀው አንድ ሚድያ ስተት ሲሰራ ባግባቡ እርማት እንዲያደርግ ይጠየቃል። ስህትት ተሰርቶ ከተገኝም አግባብ ባለው መንገድ እርምት አድርጎ ይቅርታ ይጠይቃል።። ቪኦኤን የሚያህል ግዙፍ ተቋም የሌሎችን ስራ ከማኮሰስ አልፎ በውሸት ጭብጦ የእውነትን ተራራ ለመናድ ጥረት ማድረጉ በጣም ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ከመሆን አልፎ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ የሚለውን አባባል ያስታውሰናል።ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ በዚህ የሀሰት ዘገባ ቁልፍ ሚና የተጫወተው ፒተር ሃይንላይን በአጠያያቂ መስፈርት ባለፈው ሳምንት ለሄኖክ ሰማ እግዜር “ሽልማት” ማቀበሉ ነው። ሄኖክም ይህንኑ ሽልማት ከአፍሪካ ክፍል ሃላፊው ከአቶ ንጉሴ መንገሻ እጅ ተቀብሏል። በርግጥ ሄኖክ ለማዛባትና ሃሰትን በይፋ በማሰራጨት ተወዳዳሪ ስላልተገኘለት ታላቅ ሽልማት ይገባው ይሆናል። ለጋዜጠኛነቱ ሽልማት መስጠት ግን ጋዜጠኝነትን መስደብ ነው።በዚህ አይን ከፋች በሆነ አጋጣሚ ከእነ ሄኖክና ፒተር ሃይህላይን ይልቅ የአማርኛው እና የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ የሆኑ ሁለት አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን በጣም ታዘብኩ።። ክብር ወደ ትዝብት ያለ ምክንያት እንደማይቀየር ለማንም ግልጽ ነው። ለምን ታዘብከን ብለው ከጠየቁኝ ምላሹን በዝርዝር በአደባባይ ላስረዳቸው ዝግጁ ነኝ። እስከዛው ሆድ ይፍጀው በማለት ለዛሬው የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የቪኦኤን ከድጡ ወደ ማጡ የሆነውን የሰሞኑን ጉዞ አስመልክቶ ያዘጋጀውን ምርጥ ዝግጅት ካልሰሙት አያምልጥዎ።

መልካም አዲስ አመት ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!


በህወሀት እና በአጋር ፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ ነው

ሁኔ አቢሲኒያ

እስከ ጳጉሜ 4 2006 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በርካታ እንግዳ ክስተቶችን ይዞ የተገኘ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ ስብሰባ ብአዴን እና ኦህዴድ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን የማስፈጸም ውስንነት እንደታየባቸው አልፎ ተርፎም የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ኢሊባቡር እና አምቦ የኦነግ ምሽግ የሆኑ ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በአርበኞች ግንባር ቁጥጥር ስር ለመዋል እንደተቃረበ፣ በአመራሩ እንዝህላልነት ህዝቡ ከኢህአዴግ እየራቀ እና ለድርጅቱ ጀርባውን እንደሰጠ ከመድረክ ተገልጽዋል:: በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩት የብአዴን እና የኦህዴድ አመራሮች የተቀሰው አካባቢ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሚሆኑ አባላት እጥረት እንዳለ፣ ህዝቡ በተደጋጋሚ በአካባቢው አመራሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደሚያደርስ ገልጸው ይህም ሊሆን የቻለው በአካባቢው ያለው የሀይል እጥረት እንደሆነ ገልጸዋል::

አዲሱን ዓመት በማስመልከት ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ እስር ቤት

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም፡፡ ይህ ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው፡፡ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው፡፡አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ

Ginbot 7’s point man in Eritrea arrested

According to new Ethiopian Review report :- Ato Zemene Kasse, the field representative of Ginbot 7 in Eritrea and head of political affairs, has been arrested by Shabia, according to Ethiopian Review sources.

It has been several days since Zemene had disappeared after having an argument with Eritrean intelligence agents about the detention of some young Ethiopians under his command who were recruited by Ato Andargachew Tsige and brought from Uganda and South Africa to Eritrea. Repeated request by him to get an answer for their arrest were ignored by Shabia. Then Zemene himself disappeared and one of his friends who is currently in Sudan confirmed to Ethiopian Review today that he is arrested.

Zemene is arrested simply for asking about the well-being of his comrades.

Shabia’s Eritrea has turned out to be a Bermuda Triangle for Ethiopian heroes such as Zemene, Andargachew, Tadesse, Fisseha, Getachew, Yoseph, Adane, Kassahun, and so many others. source satenaw


2007 ወሳኝ የትግል ዓመት!!!

ሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት ለኛ ለኢትዮጵያዊያን በአብዛኛው በመጥፎ የሚታወስ ዓመት ነው። 2006፣ በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ በአፍሪቃ በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ዓመት ነበር። 2006፣ ቀደም ባሉ ዓመታት አገራቸዉን ለቅቀዉ የተሰደዱ ሳይደላቸው በርካታ አዳዲስ ስደኞች ከአገር ወጥተው በበረሃዎችን ቀልጠው፤ በባህር ሰጥመው ያለቁበት አሳዛኝ ዓመት ነው። 2006፣ ጥንቃቄ በተሞላበትና በተቆጠበ መንገድም ቢሆን የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ወገኖቻችን ወደ እስር ቤቶች የተጋዙበት ዓመት ነው። 2006፣ በአምቦ፣ በለቀምት፣ በጅማ በሀረር በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተገደሉበት፤ በአስር ሺዎች የሚገመቱት ደግሞ የታሰሩበት ዓመት ነው። 2006፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባና አካባቢው በ100 ሺዎች የሚገመት ኢትዮጵያዊ የተፈናቀለበት ዓመት ነው። 2006 ቁጥራችው ቀላል ያልሆኑ የነፃነት ታጋዮች ከጎረቤት አገራት ታፍነው ወደ እስር ቤቶች የተጋዙበት ዓመት ነው። 2006 የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጉዞ ላይ እያለ በትራንዚት አውሮፕላን ለመቀየር ባረፈበት በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በየመን መንግሥት ወንበዴዎች ታፍኖ ለሸሪካቸው ህወሓት በህገወጥ መንገድ አስተላልፈው ለስቃይ እንዲዳረግ የተደረገበት ዓመት ነው። በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ነው 2006 “ጥቁር ዓመት” የሚል ስያሜ ያገኘው።ጭንቅላት የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው ድኩማን ሰላዮችና ፈንጋዮች የመጨረሻውን የመንግሥት ሥልጣን የያዙበትና ውሳኔያቸው “እሰረው፣ ክሰሰው፣ ግረፈው፣ ግደለው …” ብቻ የሆነበት ዓመት መሆኑ የ2006 ልዩ መታወቂያው ሆኖ ይቆይ ይሆናል። ይሁን እንጂ በ2006 ጨለማ ውስጥ የታዩ የብርሃን ጨረሮችም እንደነበሩና እንዳሉም መርሳት አይገባም።በሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቸውም በላይ በህወሓት አገዛዝ አምርሯል፤ በሁለገብ ትግል የህወሓትን አገዛዝ ለመፋለም የቆረጡ ወገኖች ትብብር ተጠናክሯል። በ2006፣ ኢትዮጵያ ዉስጥም ከኢትዮጵያም ውጭም የንቅናቄዓችን የግንቦት 7 ድርጅታዊ መዋቅር ተጠናክሯል። በ2006፣ ከህወሓት አገዛዝ ጋር ያለው መፋጠጥ ከሯል። እነዚህ ሁኔታዎች 2007 አገራችን በለውጥ ማዕበል የምትናጥበት ዓመት ሊሆን እንደሚችል ያመለክታሉ።በአዲሱ ሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ትልቁ ሥራ ድርጅታዊ አቅምን ማጎልበት ነው። በተለይ ወጣቶች በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ ሕዝባዊ የትግል ድርጅቶችን እንዴት መመሥረት እንደሚቻል ማጥናት እና መፈተሽ ይኖርባቸዋል። ትናንሽ የግንቦት 7 ድርጅታዊ ቋጠሮዎች በመላው አገሪቱ መሠራጨት ይኖርባቸዋል። ወጣቶች ትናንሽ ኢ-መደበኛ ስብስቦችን ቶሎ መፍጠር እና አደጋ ሲያጋጥም ቶሎ ማፍረስ መልመድ ይኖርባቸዋል። ይህንን ክህሎት ደግሞ በቀጥታ ከሌሎች አገራት ከመዋስ ሀገር በቀል ቢሆን ይመረጣል።በሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የጽዋ ማኅበሮች፣ መድረሳዎችና ጀማዎች፣ የስፓርት ቡድኖችና ደጋፊዎች፣ የመንደር ደቦዎችና የቡና ተርቲቦች፣ ስም ያላቸውም፣ ስም የሌላቸውም ስብስቦች የግንቦት 7 አባላት መገናኛዎች ይሆናሉ። በ2007 የግንቦት 7 አባል መሆን የምርጥ ዜግነት ምልክት መሆኑ በስፋት ተቀባይነት የሚያገኝበት ዓመት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በ2007 በህወሓት ካድሬዎች “ሽብርተኛ” መባል የሚያስደስትና እንደ ሽልማት ተደርጎ የሚወሰድበት ዓመት ይሆናል ብለንም ተስፋ እናደርጋለን። በ2007 እስር ማስፈራሪያ መሆኑ ያከትማል። በ2007 የኢትዮጵያ ወጣቶች በአርበኝነታቸው ይታወቃሉ። በ 2007 እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህወሓት ሹማንምትን ዘረፋ የሚያጋልጥበት ዓመት ይሆናል። 2007 ዳኞች “እንቢ፣ በሀሰት አንፈርድም”፤ የመንግሥት ጋዜጠኖች “እውነቱን ደብቀን አንዋሽም”፤ ፓሊሶች “ወገናችንን አንደበድብም፣ አናስርም፣ አንገርፍም”፤ ወታደሮች ደግሞ “በወገናችን ላይ አንተኩስም” የሚሉበት ዓመት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።በዚህም ምክንያት 2007ን የምንቀበለው በታላቅ ተስፋና ዝግጅት ነው። በ 2007 ነፃነትና አምባገነንነት፤ ዘረኛነትና አንድነት፤ እውነትና ውሸት፤ አድርባይነትና አርበኝነት፤ ዝርፊያና ንጽህና፤ ድህነትና ብልጽግና የሚፋጠጡበት ዓመት ይሆናል ብለን እንጠብቃለን። በአጭሩ 2007 የወሳኝ ትግል ዓመት ይሆናል።ሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የኢትዮጵያ መፃዒ እድል የሚወሰንበት ዓመት በመሆኑ ሁላችንም በተነሳሳ የአርበኝነት መንፈስ እንድንቀበለው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።መልካም አዲስ ዓመት!ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

የሕወሓቱ ታጋይ ሌተናንት ጀነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል በ95 ሚሊዮን ብር ቦሌ ላይ ህንፃ አስገንብተዋል

የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ።ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል።ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል። (በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል)  ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል።በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ

የትግል ምቀኝነት ወይንስ ሰርጎ ገብነት? ስለ ኤልያስ ክፍሌ የማውቀው በፈቃዱ ጌታቸው

ስለ ኤልያስ ክፍሌ የማውቀው—-

ይህ ጽሁፍ የመጨረሻዬ ነው፡፡ እስከሚቀጥለው ስድስት ወር ድረስ፡፡ ለአሁን እስቲ ሰዎችዬ አንድ ነገር ልበላችሁ፡፡ ስለኤልያስ ክፍሌ፡፡እውነት ለመናገር ይህንን ሰው በፎቶ፣በሚጽፋቸው ነገሮችና ከጥቂት አመታት በፊት በእሱ አመራር በከተማ ውስጥ ይበተኑ በነበሩ በራሪ ወረቀቶች ነው የማውቀው፡፡ቅንጅቶች የታሰሩ ጊዜ፡፡ያኔ በጩጬነታችን፡፡ተግባር ሊግ በሚባል እንቅስቃሴ ውስጥ የታቀፉ አንዳንድ ወጣቶች በየትምህርት ቤቱ ፣በማታ ተደብቀው በየመንገዱ ህዝቡን ለትግል ይቀሰቅሱ ነበር፡፡ያኔ Ethiopianreview.com እና Tegbarleague.org በሀገር ቤት አልታፈኑም ነበር፡፡ሌሎችም እነዚህን የመሰሉ የወሬ ምንጮች የተፈቀዱ ነበሩ፡፡ከሰፈር ልጆች ጋር እየተጠራራን በየኢንተርኔት ቤቱ እየሄድን በየቀኑ ምን ተባለ ብለን የምናው በዋናነት የእሱን ገጾች ነበሩ፡፡ያኔ ምንሊክ ሳልሳዊ ምናምን የሚባል ነገር አልነበረም፡፡እንዳውም አንድ ጊዜ የአርበኞች ግንባር ተብሎ ለሚጠራው ታጣቂ ሀይል(በፕሮፌሰር ሙሴ ይመራ ለነበረው) የተለያዩ ቁሳቁሶችንና አልባሳት ይዞ ወደ ኤርትራ እንደሄደም በራሱ ገጽ ላይ ለጥፎ አንብበናል፡፡ስለኤልያስ ጥሩ አመለካከት ስለነበረንም በየመንገዱ በኢትዮጵያን ሪቪው ስም የታተሙ መጽሄቶችን ሳይቀር መማሪያ ይሆኑናል፣ ቅርስም ናቸው ብለን እየገዛን ወደ ቤታችን እንገባ ነበር፡፡ገና ህወአትእንዲህ መሰረት ሳይዝ በፊት የገባ ሰሞን የተለያዩ ሀተታዎችን ይዘው ይወጡ የነበሩ መጽሄቶች፡፡በሀገር ጉዳይ ጥብቅና በመቆም ያቀረባቸው የተለያዩ ጽሁፎች ማየት ልምዳችን ነበር፡፡ምናልባት ኢትዮጵያን ሪቪው ስናነብ እንዳያመልጠን ብለን እናየው የነበረው ኢትዮሚዲያ ብቻ ነበረ፡፡

Thursday, September 11, 2014

ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ደህንነት አደጋ ላይ ነው፡፡ 



እህታችን እስከዳር ይህንን ማስታወሻ ከጻፈሽው አመት ሆነው አሁንም የርእዮት ጉዳይ አልተለወጠም አልተሻሻለም።

ማስታወሻ፦እነሆ ይህንን ማስታወሻ ከፃፍኩ ዛሬ አመት ሆነ፤ ካየኋት አመት ሞላኝሉሉዬ ምንም ባላይሽም ያጠንካራ መንፈስሽ አብሮኝ ነዉ!!መልካም በአል መልካም ዘመን ይሁንልሽ የኔ ሁሉነገር!! ጳጉሚ 2006

እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ” !
==============
"የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ " ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡ በማለት እህቷን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሄደችው Eskedar Alemu የጋጣማትን ነገር በማህበራዊ ድረ-ገፅ አሳውቃናለች፡፡

በርዕዮት ላይ እየደረሰባት ያለው ህገወጥ ተግባር ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንግድ የሚፈፀም መሆኑ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፤እየደረሰባት ላለው ህገወጥ ተግባር በመቃወም በአሁን ሰዓት ርዕዮት የርሃብ አድማ ላይ ትገኛላች፡፡
በተለይ አሚናዘር የምትባል የወያኔ ቀንደኛ አገልጋይ በርዕዮት ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እያደረሰችበት እንደምትገኝ እንዲሁም ኮ/ል ሐይማኖት የገብሩዋድ ባለቤት በመኝቷ ክፍል ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንደምታደርስባት ርዕዮት ለቤተሰቦቻ ገልፃለች፡፡

ሁኔታው ይበልጣ አሳሳቢ የሚያደርገው ርዕዮት ለቤተሰቧቻ እና ለአድናቂዋቻ ያስተላለፈችው መልዕክት ነው “ህይወቴ አደጋ ላይ መሆኑን አንድ ነገር ቢፈጠር በህመም እንዳልሆነ እንድታዉቁት እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ” ማለቷ የመንፈስ ጥንካሬዋን ቢያመላክትም እየደረሰባት ያለው በደል ከመጠን ያለፈ መሆኑ አመላካች ነው፡፡
ውድ እህቴ ርዕዮት ! ፈጣሪ ብርታቱን አብዝቶ ይስጥሽ፣ከምትወጂያቸው ቤተሰቡ እና ወዳጅ ዘመዶችሽ የምትገናኚበት ቀን እሩቁ አይሆንም!!! ይህም እውነት እንዲሆን የእውነት አምላክ ከጎናችን ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Tuesday, September 9, 2014

The betrayal of Andargachew Tsige - SPECIAL REPORT

 the past two months, Ethiopian Review has been investigating the shocking abduction of one of Ethiopia's most senior opposition leaders, Ato Andargachew Tsige, by the TPLF junta with the assistance of Yemen's secret police. Our investigation has uncovered that the Eritrean intelligence not only has passed Andargachew's itinerary to TPLF, but more importantly, they gave green light to Yemenis to carry out the kidnapping.

The trouble for Ato Andargachew started when he argued with Eritrean officials about the amount of assistance Ginbot 7 has been receiving and the obstacles they were placing against his effort to form an armed force. Despite repeated promises, year after year, he was unable to make progress with the Eritrean regime.

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት 400 ሰዎች በተገደሉበት የጋምቤላ ጭፍጨፋ የሕወሓት ባለስልጣናት መሳተፋቸውን አጋለጡ

የቀድሞው የጋምቤላ መሪ በክልሉ ለደረሰው ጭፍጨፋ የህወሃት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረጋቸውን ኢሳት ዘገበ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞት ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400 ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላው ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር ሁሉን ነገር ተናግረዋል።

እንደ ኦሞት ገለጻ የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ፀሐዬ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ያሉ ሲሆን በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር በዝርዝር ተናግረዋል።

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞድ ወደ ውጭ ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰጡት በተነገረው በዚህ ቃለምልልሳቸው ላይ 400 ሰዎች በግፍ በአባይ ፀሐዬ ከፍተኛ ሚና መገደላቸውን መዘርዘራቸው ወደፊት በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ለሚከፈተው ክስ ጥሩ ምስክር ሊሆን ይችላል ተብሏል።


በአዲስ አበባ በየሰፈሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች “ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው በሚል ወከባ ይደርስባናል” አሉ

አዲስ አበባ ውስጥ በየ ቤቱ እየዞሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው›› በሚል ወከባ እንደሚደርስባቸው ገለጹ፡፡ ወጣቶቹ ከኢሳት ውጭ ያሉ ጣቢያዎች የሚተላለፉበት ዲሽ በሚገጥሙበት ወቅትም ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው፡፡ ህዝቡ ኢሳትን እንዲያይ ታደርጋላችሁ›› በሚል በደህንነቶች ወከባ እንደሚደርስባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ከወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን ለህዝቡ እያሳያችሁ ነው›› ተብለው በፖሊስ ተይዘው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኢሳትን እንደሚገጥሙ የሚያሳዩ የዲሽ ማስታወቂያዎች ይታያሉ፡፡ ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ


በብሶት የታፈነው ህዝብ አመፅ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ወያኔ አድሮበታል።

በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ የሚመራ ልዩ የኮማንዶ እና የደህንነት ሃይል አዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋን መቆጣጠር የሚችልበትን ስልት እየነደፈ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) 2007 ለለውጥ !

- በሳሞራ የኑስ የሚመራው የኮማንዶ ጦር ህገመንግስታዊ ጥያቄ ማንሳቱ ታማኝነቱ ጥርጣሪ ውስጥ ገብቷል
- መጪው ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ገነው ይወጣሉ።
- ዲያስፖራው ከምንም ጊዜ በበለጠ ለወያኔ የጎን ውጋትና ራስ ምታት ሆኗል።
- ተቃዋሚ ሃይሎች በአሁን ወቅት ከባድ ጥንካሬ እና የትግል ስልት ሊኖራቸው ይገባል።ጊዜው ነው።

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ በብሶት የታፈነው ኢትዮጵያዊ በቀጣዮቹ ጊዜያት ከፍተኛ አመጽ ያስነሳል በሚል ስጋት ያደረበት እና አመፁ ከመንግስት ሃይሎች ቁጥትር ውጪ ይሆናል በሚል ከፍተኛ ውጥረት በስጋት የተደባለቀበት የወያኒው ጁንታ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ስብስባ የተቀመጠ ሲሆን ካለፉት ሳምንታት ተከታታይ ስብሰባዎች በተገኙ የውይይት ፍሬ ሃሳቦች መሰረት በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ የሚመራ ልዩ የኮማንዶ እና የደህንነት ሃይል አዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋን መቆጣጠር የሚችልበትን ስልት እየነደፈ ነው።

እስር ቤቶቻችን በሕገ-መንግሥት ወይንስ በ‹‹ሕገ-አራዊት››?

በጌታቸው ሺፈራው
---------------------
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትን እንዲጸድቅ በበላይነት የመሩት አቶ መለስና አቶ ሌንጮ ለታ መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡ ይህ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ባልሆኑት የተገንጣይ መሪዎች ጠንሳሽነት የጸደቀው ሕገ መንግሥት ለአገር ሉኣላዊነት፣ አንድነትና ታሪክ ክብር የሌለው ቢሆንም ዓለማቀፋዊ የሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አጠቃልሏል፡፡ ሆኖም እነዚህ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለእርዳታ ማሰባሰቢያ የተቀመጡ እንጂ ወደመሬት ወርደው ተግባራዊ መሆና ባለመቻላቸው የይስሙላህ ሕግ ሆኗል፡፡ ከሕገ መንግሥቱ ይልቅ የገዥዎች ጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ለማስጠበቅ በየጊዜው ትርጉሙ የሚቀያየረው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹‹መርሕ›› ሕዝብ ላይ የተጫነ ገዥ ሕግ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይህን ስርዓት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ‹‹ሕገ አራዊት›› ሲሉ ይገልጹታል፡፡ በዚህ ስርዓት ሕዝብ በሕግ ስም እንጂ በሕግ የሚዳኝበት አጋጣሚ አይታይም፡፡ ብዙዎቹ በዚህ ስርዓት ያለውን የኢትዮጵያን ሕዝብም የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታና ለወደፊት የሚታሰር እያሉ በቀልድ መልክ በሦስት የእስራት ምድብ ያስቀምጡታል፡፡ እንደ እኔ ሌላ አራተኛ ምድብም ሊካተት ይገባዋል፡፡ ይኸኛው እንደ ሦስቱ ምድቦች የአካል ጉዳትና ሰብኣዊ መብት ጥሰት የማይደርስበት ሕገመንግሥቱን አጽድቆ ራሱ የሚጥሰው አሳሪው ክፍል ነው፡፡ ይህ አሳሪው የኅብረተሰብ ክፍል በአካል ያልታሰረና ስርዓቱ እስካለ ድረስ በአካል ሊታሰርበት የሚችለው አጋጣሚ ጠባብ ቢሆንም የአዕምሮ እስረኛ ነው፡፡

ኢህአዴግ በአንድ አመት ውስጥ ለተለያዩ ዝግጅቶች ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱ ተሰማ

 ኢሳት ዜና :-በአለፈው አንድ አመት ውስጥ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለፓርቲው የፖለቲካ ስራ የሚጠቅም ከመንግስት ባጀት ከ900 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ማውጣቱን ምንጮች ገለጹ።

ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን፣ ለባንዲራ ቀን፣ ለመከላከያ ቀን፣ ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የፖለቲካ ስልጠና፣ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ የኢህአዴግ አባላት ስልጠና፣ ለፖሊስ ሰራዊት የተሰጠው ስልጠና፣ እንዲሁም በተለያዩ ታሃድሶ የሚል ስያሜ በተሰጣቸው ስልጠናዎችና ስብሰባዎች ከመንግስት ባጀት እስከ 900 ብር ወጪ መደረጉን እስካሁን የተሰባሰቡት የወጪ ደረሰኞች እንደሚያሳዩ ምንጮች ገልጸዋል።

አንዳንድ ወጪዎችን ክልሎች ቢያወጡዋቸውም ፣ ወጪው ከመንግስት ባጀት የሚሸፈን መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፣ አሃዙ ተጠቃሎ ሲታወቅ ወጪው ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።

ገዚው ፓርቲ ለራሱ የፖለቲካ ስራ በተለያዩ ሰበቦች ገንዘብ ከመንግስት ካዝና ማውጣት መቀጠሉ፣ ታክስ ከፋዩ ህዝብ በተዘዋዋሪ መንገድ ሳይፈልግ ፓርቲውን እዲደግፍ እያደረገው መሆኑንና የአገሪቱ አጠቃላይ ኦዲተሮችም ይህን ወጪ እንደመንግስት ወጪ በመያዝ ፓርቲውን ተጠያቂ ለማድረግ እንዳልቻሉ ምንጮች አክለው ተናግረዋል።

በተለይ የብሄር ብሄረሰቦች ፣ የባንዲራ እና የመከላከያ ቀን በሚባሉት ዝግጅቶች የአንድ አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው እነሱ በመሰረቱት የዝግጅት ኩባንያ ዝግጅት በማዘጋጀት ከፍተኛ ገቢ እንደሚያገኙ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነዚህ ሰዎች ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በፈጠሩት ሽርክና የተለያዩ ሃሳቦችን
እያመጡና እና እያስጸደቁ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመመዝበር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ግንባሩ ከዚህ ቀደም ለኤች አይ ቪ ቫይረስና ለሌሎችም በሽታዎች መከላከያ የሚመጡ ፈንዶችን ሲጠቀም መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮች፣ በተለይ ግሎባል ፈንድ የተባለው አለማቀፍ ለጋሽ ድርጅት ለኢትዮጵያ ይሰጥ የነበረውን እርዳታ መቀነሱን ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ የመንግስትን ባጀት በመጠቀም
የፖለቲካ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አንዳንድ ዝግጅቶች በመንግስት ስም እውቅና ቢሰጣቸውም ዋና ተልእኮዋቸው የኢህአዴግን አብዮታ ዲሞክራሲ

ፖሊሲ ማንጸባረቅ መሆኑን ምንጮች አያይዘው ተናግረዋል።

የለውጡ አካል መሆኛው ግዜው አሁን ነው

እኔም አንዳርጋቸው ነኝ የሚል ድምፅ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እያሰተጋባ ነው። ይሄን ድምፅ የሚያቆመው አንዳችም ምድራዊ ኃይል አልተገኘም። ኢትዮጵያዊ ባለበት ሥፍራ ሁሉ ይሄ ድምፅ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው። ይህንንም ተከትሎ “ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ” የሚለው መዝሙር በኢትዮጵያ ተራሮች እናት ላይ እየተዘመረ ነው። ፍትህ ተዋርዳለች፤እኩልነት ጠፍቷል፤ ነፃነት የለም ያሉ ምርጥ ኢትዮጵያዊያን ሳያቅማሙ አያቶቻቸው በተመላለሱበት ተራሮች ላይ ተሠማርተዋል። ሞትንም ንቀው ጋሻ አንስተዋል፤ ሰይፋቸውንም መዘዋል። ለፍትህ፤ ለዕኩልነት እና ለነፃነት የተመዘዘው ሰይፍ ከእንግዲህ ወደ ሰገባው እንደማይመለስ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን።

በኢትዮጵያችን ፍትህ ከጠፋ ብዙ ዘመን ሁኖታል። ከሁሉም ዘመን የህወሃቶች ዘመን ግን የተለየ ነው። ህወሃቶች ህግን ዜጎችን የማጥቂያ መሣሪያ አድርገው መጠቀማቸው ከሌሎች እንዲለዩ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ቡድኖች ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቂም መወጣጪያ ህጎችን አውጥተዋል። እንዲህ በማድርጋቸውም ሠላም እናገኛለን ብለው ያስባሉ። የህወሃቶች አስተሳሰብ ደካማና እርባና ቢስ መሆኑን ከሚያሳዩ ተግባሮቻቸው መካከል አንዱ ይሄው በፍትህ ሳይሆን በህግ ብዛት ሠላም እናገኛለን ብለው ተስፋ ማድረጋቸው ነው። የህግ ብዛት ሠላምን አያስገኝም፤ ፍትህንም ማስፈን አይችልም። እንዲያውም ህግ በበዛ ቁጥር ፍትህ እየጎደለች እንደምትሄድ የህወሃቶች ድርጊት ደህና ምስክር ነው። እነርሱ ዜጎችን ለመበቀያ ብለው የሚያወጧቸው ጥቃቅን ህጎች እነርሱ “ህገ መንግስት” ብለው የሚጠሩትን የሚንዱ እና ፍትህን ዋጋ የሚያሳጡ ሁነው እያየናቸው ነው። የፀረ ሽብር ህጉ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን

በቀጣዮቹ የግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባዎች ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት እንደሚሳተፉባቸው ይጠበቃል

ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባሳለፍነው ቅዳሜ፤ እሁድና ሰኞ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የተካሄዱትን ጨምሮ በደ.አፍሪካ፣ በኖርዌይ፡ በጀርመን፤ በካናዳ፡ በአውስትራሊያ፡ ፊንላንድ፡ በኒውዝላንድና በደ. ኮርያ ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል። ላንች ነው ኢትዮጵያ! የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ኢትዮጵያውያኑ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችና ንቅናቄው ወደ ፊት ሊወስድ ባሰባቸው ዕቅዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ተዘግቧል። በየመድረኩም ለወጣቶች፡ ለሴቶች ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለመከላከያ ሰራዊቱ የተቀላቀሉን ጥሪ ቀርቧል። በቀጣይ ቀናት በሚካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባዎችም በሌሎች አገራት እንደታየው ሁሉ በየ አገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት እንደሚታደሙባቸውና ከንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአገራቸው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በዚህ በያዝነው ሳምንት በሴፕቴንበር 6 በአሜሪካ በሎሳንጀለስ ግዛት፤ በአውሮጳ በእንግሊዟ ለንደንና በስዊድን እስቶኮልም እንዲሁም በሴፕቴንበር 7 በሳንቲያጎ አሜሪካና በሜልቦርን አውስትራሊያ ህዝባዊ ስብሰባዎች በድምቀት እንደሚካሄዱ ይጠበቃል። የህዝባዊ ስብሰባዎች ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ኢትዮጵያውያን እየተጠበቁ እንደሚገኙም ከየ አገራቱ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በሚካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ በየ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።


ፍርድ ቤት የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ጉዳይ በሌሉበት ማየቱን ቀጥሏል

ኢሳት ዜና :-መንግስት በመግለጫ የከሰሳቸው ጋዜጠኞች አግር ጥለው ከወጡ በሁዋላ ጉዳያቸው
በሌሉበት እየታየ ነው።
ከሳምንት በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው እኢነዲቀርቡ የታዘዙት የፋክት፣ አዲስ ጉዳይ እና ሎሚ መጽሄት አዘጋጆችና ባለቤቶች ፍርድ ቤት
ለመቅረብ ባለመቻላቸው 17ኛው ወንጀል ችሎት ጉዳያቸውን በሌሉበት ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹ ህመንግስታዊ ስርዓቱን በአመጽ ለማፍረስ አስበዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ እንደማስረጃም የቀረበው ህዝቡን ለአመጽ
የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አትመው አሰራጭተዋል የሚል ነው።
የሎሚመፅሄትስራአስኪያጅአቶግዝውታዬ ቀድም ብሎ ፍርድ ቤት በቀረሩበት ወቅት በ50 ሺ ብር ቢለቀቁም ከዚያ በሁዋላ በነበሩት ችሎቶች
ባለመገኘታቸው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ፍርድ ቤት ወስኗል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡትን የማራኪ መጽሄት ባለቤትና አዘጋጅ ሚሊዮን፣ የቃል ኪዳን መጽሄት አዘጋጅ ኤለያስ ጉዲሳ እና የአዲስ ጉዳይ ዘጋቢ
መድሃኒት ረዳን ጨምሮ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 20 ደርሷል። ኢትዮጵያ በሚሰደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር በአለም ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች።


Monday, September 8, 2014

"ሰማያዊ ፓርቲ መጥቶ ያድንሽ እያሉ ነበር ከበው የደበደቡኝ"ወይንሸት ሞላ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የሆነችው ወይንሸት ሞላ፤ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመከታተል አንዋር መስጊድ ሄዳ በነበረበት ወቅት በደህንነት ታፍና፤ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተደበደበች መወሰዷን በድረ ገጻችን ላይ ገልጸን ነበር። ከዚያም ሰውነቷ ተጎድቶ እና ደክሞ ፍርድ ቤት ትመላለስ የነበረ መሆኑን በመጨረሻም በዋስ መፈታቷን በወቅቱ ገልጸናል። ከ”ነገረ ኢትዮጵያ” መጽሄት ጋር ያደረገችው ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታተም በመደረጉ ምክንያት አዘጋጆቹ ቃለ ምልልሱን በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ለቀውታል። እኛም ይህንኑ ቃለ ምልልስ ለናንተ ልናጋራቹህ ወደድን። ከዚህ በታች አቅርበነዋል።ወ/ት ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ስትሆን ፓርቲው በሚያደርጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል እንደሆነች ይነገርላታል፡፡ ወጣቷ ፖለቲከኛ ወይንሸት ሞላ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ለዓመታት የዘለቀው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ አካል የሆነውንና በዕለቱ በአኑዋር መስጊድ የተደረገውን የተቃውሞ ሁኔታ ለማየት በቦታው ተገኝታ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ወ/ት ወይንሸት በዕለቱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ለ29 ቀናት በእስር ቆይታ በዋስ ተለቅቃለች፤ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ስለጉዳዩ አነጋግሯታል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- አንዋር መስጊድ አካባቢ ተይዘሽ ከታሰርሽ በኋላ ለምን መስጊድ ሄደች የሚሉ አካላት ነበሩ፡፡ ለመሆኑ እንዴትና ለምን ነበር የሄድሽው?
ወይንሸት፡- የሄድኩበት ምክንያት ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ እኔ የሄድኩበትን ብቻ ሳይሆን በተለይ በገዥው ፓርቲ በኩል የሙስሊሙን ማህበረሰብ እንቅስቃሴም ባልሆነ መንገድ ትርጉም እየተሰጠው ነው የሚገኘው፡፡ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ እንደሆነ አድርገው በተሳሳተ መንገድ ያቀርቡታል፡፡ የእኔንም ከዚህ በተለየ ሁኔታ አይደለም ያቀረቡት፡፡ ምን አልባት የእኔ ይለያል ከተባለ ፖለቲከኛ በመሆኔ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም እኔም የሄድኩት እንቅስቃሴውን ለማየት ነው፡፡ ይህን ለማየት የሄድኩበት ምክንያት አንደኛ ገዥው ፓርቲ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሰላማዊ አይደለም ብሎ ስለሚፈርጅ ነው፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ እንቅስቃሴው ሰላማዊ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ለህዝብ እንደቆመ እንደ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልነቴም ሆነ መሪ ለመሆን እንደምትፈልግ አንዲት ሴት ቦታው ላይ ተገኝቼ ነገሮችን ማረጋገጥ ስለነበረብኝ ቦታው ላይ ተገኝቻለሁ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- የተያዝሽበት ሁኔታስ ምን ይመስላል?

በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ የተነሳ የሥርዓቱ አሽከር የሆነው የሸዋፈራው የኮሜዲ ሾው ተሰረዘ

የሕወሓት ኢሕአዴግን አስተዳደር ደግፎ በስደት የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ በሕዝብ ፊት ተሳድቦ ከመንግስት
ባለስልጣናት ፍርፋሪ ለማግኘት ሲሰራ የቆየው ሸዋፈራው ደሳለኝ በዋሽንግተን ዲሲ ሰድቦ ለሰዳቢ ለሰጠው ሕዝብ ትያትር
ለማሳየት የመጣ ቢሆንም ዝግጅቱ ሳይደረግ መሰረዙ ተሰማ።
ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢዎች እንዳስታወቁት የወያኔ/ ኢሕአዴግ አሽከር የሆነው አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ በአሁኑ ወቅት

የኢትዮጵያውያኑን አይን ፈርቶ ተደብቆ የሚገኝ ሲሆን በየሄደበት ቦታ ሁሉ በሚደርስበት ተቃውሞ በከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ
ውስጥ መውደቁ ተሰምቷል።
መንግስትን ለማገልገል ሲል በስደት የሚገኘውን ሕዝብ ተሳድቦ፤ በዚሁ ሕዝብ ላይ ገንዘብ ለመሥራት የመጣው ሸዋፈራው ወደ
አሜሪካ ከመምጣቱ በፊት በሃገር ቤት የሚገኙ የተለያዩ ሴት አርቲስቶችን “አሜሪካ እወስዳችኋለሁ፤ እዛ ሄደን በየ ስቴቱ ትያትር
እናሳያለን” በሚል ቃል በመግባት ሴትነታቸውን ለመጠቀም ባደረገው ግፍ አርቲስቶቹ ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ መውደቃቸው
የተሰማ ሲሆን እዚህ ከመጣ በኋላ ትያትሩን ሊያቀርብ ሲል በተቃውሞ መመታቱ በሃገር ቤት የተበደሉትን ሁሉ እንዳስደሰተ
ምንጮች ጠቁመዋል።ዛሬ እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ ይደረጋል በተባለው የሸዋፈራው ኮሜዲ ሾው ላይ በዲሲ የሚገኙ ታዋቂ አክቲቪስቶች “ካሁን በኋላ
ትዕግስታችን ተሟጧል፤ የወያኔ ተላላኪዎች እንደፈለጉት አይጨፍሩብንም” በሚል በጠሩት ቦይኮት የተነሳ ዝግጅቱ ተሰርዟል።
ለዚህ ዝግጅት ከቪዛና ከትራንስፖርት ጀምሮ በብዙ ሺህ የሚቆጠሮ ዶላሮች የፈሰሱ ሲሆን በኪሳራ ሊሰረዝ በቅቷል።
ከወያኔ ጋር በመተባበር ለሆዳቸው ያደሩ አርቲስቶች በዲያስፖራው ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸው ሲሆን ሃመልማል አባተ ለሲዲ
ምርቃት በጠራችው ኮንሰርት በደረሰባት ቦይኮት 55 ሰው ብቻ ተገኝቶ አፍራ ወደ ሃገር ቤት መመለሷ መዘገቡ አይዘነጋም።
ሸዋፈራው ከዲያስፖራው አፍሰዋለው ያለው $$$ በዲሲ እንዲህ ያለው እክል ያጋጠመው ሲሆን በሌሎች ስቴቶች እንኳን
የኮሜዲ ሾው አደርጋለሁ ቢል በየቦታው ባሉ የድጋፍ ሰጪዎች ከፍተኛ የሆነ ችግር እንደሚገጥመው ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዲያፖራው ሕዝብን እየጨፈጨፈ ከሚገኘው መንግስት ጎን ለቆሙ ሆዳም አርቲስቶች ያለው ትዕግስት
ተሟጦ ማለቁ ከሚደረጉት እንስቃሴዎች እየታየ ነው።


Sunday, September 7, 2014

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በፌዴራል ፖሊስ ተከበበ

ኢህአዴግ ከተለያዩ የሃገራኅችን ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተማሪዎች በግዳጅ “የመለስ ራዕይ” እያሰለጠናቸው ይገኛል።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞንና ዓዲ ኣሕፈሮም ወረዳ የተውጣጡ ተማሪዎች ተሰብስቦውበታል። ተማሪዎቹ በስልጠና ወቅት ከህወሓት ከድሬዎች ኣቅም በላይ ጥያቄዎች በመጠየቅ ህወሓትን እያበሳጩ ከሰነበቱ በኋላ ከሓሙስ 28 / 12 / 2006 ዓ /ም ጀምረው በኣበል ክፍያ በተፈጠረ ኣለመግባባት “ከግቢው ኣንወጣም” ብለው ኣድመዋል።

በዚህ ኣድማቸው የኣቋም ለውጥ ባለማምጣታቸው ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቦ እየተጠበቀ ይገኛል። ከተማዋም ከዞኑ የተውጣጡ ፖሊሶች ተሞልታለች። የኣዲሱ ትውልድ ጀግኖች በህወሓት ፕሮፖጋንዳ በፍፁም ሊታለሉ ኣልቻሉም።

በሌላ ዜና…!
————

እሮብ 27 / 12 / 2006 ዓ/ ም ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ኢህኣዴግ ባዘጋጃቸው ተማሪዎችና የተቀረው ስልጣኝ ተማሪ በተጀመረ ግጭት የፈዴራል ፖሊስ ገብቶ ተማሪዎችን በመደብደብ ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሷል።

ስብሰባው እየመሩ የነበሩ ካድሬዎች ካዳራሹ ሮጠው ከግቢው ያመለጡ ሲሆኑ፤ ተማሪዎች እርስበርስና የፌዴራል ፖሊስ ደርሶ ባደረሰው ድብደባ ክፉኛ የተጎዱ ተማሪዎች መኖራቸው የዓይን እማኞች ከቦታው ገልፀዋል።


Imprisoning, Killing, Spying – Suppression of the Innocent Inside Ethiopia

by GRAHAM PEEBLES
Wrapped in dishonesty, arrogance and paranoia, Ethiopia’s ruling regime is following a nationwide policy of violent suppression and constitutional vandalism.
It was the 24th June – midsummer’s day – in the adopted homeland of Andargachew Tsige, when he was detained by ‘Yemeni officials’ (State heavies in suits) whilst transiting through Sana’a to Eritrea. The British citizen and leading Ethiopian political activist was quickly and quietly extradited to Addis Ababa where he was imprisoned on spurious charges of treason or some such trumped up, paranoid twaddle. He had been unfairly tried in absentia in 2009, when Amnesty report he was “sentenced to death for an alleged coup attempt. He was prosecuted in absentia again in 2012 on terrorism charges, alongside other prisoners of conscience, and sentenced to life imprisonment.”

ህዝባዊ እንቢተኝነት ለነፃነት እና ለፍትህ !

በአገራችን የፖሊቲካ ሥርዓት ሄደት ውስጥ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ከአንዱ ወደሌላው የተሸጋገረበት አጋጣሚ እጅግ በጣም አናሳነው፡፡ አብዛኛው የስልጣን ሽግግር ጉልበትና ብረትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የስልጣን ሽግግር ጉልበተኞች ሁሌም አሸናፊ የሚሆኑበት ጉልበቱ አናሳ የሆነ ከስልጣን የሚርቅበት ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡ይህም በመሆኑ በህዝብ ፍቃድ እና ምርጫ ወይም በህዝባዊ እንቢተኝነት የመንግስት የአስተዳደር የስርዓት ለውጥ ወይም ጥገናዊ ማስተካከያ ለውጥ ከዚህ ቀደም እንዲሁም ባሁን ወቅት በአገራችን ስለ መደረጉ ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ ስለመኖሩ ያጠራጥራል፡፡ ለዚህም ነው ሰላማዊ ትግል በአገራችን ተስፋ አስቆራጭ እና የማይሞከር መስሎ የሚታየው፡፡
እርግጥነው በሰላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ውጣ ውረዶ የበዛ ነው፡፡ በዓለማችን ላይ የተካሄዱት ሠላማዊ ትግሎች ውጤት ያስመዘገብት መተኪያ የሌለውን የሰውልጅ ሕይወትን እስከመንጠቅ በመድረሰ ነው፡፡ ይበልጥ ደግሞ ትግሉ አስቸጋሪ የሚያስመስለው ውጤቱ የሚፈጀው ጊዜ ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ማለት ታጋዩ የሚታገልለትን ውጤት ሣይመለከት በትግሉ ሂደት የሚሰዋበት ነገር ነው እስከመባል ይደርሳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ደረጃ ለመድረስ ከሌላ ጋር ሣይሆን ከእራስ አስተሳሰብ ጋር ይህ ቀረሽ የማይባል ትግልን ማካሄድ ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ-አይነቱ የአስተሳሰብ ልዕልና ለመድረስ ገፊ ምክንያቶች ካሉ፣ ምክንያቶችሁ በስትራቴጂ ከተነደፉ፣ የገዥው ስርዓት ደካማ ጎኖ በሚገባ ከታወቀና ከተለየ፣ ተምሳሌታዊ እንዲሁም ደረጃ በደረጃ የሚያድግ ሰላማዊት ግሉን የሚመራ ጠንካራ

Saturday, September 6, 2014

በወያኔ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት፣ የወያኔ አገልጋይ  ኢሕአዴግ፣የአፋኞችና የነፍሰ ገዳዮች ምሽግ- የወያኔ ደህንነት

የንቅናቄአችን ዋና ጸሃፊና የትግል ጓዳችን  አንዳርጋቸው ጽጌ  በየመን ትብብር በፋሽስታዊ ወያኔ አፋኞች  እጅ መውደቅ ያስቆጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባሳየው ወገናዊነት ልባችን ተነክቷል። የአንዳርጋቸው መታሰር ይቆጨናል፤ እየደረሰበት ያለው ስቃይ ያንገበግበናል፤ የሱን አይነት ብርቱ፣ ቆራጥ፣ አስተዋይና ብቃት ያለው ታጋይ ትግሉ ማጣቱ ይጎዳናል:: አንዳርጋቸው በሳል የፖለቲካ ሰውና ቆራጥ የተግባር ታጋይ ብቻ አይደለም። በግል ለማታውቁት በበርካታ የእውቀት ዘርፎች በጥልቀት ያነበበ፤ ፍልስፍና፣ ሊትሬቸር፣ ሲኒማ የሚወድና ህሊናው በዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ነው። የሰው ልጅ መከራ፣ በደልና ስቃይ እስከ አጥንቱ ይሰማዋል። ዱባይ ላይ ከአመት በፊት ስላገኛት ኢትዮያዊት የነገረኝ ሲቃ እየተናነቀው ነበር።ልጅቷ ሲያገኛት ያለማቋረጥ ታለቅሳለች፤ ምን እንደሆነች ቢጠይቃት ለመናገር ባትፈቅድም አጥበቆ ሲይዛት እንደተናገረችው፤ ተቀጥራ በምትሰራበት  የቤቱ ባለቤት ሽማግሌ አረብና አራት ወንድ ልጆቹ በየገዜው ተራ በተራ ደፍረዋታል። የሚያስነባት ይህ ነበር። አንዳርጋቸው “የኢትዮጵያውያን መከራና ውርደት መቼ ነው የሚያበቃው” በሚል ነበር ሲቃ እየተናነቀው ያጫወተኝ።

አንዳርጋቸው የንዋይና የስልጣን ፍቅር የለበትም። ፍላጎቱ ያ ቢሆን ኖሮ ዛሬ  ወያኔ ከሰበሰባቸውና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የወያኔ ሎሌዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ባገኘነው ነበር። በምንም መለኪያ በሱ ደረጃ ብቃት፣ ምሁራዊ ብስለትና ስብዕና  የተላበሡ እንደሌሉባቸው ግልጽ ነው። አንዳርጋቸው የመረጠው የፍትሕ፣ የነጻነትና የእውነትን መንገድ ሲሆን እሱ የመረጠው ከህሊናው ጋር መኖርን ነው።  ለዚህም ነው ስልጣን እና ገንዘብን ገፍቶ፣ የአውሮፓን ምቾት ትቶ፣ በርሃ ወርዶ አፈር ላይ እየተኛ በርካታ ታጋዮችን አስተምሮ ትግሉን ጠንካራ መሰረት ላይ የተከለው – ትግሉን መስመር አስይዞ ዛሬ በፋሺስቶች እጅ ቢወድቅም።

የዓመቱ አነጋጋሪና አወዛጋቢ ክስተቶች

በዓመቱ መጀመሪያ በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም ለ12 ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፤ ከስልጣናቸው የወረዱ ሲሆን በቦታቸውም ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተተክተዋል፡፡ በአምባሳደርነት ዘመናቸው የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣትና አገር ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማግባባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው የሚነገርላቸው ዶ/ር ሙላቱ፤ የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላም ሥራቸው በቤተመንግስት አካባቢ የተገደበ አልሆነም፡፡ በተለያዩ አገራት እየዞሩ የውጭ ኢንቨስተሮችን የማግባባት ሥራቸውን ቀጥለውበታል፡፡

በዓመቱ ከተከናወኑ አነጋጋሪ ጉዳዮች መካከል አንድነት ፓርቲ ከሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተገናኘ የመብት ጥሰትና መጉላላት ተፈጽሞብኛል በማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባንና የከተማዋን ፖሊስ ኮሚሽን በፍ/ቤት መክሰሱ ተጠቃሽ ነው፡፡

Ethiopian Journalists Exodus Continues

The number of journalists fleeing from the world’s most oppressed nation, Ethiopia, has continued to rise making the country one of the world top five nations many journalists fled from. The number of the journalists fleeing the country is alarmingly increasing as the regime continues its crackdown on the media institutions and professional associations operating in the country. According to recent reports, the number of the journalists fled the country in the past few months only has reached 22. The current exodus is said to be the worst ever. The Ethiopian Revolutionary Democratic Movement (EPRDF), which has been in power since 1991, has begun the recent media crackdown on one bloggers’ groups known as Zone 9 and a journalist association called Ethiopian Journalists Forum (EJF). And the crackdown is said to be strategically orchestrated to silence criticism and avoid possible challenges before the elections in 2015. Here is the list of the Journalists:
1 Journalist Betre Yacob (President of Ethiopian Journalists Forum(EJF), columnist at Ebony Magazine, correspondent for ASSAMAN Magazine, writer for THE DAILY JOURNALIST, contributor to ECADF and other Ethiopian online news websites, and blogger at ETHIOPIAHOT .
2 Journalist Tesema Desalegn (Founder and Managing editor of Ebony magazine)
3 Journalist Zerihun Mulugeta (Public Relation of EJF and Senior Reporter at Sendek newspaper)
4 Journalist Melaku Amare (Founder and Managing editor of Lia magazine)
5 Journalist Gizaw Taye (Founder and Managing editor of Lomi magazine)
6 Journalist Tomas Ayalew (Managing editor of Afro-Times magazine)
7 Sebeleworke Mekete (Senior Reporter at Lomi magazine)
8 Bisrat Woldemichael (Training and Education Head of EJF, Editor of Finote- Netanet Newspaper and Editor in Chief of Ebony Magazine, Contributor to ZEHABESHA and other Ethiopian online news websites, and blogger at ADDISMEDIA.
9 Abonesh Abera (Senior Reporter at Lomi magazine)
10 Yetneberk tadele (Editor in Chief of Fortune Newspaper)
11 Senay Abate (Editor in Chief of Lomi magazine)
12 Asnake Lebawi (Managing Editor of Jano Megazine)
13 Sisay Saylie (Founder and Managing editor of Piassa Newspaper)
14 Endalkachew Tesfaye (Founder and Managing editor of Addis Guday Magazine)
15 Endale Teshi (Editor in Chief of Addis Guday Magazine)
16 Ibrahim Shafi (Vice Editor in Chief of Addis Guday Magazine)
17 Habtamu Seyoum (Executive Committee Member of EJF and Columnist at Addis Guday Magazine)
18 Dawt Solomon (Editor in Chief of Finote-Netanet Newspaper and Life Magazine)
19 Daniel Dirsha (Media Director of Lomi Megazine) and Three other Journalists


ሙስና፣ ዮሴፍ “ገይድ”ና መለስ,,,አርአያ ተስፋማሪያም

« አንድ የውጭ መርማሪ አቋቁመን ሥር ሰዷል የተባለውን ሙስና ከማረት ስንመረምር የት እንደገባ የማይታወቅ 5ሚሊዮን 60ሺህ ብር ተገኘ። ተጠያቂ ሆኖ የተገኘው ግርማይ ካህሳይ የሚባል የድርጅቱ ሒሳብ ሰራተኛ ሲሆን ሌላው ተጠያቂ ደግሞ ተክለ ወይኒ ነበር። ግርማይ ፍ/ቤት ሳይቀርብ 1ሚሊዮን 5መቶ ሺህ ብር መቀሌ ላይ አስረከበን። አዲስ አበባ ላይ በክንፈ ገ/መድህንና ጌታቸው አሰፋ በኩል 1ሚሊዮን 5መቶ ሺህ ብር በካሽ አስረከበ። ..ይህ ሁሉ ሲሆን ከግርማይ ይልቅ ከፍተኛ ስጋት ያደረበት ተክለወይኒ « ይህ ኮራፕሽን እያላችሁ የምታደርጉት ምርመራ ትክክል አይደለም፤ ማረት ላይ የተከሰተው ችግር የአሰራር ግድፈት እንጂ ሙስና አይደለም፤ እያንዳንዱ የህወሀት አመራር አባል ቢፈተሽ ተመሳሳይ ግድፈት ሊገኝበት ይችላል። ዓባይ ፀሐዬ ደግሞ ከሁሉም የባሰ ሙሰኛ እንጂ ሙስናን ሊታገል የሚችል፤ ሰው አይደለም» እያለ ያማርር ነበር። (ገፅ 322 -323)….
ወደ ሌላው ልሻገር፤ ዮሴፍ ረታ (በቅፅል ስማቸው ገይድ) የአማራ ክልል ፕ/ትና የብአዴን ማ/ኮሚቴ አባል ነበሩ። አቶ ዮሴፍ አቶ መለስና ተከታዮቻቸውን ከስልጣን እንዲወርዱ የጠየቁ ተቀዳሚ ሰው ናቸው፤ « ጠ/ሚ/ርና የአገሪቱ የጦር ኅይሎች ጠ/አዛዥ መለስ ዜናዊ፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ስዩም መስፍን፣ ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሻዕቢያን ወረራ ለመቀልበስ የሚደረገውን ጦርነት እየተቃወሙ እንዴት ባሉበት የሥልጣን ደረጃ ሊቆዩ ይችላሉ? ለምናደርገው የሻዕቢያን ወረራ የመቀልበስ ጦርነትስ ዕንቅፋት አይሆንሁም ወይ? በማያምኑበት ጦርነት እንዴት ንቁ ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ? ስለዚህ ከዚሁ ውሳኒያችን ጋር የሥልጣን ሹም ሽር ማድረግ የለብንም ወይ?» ሲሉ መጠየቃቸውን የአቶ ገብሩ አሥራት መፅሐፍ በገፅ 306 አስፍሮዋል።
አቶ አውአሎም ወልዱ ተመሳሳይ ጥያቄ ሰንዝረዋል። አቶ ዮሴፍ ከዚህ ጥያቄ በኋላ በመለስ ዜናዊ ምን እንደደረሰባቸው ወይም ያሉበትን ሁኔታ መፅሐፉ ባይገልፅም ነገር ግን በመለስ ተባረው በእርሻ ስራ እንደተሰማሩ ማወቅ ተችሏል። አቶ ዮሴፍ የህሊና ነፃነታቸውን ይዘው የሚኖሩ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ብያቸዋለሁ!! .
.የአቶ ገብሩ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” መፅሐፍ በተለይ ሕወሐት ውስጥ ተዳፍኖ የቆየውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደሚያቀጣጥለው ምንም አያጠራጥርም። በገዢው ሰፈር ከባድ ቀውስ የሚያስነሳ እንደሆነ አያጠራጥርም!! ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የቀድሞ የገዢው ባለስልጣናት፣ የህግ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ዜጎች ስለመፅሐፉ የላቀ ትኩረትና ግምት ሰጥተው እየተነጋገሩበት ነው። ብዙ ጉድና ምስጢር የያዘ መፅሐፍ