Tuesday, February 16, 2016

ኢሳት በናይልሳት የ24 ሰዓት ሬዲዮ ስርጭት ጀመረ!

ኢሳት (የካቲት 8 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ወደ ኢትዮጵያ ሲያሰራጭ የቆየውንና የተቋረጠውን ፕሮግራሙን በሬዲዮ ጀመረ። የቴሌቪዥን ስርጭቱን ለማስቀጠልም ከሳተላይት አቅራቢ ኩባንያዎች ጋር ቴክኒካዊ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም የኢሳት ማኔጅመንት አስታውቋል።
...
አሁን በናይል ሳተላይት የሚተላለፈው የኢሳት ሬዲዮ ስርጭት ለ24 ሰዓታት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑም ታውቋል። ስርጭቱ በ Nilesat 12604 horizontal ላይ በመተላለፍ ላይ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። ከኢሳት ማኔጅመንት መረዳት እንደተቻለው የኢሳት የ24 ሰዓታት የቴሌቪዥን ስርጭት በቅርቡ ይጀምራል።
ኢሳት በተለያዩ ሳተላይቶች ወደኢትዮጵያ ሲያስተላልፋቸው የነበሩ ፕሮግራሞች ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የውጭ ባለሙያዎችንና የውጭ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አስተጓጉሎት ቆይቷል ያለው የኢሳት ማኔጅመት በዚህ ሳምንት ኢሳት በሬዲዮ ስርጭት ወደ አየር መመለሱን አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment