Tuesday, February 2, 2016

ቃልቲ የሚገኙ የኦሮሞ እስረኞች ራቁታቸውን ሆነው መገረፋቸውን አንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ገለጸ

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ በቃሊቲ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ እስረኞች ራቁታቸውን ሆነው በመደብደባቸው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።ብዙዎች ደማቸውን እያዘሩ ታንከር ወደሚባለው ጨለማ ክፍል መወሰዳቸውንም ገልጿል።
የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገብረእግዚአብሄር በተባለ የእስር ቤቱ ሃላፊ ትእዛዝ የተፈጸመው ድብደባ ከምሽቱ 3 ሰአት እስከ 9 ሰአት የዘለቀ መሆኑንም ገልጿል። ከድር ዝናቡ፣ አብዲሳ ኢፋ፣ አብዲ ብሩ፣ ባንቲ ደገፋ፣ ደጃዝማች በያና፣ እና ሁሴን አብዱረህማን የተባሉት እስረኞች በከፍተኛ ሁኔታ ከተደበደቡትና ጨለማ ቤት ውስጥ ከተላኩት መካከል ይገኙበታል። ሁሴን አብዱራህማን ከሌሎች ተለይቶ መወሰዱንና ድብደባው ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ የት እንዳለ አለመታወቁን ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment