Thursday, December 10, 2015

በሰሜን ጎንደር ኢህአዴግ ያስታጠቃቸው ሰዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ

ኀዳር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር መተማ ወረዳ ገዢው ፓርቲ ከተለያዩ አካባቢዎች አሰባስቦ መሳሪያ ያስታጠቃቸው ሰዎች አማራና ቅማንት በሚል ከፋፍሎ ግጭት ማስነሳቱን ተከትሎ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ግጭቱ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው የሚሉት ምንጮች፣ ግጭቱ ወደ ጭልጋና አጎራባች ቀበሌዎች መዛመቱም ታውቋል።

ግጭቱ በሽንፋና በኩመር አካባቢዎቸ ደም አፋሳሽ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment