Thursday, December 17, 2015

ምእራብ ሸዋ ሚታ ሮቢ ከተማ ከባድ ተቃዉሞ ተጀምሯል:: ከ11 ሽህ በላይ ገበሬ ከሚናሬ ወደ ሽኖ ከተማ እየተመመ ነዉ::

ምእራብ ሸዋ ሚታ ሮቢ ከተማ ከባድ ተቃዉሞ ተጀምሯል::

ከ11 ሽህ በላይ ገበሬ ከሚናሬ ወደ ሽኖ ከተማ እየተመመ ነዉ::
ወያኔ አንድም እርምጃ ቢወስድ ምላሹ የከፋና በቂም የታጀበ ይሆናል:: በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ያቀረበን መግደል ማቁሰል የከፋ ዉጤት አለዉ::
በወለጋም በርካታ ቦታወች ተቃዉሞዉ የመለስ ዜናዊይን ምስል የኦህዴድን አርማ እየለቀሙ በማጋየት የቀጠለ ሲሆን ወሳኝ ወሳኝ መንገዶችም በመዘጋት ላይ ናቸዉ::
አዲስ አበባ በኦሮሞ ተወላጆች መኖሪያ ቤት ፍተሻ ተጀምሯል:: ወያኔ ያቄመዉ ሰዉ ቤት ፈንጅና ጦር መሳሪያ አስቀምጦ ድራማ ሊሰራ አስቧል::
በህዝብ ባስ በሰላም ባስ ህዝቡ መሄድ አደገኛና የወያኔ ቀጢይ ድራማ ሰለባ መሆን ነዉ:: ቤተክርስትያን መስጊድ ገበያ ሲኒማ ቤት ወዘተ… ህዝብ የሚሰበሰብባቸዉ አካባቢ ህዝቡ ጥንቃቄ ያድርግ:: ወያኒ አሸባሪ ፀረ ሰላም አፈነዳዉ ብሎ ህዝብን ንብረትን ለማዉደም አስቧል::
ጎንደር ፍጥጫዉ ቀጥሏል:: ከተማዋ እስከ መተማ አገሪቱ ተወጥራለች:: ባህርዳርና የጎጃም ከተሞች ሊወልዱ ምጥ ላይ ናቸዉ::
አርበኞች ግንቦት ሰባት ወያኔን ቁም ስቅሉን በማሳየትና የህዝብን ደም በመመለስና ተቃዉሞወችን በማቀናጀት የወያኔን ሴራ በማጋለጥ ተጠምዷል::

No comments:

Post a Comment