Wednesday, December 9, 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረሰበት የቴክኒክ ችግር ምክንያት ሴኔጋል ለማረፍ ተገደደ

ኀዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መነሻውን ከአዲስ አበባ በማድረግ ወደ ማሊ ባማኮ 139 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን አየር ላይ እያለ በአውሮፕላኑ ክንፍ ላይ በደረሰበት ድንገተኛ የቴክኒክ ብልሽት ከ45 አቂቃ በረራ በኋላ ሴኔጋል ዳካር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል።

አውሮፕላኑ በሰላም በማረፉ በመንገደኞች ላይም ሆነ በንብረት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን ጋና ዌብ አክሎ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment