Saturday, December 12, 2015

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። የፓርቲ መሪዎች የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ በቀለ ነጋ በፖሊሶች ታይዘው ተወሰዱ::

ምኒሊክ ሳልሳዊ #Ethiopia #Oromoprotests is Underway in Welega University – በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።በአምቦ ገበያው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተቀየረ::በቀበሌ 6 አምቦ ለቅዳሜ ገበያ የወጣ ሕዝብ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማ ነው::

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪው በአሁኑ ሰአት ተቃውሞውን እያሰማ ከዩኒቨርሲቲው በመውጣት ወደ ከተማ በመጓዝ ላይ ይገኛል። ተማሪዎች ከወያኔ ወታደሮች ጋት ተፋጠዋል::… እንዲሁም በግንደበረት አውራጃ በሃረርጌ እና በአሩሲ  በባሌና በሸዋ አብይ ከተሞች ተማሪዎች እና ነዋሪዎቹተቃውሞ ለማሰማት አደባባይ ወጥተዋል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ በአዳማ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ በቀለ ነጋ በፖሊሶች ታይዘው ከተወሰዱ በኋላ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የፖለቲካ መሪዎቹ ከከፍተኛ ወከባ በኋላ ተለቀዋል::

No comments:

Post a Comment