Thursday, December 17, 2015

ከአራዳ ፍርድ ቤት እስረኞች አመለጡ | አካባቢው በተኩስ ተናወጠ

(ዘ-ሐበሻ) ከጥቂቅ ደቂቃዎች በፊት ለዘ-ሐበሻ በደረሰው ዜና መሠረት በአራዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ነውጥ ነበር:: የዚህ የተኩስ መነሻ ከልደታ ፍርድ ቤት እስረኞች ስላመለጡ ነው ተብሏል::
የአይን እማኞች እንደሚገልጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም እስረኞች ያመለጡ ሲሆን አክባቢው ተረብሾ ይገኛል::
የአይን እማኞች እንደሚገልጹት እስረኞች አምልጠዋል በሚል ከሃያ በላይ የጥይት ድምጾችን ሰምተዋል:: በተለይም በዛሬው ዕለት በዚሁ ፍርድ ቤት መምህር ግርማ ቀጠሮ ስለነበራቸው በርካታ ሕዝብ በአካባቢው ይገኝ እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸው ተኩሱ በተሰማበት ወቅት ፖሊስ ዛሬ በዳኛ አለመኖር ወደ ነገ ቀጠሯቸው የተሻገረው መምህር ግርማን በአስቸኳይ ይዞ ወደ ማረፊያ ቤት ይዟቸው ሄዷል::

No comments:

Post a Comment