Tuesday, December 8, 2015

የወያኔ የጦር መሐንዲስ ተገደለ

የነጻነት ትግሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሰራዊቱ እየከዳና እየተመናመነ ይገኛል አንድ ሻለቃ አዘዞ የሚባል ወያኔ አለኝ የሚለዉ የጦር መሐንዲስና አዋጊ በትናንተናዉ እለት በአርበኞች ተገድሏል። በትናንትናዉ እለት የወታደራዊ ደህንነቱ መረጃ ክፍል ለእዝ መምሪያ ቀጠና እንዳስተላለፈዉ በቡሬ ግንባር አካባቢ የተሰማሩ 26 የሚጠጉ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ከወያኔ ጋር ተፋልመዉ 6ቱ ሲገድሉ አንዱ የቆሰለ ሲሆን 19ኙ የገቡበት አልታወቀም በተመሳሳይ ከወያኔ በኩል 11 ተደምስሰዋል ይላል። በጎንደር ከአርበኞች ግንባር ጋር እየተደረገ ያለዉን ስብጥር እና ጉሬላ ዉጊያን ከሰራዊቱ ለመሸሸግ ሲባል ብቻ ወያኔ ጦርነቱ ከሻቢያ ጋር ነዉ እያለ ወታደሩን ለማታለል በመሞከሩ ምክንያት ይህንንም ቅጥፈት ሰራዊቱ በማወቁ ዉጊያዉ ላይ ወታደራዊ ኪሳራዎች እየበረቱ ይገኛሉ።በኦጋዴን ክፍት የሆነዉን የምስራቅ ቦርደር ቆርጠዉ የገቡ የነጻነት ሐይሎች የምስራቅ ኮከብ የተባለለትን የወያኔን ጁንታ እያሽመደመዱት ነዉ።
በከተማ ዉስጥ ተቃዉሞ በርትቷል የህዝብ አመጽ ከቦታ ወደ ቦታ እንደወረሽኝ እየተበራከተ ነው አንዳንድ የወያኔ ፖሊሶች ለህዝብ አግዛችኍል እየተባሉ እየታሰሩ ሲሆን ፍደራል ፖሊስና አጋዚ የተባለዉ ወንጀለኛ ሐይል አጥብቂኝ ዉስጥ መሆኑን ምንጮች ያመላክታሉ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስቷል ከእንግዲህ የሚያቆመዉ የለም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

No comments:

Post a Comment