Monday, December 14, 2015

ሕዝብን ከመጨፍጨፍ እየዘመተ ያለው ጦር –

በነሶሞራ የሚመራው እዝ፣ ህዝብን ለመጨረስና በሃይል አንገትን ለማስደፋት ሁለት ዲቪዝን ጦር ወደ ምራብ ሸዋና ወለጎ እየወሰደ ነው። ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ አገዛዙ ሊወስደው የሚችለው የመጨረሻ ተግባር ነው። ጎንደር ላይ ከሰፈረው ጦር በተጨማሪ ወደ ኦሮሚያ እየተሰማራ ያለው ሲደመርበት በሌሎች ከተሞች የሚኖረው ጦር በጣም የተመናመነ ነው።

በመሆኑም በአዲስ አበባ. በጎጃም፣ በወለኦ፣ በሰሜን ሸዋ፣ እና በደቡብ ክልል ሕዝቡ ለነጻነትና ለመብት ድምጹን ማሰማት ቢጀመር ይሄ ስርዓትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመገርሰስ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።
በመሆኑም ሌላው ማሀበረሰብ ድምጹን ያሰማ ዘንድና በኦሮሚያና በጎንደር ለመብታቸው ከቆሙ እየተገደሉ ካሉ ወገኖቻችን ጎን እንዲቆም ያስፈልጋል።
እስከአሁን በጎንደር ከ150 በላይ ዜጎንች የተገደሉ ሲሆን በኦሮሚያ የዛሬን ቀን ሳይጨመር ከሰባ በላይ ሕይወታቸው አልፏል።

No comments:

Post a Comment