Saturday, December 12, 2015

በምዕራብ ሸዋ የተለያዩ መንደሮች ከ100, 000 ሕዝብ በላይ ለተቃውሞ አደባባይ ወጣ

በምዕራብ ሸዋ በጊንዶ ከተማና በአካባቢዋ የሚገኙ መንደሮች በአጠቃላይ ከ100 ሺህ ህዝብ በላይ ወጥቶ ስርዓቱን በመቃወም ላይ ይገኛል:: ዛሬ ዴሴምበር 12, 2015 የተደረገውን ተቃውሞ ትላልቅ እናት እና አባቶች ሳይቀሩ ተቀላቅለውታል:: በጊንዶ ከተማ የተለያዩ ቃጠሎች በየአደባባዩ እየታዩ ሲሆን የአጋዚ ጦር አካባቢውን በሁለት አቅጣጫ እንደከበበው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል:: ቀጣይ ፎቶዎች ይናገራሉ:: ከዚህ ቀደም በነበረው የዘ-ሐበሻ ዜና በጅማ ከተማ የተፈጠረው ተቃውሞ አሁንም እንዳልበረደ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ:: በባሌ ደንበል ታውን የተነሳው ተቃውሞም እንደቀጠለ ነው:: 

No comments:

Post a Comment