Monday, December 28, 2015

ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ማሰር መቀጠሉ እያሳሰበው እንደመጣ አሳወቀ።

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እለተ ዐርብ በጸጥታ ኃይሎች ከመንገድ ላይ ተይዞ የታሰረ ሲሆን፣የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ሚርካናም በደኅንነት ኃይሎች ተይዞ ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ ጂፒጄ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔት እየከፋ መምጣቱንና በአፍሪካ ውስጥ ካሉ አገራት ጋዜጠኞችን በማሰር የኢትዮጵያ መንግስት ከቀዳሚዎቹ ተርታ መቀመጡን ሲፒጄ በሪፖርቱ አስታውቋል።
የነገረ ኢትዮጵያው ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን በርካታ ጽሁፎችን በድፍረት በመጻፍ እንዲሁም በእስር ቤት የሚንገላቱ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ ተከታትሎ በመዘገብ ይታወቃል።
ከገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው እንደነበርና የታሰረውም ከስራው ጋር በተያያዘ መሆኑን ጋዜጠኛ ጌታቸው ለፍርድ ቤት ገልጿል።ሌሎች የሰማያዊ አባላትም ከጋዜጠኛ ጌታቸው ጋር አብረው ተይዘው ታስረዋል

No comments:

Post a Comment