Tuesday, December 15, 2015

በሰሜን ጎንደር የመንግስት ሹመኞች የለኮሱት ግጭት ደም አፋሳሽ ሆነ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሆን ብለው በቀሰቀሱት ግጭት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እየተፈናቀሉ ነው።

ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት ጥቃቱን የሚፈጽሙት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው የመንግስት ሚሊሺያዎችና አስተዳዳሪዎች ናቸው። አንድ ባሏ ፊቷ ላይ የተገደለባት ሴት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በመንግስት አቀናባሪነት መፈጸሙን ገልጻለች።

ታጣቂዎቹ ባል ወይም ሚስት አማራ ከሆኑ እርስ በርስ እንዲፋቱ በማድረግ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተናግራለች።ልጃቸው የተገደለባቸው ሌላ ተፈናቃይም እንዲሁ ድርጊቱ በመንግስት ተቀናብሮ የሚካሄድ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ግጭቱ ወደ አደገኛ ሁኔታ ማምራቱን የገለጸው ሌላው ተፈናቃይ፣ ለዘመናት በአንድነት የኖሩትን ነዋሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት ሆን ብለው በማበጣበጥ እና መፍትሄ እንዳይፈለግ በማድረግ በህዝቡ መካከል ቁርሾ እንዲፈጠር እያደረጉ ነው
ችግሩ ለበርካታ ዜጎች መሞት ምክንያት ከሆነ በሁዋላ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወታደሮች ታጅበው የተመረጡ የአካባቢውን ሰዎች ሰብስበው አነጋግረዋል። በስብሰባው ህዝቡ የምታፋጁን እናንተ ናችሁ በማለት ለባለስልጣኑ በድፍረት መናገሩ ተውቋል።

No comments:

Post a Comment